Official Fenote Loza Media
Статистикаይሄ መንፈሳዊ ቻናል በፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት ምዕመናንን ለማስተማርና ጠንካራ መንፈሳዊ ህይወት እንዲኖራቸው ለማድረግ የተከፈተ ሲሆን ሰብስክራብ በማድረግ እና ለሌሎች ቻናሉን በማጋራት የመንፈሳዊ ቤተሰባችን አባል ይሁኑ ። አብረን በመንፈሳዊነት እንድናድግ ፣ እንድንማር እንዲሁም እንድናዉቅ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጋብዘኖታል።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 165
- 1/48двое суток
- 189
- 1/72трое суток
- 203
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
"መከራ እግዚአብሔር እንደ ሐኪም ፈውስን የሚሰጥበት መድኃኒት እንጂ የሚቀጣበት ጅራፍ እንዳልሆነ እንረዳ።" ሊቁ አውግስጢኖስ መከራ ሁላችንም በስምምነት የምንሸሸውና የምንፈራው የሕይወታችን አካል ነው። ይህ ሽሽት ተፈጥሮአዊ ነገር ቢሆንም የሚደንቀው ነገር በድሮ ጊዜና በዘመናችን የተነሱ ፈላስፎች ሳይቀሩ የመከራን ጠቀሜታ መናገራቸው ነው። የሰው ልጅ በምቾት ሕይወት ውስጥ የተደበቀው አቅሙ በመከራ ጊዜ እንደሚገለጥና እንደሚጠነክር ይናገራሉ። ለክርስቲያን ግን መከራ ከዚህ የላቀ ጥቅም አለው። መከራ በዚህ ዓለም ምቾት ተዘፍቆ ይህችን ምድር እንደ ዘላቂ መኖርያው መጠበቅ ለሚፈልገው ሰው የዚህን አስተሳስብ ስህተትነት በታላቅ ድምጽ ትናገራለች። ለሰው ልጅ እውነተኛ ደስታና ሰላም በዚህ ዓለም እንደማይገኝ ትመሰክራለች። እግዚአብሔርም በመከራ መድኃኒትነት ይህችን ዓለም ቤታቸው ለማድረግ የሚጥሩ ነፍሳትን ይጠራል። ይህ ዓለም የጭንቀትና ችግር መፈራረቂያ የሆነበትም ሰው እውነትኛ ሰላምና እረፍትን ፍለጋ ከአምላኩ ጋር ይጣበቃል። "Let us understand God is a physician and suffering is a medicine for salvation, not a punishment for damnation." Augustine of Hippo Suffering is the main taboo in our society that we all collectively agree to flee from. That is natural, as who would want to be in pain? But not only the christians but the atheistic philosophers of old times and now have agreed to the salvific effect of suffering. They have observed suffering has the capacity to reveal the true potential of a person otherwise hidden in the comfort zone of life. A christian agrees to this saying and more over derives another meaning to suffering. For the christian, suffering loudens the alarm letting one know that true comfort and happiness is not to be found on earth, as it doesn't exist. If one gets accustomed to a life of comfort here, one will inevitably believe it to be its true home. Thus, God, who has destined man for a greater dwelling than here, teaches him to pine after his true home by medicating him in suffering. The sufferer will then long after true rest as he is not finding it here, thus possessing true comfort in God through the process. ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የቀጠለ.... የመናኞቹ መንገድ 📖 ✨ ምዕራፍ አስራ ዘጠኝ፡ ስለ ጸሎት ✨ ክፍል ሦስት ንቅአ ሕሊናን የሚለማመድ ሰው ምላሱን ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ ማንነቱንም ወደ ጥልቅ በመግባት መፈተሽና መጠበቅ ይኖርበታል (ገላ 6፤1)፡፡ በንቅአት ሊጠበቁ የሚገባቸውን በውስጣቸውም የኃጢያት ትዝታዎችንና ሃሳቦችን የያዙ ሰፊ መዝገብ ቤቶችን ያገኛል፡፡ ጸሎትህን የሚረብሽ ትዝታን በመኮርኮር ለማስታወስ አትሞክር፤ ባለፉ ኃጢያቶች ውስጥ በመርመስመስ ወደትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ አትሁን(ምሳ 26፤11)፡፡ ይህ የባላጋራህ ተወዳጅ መፋለሚያ ሲሆን ከርሱ ጋር ንግግር እንድትጀምር እንዲሁም ፈተናውን እንድትቀበለው የሚያደርግበት ቦታ ያንተ ሐሳብ እንደሆነ ተገንዝበህ የተለያዩ ፍላጎቶችን የሚያነሳሱ ትዝታዎችና ሐሳቦች ላይ ጊዜህን አታጥፋ፡፡ በምናብ ዓለም ውስጥ ጥርጥርና ጭንቀት እንዲሁም አመክንዮአዊ ንግግሮችና ምስክሮችን እና የማይጠቅሙ ጥያቄዎችን ከራስህ ከሚገኙ መልሶች ጋር የሚዘራበት ተመራጭ ቦታው ነውና እነዚህ ነገሮች ሲቀርቡህ በመዝሙረኛው ቃላት እናንተ ኃጢያተኞች ከእኔ ራቁ ብለህ አባራቸው(መዝ 119፤115)፡፡ ✨Chapter Nineteen : ON PRAYER✨ part three But it is not only the tongue that the person who practices the art of watchfulness must control. He must look to himself (Galatians 6:1) in every detail, and his care must extend to the depths of his being. Deep within he finds immeasurable store-rooms, where memories and thoughts and fantasies stir about and must be restrained. Do not stir up a memory that will cover your prayer with mud, do not root around in the soil of your old sins. Do not be like the dog that returneth to his vomit (Proverbs 26:11). Do not let your memory linger on private matters that can reawaken your desire or set your imagination going. The devil's favourite wrestling-place is precisely our imagination; through it he draws us to further intercourse with him, to consent and action. In your thought-world he sows doubt and worry, attempts at logical reasoning and proof, fruitless questions and self-found answers. Meet all such things with the words of the Psalm: Away from me ye wicked (Psalm 1 119:115). ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌸 ገብረ መንፈስ ቅዱስ 🌸 ቆሚያለሁ ሁሉንም አልፌ በምልጃው ከሞት ተርፌ ፀሎቱ ኃይል አደረገልኝ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረዳኝ (2) አዝ አበቃ ሲባል አልቆ ተስፋዬ በሃዘን ብዛት ሲፈስ እንባዬ ገብረ ሕይወት መጣ ፃድቁ አባቴ ደዌዬ ተሻረ ፀና ጉልበቴ (2) አዝ የጭንቁን ዘመን እረስቻለሁ ከሰዎች እኩል በእግር ቆሚያለሁ እርሱ ባይቆምልኝ በእግዚአብሔር ፊት አልቆምም ነበር ዛሬ በሕይወት አልኖርም ነበር ዛሬ በሕይወት አዝ በፅድቅ ክንዱ እየደገፈ ክፉን በምልጃው እያሳለፈ ስለ ቃልኪዳኑ በስሙ ታምኜ አልጠግብም ፃድቁን እርሱን አመስግኜ(2) አዝ በደዌ ኃጢያት የተጠቃችሁ ሞትን በችግር ለጠበቃችሁ ፃድቁን ጥሩት ይረዳችኋል ከአፈር ከትቢያ ያነሳችኋል(2) ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የመጽሐፍ ዳሰሳ📚 የኤፍራጥስ ወንዝ ደራሲ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መግቢያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ የሥነ-ጽሑፍ ጉዞ ውስጥ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥልቅ የነገረ መለኮት ምሥጢራትን ከውብና ማራኪ ሥነ-ጽሑፋዊ ለዛ ጋር አዋሕዶ በማቅረብ ረገድ ልዩ ቦታ ያለው ደራሲና ሰባኪ ነው:: «የኤፍራጥስ ወንዝ እና ሌሎች መጣጥፎች» የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ደግሞ የዚሁ ጥበባዊና መንፈሳዊ አገልግሎቱ አንዱ ማሳያ ነው:: መጽሐፉ በመንፈሳዊ ሕይወት፣ በነገረ መለኮታዊ ትርጓሜ፣ በማሕበራዊና ቤተ ክርስቲያናዊ ምግባር እንዲሁም በበዓላት ስብከቶች ዙሪያ የተጻፉ አእምሮን የሚያንጹና ልብን የሚነኩ በርካታ መጣጥፎችን አቃፊ ነው:: ደራሲው መጽሐፉን «በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በባሌ፣ በምዕራብ አርሲ፣ በኮፈሌና በዶዶላ ለቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው ሲሉ በግፍ ለተሠዉ ሰማዕታተ ክርስቶስ» መታሰቢያ ማድረጉ፣ የመጽሐፉን መንፈሳዊና ታሪካዊ ክብደት ከመጀመሪያውኑ ያጎላዋል:: እንደ አንድ አንባቢ ይህን መጽሐፍ ስታነቡ በቀላሉ የሚታለፍ አጫጭር ጽሑፎች ስብስብ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ምዕራፍ የራሱ የሆነ የነፍስ ምግብና የሕይወት መስታወት የያዘበት ጥልቅ ጉዞ እንደሆነ ይረዳሉ:: ይቀጥላል... በቀጣይ ክፍል ስለ መጽሐፋ መዋቅር እና አቀራረብ ዘይቤውን የምንመለከት ይሆናል ... ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማሳሰቢያ 👉 ይህንን ምስባክ ስናዘጋጅ በግጻዌው መሠረት ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ሊቃውንቱ ከወቅቱ፣ ከደብሩ፣ ከዕለቱ እና ከምሥጢሩ ተነሥተው እንደ ሁኔታው ሊቀይሩት ስለሚችሉ ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባ ለማለት እንወዳለን። ✨✨✨✨✨✨ ✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
''ልበ ንጹሐን ደስ ይበላቸው፤ ልባቸው የእግዚአብሔር ዙፋን ሆኗልና!'' ቅዱስ ኔክታርዮስ የሰውን ልብ የሚያረክሱም ሆነ የሚቀድሱት ነገሮች በተለያዩ መንገዶች ወደሰው ልቦና ይገባሉ። በዘመናችን በውዴታም ሆነ ያለፍቃዳችን ራሳችንን ለተለያዩ የመረጃ ምንጮች እናጋልጣለን። ከእኛ የማስተዋል ችሎታ ስውር በሆነው አቅማቸውም ማንነታችንን ቀስ በቀስ ይገነባሉ። ለመዝናኛነት የተጠቀምካቸው ነገሮች ባንተ ማንነት ላይ ምን አይነት ተጽእኖ ሊኖራቸው እንደሚችል አስበህ ታውቅ ይሆን? የምንመለከታቸው መዝናኛዎች በሚያስተላልፉት ሐሳብ ባንስማማ እንኳን መመልከታችን ብቻ የያዙትን የጠለሸ ሐሳብ በልባችን ቦታ እንዲይዝ በፈቃደኝነት ጋብዘናል። ጨለማ በነገሰበት ልብ ውስጥ ብርሃን የሆነው አምላክ ሊገባበት አይቻለውም፤ ጨለማና ብርሃን ሕብረት የላቸውምና! ስለዚህም ልባችን የርሱ ብቻ ዙፋን ይሆን ዘንድ ካሻን መዝናኛዎችን ለመመልከት የምንጠቀምባቸውን ጊዜዎች በመንፈሳዊ ንባብና ተመስጦ እንለውጠው። ከዛም በአመታት የመዝናኛ መፈራረቅ ብርድ የተያዘችው ልባችን ፈጣሪዋ እግዚአብሔር ያለምንም ከልካይ ዙፋኗ ላይ በምልዓት ይነግስ ዘንድ ይቻለዋል። "Happy is the pure heart, for such a heart becomes the throne of God" Saint Nektarios That which defiles or sanctifies the heart of man enters through various channels. We currently live at a time where numerous information enters through our senses voluntarily or with out our due consent. These multi fashioned figures affect our inner being without our notice, thus shaping our personality subtly. Have you ever considered the nature of the entertainments you consume and how they affect your mindset? Probably not. Regardless of whether we agree or not with the contents of the things we entertain ourselves with, we have given consent for their dark sides to have a place in our heart. A heart that is already occupied with darkness can not readily welcome the light of God, as light and darkness have nothing in common. Thus, if we wish God to occupy the major seat of our very being, let us lessen the time we consume with the amusements of our times and spend more time with God through spiritual readings and contemplation. Then, the heart that has become spiritually cold through years of "fun" and pleasure, will gradually learn to grasp the light and warmth of living with its God and creator. ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
без подписи
без подписи
без подписи
🌸ጸጋህ ይብዛልኝ🌸 ጸጋህ ይብዛልኝ ምህረት አይራቀኝ አማኑኤል ሆይ ስራህ ደነቀኝ ተመስገን ልበል ላቅርብ ምስጋና በአንተ ቸርነት ቁምያለሁና አዝ ጸጋ በዝቶልኝ እዘምርልሃለው በምስጋና ላይ ምስጋና አብዛለው አለኝ ሺህ ቃላት አለኝ ብዙ ቋንቋ አንተን መግለጫ ለዓለም የሚበቃ አዝ የተናገርከው ያሰብክልኝ ሆነ የልቤ መሻት ይህንን ነበረ አስተካከልከኝ ከሃያላን ጋራ አማኑኤል ሆይ እፁብ ያንተ ሥራ አዝ በለምለሙ መስክ ኣሳድረኸኛል ያ የጭንቁ ቀን አሳልፈኸኛል የምስጋና እርሻ ሆነልኝ ደጅአፌ አባት ሆይ ስለው ማር ማር አለው አፌ አዝ ባዝን ብደሰት ብወድቅ ብነሳ እስከ እሁን አለው በአንተ የተነሳ መርከቤን ጥዬ ተስፋ አደርገሃለሁ እንደምትሞላው እተማመናለሁ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የቀጠለ.... የመናኞቹ መንገድ 📖 ✨ ምዕራፍ አስራ ዘጠኝ፡ ስለ ጸሎት ✨ ክፍል ሁለት እውነተኛ ደስታ ጸጥተኛና የማይቆራረጥ ነው ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ሁሉጊዜ ደስ ይበላችሁ አለ(1 ተሰ 5፤16)፡፡ እውነተኛ ደስታ አንድ ሰው ማንነቱና አለም ሁሉ ከእውነተኛው ብርሃን በመዞራቸው ምክንያት እየተጸጸተ በማንባት ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ጌታችን የሚያዝኑ ብጹአን ናቸው(ማቴ 5፤4)፤ እናንተ አሁን በስጋችሁ የምታዝኑ ብጹአን ናችሁ፤ በመንፈስ መጽናናትን ታገኛላችሁና(ሉቃ 6፤21) እንዳለ እውነተኛ ደስታ ሃዘን ውስጥ ይገኛልና፡፡ እውነተኛ ደስታ የመጽናናትና ሰው የራሱን ደካማነትና የአምላኩን ምህረት በማሰብ የሚመጣ እንጂ ጥርስን በማሳየት ብቻ የሚገለጽ አይደለም፡፡ በአለማዊ ነገር የታሰረ ሰው ስሜቱ ተለዋዋጭ ነውና አንዳንዴ ሊደሰት አንዳንዴ ደግሞ በአለማዊ ችግሮች ሊከፋና ሊረበሽ ይችላል፡፡ ያንተ ጌታ(ማቴ 25፤21)የሚሰጠው ደስታ ግን እንደ እርሱ ባህርይ የማይለዋወጥ ነው፡፡ ስለዚህም ስጋህን በስርአትና በጾም በምትገዛበት ጊዜ ምላስህንም መቆጣጠር እንዳትዘነጋ፡፡ ብዙ ማውራት የጸሎት ጠላት ነውና፡፡ ብዙ የማይጠቅሙ ቃላት በመዘርገፍ ሲወጡ ለጸሎት የሚወጡ ቃላት ላይ በተቃራኒ ይቆማሉ፡፡ ለዚህም ነው ስለምንናገረው ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ የምንሰጥበት(ማቴ 12፤36)፡፡ ሰው በጽዳት ለመጠበቅ የሚፈልገው ክፍል ውስጥ አቧራ ይዞ መግባት እንደማይገባው ሁሉ አንተም ልብህን ከሃሜትና ባሳለፍከው ቀን ውስጥ ከገጠመህ ጥቅም ከሌለው ወሬ ጠብቅ፡፡ ምላስ እንደ እሳት ናታና እንዴት ትንሽ እሳት ትልቅ ጫካ እንደምታቃጥል አስብ( ያዕ 3፤5-6)፡፡ ትንሽ ነበልባል አየር ካላገኘ እንደሚጠፋው ሁሉ አንተም ለስጋ ፈቃድህ አየር ካልሰጠኸው በጊዜ ሂደት ይጠፋል፡፡ በቶሎ የምትናደድ ከሆነ በዝምታ በማለፍ አምላክ ብቻ ኑዛዜህን እንዲሰማ አድርገህ እሳቱን ሳይቀጣጠል አጥፋው፡፡ በሌሎች ሰዎች ጥፋት ከተረበሽህ የሴምና ያፌትን ምሳሌ በመከተል በዝምታ ሸማ ጥፋቱን ሸፍን(ዘፍ 9፤23)፡፡ ይህንን በማድረግህም ሌሎች ላይ ለመፍረድ ያለህን ፍላጎት ከመፈንዳቱ በፊት አጠፋኸው፡፡ ሰሃን ውሃ በውስጡ ሞልቶ እንደሚይዘው ዝምታም በጸሎት መሞላት እንደሚችል ልብ በል፡፡ ✨Chapter Nineteen : ON PRAYER✨ Part two True joy is quiet and constant, wherefore the apostle urges us to rejoice evermore (I Thessalonians 5:16). It proceeds from a heart that weeps over the world's (and its own) turning from the Light; true joy is to be found in grief. For it is said: Blessed are they that mourn (Matthew 5:4) and Blessed are ye that weep now with your carnal self for ye shall laugh with your spiritual (Luke 6:2 I). True joy is the joy of consolation, the joy that wells up in the knowledge of one's own weakness and the Lord's mercy, and that does not need the bared teeth of laughter to express itself. Think also of this: the person who is bound to earthly things may rejoice but may also be upset or disturbed or grieved over earthly things: his mind is exposed to continual changes. But the joy of your master (Matthew 25:21) is enduring, for God is unchangeable. Thus control your tongue at the same time as you discipline your body with fasting and strictness. Talkativeness is a great enemy of prayer. A spate of fluttering words stands in the way of the words of prayer. This is the reason that we shall render account for every careless word we utter (Matthew 12:36). One does not bring the dust of the road into a room that one wishes to keep clean; thus keep your heart free from gossip and chatter about the events of the day that is past. The tongue is a fire, and consider how great a matter a little fire kindleth (James 3:5-6). But if one gives a blaze no air, it dies out: if you do not give air to your passions they are gradually quenched. If you are kindled to anger, be silent and do not let it be noticed outwardly. Only the Lord may hear your confession. Thus you extinguish the burning brand at the beginning. If you are disturbed over the mistakes of another, follow the example of Shem and Japheth: cover them with the mantle of silence(Genesis 9:23); thus you quench your desire to judge before it bursts into flame. Silence can be filled with watchful prayer as a bowl holds water. ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ያልተኖረ ተስፋ እኛ የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ስንኖር ፍላጎቶቻችን እና ልናሳካቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች እጅግ ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ መልካም ብለን ተስፋ የምናደርገውን እና የምንመኘውን ህይወት ለመኖር ብዙ አናቅዳለን፡፡ በሰዎች እና በራሳችን ተማምነን በምዕናባችን(አእምሮ) ውስጥ ወደፊት የሚኖረንን ስኬታማ ህይወት ስዕል አኑረናል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ እነዚህ ምናባዊ ስዕሎች ከምናባዊነታቸው አይዘሉም፡፡ በመጀመሪያ ምኞት ከዛም የቀን ህልም፣ ያልተኖሩ ተስፋዎች ይሆናሉ፤ ይህም ቀስበቀስ ፍላጎት ወደማጣት ድብርት ብሎም ድባቴ (Depression) የምንለው የሥነልቦና ችግር ውስጥ ይዘፍቀናል፡፡ ይህም የማያቋርጥ ፍላጎት ማጣት ተስፋቢስ አድርጎን እራሳችንን እስክንጸየፍ ይከፋል፡፡ እኛ አርቶዶክሳውያን በእንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ ገብተን ወይም በሰዎች ላይ አስተዉለነው ሊሆን ይችላል፡፡ ግን መገንዘብ ያለብን ታላቅ እውነት በዚህ ዓለም ላጣነው እና ላላገኘነው ነገር ሀዘናችን የተመጠነ መሆን እንዳለበት ነው፤ ታላቅ ሃዘን ወደ ሞት ይወስደናልና “የዓለም ሀዘን ግን ሞትን ያመጣል” (ሮሜ 7፤10)። በዚህ ዓለም ያለ ሁሉ ከእኛ በታች ነው፤ እንገዛዉ ዘንድ እንጂ ስሜታችንን ይቆጣጠረን ዘንድ መልካም አይደለም፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የምናምን እኛ ተስፋ አንቆርጥም፤ በአምላካችን ደም የተገዛን ተስፋችን ከዚህ ምድር ያልሆነና ከቁሳዊነት የላቀ ነዉ፡፡ ተስፋም ብንቆርጥ በዓለሙ እና በዓለማውያኑ ተስፋ አንቆርጣለን አንጂ በራሳችን አንቆርጥም፤ እኛ ሰማያዊ ርስት ያለን ወራሾች ነንና! ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳን አሜን! ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
без подписи
✨✨✨✨የአያት ጌቴሴማኒ ቅድስት ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፍኖተ ሎዛ ሠንበት ት/ቤት በዚሁ በኛዉ ደብር የፈተና ጣቢያ ሆኖ በማገልገል የራሱን ተማሪዎች ጨምሮ የአያት ፈለገሕይወት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ እና የአያት ሾላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤቶችን ቁጥራቸዉ ከ200 በላይ የ4ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን አስፈትኗል ።✨✨✨✨ ይህንን ያደረገ የሠራዊት አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን።
ማሳሰቢያ 👉 ይህንን ምስባክ ስናዘጋጅ በግጻዌው መሠረት ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ሊቃውንቱ ከወቅቱ፣ ከደብሩ፣ ከዕለቱ እና ከምሥጢሩ ተነሥተው እንደ ሁኔታው ሊቀይሩት ስለሚችሉ ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባ ለማለት እንወዳለን። ✨✨✨✨✨✨ ✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የምስጋና ሕይወት ይህ መጽሐፍ በ1988 ዓም በብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የተጻፈ ሲሆን በ 2000 ዓም በዲ/ን ዘኤልያስ ወ/ሚካኤል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ የበቃ መጽሐፍ ነው። የምስጋና ሕይወት በአራት ምዕራፎች በ 99 ገጾች ላይ የሰፈረች በይዘቷ አነስ ያለች መጽሐፍ ስትሆን ስለ ምስጋና ሰፋ አድርጋ አቅርባለች። በዚህች መጽሐፍ ስለ ምስጋና ምንነት፣ ማመስገን ያለብን ማንን እንደሆነ ፣ የማመስገኛ ምክንያቶችን በመዘርዘር ታስረዳለች። "ዲያብሎስ በእናንተ ላይ እጅግ ክፉ ነገርን በማምጣት አሳዝኖአችኋልን? እናንተም ኢዮብን አብነት አድርጋችሁ እግዚአብሔር ይመስገን በማለት አሳዝኑት፡፡ ዲያብሎስን ድል ማድረግ ስትሹ ይህን መሣርያ ዘወትር ያዙ፤ ምስጋናን፡፡" ብሎ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረ የምስጋና ሕይወት ምስጋናን እንዴት ከዘወትር ሕይወታችን ጋር እንደምናቆራኝ፣ ከምስጋና ጋር ግንኙነት ያላቸው ምግባራትን እንዴት እንደምንይዝ እንዲሁም ለምን እናመሰግናለን ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ትሰጠናለች። "እርሱን እንድናውቀው ራሱን ስለሰጠን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ TikTok | Instagram | YouTube ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨