ቅዱሳት መጻሕፍት
описание
በዚህ ቻናል 👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ:: 👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ:: 👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @Holy_scriptures
7 738
подписчиков
Охват к подписчикам
10,2%
ERR
Реакции к просмотрам
0,66%
364 на 39 постов
Пересылки к просмотрам
1,45%
800
Постов в день
2,0
всего 39
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 15 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።” መዝሙር 85፥8 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures6,08%
- 14 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥10 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures2,60%
- 14 авг.#አዲስ_ዓመት የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም ክፍል-3 የእግዚአብሔር ቃል ያነጻል የእግዚአብሔር ቃል የምንፀዳበትና የምንቀደስበት ብቸኛ የእግዚአብሔር መንገድ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ያደረገላትን ሲገልጥ ‹‹በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ›› (ኤፌ.5፡25) ይላል፡፡ በዮሐ.17፡17ም እንዲሁ…2,25%
- 10 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።” ኤርምያስ 29፥11 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures2,09%
- 11 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።” 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥24 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures1,86%
- 12 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።” ዘፍጥረት 49፥22 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures1,80%
- 13 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።” ዘፍጥረት 2፥15 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures1,78%
- 9 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ "እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።" መዝሙር 116፥1-2 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures1,69%
- 7 авг.. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።” ሉቃስ 1፥79 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures1,44%
- 13 авг.#አዲስ_ዓመት የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም ክፍል-2 የእግዚአብሔር ቃል መሪያችን ነው መዝሙረኛው በመዝ.119፡9 ‹‹ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው›› ይላል፡፡ ወረድ ብሎም በቊጥር 11 ላይ ‹‹አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ›› ሲል በቁ.105 ላይ ደግሞ ‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው›› ይላል፡፡ እግዚአብሔር…1,42%
- 11 авг.#አዲስ_ዓመት የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም ክፍል-1 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን በማዘውተር ታነቡ እንደሆነ ልጠይቃችሁ እወዳለሁ፡፡ ቤተሰብ በገበታ ሲሰበሰብ ወይም በተለምዶ እንደሚደረግ ማለቴ ሳይሆን ለራሳችሁ ብላችሁ ብቻችሁን ስትሆኑ ታነቡ እንደሆነ ልጠይቅ ፈልጌ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ማዘውተሩ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ አማኝ የእግዚአብሔርን ቃል የማያነብ ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ኅብረት አይኖረውም፤ ደስታውም የተሟላ አይሆንም፡፡ እንደዚህ ማለታችንም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅም ማጋነን አይሆንም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነና እግዚአብሔርንና ሐሳቡንም ማወቅ የምንችለው ደግሞ በቃሉ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር በቃሉ ራሱን ገለጠ፤ ቃሉንም እንዲጻፍ አደረገው፡፡ በዚህ ቃሉም ማንነቱን ገለጠ፡፡ ያደረገውን፣ ሊያደርገው ያለውንና ሰው እንዴት ሊያገለግለው እንደሚገባም በቃሉ ተናገረ፡፡ ከዚያም ወልድ ወደ ምድር መጣና እግዚአብሔርን ተረከው (ዮሐ.1፡18) እንደዚሁም ስለወልድ ሕይወት ማለትም ስለ ልደቱ፣ ኑሮውና ሞቱ ስለ ተናገረውና ስለ ሥራውም ማወቅ የምንችለው በቃሉ ብቻ ነው፡፡ አሁን በምድር ላይ በአማንያን የሚያድር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በቃሉ በኩል ሁሉን ነገር ይገልጽልናል፡፡ ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስን የማይወድ አማኝ ካለ አሳዛኝ ነው፡፡ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት ማደግም ለቃሉ ካለን ፍቅርና ከቃሉ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አዲሱ ልደት- በእግዚአብሔር ቃል ለምሳሌ መዝ.119ን ስንመለከት የዘማሪው እያንዳንዱ መንፈሳዊ ደረጃ ከቃሉ ጋር የተያያዘ ሆኖ እናገኛለን፡፡ በዚሁ መዝሙር ቁ.93ን ስናይ ‹‹በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘላለም አልረሳም›› በማለት አዲሱ ሕይወት ከቃሉ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡ እንደዚሁም በሌሎች ቁጥሮች ማለትም ቁጥር 25፣ 37፣ 41፣ 50፣ 88፣ 107፣ 116፣ 144፣ 149፣ 154፣ 156፣ 159 እና 175ን መመልከት ይቻላል፡፡ ይህ ሐሳብ በሌሎች በርካታ ምንባቦችም በግልጥ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ‹‹ለፍጥረቱ የበኩራት ዓይነት እንሆን ዘንድ በእውነት ቃል አስቦ ወለደን›› (ያዕ.1፡18) የሚል እናያለን፡፡ በሌላ ስፍራም ‹‹ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ›› (1ጴጥ.1፡23) ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የኃጢአተኛን ሰው ኅሊና ወደ እግዚአብሔር ብርሃን እንዲመጣ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ሰው ማን መሆኑን አይቶ ራሱን ያወግዛል፤ ወደ እግዚአብሔርም ይናዘዛል፤ ይህም መለወጥ ማለት ነው፡፡ ራስን መመርመርና በራስ መፍረድም የሰውን ልብ ያነፃል፤ መንፈስ ቅዱስም በቃሉ በኩል አዲስ ሕይወትን በሰውዬው ውስጥ ይሠራል፡፡ ስለዚህ ለማያምኑት ሰዎች ወንጌልን ስንነግር የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ አለብን፡፡ የራሳችን ቃል ሰውን ወደ እምነት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ሰውን መለወጥ የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡ ‹‹እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡›› (ሮሜ.10፡17)፡፡ የአዲሱ ሕይወት ምግብ በተጨማሪም መዝሙረኛው ስለ እግዚአብሔር ቃል ሲናገር ‹‹ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ፤››(መዝ.119፡103) ‹‹ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል››(መዝ.19፡10) በማለት የቃሉን ጣፋጭነትና ምግብነት በማድነቅ ተናግሯል፡፡ ይህም ጣፋጭ ምግብ ደግሞ ለአዲስ ሕይወት ምግብ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ሰው ‹‹ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም›› በማለት ቃሉ በሕይወት የምንኖርበት ምግብ እንደሆነ ተናግሯል (ማቴ.4፡4፣ ዕብ.5፡12-14፣ 1ጴጥ1፡25-2፡2)፡፡ በቃሉ የተገኘው አዲሱ ሕይወታችን የሚስማማውን ምግብ ማግኘት አለበት፡፡ ይህም ምግብ አዳኛችንና የሞተልን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤(ዮሐ.6፡56) እርሱ በምድር ቅዱስ ሰው ሆኖ የተመላለሰና በሰማይ ደግሞ የከበረ ጌታ ሆኖ የተቀመጠ የአማኞች ምግብ ነው፡፡ እርሱ የምድረ በዳውን መና የተካ፣ የከነዓን የምድር ፍሬ፣ እንደዚሁም ለአማኞች የዘወትር መብል የሆነ ከሰማይ የወረደ አማናዊ መና ነው (ኢያ.5፡11-13) ይህንንም ምግብ የምናገኘው በቃሉ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ጌታ በብሉይ ኪዳን በጥላዎችና በምሳሌዎች እየሆነ በትንቢቶች እና በነቢያት ይታያል፡፡ በአዲስ ኪዳን ደግሞ በሕይወቱ በሞቱና በክብሩ ከወንጌላት እስከ ራእይ በተጻፈው ይታያል፡፡ ታዲያ ብዙዎች መንፈሳዊ ሕይወታቸው ደክሞ አቅመቢስ ሆነው ጠንካራ ምግብ መውሰድ ተስኖአቸው ወተት ብቻ የሚያስፈልጋቸው (ዕብ.5፡12-14) ወደ ጉባኤ ስለማይመጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስለማይከታተሉ ራሳቸውም ቃሉን ስለማያነቡ አይደለምን? ልናድግና ጤናማ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት ሊኖረን የሚችለው ዕለት ዕለት ያለማቋረጥ ቃሉን ስንመገብ ብቻ ነው፡፡ ይቀጥላል... ምንጭ፦ gbv-online.org ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures1,36%
- 14 авг.без подписи1,26%