ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ጅጅጋ
Статистикаይህ ይፋዊ የጅ/ር/አ/ወገ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ ዓ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ገጽ ነው፡፡ በዚህ ገጽ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡ - የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡ ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡https://t.me/@Amde hayimanot
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 89
- 1/48двое суток
- 101
- 1/72трое суток
- 110
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ስድስት በዚች ቀን ከቂሳርያና ከቀጰዶቅያ አገር የከበረች ኢየሉጣ ምስክር ሁና ሞተች ። ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብን ወረሰች ከታጋዮችም አንዱ በግፍ በላይዋ ተነሥቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿንም ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት ። ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት ። በልቧም እንዲህ አለች የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም ። ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች ። ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት ። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች ። ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለኢየሉጣ እንበይነ ምግባራ ሠናይ ። በውስተ እቶን ዘእብእዋ በውዴተ ብእሲ እኩይ ። እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ ። ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ ። አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ ። በዚችም ቀን የአባ ሲኖዳ ረድእ ቅዱስ አባ ዊፃ አረፈ ። እርሱም ከእግዚአብሔር ብዙ ምሥጢራትን የሰማና የአባ ሲኖዳንም ገድል እንደ አየና እንደሰማ የጻፈ ነው መልካም አካሔዱንም እንዴት እንደፈጸመ ከእርሱ ከአባ ሲኖዳ ሰማ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። እግዚአብሔርም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች መግደላዊት ማርያም አረፈች ። ከዘህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ አገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ አለች እስከ ቀበሩትም ድረስ አልተለየችም ። በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች ። መልአኩም እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል አላቸው ። ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው አላት ። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው ። ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች ። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀበለችው ። ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው ። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም በፍቅር አረፈች ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለመግደላዊት ማርያም ስማ ። ለኢየሱስ ዘርእየቶ እምሐዋርያት ቀዲማ ወለአንስት ሰላም ዘተሳተፋ ድካማ ። እንዘ ይትራወጻ ኀበ መቃብሩ ለፌማ ። እንበለ ያፍርሆን ዘሌሊት ግርማ ። ነሐሴ ፮ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ቅድስት ማርያም መግደላዊት (ከ፫፮ቱ ቅዱሳት አንስት) ፪.ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት (ዘቂሣርያ) ፫.አባ ዊጻ (የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር) ወርኀዊ በዓላት ፩.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም ፪.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ፫.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል ፬.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ ፭.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ፮.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ፯.ቅድስት ሰሎሜ ፰.አባ አርከ ሥሉስ ፱.አባ ጽጌ ድንግል ፲.ቅድስት አርሴማ ድንግል ጌታ ኢየሱስም:- ማርያም አላት ። እርሷ ዘወር ብላ በእብራይስጥ:-ረቡኒ አለችው ። ትርጉዋሜውም መምሕር ሆይ! ማለት ነው ። ጌታ ኢየሱስም:- ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ። ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሔደሽ .. ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው" አላት ። መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይሕንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች ። (ዮሐ ፳ ፥፲፮) ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን ። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን ። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን ። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል ። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን ። ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝ ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝ ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝
" http://tiktok.com/@amdehaymanot121 " ይህ የሰ/ት/ቤታችን የ tiktok አካውንት ነው ከላይ ☝️ ያለውን ሊንክ ተጭኖ በመግባትና የመደመር "+" ምልክቱን በመንካት ቤተሰብ ይሁኑ!!! ወዳጅ ዘመድዎን በመጋበዝ ሰንበት ት/ቤታችንን ይደግፉ። 🙏🙏🙏 እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
без подписи
በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ ። በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ. የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው ። (፪ኛ ቆሮ ፲፩፥፳፫) • ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን ። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን ። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን ። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል ። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን ። ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝ ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝ ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝
ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፭ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሔሴ አምስት በዚች ቀን ሌላው አብርሃም አረፈ ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ባለጸጎች ናቸው በተግሣጽና ፈሪሃ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት ። በአደገ ጊዜም ያለ ፈቃዱ አጋቡት እግዚአብሔርም ወደሚፈቅደው ይመራው ዘንድ ሲለምን ኖረ ። በሰባተኛውም ቀን በዐልጋው ላይ ሳለ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሳሥቶት ከጫጉላ ቤቱ ወጣ ብርሃን እየመራው ሒዶ ባዶ ቤት አግኝቶ በውስጡ ገብቶ ኖረ ምግቡን ከሚቀበልባት ከጥቂት መስኮት በቀር መዝጊያ ሠርቶ ደጁን ዘጋ ። ዓለምን ከተወ በዓሥረኛው ዓመት አባትና እናቱ ብዙ ጥሪት ትተውለት ሞቱ እርሱ ግን ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ በጾምና በጸሎት ተወስኖ እየተጋደለ ኖረ ከአንድ ዐጽፍና ሰሌን በቀር ምንም ምን ጥሪት አላኖረም እንዲህም ሆኖ ዐሥር ዓመት ተጋደለ ። እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አየ በአንዲት አገርም አረማውያን ነበሩ ከታናሾቻቸው እስከ ታላላቆቻቸው ወደ ሃይማኖት ሊመልሳቸው የሚችል የሌለ ። በአንዲት ቀንም አባ አብርሃምን ጳጳሱ አሰበው ብርታቱንና ብልህነቱንም አይቶ ቄስ እንዲሆንና እነዚያን አረማውያን እንዲመልሳቸው አስገደደው በግድ አስጨንቆም ቅስና ሾመው ። ወደዚያም ቦታ ደርሶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ እነዚያን አረማውያን እርሱን ፈጣሪያቸውን ወደ ማወቅ ይመልሳቸው ዘንድ በውስጧ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ። በአንዲት ቀንም ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ገባ ያን ጊዜ ጣዖታቱን ከመቀመጫቸው ጣላቸው የአገር ሰዎችም በአዩ ጊዜ ቁጣን ተመልተው አብዝተው ደበደቡትና ከአገር አበረሩት በጥዋትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲጸልይ አገኙት ። ሁለተኛም በገመድ አሥረው ወደ ከተማው ውጭ ጐትተው በላዩም አፈር ቆልለው እንዳይሞት ጥቂት መተንፈሻ ትተው አልፈው ከዚያ ሔዱ ። በእግዚአብሔርም ኃያል ተነሥቶ ሔደ ስለ መመለሳቸውም ሲጸልይ አገኙት በእንዲህ ያለ ሥራም እየተጋደለ ዐሥር ዓመት ኖረ ። የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ልባቸውን መለሰ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከታናናሾች እስከ ታላላቆች ድረስ ሁሉንም አጠመቃቸው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖትም ጸኑ ። ከዚህም በኋላ በሃይማኖታቸው መጽናታቸውን ባየ ጊዜ ከንቱ ውዳሴ እንዳያመጣበት ፈርቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አገሪቱንም በመስቀል ምልክት አማተበባትና ማንም ሳያውቅ ወጥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ ። ሰይጣንም በሚያስፈራው በብዙ ሥራ ይፈታተነው ነበር ቅዱሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኃይል አሸነፈው ። ጽኑ በሆነ ተጋድሎም ኖረ ያለ ዕንባም ሰዓት አላለፈችውም በጥርሶቹም አልሳቀም በከንፈሮቹም ፈገግ አላለም ስጋውን ቅባት አልነካውም ስጋውንና ደሙን ከሚቀበልበት ጊዜ በቀር ፊቱንና እግሩን አልታጠበም ። እናትና አባቱ በስድስት ዓመቷ ትተዋት የሞቱ እኅት ነበረችው ስሟም ማርያ ይባላል ዘመዶቿም ወደ አብርሃም አምጥተዋት ፈሪሀ እግዚአብሔር ሃያ ዓመት ሆናት ድረስ ትሕትናንም እያስተማራት በእርሱ ዘንድ አደገች ። ከዚህም በኋላ ሰይጣን ቀንቶባት ከአንድ መነኩሴ ጋር አፋቀራት ድንግልናዋንም አጠፉች ልብሷንና አስኬማዋን ለውጣ ወደ ሌላ አገር ሔደች ። አባ አብርሃምም በዚያች ሌሊት ታላቅ ከይሲ ርግቢቱን ሲውጣትና ጥቂት ቆይቶ ከእግሩ በታች ሲተፋት ራእይን አየ ። በማግሥቱም ማርያ ከቦታዋ ታጣች አባ አብረሃምም ደነገጠ ወደ እግዚአብሔርም ከብዙ ዕንባ ጋር ጸለየ እርሷን ያገናኘው ዘንድ ። ከጥቂት ወራትም በኋላ እኅቱ ያለችበትን አባ አብርሃም ሰማ ሰዎችም እንዳያውቁት የምንኩስናውን ልብስ ለውጦ ፊቱንም ተከናንቦ የወታደር ልብስ ለብሶ በፈረስ ተቀምጦ ወዳአለችበት አገር ሔደ ከዚያም ደርሶ ማርያ ወዳለችበት ገባ የመሸተኛንም ልብስ ለብሳ በአያት ጊዜ እጅግ አዘነ ነገር ግን እንዳትሸሸው እንድታውቀው አልሆነም ። ከዚህም በኋላ ለሚያገለግላት አሽከር ከማርያ ጋር የሚደሰትበት መብልና መጠጥ እንዲያዘጋጅ የወርቅ ዲናር ሰጠው ለርካሽ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ይመስላት ዘንድ ። ከራት በኋላም ወደ ውስጠኛው ቤት አስገባት በሩንም ዘጋ እጇንም ይዞ ራሱን ገለጠላት በአወቀችውም ጊዜ ደንግጣ እንደ በድን ሆነች ልጄ ሆይ አይዞሽ ከእግዚአብሔር በቀር ከኃጢአት ንጹሕ የሆነ የለም ነገር ግን ወደ ንስሐ ተመለሺ ወደቦታሽም ገብተሽ የቀድሞ ሥርዓትሽን ያዢ አላት እርሷም እሺ አለች ። በነጋም ጊዜም ወስዶ በፈረሱ አስቀመጣትና ደስ እያለው ተመለሰ እኅቱን ከሰይጣን እጅ ማርኳልና ወደቦታውም በደረሰ ጊዜ የቤቷን ደጅ ዘግቶላት ማቅ በመልበስ እየተጸጸተች የተጋድሎንም ሥራ እየተማረች በብርታቷና በተጋድሎዋ ያዩ ሁሉ እስቲአደንቁ ጸንታ ኖረች ። እግዚአብሔርም በዚህ ቅዱስ ሰው እጆች ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ አጋንንትን በማስወጣት በሽተኞችን በማዳን ከአንዲት ዓመትም በኋላ የማርያን ንስሓዋን አይቶ በሰባ ዘመኑ የተመሰገነ እግዚአብሔርን እያመሰገነ አረፈ ። ማርያ እኅቱም ከለቅሶ ጋር ትርኅምትን በማብዛት ቀንና ሌሊት እየተጋደለች ሌሎች አምስት ዓመታትን ኖረች ከዚያም በኋላ አረፈች ያዩዋትም በፊቷ ውስጥ ሰለአለው ብርሃን እግዚአብሔርን አመሰገኑ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን ለዘለአለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለአብርሃም ዘተሰደ ወተዘብጠ ። እምሕርትምና ወካህድ አረማውያነ እስከ ሜጠ ። ወነፍስ እኅቱ ፄዊዎ እምአፈ ከይሲ መሠጠ ። እስመ ኢጸግበ እምተጋድሎ እስከ ዕድሜሁ ሰለጠ ። መዋዕለ ዓመታት ፸ ኮናሁ ኅዳጠ። በዚችም ቀን የከበረ ተጋዳይ ወታደር ዮሐንስ አረፈ ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው እርሱም በከሀዲ በዑልያኖስ ሠራዊት ውስጥ ወታደር ሆነ ። ንጉሡም ከባልንጀሮቹ ወታደሮች ጋራ ላከው የክርስቲያን ወገኖችንም በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዛቸው ። እርሱም ለባልንጀሮች ጭፍሮች ክርስቲያኖችን እጅግ እንደሚጠላቸውና እንደሚጣላቸው ይገልጽላቸዋል በጭልታም ገብቶ በጎ ነገርን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል ያጽናናቸዋልም ። ሁል ጊዜም ይጸልያል ይጾማል ይመጸውታልም የቅዱሳንንም አኗኗር ኖረ ምስጉን እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለእርሱም ለጌታ ምስጋና ይሁን ። የቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ዕብል ለዮሐንስ ሐራዊ ። እምአብያጺሁ ዘኀብአ ሕገ ክርስቲያናዊ ። ለምእመናን ያሠኒ በይነ ይቀትል ወያደዊ ። ጸውዖ እንበይነዝ እግዚአብሔር ማሕየዊ ለከብካብ ሰማይ ድልው ለዝንቱ መርዓዊ ። በዚችም ቀን የደብረ ቢዘን አባ ፊልጶስ አረፈ ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለፊልጶስ እንተ ክህለ ያዕዱ ። ለዘጸውዖ ብእሲ ለውኂዘ ክረምት እምነ ሞገዱ ። ወእምኔሁ አብ እለ በመንፈስ ተወልዱ ። እንዘ ይዜንዉ ኃይሎ ወምግባረ ጽድቁ ይንዕዱ ። ስሙዓቲሁ ወጽአ ለዓለም በዐውዱ ። ነሐሴ ፭ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ቅዱስ አባ አብርሃም ገዳማዊ ፪.ቅድስት ማርያ እህቱ ፫.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ፬.አባ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን ወርኀዊ በዓላት ፩.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ፪.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም ፫.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፬.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ ፭.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ ፮.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
без подписи
ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፬ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አራት በዚች ቀን ከዳዊት ዘር የሆነ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ ንጉሥ አረፈ ። ከጻድቁ ንጉሥ ከዳዊት በኋላ እንደ ሕዝቅያስ ያለ በእስራኤል ውስጥ አልተሾመም ከዚህ ጻድቅ ንጉሥ በቀር ሁሉም ጣዖትን አምልከዋልና መሠዊያም ሠርተዋልና ። እርሱም በነገሠ ጊዜ ጣዖታትን ሰበረ መሠዊያቸውንም አፈረሰ ከነሐስ የተሠራውንም እባብ ቆራረጠ የእስራኤል ልጆች አምልከውት ነበርና እግዚአብሔርም ዘመነ መንግሥቱን እጅግ አሳመረለት በጎ ነገርንም ሁሉ ሰጠው ። ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዘመን የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም በዘመኑ እንደርሱ ያለ የሌለ ኃይለኛ ብርቱ የምድር ነገሥታት ሁሉ የፈሩትና የታዘዙለት ነው ። ሕዝቅያስም ከእርሱ ግርማ የተነሣ ፈርቶ አገሩን እንዳያጠፋ ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ላከለት ሰናክሬምም ደስ ብሎት ምንም ምን አልተቀበለም በእርሱ ላይና በልዑል እግዚአብሔር ላይ ተቆጥቶ እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያድናችሁ አይችልም በማለት የስድብን ቃል ላከ እንጂ ሁለተኛም በልዑል ስም ላይ ስድብና ቍጣ የተጻፈበትን ደብዳቤ ላከ ሕዝቅያስም በሰማ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ ለበሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ ። አቤቱ የእስራኤል አምላክ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ አንተም ብቻህን በዓለም መንግሥታት ላይ ንጉሥ የሆንክ አንተም ሰማይና ምድርን የፈጠርህ ልመናዬን አድምጥ ። ዐይኖችህን ገልጠህ ተመልከት ሕያው እግዚአብሔር አንተን እያቃለለ ሰናክሬም የላከውን ቃሉን ስማ ። ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም የተናገውን እንዲነግሩትና ስለርሱና ስለ ሕዝቡ ይጸልይ ዘንድ ወደ ኢሳይያስ መልእክተኞችን ላከ ። ኢሳይያስም ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ እንዲህ ብሎ መለሰለት ልብህን አጽና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ ሊሠራ እግዚአብሔር አለውና ። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የላከው መልአክ መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ የለኪሶም ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አገኙ የተረፉትም ከንጉሣቸው ጋራ ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ ። ሰናክሬምም ሊጸልይ ወደጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ልጆቹ አድራማሌክና ሶርሶር በሰይፍ መትተው ገደሉት ። ሕዝቅያስምከሰናክሬም እጅ ድኖ የተመሰገነ እግዚአብሔርን አመሰገነ ። በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ ለሞትም ደረሰ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስም ወደረሱ መጥቶ እግዚአብሔር እንዲህ አለ ትሞታለህ እንጂ አትድንምና ቤትህን ሥራ አለው ። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ እያመሰገነውም እንዲህ አለ አቤቱ በቀና ልቡና በዕውነት ሥራ በፊትህ ጸንቼ እንደኖርኩ ፈቃድህንም እንደፈጸምሁ አስብ ብሎ ሕዝቅያስ ፈጽሞ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰ ። ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ዐፀድ ደረሰ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው ሒደህ ለወገኖቼ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ያባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር እንዲህ አለ በለው ። ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ እስከ ሦስት ቀንም ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ ። በዘመኖችህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይቺንም አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ ። ሕዝቅያስም ኢሳይያስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር እንደሚያድነኝና እስከ ሦስት ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመውጣቴ ምልክቱ ምንድ ነው ። ኢሳይያስም እንዲህ አለው የተናገረውን ቃል ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምልክቱ ይህ ነው እነሆ ጥላው ወደ ዐሥረኛው እርከን ቢመለስ ምልክቱ ይህ ነው ። ሕዝቅያስም እንዲህ አይደለም የጥላው ወደ ዐሥረኛ እርከን መመለስ ቀላል ነው ። መመለስስ ከሆነ ፀሐይ ወደ ዐሥረኛው እርከን ይመለስ አለ ። ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፀሐይም ዐሥሩን እርከን ተመለሰ ። ሕዝቅያስንም የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈሩት እጅ መንሻም አገቡለት የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋራ እንዳለ አውቀዋልና ። በመንበረ መንግሥቱም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነግሦ ኖረ ። እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለሕዝቅያስ ዘጸለየ በሕቱ ። ዘተወሰከ ዘመኑ ወፈድፈደ እምኁልቁ እመኒ ሶቢሃ ተዐየርዋ ለጽድቁ ። በእደ መልአክ ሠራዊተ ፋርስ ኅልቁ ወለመልአኮሙ ቀተልዎ ደቁ ። በዚችም ቀን የከበሩ ዳዊትና ወንድሞቹ ከግብጽ ደቡብ ስንካር ከሚባል አገር ፊልጶስም በሰማዕትነት ሞቱ ። በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን እንደ በግ የጸጒር ልብስ ለብሶ በበረሃ የሚኖር አባ ማቴዎስ አረፈ ። እርሱም መርምኀናምን ያሳመነው ሣራንም ከለምፅዋ ያነፃት ነው ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ነሐሴ ፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ቅዱስ ሕዝቅያስ ጻድቅ (ንጉሠ ይሁዳ) ፪.አባ ማቴዎስ ገዳማዊ ፫.ቅዱስ ዳዊት ሰማዕት ወርኀዊ በዓላት ፩.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው) ፪.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ ፫.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት ፬.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል ። በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል ። የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው ። የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም ። በበጐ በረከት ደርሰህለታልና ። ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ ። ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም ። ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ ። በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው ። (መዝ ፳ ፩-፭) ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን ። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን ። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን ። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል ። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን ። ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝ ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝ ✝ http://tiktok.com/@amdehaymanot121 ✝
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
#ዜና_ቤተ_ክርስቲያን 👉 በዛሬው እለት በሶማሌ ሀገረ ስብከት የጅግጅጋ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ ፍሬ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት የ2018 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት የማጠቃለያና የካርድ መርሐግብር ያከናወነ ሲሆን በእለቱ የደብሩ አስተዳደሪ መልአከ ምህረት ቀሲስ ክብሬ እድሜአለም ፣ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ ላዕከ ወንጌል ሊቀ ዲያቆናት ንጋቱ አለሙ ፣ የሰ/ት/ቤቱ ሥራ አመራር አባላት እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል። በመርሐግብሩ ዝማሬ ና ግጥም በተማሪዎች ፣ የዓመቱ ሪፖርት በሰ/ት/ቤቱ ፀሐፊ ወጣት እሱባለው አለማየሁ ፣ በሥርዓተ ትምህርቱ ከ 1 - 3 ለወጡ የ 1ኛ እና የ 6 ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪዎች ሽልማት ና መልእክትና የምዝገባ ጥሪ በሰ/ት/ቤቱ ም/ሰብሳቢ ወጣት አቤል አካሉ ቀርቧል። በተጨማሪም የ 4ኛ ክፍል ተማሪዎችን አስተምሮ በአንድነቱ ምዘና ያሰጠ ሲሆን ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። በመጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ አባታዊ መልእክት አስተላልፈው የመርሐግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።✝✝✝ ✏️ዓምደ ሃይማኖት ሚዲያ
без подписи
без подписи