ተስፋ በኢየሱስ
Статистикаየኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን። 2ቆሮ4-10 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ 👉 @Tes_b37
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- Категория
- Instagram (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 284
- 1/48двое суток
- 325
- 1/72трое суток
- 351
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹ የምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
*ከታማኙ ጋር ታማኝ ትሆናለህ እንከን ከሌለበት ጋር ያለ እንከን ትሆናለህ* *ከንጹሑ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ለጠማማው አንተ ትጠምበታለህ።* *አንተ ትሑታንን ታድናለህ ትዕቢተኛውን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።* *እግዚአብሔር ሆይ አንተ መብራቴን ታበራለህ አምላኬ ሆይ ጨለማዬን ብርሃን ታደርገዋለህ።* *በአንተ ጒልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ።* የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ እርሱ ጋሻ ነው።* 📖መዝሙር 18÷25-30📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
"ሕይወትን ብቻችንን እንድንጋፈጠው ፈጽሞ አልተፈጠርንም! እግዚአብሔር በምናደርገው ነገር ሁሉ የሚረዳንና ሁልጊዜ ከእኛ ጋር የሚኖር አጋራችን እንዲሆን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሰጥቶናል።" *ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል በከፍታዎችም ላይ ያቆመኛል።* *እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል ክንዴም የናስ ቀስት መገተር ይችላል።* *የድል ጋሻ ሰጥተኸኛል ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች ዝቅ ብለህም ከፍ አደረግኸኝ።* ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ እግሬም አልተንሸራተተም።* 📖መዝሙር 18÷32-36📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
"ነገሮች መልካም በሆኑበት ጊዜ በእግዚአብሔር ማመኑ ቀላል ነው ነገር ግን እምነታችሁ የሚገነባው ነገሮች አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ ነው።" *ወንድሞች ሆይ፤ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር።* *በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤ ይህም የሆነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንድንታመን እንጂ፣ በራሳችን እንዳንታመን ነው።* *እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል።* 📖 2ኛ ቆሮንቶስ 1÷8-10📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
*አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረ በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ።* *ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ።* 📖ዕብራውያን 11÷11 📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
የበደለኛነት ስሜት ወደኋላ እየጎተታችሁ ከሆነ ልቀቁት። ይቅርታውን ተቀበሉ። ምሕረቱን ተቀበሉ። ዛሬ የአዲስ ነገር መጀመሪያ ነው እንግዲህ ያለፈውን መሸከም አይጠበቅባችሁም ኢየሱስ እያንዳንዱን ትግሏችሁን፣ እያንዳንዱን ፈተናችሁን እና እያንዳንዱን ድካማችሁን ይረዳል — ወደ እርሱም መጥታችሁ ምሕረትንና ጸጋን በድፍረት እንድትቀበሉ ይጋብዛችኋል። ራሳችሁን መቅጣት አቁሙ። እግዚአብሔር በነጻ የሚሰጣችሁን ተቀበሉ። እርሱ ከእናንተ ጋር ነው። *እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።* *በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።* 📖ዕብራውያን 4÷14-16📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
*በያዕቆብ መጥፎ ነገር አልተገኘም በእስራኤልም ጒስቍልና አልታየም እግዚአብሔር አምላኩ (ያህዌ ኤሎሂም) ከእርሱ ጋር ነው የንጉሡም እልልታ በመካከላቸው ነው።* * እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከግብፅ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጎሽ ብርታት ነው።* * በያዕቆብ ላይ የሚሠራ አስማት የለም፤ በእስራኤልም ላይ የሚሠራ ሟርት አይኖርም ለያዕቆብና ለእስራኤል እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያደረገውን እዩ ይባልላቸዋል።* *ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል ያደነውን እስኪያነክት የገደለውንም ደም እስኪጠጣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።* 📖 ዘኁልቁ 23÷21-24📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
*በተበላሹትና በተሳሳቱት ነገሮች ላይ ማተኮር ቀላል ነው::* *ነገር ግን ትክክል በሆኑትና በጎ በሆኑት ነገሮች ላይ ማተኮርንም አትርሱ።* ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
ትተውት የወጡትን አገር ቢያስቡ ኖሮ፣ ወደዚያ የመመለስ ዕድል ነበራቸው።* * አሁን ግን ከዚህ የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ* * ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አላፈረም፤ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።* 📖ዕብራውያን 11÷15-16📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
ዓለም ተሰጥኦን ያደንቃል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል። ስጦታዎች በነጻ የሚሰጡ ናቸው ባህሪ ግን በሂደት የሚገነባ ነው—እርሱም ከሁሉ በላይ ዋጋ የሚሰጠው ለዚህ ነው። ይበልጥ ጥልቅ የሆነ ሕይወት እንኑር እርሱንም የሚያንጸባርቅ ፍሬ እናፍራ። *እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ። የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት* 📖 ዕብራውያን 12÷1-2📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
*ይህን ሁሉ አግኝቻለሁ ወይም ፍጹም ሆኛለሁ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ እኔን የራሱ ያደረገበትን ያን፣ እኔም የራሴ ለማድረግ እጣጣራለሁ።* *ወንድሞች ሆይ፤ እኔ ገና እንደያዝሁት አድርጌ ራሴን አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ከኋላዬ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ።* *እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ላይ ስለ ጠራኝ፣ ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።* 📖 ፊልጵስዩስ 3÷12-17📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
. መንፈሳዊ ባለስልጣን ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጒዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው። አለበለዚያ አይበጃችሁም። 📖 ዕብራውያን 13÷17📖 በዚህ ዘመናዊው ዓለም ህብረተሰቡ ፍጹም በሆነ ዓመጽ ተሞልቷል፡፡ ዓመጽ ደግሞ እግዚአብሔርን እንዳንሰማ ያደርጋል፡፡ እኔ በብዙ የተመለከትኩትና የታዘብኩት ብዙ ብዙ ሰዎች ከስለጣን ጋር በተያያዘ ብዙ ግጭት ውስጥ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ይህም በጋብቻ ውስጥ፣ በቤተሰብ፣ በንግዱ ዓለም፣ በሲቪል እንቅስቃሴ፣ና በሁሉም ባህሎች ውስጥ የሚታዩ እውነት ነው፡፡ ለመንፈሳዊ ባለስልጣን አለመታዘዝ በተለየ ሁኔታ እየታየ አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ መጋቢ የሰዎችን አንዳንድ ስህተት ለማረም ከሞከረ ሰዎች ወደ ብጥብጥና ኩርፊያ ያዘነብሉና ቤተክርስቲያንን ለቅቀው ለመሄድ ይሞክራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም፡፡ ጳውሎስ በተደጋጋሚ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ያርም ነበር፤ ይህ ደግሞ እንደ አንድ መንፈሳዊ መሪ አንዱ ሥራው ስለሆነና ዛሬም ድረስ የቀጠለ መንፈሳዊ መሪዎች ኃላፊነት ነው፡፡ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ‹‹ … ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን እንጂ፥ በእምነታችሁ በእናንተ ላይ የምንገዛ አይደለንም። በእምነታችሁ ቆማችኋልና››(2ኛቆሮ.1፡24) ። ለመንፈሳዊ ባለስልጣን መኖር ለደስታችን መብዛት መሆኑን ስንረዳና ስናውቅ እንቀበለዋለን፤ እናደርገዋለን፡፡ ደስታችንም ይጨመራል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን የመስማት ብቃታችንም ይጨምራል፡፡ እንደ 2ኛተሰ.2፡7 – 8 መሠረት ዛሬ በዓለም ላይ እየሠራ ያለው የዓመጽ መንፈስ የክርስቶስ ተቃዋሚ (የሐሰተኛ ክርስቶስ) መንፈስ ነው፡፡ ይህ ለማንም ሰው ለመታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆኑ ማለት ነው፡፡ ዛሬ ሰዎች መብታችንን መጠየቅ ብለው ይከራከራሉ፡፡ ነገር ግን እውነታው አብዛኛውን ጊዜ ባለስልጣናትን በመቃወም የራሳቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ *ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ለጌታ እንደምታገለግል ለባለስልጣን ታዘዝ (ተገዛ) እርሱ ደግሞ ይባርክሃል፤ ያበለጽግሃል፡፡* ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
. 📖መዝሙር 27፥1-3📖 « እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ? ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ። ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤ ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ። ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
*እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦* *ትዕቢተኛ ዐይን፣ሐሰተኛ ምላስ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣* *ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች* *በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣* *በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።* 📖 ምሳሌ 6÷16-19 📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
*የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ* * እርስ በርሳችንም ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ።* *አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።* 📖ዕብራውያን 10÷23-25📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
. ልብህን ክፈት «… ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ» (ዮሐ.11፡35) ። ብዙ ሰዎች ትክክለኛውን መንፈሳዊ ስሜት የማይሰማቸው ናቸው፣ ምክንያቱም በቀደመው ህይወታቸው ብዙ ከባድ ጉዳቶችን አስተናግደው ስለነበር ለዚህም ስሜታቸው በቀላሉ «ዝግ» አድርገውታል። ሰዎች ለረጅም ጊዜ ያህል ምንም እንዳይሰማቸው ዝግ አድረገው ቆይተው እንደገና ወደ ቀደመው ስሜታቸው ለመመለስና ለመጀመር ያሳፍራቸዋል። ምክንያቱም የተጎዱበትን ስሜት መልሰው ስለሚያስታውሳቸው ነው። በመጨረሻ ስሜታዊ ጉዳት መዳኘት (መታየት) ያለበት በመንሳዊ ህይወት በተቃኘ መንፈሳዊ ስሜት እንዲሆን መፍቀድ አለብን። ወደ ቀደመው መንፈሳዊ ስሜት ለመመለስ ስንፈቅድ ከልበ ደንዳናነት ወደ ተሰበረ ልብ (ለቃሉ ወደ ሚንቀጠቀጥ) እንደመለሳለን። ነገር ግን ወደ ቀደመው ስሜታችን ለመመለስ ከእግዚእበሔር ጋር ለመስራት መታገስና ፈቃደኛነትን መግለጥ ይጠይቃል። የተጎዳውን ስሜትህ መነሻው ምን እንደሆነና እንዴት አስፈሪ እንደነበር ማሰብ ከባድ ቢሆንም በልበ ደንዳናነት እስራት ውስጥ ግን መታሰር ና መቆየት የለብንም። ይህ የችግሮቹን ምልክቶች ብቻ ማከም ይሆናል እንጂ የጉዳትህን ሥር ማግኘት አይሆንም። ይህ ነገም ሊመጣብህ ካለ የበለጠ ጉዳት አይከላከልህም። እንዲያውም የእግዚአብሔርን ድምጽ የመስማት ብቃትህን ይገድበዋል። ልበ ደንዳናነት ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እርሱ በጎ ስሜት የሚሰማን አድርጎ ነበር የፈጠረን። በዛሬው በመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሠረት ኢየሱስ ራሱ እንዳለቀሰ ይናገራል። ሁልጊዜ (መቼም) ራስህን በጎ ስሜት የሚሰማው እንዲሆን ፍቀድለት። በስሜት መጎዳት በቀላሉ ልትጎዳ ትችላለህ። ነገር ግን በውስጥህ ያለውን ፈዋሹ ኢየሱስ ሲኖር የተለየ ይሆናል። መቼም ቢሆን ጉዳት ያጋጥምሃል፤ እርሱ ደግሞ የተጎዳኸውን ቁስለት ሊፈውስህ በአጠገብህ በዚያ አለ። ስሜትህን ዝግ ካደረግኸው የእግዚእበሔርን ድምጽ የመስማት ብቃትህ ላይ እያመቻመችህ እንዳለህ ማስረገጥ ነው። እግዚአብሔር እርሱ የሚፈራውን ልብ (የተሰበረ) ልብ እንዲሰጥህና እንዲፈውስህ ለእርሱ ልብህን ክፈት። የእርሱን ድምጽ ለመስማት እንድትችልና ከእርሱ ጋር ባለህ የጠበቀ ህብረት ደስተኛ መሆን እንድትችል ጸልይ። *ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ራስህን ከሰዎች ለመለየትና ከህይወትህ እንዲወጡ ለማድረግ ግምብ የምትሠራ ከሆነ አንተ በራስህ አስራት ታስረህ ከግምቡ በስተጀርባ ታስረህ ትኖራለህ።* ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፤ “ሀልዎትህ ከእኛ ጋር ካልሄደ ከዚህ አትስደደን። አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ አንተ በእኔና በሕዝብህ መደሰትህን ሌላው እንዴት ያውቃል? እኔንና ሕዝብህንስ በገጸ ምድር ከሚገኙት ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ ልዩ የሚያደርገን ሌላ ምን አለ?” 📖 ዘፀዓት 33÷15-16📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
እግዚአብሔር በተከፈቱና በተዘጉ የእድል በሮች ይናገራል ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፣ የዳዊትንም መክፈቻ በእጁ የያዘው እንዲህ ይላል፤ እርሱ የከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም፤ የዘጋውንም ማንም ሊከፍተው አይችልም። 📖ራዕይ 3÷ 7📖 አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር እኛ ለማድረግ የፈለግነውን ነገር በሮችን በመክፈትና በመዝጋት ይናገራል፡፡ ጳውሎስና ስላስ ወደ ቢታኒያ ሄደው እዚያ ላሉት ሕዝብ ወንጌል ለመስበክ መከሩ፡፡ ነገር ግን የኢየሱስ መንፈስ እንዳያደርጉ ከለከላቸው፡፡ (የሐዋ 16 6-7 ተመልከት) ነገሩ እንዴት እንደተደረገ እርግጠኛውን ነገር አናውቅም፡፡ ወደ ግዛቱ ለመሄድ እንዲሞክሩ በእርግጥ መገመት አያቅትም ሆኖም ግን እግዚአብሔር ወደዚያ ከመግባት ጠበቃቸው፡፡ እኔ በህይወቴ የተለማመድኩት እግዚአብሔር በሮችን ይከፍትል ያንን የዕድል በሮች ደግሞ ማንም መዘንጋት አይችልም፡፡ እንዲሁም ደግሞ በሮችን ይዘጋል ያንን በር ማንም በቀላሉ ሊከፍተው አይችልም፡፡ ያ የተዘጋው በር እውነትነት ያለው ነገር ሊሆን ይችላል በሰዓቱ ላዝን እችላለሁ ፡፡ ነገሩ ስህተት መሆኑ ሲረጋገጥ ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ እርሱ ፍቃድ ያልሆነውን በሮች እንዲዘጋው በእግዚአብሔር እደገፋለሁ፡፡ በሕይወቴ ለዓመታት እኔ የምፈልገው ነገር እንዲሆን በመሞከር ነው ያሳለፍኩት ውጤቱ ግን ተስፋ መቁረጥና፣ ቅር መሰኘት ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ የእኔ ድርሻ በብዙ በጣም ሠላማዊና አስደሳች የሆነው እኔ የእራሴን ድርሻ በማድረብ በእግዚብሔር ላይ በቀላሉ በመታመን እርሱ ከእርሱ ዕቅድ ጋር የሚስማማውን በሮች እንዲከፍተውና የእርሱ ፈቃድና እቅድ ያልሆነውን አጥብቆ እንዲዘጋው ሕይወቴን እተውለታለሁ። *ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በሕይወትህ በአንተ በራስህ ለአንተ ለራስህ አንዳች ነገር እንዲከናወን አትሞክር እግዚአብሔር ለአንተ ትክክለኛውን በሮች በመክፈትና የስህተት በሮችን እንዲዘጋልህ እርሱን ታመነው*
*በዝቶ ካለው ጩሁት ሸተተኝ ሰላሙ ከጨለማው መሀል ታየኝ ወጋገኑ ከድፍርሱ መሀል ኩልል ያለ ነገር ይታየኝ ጀመረ 🥰በቃልህ ስታመን*🥰 ተስፋበኢየሱስ Channel 📖 😍 @HopeOfJesusChannel 📖😍
*ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ ለእርሱ በተነገረው መሠረት፣ ምንም ተስፋ በሌለበት፣ አብርሃም በተስፋ አምኖ የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።* *እርሱ የመቶ ዓመት ሰው ሆኖ ሳለ፣ የራሱም ሰውነት ሆነ የሣራ ማሕፀን ምዉት እንደ ነበረ እያወቀ በእምነቱ አልደከመም።* *ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም* *እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም በሙሉ ልብ ርግጠኛ ነበር።* 📖 ሮሜ4÷18-21📖 ተስፋበኢየሱስ Channel 🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆