tgindex

ቅዱሳት መጻሕፍት

описание

በዚህ ቻናል 👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ:: 👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ:: 👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @Holy_scriptures

7 748
подписчиков

Лучшие посты

за три месяца
  • 7 авг.1 339 просмотров4 реакций2 пересылок

    без подписи

  • 8 авг.1 295 просмотров9 реакций18 пересылок

    የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት እግዚአብሔር የሰጠን አገልግሎት ምን እንደሆነ ለይቶ ማወቅ በረከት ነው። ጊዜያችንን በሚገባ ለመጠቀምና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠንቅቆ ለመፈጸም እጅግ አስፈላጊ ነው። የተሰጠንን አገልግሎት ለይቶ አለማወቅ ከመቅበዝበዝ ባሻገር ሌሎችንም ከመጥቀም ይልቅ ስናውክ እንድንሰነብት ያደርገናል። እስቲ ለዮሐንስ ከሰማይ ተሰፍሮ የተሰጠውን አገልግሎት እንመልከት በዚያውም የራሳችንን እንፈትሽ። 1. የልዑል ነቢይ መሆን “ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥” ሉቃስ 1፥76 ይህ የዮሐንስ ዋና አገልግሎት ነበር። እርሱም የእግዚአብሔር ነቢይ መሆን የእግዚአብሔርን መልእክት ለእስራኤል ይናገር ነበር። እርሱ የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነቢይ እና በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን መካከል ያለው ድልድይ ነበር (ሚል. 3፥1፤ ኢሳ. 40፥3፤ ማቴ. 11፥9-10)። 2. በጌታ ፊት መሄድ “. . . በጌታ ፊት ትሄዳለህና፤” ሉቃስ 1፥76 የዮሐንስ ተልእኮ ሰዎችን ወደ ራሱ መጠቆም ሳይሆን ለመሲሑ ለኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ማዘጋጀት ነበር። በጌታ ፊት በመሄዱም ዋና አገልግሎቱ ይህ ነበር። 3. የጌታን መንገድ መጥረግ ወይም ማዘጋጀት “. . . መንገዱን ልትጠርግ . . . ” (ሉቃስ 1፥76) ዮሐንስ ሰዎች ክርስቶስን እንዲቀበሉ መንፈሳዊ እንቅፋቶችን ያስወግድ ነበር (ሉቃስ 3፥3–6)። ዮሐንስ ሰዎችን በመንፈሳዊ መንገድ ያዘጋጀው፦ 👉ንስሐን በመስበክ። 👉እስራኤልን ወደ እግዚአብሔር በመጥራት። 👉ንስሐ የገቡትን በማጥመቅ። 4. የመዳንን እውቀት መስጠት “. . . የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤” (ሉቃስ 1፥77) ዮሐንስ ለሰዎች መዳን እንዴት እንደሚመጣ አስተምሯል። በዘር ሐረግ ወይም ሕጉን ብቻ በመጠበቅ ሳይሆን በእግዚአብሔር ተስፋ በተሰጠው መሲሕ በኩል ሰዎችን ወደ ኢየሱስ መርቷል። 5. የኃጢአትን ይቅርታን ማወጅ “እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤” ሉቃስ 1፥77 ዮሐንስ ሰብኳል። ምን በማለት? "ንስሐ ግቡ!" 6. ስለሚመጣው ብርሃን መመስከር ሉቃስ1፥78–79 መሲሑን ከሰማይ የሚወጣ ፀሐይ እንደሆነ ይገልፃል። የዮሐንስ ተግባር ይህ ብርሃን እንደሚመጣ ማወጅ ነበር። ይህም ከዚህ ጋር ይስማማል፦ "ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ። ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።" ዮሐንስ 1፥6-8 7. ሰዎች በሰላም መንገድ እንዲሄዱ መርዳት “. . . እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።” ሉቃስ 1፥79 ዮሐንስ በስብከቱ አማካኝነት ሰዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ሰላም እንዲቀበሉ አዘጋጅቷል። ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 7 авг.1 251 просмотров18 реакций1 пересылок

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።” ሉቃስ 1፥79 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 6 авг.1 250 просмотров4 реакций34 пересылок

    📜ርዕስ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር 💾መጠን፦ 198.9MB ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 6 авг.1 199 просмотров3 пересылок

    без подписи

  • 7 авг.1 182 просмотров11 пересылок

    Title: Smith's Bible Dictionary Author: Smith, William Publisher: Grand Rapids, MI: Christian Classics Ethereal Library Year: 1884 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 6 авг.1 180 просмотров8 пересылок

    ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 8 авг.1 152 просмотров14 реакций4 пересылок

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ስለ እግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት በጀመረው ሥራ ሁሉ፥ በሕጉና በትእዛዙም፥ አምላኩን ለመፈለግ በፍጹም ልቡ አደረገው፥ ተከናወነለትም።” 2 ዜና 31፥21 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 9 авг.1 123 просмотров19 реакций3 пересылок

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ "እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።" መዝሙር 116፥1-2 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 9 авг.1 077 просмотров3 реакций2 пересылок

    без подписи

  • 9 авг.1 056 просмотров3 реакций1 пересылок

    #እራሳችንን_እንመርምር ስብከት ምንድነው? ጠቀሜታው ላላመነ ወይስ ላመነም ጭምር? “በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።” 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥21 “አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5 “እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?” ሮሜ 10፥14 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 10 авг.1 054 просмотров22 реакций2 пересылок

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።” ኤርምያስ 29፥11 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 10 авг.961 просмотров5 реакций2 пересылок

    без подписи

  • 11 авг.862 просмотров16 реакций1 пересылок

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።” 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥24 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 12 авг.833 просмотров15 реакций2 пересылок

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።” ዘፍጥረት 49፥22 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 11 авг.806 просмотров11 реакций15 пересылок

    #አዲስ_ዓመት የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም ክፍል-1 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን በማዘውተር ታነቡ እንደሆነ ልጠይቃችሁ እወዳለሁ፡፡ ቤተሰብ በገበታ ሲሰበሰብ ወይም በተለምዶ እንደሚደረግ ማለቴ ሳይሆን ለራሳችሁ ብላችሁ ብቻችሁን ስትሆኑ ታነቡ እንደሆነ ልጠይቅ ፈልጌ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ማዘውተሩ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ አማኝ የእግዚአብሔርን ቃል የማያነብ ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ኅብረት አይኖረውም፤ ደስታውም የተሟላ አይሆንም፡፡ እንደዚህ ማለታችንም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅም ማጋነን አይሆንም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነና እግዚአብሔርንና ሐሳቡንም ማወቅ የምንችለው ደግሞ በቃሉ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር በቃሉ ራሱን ገለጠ፤ ቃሉንም እንዲጻፍ አደረገው፡፡ በዚህ ቃሉም ማንነቱን ገለጠ፡፡ ያደረገውን፣ ሊያደርገው ያለውንና ሰው እንዴት ሊያገለግለው እንደሚገባም በቃሉ ተናገረ፡፡ ከዚያም ወልድ ወደ ምድር መጣና እግዚአብሔርን ተረከው (ዮሐ.1፡18) እንደዚሁም ስለወልድ ሕይወት ማለትም ስለ ልደቱ፣ ኑሮውና ሞቱ ስለ ተናገረውና ስለ ሥራውም ማወቅ የምንችለው በቃሉ ብቻ ነው፡፡ አሁን በምድር ላይ በአማንያን የሚያድር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በቃሉ በኩል ሁሉን ነገር ይገልጽልናል፡፡ ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስን የማይወድ አማኝ ካለ አሳዛኝ ነው፡፡ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት ማደግም ለቃሉ ካለን ፍቅርና ከቃሉ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አዲሱ ልደት- በእግዚአብሔር ቃል ለምሳሌ መዝ.119ን ስንመለከት የዘማሪው እያንዳንዱ መንፈሳዊ ደረጃ ከቃሉ ጋር የተያያዘ ሆኖ እናገኛለን፡፡ በዚሁ መዝሙር ቁ.93ን ስናይ ‹‹በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘላለም አልረሳም›› በማለት አዲሱ ሕይወት ከቃሉ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡ እንደዚሁም በሌሎች ቁጥሮች ማለትም ቁጥር 25፣ 37፣ 41፣ 50፣ 88፣ 107፣ 116፣ 144፣ 149፣ 154፣ 156፣ 159 እና 175ን መመልከት ይቻላል፡፡ ይህ ሐሳብ በሌሎች በርካታ ምንባቦችም በግልጥ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ‹‹ለፍጥረቱ የበኩራት ዓይነት እንሆን ዘንድ በእውነት ቃል አስቦ ወለደን›› (ያዕ.1፡18) የሚል እናያለን፡፡ በሌላ ስፍራም ‹‹ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ›› (1ጴጥ.1፡23) ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የኃጢአተኛን ሰው ኅሊና ወደ እግዚአብሔር ብርሃን እንዲመጣ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ሰው ማን መሆኑን አይቶ ራሱን ያወግዛል፤ ወደ እግዚአብሔርም ይናዘዛል፤ ይህም መለወጥ ማለት ነው፡፡ ራስን መመርመርና በራስ መፍረድም የሰውን ልብ ያነፃል፤ መንፈስ ቅዱስም በቃሉ በኩል አዲስ ሕይወትን በሰውዬው ውስጥ ይሠራል፡፡ ስለዚህ ለማያምኑት ሰዎች ወንጌልን ስንነግር የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ አለብን፡፡ የራሳችን ቃል ሰውን ወደ እምነት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ሰውን መለወጥ የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡ ‹‹እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡›› (ሮሜ.10፡17)፡፡ የአዲሱ ሕይወት ምግብ በተጨማሪም መዝሙረኛው ስለ እግዚአብሔር ቃል ሲናገር ‹‹ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ፤››(መዝ.119፡103) ‹‹ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል››(መዝ.19፡10) በማለት የቃሉን ጣፋጭነትና ምግብነት በማድነቅ ተናግሯል፡፡ ይህም ጣፋጭ ምግብ ደግሞ ለአዲስ ሕይወት ምግብ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ሰው ‹‹ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም›› በማለት ቃሉ በሕይወት የምንኖርበት ምግብ እንደሆነ ተናግሯል (ማቴ.4፡4፣ ዕብ.5፡12-14፣ 1ጴጥ1፡25-2፡2)፡፡ በቃሉ የተገኘው አዲሱ ሕይወታችን የሚስማማውን ምግብ ማግኘት አለበት፡፡ ይህም ምግብ አዳኛችንና የሞተልን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤(ዮሐ.6፡56) እርሱ በምድር ቅዱስ ሰው ሆኖ የተመላለሰና በሰማይ ደግሞ የከበረ ጌታ ሆኖ የተቀመጠ የአማኞች ምግብ ነው፡፡ እርሱ የምድረ በዳውን መና የተካ፣ የከነዓን የምድር ፍሬ፣ እንደዚሁም ለአማኞች የዘወትር መብል የሆነ ከሰማይ የወረደ አማናዊ መና ነው (ኢያ.5፡11-13) ይህንንም ምግብ የምናገኘው በቃሉ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ጌታ በብሉይ ኪዳን በጥላዎችና በምሳሌዎች እየሆነ በትንቢቶች እና በነቢያት ይታያል፡፡ በአዲስ ኪዳን ደግሞ በሕይወቱ በሞቱና በክብሩ ከወንጌላት እስከ ራእይ በተጻፈው ይታያል፡፡ ታዲያ ብዙዎች መንፈሳዊ ሕይወታቸው ደክሞ አቅመቢስ ሆነው ጠንካራ ምግብ መውሰድ ተስኖአቸው ወተት ብቻ የሚያስፈልጋቸው (ዕብ.5፡12-14) ወደ ጉባኤ ስለማይመጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስለማይከታተሉ ራሳቸውም ቃሉን ስለማያነቡ አይደለምን? ልናድግና ጤናማ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት ሊኖረን የሚችለው ዕለት ዕለት ያለማቋረጥ ቃሉን ስንመገብ ብቻ ነው፡፡ ይቀጥላል... ምንጭ፦ gbv-online.org ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

  • 11 авг.774 просмотров2 пересылок

    без подписи

  • 12 авг.759 просмотров2 пересылок

    без подписи

  • 12 авг.706 просмотров6 реакций12 пересылок

    #አዲስ_ዓመት የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም ክፍል-1 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን በማዘውተር ታነቡ እንደሆነ ልጠይቃችሁ እወዳለሁ፡፡ ቤተሰብ በገበታ ሲሰበሰብ ወይም በተለምዶ እንደሚደረግ ማለቴ ሳይሆን ለራሳችሁ ብላችሁ ብቻችሁን ስትሆኑ ታነቡ እንደሆነ ልጠይቅ ፈልጌ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ማዘውተሩ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ አማኝ የእግዚአብሔርን ቃል የማያነብ ከሆነ…

  • 13 авг.618 просмотров11 реакций

    . ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።” ዘፍጥረት 2፥15 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures