tgindex

Event Addis Media

описание

Connect with Addis artistic community! Contact: @Tmanaye

9 424
подписчиков
Охват к подписчикам
29,0%
ERR
Реакции к просмотрам
0,46%
266 на 22 постов
Пересылки к просмотрам
0,61%
359
Постов в день
1,1
всего 22

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 13:46🔶አሻም ቲቪ በፍርድ ቤት ክርክር ተሸነፈ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ የሰራተኞቹን የ4 ወር ያልተከፈለ ደሞዝ ሳይከፍል ተቋሙን መዝጋቱን ተከትሎ፣ የቀድሞ ሰራተኞቹ ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤት የሰራተኞቹን አሸናፊነት የሚገልፅ ውሳኔ አስተላልፏል። ​ሰራተኞቹ መብታቸውን ለማስከበር ላለፉት 6 ወራት በፍርድ ቤት በጽናት ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረትም ተቋሙ ለሠራተኞቹ ያልከፈላቸውን ደሞዝ እና ተያያዥ ጥቅማጥቅሞች እንዲከፍል የሚያስገድድ ውሳኔ ወስኗል። ​ይህ ውሳኔ በሚዲያ ዘርፉ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን የሰራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር ትልቅ ማሳያ የሚሆን ሲሆን፣ ተቋማት የፋይናንስ ፈተና ቢገጥማቸው እንኳ የህግና የውል ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ግልፅ መልእክት አስተላልፏል። ​ ​ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis11,58%
  • 10 авг.🔶 ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ ነው ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንደሆነ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው በአሁኑ ወቅት ከሆቴሉ ጀርባ የሚገኙት ቦታዎችና ግንባታዎች በመፍረስ ላይ ሲሆኑ ሆቴሉ እስከሚቀጥለው ጥቅምት ፈርሶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ተብሏል። ይህ ሆቴል የሚፈርሰው በምትኩ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ሊሰራበት ነው፡፡ የሆቴሉ ባለቤት የሆነው ቢኬ ግሩፕ ከመንግስት ከገዛው በኋላ የማስፋፊያ ስራ ወዲያውኑ የጀመረ ሲሆን ከይዞታው 4000 ካሬ ሜትር በተጨማሪ በ5500 ካሬ ሜትር ላይ ትልቅ ህንፃ የመገንባት እቅድ እንዳለው አስታውቆ ነበር፡፡ ከመነሻው እቅዱ ባለ63 ፎቅ ህንፃ የመገንባት ቢሆንም ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/309 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis11,50%
  • 11 авг.🔶"ለድምጽ ብክለት የሚጣለው ቅጣት ትንሹ 5 ሺህ ብር፤ ትልቁ ደግሞ 25 ሺህ ብር ነው" አዲስ አበባ የድምጽ ብክለት በሚፈጥሩ ተቋማት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት ልትጥል ነው አዲሱ መመሪያ የበለጠ አስተማሪ እና አጥፊዎችን ቆንጠጥ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለድምጽ ብክለት የሚጣለው ቅጣት ትንሹ 5 ሺህ ብር፤ ትልቁ ደግሞ 25 ሺህ ብር ነው፡፡ በ2018 በጀት ዓመት 12,376 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የድምጽ ብክለት ቁጥጥር ተደርጓል፦ 3,116 አገልግሎት ሰጪዎች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፣ 28 ታሽገዋል፣ ከተላለፈ የገንዘብ ቅጣት 140,000 ብር ተሰብስቧል፡፡ የቅጣት እርከኑን በአዲስ አበባ ለመተግበር የሚያስችለው አዲስ ረቂቅ መመሪያ ለከተማ አስተዳደሩ ፍትሕ ቢሮ መላኩን የሀገር ውስጥ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,84%
  • 11 авг.🔶የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት 1 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ መሆኑን ዐቢይ አህመድ ጠቅሰዋል። ‎ ‎ፓርኩ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ መሆኑን በመጥቀስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል ሲሉም አስፍረዋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,81%
  • 5 авг.🔶የጠላ፣ጠጅና አረቄ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጨመረ በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡ በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡ ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ። ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ። በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው አጥናፉ የጥናቱን ውጤት ጠቅሰው ነግረውናል፡፡ በሌላ በኩል መንግስት የሚያገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉንም በጥናቱ አረጋግጠናል ይላሉ። የፍኖት አሶሼት መስራች አባል እና የፍኖት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶ/ር ፅኑኤል ግርማ በበኩላቸው እንደ ትንባሆ እና ሲጋራ ምርቶች በህገወጥ መንገድ አሁንም እየገቡ መሆኑን ነግረውናል። በፍኖት አሶሼት የፋይናንሲንግ ም/ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ደዬ በፋብሪካዎች የማይመረቱ፣ የአልኮል መጠናቸውም በማይታወቁ እንደ ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄ ያሉ መጠጦች በሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያመጡ ነው ብለዋል ። በሌላ በኩል በህገወጥ የሚገቡ ምርቶችን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል። ©️ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ======== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio10,80%
  • 12 авг.🔶ሀሰተኛው ሞትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት በቻይና ሁናን ግዛት ሰክሮ በማሽከርከሩ የሚጠብቀውን የሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ የሐሰት ሞትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ያዘጋጀው ወጣት በቁጥጥር ሥር ዋለ። ሲ የተባለው ግለሰብ የሕግ ተጠያቂነትን ለማምለጥ ሲል ከቤተሰቡ ጋር በመተባበር የሐሰት የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸሙን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ግለሰቡ ቀደም ሲል ያለ መንጃ ፈቃድ በስካር በማሽከርከር ሁለት ጊዜ የተያዘ ሲሆን፣ ለሦስተኛ ጊዜ በተመሳሳይ ጥፋት በመያዙ ምክንያት የሚጠብቀውን የእስራት ቅጣት በመፍራት በዋስ ከተለቀቀ በኋላ ከሀገር ለማምለጥ አቅዷል። በመቀጠልም ሲ እና ቤተሰቦቹ አስቀድመው የሬሳ ሣጥን በመግዛት ዕቅዳቸውን መተግበር ጀምረዋል። ፖሊስ እንዳወጣው መረጃ፤ አቶ ሲ በመድኃኒት መጠን ማለፍ ምክንያት እንደሞተ ለማስመሰል ባዶ የመድኃኒት ብልቃጦችን በቤቱ በመበተን፣ እስትንፋስን የመያዝ ልምምድ በማድረግና የሰውነት ሙቀትን የሚቀንሱ መሣሪያዎችን በመጠቀም የሐሰት ሞቱን አስመስሏል። የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በተካሄደበት ዕለትም እናቱና አያቱ የሲ ፊት በመድኃኒቱ ምክንያት ተበላሽቷል የሚል ምክንያት በመስጠት ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ቀብሩን ፈጽመዋል። የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት በሚከናወንበት ወቅት ግን ግለሰቡ ወደ ሌላ ግዛት በማምለጥ ላይ ነበር። የፖሊስ አባላት ድራማውን በቀላሉ ሊደርሱበት የቻሉት የሬሳ ሣጥኑ ግለሰቡ ከመሞቱ በፊት በመገዛቱ፣ የሕክምና እርዳታ ወይም ፖሊስ ባለመጠራቱ፣ የሞት ምስክር ወረቀት ባለመኖሩና የክትትል ካሜራዎች እንዲሁም የባንክ እንቅስቃሴዎች ግለሰቡ በሕይወት መኖሩን በማረጋገጣቸው ነበር። በክትትሉም ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ የ5 ወራት የእስራት ቅጣትና የ20 ሺህ ዩዋን የገንዘብ መቀጮ ተጥሉበታል። ©️ቻናል ዋን ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,75%
  • 11 авг.🔶3ኛው ‘አዲስ ኬክ እና ቤክ ኤክስፖ’ ይካሄዳል በኤክስፖው ላይ ታዋቂ ካፌዎች፣ ዳቦ ቤት እና ኬክ ቤቶች እንዲሁም የኬክ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ይሳተፋሉ። በተጨማሪም የተለያየ ባለሙያ ሼፎች ስለ ኬክ አሰራር እና የዘርፉን አዳዲስ ነገሮች ትምህርት እና ልምድ ይሰጣሉ። እንዲሁም የተለያዩ ጌሞች፣ የሼፎች ውድድሮች እና ለታዳሚዎች የተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ውድድሮች መዘጋጀታቸውን አዘጋጆቹ ለአራዳ አስታውቀዋል። 3ኛው ‘አዲስ ኬክ እና ቤክ ኤክስፖ’ addis cake and bake expo ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል። መግቢያው በነፃ በመሆኑ ታዳሚዎች ይህን ልዩ ኩነት እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,61%
  • 28 июл.🔶የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ አዲስ መጽሐፍ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ "አደይ እና ጥቀርሻ" የተሰኘ የግጥም መፅሐፉን በቅርቡ ለንባብ ያበቃል። ይህ መጽሐፍ የበድሉ ዋቅጅራ ስድስተኛ የሥነግጥም መጸሐፉ ነው። አስቀድሞ የፍካት ናፋቂዎች፣እውነት ማለት የእኔ ልጅ፣የተስፋ ክትባት፣የወይራ ስር ፀሎት፣የራስ ምስል የተሰኙ አምስት የግጥም መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,50%
  • 2 авг.🔶“የቃል ሊቀ መኳስ” አዲስ መጽሐፍ በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፍ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጌራወርቅ ጥላዬ “የቃል ሊቀ መኳስ” በሚል ዐዲስ መጽሐፍ መጥቷል። ኤቨንት አዲስ ቀድማ እንደሰማሁ ከሆነ መጽሐፉ አንድ ሺህ ኮፒ ብዛት፣ በ128 ገጽ ታትሞ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ በዚህ ሳምንት ከሕትመት ቤት የወጣ ሲሆን ለአንበባቢ ይፋ የሚሆንበት ቀን ግን ገና እንዳልተወሰነ ነው። ጌራወርቅ ከዚህ ቀደም በነበረው በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፍ በ2016ዓ.ም በተካሄደው የክብር አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ” በሚል ዘርፍ አሸናፊ ነበር። ከመጽሐፍ ባለፈ የሙዚቃ ግጥም ደራሲ ሲሆን የሃሌሉያ ተ/ጻዲቅ “የልቤ ቁምነገር” የሚለው ተወዳጅ ሥራዋ የጌራ ድርሰት ነው። ይህም ሙዚቃ በአፍሪማ አዋርድ እጩ የነበረና በዩጋንዳ በተካሄደው አይኮኒክ አዋርድ ደግሞ “የዓመቱ ምርጥ ዘፈን” በሚል ተሸላሚ ነበር። ከዓመታት በፊት “ሙሉ አካል ትዝታ” በሚል ልቦለድ እንደሚመጣ ተናግሮ እንደነበር አይዘነጋም። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,49%
  • 10 авг.🔶የዕድሜ ደመራ መጽሐፍ ተመረቀ የደራሲት፣ መምህርትና ጋዜጠኛ ውድአላት ገዳሙ ተሻለ የዕድሜ ደመራ መጽሐፍ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በድምቀት ተመርቋል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደራሲቷ የቅርብ ዘመዶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በርካታ የጥበብ ወዳጆች ተገኝተዋል። ይህ መጽሐፍ የውድአላት ገዳሙ ተሻለን የሕይወት ትውስታዎችንና የልጅነት ጉዞዎችን የሚዳስስ ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,42%
  • 8 авг.🔸 ጣፋጭ ሕይወት በአራዳ 95.1 ከወራት እረፍት በኋላ ዛሬ ወደ አየር ይመለሳል። ከ8ዓመታት በላይ የአድማጮችን ልብ ያሸነፈው ፕሮግራም በአራዳ FM 95.1 ዛሬ ይጀምራል! ከ8ዓመታት በላይ የአድማጮችን ልብ በሀሳብ፣ በተስፋ እና በአዎንታዊ እይታ ያጣፈጠው "ጣፋጭ ሕይወት" የሬዲዮ ፕሮግራም... አሁን ትልቅ የሆነ አዲስ ምዕራፍ ይጀምራል! ከነሐሴ 2 ጀምሮ በአራዳ FM 95.1 በአዲስ አቀራረብ፣ በአዲስ ጉልበት እና በተሻሻለ ይዘት ዛሬ ወደ አየር ይመለሳል። "አመለካከት ሲቀየር ሕይወት ይጣፍጣል!" የቅዳሜ ምሽቶቻችሁ... ከእንግዲህ የተለየ ጣዕም ይኖራቸዋል። ዛሬ ምሽት ነሐሴ 2 በ12:00-2:000,42%
  • 5 авг.🔶ቅዳሜ ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም 192 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተመልካቾች ባሉት አማዞን ፕራይም አማካኝነት የሚተላለፈው እና የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ፣ የባህልና የቅርስ ሀብቶች እንዲሁም የከተማችንን አዲስ ገጽታን የሚያስቃኘው “Why Are You Not Here?” የተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ሲሪየስ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በይፋ ለዕይታ ይበቃል። ይህ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተው ሲሪየስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቶ በሃገሪቷ ፍቅር፣ በባህሏ፣ በቅርሶቿና በህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት ስለተማረከ አፍሪካዊ-አሜሪካዊ ገጣሚ የሚተርክ ልዩ ሥራ ነው። በምርቃቱ ላይ በመገኘትዎ: • ሁነቱን በነፃ የመታደም እድል ያገኛሉ። • የዓድዋ ድል መታሰቢያን ይጎበኛሉ። • ከአለም አቀፍ እንግዶች ጋር የመገናኘትና የመተዋወቅ አጋጣሚ ይኖርዎታል። ቦታ: ዓድዋ ድል መታሰቢያ ቀን: ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት: ከቀኑ 9:00 ሰዓት መግቢያ: በነፃ ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ: EthiopianRSVP.com ቀድመው ይመዝገቡ፣ ፖስቱንም ለወዳጅዎ ያጋሩ ያድርጉ! http://www.ethiopiarsvp.com/ ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis10,39%