tgindex
www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn

www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn

Статистика

ይህ የዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ telegram channel ነው። በዚህ ቻናል ➟ በየቀኑ አዳዲስ ዝማሬዎችን ➟ ቆየት ያሉና ነባር ዝማሬዎችን ➟ የተለያዩ አስተማሪ ፅሁፎችን  ያገኛሉ። #ሊያድነን_ከሰማያት_የመጣው #የእግዚአብሔር_ልጅ_ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ይወደናል። @HawazTegegn @HawazTegegn

Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
3 910
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
 
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 384
20 постов
Вовлечённость
35,4%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
226
1/48двое суток
258
1/72трое суток
279

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://youtu.be/bYglN5IghgE?si=j6lUYwDFDvdoTddU

  • በህፃንነት ጆሮዬ የሰማሁት የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት እያለ ሲዘምር ከታላቅ እህቴ ጋ ድምጽ መጨመሪያው በማይሰራው ቴፕ 📻 ጆሮአችንን አስደግፈን በጉጉት እንሰማው ነበር:: ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገው እያለ ሲዘምር በልጅነት ድምፄ መዝሙሩን አብሬ ለማዜም እውተረተር ነበር : የተዋህዶ ልጆች ሁላችን የምንወደው ሙኃዘ ሥብሃት ዳግማዊ ደርቤ :: እግዚአብሔር ይመስገን ዘመናት አልፈው ዛሬ ያንን ያደግሁበትን ዝማሬ ለማድመጥ ብቻ ሳይሆን ለማቀናበር በቃሁ ይህንን የአገልግሎት እድል እና መንገድም እግዚአብሔር ሰጠኝ :: 🎙️በዜማ ሐዋዝ ሪከርዲንግስ 🎚️ የተቀረጸ እና የተቀናበረውን የእመቤታችን ኪዳነ ምሕረትን የምናመሰግንበት ወላዲተ አምላክን ምልጃዋን እና ፍቅሯን ምናወሳበት እጅግ ውብ የሆነ ዝማሬውን እነሆ ተጋበዙልኝ:: ዳጊዬ ወንድሜ ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን :: ሌሎች ስራዎችንም በቅርብ ቀን ይጠብቁን:: ከስር ባለው ሊንክ እየገባችሁ ዝማሬውን አድምጡት 👉👉👇

  • видео или голосовое, без подписи

  • 👉ቅዱሳን መላዕክት ስለእኛ ያውቃሉ? አዎ ! 👉ቅዱሳን መላዕክት ሊያስታውቁን ይችላሉ ? አዎ ! 👉ቅዱሳን መላዕክትን እግዚአብሔር ከሰጣቸው ግርማ እና ስልጣን የተነሳ በአክብሮት በፊታቸው እንሰግዳለን ወይ ? አዎ! እንደው በቅተን ቅዱሳን መላዕክትን ለማየት አንደርስም እንጂ በግርማቸው ቢገለጡ እንካን መስገድ በፍጥረታዊ ድፍረት እና አቅም መቆምም አንችልም 🫵🏽 ያው ያኔ ተገዶ ከመስገድ አሁን በፍቅር መስገድ በረከት አለው:: 👉ቅዱሳን መላዕክት ሊዳስሱን ሊቀርቡን ይችላሉ ወይ? አዎ👉👇👇 ዳንኤል 8 : 16 በኡባልም ወንዝ መካከል፡— ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ። 17 እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም፡— የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል፡ አለኝ። 18 ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ። ቅዱስ ገብርኤል ሆይ የእግዚአብሔርን የፈቃዱን ምስጢር እናውቅ እናስተውል ዘንድ ቅረበን: የጌታ መልዓክ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ የሚለው ድምፅህ ዛሬም በምንወድህ ልጆችህ ልቡና ላይ ያስተጋባል: በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም እኛን ወዳጆችህን አስበን : እንኳን የአምላክ ባለሟል የንጉሥ አጋዥ ያኮራል የለ? እሳቱን ስታበርድ ሠማዕታትን ስታጸና ሰምተን ተጽናንተናል : ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣን የእግዚአብሔርን የፈቃዱን ምስጢር ገልጠህላቸዋልና:: መጋቤ ኃዲስ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን አስታውቀኸናል አሁንም ቅዱስ ስሙን በልባችን ዘወትር አትምልን : ለተቀበሉት በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ ተብሎ እንደተጻፈልን በእምነት ጸንተን እንድንቆም ተራዳኢነትህ ይደግፈን:: ዳንኤል 9:21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። 22 አስተማረኝም፥ ተናገረኝም እንዲህም አለ፡— ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ። ገብርኤል ብሂል ብዕሲ ወአምላክ እምሃበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ (ቅዱስ ያሬድ ማሕሌተ ጽጌ) ትርጉም:- ገብርኤል ማለት ሰው እና አምላክ ማለት ነው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መልዕክተኛ ማለት ነው:: ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላክኸው ቅዱሱ መልዓክ ዳንኤልን እንደዳሰስከው እኛንም ዳስሰን አቤቱ ተናገረንም ማስተዋል እና ጥበብን ስጠን:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ይገለጣልና ገብርኤል የእግዚአብሔር ኃይል / ገብርኤል ሰውእና አምላክ ( የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምስጢረ ሥጋዌ ገልጧልና) ገብርኤል (እግዚአብሔር ብርታቴ ነው) :: እንኳን አደረሳችሁ የሊቀ መልዓኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ለሁላችን ይድረሰን:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ታናሽ ወንድማችሁ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ 19/11/2018 ዓ.ም

  • 12 июл.1 12013

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.1 02010

    ዛሬ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅዱሳን ሐዋርያትን የሰማዕትነት ክብር የምታስበው ከስብከታቸው ቃል : ከሕይወት ምስክርነታቸው : ለእግዚአብሔር ከተሰጠው ዕጹብ ማንነታቸው ጋር ነው:: ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ዓለም ሁሉ ይሰማ ያምን ዘንድ እስከ ሞት ድረስ ታምነው መስክረዋል:: የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት መፈክር ሳይሆን እውነተኛ የሕይወት መሰጠት እና ራስን አሳልፎ ለእግዚአብሔር የማስረከብ እንደሆነ አስተምረውናል :: በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርና በሰይፍ አንገቱ የተቀላውን ቅዱስ ጳውሎስን እንዲሁም ቁልቁል የተሰቀለውን ቅዱስ ጴጥሮስን በሌሊት ቤተክርስትያን እንዲህ ስትል ቅዱስ ያሬድ በጻፈው ድንቅ ቃል በፍቅር ስታወሳቸው አድራለች :- ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስለ መዓዛሁ ቅድው። ቃለ ደምክሙ ሐዋርያ ዘእግሩ ከዋው። ትርጉም:- የሐዋርያት የደማችሁ ድምፅ የእግሩ ኮቴ (የስብከቱ ጉዞ) : የተቀደሰ መዓዛው ከነበረው ውበት ጋር በልቤ ውስጥ ተመላለሰ: 🔶ደማቸው ክርስቶስን ያስታውሰናል ስለ ስሙ ነው የተሰውት:: 🔶ደማችው ስብከታቸውን ያስታውሰናል እንደ ሚታረድ በግ ተቆጠርን ብለው እንደተናገሩ ሞትን በዝምታ እምነታቸውን ደግሞ በአንክሮ ቃል ወደ አለም ሁሉ አስተጋብተዋልና :: 🔶ደማቸው የኮቴ ድምፅ አለው ቅድስናን ያውጃል 🔶ደማቸው መአዛ አለው ክርስቶስን ለብሰውታልና የዓለም ብርሃን የሆናችሁ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ዛሬም ምልጃችሁ እና ጸሎታችሁ ለእኛ ለልጆቻችሁ ይድረሰን:: እናንተ የክርስቶስ ሙሽሮች በስብክታችሁ አምነን በስሙ ተጠምቀናል ዛሬ በእምነታችን እንዳንደክም ምልጃ እና በረከታችሁን እናገኝ ዘንድ ደጅ እንጠናለን:: እናንተ በሰይፍ በሞታችሁ ክርስቶስን አከበራችሁ እኛ በሕይወት እያለን በምቾት መሃል ለምንባዝን ጸጋችሁ መንገዳችንን ያቅናልን:: ይህች ቀን እጅግ የከበረች ናትና ሞታችሁን ሳይሆን በክርስቶስ ሕያው መሆናችሁን ደግሞም በተሰጣችሁ ቃልኪዳን ልጆቻችሁ ለሆንን ለእኛ ምልጃ ጸሎታችሁ እንዳለን እያሰብን የሃዘን ሳይሆን የደስታን እንባ በአይኖቻችን አቅርረን : የስብክታችሁ መዓዛ የሆነውን መአዛ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስን በደማችሁ መፍሰስ ያከበራችሁትን በምስጋና በፊቱ እንቆማለን:: ዛሬም በሃገራችን በኢትዮጵያ ያሉ ሰማዕታትን የእናንተን ዋጋ ያገኙ ዘንድ በረክታችሁ በምድራችን ላይ ይደር:: እናንተ ሰማዕታት ብርሃናተ ዓለም ሆይ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን አብርታችሁልናልና አሁን በብርሃን ነን እንጂ ጨለማ አይጨልምብንም:: ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ሐምሌ 05 2018 ከታናሽ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 4 ከቀኑ 7:00 ሰአት ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አራተኛ ፎቅ ላይ ያለው አዳራሽ:: የመምሕር ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ሁለት ድንቅ መንፈሳዊ መጻሕፍት ይመረቃሉ በቸር ያገነኘን::

  • 1 июл.1 310321

    አርሴማ ፈርኒቸር +251916581980 ሰአሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ጋር የሚገኘው የገበያ ማዕከል ውስጥ ያገኙታል:: አርሴማ ፈርኒቸር በጣም እናመሰግናለን::

  • 17 июн.2 540353

    በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ በትናንትናው እለት ዜማ ሐዋዝ ሪከርዲንግስ በካህናት አባቶች ቡራኬ እና ጸሎት በርካታ አገልጋዮች ሰባክያን ዘማርያን እንዲሁም የሚድያ ሰዎች በተገኙበት በ09/10/2018 ዓ.ም በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሮአል:: ሙሉ የቡራኬ እና የምሥጋና ቪዲዮውን ይጠብቁን:: እግዚአብሔር ይመስገን "By the grace of the Almighty, Zema Hawaz Recordings officially opened its doors yesterday (Sene 9, 2018 E.C.). We were honored to begin our journey with the blessings and prayers of our spiritual fathers, surrounded by ministers, preachers, singers, and media guests. The full video of the blessing and thanksgiving ceremony is coming soon. Praise be to God!"

  • 14 мая1 900431

    ዜማ ሐዋዝ ሪከርዲንግስ :- የመንፈሣዊ መርሃግብሮችን ሳውንድ ሲስተም እና አጠቃላይ የድምጽ ቅንብር አገልግሎት ለእኛ ያስረክቡን በጥራት እና በትጋታችን ይደሰታሉ:: ለማንኛውም መረጃ በፌስቡክ አካውንት በinbox መልዕክት ቢያስቀምጡልን ያገኙናል :: ስለ ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን::

  • 12 мая1 932201

    አካውንት ቁጥር :- 1000153401768 ለበለጠ መረጃ :- 0911890696 0913039824

  • 2 мая1 88025

    እሁድ : ሰኞ : ማክሰኞ ሚያዝያ 25,26 እና 27 ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰሚት መካነ ሠላም መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ ቤ/ክን ከቀኑ 11 : ሰአት ጀምሮ ሁላችን ተጠርተናል እግዚአብሔር በቅዱስ እልፍኙ ይሰብስበን::

  • 7 апр.2 09247

    ኢሳ 53:7 ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

  • 4 апр.2 152491

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 апр.1 902171

    ማቴ 21 : 10 ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ፡— ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ። በትሕትና የተገለጠ ንጉስ እንደ ኃያል ጦረኛ በፈረስ መግባትን አልመረጠም ሠላማዊ ነውና : እንደ ብርቱ ሠልፈኛ በጦር አጀብ መግባትን አልወደደም እርሱ ፍቅር ነውና:: በአህያይቱ እና በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሣሌም ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ገባ:: ንጉሠ ሣሌም የሠላም ንጉስ ንጉሠ ጼዴቅ የጽድቅ ንጉስ:: ድል የሚነሳው ሞትን እና ጨለማን ነው ኃጢአት እና አመጻን ለተሞላው ዓለም የጽድቅን ብርሃን የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ነው እርሱ:: አቤቱ ኃያል ሆይ ኪሩቤል ጀርባ ላይ የተቀመጥህ : ክዋክብትን በየሥማቸው በምሕዋራቸው ያከተምክ : የሌለውን ነገር እንዳለ አድርገህ የምትጠራ ፈጣሬ አለማት : ኃያልነትህ ፍቅርህን ሳይሸሽግብን በመውደድህ ቀረብከን:: ማንም በፊትህ መቆም የማይችል : ራስህን ያለ መሰሰት አስረዳኸን : ጦረኛ አይደለሁም ለ ምድራዊ ንግስና አልመጣሁም ስትል : በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጠህ ወደ ኢየሩሳሌም ገባህ:: ልዑል ሆይ “ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም” ያልህ የተፈራህ ገናና በሕብዝ መሃል ታየህ ትዳሰህም : የዳሰሱህም የዳሰስካቸውም ሁሉ ዳኑ:: ፍቅርህ እና ምሕረትህ እንደምን የበዛ ነው?? ዜማ አንተን ክፍ ላያደርግህ : ምስጋና ዙፋንህን ላይመጥን : አመስጋኞች በምስጋናህ ይከብሩ ዘንድ ዜመኞች በአንተ ይባረኩ ዘንድ ከሚጠቡ አንደበት ቅኔን ታደምጥ ዘንድ ወደድህ ለአንተ የሚመጥን መስዋዕት የተሰበረ ንጹህ ልብ ነውና:: አንደበት ቢዘጋ ድንጋዮች ባለቅኔ የሚሆኑልህ : አለቶች እልልታን የሚያስትጋቡልህ የፍጥረታት ንጉስ ነህ አንተ:: ሆሳዕና እንልሃለን አቤቱ አሁን አድን እውነተኛ መድኃኒት አንተ ነህና:: ወልደ አብ ሕያው ወልደ ማርያም ሥግው : : ማስያስ ሆይ በምሕረትህ ጎብኘን:: ህመም ላጎበጣት ምድር : እምቢታ ምሥጋናዋን ለቀማት ዓለም አንተ ፍሥሃ ነህና እለፍ ግባ በሕይወታችን ውስጥ :: አቤቱ በመቅድስህ የተሰበሰብን የዘንባባ ዝንጣፊን ብቻ ሳይሆን ራሳችንን በፊትህ አንጥፈን ሆሳዕና እንልሃለን:: ይባዕ ንጉሠ ሥብሃት እንደተባለ የክብር ንጉስ ሆይ ግባ:: እንቆቅልሻችን ይፈታ ስምህ መድኃኒት ነውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ : አቤቱ አሁን አድነን:: ለበደለው ማንነታችን ይቅርታን በጥፋት ለተሞላው እልፍኛችን ምሕረት አድርግልን:: ንጹህ ምንጭ ለሚያደፈርስ እግራችን : ለምለሙን ለሚቀጥፍ እጃችን : አመጻን ለሚያማትረው የአይኖቻችን ማንነት አቤቱ በቁጣህ ሳትቀስፈን ምሕረት አድርግልን:: ለታመመው ምስኪን ደራሽ ለተጨነቀችይቱ መበለት ተስፋዋ : በደይን ለተያዙ እፎይታ ኣንተ ነህና መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሆሳዕና : አቤቱ አሁን አድን:: ይቅር በለን ማረንም:: ከፍርድህ ቁጣ ስር መሆን ያስፈራልና መሃሪ ሆይ በምሕረትህ ጎብኘን:: አትለፈን ይባዕ ንጉሠ ሥብሃት:: ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ከታናሽ ወንድማችሁ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ 26/07/2018 ዓ.ም

  • 2 апр.1 65015

    "ለእናት መራሔ ብርሃናት - ከምሽት እስከ ንጋት " መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ እስከ ንጋት የሚዘልቅ : በጅምር የቆመውን የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል መራሔ ብርሃናት ሰንበት ት/ቤታችንን ሕንጻ ከፍጻሜ የምናደርስበት : ስባክያነ ወንጌል መምህራን ዘማርያንና ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሚታደሙበት ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንፈሳዊ መርሃ ግብር : * ትምህርተ ወንጌል  * የበገና ዝማሬ አገልግሎት ምሽት    *ሥነ ጽሑፍ  * ዝማሬ በተጋባዥ  ደብር *61ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ ቅኝት  እነሆ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ  በመራሔ ብርሃናት ሰንበት ት/ቤታችን ከህጻንነት እድሜ እስከ ጉልምስና በእውቀት በጥበብ ታንጻችሁ ያደጋችሁ ፣ በትናንት አገልግሎት ዛሬም በረከትን ያተረፋችሁ : እናቶችና አባቶች: ወንድሞችና እና እህቶች እንዲሁን ለመላው የኦኦተቤ ምእመናን ወምእመናት ሁላችሁ : የሰንበት ት/ቤታችንን ጅምር ሕንጻ በማስፈጸም : ታላቁን መንፈሳዊ አገልግሎት ታስቀጥሉ ዘንድ : በእነዚህ ምሽቶች የእጅ ስልካችሁን በመጠቀም የ online መርሀ ግብሩን እንድትሳተፋ እና የበኩላችሁን አስተዋጽኦና ድጋፍ ታበረክቱ ዘንድ የሁላችን እናት መራሔ ብርሃናት ሰ/ት/ቤት በአክብሮት ትጋብዛለች ። የቀጥታ ስርጭት መከታተያ ማህበራዊ ገጾች https://youtu.be/@merahe22 facebook @merahe 22 Tiktok @merahe 22 የባንክ አካውንቶች cbe : 2221 አባይ ባንክ : 2222 ቴሌ ብር 0949-09-83-01 Cashapp- $merahe22 Zelle - 4044726429 (Alazar Tefera) https://gofund.me/b8d76506f ስልኮች +251 977-25-22-22 +251 910-00-78-95 +251 949-09-83-01

  • 2 апр.1 340

    https://vt.tiktok.com/ZSHMdcPfQ

  • 24 мар.2 000311

    የሠዓሊ ጌታቸው ታደለ ከወርቅ እና ከአልማዝ የተሳለ የእመቤታችንን ሐዘን ሚገልጥ ቅዱስ ሥዕል መጋቢት 20 ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ ጋር የሚገኘው አዲሱ የተሰራው ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ሆቴል :: መግቢያ በነጻ

www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn — tgindex