Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
СтатистикаFDRE, Ministry of Labor and Skills
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7 505
- 1/48двое суток
- 8 600
- 1/72трое суток
- 9 276
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን ገመገመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን በጋራ ገምግሟል። በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በመድረኩ በሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ የትኪረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ፅናትን፣ ትጋትንና ጥንካሬን የተላበሱ ወጣቶች የስኬት መንገድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮንሶ ዞን፣ ካራት ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት መንግስቱ ለጋ ከአመታት በፊት ነበር በኢንጂነሪንግ የትምህርት መስክ የተመረቀው፡፡ በተማረው ትምህርት ሥራ አለማግኘቱ ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዲያመራው አልፈቀደም፡፡ ከመሰል ጓደኞቹ ጋር በጋራ በመደራጀት "ኤግሊስ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ማህበር "ን አቋቋሙ፡፡ የማህበሩ ሰብሳቢ የሆነውን ወጣት መንግስቱ ለጋን ጨምሮ 6 አባላት ባዋጡት 6 መቶ ሺህ ብር ወደ ስራ የገባዉ የኤግል የእንቁላል ጣይ ዶሮ ማህበር ዛሬ ላይ የ6ሚሊዮን ብር ካፒታል ባለቤት ለመሆን በቅቷል። በማህበሩ ጊዜአዊ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸዉ አራት አባላት የተሻለ ገቢ ማመንጨት የቻሉ ሲሆን በተፈጠረላቸዉ የሥራ ዕድል ደስተኛ መሆናቸዉንም ይናገራሉ። 1,600 እንቁላል ጣይ የ45 ቀን ጫጩትና እንቁላል በመጣል ላይ ያሉ 2000 ዶሮዎችን በማርባት ላይ የሚገኝ ማህበር በዋናነት የእንቁላል ምርትን ለትምህርት ቤቶችና ለተጠቃሚ ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል፡፡ ማህበሩ በቀጣይ ተጨማሪ የዶሮ ማርቢያ ሼድ በመገንባት የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በስፋት የማምረትና ከእንቁላል ምርት በተጨማሪ የወተት ላም በማርባት ወተትና የወተት ተዋፅኦ ምርቶችን ለተጠቃሚ ማህበረሰብ የማቅረብ ዕቅድ እንዳለው አባላቱ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ችግርን ፈርቶ ሳይሆን በፅናትና ደጋግሞ በመሞከር ወደ ስኬት መድረስ ይቻላል›› የሚለው ወጣት መንግስቱ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው የራሳቸውን ሥራ ለመፍጠርና ህይወታቸውን ለመቀየር ትጋትና ጥንካሬን ሊላበሱ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ዘገባዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ለኢንዱስትሪው ፍላጎት የተጣጣመ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ለመገንባት የሚያስችል ጠንካራ የአጋርነት መድረክ ተመሠረተ በየዓመቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም የሚቀላቀሉ ቢሆንም፣ ከግማሽ ሚሊዮን ያነሱት ብቻ ናቸው የክህሎት ሥልጠና የማግኘት ዕድል ያላቸው። የሥልጠና ዕድሉን አግኝተው ከሚመረቁት መካከልም ቢሆን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡት ሥልጠና ከኢንዱስትሪው እውነተኛ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር አለመጣጣሙ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለምርታማነትና ለንግድ ተወዳዳሪነት ትልቅ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን መዋቅራዊ ችግር በመፍታት የሥልጠና ሥርዓቱ የሥራ ገበያውን እውነተኛ ፍላጎት ያገናዘበ እንዲሆን ለማድረግ በግል ባለሀብቶች፣ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል። ይህንን ዓላማ ስኬታማ ለማድረግም የኢትዮ-ጀርመን የዘላቂ ሥልጠናና ትምህርት ፕሮግራም (STEP IV) በክህሎት ልማት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ዋና ዋና የመንግሥትና የግል ዘርፍ ባለድርሻ አካላትን በባህር ዳር ከተማ አሰባስቧል። በተካሄደው የምክክር መድረክም በመንግሥት ተቋማት፣ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ በኢንዱስትሪዎች፣ በኩባንያዎች እና በንግድ ማህበራት መካከል በተግባር ላይ የተመሠረተ የሥራ ላይ ሥልጠና (Cooperative Training) ትስስርን የሚያጠናክር "የአማራ ክልል የቴክኒክና ሙያ የትብብር ሥልጠና ፎረም “ እንዲመሠረት ተደርጓል። በአማራ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ እንደገለፁት፤ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የቴክኒክና ሙያ ሥርዓት ለመገንባት በኢንዱስትሪዎች የሚመራ አጋርነት መፍጠር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል። በእነዚህ መሰል ጥረቶች አማካኝነት STEP IV በክህሎት ልማትና በሥራ ገበያው ፍላጎት መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር ላይ ይገኛል። የኢትዮ-ጀርመን የዘላቂ ሥልጠናና ትምህርት ፕሮግራም (STEP IV) በጀርመን መንግሥት ስም የሚተገበርና በአውሮፓ ኅብረት (EU) በጋራ የሚሸፈን ፕሮጀክት ነው። ነሀሴ 2/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችል አቅም መፍጠርን ያለመ ስልጠና የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራና ክህሎት ቢሮ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በጣልያን ፕሮጀክትና በሴቭ ዘ ችልድረን የፋይናንስ ድጋፍ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና በዘርፉ አዲስ እሳቤ፣ በባዮሜትርክስ ምዝገባና በዕቅድና ሪፖርት ዝግጅት ላይ ያተኩራል፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአፋር ክልል፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ኢብራሂም ስልጠናው በዋነኛነት በየእርከኑ የሚገኙ አመራርና ባለሙያዎች የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችላቸውን አቅም ለማጎልበት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በሚገኙ 30 የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊዎች የባዮ ሜትሪክስ ምዝገባ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ቢሮ ኃላፊው የምዝገባ ሂደቱን በሚጠበቀው ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ዕውቀትን ቢሮው ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ በሥራና ክህሎት ዘርፍ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉ ከዕቅድ ዝግጅት የሚጀምሩ እንደመሆናቸው ‹‹አንድ ዕቅድ፣ አንድ ሪፖርት›› የሚለውን የሚኒስቴር መ/ቤቱን መርህ ለመተግበርና የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ ስልጠናው ጉልህ ሚና አንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡ የሥራ ማዕከላትን ለማጠናከር በተጀመሩ ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ወጣቶችን ከአዳዲስ የሥራ ዕድል ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ያነሱት የቢሮ ኃላፊው የማዕከላቱን ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ የሚሰጡ መሰል ስልጠናዎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የሆኑ የሥራ ማዕከላትን እውን ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው የክልሉን ሰፊ የተፈጥሮ ፀጋ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚኖርባቸውም የቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ብቁ ባለሙያዎች የሚፈልቁባቸው ማዕከላት ለማድረግ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም በአፅንኦት አንስተዋል፡፡ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
የበጎ ፈቃድና የልማት ሥራዎች ሕዝባዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ናቸው፡፡ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የበጎ ፈቃድና የልማት ሥራዎች ቁሳቁሳዊና የመሠረተ ልማት ፋይዳ ከማስገኘታቸው ባሻገር በማህበረሰቡ መካከል የሚፈጥረው የእርስ በእርስ መተዋወቅ፣ ትስስርና አገራዊ ፍቅር ትልቅ መሆኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትር ዴኤታው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ እና በሸካ ዞኖች እየተከናወነ የሚገኘውን የክረምት የበጎ ፈቃድና የልማት መርሃ ግብር አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በመንቀሳቀስ የባህልና የልማት እቅዶችን ለመገንዘብ እንዲሁም የሕዝቦች እርስ በእርስ ትስስርንና አገራዊ ፍቅርን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በተከናወኑት ተግባራትም በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቤንች ሸኮ እና በሸካ ዞኖች እያንዳንዳቸው 10 ሺህ፣ በድምሩ 20 ሺህ የቡና ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። በተመሳሳይ በሁለቱም ዞኖች እያንዳንዳቸው 15 ሚሊዮን ብር፣ በድምሩ 30 ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ የሚደረግባቸው ሁለት የቅድመ-አንደኛ ደረጃ (ኪንደርጋርተን) ትምህርት ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር የመሠረተ ድንጋይ መቀመጡ ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የመስጠት መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን፤ በቤንች ሸኮ እና በሸካ ዞኖች ከ400 በላይ ወጣቶች በሥራ እድል ፈጠራ፣ በኢንተርፕረነርሺፕ፣ በሀገር ፍቅርና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ያተኮረ የማነቃቂያ ሥልጠና ማግኘታቸውን አስረድተዋል።
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ ***** ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው። መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል። ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው። ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል። ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል ። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) * ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሐ ግብር አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል። በዚህም ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል፡፡ በዚህ ደማቅ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ 26.2 ሚሊዮን ዜጎች በነቂስ ወጥተው እጅግ ከፍተኛ እና የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ የአንድ ጀምበር ተሳትፎ 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት የአረንጓዴ ዐሻራ መልበስ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 805.3 ሚሊየን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 26.2 ሚሊየን ሰዎች ተሳትፈዋል፤ በዚህም 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት ተሸፍኗል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አረንጓዴ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ዘመቻ አካል በመሆን፣ "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል፡፡ በመርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እና ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የክልሉ፣ የዞንና ወረዳው አመራሮች፣ የግብርና ኮሌጆች ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሏን ጠቅሰው፣ ዘንድሮም ወደ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለማድረስ ግብ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ክቡር ዶ/ር ተሻለ አክለውም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አረንጓዴ አካባቢዎችን በመፍጠር፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት፣ የፍራፍሬ ልማትን በማስፋፋት፣ የውጭ ምንዛሬ በማሳደግ እና ለCOP32 የኢትዮጵያን ዝግጁነት በማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የቡና፣ የአቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ልማቶች ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የገቢ ምንጭን በማስፋት፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን አስረድተዋል። መንግስት እየተገበረ ባለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመተሳሰብ ባህል በመላ ሀገሪቱ እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለትውልድ የሚተርፍ አሻራ ከመሆኑም ባሻገር የአንድነትና የመተጋገዝ እሴቶችን የሚያጠናክር ሀገራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሚኒስቴሩ በክልሉ እያከናወነ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ እና በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ 20 ሺህ የቡና ችግኞች በመትከል የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሁለቱም ዞኖች የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ ለ400 ወጣቶች የኢንተርፕረነርሺፕ እና የማነቃቂያ ስልጠና፣ ለ400 ልጆች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ እንዲሁም የደም ልገሳ መርሃ ግብሮች በተጓዳኝ መካሄዳቸውን ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ የተሳተፉት የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሠራተኞች ችግኞችን መትከል ለአረንጓዴ ልማት፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለዘላቂ ልማት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ ጥበቃን ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ፈጠራ፣ ከምግብ ዋስትና፣ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና ከአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም ጋር በማስተሳሰር፣ ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ፣ ምርታማና ዘላቂ ኢትዮጵያን ለማስረከብ የሚደረግ ሀገራዊ ጥረት መሆኑ ተገልጿል። ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ተስፋን እንትከል! 🌱 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሃገራዊ ንቅናቄ አካል በመሆን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሩን እያካሄደ ይገኛል። "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው በዚህ መርሃ-ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮችና የግብርና ኮሌጆች ዲኖችን ጨምሮ የአካባቢው ህብረተሰብ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን በማኖር ላይ ናቸው። እተካሄደ በሚገኘው መርሃ ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሁለት ዞኖች ብቻ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በማለም 20 ሺህ የሚሆኑት የቡና ችግኞች ናቸው፡፡ በዘርፉ የአካባቢ ጥበቃችንን በማረጋገጥ ለዘላቂ ሥራ ዕድል ፈጠራና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንዳለ በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡ ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
እየተከናወነ ያለው ሥራ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ ኮሪደር ልማት መርሃ-ግብር ላይ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት 8 ዓመታት በተከታታይ በተሰራው ሥራው ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል፤ ዓለም አቀፍ እውቅናም አግንቷል ብለዋል፡፡ አሁን እየተከናወኑ ያለሉ ሥራዎችም ቀጣይነቱን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን እና ሁሉም ተቋማት የተለየ ተልዕኮ ወስደው እየሰሩ ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ለማስተናገድ እየተደረገ መሆኑን አንስተው ሥራው የተቀመጠውን ስታንዳርድ ጠብቆ የሚከናወን እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ መርሃግብሩ ከአዲስ አበባ እስከ ቢሾፍቱ ደቡብ መውጫ ድረስ ባለው 45 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ኮሪደር ላይ የሚተገበር ሲሆን፣ ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ 6.3 ሄክታር የመንገድ ዳርቻና የመንገድ አካፋይን በአረንጓዴ ልማት ይሸፍናል። በአፈር ሁኔታ፣ በመሬት አቀማመጥ እና በሥነ-ምህዳር ተስማሚነት መሠረት በአምስት ብሎኮች የሚተገበረው ፕሮጀክቱ የቡና፣ የተለያዩ ፍራፍሬዎችና የአገር በቀል ዛፎችን ያካትታል። መርሃግብሩ የከተሞችን ውበት ከማሳደግ ባሻገር የካርቦን ክምችትን በማሳደግ፣ የአየር ጥራትን በማሻሻል፣ የከተማ ሙቀትን በመቀነስ፣ የአፈርና የውሃ ሀብትን በመጠበቅ፣ የብዝሃ ሕይወትን በማጎልበት እና የምግብ ዋስትናን በማጠናከር ረገድ ፋዳው የላቀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ መርሃ ግብሩ በመሬት አስተዳደር፣ በመስኖ፣ በከተማ አረንጓዴ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች አዳዲስ የአረንጓዴ ሥራ ዕድሎችን (Green Jobs) በመፍጠር ለወጣቶች እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድግም ተገልጿል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን በማስፋፋት፣ ለአረንጓዴ ሥራዎች የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን በማሳደግ፣ የሰው ኃይልን በማብቃት እና የዘላቂ ልማትን የሚያጎለብቱ ሀገራዊ ፕሮግራሞችን በመደገፍ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተገለፀው፡፡ ሀምሌ 25/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ወጣቶችን ከአካባቢያቸው ፀጋ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስቻል ጉዞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ሥራና ክህሎት ቢሮ ከክልሉ ማዕድን ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችለውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ በአርባምንጭ ከተማ ተፈራርሟል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሥራ፣ሥራ ስምሪትና ገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘዉዱ ሳሙኤል በፊርማ ስነ-ስርዓት ወቅት ክልሉ በማዕድን ሀብት የታደለ በመሆኑ ወጣቶች በሚፈልጉት የሥራ ዘርፍ ተሰማርተዉ ቢሰሩ ዉጤታማ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። የመግባቢያ ስምምነቱ ዋንኛ ዓላማ ወጣቶችን በማዕድን ልማት ሥራዎች ላይ በመሰማራትና ቅድመ ስምሪት ቁጠባ በማስቆጠብ ወደ ቋሚ ሥራ ለማሸጋገር እንደሆነም አቶ ዘዉዱ አብራርተዋል። የክልሉ ማዕድን ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ መርክነህ ቦጋለ በበኩላቸዉ የወጣቱ ሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተዉ ሳይሆን የሚመለከታቸዉ የባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት መረባረብ እንደሚገባቸዉ ጠቁመዋል። ወጣቶች ከአካባቢያቸው ፀጋ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻል አንፃርም በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡ ምንጭ - የደቡብ ኢትዮጵያ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀምሌ 24/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ምክር ቤቱ ፍትሃዊነትን፣ ተጠያቂነትንና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ለ144,339 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ይሰራል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ስምሪት ምክር ቤት አስተግባሪ ተቋማት በ2019 በጀት ዓመት 144,339 የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። የአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ስምሪት ምክር ቤት አስተግባሪ ተቋማት በ2019 በጀት ዓመት 144,339 የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው። ስምምነቱ 9 ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያስችልም ተመላክቷል። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን፣ በተቀናጀ የተቋማት ትብብር 371,354 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ከነዚህም መካከል 53 በመቶው ሴቶች ናቸው። በምክትል ካንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገብነው ስኬት የጋራ ርብርብ ውጤት ነው ብለዋል። በ2019 በጀት ዓመትም ፍትሃዊነትን፣ ተጠያቂነትንና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ለ144,339 ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የከተማችንን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን ምክር ቤቱ እንደሚሠራ ተመላክቷል። መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ነው። ሀምሌ 23/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
видео или голосовое, без подписи
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የካውንስል አባላት በሳይንስ ሙዚየም የኤአይ ስታርትአፖችን የፈጠራ ሥራዎች ጎበኙ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የካውንስል አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ኢንስቲትዩት ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የኤአይ (AI) ስታርትአፕ ተመራቂዎች የፈጠራ ሥራዎች በሳይንስ ሙዚየም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በዚህ ቴክኖሎጂ አውደ-ርዕይ ተመራቂዎቹ በጤና፣ በትምህርት፣ በትራንስፖርት፣ በቋንቋ ቴክኖሎጂ፣ በስማርት ሲቲ፣ በፋይናንስ እንዲሁም በሰብዓዊ ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮሩና አገራዊ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለዕይታ አቅርበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንስቲትዩቱ የሰለጠኑት አዳዲስ ተመራቂዎች ያቀረቧቸው ውጤቶች የተፈተሹ፣ ተግባር ላይ የዋሉ እና በስፋት ወደ ገበያ ለማስገባት ብቁ የሆኑ ናቸው ተብሏል፡፡ እነዚህ አገራዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን በከፍተኛ ደረጃ የማፋጠን አቅም ያላቸው የፈጠራ ሥራዎች የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ወደ ተጨባጭ ተግባር መሸጋገሩን የሚያረጋግጡ መሆናቸውም ተነግሯል። ይህ አውደ-ርዕይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ኢንስቲትዩት ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እና ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ በተግባር ያሳየ መሆኑ ተመልክቷል። ሀምሌ 21/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ቅንጅታዊ አሠራሮችን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ተገለጸ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መርህ መሠረት በማጠናከር፣ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ በሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ባካሄዱት የጋራ ውይይት ተገልጿል። በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር፣ ክቡር አምባሳደር አዲስዓለም መለሰ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። ውይይቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ እስካሁን የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የቀጣይ የጋራ ትኩረት አቅጣጫዎችን በስፋት ገምግሟል። በተለይም የሁለቱ ሚኒስቴሮች የተቀናጀ አሠራር ሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ይበልጥ ምቹ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ መሠረት የመረጃ ልውውጥን፣ የተቀናጀ ክትትልን፣ የጋራ የተግባር አፈጻጸምን እና የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ይበልጥ በማጠናከር የሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ፣ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ክብር በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችንና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚያሳድጉ ተግባራት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በውይይቱ ላይ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መርህ መሠረት በሀገር ውጭ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ሥርዓቱ የተቀናጀ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት እንዲሆን ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን ትብብር የበለጠ እንደሚያጠናክሩም ተገልጿል። ይህ ቅንጅታዊ አሠራር ሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን የበለጠ ውጤታማ ከማድረጉ ባሻገር፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል። ሀምሌ 18/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ይፋት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ (ISO) ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ በአማራ ክልል የሚገኘው የይፋት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሥራ አመራር ሥርዓት ዘርፍ የዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ (ISO 21001:2025) ሰርተፊኬት ባለቤት ሆኗል፡፡ ኮሌጁ ይህንን እውቅና ያገኘው የትምህርትና ሥልጠና አሰጣጥ ጥራቱን፣ የተቋማዊ አመራር ሥርዓቱን እንዲሁም ለሰልጣኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ከአለም አቀፍ የመመዘኛ መስፈርቶች ጋር በማጣጣሙና ማሟላት በመቻሉ ነው፡፡ ይህ የተገኘው የጥራት ሰርተፊኬት የኮሌጁን ሰልጣኞች በክህሎትና በእውቀት ብቁ እንዲሆኑ ለማስቻል፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ ገበያ ተወዳዳሪነታቻን ለማረጋገጥ እንዲሁም የተቋሙን ተወዳዳሪነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የክህሎት ልማት ጥራት ለማሳደግ እያከናወናቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል ቀዳሚው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሀምሌ 17/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
ደብረ ብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በምሥራቅ አማራ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ሊያገለግል እንደሆነ ተገለጸ፤ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት በአማራ ክልል ቀዳሚ ደረጃን ይዞ የቆየው ደብረ ብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ በምሥራቅ አማራ ለሚገኙ ኮሌጆች የአቅም ግንባታ በማድረግ የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence) ሆኖ እንዲያገለግል አቅጣጫ ተሰጥቶታል። ይህ የተገለጸው የሰሜን ሸዋ ዞን የከተማ ልማት ክላስተር ሱፐርቪዥን ቡድን በኮሌጁ ባካሄደው የሥራ ምዘናና የመስክ ጉብኝት ወቅት ነው። የክላስተሩ አስተባባሪ ዶክተር አየለ አናውጤ ኮሌጁ ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርናና ለኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎችንና የሰው ኃይል በብቃት እያፈራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ኮሌጁ በቅርቡ ከ1,200 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፣ ይህም በክልሉ ከ40 በላይ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች መካከል ግንባር ቀደም ተቋም እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል። እንዲሁም ለሆቴልና ቱሪዝም፣ ለስፖርት፣ ለግብርናና ለመሬት አስተዳደር ዘርፎች የቴክኖሎጂ ድጋፍ በመስጠት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ እታገኘሁ አደመ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በሽግግር እና በተቀናጀ የቡድን ሥራ ያስመዘገበው ውጤት ለሌሎች ተቋማት አርዓያ መሆኑን ጠቅሰው፣ የተገኘው ልምድ ወደ ሌሎች ኮሌጆችና ወደ ግብርና ዘርፍ ሊሸጋገር እንደሚገባ አሳስበዋል። በተጨማሪም ኮሌጁ 97 በመቶ የሥራ ትስስር በመፍጠር ሰልጣኞችን ለሥራ ገበያ በብቃት እያበቃ መሆኑን፣ ለከተማና ለገጠር ልማት የሚያገለግሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማበልጸግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገልጿል። በጉብኝቱ ወቅት የኮሌጁ የመሠረተ ልማት ሥራዎች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓቶችና የጥራት አስተዳደር ሥርዓቶች ተጎብኝተው ከፍተኛ እውቅና እንዳገኙ ተገልጿል። ሀምሌ 16/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
«ብልህ ወጣቶች፣ የኤአይ ክህሎቶችና የኢትይጵያን የወደፊት የፈጠራ እጣ ፈንታ መገንባት» የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው 6ኛው የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ባህል ግንባታ መድረክ «ብልህ ወጣቶች፣ የኤአይ ክህሎቶችና የኢትዮጵያን የወደፊት የፈጠራ እጣ ፈንታ መገንባት» በሚል መሪ መልዕክት ተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ፤ የዘመናችን የዓለም ውድድር በዲጂታላይዜሽን በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም የመድረኩ ዋና ዓላማ ተቋማት የሰሯቸውን የኤ.አይ ፊውቸሮች ከመተንተን ባለፈ በዘርፉ የኢትዮጵያውያን ዝግጁነት ምን እንደሚመስልና ወደፊት መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ሀሳብ ለመለዋወጥ መሆኑን አሳስበዋል፡፡ አገራት በዲጂታላይዜሽን ላይ ሉዓላዊነታቸውን ሳያረጋግጡ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸውን ማረጋገጥ እንደማይችሉ በማስገንዘብ የኤአይ ዘርፍ ለሀገር ህልውና ወሳኝ በመሆኑ በውድድሩ ውስጥ መገኘት ግዴታ መሆኑን ወ/ሮ ፀዳለ ተናግረዋል፡፡ በአገራችን ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝ በመጥቀስም የዲጂታል 2025 ግብ ተሳክቶ ወደ 2030 እቅድ መሸጋገሩን፣ የኤ.አይ ኢንስቲትዩት መቋቋሙን እና የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም ዝግጅት መጠናቀቁን በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱም የበቃ የሰው ሀይል ለማፍራት የስልጠና ፕሮግራሞችን ከመክፈት ባሻገር በቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ፕሮግራሞች አዳዲስ ፈጠራዎችን እያበለጸገ ይገኛል። በመጨረሻም ም/ዋና ዳይሬክተሯ ወጣቱ ትውልድ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ያለው ንቃት የሚደነቅ ቢሆንም ከአጠቃቀም አንጻር ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከሁሉም በላይ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ራሳችንንና አገራችንን ልንለውጥበት በምንችልበት አወንታዊ አግባብ ልንጠቀምበት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። (መረጃው የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ነው፡፡) ሀምሌ 15/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
በሲዳማ ክልል ከ11 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሞዴል አርሶ አደሮች የሙያ ብቃት ምዘና መሰጠት ጀመረ በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ እና ማዕከላዊ ዞኖች የሚገኙ 11 ሺህ 400 ሞዴል አርሶ አደሮች የሙያ ብቃት ምዘና እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታወቀ። ምዘናው እየተካሄደ የሚገኘው የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ከሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት ሲሆን፣ በ20 የአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላት እና በግንባር ቀደም አርሶ አደሮች ማሣ ላይ እየተከናወነ ይገኛል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ እንደገለጹት፤ የምዘናው ዋና ዓላማ የአርሶ አደሩን ክህሎት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንዲሁም ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የኤክስፖርት ምርቶችን ጥራት ማሻሻል ነው። በምዘና ሂደቱ ላይ የተሳተፉ መዛኞችና ሱፐርቫይዘሮች በበኩላቸው፤ ምዘናው ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ ያተኮረና የአርሶ አደሩን እውነተኛ የዕለት ተዕለት የግብርና ክህሎት የሚመዝን መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ አሰራር የግብርናውን ክፍለ-ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል። በምዘናው ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት፤ ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረውን ባህላዊ አሰራር በስልጠና እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመተካታቸው የምርት መጠናቸውና ጥራታቸው መጨመሩን ገልጸዋል። መረጃው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡ ሀምሌ 15/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI