tgindex
የገጣሚያን ማኅበር

የገጣሚያን ማኅበር

Статистика

እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦ 👉መንፈሳዊ ግጥም ፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ 👉ግጥማዊ ትረካ ይቀላቀሉን Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber Group👉 @yegetamianmahiber Owner:- @S_o_L_e_N_y

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Instagram (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
22 928
+21 за 5 дн.
Сутки
−21
−0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 144
26 постов
Вовлечённость
5,0%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 26
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
по 3 постам
1/24сутки в ленте
783
1/48двое суток
1 060
1/72трое суток
1 143

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 14 авг.1183удалён 14 авг.

    без подписи

  • 14 авг.1 049611

    без подписи

  • 13 авг.1 301107

    ነፃነት የሰው ልጅ እውቀቱ እየበዛ ሄደ፤ ሃጥያትና አመፃ እጅጉን ጨመረ፤ ነፃነትም በዛ ሁሉ ተፈቀደ፤ በፈጣሪ ስራ እጁን አጠለቀ፤ አዳም ከአዳም ጋር ካልተጋባው አለ፤ እውቀቱ እየበዛ የሄደ ሲመስለው፤ አምላኩን እረስቶ ለሌላ ሰገደ፤ የኋላውን ሳያይ መጓዝን መረጠ:: የነፃነት ብዛት ህግን እያላላ፤ መብቴ ነው እያለ እንዲሁ ሲያወራ፤ ፆታዬን ካልቀየርኩ ብሎ እሱም አወራ፤ እግዜር በሱ ስራ የራሱን መብት አጣ:: ባበጃጀው ፍጥረት በእጆቹ ስራ፤ የሱ መብት ተገፎ ነፃነትን አጣ:: በነፃነት ሰበብ መብቴ ነው እያለ፤ ያልተፈቀደውን ሁሉ አደረገ፤ የተፈጥሮን ትዛዝ ህግን ሁሉ ሻረ፤ ፆታዬን ቀይሬ ሴት ካልሆንኩኝ አለ፤ በእግዜር ስራ ገብቶ እኔ አውቃለሁ አለ። የማይገባውን ይገባል እያለ ፤ ያልተፈቀደውን ተፈቅዷል እያለ ፤ ለራሱ ተሳስቶ ሌላን አሳሳተ፤ የእግዜርን መብት ገፎ ጌታ ካልሆንኩ አለ። አይ ሰው.... የሰውማ ነገር መች ተነግሮ ያልቃል ፤ መብቴ ነው እያለ ሁሉን እያረገ ፤ ነፃነት ነው ብሎ ህግን እየሻረ ፤ በፈጣሪ ስራ እጁን እየላከ ፤ ተፈጣሪ ሳልሆን ፈጣሪ ነኝ አለ።                                                        ✍️Yididiya .H @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 13 авг.1 16694

    መሀሪ ነው እሱ part 2😁 ግን አንድ ዜና ካለንበት መጣ "ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ ከመቃብር ወጣ" 😱😱ኸረ እኔ አላምንም ላይሞት ሰው ሲነሳ በፍጹም አላውቅም በተዘጋ ቤት ሳለ ሁሉም ሰው በፍርሀት በትንሳኤ አካል ክብር ለብሶ መጣ ስናየው ደስ አለን ዳግም ሞት ተረታ አዎ ምስክር ነኝ ኢየሱስ ተነስቷል እስከ አለም ፍፃሜ ከእኛጋር ሊሆን ደግሞም ቃል ገብቷል ለእኔም የእሱ ነኝ ለማለት አንድ እድል ተሰቷል ማነው ምህረትን አላገኝም ያለ? ዝምታውን ፈርቶ በአለም የዋለ ማነው ሚርበተበት? እርሱን ለመናገር ፍርሀት ያለበት ወደ ጌታ ይምጣ ሸክሙንም ይጣለው ያለበትን ጣጣ ይለምን ምህረት ይመለስ ወደ እርሱ ሁል ጊዜም በፀፀት ወደ እርሱ ይመለስ ይጠይቅ ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ እግዚአብሔር መሀሪ የሆነው ቸር ምህረትን መስጠቱ መቼም ነው ማይቀር ልጁን የላከልን ለሀጥያት ሊሰዋው የምር እኔን ስሙ እርሱ መሀሪ ነው🥰🥰 እስኪ በ reaction ስለግጥሙ ✍️ by sulamatiswa @talent133 @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • ይድረስ ለእግዚያር) ከበሬ ደጅ ብትጠና፣               አንኳክተህ ልቤን ብትመታው አልከፍትም አትድከም ከንቱ፣               እኔ እንደው ቃሌን አልፈታው ብትለምን ዘመን ብትፈጅም               ልትገባ በሽህ ቃል ብትጥር ተዘግቷል ቁርጥህን እወቅ                እሾህ ነው የልቤ አጥር።                  ; እያልኩኝ ደጄን ሳስጠናህ፣                 ከአሪያም እንዳትመለስ ከገነት እሳት አጥሩ፣              አሻግረኝ ለህይወት በለስ በሃይልህ ልቤን አብጀው፣               ዝናህም በአይሁድ ይክበር ትንሳኤ በሰጠህ አካል፣                ግባብኝ በሐዋሪያት በር።                     (በተዘጋው በር) by ሰምረ የሽዋስ @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 12 авг.1 3551214

    መሀሪ ነው እሱ እኔ ስምኦን ነኝ ኬፋ የተባልኩኝ ከአሳ አጥማጅነት ሰው አጥማጅ የሆንኩኝ በወንድሜ ስብከት ይህን ጌታ አውቄ ተከተልኩት ቡቱቱዬን አዉልቄ ከኢየሱስ ጋር ብዙ አሳልፊያለው ብዙ ተአምራትን በእጁ አይቻለው ይሄ ክርስቶስ መሲሁ መሆኑን ከልቤ አምኛለው መምህር ጌትነቱን ግን ድንገት አንድቀን እንዲ አለኝ መምህሬ ከዚቀን ቦሀላ ትሰማላቹ የመሞቴን ወሬ እኔም ደነገጥኩኝ😱 ሳስበው ይህ መንጋ ሊበተን መሆኑን ኸ...😳ኸረ እኔ እሞታለው እኔም ከአንተ ጋር መከራን አያለው ስለው አርሱም አለኝ ዶሮ ሳይጮህ ጓዴ ሶስቴ ነው ምትክደኝ ምሞት እንኳን ቢሆን ከቶ አልክድህም እኔ ግን ምን ያረጋል ቃሌን አልጠበኩኝ ሳይጮህ ዶሮ ገና ሶስቴ ሰውፊት ካድኩኝ ከሊቀ ካህናት ገረድ የሆነች ሴት መጣች እኔም እሳት ስሞቅ ልክ አይኔን እንዳየች ከእርሱ ጋር ነበረ ስትል መሠከረች አይ አይ እኔ አልነበርኩም ያልሽውንም ሰው ፈጽሞ አላውቀውም ብዬ እንዳለፍኳት ኸረ እረሷ መች በዋዛ ልትለቀኝ ነበረ ይሄ ሰው ከርሱ ጋር ስትለኝ አይኔን ግንባር ያርገው እኔ አላውቀውም ይህንን ሰውዬ ራቂ ከእኔ አልኳት ጀንበር እየወጣች ሊነጋ እያለ አብሮኝ ሲሞቅ እሳት የነበረ አንዱ ደሞ መቶ በድፍረት እንዲ አለ ይሄ ሰው ከእርሱ ጋር ገሊላ ነበረ እያለ ሲከሰኝ ጠንቀቁሎ ጣቶቹን መሀል አናቴ ላይ ኸረ እኔ አላውቀውም ከርሱ ጋር መሆኑን ፈጽሞ አልሻውም ብዬ ሳልጨርሰው ዶሮውም መጮሁን በቅስፈት ጀመረው ወዲያው ጌታ ያለውን ቃሎቹን አስታወስኩ በፀፀት ወጥቼ በምሬት አለቀስኩ ዳግመኛ እድልን ማግኘት ፈለኩ አሁን እሱ ሙቷል እስኪሞትም ድረስ እልፍ ስቃይ አይቷል እኛም በጣም አዝነናል ረቢ በመሞቱ በጣም አልቅሠናል by sulamatiswa part2 ይቀጥላል😊😊የተመቸው በ Reaction @talent133 @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 12 авг.1 22974

    ዋዜማ በአክሳን አዳነ በምድር ስንኖር ለብዙ አመታት ቀኑ ሲፈራረቅ ሲሄዱ ሰአታት ምንም አይመስለንም መምጫው የቀረበ አንድም አልሰራንም ገና ቀናት ሳለ ድንገት ድንገት ይሄኛው ቀን ዋዜማ የኢየሱስ መምጫ የዚህ አለም ማብቂያ ቢሆንስ በድንገት እኛ ሳንዘጋጅ በድንገት ቢደርስስ ሙሽራችን ከደጅ ምን የሠራነውን ምን እንመልሳለን ምን ያደረግነውን ? በጌታ ፊት ቆመን ስለዚህ ወገኔ አይታወቅምና ቶሎ ቶሎ እንበል ቀኑ ሳያበቃ ለተፈጠርንበት አላማ እንዋል እጣችሁ እንዳይሆን አላውቃችሁም መባል ታሞ ሳንጎበኘው ታስሮ ሳንጠይቀው በኋላ ቀኑ ሲደርስ ምንድነው ምንለው ስለዚህ ተነሱ የጌታ ሰዎች ወንድሜ አታመንታ ከቶ አትሰላች እህቴ ተነሺ አንቺም ካለሽበት ጊዜው ሳያበቃ ተነሺ እንስራበት  @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 11 авг.1 6111110

    🙏✝️የማይነገር ውለታህ🛐 ይህ ነው ብዬ የማልገልፀዉ ሰማይ ምድር የከበደዉ በልቤ ታፍኖ መተንፈሻ ያጣዉ ሌላ ምንም ሳይሆን ያንተ ዉለታ ነዉ ምንም በሌለበት ደረቅ ምድረበዳ ያስገባኝ ፍቅርህ ነዉ አቅፎ ካንተ ጓዳ ጓዳህ ያማረ ነዉ ውበት የሞላበት አይገባም ነበር ይሄ ለኔ ህይወት ዛሬ ግን በቤትህ ራሴን አየሁት በላይ በዙፋኑ አንተ ባለህበት ታዲያ ምን ይባላል ለማንስ ይወራል አይገርምም ዉለታህ ከአይምሮ በላይ ነዉ ስራህ እንዴት ላዉራ ልንገርልህ ምንስ ብዬ ልደምድምህ የቃላት ክምር ፊደል የማይፅፍህ የማይነገር ነዉ ኢየሱሴ ዉለታህ በምንም በማንም የማልመልስልህ  @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • የምጓጓለትን ባውቅስ እንዴት ልሻው? መውደቅ ሆኖ ቀርቷል፤ ምኞት መጨረሻው። By Red-8 @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 10 авг.1 039124

    የበለጠ እንዳንወድቅ ትናንትን ኖረን=ዛሬን ሙተን፣ ነገን ሰንቀን=አሁኗን ቀብረን፣ ሄዱ ስንባል=ድጌ ተመለስን፣ አለፉ ስሉን=ወድቀን ተቀበርን፣ አቤቱ.... የበለጠ እንዳንወድቅ ስቃያችን መከራችን አታብዛ፤ መምጣትህ ካልቀረ እባክህን አይንዛዛ። Date 4/12/208 E.C ሶለን ጽፎአል (በድምቱ ከተማ) @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • New Challenge Accepted!! በየቀኑ አንድ ግጥም መጻፍ በአንድ ወር ወስጥ ሠላሳ ግጥም መግጠም ከዛም በሁለተኛው ወር ስድሳ ግጥም ለአንድ ሰው ይኖረዋል። ለመቀላቀል የምፈልግ በውስጥ አናግሩኝ ዛሬ ይጀመራል። በአራተኛው ወር መድብል እናደርጋለን።🤓😊 ጸጋችሁን አካፍሉ አሳድጉ😊 Inbox @S_o_L_e_N_y @S_o_L_e_N_y

  • 10 авг.1 68363

    የነፍሴ_ደዋሪ ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤ ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤ በደሳሳ ጎጆ፥ ሙላተ ማድጋ፤ በነጠፈ ተስፋ፥ ብርቱ ባለጠጋ፤ የሻገተውን፥ ፈጽሞ አለምላሚ፤ የተቆረጠውን፥ እንደአዲስ ገጣሚ፤ ከጥንት ጥንትን መስራች፥ ከዘላለም ዘላለምን ሰሪ፤ የህይወትን ትርጉም፥ የህይወትን ፍቺ፥ ብቻውን ቀማሪ፤ የሰማይ ሰራዊት እና የምድር አራዊት ደዋሪ፤ እውነተኛው ፈገግታችን፤ ሀዘን የለሹ ደስታችን፤ ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤ ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤ መቼ ነው መምጣትህ? መቼ ነው ምጻትህ? መችም እንደጥንቱ በረት አትወርድም፤ ዳግም ለእኛው፥ በእኛው አትዋረድም፤ ሰማይ እያወጋህ፥ ምድርም ሸሽጋህ፥ ጠባብ ደረት፤ አጭር ቁምጣ አያመጣህም። ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤ ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤ ልክ እንደሙሽሪት፥ ተጠናቃ ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ፤ በንጽህና፥ እንደምትናፍቅ፤ መቼ ነው፥ `ምትመጣው? መች አንተን፥ እንጠብቅ? ምራዊ ሳቃችን፤ ምታስፈነድቀን ህያው ተስፋችን፤ የምትናፍቀን አሜን እንደናፈቅንህ፤ አሜን እንደራብከን፤ ሳይቀዘቅዝ ለአንተ ያለን ንጡህ ፍቅር ታጥበን ነፅተን እስክትመጣ እንጠብቅህ።  @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 9 авг.1 034134

    /// " ተዘንግቷል ስምህ " /// ይኽ ሁሉ መከራ ፣ ይኼ ሁሉ ፍዳ፤ ለሰው ልጆች ፍቅር ፣ የተከፈለ እዳ፤ ለድህነት ነበረ ፣ እንዲኖር ተምሮ፤ ይበልጡን ከፋ እንጂ ፣ በደልን ጨምሮ፤ እንኳን ግርፋትህ ፣ ሊታየው መስቀሉ፤ ስምህ ተዘንግቷል ፣ አልኖረም በቃሉ፤ የከፈልከው አዳ ፤ መዳብ ሆኖ ዛሬ፤ ተዘንግቷል ስምህ ፣ እኔንም ጨምሬ፤ ጌታ በፍቅርኽ ነው ፣ የቆምነው በጸጋ ስራችን ከንቱ ነው ፣ አያወጣም ዋጋ። /// ስንታየሁ ሀብታሙ /// @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 9 авг.1 108711

    ልቤንማ ልፍራ የእግዜር ታላቅነት፣ እየተነገረው እንደልብህ ሆኖ ፣ አባቱን እያየው በቤትህ ከአንተ ስር፣ያደገው ይሄ ሰው ሕዝብህን ሊመራ፣ሊነግስ ተወዶ ክብርን በሱ ልትገለጥ፣ልታጸናው ደግሞ ይሄንስ ለማግኘት፣መቼ ተሯሩጦ ከእኩዮቹ መሀል፣እርሱማ ተመርጦ ። በድኳንህ ገባ፣መስዕዋትን ሰዋ አንተን አከበረህ፣ካሳብህ ተሰማማ ጠየከው መሻቱን፣የልቡን ፍላጎት በውስጡ ያለዉን፣ እውነተኛ ጩኸት። ከልቡ ሆነና፣ጥበብን ለመነ ማስተዋል እውቀትን፣ፍርድንም ጨመረ ፀሎቱም ተሰማ፣ባንተ ዘንድ ከበረ ሀብት ብልፅግናው፣ሌላም ተጨመረ ካሰበውም በላይ፣እጅግ ተከበረ እርሱን የሚመስለው፣እዳይኖረው ሆነ ከታየውም በፊት፣ከእርሱ ቀጥሎ ከኃላውም ደግሞ፣እሱን ተከትሎ ማንም እዳይመጣ፣በሱ ተመስሎ። ባንተም በህዝቡም ፊት፣ሞገስን አገኘ እንደዚህ አይነት ሰዉ ፣ ኧረ ኬት ተገኘ ባስደናቂ ፍርዱ፣ ሕዝቡን እየዳኘ ድብቁንም ሚስጥር፣ወዲያው እያገኘ። በዚህ ታላቅነት፣ዓለም ተደነቀ ያፉ ቃል ሊሰማ፣እጅግ ተናፈቀ አቤት ቃላት ምርጫ፣አቤት አነጋገር ይህን ሰዉ ለመስማት ፣ መጡ ከሩቅ ሀገር ነገስታት ጐረፉ ፣ ጠቢቡን አገኙ በጆሮ የሰሙትን፣በአይናቸው አዩ በልዩ ጥያቄ፣እውቀቱን መዘኑት በእቆቅልሽ ብዛት ፣ጥበቡን ፈተኑት እርሱ ጋ ደርሶማ፣ምን አለ ሚያስቸግር የቱም ጥበበኛ፣ቢያመጣ ሚስጥር ይፈታል ነገሩ፣ ይገኛል መፍትሄው ያየው ሰው በሙሉ፣ተደንቆ ነው ሚሄደው። መቼ በዚህ አበቃ !!! ቤትህን ሊሰራ፣ ባንተ ተመረጠ አባቱ ያሰበውን ፣እሱኮ ፈጸመ ከመቅደሱ የገባ ፣ፀሎቱ ተሰምቶ እውነተኛን አምላክ፣ያህዌን አግኝቶ ከሃዘኑ ወጥቶ ፣ ሊሄድ ተደስቶ። ከኖሩማ እንደዚ፣በሚያሰኘው ሕይወት የሰማይ የምድር፣ሞልቶበት በረከት ታዲያ ምን ያረጋል፣ መቼ ዘለቀበት ወርቃማው ዘመኑን፣ጭቃ ለጠፈበት። ልቡን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ፈጥኖ ሲያስኮበልል ለአንድ ሺህ ሰዎች፣ ከፋፍሎ ሲያድል 👑#ንጉሱ ሰለሞን👑 'ጅማሬው ሲያምር'፣በሚል ቃል ታለፈ ያ ሁሉ ክብር እኮ፣ በዜሮ ታጠፈ አወቅሁኝ እያለ፣በሚያየው ገመድ እዚያው ተጠለፈ ዳግም ላይነሳ ፤ ተዘረጋገፈ የራሱን አባክኖ፣ስለ አባቱ ቃል በንግስና አለፈ #እኛስ ምን እንፍራ ? ከልባችን ሌላ ፣ምን አለ ሚያስፈራ ሁሌ ሚያስቸግረው፣ሚለው አልገራ መፍትሄው ምንድር ነው?እንሁን ጥገኛ በእግዚአብሔር እንጂ፣አንቁም በእኛ እንደዚህ ከሆነ፣ጅማሬውም ያምራል ፍጻሜውም ደግሞ፣እጅግ ይተልቃል። @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 8 авг.1 168166

    ትውልድ አለ! ዘበት ሆነ ክብርን መጣል፤ ስጋት ፣ ስጋን እያሳሳው፤ ክፋት ኮራጅ በረከተ ፤ ፀጋ  ሚሸጥ እንደ ኤሳው። ፧ የኤልዛቤልም ቅሪት አካል ፤ አልተበላም በዓለም አለ ፤ ብሎ ሰማይ የሚዘጋ፤ ኤልያስስ ታዲያ የታለ ? ፧ እንዳልልህ በሰነፍ ቃል ፣ ትውልድ አለ የምትሰራው፤ ብድራቱን ተመልክቶ ፤ ነገና ሞት ማያስፈራው። ፧ በጓዳው ላይ በመንፈሱ፤ ጥዋት ማታ የሚቃጠል ፤ ፍቅርህ ልቡን አሸንፎት ፤ የቆረጠ ለመሰቀል ። ፧ እውነት ይዞ ሚመሽበት ፤ ወንጌልህን የማይለውጥ ፤ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ፤ ኤልዛቤልን ሚፈጠፍጥ ። ... @debi~isa @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 7 авг.2 100912

    ርዕስ:- እግዚአብሔር ትልቅ ነው ዘመን ሲሄድ በሌላ ሲተካ የሚሻረው በአዲስ እየተተካ ዘመን እየተቀየረ ሰውም እያለፈ የማያልፍ ግን አለ ሁሉ እያለፈ እርሱም እግዚአብሔር ነው በሌላ የማይተካ ስፍራውን የማይለቅ ነው ዘመናት ሲፈራረቁ ሰዓታት ቀናት አመታት እያሉ እርሱ ግን አለ በእነዚህ ሁሉ እንደ እርሱ ያለ ቢፈለግ በምድር ሰማይ ታጣ ታጣ እርሱን መሳይ ታላቅነቱ በምንም በማንም የማይተካ እርሱ ነው ሰማያትን በስንዝር የሚለካ የምድር ሕዝብ ለእርሱ እንደ ውሃ ጠብታ እርሱ ነው ከዋክብትን በየስማቸው የሚያውቅ በየተርታ ኦ ታላቅ ነው ይሄ ጌታ ለታላቅነቱ ሚዛን መስፈርያ የሌለው እርሱ ነው ሰማያትን ያለ ምሰሶ ያቆመው በእውነት እግዚአብሔር ድንቅ ነው በእውቀት የማይመረመር በሰው ስሙ ይባረክ የዚህ ድንቅ ጌታ ይድረሰው ታላቅ እልልታ በሆታ ምን እላለሁ ከማመስገን በቀር እርሱ ድንቅ ነው የማይመረመር አመልከዋለሁ ሁሌ ጠዋት ማታ እከተለዋለሁ ሁሌም ይሄን ጌታ @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber

  • 7 авг.1 149184

    የኔ ኢየሱስ፣ ካንተ የምደብቀው ድክመት የለኝም፤ 🙏 ሁሉ ነገሬ ይገባሃል። 🥺 የልቤ ጓደኛ፣ የውስጤን አዋቂ፣ 😥 ገመናዬን ሸፋኝ፣ ሚስጥሬን ደባቂ፤ 🥺 ማን አለኝ እንደ አንተ ሚሆንልኝ ለኔ? 😢 ኢየሱስ፣ አንተ ነህ ያለኸኝ ከጎኔ። 🥰 📖 አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ። (መዝሙረ ዳዊት 32፥7) @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber