tgindex
ዲ/ን ዘማስያስ/@Masiyas

ዲ/ን ዘማስያስ/@Masiyas

Статистика

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ቻናል ነው። ማቴዎስ ፲፩፥፳፰-፴ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" +251918031244 @Geez44

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
11
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 758
−4 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
261
21 постов
Вовлечённость
9,5%
к подписчикам
Постов в день
1,6
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
109
1/48двое суток
124
1/72трое суток
134

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #ቢቆጠር ኖሮ በደሌ❤️❤️ ቢቆጠር ኖሮ በደሌ ቢቆጠር ኖሮ ኃጢአቴ ቢቆጠር ኖሮ በደሌ ቢቆጠር ኖሮ ኃጢአቴ እንዴት እቆም ነበረ በፊትህ አባቴ [፪] እስከነ ድካሜ ወደ አንተ መጥቼ ድንግዝግዙ ቀረ አየሁኝ አጥርቼ ትናንትናን ሳታይ በዛሬ መዝነህ ተቀብለኽኛል ፍሪዳህን አርደህ ወደ አንተ የመጣ ወደ አንተ የመጣ      ወደ ውጪ አይወጣ አዝ-----❤️❤️ እያገለገልኩ በጥቂቷ ትጋት አብዝተህ ስትሰጠኝ ጸጋህን ሳሰስት አንተ የወይን ግንድ እኔ ቅርንጫፍ ነኝ ከአንተ ከተለየው አንዳችም የሌለኝ ወደ አንተ የመጣ ወደ አንተ የመጣ      ወደ ውጪ አይወጣ አዝ-----❤️❤️ አሰናበትከኝ ብለህ አትበድል በሕይወት እንድኖር እየሰጠህ ዕድል እንደ ክሴ መዝገብ እንደኔማ ጥፋት ይገባኝ ነበረ መወገር መገፋት ወደ አንተ የመጣ ወደ አንተ የመጣ      ወደ ውጪ አይወጣ አዝ-----❤️❤️ ኃጢአትን እንጂ አንተ 'ምትጠላው ኃጢአተኛውማ የእጅህ ሥራ ነው ከቀራጮች አንዱ ደካማው እኔ ነኝ ቸርነትህ በዝቶ ይቅርታህ ያቆመኝ ወደ አንተ የመጣ ወደ አንተ የመጣ      ወደ ውጪ አይወጣ አዝ-----❤️❤️ ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ ከባቴ አበሳ ይኽው ዛሬም ቆምኩኝ በአንተ የተነሳ ማዕመረኩሉ የሰው ድካም አውቀህ በደሉን ሸፍነህ ሁሉን ታኖራለህ ወደ አንተ የመጣ ወደ አንተ የመጣ        ወደ ውጪ አይወጣ               አዲስ ዝማሬ ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ◈           🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺   መዝሙር ለወዳጅ ሼር ያድርጉ🙏

  • 📅 ቀን: ነሐሴ 7 📌 በዓል: ፅንሰታ ለእግዝእትነ ወተስእሎተ ቂሣርያ ወጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት ወልደቱ ለዮሴፍ ወልደ ራሄል ወናዖድ ንጉሠ ኢትዮጵያ — 📖 የነግኅ ምንባባት 📜 ምስባክ           መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡፡  ያበድሮን እግዚአብሐር ለአናቅጸ ጽዮን እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ፡፡           መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።           His foundation is in the holy mountains. The LORD loveth the gates of Zion more than all the dwellings of Jacob. መዝሙረ ዳዊት 85:1-2 📜 ወንጌል መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ..... ወንጌል ዘማቴዎስ 1:1- — ⛪ የቅዳሴ ምንባባት 📜 ምስባክ           ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ ወዘመሀርኮ ሕገከ ከመይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት ፡፡ መዝሙረ ዳዊት 93:12-13  📜 መልዕክተ ጳውሎስ           ወለቀዳሚትነ ደብተራ፡.... ዕብራውያን 9:1-ፍ.ም  📜 7ቱ መልዕክታት           እስመ ከመዝ ጽሑፍ ናሁ እሠይም.... 1 ጴጥሮስ 2:6-ፍ.ም  📜 ግብረ ሐዋርያት           ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ... ግብረ ሐዋርያት 10:1-ፍ.ም  📜 ወንጌል           ወበጺሖ ኢየሱስ ብሔረ ቂሣርያ..... ወንጌል ዘማቴዎስ 16:13-ፍ.ም  — 🙏 ቅዳሴ     ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) — መልካም ቅዳሴ!

  • አላምናቸው! "አላምናቸው ጓደኞቼን፣ ጓደኛዎች ዘመዶቼን፣ ያጋልጡኛል ቀን ጠብቀው፣ አይችሉትም ጉዴን ተሸክመው፣ ወረት አይቀይረው ጌታዬ፣ ዘለዓለም ምስጢረኛዬ፣ የልቤን አጫውተዋለው፣ ገበናዬን አሳይቼ!

  • እንስገድለት! "ስንጸልይ ስግደት ከሌለው እግዚአብሔርን እያመለክን አይደለም።" ዲብጋ

  • የሚያምነው! "አንተን ብቻ ነው ልቤ የሚያምነው።"

  • ለመጸለይ! "ለመጸለይ መፍትሔው መጸለይ ነው።"

  • "መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ባጠናን ቁጥር እንደ ክርስቶስ መናገርና መኖር እንጀምራለን!"

  • ወዳጆቼ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል! እንዲያውም አሁን ሊሆን ይችላል!

  • ተወዳጆች ሆይ! "አብዝታችሁ ዋጋ የከፈላችሁበት ቦታ ላይ አንሳችሁ ትገኛላችሁ።" ለምን?

  • 📅 ቀን: ነሐሴ 5 📌 በዓል: አብርሃም ካልእ ወዮሐንስ ሐራ ወአባ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን — 📖 የነግኅ ምንባባት _ ⛪ የቅዳሴ ምንባባት 📜 ምስባክ           ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ፡፡  ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ፡፡  ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ፡፡ መዝሙረ ዳዊት 17:43-44  📜 መልዕክተ ጳውሎስ           ወበእንተ ዝንቱ ሠመርኩ በሕማምየ.... 1ኛ ቆሮንቶስ 12:10-ፍ.ም  📜 7ቱ መልዕክታት           ወዛቲ ይእቲ እንተ ብነ ገጽ በኀቤሁ.... 1 ዮሐንስ 5:14-ፍ.ም  📜 ግብረ ሐዋርያት           ወቦ እለ ወረዱ እምብሔረ ይሁዳ፡... ግብረ ሐዋርያት 15:1-ፍ.ም  📜 ወንጌል           ወሀለዉ ይቀርብዎ  መጸብሐውያን..... ወንጌል ዘሉቃስ 15:1-ፍ.ም  — 🙏 ቅዳሴ     ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) ዓዲ (ወይም) ግሩም (ሠለስቱ ምዕት) መልካም ቅዳሴ!

  • እየጸለያችሁ ነው ? የውስጤን የምነግረው ሰው የለኝም ትላላችሁ ፣ ልስማችሁ የሚለውን አምላክ ግን ገፍታሁ ትሄዳላችሁ? የእናንተ ባልሆነች እስትንፋስ እየኖራችሁ የእስትንፋሳችሁን ጌታ ገሸሽ ትላላችሁ። ብቸኝነት በጣም እያጠቃችሁ ነው ፣ መጸለይ ግን ትልቅ ጥንካሬ እንደሚያመጣ አልተረዳችሁም። ብዙ ምሥጢራችሁን ስለ እናንተ ግድ ለሌላቸው ሰዎች በአደባባይ ታወራላችሁ፣ በድብቅ ሰምቶ በግልጽ ለሚመልሰው አምላክ ግን ዱዳ ትሆናላችሁ። ይህ መንገድ አያዋጣም ጸልዩ! እንጸልይ!

  • 4 авг.317115

    ይገርመኛል 2 !!! – ዝም ያለውን ሰው መቆስቆሳችን፣ ያልበደለንን መጉዳታችን፣ – የሥራ ደቦ ትተን የጠብ ደቦ መውደዳችን፣ – ሃይማኖትን በእምነት ሳይሆን በወኔ መያዛችን፣ – ስርቆትን እየተጸየፍን ነፍስ ማጥፋታችን፣ – በጽድቅ ሳይሆን በኃጢአት ዓይነት መጽናናታችን፣ – መብቱን ሰጥተነው ሳለ ከድሀ ምርቃት መጠበቃችን፣ – አገር እያፈረስን ቤት ለመሥራት መሯሯጣችን፣ – ጳጳስ እየሰደብን የእኔን ዲቁና አክብሩልኝ ማለታችን፣ – ጎሣችን እስኪመጣ ሃይማኖተኛ መምሰላችን፣ – ተገልብጠን ለመጣ ሁሉ ማዜማችን፣ – መንኩሰን ከሞትን በኋላ ጎሣ ያለን መሆናችን፣ – ዕድሜአችንን እየደበቅን ዕድሜ ስጠኝ ማለታችን፣ – መጸለይን ትተን የሰውን ኀዘኔታ መፈለጋችን፣ – ዕራቁት ተወልደን በካባ መኩራታችን፣ – ቆሻሻ ተሸክመን በሽቱ መመጻደቃችን፣ – እግዚአብሔርን እየጠራን ብቸኛ ነኝ ማለታችን። ይገርመኛል !!!

  • ይገርመኛል!!! • ያልገባንን ነገር ለመናገር መቸኮላችን፣ • ወቅታዊ እንጂ ዘላለማዊ ርእስ አለመፈለጋችን፣ • ሞታችንን ረስተን መግደላችን፣ • ስለማናውቀው ሰው ከሚያውቁት በላይ ክፉ ማውራታችን፣ • እያመሰገንን ተዋውቀን እየተሳደብን መለያየታችን፣ • ደመወዝ እያለን ጉቦ መፈለጋችን፣ • እኔ የወደድሁትን ብቻ ውደዱ ማለታችን፣ • ሟችን ረስተን ለገዳይ ማዜማችን፣ • ለሬሳ ዘር ማውጣታችን፣ • መርጠን ማልቀሳችን፣ • ነግ በእኔ ይደርሳል አለማለታችን፣ • ክፋትን በክፋት ማረማችን፣ • የማያልቅ ብቀላ ውስጥ መግባታችን፣ • በአንድ ክፉ ሚሊየኖችን ክፉ ማለታችን፣ • መኖር እየፈለግን ሌላውን እንዳይኖር ማድረጋችን። ይገርመኛል!

  • ይህንን መጽሐፍ እንድታነቡት እመክራለሁ።

  • ስለዚህ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል 118፥57-67 ያለውን በበቂ ማብራሪያ ዩቱዩብ ላይ ሰርቻለሁ ገብታችሁ እዩት። ሊንኩ ይሄው 👇👇 https://youtu.be/bmsNVkM0Joc?si=65U3J8SjpS1QzNfQ

  • ማርያም ሆይ ! የልብ አውቃው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን! የደስታ ጥጉ የፋሲካው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን! ሸሽጎ የሚያጎርሰው የሰጪው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን! የፍሬው የኢየሱስ እናት አበባ ማርያም ሆይ እንወድሻለን! ሁሉን ሳይዘነጋ የሚያስበው የመልካሙ የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን ! የድሆች ወዳጅ የተባለው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን ! ልማዱ ሰውን ማፍቀር የሆነው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን ! ላመኑበት የማይጠልቀው ፀሐይ የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን ! ከማለዳ ይልቅ የተዋበው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን! የረሀብ መድኃኒት የሆነው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን! የክፉ ዘመን መጠጊያ የሆነው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን! አንቺን የወደደ አንዱ አብ ቡሩክ ነው፣ ለእናትነት የመረጠሽ አንዱ ወልድ ቡሩክ ነው ፣ ያጸናሽ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቡሩክ ነው።

  • አገልግሎቱን ለማሳደግ ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ! ዲ/ን ዘማስያስ https://youtu.be/QTTzi19cxpw?si=TnSgqo_q1Dysb40T

  • https://youtu.be/bmsNVkM0Joc?si=65U3J8SjpS1QzNfQ

  • https://youtu.be/4HXJOzSNtQM?si=zelq-xztgemDgPGs

  • ስለ ዝናብ ጸልዩ! ስለ ዝናብ ጸልዩ! ስለ ዝናብ ጸልዩ!

ዲ/ን ዘማስያስ/@Masiyas — tgindex