Awda Hasab - አውደ ሓሳብ
Статистикаአውደ ሓሳብ፣ 'የሓሳብ መድረክ' ማለት ነው። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሓሳቤ እና እይታዬን የማጋራበት ነው። Awde Hasab, meaning "Idea Forum," is a space where I share my thoughts and perspectives on a wide range of topics.
- Последний пост
- 25 апр.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 42
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከTelegram ሳትወጡ $5 በቀላሉ የምትሰሩበትን አንድ ስራ ልጠቁማችሁ በመጀመርያ ከታች ያሉዉን Link ነክታችሁ ትገባላችሁ ይሄ ስራ ምትሰሩት Bot ላይ ነው ሊንኩን ነክታችሁ ወደ ቦቱ እንደገባችሁ ከላይ ምስሉ ላይ እንዳለዉ አይነት ያመጣላችዋል እናተ አዲስ ገቢ ስለሆናችሁ 3 Spin ይሰጣችዋል በዛ Spin ወደ $0.7 ትደርሳላችሁ ከዛ የነሱን Channel Join አርጉ እና ተጨማሪ +3 Spin ይሰጣችዋል ይላችዋል። Join ታደርጉ እና +3 ተቀብላችሁ ከዛ Spin ታደርጋላችሁ። ከዛ ወደ $0.8 ወይም 0.9 ትደርሳላችሁ። ማስታወቂያዎችን በመስራት/በማየት ተጨማሪ ታገኛላችሁ። ቀጥታ የእናንተን መጋበዣ Link ወስዳችሁ ሌላ አካዉንት ወይም ለሌላ ሰዉ Share እያረጋችሁ እነሱ ሊንኩን ነክተዉ የተሰጣቸዉን 3 Spin እንደሞከሩ 1 Spin ይሰጣችዋል። በአንድ ሰዉ ቀጥታ $1 እንደደረሳችሁ ማዉጣት ትችላላችሁ። ማወቅ ያለባችሁ ነገር $1 ሞልታችሁ ቀጥታ እንዳወጣችሁ በሌላ አካዉንት ስሩ። እንደዛ ካልሆነ በጣም ብዙ ሰዉ መጋበዝ ይኖርባችዋል። ስለዚህ ማድረግ ያለባችሁ $1 እንዳወጣችሁ በሌላ Telegram አካዉንት መስራት ጀምሩ። መልካም እድል🙏 ➡️👇👇👇 https://t.me/earncraft_bot/app?startapp=NjEyOTE0OTc3N18x
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር (የቢቢሲ - ዘጋቢ ፊልም) . . .
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር (የቢቢሲ - ዘጋቢ ፊልም) . . .
#BREAKING መረጃ የቴዎድሮስ ካሳሁን ( Teddy Afro ) "ኢቶሪካ" የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ከመለቀቁ በፊት ግጥሙ፣ ዜማና ድምጹ በAi ተቀናብሮ #Youtube ላይ በስፋት እየተሸቀለበት ነው። #tiktok ላይም ተቆራርጦ እየተደመጠ ነው። . . .
без подписи
#ትኩስ_መረጃ በዜጎች ላይ ወደ 600 ሚሊዮን ብር አካባቢ በማጭበርበር የተጠረጠሩት የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መስራች፣ ባለቤቶች እና ተባባሪዎች ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ማጣራት የገንዘብ መጠኑ 1.7 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ምርመራው ተጠናቅቆ ክስ መመሥረቱም ፌዴራል ፖሊስን በመጥቀስ Ethiopian Broadcasting Corporation ዘግቧል።
ChatPDF - መተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ጓደኛ አድርጉት ❤ PDF ፋይሎችን በቀላሉ ለማንበብ እና ለመረዳት የሚያግዝ ድንቅ Artificial Intelligence (AI) ነው። ጓደኛም ልትሉት ትችላላችሁ። ረጅም ፒዲኤፎ ፋይሎችን ከምታነቡ #አጤሬራ ያደርግላችኋል። ኧረ እንዳውም ልክ እንደ ሰው ከሰነዱ ጋር "ለማውራትም" ያስችላችኋል። ለምሳሌ መደመር መጽሃፍ #Upload አድርጋችሁ ፖለቲካ ይዘቱን ብቻ አጤሬራ ይሰጣችኋል። ካሻችሁም ኢኮኖሚያዊ ይዘቱን መጠየቅ ትችላላችሁ። የተቃረኑ ሀሳቦችን ለይቶ እንዲያወጣላችሁም መጠየቅ ትችላላችሁ። ምንም ሳይሰለች ያላችሁትን ሁሉ ያደርግላችኋል። በዛ ላይ ቋንቋ ይተረጉማል። ፋይሉ በእንግሊዝኛ ቢሆንም እንኳ በአማርኛ ብትጠይቁት ፈልጎ ላይም ልስላችኋል። ይሄ ሁሉ ሲሆን የሚሰጣችሁ መልስ ከየትኛው ገጽ ላይ እንደተወሰደ ይጽፍላችኋል። ይህም መረጃው ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችላችኋል። ለሁሉም ሰው በጣም ጣቃሚ ቢሆንም ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች (ለፈተና/ለማጥናት ወይም የሪሰርች መጽሐፍትን በፍጥነት ለማገላበጥ) ከምርጦች ምርጥ ነው። ሳይንሳዊ ጽሑፎችን በጥልቀት ለሚተነትኑ ተመራማሪዎች እንዲሁም ረጃጅም የሥራ ሪፖርቶችን፣ ስምምነቶችን፣ ውሳኔዎችን . . . ለመረዳት "በAi የሚሰራ ሚሳይል" ሊባል የሚችል ነው። ChatPDFን መጠቀም (ለመጀመር) የሚጠበቅባችሁ ድረ ገጹ ላይ በመግባት PDF ፋይሉን "Upload" ማድረግ ብቻ ነው። 👋
#የኤፕስቴይን_ፋይል የእንግሊዝ ፖለቲካን እየናጠ ነው! 😵 ስታርመር በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ሰበር ዜና እያስተጋቡ ነው
#የኤፕስቴይን_ፋይል የእንግሊዝ ፖለቲካን እየናጠ ነው! 😵 ስታርመር በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ሰበር ዜና እያስተጋቡ ነው
#የማይፈታው_የኤፕስታይን_እንቆቅልሽ |ክፍል - 2| እኤአ መጋቢት 2005 አንዲት በጭንቀት የተሞላች እናት ወደፓልም ቢች ፖሊስ ቀርባ ቅሬታ አቀረበች። ቅሬታዋ "የ14 ዓመት ታዳጊ ሴት ልጄ 'የአካል ብቃት እንቅስቃሴ' እንድታደርግ ተብላ በአንዲት ሴት ወደ ኤፕስታይን ቤት ከተወሰደች በኋላ እርቃኗን እንድትጋለጥ ተደርጋ የወሲብ ጥቃት ተፈጸመባት" የሚል ነበር:: ቅሬታውን የተቀበለው ጆሴፍ ሬክሊን የተባለ የፓልም ቢች ፖሊስ መርማሪ ነው። ሬክሊን በስራው የታወቀና የተደነቀ መርማሪ ነበር:: በጉዳዩ ላይ እጅግ ጥብቅ እና ጥልቅ ምርመራ ለማካሄድ ወሰነ፤ ወደ ተግባር ሲገባም ኤፕስታይን በስፋት ወንጀል እየፈጸመ መሆኑን የሚያመላክቱ ብዙ ጠቋሚ መረጃዎችን አገኘ። ይህም የኤፕስታይንን ቤት እንዲፈትሽ እና ሰፋ ያለ ምርመራ እንዲጀምር በር ከፈተ። ነገሩ ግን እንደታሰበው ቀላል ሆኖ አላገኘውም። መርማሪ ሬክሊን በኤፕስታይን ቤት ውስጥ የተቀጠሩ ሰራተኞችን ማነጋገር ሲጀምር ጉዳዩ የአንዲት ታዳጊ ጉዳይ እንዳልሆነ ተረዳ። የህጻናት የወሲብ ጥቃት ብቻ ሳይሆን የሰዎች ዝውውር ባሕርይ እንዳለውም ተገነዘበ፤ በምርመራውም መረጃ ማስረጃ እየጎተተ ሁለት ዓመታትን (2005 - 2006) ፈጀ። በመጨረሻም ኤፕስታይን ልጃገረዶችን በግል አውሮፕላኑ በተለያዩ ግዛቶች እንደሚያዘዋውር አረጋግጦ (የክልል ወሰንን የሚያቋርጥ በመሆኑ) ሰኔ 2006 ላይ FBI በይፋ ጣልቃ ገብቶ በፌዴራል ደረጃ ምርመራ እንዲጀምር ያሰባሰባቸውን ማስረጃዎች አስረከበ። FBI በበኩሉ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ገደማ ጥልቅ ምርመራ አካሂዶ በ2008 መጀመሪያ አካባቢ ባለ 53 ገጽ ዝነኛ የክስ ረቂቅ አዘጋጀ። ረቂቅ ክሱ ኤፕስታይን ከ80 በላይ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጃገረዶችን በስልታዊ መንገድ የመለመለበት እና የበዘበዘበትን ወንጀል የሚያረጋግጥ የተጠቂዎች እና የምስክሮች ቃል በዝርዝር ያካታተ ነበር። የተሰበሰቡት ማስረጃዎች ኤፕስታይንን እስከ ዕድሜ ልክ እስራት ሊዳርጉት እንደሚችሉ መርማሪዎቹ እርግጠኞች ነበሩ:: . . . #አስደንጋጭ_የፍትህ_ቅልበሳ አሜሪካኖች በፌደራል ደረጃ Crime Victims' Rights Act የሚባል ህግ አላቸው። አቃቤ ሕግ በልዩ ምክንያት ተጎጂዎችን በማሳወቅ እና ከተስማሙ የወንጀል ክስ የሚቋረጥበት ነው:: ነገር ግን በወቅቱ የፍሎሪዳ ደቡባዊ ዲስትሪክት የዩኤስ አቃቤ ሕግ የነበሩት የአሌክሳንደር አኮስታ ከኤፕስታይን ጠበቆች ጋር በሚስጥር ተደራድረው የፌደራል ክሱን ለማቋረጥ ተስማሙ:: ስምምነቱ በህጉ መሰረት ተጎጂዎችም ሆኑ ጠበቆቻቸው ሳያውቁትና ሳይስማሙበት የተፈጸመ ነበር:: ስምምነቱ በጄፍሪ ኤፕስታይን የወንጀል ድር ውስጥ "ቀኝ እጅ" እና ዋነኛ አስተባባሪ የነበረችው ጊስሌይን ማክስዌልን ጨምሮ አጠቃላይ ተባባሪዎችን ከመከሰስ ነጻ የሚያደርግ ነበር:: ይህም የFBI እና የፓልም ቢች ፖሊስ መርማሪዎችን ክፉኛ ቢያስቆጣም መፍትሄ አልነበረውም። ይሁንና በአሜሪካ የፍትህ ታሪክ ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ከሆኑ ውሳኔዎች ቀዳሚ ተደርጎም ተመዘገበ:: የፌደራል ክስ መሰረዙን ተከትሎ በምትኩ ኤፕስታይን በፓልም ቢች ክልል ሁለት ቀላል ክሶች ብቻ እንዲቀርብበት ተደርጎ ጥፋተኛ ተብሏል:: ጥፋተኛ የተባለው ለአቅመ አዳም ያልደረሰች ልጅን ለዝሙት በማባበል እና በሌላ ተያያዥ ቀላል የወንጀል ክሶች ነበር:: የተፈረደበትም የ13 ወራት እስራት ብቻ ሲሆን ቅጣቱን የፈጸመው ለየት ያለ ልዩ መብት ተካትቶለት በካውንቲ ወህኒ ቤት ነበር። ይኸውም በሳምንት ለ6 ቀናት፣ በቀን እስከ 12 ሰዓት ድረስ ከእስር ቤት ወጥቶ በራሱ ቢሮ ውስጥ እንዲሠራ የሚፈቅድ ነበር:: እንዳውም የራሱ የግል ጠባቂዎች እንዲያጅቡት ተፈቅዶለት ነበር። በዚህም "ከገንዘብ በላይ የሚጮህ ድምፅ፣ ከሥልጣን በላይ የሚበረታ ክንድ የለም" እንደሚባለው ኤፕስታይንም ግዙፍ ሀብቱን ሕግን የመግዣ ጋሻ አደረገው:: ገንዘቡን ለጥፋቱ ፈውስ ተጠቀመበት፤ በዙሪያው ያሰባሰባቸው ባለስልጣናት የወንጀሉ መደበቂያ ካባ አደረጋቸው። ተጠያቂነትን ለማክሰም ማዳፈኛ ሆኑት። ለፍላጎቶቻቸው ማርኪያ የታደኑ ሴቶች እምባ ከንቱ ሆነ። የፍትሕ መዛባት ነገሰ። ዓለም በሀብታሞች ወንጀል፣ በባለሥልጣናት ጥበቃና በተጎጂዎች እንባ የምትመራ መስላ ታየች። ነገሮች በዚህ መንገድ ተድበስብሰው ታለፉ:: . . . #ደሴቱ እና #ገመናው ጄፍሪ ኤፕስታይን በካሪቢያን ባሕር ውስጥ ሁለት የግል ደሴቶች ነበሩት። በዋናነት ለወንጀል ተግባሩ ይጠቀምበት የነበረው ዝነኛው ደሴት #ሊትል_ሴንት_ጀምስ ይባላል። አሁን ብዙዎች የሚጠሩት "የዝሙት ደሴት/የኃጢአት ደሴት/Paedophile Island " ብለው ነው።) ደሴቱ የሚገኘው በአሜሪካ ቨርጂን አይላንድስ ውስጥ ሲሆን፣ ከኒው ዮርክ ከተማ 2,575 ኪሎ ሜትር አካባቢ ይርቃል። በደሴቱ ላይ አንድ ትልቅ ዋና መኖሪያ ቤት፣ የቤተ መጻሕፍት ሕንፃ፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና አንድ እንቆቅልሽ የሆነ "ቤተ መቅደስ" የሚመስል ሰማያዊና ነጭ ቀለም ያለው ሕንፃ ይገኝበታል። በ53 ገጹ የFBI የምርመራ ውጤት በዚህ ደሴትና ክፍሎች በሴት ህጻናት ላይ የሚፈጸሙት የወሲብ ጥቃቶች በማያከራክር መልኩ ተሰንደው ነበር። ሂደቱም #ጊስሌይን ልጃገረዶቹን "ለትምህርት እድል" ወይም "ለሞዴሊንግ" በሚል ተስፋ ትመለምላቸዋለች። ከተመለመሉበትም "ሎሊታ ኤክስፕረስ" በተባለው የኤፕስቴይን የግል አውሮፕላን ተጭነው ወደ ደሴቱ ይወሰዳሉ። ከዚያም ለኤፕስተን እና ለታዋቂ እንግዶቹ "ማሳጅ" እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። በሰነዶቹ ውስጥ "ማሳጅ" የተባለው ቃል የወሲብ ብዝበዛ ኮድ ነው። ቃላቸውን የሰጡ ተጠቂዎች እንደገለጹት ተደጋጋሚ ከፍተኛ አስገዳጅ የፆታ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል። በመላ ደሴቱ በተለይም "ማሳጅ" በሚፈጸምባቸው ክፍሎችና ቦታዎች ኤፕስታይን በርካታ የደህንነት ካሜራዎችን ጠምዶ እንደነበርም ተረጋግጧል። እንግዶቹን የሚጋብዘውም እንዲደሰቱና እንዲከፍሉ ብቻ አልነበረም። ይልቁንም ድርጊታቸውን በቪዲዮ በመቅረጽ "ለማስፈራሪያነት" ለመጠቀምም ነበር። ኤፕስቴይንን ለዓመታት ከሕግ በላይ እንዲሆን ያደረገውም ይሄ እንደሆነ ይታመናል። . . . ጋዜጠኛ ጁሊ ኬ. ብራውን (የመጨረሻው መጀመሪያ) . . . /ይቀጥላል🙏
без подписи
#የማይፈታው_የኤፕስታይን_እንቆቅል
#የማይፈታው_የኤፕስታይን_እንቆቅል
#የማይፈታው_የኤፕስታይን_እንቆቅል
без подписи
#ሀሰተኛ_ደረሰኞች . . . ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት በቴክኖሎጂ ዘመን ደረሰኝ፣ ደብዳቤ፣ ስክሪንሾት፣ የጽሁፍ መልዕክት (SMS) . . . ማዘጋጀት ከባድ አይደለም:: እንዳውም በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ በርካታ አገራት እንዲህ አይነት ዶክመንቶች ብቻቸውን በፍርድ ቤት ለሚመሰረቱ ክሶች ማስረጃ ሆነው እንዳይቀርቡ እስከማገድ ደርሰዋል:: በተመሳሳይም ለመንግስታዊ ተቋማት ብቸኛ ማስረጃ ሆነው አይቀርቡም:: በኛ አገር ግን በተለይም በጉምሩክ ድርጅት ሀሰተኛ ደብዳቤዎች፣ ደረሰኞች፣ የመኪና እና ሌሎች ሰነዶች . . . በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይነገራል:: ከዚህም አልፎ የማያውቁ ሰዎችን ሳይቀር ራሳቸው ሰርተው/አሳርተው "ተገቢ" ክፍያቸውን የሚቦጭቁ ሰራተኞች እንዳሉ ገጠመኛቸውን የሚናገሩ ያጋጥማሉ:: . . . በዚህ ጽሁፍ የጥንቃቄ ምርልዕክት ማጋራት የፈለግኩት ግን ከባንክ ደረሰኝ ጋር በተያያዘ ነው:: ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ዲጂታል የክፍያ ስርዓቶች በእጅጉ ተደራሽ እየሆኑና እየተለመዱ በዛው መጠንም የተራቀቁ ማጭበርበሮች እየተስፋፉ በመሆናቸው ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ማስጠንቀቅ የሚጠበቅ በመሆኑ ነው:: . . . . #ሀሰተኛ_ደረሰኞች እንዴት ይሰራሉ? 😵 ተራ አጭበርባሪዎች Photoshopን ጨምሮ ሌሎች የላፕቶፕ ወይም የሞባይል ነጻ የፎቶ ማቀናበሪያ ( Graphics Editing) በመጠቀም ትክክለኛውን የባንክ ደረሰኝ ስም፣ ቀን እና የገንዘብ መጠንን ይቀይራል። 😡 መካከለኛ እና የተራቀቁ አጭበርባሪዎች በቴሌግራም ወይም በተለያዩ ድረገጾች ላይ ደረሰኝ የሚሰሩ (Receipt Generator) ቦቶችና አፕሊኬሽኖች በመጠቀም የሚፈልጉትን ስም፣ አካውንት፣ ብር . . . በመሙላት ልክ እንደ ባንክ ደረሰኝ አድርገው ማውጣትና ማሳየት ይችላሉ:: 👹 እንዲህ አይነት አጭበርባሪዎች Clone Appsም ሊጠቀሙ ይችላሉ:: የባንኩን አፕሊኬሽን ገጽታ (UI) ብቻ የሚመስሉ ነገር ግን ከባንክ ሲስተም ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የውሸት #አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም ስክሪንሻት ያደርጋሉ። እርግጠኛ ባልሆንም ከቻይናውያን ጋር በመተባበር የባንክ API (Application Programming Interface)ን Rebuild በማድረግ ደረሰኝ የሚሰሩ እንዳሉም ይነገራል:: (ይሄን መረጃ በሰማሁበት ወቅት ቦሌ አካባቢ ደረሰኝ በማሳየት የተፈፀመ ዘረፋን በመጥቀስ አጋርቼ ነበር) --- . . . መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ምንድነው? 😠 በፎቶሾፕና በመሳሰሉ ሶፍትዌሮች በማጥፋትና አስመስሎ በመጻፍ የሚደረጉ ተራ ማጭበርበሮች ብዙ ስህተቶች ስለሚኖሩት በማየት ብቻ ይታወቃል:: ለምሳሌ አያይዤ ያጋራሁት ደረሰኝ:- | በግልጽ የሚታይ የሂሳብ ስሌት ስህተት አለበት። "15% VAT of ETB 0.45.0" ይላል። 0.45.0 የሚባል ቁጥር የለም (ሁለት ቦታ ነጥብ አይኖርም)። | የፊደል አጻጻፉ (Typography) የተዝረከረኩ፣ ወጥ ያልሆኑ እና የጥራት ደረጃቸው የወረደ ነው። . . . በእውቀት የተመሰረቱ ማጭበርበሮች:- በቴሌግራም፣ በተለያዩ ድረገጾች፣ በReceipt Generator ቦቶችና አፕሊኬሽኖች እንዲሁም በClone Apps የሚሰሩ ደረሰኞች በፍፁም በማየት ላይለዩ ይችላሉ። 😠 ስለሆነም መፍትሄው:- 👉 የባንክ የመሳሰሉ ደረሰኞች በማየት ከማመን ይልቅ የራሳችሁን ትክክለኛ የባንክ አፕሊኬሽን (ለምሳሌ CBE) በመክፈትና Transaction History በማየት ማረጋገጥ ይገባል:: 👉 የባንኩን ትክክለኛ መልዕክት (Official SMS) CBE ( Commercial Bank of Ethiopia) በሚለው የራሱ (አጭር ቁጥር ስም) የሚልከውን የገቢ መልዕክት በማየት ማረጋገጥ ይገባል:: (ባንክ ከግል ስልክ ቁጥር "ገንዘብ ገብቶልዎታል" የሚል መልዕክት አይልክም::) 👉 ብዙውን ጊዜ አጭበርባሪዎች (ሌቦች) በጣም የቸኮሉ በመምሰል ችግሩ የባንክ ሲስተም ሊሆን እንደሚችል ለማሳመን ይጣደፋሉ:: ወከባ ይፈጥራሉ:: እንዲህ አይነት ሰዎች ሲገጥሙ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በእርግጥም በጣም እልፍ አልፎ የሚዘገይበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል:: እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር ባንክ በአካል በመሄድ ወይም ደውሎ ገንዘብ አካውንታችሁ ላይ ገብቶ ከሆነ ማረጋገጥ ካልሆነም የሚያሳዩዋችሁ ደረሰኝ ላይ ያለውን QR Code በባንኩ ኦፊሴላዊ አፕሊኬሽን Scan ማድረግ ያስፈልጋል:: ትክክለኛ ከሆነ የላኪውንና የተቀባዩን መረጃ ያሳያችኋል። (ሀሰተኛ ደረሰኝ ከሆነ QR ኮድ Scan ሲደረግ ምንም መረጃ አይሰጥም ወይም ከደረሰኙ ጋር የማይገናኝ ዝባዝንኬ ጽሁፍ ያሳያሉ።) ከዚህ ውጭ ማንም ስለቸኮለ እና ስላዋከበ ብቻ ደረሰኝ አይቶ ገንዘብ ገብቷል ብሎ ማመን አደገኛ ነው። . . . . . በተያያዘ ወይም ባልተያያዘ 🙋 National ID Ethiopia ዛሬ ማምሻውን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጸው ፋይዳ መታወቂያ .PDF መላክ አቋርጧል:: ከጠቀሳቸው ምክንያቶችም ሚዛን የሚደፉት በፎቶ ማቀናበሪያ ሶፍትዌሮች በማቀናበር የሚፈፀሙ የማጭበርበር ተግባራት ይጠቀሳሉ:: በጣም የሚገርመው ግን እስከ አሁን #በPDF በስፋት በተሰራጨው ፋይዳ መታወቂያ ማጭበርበሩ እንደሚቀጥል እየተወቀ ስለመፍትሄው ምንም አለማለቱ ነው:: ስለሆነም አጠራጣሪ ፋይዳ መታወቂያ ከገጠማችሁ ልክ እንደባንኩ ደረሰኝ QR Code Scan በማድረግ መለየት እንደምትችሉ ማስታወስ ያሻል::
без подписи
#ሀሰተኛ_ደረሰኞች . . .
በነገራችን ላይ . . . ☺በምንም መንገድ መለየት የማይቻል የኢሜይል መልዕክት inbox ውስጥ ማስገባት ይቻላል:: 🤔 በስልካችን ላይ በምንም መልኩ መለየት የማይቻል የጽሁፍ (SMS) መልእክት ከዚህ ቀደም ከተላኩት መሃል ሳይቀር ማካተት ይቻላል:: . . . 🙉ለምሳሌ - ከላይ ያያዝኩት የSMS መልእክት በምንም መልኩ ማንም መለየት አይችልም:: ሌላው ቀርቶ የተጻፈበት ጊዜ 2024 ይላል (በተፈለገው ማድረግይቻላል):: 👉 የEmail ደግሞ ከዚህም ይቀላል:: በአራት ነጥብ - ከምታምኑ ብትጠራጠሩ ይሻላል 👌 . . . 👌ማንም እየየተነሳም አይጃጃልባችሁ👌 . . . ለተጨማሪ ተመሳሳይ መረጃዎች 👇ተቀላቀሉ https://www.facebook.com/share/18J3QstZkv
"ካልከፈልክበት፣ ሸቀጡ አንተ ነህ" | | | ለርዕስነት የተጠቀምኩት የቴክኖሎጂ ዓለም የተለመደ አባባል ነው:: አባባሉ ለAI ተጠቃሚዎችም በትክክል ይሠራል:: ብዙ ተጠቃሚዎች #ከAI ነጻ አገልግሎቶች በስተጀርባ ያለውን እውነት በጥልቀት አይረዱም:: ባለማወቃቸውም "ለምን በነጻ ይሰጡናል?" እያሉ ይጠይቃሉ:: በግድየለሽነት የግል መረጃዎቻቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። እንደ Gemini፣ ChatGPT፣ Claude፣ DeepSeek እና ሌሎችም በነጻ የሚያገለግሉን ለበጎ አድራጎት የተቋቋሙ አይደሉም። ከገንዘብ የሚገዝፍ ትርፍ ስለሚያግበሰብሱበት ነው:: ለአብነት:- 🙏1. መረጃ - አዲሱ የዓለማችን ነዳጅ የAI ድርጅቶች ትልቁ ሀብታቸው መረጃ ነው:: እኛ በነጻ ስንጠቀም የምናስገባቸው ጥያቄዎች፣ የምንጽፋቸው ጽሁፎች፣ የምንጭናቸው ፎቶግራፎች፣ ሰነዶች . . . እና የምንሰጣቸው ግብረ-መልሶች ለድርጅቶቹ እጅግ ውድ ግብዓቶች ናቸው:: አገልግሎታቸውን ማዘመን የሚያስችል ጥናት የሚያደርጉትና በግብአትነት የሚጠቀሙት ከእኛ ላይ "በነጻ ሽፋን" የሚሰበስቡት ዳታ ነው:: በተጨማሪም ሞዴሉን የሚያሰለጥኑት ስንጠቀም በሚሰበስቡት ዳታ ነው:: በጠየቅን ቁጥር #AI ስህተቱን እንዲያርም እና የሰውን ልጅ አነጋገር/ፍላጎት ይበልጥ እንዲረዳ ያደርጋሉ:: የምንመርጣቸው ርዕሶች፣ ፍላጎቶቻችን እና የባህርይ ዘይቤያችን ተጠንቶ ለንግድ ማስታወቂያዎች ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች ይውላሉ:: አሁን #GeminiAI የጀመራቸው አይነት ከGmail፣ ከWhatsApp፣ ከPhone፣ ከYoutube፣ ከGoogle Drive . . . በማገናኘት ተጨማሪ አገልግሎቶችን የመስጠት አሰራርም ምንም ዓይነ የግል መረጃ እንዳይኖረን የሚያደርግ ነው። ሌላው ቀርቶ በምንጠቀምባቸው ስልኮችና ላፕቶፓች ምንም ዓይነት የግል መረጃ አይኖረንም። የSMS መልእክቶቻችን ሳይቀሩ ለእነሱ ተደራሽ ናቸው። 🙏2. "Hidden" ወይም ስውር ክፍያዎች ምንም እንኳን ቀጥታ ከኪሳችን ብር ባይወጣም፣ ተጠቃሚው የሚከፍላቸው ሌሎች ዋጋዎች አሉ። ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በሚወሰዱ ዳታዎች 'የግል ምስጢራዊነት' ዋጋ እንከፍላለን። የምናስገባቸው ምስጢራዊ መረጃዎች በድርጅቱ ሰርቨር ላይ ይቀመጣሉ:: ፈላጊ ሲያገኙም መረጃዎቻችንን ይሸጡታል። ስነምግባር የጎደላቸው የድርጅቱ ሰራተኞች በተለይም ሲለቁ በፈለጉት ጊዜ ያሻቸውን ሳይበር ጥቃት ሊፈጽሙብንና ሊያስፈጽሙብን ይችላሉ። ለAIው የምንሰጠው አዲስ ሃሳብ ወይም የፈጠራ ስራ በነጻ የድርጅቱ ንብረት ይሆናል። 🙏3. የሚያገኟቸው ሌሎች ጥቅሞች ድርጅቶቹ "ነጻ" አገልግሎት በመስጠት ብዙ ተጠቃሚ ያፈራሉ፤ ተወዳዳሪዎቻቸውንም ከገበያ ያስወጣሉ:: ይህም የገበያ የበላይነት እንዲይዙ ያደርጋቸዋል። ሰዎች በነጻው አገልግሎት ከተላመዱ በኋላ ሱሰኛ ሆነው ወደ ላቀው (Premium) አገልግሎት እንዲቀይሩ ይገፋፋሉ:: ሚሊዮኖች የስርዓት ሙከራ (Beta Testing) ሲጠቀሙበት ሲስተሙ ያለበትን ስህተት (Bug) በነጻ እንዲያርሙ ያስችላቸዋል። ባጭሩ በ"ነጻ" ተጠቃሚነት ስም የAI ድርጅቶችን ምርት እያሻሻልን፣ መረጃ እየመገብን፣ ግላዊነታችንን እያጣን እና ገበያቸውን እያሰፋንላቸው ነው። እኛ የምናገኘው ፈጣን መልስ ሲሆን እነሱ ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ የእውቀት እና የመረጃ ክምችት ይገነባሉ:: አገልግሎታቸውን አሻሽለው ወይም ዳታውን ሸጠውም ቢሊዮን ዶላሮችን ያግበሰብሳሉ። . . . #ጥብቅ_ማሳሰቢያ:- ማንኛውንም የAI አገልግሎት በምትጠቀሙበት ስልክ ወይም ላፕቶፕ የግል ምስጢራችሁን፣ የባንክ መረጃዎቻችሁን ወይም የንግድ ምስጢሮቻችሁን ባታስቀምጡ ይመከራል። ካልሆነ ግን ነገሩ "ወደሽ ካጎነበስሽ ምን ቢያደርጉሽ አይክፋሽ" እንደሚባለው መሆኑ የማይቀር ነው።