tgindex
ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

Статистика

“ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም” ቅዱስ ያሬድ ይኽ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡ መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካሎት ⬇️⬇️

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
15
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
6 036
−6 за 2 дн.
Сутки
−2
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
549
29 постов
Вовлечённость
9,1%
к подписчикам
Постов в день
2,1
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
463
1/48двое суток
530
1/72трое суток
572

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ። ሠምሩ ሲል ነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይህን ዓለም እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ካለመኖር ወደ መኖር ካለመታየት ወደ መታየት አምጥተው የበቃ የነቃ አድርገው ፈጠሩ፤ ወርእየ እግዚአብሔር ኵሎ ዘፈጠረ ከመ ሠናይ እንዲል፡፡ አንድም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይኄልዩ᎓᎓ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አዳምን እንፍጠር ብለው አሰቡ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይትናገሩ፡፡ ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ ብለው ተናገሩ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ፤ አዳምን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከአምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ፈጠሩ፡፡ አንድም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይኄልዩ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ወልድን ሥጋ እናልብስ ብለው አሰቡ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይትናገሩ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የነቢያት አድረው ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት ተናገሩ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ወልድን ሥጋ አለበሱ። አንድም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይኄልዩ፤ ድኅነተ ዓለምን አሰቡ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይትናገሩ፡፡ በነቢያት አድረው ተናገሩ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ፤ ያናገሩትን ድኅነተ ዓለምን ፈጸሙ። አንድም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይኄልዩ፤ ኅልፈተ ዓለምን አሰቡ! አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይትናገሩ፡፡ በነቢያት አድረው ተናገሩ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ ያናገሩትን ኅልፈተ ዓለምን ፈጸሙ:: 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለቅዱስ_አባ_ኦሪ_ቀሲስ_(ሰማዕት) እንዲኹም #ለአባ_ጲላጦስ_ሊቀ_ጳጳሳት ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳኑ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ይ ፡ ሕ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። ሕዝቡ አቤቱ ኋላ በጌትነትህ በመጣህ ጊዜ። አንድም በመንግሥተ ሰማያት አስበን። ተዘከረነ ኦ ሊቅነ በውስተ መንግሥትከ። አቤቱ አስታራቂያችን አስበን ይበሉ። ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። አቤቱ በጌትነትህ በመጣህ ጊዜ አስበን። ሐተታ ለአጠይቆተ አካላት ሦስት ጊዜ መላልሶ ተናገረ። በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ። በመልዕልተ መስቀል ተሰቅለህ ሳለህ ፈያታዊ ዘየማንን እንዳሰብከው አስበን። ሐተታ መስቀሉን ቅዱስ አለው አጋንንትን ድል ነሥቶበታልና። ታሪክ:- ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ሁለቱን ቀማኞች በቀኝ በግራ አድርገው ሰቅለውት ነበር። ስለምን ቢሉ በቀኝ የመጣው በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ ዐይቶ ይህ ምንድነው ሲል ወንበዴ ነው። ጌታን ይህሳ ሲል ይህስ ከእሱ ልዩ ነውን። በግራ የመጣው በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ ዐይቶ ይህ ምንድነው ሲል ወንበዴ ነው። ጌታን ይህሳ ሲል። ይህስ ከእሱ ልዩ ነውን ለማለት ለማሳሳት። አንድም አነገሥንህ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልህ ለማለት ለመዘበት። አንድም ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ያለው የነቢዩ ቃል እንደ ተፈጸመ ለማጠየቅ። አንድም በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥአንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለህ ሲያሰኛቸው ነው። በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ይባላል። በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ ፀሐይ ስትጨልም፥ ጨረቃ ደም ስትሆን፥ ከዋክብት ሲረግፉ አእባን ሲፈቱ፥ መቃብራት ሲከፈቱ፥ ሙታን ሲነሡ፥ መንጦላዕተ ምኵራብ ከሁለት ከሦስት ሲቀደድ፥ ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ አይቶ ይልቁንም ፀሐይን አይቶ አምላክነቱን ተረድቶ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ በዳግም ምጽአትከ እያለ ሲጸልይ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ቢሰማው 'ለራሱ አያውቅ ነዳይ ቅቤ ለመነ ለዋይ' እንዲሉ ለራሱ ከእኛ ጋራ ተሰቅሎ ይጨነቃል እኛን ያድነናል ብለህ ትለምናለህን አለው የማናይም እኛስ መሰቀላችን ነፍስ ገድለን ኃጢአት ሠርተን በፍዳችን ነው። ለነሰ ዘበርቱዕ ረከበነ ወበከመ ምግባሪነ ተፈደይነ እንዲል ። እሱ ግን ኃጢአት የሌለበት የባሕርይ አምላክ ንጹሐ ባሕርይ ሲሆን ለቤዛ ዓለም ብሎ ቢሰቀል ፈጣሪህን አትፈራውምን አለው ኢትፈርሆኑ ለእግዚአብሔር አምላክከ እንዲል በዚህ ጊዜ በጌትነቱ እንዳለ በመንበረ ጸባኦት ሆኖ ታየው። እሱም ዐይቶ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ ቢለው ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት ብሎ ጥጦስ ወደ ምድረ ግብፅ ስንወርድ የነገርኩህ ሁሉ ተፈጸመ ከሞት በቀር የቀረ የለም አሁንም ሂድ ገነት ግባ ብሎ ደመ ማኅተሙን ሰጥቶ ሰደደው። የገነት ጠባቂዋ መልአክ ደመ ማኅተሙን ዐይቶ ፈርቶ እየሸሸ አንተ ማነህ የት ትሄዳለህ ቢለው ወንድሜ አልሰማህምን አምላክ እንጂ ሞቶ በሞቱ ዓለምን አዳነ ለእኔም ማኅተመ ደሙን ሰጥቶ ሰደደኝ አለው መልአኩም አንተሳ ማነህ አዳምን ነህ አብርሃምን ነህ ይስሐቅን ነህ ያዕቆብን ነህ እያለ ደጋግ ደጋጎቹን ሁሉ እየጠራ ቢጠይቀው ሁሉንም አይደለሁም እጄን በሰው ደም ነክሬ የምኖር ወንበዴ ነኝ አለው እንዲህ ያለ ወንበዴ ስትሆን ለእንደዚህ ያለ ጸጋ ክብር ያበቃህ ምንድነው ቢለው ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ ዐይቼ አምላክነቱን ተረድቼ አምኜ ብለምነው ለእንዲህ ያለ ጸጋ ክብር አበቃኝ አለው። አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን ተዘግታ ትኖር የነበረች ገነትን በጌታ ደመ ማኅተም ከፍቶ አንተ ትቀድሞ ለአዳም በዊአ ውስተ ገነት ብሎት ነበርና ከአዳም አስቀድሞ እሱ ገባ። ከዚህ በኋላ አዳም ከነልጆቹ ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘአውረሰነ መንግሥቶ ሰማያዊተ እያሉ ገብተዋልና እንዲህ አለ። 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ለሚስቱ #ለቅድስት_ሰሎሜ እንዲሁም ለሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም_አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር_አስዮና_ስሙና_እና_መርካሎት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህች ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_አሞን ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ኮነ ሰብአ ወኵሉ ሕገ ሰብአ ፈጸመ እንበለ ኃጢአት ባሕቲታ። ሰው ሆነ። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር የሰውን ሥራ ሁሉ ፈጸመ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ። ሐተታ ይህስ ወዳጆቹ ጻድቃንስ እንኳ አበዊነሰ መልዕልተ ሕግ እሙንቱ ይላቸዋል ብሎ ሠራዔ ሕግ ተባለ። እስመ ሐጋጌ ብሉይ ወሐዲስ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲል። አንድም በየጥቂቱ አደገ። ወተምሕረ ሕገ ዕብራውያን ፊደለ ዕብራውያንን ተማረ። ታሪክ እመቤታችን ወስዳ ከተማሪ ቤት ከመምህር ዘንድ ሰጠችው አሌፍ በል አለው። አሌፍ አለ ቤት በል አለው ምንት ውእቱ ትርጓሜሁ ለአሌፍ፤ አሌፍ ማለት ምን ማለት ነው ትርጓሜውን ሳትነግረኝ አለው። ሕፃን የነገሩትን ይቀበላል እንጂ ያልነገሩትን ይጠይቃል ብሎ በዚህ አምላክነቱን ተረድቶ እኔ ይህን ማስተማር አይሆንልኝም ብሎ መልሶታል። ዳግመኛ ወስዳ ለሌላ መምህር ሰጠችው፤ ይህም ጸሐፊ ነው ለተግባሩ ከቤት ገብቶ ሳለ ቀዩን ቀለም ከጥቁሩ ቀለም ቀላቀለበት፤ ተበሳጭቶ ዝንቱ ወልደ መበለት አማሰነ ቀለምየ ብሎ ፊቱን ጸፋው። ለይልኝ ትለኛለህ እንጂ ለምን ትመታኛለህ አለው ከቀደመው የአሁኑ ይባስ ብሎ ገሠጸው። ከዚህ በኋላ ቀዩን ለብቻ ጥቁሩን ለይቶ ሰጥቶታል በዚህም አምላክነቱን ተረድቷል። አንድም፡ ምንጣፍ መሥራት፥ ቀለም ማግባት፥ ስፌት መስፋት ተማረ፤ አንዲት ሴት መጥታ ቀለም አግባልኝ አለችው፤ አግብቶ ሰጣት ተመልሳ መጥታ ዋጋ የማያወጣልኝ ሆነ አለችው እንደቀደመው አድርጎ ሰጥቷታል። በዚህ ሁሉ አምላክነቱን አውቀው ተረድተዋል። አንድም ሕገ ኦሪትን ተማረ። እም ኀበ ዮሐንስ ተጠምቀ። ይቆየን..... 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለሐዋርያት_አለቃ_ለቅዱስ_ጴጥሮስ የሕያው እግዚብሔር ልጅ ብሎ ለመሰከረበትና ሥልጣነ ክህነት (የመንግሥተ ሰማያትን ምክፈቻ ቊልፍ) ለተቀበለበት በዓልና እግዚአብሔር ለሚወድ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለቅዱስ_ናዖድ_ለዕረፍት በዓል (8ሺህ ዘመን አታሳየኝ ብለው ሲጸልዩ 8ሺህ ሳይገባ 1500 ዓ.ም ያረፉት)፣ ለራሔል ልጅ #ለቅዱስ_ዮሴፍ ልደትና ለእስክድርያ ሃያ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጢሞቴዎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ይ.ዲ. ውስተ ጽባሕ ነጽሩ ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ ይበል። ሐተታ ምሥራቅ ማኅደረ እግዚአብሔር ምዕራብ ማኅደረ ዲያብሎስ መሆኑን መናገር ነው። አንድም በምሥራቃዊ ሕገ ወንጌል እመኑ። አንድም ምሥራቃውያን ሰብአ ሰገል ባመኑበት በወንጌል እመኑ። አንድም የጌታን ነገረ ምጽአቱን አስቡ። ወውእተ አሚረ ይቀውማ እገሪሁ ለእግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት እንተ መንገለ ጽባሒሃ ለኢየሩሳሌም እንዲል አንድም ውስተ ጽባሕ ነጽሩ ወደ እመቤታችን ተመልከቱ። ምሥራቅ ዕፁት ይላታልና። አንድም ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልከቱ። ይኸውም በከንቱ አይደለም ምሥጢር ያለበት ነው። ገጠር የሆነ እንደሆነ የሰጎን ዕንቍላል ከተማ የሆነ እንደሆነ የወርቅ የብር የዕንቍ ያደርጉበታል። ሐተታ ከሰጎን አብነት ነሥቶ ተናገረ። ይህቺ ሰጎን ዕንቍላሏን ቀፍቅፋ እስክታወጣ ድረስ ስትመለከት ትኖራለች። ምግቧን በምትፈልግበት ጊዜ ቅሉ ተባዕቱን ተክታ ነው። አንድ ጊዜስ እንኳ ጥላው ዘወር ያለች እንደሆነ ይለውጥባታል። ደርቆ አይፈለፈልላትም። ፵ ቀን ሲሆናት ድምፅ ታሰማቸዋለች እነሱም በውስጥ ሁነው ድምፅ ያሰሟታል ፈልፍላ ታወጣቸዋለች። ሰጎን የመንፈስ ቅዱስ ጫጩቱ የምእመናን ቅርፊቱ የፍዳ የመርገም ድምፅ ሲያሰሟት ቀፍቅፋ እንድታወጣቸው እኛም አቡነ ብለን በጸራነው ጊዜ ከግብረ ዓለም ይለየናልና። አንድም ሰጎን የምእመናን ዕንቍላሉ የተዘክሮተ እግዚአብሔር። ይህች ሰጎን ዕንቍላሏን ቀፍቅፋ እስክታወጣው ድረስ ዕንቁላሏን ስትመለከት ትኖራለች። ምእመናንም መድኃኒታቸው ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ እስኪመጣላቸው ድረስ መስቀሉን እያዩ ሕማሙን ሞቱን ሲዘከሩ እርሱን ሲያስቡ ይኖራሉና የዚያ ምሳሌ። ምእመናን ወደ ቤተ ክር ስቲያን ሲገቡ ይህ ምንድነው ብለው በጠየቁ ጊዜ መምህራን ይኸን ተርጕመው ሊነግሯቸው ይገባል። ከ፵ ቀን አስቀድሞ አንስሐስሖ ሳያደርጉ ፈልፍላ አታወጣቸውም እኛም መንፈሳዊ አንስሐስሖ ሳናደርግ አያድርብንም ጠንቅቀን ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ናርምም ዝም እንበል። ይቆየን.... 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ጌታችን_ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ላወጣላት #ከ36_ቅዱሳት_አንስት አንዷ ለሆነችው ለእናታች #ለቅድስት_መግደላዊት_ማርያም_ለዕረፍት በዐል መታሰቢያና #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር ለሆነች ለከበረች #ለቅድስት_ኢየሉጣ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ዕለት ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሲኖዳ_ረድእ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዊፃ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • ወጽአ እምኔኪ ፍሬ ሕይወት፡፡ ወደ ምሥጢር ሄዶ ፍሬ ሕይወት አለ ፍሬ ሕይወት ጌታ ካንች ተወለደ፡፡ አንቲ ውእቱ መዝገብ ዘተሣየጠ ዮሴፍ ወረከበ በውስቴታ ባሕርየ ዕንቈ ክቡረ ዮሴፍ እየጠፋ የከበረብሽ ድልብ አንቺ ነሽ፡፡ አንድም ገበያ ወጥቶ እንደ ተቆለፈች ሣጥን ከነመክፈቻዋ ገዝቶ ወስዶ ቢከፍታት ዕንቁን አግኝቶባታል ሣጥን የመቤታችን መቈለፊያው የማኅተመ ድንግልናዋ ዕንቊ የጌታ ምሳሌ ወልድ ይትሜሰል በዕንቈ ባሕርይ ሥጋሓ በሥጋሁ ወብርሃና በመለኮቱ እንዲል፡፡ አንድም አረጋዊ ዮሴፍ በትሩፋተ ደሙ የዋጀሽ ዕንቊ ጌታን ያገኘብሽ ሣጥን አንች ነሽ። ዘውዕቱ መድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ይኸውም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ተፀውረ በከርሥኪ ወወለድኪዮ ውሰተ ዓለም፡፡ ዘተፀውረ ወዘወለድኪዮ እስመ ተፀውረ ወእስመ መለድኪዮ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ በዕንቊ ከተመሰለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጒት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ አዕምሮውን ለብዎውን በልቦናችን ሳይብን አሳድሪብን። ተፈስሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ሐሴቶሙ ለመላእክት። ይቆየን...

  • አንቲ ውእቱ ገራህት ዘኢተዘርዓ ውስቴታ ዘርዕ፡፡ ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት ያልጋረባት ለታብቊል (ታብቅል) ባለው ቃል ከልምላሜ ከጽጌ ከፍሬ የተገኘች ገራህተ ሠሉስ አንች ነሽ፡፡ አንድም ገራህተ ሙሴ አንች ነሽ ሙሴ ከባለሟልነቱ የተነሳ ባይህ እወዳለሁ አለው አልቦ ዘይሬኢ ገጽየ ወየሐዩ አሐተ ሰዓተ እምዘሕይወቱ በዲበ ምድር። የኔን ፊት ዐይቶ አንድ ሰዓት መቆም መቆየት የሚቻለው የለም አለው ካላየሁማ ለምን ባለሟልህ ተባልሁ አለው ገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድኅሬየሰ ሬኢ ብሎታል፡፡ ዘር ካልወደቀባት ምድር የበቀለ ስንዴ አምጥተህ ብትሠዋልኝ እታይሃለሁ አለው። ለጊዜው ሙሴ ማለት የዋሕ ማለት ነውና በራዕይ ሲባክን አድሯል፤ ፍጻሜው ግን በዘር ከተወለደች ከድንግል እንበለ ዘር ተወልጄ ኋላ በደብረ ታቦር መሥዋዕት ሁኜ በምቀርብበት ጊዜ እታይሃለሁ ሲል ነው፡፡ መምሕር ኤስድሮስ ግን የብርት መደብ አሠርቶ ውሀ እያጠጣ አሸክሞ አርባ ዘመን ዙሯል ብለዋል። አንድም ገራህተ አብርሃም አንቺ ነሽ እግዝዕትየ ገራህቱ ለአብርሃም እንዲላት፡፡ ያች በታች ይቀበሩባታል በላይ ቤት ይሠሩባታል ዘርዕ ይዘሩባታል፡፡ አንድም በአተ ካዕበት ይላታል እልፍኝ ካዳራሽ ናት የሰነበተውን አስክሬን ወደውስጥ ገፍተው ትኩሱን አስክሬን የሚያኖሩባት ናት፡፡ እመቤታችንም እናትነት ከድንግልና አስተባብራ ይዛ ተገኝታለችና፡፡

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ። አበው ቀደምት ያለውን ይተረትራል። አመ ተሰደ ሲል ነው። አመ ይትበሃሎ ለሰይጣን አመ ይወፅኡ እስራኤል እምግብጽ እንዲል። አዳም ከገነት በወጣ ጊዜ ተስፋው አንቺ ነሽ ታሪክ ይህስ እንደምን ነው ቢሉ ጌታ አዳምን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከአምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ በገነት አኖረው ሰባቱን ዓመት በሕግ ጸንቶ አትብላ ያለውን ዕፀ በለስ ሳይበላ ጠብቆ ኖረ  ከዚያ በኋላ አትብላ ያለውን ዕፀ በለስን በላ ሕጉንም አፈረሰ። እንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ መኖር አይገባህም ብሎ ከገነት አስወጥቶ በገነት አንጻር በደብር ቅዱስ አኖረው ስለምን ቢሉ ኀዘን እንዲጸናበት። ወደ ቀደመ ቦታዬ!ይመልሰኝ ይሆን እያለ ተስፋ እንዳይቆርጽ ከዕለታት ባንዳቸው እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ ባንች ምክንያት አጣሁ ብሎ ፊት ነሣት ሴቶች ድንጉፆች ናቸውና ሸሽታ ሂዳለች መልአኩ መጥቶ አትታረቃትምን አለው እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ ያጣሁት በእሷ ምክንያት አይደለም አይሆንም አለው በእሷ ብታጣ መታረቂያህም እሷ ናትና ታረቃት አለው። ኢትከውነኒ ናዛዚተ እሷስ መታረቂያም አትሆነኝ አለው። ከዚህ በኋላ መላእክት ጊዜያት አስተምረውት ነበርና ሲጸልይ መልአክ መጥቶ አዳም ምን ይሆንሃል የመስተቀይምን ጸሎት እግዚአብሔር አይቀበለው አለው አንተ ሂደህ አምጣልኛ አለው። እንዳበረርሃት አንተ ሂደህ አምጣት እንጂ እኔ ምን ባይ ነኝ አለው። ከዚህ በኋላ ሂዶ አምጥቷታል። እሷም ከጫማው ወድቃ ማረኝ ብላለች። ከዚህ በኋላ አትለያት ብሎታል ይህ ዛሬ ለሴቶች አብነት ሁኗቸው ምንም ተርታ ሴት ብትሆን ወንድ ይማልዳታል እንጂ ሴት አትማልድም። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንደተጣላን ይቀር ይሆን አለችው። እሱስ መሓሪ ነው ዳሩ ግን አንች አለሽና ምን ይሆናላ አላት ከእንግዲህስ ወዲህ ካንተ ፈቃድ አልወጣም አለችው ከዚያ በኋላ ሄደው ከባሕር ገብተው ይጸልዩ ጀመር። ብለህ ዓለም የሚድን በሩቅ ብእሲ መሥዋዕትነት አይደለም እንደ ቅዳሴ ሐዋርያት ተርክ ። ትርፍ እኔ ከሰማየ ሰማያት ወርጄ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ሲል። በኀሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ብሎ ተስፋውን ነግሮታልና የአዳም ተስፋው አንች ነሽ አለ አዳም ማለት ሥግው እመሬት  ዘተሰግወ እምድር ይህ ቀረህ የማይባል ፍጹም መልከ መልካም ፍጥረት ማለት ነው። የዋህቱ ለአቤል ዘተቀትለ በዓመጻ። ይቆየን..... 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለቅዱስ_አባ_አብርሐም_ገዳማዊ፣ #ለቅድስት_ማርያ_እህቱ፣ #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰቡ፡ ከከበሩ #ከአባ_ፊልጶስ_ዘደብረ_ቢዘን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • ✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨ ልጅነት ናፈቀኝ ‎ልጅ መሆን ናፈቀኝ ከደጅሽ እንዳልርቅ፥ ‎እንዳሻኝ እንድሆን በፊትሽ ልቦርቅ፤ ‎ነጠላ አጣጥዬ መሬት እየጠረግሁ፥ ‎ሮጬ ሮጬ ከመቅደሱ ፊት ገጽ ደርሼ እንደቆምሁ፤‎አሐዱ አብ ቅዱስ ሲባል በፍርሃት፥‎የእግዚአብሔርን መውረድ በውስጤ እያሰብኩት፤ ‎በፍጹም ፍርሃት በፍጹምም ፍቅር በፊትሽ የቆምኩበት፥ ‎ልጅነት ናፈቀኝ ድጋሚ ቢመጣ በሚል ተመኘሁት፤ ‎ቁርባኔን ቆርቤ እመቅደሱ መሃል ጢቢኛ ስበላ፥ ‎በፍቅርሽ ታሥሬ ሕግጋትን ስጥስ ከልጆች ስጣላ፤ ‎ልጅ መሆን ናፈቀኝ ከደጅሽ እንድቆም እንድትባርኪኝ፥ ‎ፍልሰታ ደረሰች ብዬ እንድደሰት እንደምትናፍቂኝ፤ ‎ወጣትነት አሥሮኝ ከደጅሽ ባልቆምም፥ ‎በጉልምስናዬ ለቅዳሴ ሮጬ አሐዱን ባልቀድምም፥ ‎እንደልጅነቴ ጓደኛዬ ሲቆርብ ቀኝቼ ባልቆርብም፤ ‎ጢቢኛ በኪሴ ይዤ ባልገኝም ባልደባደብም፤ ‎ካለሁበት ሆኜ ትናፍቂኛለሽ ስዕሉ ይታየኛል፥ ‎ፍልሰታ ደረሰች በል ሩጥ እያለ ደርሶ ይገፋኛል፥ ‎ከመቅደሱ ግባ ከቅዳሴው ቅመስ በል ፍጠን ይለኛል፤ ‎ሰላም ለኪ እያልክ ሰዓታቱን አድርስ ትርጓሜ አድምጥ፥ ‎ቁጭ በል ከመቅደስ ውዳሴዋን ጸልይ ከሥዕሏ ተሻሽ፥ ‎ሽምብራ ተቀበል ፍትፍቱን አጣጥም ከሰንበቴ አዳራሽ፤ ‎ከዳቤው አትለፍ ቅዳሴ ጸበሉን ለምዕመናን አዳርስ፥ ‎መጠለያ ግባ ከዝናቡ አምልጥ ደግሞ እንዳትበሰብስ፤ ‎ሱባዔውን ግባ ከቅጽሯ አንድ ጥግ ቦታ አመቻችና፥ ‎ፍልሰታ ደረሰች እንደልጅነትህ በል ሁን እንደገና፤ ‎ለሥጋዬ ስሮጥ ነፍሴ ተሰቃየች ማረፊያ እንዳጣ ወፍ፥ ‎ፍልሰታ ደርሳለች ድንግል ፍቀጂልኝ ከእቅፍሽ ልረፍ፤ ‎ከቅዳሴሽ ልገኝ ከቁርባኑ ልቅረብ ሰዓታቱን ላድርስ፥ ‎የተዘናጋውን የተዳቀቀውን እኔነቴን ላድስ፥ ‎ፍልሰታ ደረሰች እንደልጅነቴ ውዳሴሽን ላድርስ፥ ‎ከሕግ በላይ ልሁን ከእቅፍሽ ገብቼ ነጻነቴን ላድስ፥አርአያ ሥላሴ የሆንኩኝ ልጅሽ በፍቅርሽ ልታደስ። 📝ማርቆስ በላይ ✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ከዳዊት_ዘር_ለሆነ ለአካዝ ልጅ ንስሐ በመግባቱ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት ለተጨመረለት #ለንጉሥ_ቅዱስ_ሕዝቅያስና እንደ በግ የጸጉር ልብስ ለብሶ በበረሃ ለሚኖር ሰማዕቱ #ቅዱስ_መርምኅናምን ላሳመነና እህቱን ሣራንም ከለምፅዋ ላነፃት ለአባታችን #አባ_ማቴዎስ_ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ዳዊትና_ወንድሞቹ እና ከግብፅ ደቡብ ስንካር ከሚባል አገር በሰማዕትነት ከዐረፈ #ከቅዱስ_ፊልጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ። መጽሐፍ ምሥጢርን ከምሥጢር አያይዞ መናገር ልማዱ ነው። አባቷ ዳዊት ለንጉሠ ሰማይ ወምድር ለእግዚአብሔር ምሥጋና ላቅርብ ባለ ጊዜ ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ብሎ እንደተናገረ ከዚህም አባ ሕርያቆስም ለንግሥተ ሰማይ ወምድር ለእመቤታችን ምሥጋና ላቅርብ ባለ ጊዜ ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ብሎ ተናገረ ወአነ አየድዕ ማንሻ፡፡ አንድም በዳዊት አድሮ የተናገረ መንፈስ ቅዱስ በአባ ሕርያቆስም አድሮ ተናገረ፡፡ ልሕኵት ልቦናዬ በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ፈላ፤ ፈላና በጎ በጎ ነገርን አውጥቶ ተናገረ፡፡ ወትጕሥዖሙ ይእቲ ባሕር ለነጋድያን እንዲል ወአነ አየድዕ ማንሻ፡፡ አንድም ልሕኵት ልቦናዬ ስንቡል መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በጎ በጎ ነገርን ገሣ፡፡ በሀገራቸው የበሉት የጠጡት ያልተስማማቸው እንደሆነ ዑድ ሰንደል የሚባል ሽቱ አለ ያን ተመግበው በጎ በጎ ነገር ገሣሁ እንዲሉ፡፡ ሦስት ጐሥዐ ተናገረ ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም፣ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ ለድንግል፣ ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ለድንግል ብሎ የሚያመጣው ነውና ለዚያ አርእስት ነው፡፡ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ሦስት ጊዜ መላልሶ መናገሩ የሦስትነት ቃሉ አንድ ዐይነት መሆኑ (ያለመለወጡ) የአንድነታቸው ምሳሌ:: አንድም እመቤታችን በዚህ ዓለም፣ በገነት፣ በመንግሥተ ሰማያት ትመሰገናለችና፡፡ አንድም በመንግሥተ ሰማያት ያሉ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ስለሆነ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያት የገባ የለም ብሎ ኋላ መንግሥተ ሰማያት የሚገቡ ጻድቃ የሚያመሰግኗት ስለሆነ፤ አንድም በነገደ ሴም፣ በነገደ ካም፣ በነገደ ያፌት ትመሰገናለችና፡፡ አንድም በወጣንያን፣ በማዕከላውያን፣ በፍጹማን አንደበት ትመሰገናለችና፡፡ አንድም በመላእክት፣ በደቂቀ አዳም፣ በካልዕ ፍጥረት ትመሰገናለችና፡፡ አንድም የንጽሐ ሥጋ፣ የንጽሐ ነፍስ፣ የንጽሐ ልቦናዋ ምሳሌ ነው፡፡ እሱስ የተናገረው አንድ ጐሥዐ ነው ቅዱስ ያሬድ ለዜማ ማቅኛ ሦስት አድርጎ ተናግሮታል እንጂ፡፡ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ ለድንግል። እኔስ የድንግልን ምሥጋና እናገራለሁ:: ሁለት ጐሥዐ ተናግሮ ነበርና ለዚያ አርእስት ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ድንግል አኮ ወራዙት ስፉጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወጹኪ መተብህለ ካህናት ወሊቀ ካህናት ብሎ የሚያመጣው ነውና ለዚያ አርእስት ነው᎓᎓ አኮ በአንኆ በቃለ ዝንጋዔ። ይቆየን.... 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #በገድል_ለተጠመዱ ስልሳ ክንድ የድንጋይ ምሰሶ ላይ ወጥተው በዚያም ሳይቀመጡ ቆመው እያስተማሩና እየጸለዩ #ለ42_ዓመታት ለተጋደሉ ለታላቁ አባት #ለአባ_ስምዖን_ዘዓምድ_ሶርያዊ ለዕረፍት በዐልና ከመንግሥት ወገን ለሆነች #ለቅድስት_ሶፍያ_ዘሮምና_ለሦስት_ሴት_ደናግል ልጆቿ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳኑ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

  • 8 авг.6852416

    🌿🌿🌿🍁🌿🍁✨✨✨ ድሮኮ ፍልሰታን አልወዳትም ነበር!!! ክረምት ክረምት ጓደኛዬ አቤል ፍስለታ ሲል እሰማዋለሁ።ምን እንደሆን ግን አላቅም።ህፃን እያለን የቦይ ውሀ ስንገድብ፤ካፊያ ውስጥ ቢራቢሮ ስናባርር፤አኩኩሉ ስንጫወት ቆይተን ልክ 5ሰአት ሲል ተነስቶ ፍስለታ ሄዳለሁ ይለኛል። ድንገት እየመጣች አባሮሼን ምታበላሸው፤ እቃቃዬን ምትበትነው፤ብቻዬን ምታስውለኝ ፍስለታ ማናት?? እላለሁ።የሚነግረኝ የለም።ብቻ እነ አቤል ተሰብስበው ፍስለታ እያሉ ሲሄዱ፤ነጠላ ለብሰው ሄደው አፋቸውን ሸፍነው ሲመለሱ፤ከዛ በኋላ አንጫወትም ሲሉ ይከፋኛል።ብቻዬን የሆንኩ ያህል ይሰማኛል።አንድ ቀን ታድያ ቢመረኝ እናቴ ጋ ሂጄ እንባ እየቀረረኝ... ፍስለታ ሄዳለሁ...አልኳት ያው ከጓደኛዬ የሰማሁትን ነው። ዝጋ አናትህ ይፍለስ!!እንደውም ከዚ በኋላ እጫወታለሁ ብለህ ከቤት ትወጣና....!!!ክፉኛ ዛተችብኝ 🌿🍁✨✨ እናቴ ከሰፈሩ ለየት ያለች ናት።ሰወች በጥቁረቷ የሚጠሏት ይመስለኝ ነበር።"የጠንቋይዋ ልጅ"ሲሉኝ ፈገግ ብዬ እያየኋቸው "አቤ" እል ነበር።ስድብ መሆኑ መች ገብቶኝ.....ያን ቀን ግን እማዬን ተቀየምኳት። መሄዱን ብከለከል መኝታ ቤት ገብቼ የእልህ... ፍስለታ ፍስለታ ፍስለታ ፍስለታ....( እያልኩ እየለፈለፍኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ።በነጋታው ከነአቤል ጋ ለመጥፋት ወስኜ ነበር የወጣሁት።እማ የት ታቃለች??ብታቅስ አንድ ቀን ብገረፍ ነው...ዋናው ፍስለታ ልሂድ እንጂ(እያልኩ በጠዋት አቤልጋ ሄጄ "ፍስለታ ውሰደኝ" አልኩት።አቤል እንደሚወደኝ አውቃለሁ።ግን ደሞ ከቤት እንደማይፈቀድ ስለሚያቅ ... አይሆንም እናትህ ትቆጣለች..አለኝ እናቴን እንደምሸውዳት የቆጥ የባጡን ቀባጥሬ ተከትዬው ሄድኩ።በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ጠባብ ደረቴ ላይ ልቤ ስትነጥር ተሰማኝ።ጓደኞቼ ሁሉ ነጭ ነጠላ ለብሰው እኔ በቁምጣ እና በከነቴራ ጭቃ በከበባት ዚኮ ጫማ እየተከተልኩ ቤተክርስትያን ገባሁ።የሚያምር ሰፊ ጊቢ ብዙ ህፃናት ብዙ ትልልቆች ያሉበት ጊቢ ገባሁ።ጠረኑ ..ከአበበ ጉሬው ሱቅ በላይ ደስ ይላል፤ከናና ከከረሜላ ሽታ በላይ የሚያውድ ደስ የሚል ግቢ ውስጥ ገባው።አቤል መውጫ መግቢያውን ያውቃል ።ከፊት እየቀደመ ግቢ ውስጥ ወዳለ ቤት ሲገባ እኔ ስከተለው ግን ከኋላዬ ሌላ ድምፅ ሰማሁና ደርቄ ቀረሁ ና ተመለስ አንተ ውሪ!!! 🌿🍁✨✨ ድምፁ ጎረነነ እንጂ ትክክለኛ የእማዬ ስድብ ነው።በቆምኩበት ሽንቴን ልለቅ ስል ሌላ ሰው ድንገት ጀርባዬን እያቀፈኝ "አቡሽዬ ቆይ ና እሺ"ብሎ ብቻዬን ወሰደኝ።የማላቅበት ቦታ ላይ ብቻዬን መወሰዴን አልፈራሁም።ብቻ ፍስለታ መምጣቴ ደስ ብሎኝ ሰውየውን ተከተልኩት አቡሽዬ እንደዚ አይገባም እሺ አሁን እግርህን ልጠብህ... ሰውየው ጥቁረቱ ከእማዬ መለስ ያለ ነው።በዛላይ ሲስቅ ደስ ይላል።ትንንሽ እግሮቼን በመዳፉ እያሸ በዝናብ ውሀ ሲያጥበኝ ሳላቀው ሳቅ አልኩኝ።ትንሽ ቆይቶ ደሞ ከአቤል የበለጠ ረጅም ነጭ ነጠላ ሰጥቶኝ አቤል ወደገባበት ይዞኝ ሲገባ የማላቀው የደስታ የስሜት ባህር ውስጥ እቀዝፍ ያዝኩኝ..... የሆነ ደስ የሚል የሚያባብል ብሉኝ ብሉኝ የሚል ሽቱ ውስጥ የተዘፈቅኩ መሠለኝ።መሬቱ ንፁህ፤ግርግዳው ስእል፤ሁሉም ክፍሉ መብራት ነው።ከፊቴ አንዲት ምታምር ሴት ልጇን አቅፋ ክንፍ ባላቸው ነጫጭ ሰወች ተከባ ይታየኛል።ሳማት ሳማት ቢለኝም እነአቤል ስር ሂጄ ቁጭ አልኩ።የሆኑ ሽማግሌ ከወጣት ጋ እየተቀባበሉ በዜማ ሲያወሩም ትዝ ይለኛል።ብቻ ያን ቀን ቁርሴን ሳልበላ ሳይርበኝ ፍስለታዬን ሂጄ ምሳዬን በልቼ ተመለስኩ።ምን ያደርጋል....ስመለስ እማዬ ዱላዋን ይዛ በር ላይ ጠበቀቺኝ።አንዴ በአርጩሜ ሲላት በንክሻ እርርር እስክል ገረፈቺኝ።ከዛ ወዲህ ፍስለታ ምትባል ተውኩ።ማን ትሁን..ምን ትሁን ሳልጠይቅ እንደናፈቀቺኝ አመታት አለፈ። 🌿🍁✨✨ እናቴ ጠንቋይ እንደተባለች ስም እንደወጣላት ሰፈር እንደሸሻት 6ኛ ክፍል ስገባ ሞተች።እሷ ብቻ ስላለቺኝ አንድ አመት ትምህርት አቆምኩ።ብቸኛ ሆንኩ።እሷ ሞታ ደሞ ገና በሁለት ወሯ ክረምቱ ሲገባ ጭራሽ ጨነቀኝ።ዘመድ አልባነት ተጫጫነኝ።ያለው አንድ ጓደኛዬ አቤል ነው።ምሳ እያመጣ ያጎርሰኛል።ታድያ አንድ ቀን በሬ በስሱ ተንኳኳ።ያው የማውቀው አቤል ነው ብዬ ስከፍት ቀይ ረጅም ቄስ ከነጭራቸው ቆመው ጠበቁኝ 🌿🍁✨✨ አቤት አባ ሰላም ዋሉ እግዜሀር ይመስገን ልጄ ደናህን ሰነበትክ?? አዎ አልኳቸው።ውሸቴን እንደሆን ገምተዋል ሰፈራችን ሰው ሁሉ ሚወዳቸው ካህን ናቸው። በል ና ብቻ ብለው ሲሄዱ ሳልጠይቅ ተከተልኳቸው።በር ላይ አቤል ቆሟል።ሲያየኝ ፈገግ ሲል ሰላም መሆኑ ገባኝ።ከተማ ሄዴን ልብስ ጫማ ገዝተውልኝ ሲያበቁ አስከትለውኝ ወደ እንጦጦ ኪዳነምህረት አመሩ።ለምን እንደሆን ሳላውቅ በሩን እያየሁ እንባዬ እርግፍ እርግፍ ይል ጀመር።አቤል ከሚያወራው ነገር ውጪ ስለ ቤተክርስትያን ምንም አላቅም።ብቻ ህፃን ሆነን ሳለ ያቺ ልጅ አቅፋ የተቀመጠችው ቀይ ሴትዮ ማርያምን ማየት ፈለኩ።ድሮ ስሟን ሳላውቅ እንደዛ የወደድኳትን ማርያምን የከፋኝን ልነግራት "እናት ሁኚኝ"ልላት ፈለኩ።አባም የውስጤን ያወቁልኝ ያህል "በል እንካ "ብለው እንደልጅነቴ ነጠላ አቀበሉኝ።አቤልን ተከትዬ ወደ ቤተመቅደሱ ገባሁኝ።ያቺ የዋህ እናት ስር ገብቼ ስቅስቅቅቅቅ ብዬ አለቀስኩኝ።ከአመታት በፊት የነበረው ውበት ሙሉ ሆኖ ጠበቀኝ።አቤልም ጠጋ ብሎ በጆሮዬ አይዞህ ማርያም እናትህ ትሆንሀለች እሺ አለኝ (ፍስለታ) ብዬ የወደድኳት በፍልሰታ እናቴን እንደገና ተዋወቅኳት።የጠንቋይ ልጅ ከመባል የማርያም ልጅ ወደመባል ተሸጋገርኩ።ከጥቂት አመታት በኋላ ደሞ ስሜ ዲያቆን ስሙር ተባለ። 🌿🌿🌿🍁🌿🍁✨✨✨

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ኮነ ሰብአ ወኵሉ ሕገ ሰብአ ፈጸመ እንበለ ኃጢአት ባሕቲታ። ሰው ሆነ። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር የሰውን ሥራ ሁሉ ፈጸመ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ። ሐተታ ይህስ ወዳጆቹ ጻድቃንስ እንኳ አበዊነሰ መልዕልተ ሕግ እሙንቱ ይላቸዋል ብሎ ሠራዔ ሕግ ተባለ። እስመ ሐጋጌ ብሉይ ወሐዲስ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲል። አንድም በየጥቂቱ አደገ። ወተምሕረ ሕገ ዕብራውያን ፊደለ ዕብራውያንን ተማረ። ታሪክ እመቤታችን ወስዳ ከተማሪ ቤት ከመምህር ዘንድ ሰጠችው አሌፍ በል አለው። አሌፍ አለ ቤት በል አለው ምንት ውእቱ ትርጓሜሁ ለአሌፍ፤ አሌፍ ማለት ምን ማለት ነው ትርጓሜውን ሳትነግረኝ አለው። ሕፃን የነገሩትን ይቀበላል እንጂ ያልነገሩትን ይጠይቃል ብሎ በዚህ አምላክነቱን ተረድቶ እኔ ይህን ማስተማር አይሆንልኝም ብሎ መልሶታል። ዳግመኛ ወስዳ ለሌላ መምህር ሰጠችው፤ ይህም ጸሐፊ ነው ለተግባሩ ከቤት ገብቶ ሳለ ቀዩን ቀለም ከጥቁሩ ቀለም ቀላቀለበት፤ ተበሳጭቶ ዝንቱ ወልደ መበለት አማሰነ ቀለምየ ብሎ ፊቱን ጸፋው። ለይልኝ ትለኛለህ እንጂ ለምን ትመታኛለህ አለው ከቀደመው የአሁኑ ይባስ ብሎ ገሠጸው። ከዚህ በኋላ ቀዩን ለብቻ ጥቁሩን ለይቶ ሰጥቶታል በዚህም አምላክነቱን ተረድቷል። አንድም፡ ምንጣፍ መሥራት፥ ቀለም ማግባት፥ ስፌት መስፋት ተማረ፤ አንዲት ሴት መጥታ ቀለም አግባልኝ አለችው፤ አግብቶ ሰጣት ተመልሳ መጥታ ዋጋ የማያወጣልኝ ሆነ አለችው እንደቀደመው አድርጎ ሰጥቷታል። በዚህ ሁሉ አምላክነቱን አውቀው ተረድተዋል። አንድም ሕገ ኦሪትን ተማረ። እም ኀበ ዮሐንስ ተጠምቀ። ይቆየን..... 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

  • 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #በአባ_ዮሐንስ_ሐጺር ምክር ለንስሐ በቅታ ከዘማዊነት ለተመለሰች #ለቅድስት_አትናስያና ከነገሥታት ወገን ለሆነች #ለቅድስት_ኢዮጰራቅስያ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከዲያቆናዊት_ኢዮኤልያና ዕረፍት፣ #ከሰማዕቱ_ደሚናና ሰማዕታት ከሆኑ ወንድሞቹ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት — tgindex