- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 133
- 1/48двое суток
- 152
- 1/72трое суток
- 164
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እጅግ ከምወዳትና ከማከብራት ልምድ የጠገበች ፣አመለ ሸጋዋ የስነ ልቦና ባለሙያ ትዕግስት ዋልተንጉስ(ቲጂ)ጋር ስለ ጋብቻ ጥሩ ቆይታ አድርገናል በትሕትና ልጋብዛችሁ።
https://youtu.be/L7UaEVVqrQU?si=UzoftAa_pWU9jBS0
https://www.facebook.com/share/p/1Ba22K1TUR/
https://www.facebook.com/share/p/1DwjGmzsQN/
https://www.facebook.com/share/p/1DC5fBq9V4/
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02EEKyz4kfyrvMc1y75nDsTjMYSzovCCs2EPJR5uJM9YiKrH71eVWYcAARp5pRKSHUl&id=100010628885404
ይድረስ ለገዳዮች! ይድርስ ገዳዮችን ለምታውቋቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው! ይድረስ ለምታሰማሯቸው! ህያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ከገደላችኋቸው ይልቅ ለእናንተ ከልቤ አዝኛለሁ አልቅሻለሁ። ጨካኝነት ልክ አለው ፣በእናንተ የማያበቃ ለልጅ ልጆቻችሁ የሚተርፍ ግፍ አድርጋችኋል። የዘራችሁት በቅሎ፣ ጽዋው ሲሞላ ጨልጣችሁ ትጠጡታላችሁ። ብትጮኹ የማትሰሙ ፣ምድር የከዳችው ከርታት ትሆናላችሁ ። ሰማይ ብቻ ደሞዝ የሚከፈል እንዳይመስላችሁ በዘራችሁበት ምድር እዚሁ ትከፍላላችሁ። እናንተ በጨለማ አድርጋችሁታል በብርሃን ትከፍላላችሁ። በቃሉ የሰውን ደም የሚያፈስ የእርሱ ደም ይፈሳል ።እግዚአብሔር በአምሳሉ ፈጥሮታልና ያለ እግዚአብሔር በዙፋኑ አለ። እውነተኛ ዳኛ ነው ይፈርዳል። ከዚህ ለመዳን አንድ ዕድል ብቻ አላችሁ ፣ የገደላችኋቸውን ቤተሰብ፣ወዳጅ፣የሃይማኖት አባቶች አልቅሳችሁ እናንተ ይቅርታ አድርጉልን አምላካችሁንም ምህረት ለምኑልን በሏቸው ። መቼም ለእናንተ አሁን ይህ የሞኝ ምክር ይሆናል። የዘራችሁት በቅሎ ስታጭዱ ግን ግሩም ምክር ነበር ያስብላችኋል። ማስተዋል ይብዛላችሁ!!
без подписи
ክፋ ቀን ያልፋል እንረዳዳ!! በሰዎች የኑሮ ጫና በተለይም በወዳጅ ዘመዶቻችን ውስጣችን ያዝናል ፣እንጸልያለን መልካም ነው። እኛስ እያካፈልን ነው? የአንዳንዶቻችን ማኪያቶ(ቡና) የአንድ ቤተሰብ ቁርስ ምሳ እራት ይሆናል እናስብበት።የሚካፈል ጠፍቶ ሳይሆን፣የሚከፈል ልብ አጥተን እንዲሆን ራሳችንን እንይ። ለሚለምን መስጠት ደግ ልብ ያለው ማንነት ነው።ነገር ግን መለመን የማይችል፣ ልጆቼን ምን ላጉርስ? የሚል ብዙ አለና ወንድሜ፣ እህቴ እንዴት እየኖርክ ነው? ብለን በጎደለው በኩል እንሁን። የእማዬና የአባዬ ጓደኛ እንዴት ናቸው? እኩዮቻችን አብረን ያደግናቸውና የተማርናቸው ደህና ናቸው? ያለፈው አልፏል ተነሳ አሁን እንጠይቃቸው። ሥራ ያጣን ፣አቅጣጫ የጠፋውን፤ ሥራ ከመስጠት አቅጣጫ ከመጠቆም የበለጠ ልግስና የለምና እንተያይ ። እነርሱ፣ በልቶ ከጠገቡ ፣ጠጥቶ ከረኩ፣ለብሰው ከሞቃቸው ስለ ሌላው ግድም የላቸው። ከሚባሉ አንሁን ቀን ያልፋል ። የተለያየ መንፈሳዊም ሆነ ሌላ አለማዊ ቅጥ ያጣ ድግስ ግድ የላችሁም ወጭውን ኑሮ ለተጫነው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ አድርጉት አልልም ።ለራሳችሁ ወዳጅ ዘመዳችሁ አድርጉት። የእምነት ተቋማት እናንተን እንዲህ አድርጉ ማለት ቢከብደኝም ከሌላው ጊዜ በተለየ ምዕመኔን በምን ላግዘው እችላለሁ? ብሎ ለማሰብ ጊዜው አሁን ነው። እንኳን ገንዘቡን ነፍሱን ለመስጠት የማይሰስተው ልጃችሁ ነው ኑሮ ያጎበጠውና አግዙት። መንግሥት ፣የእምነት ተቋማት፣የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና እያንዳንዳችን በአቅማችን ከተረዳዳን ቀን ያልፋል ። እንተዛዘን ፣እንረዳዳ፣እንተያይ፣እንደጋገፍ! ክፋ ቀን ያልፋል እግዚአብሔር ያግዘን ።
https://www.facebook.com/share/p/18Z3sWNK5n/
https://www.facebook.com/share/p/18WHXGN5AR/
https://www.facebook.com/share/p/18wVexpdTb/
የእግዚአብሔር ተቋም ሲፈርስ እኛ እንዴት ተባባሪ እንሆናለን? ፍቺ አሳሳቢ እየሆነ ነው!! ማንም ለመፋታት አይገባም ስላልቻለ ብቻ ነው። በማንም ከመፍረድ መቆጠብ ተገቢ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ መወያየት መመካከር ደግሞ ተገቢ ነው። ምክንያቶች ለሁሉም ለራሱ በቂ ነው።ለራስ በቂ ነው ማለት ልክ ነው ማለት እንዳልሆነ መረዳት በጣም ወሳኝ ነገር ነው። በወፍ በረር ብናየው የዘመናችን የጋብቻ ፈተናዎች ብዙ ቢሆኑም ዋንኛዎቹ ፣ ⑴ የኑሮ ጫና (ገንዘብ) ⑵ የቤተሰብና የወዳጅ ጣልቃ ገብነት ⑶ ሩካቤ ⑷ የተግባቦት ድክመት ይመስለኛል። መፍትሄው መፋታት ይመስላል ግን መፋታት ውጤቱ ኪሳራ ብቻ ነው። ምን ይደረግ?? ከችግር ነፃ ትዳር ከሰማይ አይወርድም በአንድ ቀንም አይገነባም።ጊዜ ወስደን እንምከር፣እንማር፣እናማክር ። በተለይ ወንድሞቼ አማካሪ ጋር ለመሄድ እናስቸግራለንና ራሳችንን ብናስተካክል ብዙ ነገር የሚስተካከል ይመስለኛል። የሚፈርሰው የእግዚአብሔር ተቋም ነው ።እኛ አፍራሽ ሃይል መሆን ይገባናል?? እግዚአብሔር መፋታት ይጠላል መንፈሳችንን እንጠብቅ። እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!! ተረፈ አበራ
без подписи
без подписи
ማራናት ማራናት ማራናት አሜን ኢየሱስ ቶሎ ና!!!
ልጆቻችንን ወደ ቄሳር ትምህርት ቤት እየላክን፥ ሮማውያን ሆነው ሲመጡ መደነቅ የለብንም! _ቮዲ ቦካም
ክርስቶስን በማን ልክ ነው የምናየው? ክርስቶስን በአብያተ ክርስቲያናት ልክ አላየውም፣ ከተልዕኮአቸው አፈንግጠው ክርስቶሳውያንን ሲያወግዙ አይቻለሁ። አይተው ሰምተው የማያውቁት ጭምት የጌታ ባርያ ላይ የሞት እዘዝን ሲያውጁ አይቻለሁ። ኢየሱስን በ"አገልጋዮች" አልተምነውም፣ ኢየሱስ የሞተላቸውን ያለርህራሄ ሲያሳድዱ፣ መድረሻ ሲያሳጡ ተመልክቻለሁ። የሀኬታቸው ተባባሪ ያልሆነን ጥላሸት ሲቀቡ፣ ያሳወሩትን መንጋ ሲያዘምቱበት ተመልክቻለሁ። ኢየሱስን በምዕመናን አልመዝነውም፣ በጭንቅ ዘመን በቃል ያፅናናቸውን፣ መንገድ የመራቸውን፣ "እንዴት፣ ለምን" ሳይሉ፣ ዘመነኛ ተሳዳቢ ጋር አድመው ያለርህራሄ አምሳለ ሥላሴን ሲቀረጥፉ አይቻለሁ። ስለዚህ ክርስቶስን ብቻውን አምነዋለሁ፣ በመስቀሉ አየዋለሁ፣ በዙፋኑ አስተውለዋለሁ። ሰዎችንም ዓለምንም አጥርቼ የማይበት መስተዋቴ እርሱ ነው። በክርስቶስ የምለካው እንጂ፣ ክርስቶስን የምለካበት ተቋም፣ ህብረት ወይም ግለሰብ የለኝም። አልፋዬና ኦሜጋዬ ኢየሱስ!!!
https://www.facebook.com/share/v/1BMDzkVSe6/
ሰላም እንፈልጋለን? የሞኝ ጥያቄ እንደሚመስል እረዳለሁ።ሁሉ ሰላምን ይፈልጋልና ።ነገር ግን አንድን ነገር ከማይገኝበት መፈለግ ትርፉ ድካም ነው። ሰላም ይሰጣሉ ብለን የተደገፍንባቸው ሸንበቆዎች ሁሉ ምርኩዝ መሳይ ተሰባሪዎች ናቸው። ሰላም የሚሰጥ ነው።የማይወሰድ ሰላም ያለው ከጌታ ከኢየሱስ ብቻ ነው።እርሱ ሰላማችን ነው ።የከፈለው ዋጋ ሁሉ ለእኔ ፣ለአንተና ለአንቺ አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም ሊሰጠን ነው። ሰላምን ሰጠኸን ሰላምን ተውክልን እያላችሁ ትዘምሩ ዘንድ በፍቅር ጋበዝኳችሁ። ሰላምን ሰጠኸኝ ሰላምህን ተውክልኝ አእምሮን የሚያልፍ ሰላም አገኘሁኝ ክብር ለአንተ ይሁን እዘምራለሁኝ የተለየ ሰላም ሰላምህን ተውክልኝ ከቀራንዮ ጣር ሰላም ፈሰሰልኝ ኃጢአቴም ተተወ ድኛለሁ ላልጠፋ የሰላም አምላክ ሆይ ክብር ላንተ ይብዛ ሰላምን ልትሰጠኝ አነባህ ስለ እኔ ኃጢአት ያላወቀህ ወሰድክ አበሳዬን የጎልጎታ ጭንቅህ ለእኔ ዕረፍት ሆነ ሰማይና ምድር በደምህ ታረቀ (2X) ከመከራ ስጋት ከፍርሃት ዳንኩኝ በአለቱ በአንተ ስለተሸሸኩኝ ተናውጠው ቢጠፉ ምድርና ሰማይ ሰላሜ ባንተ ነው ምንም አያስፈራኝ የሰላሜና የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ አንተ ነህ የሕይወቴ መልህቅ ስወድቅ አንስተኸኝ ቆሜአለሁ ታስቤ በምሕረትህ ብዛት በዝቶልኝ ሰላሜ (2) ሰላምን ሰጠኸኝ ሰላምህን ተውክልኝ አእምሮን የሚያልፍ ሰላም አገኘሁኝ ክብር ለአንተ ይሁን እዘምራለሁኝ