CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
Статистика"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21) 🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡ 📌 በተጨማሪም ◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች ◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች ◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና ◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል ✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇 📩 @Christ_Tube_Bot Creator @Beki_MW
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 70
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Instagram (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 647
- 1/48двое суток
- 741
- 1/72трое суток
- 799
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹ የምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ክፍል ስድስት “ሌሎች ሲቀድሙኝ ምን አደርጋለሁ?” አንዳንድ ጊዜ መጠበቅ የሚያደክመው ምክንያት የምንጠብቀው ነገር ብቻ አይደለም። ሌሎች ሰዎች የጠበቁትን ነገር ሲያገኙ ማየታቸው ነው። 😔 “እሷ አገኘች…” “እሱ ተሳካለት…” “እኔ ግን እስካሁን እጠብቃለሁ…” እዚህ ላይ ልብ በቀላሉ ይደክማል። 1️⃣ የሌላ ሰው ጊዜ የአንተ መለኪያ አይደለም እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የተለየ ጉዞ አለው። የሌላ ሰው ፍጻሜ አንተ ዘግይተሃል ማለት አይደለም። አንድ ዘር በፍጥነት ሊበቅል ይችላል፤ ሌላው ግን ትንሽ ይዘገያል። የዘገየው ግን ፍሬ አያፈራም ማለት አይደለም። 2️⃣ ንጽጽር የመጠበቅን ሰላም ይሰርቃል “እሷ ለምን?” “እኔ ለምን አይደለሁም?” የሚለው ጥያቄ እምነትን ሳይሆን ልብን ያደክማል። እግዚአብሔር ግን፦ “የእኔን ጉዞ ተከተል፤ የሌላውን አትመዝን” እንደሚል እንይ። 3️⃣ የሚያምር ነገር አለ ሌላ ሰው ሲያገኝ መደሰት እና የራስህን ጊዜ መጠበቅ በአንድ ላይ ይቻላል። “ጌታ ሆይ፣ ለእሷ ስለሰጠህ አመሰግንሃለሁ። የእኔንም ጊዜ አምነሃለሁ።” ይህ የብስለት እምነት ነው። 🙏 4️⃣ የሌላው ምስክርነት የአንተን ተስፋ አይሰርቅ አንድ ሰው የተቀበለው በረከት እግዚአብሔር ለአንተ የሚያደርገውን አይቀንስም። የሌላው በረከት የአንተ እጦት ማስረጃ አይደለም። “እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ።” — ኢሳይያስ 40፥31 #“ሌሎች ሲቀድሙኝ እኔ አልዘገየሁም፤ እኔ በራሴ ጉዞ ላይ ነኝ። የእግዚአብሔር ጊዜ ለእኔም ትክክል ነው።” ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
#የማለዳ_ቃል 🌤☀️ 1 ዜና 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። ¹¹ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። መልካም ቀን! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
#የማለዳ_ቃል 🌤 በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን። መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይለናል። -መዝ 90፥14-15 መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
ክፍል አምስት እግዚአብሔር ዝም ሲል…” አንዳንድ ጊዜ ትጸልያለህ። ትጠይቃለህ። ታለቅሳለህ። ትጠብቃለህ። ግን… ምንም ምላሽ እንደሌለ ይሰማሃል። “ጌታ ሆይ፣ አልሰማኸኝም?” “ረሳኸኝ?” “ለምን ዝም አልክ?” 😔 እዚህ ላይ ነው እምነት በጣም የሚፈተነው። 1️⃣ የእግዚአብሔር ዝምታ የእርሱ መቅረት አይደለም ልብህ ሊል ይችላል፦ “አልሰማኝም።” ግን እውነቱ፦ እርሱ አለ። “እኔ ከእናንተ ጋር ሁልጊዜ ነኝ።” — ማቴዎስ 28፥20 እግዚአብሔር ዝም ሲል ከአንተ ርቆ ሄዷል ማለት አይደለም። 2️⃣ ዝምታው እምነትህን ሊያሳድግ ይችላል ብርሃን ሁልጊዜ እያየህ መሄድ ቀላል ነው። ግን በጨለማ ውስጥ እግዚአብሔርን ማመን—ያ ነው እምነት። “ምንም ባላይም፣ አምንሃለሁ።” ይህ በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ እምነት ነው። 3️⃣ ዝምታውን እንደ “አልሆነም” አትቁጠረው አንዳንዴ እኛ “አልመጣም” እንላለን፤ እግዚአብሔር ግን “ገና ነው” ሊል ይችላል። “አይደለም” እና “ገና አይደለም” በጣም ይለያያሉ። ስለዚህ በዝምታ ውስጥ ተስፋህን አትቅበር። 4️⃣ በዝምታው ውስጥ አንተ ምን ታደርጋለህ? ጸልይ። 🙏 ቃሉን አንብብ። 📖 ተስፋ አድርግ። 🌱 በትዕግሥት ጠብቅ። ❤️ መልስ እስኪመጣ ድረስ ሕይወትህን አታቁም። “ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ትተክያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትወክያለሽ? በእግዚአብሔር ተስፋ አድርጊ…” — መዝሙር 42፥5 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
#የማለዳ_ቃል 🌤 እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ፤ ከተስፋዬም አልፈር። እርዳኝ እድናለሁም፥ ሁልጊዜም ሥርዓትህን እመረምራለሁ። -መዝ 119፥116-117 መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
ክፍል አራት ሳናይ እንዴት እናምናለን? እምነት ቀላል የሚሆነው የምንጠብቀውን ነገር ስናይ ነው። ግን እውነተኛ የእምነት ጥንካሬ የሚታየው ገና ሳናይ ስንጠብቅ ነው። “በማየት ሳይሆን በእምነት እንመላለሳለን።” — 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥7 1️⃣ ሳታይ ማመን ማለት ምንድነው? ማለት፦“ውጤቱን ገና አላየሁም፤ ግን እግዚአብሔርን አውቃለሁ።” ነገሩን ስላላየኸው እምነትህን አትጣም። የምታምነው ነገር ከሁኔታው ይልቅ በእግዚአብሔር ባህርይ ላይ ይመሠረታል። 2️⃣ ሁኔታው ሲቃረን ምን እናድርግ? አንዳንድ ጊዜ የምታየው ነገር ተስፋ የሚያስቆርጥ ይሆናል። “እየጸለይኩ ነው፣ ግን ምንም አልተለወጠም!” እዚያ ላይ እምነት እንዲህ ይላል፦ “የማየው ሁኔታ የመጨረሻው ቃል አይደለም።” እግዚአብሔር ከምታየው በላይ እያየ ነው። 3️⃣ እምነት ከተስፋ ጋር ይሄዳል እምነት፦ “እግዚአብሔር ይችላል።” ተስፋ፦ “እግዚአብሔር ጊዜውን ያውቃል።” ትዕግሥት፦ “እስከዚያ ድረስ እቆያለሁ።” #እነዚህ ሦስቱ በመጠበቅ ወቅት ልብን ያጸናሉ። “እግዚአብሔር እየሠራ መሆኑን ለማመን ሥራውን በዓይኔ ማየት ያስፈልገኛል?” አይ። እምነት የሚጀምረው ዓይን በሚያየው ሳይሆን ልብ በሚያምነው ነው። 🙏 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
ክፍል ሶስት የእግዚአብሔር ጊዜ እና የእኛ ጊዜ ብዙ ጊዜ እኛ እንዲህ እንላለን፦ “ጌታ ሆይ፣ መቼ ነው?” መልሱ ግን ወዲያው ሳይመጣ ይቆያል። ከዚያም ልባችን መጠራጠር ይጀምራል፦ “ምናልባት አይሆንም?” “ምናልባት እግዚአብሔር ረስቶኝ ይሆን?” “ለምን እኔ ብቻ እጠብቃለሁ?” ነገር ግን መዘግየት መከልከል አይደለም። እኛ የምንመለከተው ዛሬን ነው፤ እግዚአብሔር ግን መጀመሪያውን፣ መካከሉንና መጨረሻውን ያያል። 1. የእግዚአብሔር ጊዜ ፍጹም ነው “ሁሉን በየጊዜው መልካም አድርጎአል።” — መክብብ 3፥11 አንድ ነገር ዛሬ ቢሆን ለእኛ መልካም ይመስላል። ነገር ግን እግዚአብሔር “ገና አይደለም” ሊል ይችላል። ምክንያቱም ነገሩን ብቻ ሳይሆን ጊዜውንም ያውቃል። 2. መጠበቅ እምነትን ይፈትናል በቀላሉ ነገር ሲሳካልን ማመን ቀላል ነው። ግን ምንም ሳናይ ስንጠብቅ፣ “እኔ ባላየውም እግዚአብሔር እያየው ነው” ማለት እምነት ነው። “ራእዩ ገና ለተወሰነው ጊዜ ነው… ቢዘገይ እንኳ ተጠባበቀው፤ በእርግጥ ይመጣል፥ አይዘገይም።” — ዕንባቆም 2፥3 3. በመጠበቅህ ውስጥ አትቁም እየጠበቅክ ነው ማለት ሕይወትህን አቁመህ መቀመጥ አይደለም።እየጠበቅክ ስትማር፣ ስትሠራ፣ ስትጸልይ፣ ራስህን ስታዘጋጅ እና በታማኝነት ስትመላለስ መቀጠል ነው። ዮሴፍ ቃል ኪዳኑ እስኪፈጸም ድረስ ብቻ አልተቀመጠም። በየቦታው ታማኝ ሆኖ ቀጠለ። የእግዚአብሔር ጊዜ ሲደርስ ያዘጋጀው ቦታ ላይ አገኘው። ❤️ ዛሬ የምታስታውሰው “እግዚአብሔር እየዘገየ አይደለም፤ እኔ ከጊዜው ቀድሜ መልስ እፈልጋለሁ።” ምናልባት አሁን በስራ፣ በገንዘብ፣ በትዳር ወይም በሌላ የሕይወትህ ጉዳይ ላይ እየጠበቅክ ይሆናል። ዛሬ ምንም እየተለወጠ እንደሌለ ቢመስልም፣ “ገና አልተለወጠም” ማለት “ፈጽሞ አይለወጥም” ማለት አይደለም። ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
#የማለዳ_ቃል 🌤 ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው።እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና። -ሮሜ2፥10-11 መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
🎉🎉 መልካም ዜና 🎉🎉 ለቴሌግራም ተከታታዮቻችን ለብዙ አመታት በቴሌግራም አገልግሎቱ የምታቁት ቻናላችን አሁን ተደራሽነቱን አስፍቶ የTiktok አካውንት መክፈታችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው። በመሆኑም ሁላችሁም ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ ሊንክ በመግባት ወይም Photoን Scan በማድረግ ቻናሉን የምታገኙ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን! 👇👇👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@christtubeeth?_r=1&_t=ZS-98hnS1mRN93 https://www.tiktok.com/@christtubeeth?_r=1&_t=ZS-98hnS1mRN93
በማለዳ እንመርቃችሁ! - ከክፋ ጋርዶ የሚያሳልፍ የእግዚአብሔር እጅ ያግኛችሁ! - አስባችሁ በወጣችሁበት ጉዳይ እግዚአብሔር ድል ይስጣችሁ! ተባረኩ!! @CHRIST_TUBE
#የማለዳ_ቃል 🌤☀️ ዳንኤል 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰ ወደ ጕድጓዱም ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኀዘን ቃል ጠራው፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም፦ የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ፥ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? አለው። ²¹ ዳንኤልም ንጉሡን፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ። ²² በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፥ ንጉሥ ሆይ፥ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው። መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
ክፍል 2 ለምን እግዚአብሔር እንድንጠብቅ ይፈቅዳል? "ጌታን ተጠባበቅ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እንደገናም ጌታን ተጠባበቅ።" — መዝሙር 27፥14 ብዙ ጊዜ እኛ የምንፈልገው "አሁኑኑ መልስ" ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚያየው ከእኛ እይታ ይሰፋል። አንዳንድ ጊዜ መጠበቅ የሚያስተምረን፦ 1. እምነትን — ምንም ባናይም እግዚአብሔር እየሠራ እንዳለ ማመን። 2. ትዕግሥትን — ሁሉም ነገር በራሱ ጊዜ እንደሚመጣ መማር። 3. የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳት — እኛ የምንፈልገው ሁልጊዜ ለእኛ የሚበጀው ላይሆን ይችላል። እንደ ዮሴፍ እንመልከት፤ በወንድሞቹ ተሸጠ፣ በእስር ቤትም ቆየ። ያ ጊዜ የመዘግየት ጊዜ ይመስል ነበር፤ ግን እግዚአብሔር ለትልቅ አላማ እያዘጋጀው ነበር። "እኔ እየጠበቅኩት ያለሁት ነገር ምን ነው? በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በእኔ ውስጥ ምን እየሠራ ይሆን?" በመጠበቅ ጊዜ ምን ማድረግ አለብን? "በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን በእግዚአብሔር ዘንድ አስታውቁ።" — ፊልጵስዩስ 4፥6 መጠበቅ ማለት ቁጭ ብሎ ጊዜን መቁጠር ብቻ አይደለም። በመጠበቅ ወቅት ልባችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ አለብን። 1. በጸሎት መቆየት ችግሩን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም ለእግዚአብሔር እንነግራለን። ጸሎት የሚቀይረው ሁኔታን ብቻ ሳይሆን እኛንም ነው። 2. በቃሉ መሙላት መጠበቅ ጊዜ ልብ በፍርሃት ሊሞላ ይችላል፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ሰላምና ጽናት ይሰጣል። 3. ማመስገን ሁኔታው ገና ባይቀየርም እግዚአብሔር መልካም መሆኑን ማመን ነው። 4. መልካም ነገር ማድረግ መቀጠል መልሱን እየጠበቅን ሳለን እጃችንን ማጠፍ አይደለም፤ በታማኝነት መራመድ ነው። ማሰላሰያ፦ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የምንጠይቀውን ነገር ሳይሰጠን በፊት የሚያዘጋጀው ልባችንን ነው። ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
አቤት ምህረት የበዛለት Lidya Gossaye Kingdom Sound Worship Night 2026 “Abet Mihret“ Org song by Daniel Amdemichael ------------------------------------ Amazing Worship Song ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው! ▱ @CHRIST_TUBE ▱ ▱ @CHRIST_TUBE ▱
አቤት ምህረት የበዛለት Lidya Gossaye Kingdom Sound Worship Night 2026 “Abet Mihret“ Org song by Daniel Amdemichael 🎥 Video Check on Youtube https://youtu.be/MVTeX_-LwMo ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው! ▱ @CHRIST_TUBE ▱ ▱ @CHRIST_TUBE ▱
እሩጫችን በምን ይሁን...? 🤔 ✍ ወደድንም ጠላን በህይወት እስካለን የምትሮጥለት/የምንኖርለት ነገር አለ። የአብዛኛዎቻችን ችግር የምንሮጥለትን ነገር ሳነሠውቅ መሮጣችን ሌሎቻችን የምንሮጥለት ነገር አቅጣጫውን ባለማወቅ ስንሮጥ ደክመን መድረሻችን የያልጠበቅነው ሆኖ ተስፋ ቆርጠናል ወይም ያስቆርጠናል። ✍ አንድ #እሯጭ በሩጫ ሚዳ ውስጥ የፈለገውን የመዘነጫ ልብሱን ለብሶ መግባት እንደማይችል የግድ ለሩጫ የሚመቸውን የሩጫ ልብሱን ለብሶ እንደሚገባ ሁሉ... በዚህ ክፉ ዘመን በማስተዋልና በጥበብ እሩጫችንን በትግስት ልንሮጥ ያስፈልጋል። 1☞ የምንሮጥለትን ነገርን በደንብ ጠንቅቀን እንወቅ። 2☞ የምንሮጥለት ነገር ጋ የሚያደርሰንን መንገድ በደንብ ጠንቅቀን እንወቅ። 3☞ የምንሮጥለት ነገር ጋ የሚያደርሰንን ነገር ብቻ እንጂ ሁሉንም ነገር አናግበስብስ። “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።” (ኤፌ 5 :16-17) ተባረኩ! መልካም ቀን 👐 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRIST_TUBE
#የማለዳ_ቃል 🌤☀️ “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።” — ኢሳይያስ 40፥31 መልካም ቀን ! ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
"በስሜ ታውቀኛለህ ብዬ ሲገርመኝ አቅጄሽ ነው አልከኝ እንዳቀድከኝ ሲገርመኝ አከብርሻለው አልከኝ ይህም ሲደንቀኝ ለዘለዓለም ከኔ ጋር በህይወት ኑሪ አልከኝ።" #አይገርምም ያውቀናል ፣ ይወደናል እንደሰው ክፋት ሳይሆን እንደምህረቱ ብዛት በፍቅሩ ተሽክሞ ያኖረናል። “በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።” — ኤርምያስ 1፥5 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY