tgindex
Life Coach Sammy - 𝐋𝐂𝐒

Life Coach Sammy - 𝐋𝐂𝐒

Статистика

በትምህርት ያወቅነውን፤ በልምድ ያካበትነውን ፤ አንብበን የተገነዘብነወን የምንጋራበት የመሐበራዊ ገፅ! https://www.youtube.com/channel/UC7SW1Mw3XJk9uwntTemaUMg?sub_confirmation=1

Последний пост
28 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
763
+1 Са 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
517
20 постов
Вовлечённость
67,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሰኔ የልደት ወሬ ነው! ልክ የዛሬ ወር ሰኔ 21 ደግሞ ወደዚች አለም የመጣሁበት ቀን ነው! እንደተለመደው ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 21 ለቀጣዮቹ 30 ቀናት እራሴን ከማንኛውም ማሕበራዊ ሚዲያ ገትቼ የግል ግምገማ እና የጥሞና ጊዜ የማደርግበት ወቅት ነው። ሰኔ... ለእኔ የልደት ወር ብቻ ሳይሆን፤ ያለፈውን ሕይወቴን እንደገና የምመለከትበት፣ የማንነቴን ጉዞ የምገምግምበት እና ለቀጣዩ ምዕራፍ ራሴን የማዘጋጅበት ወር ነው። እናም በመጪዎቹ 30 ቀናት ውስጥ የሕይወቴን ጉዞ ለመገምገም፣ ስህተቶችን ነቅሼ በማወቅ ከነሱ ለመማር፣ ያልጨረስኩትን በቶሎ ለማጠናቀቅ፣ የተሻለ ማንነት ለመገንባት፣ኀ ኀኀ ,.,.,.,.,.ከራሴ ጋር ጥልቅ ስብሰባ እቀመጣለሁ! ከማህበራዊ ገፅ ይዘቶች፣ ማስታወቂያዎች እና ከየቀኑ የማያቋርጥ የመረጃ ጫና ፋታ ወስጄ ስለራሴ፣ ስለቤተሰቤ፣ ስለልጆቼ፣ ስለወዳጆቼ እና ሾለ መጪው ሕይወቴ በጥልቀት ለማሰብ እድል አገኛለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በተቻለ መጠን ጊዜዬን፦ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ ለመጸለይ፣ ለመማር፣ እና ከልጆቼ፣ ከባለቤቴ፣ ከቤተሰቤ እና ከወዳጆቼ ጋር እውነተኛ ጊዜ ለማሳለፍ እጠቀምበታለሁ። በተለያዩ የ Social Media ገፆች ለምትከተሉኝ ሁሉ ከሰኔ 21 በኋላ በበለጠ ጥልቀት፣ በበለጠ ጥበብ፣ በበለጠ ጥንካሬ፣ እና በበለጠ ዓላማ፣ በየቀኑ የምለቃቸው የማህበራዊ ገፅ ይዘቶቼ በስፋት ይቀጥላሉ። እስከዚያው ግን…...ራሴን ለማግኘት ጊዜ እወስዳለሁ! በጣም አስቸኳይ እና አጣዳፊ ጉዳይ ካለ እጅግ ከላቀ ይቅርታ እና አክብሮት ጋር በእጅ ስልኬ መልዕክት መላክ እንደምትችሉ አሳውቃለሁ። እናም ውሳኔዬን እንደምታከብሩልኝ አልጠራጠርም! 🙏ሰላም ያገናኘን! ግንቦት 20 2018 ዓ.ም - ሣሙኤል ተክለየሱስ (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • የስኬት ቀመር! ትልቅ ህልም + ትጋት = ውጤታማነት ትልቅ ህልም + ስንፍና = ባዶ ቅዠት ትላልቅ ግቦች ስላሉን ወይም ትልቅ ህልም ስላለምን ብቻ ሳይሆን ግብ እና ህልማችን ላይ የምንደምረው ትጋት በትልቁ ውጤታማ ያደርገናል። 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ!      - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ይህ ምክር ለወጣቶች ነው! አብዝቼ ከወጣቶች ጋር እንደመስራቴ መጠን...የብዙ ወጣቶች ፍላጎት በሆነ መንገድ ሀብት ወይ ዝና ወይ ማግኘት መሆኑን እገነዘባለሁ። ወጣቶች ይህን መፈለጋቸው ክፋት የለውም እንደውም ይህ ልናበረታታው የሚገባ ጥሩ ነገር ነው። ችግሩ ብዙዎች ሀብትን እና ዝናን የሚፈልጉት በአቋራጭ እና ምቾት ውስጥ ሁነው መሆኑ ነው። መልሊ ሐቅ ደግሞ.... ወጣትነትህ የተረጋጋ ገቢ የምናገኝበት ሳይሆን፣ በንቃት የተለያዩ የገቢ ማግኛ መንገድ መሰረቶችን የምንገነባበት ወቅት መሆኑ ነው። ስለዚህ አጥብቀን እዚህ ላይ አናተኩር፦ ✅ የገቢ ኃይልን መገንባት ✅ የግል ብራንድ መገንባት ✅ ዲስፕሊን የለው ማንነትን መገንባት ✅ ከሁሉ በላይ እኛ ባንኖርም የሚሰራ ስርዓትን መገንባት የማይቋርጠው ገቢ ከምኞት ሳይሆን ከታላቅ ተጋድሎ በዝግታ፣ ሆን ተብሎ፣ በተደጋጋሚ ከሚገነባ ከስርዓት ይመጣል። ብዙዎች በመጀመሪያ ዋጋ ሳይከፍሉ ነፃነት ይፈልጋሉ፣ መጀመሪያ የሚሸጡት ልዩ ማንነት ሳይኖራቸው ገቢን ይፈልጋሉ፣ እንዴት መገንባት እና መስራት እንዳለባቸው ሳይማሩ የራሳቸውን ሲስተም እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ ቅዠት ነው ለምን ቢሉ ደግሞ ቀድመው በትጋት የፈጠሩት ሲስተም ወይም ስርአት ሳይኖራቸው "እነሱ ተኝተው ገንዘብ በአቋረጭ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ" መመኘታቸው ሞኝነት ስለሆነ ነው። ❗️ስለዚህ ወጣቶች ከቅዠቱ ንቁ 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ብዙ ሰዎች 𝐀𝐈 ለቴክኖሎጂ ሰዎች ብቻ እንደሆነ ያስባሉ። ....ይህ ፍፁም የተሳሳተ እሳቤ ነው! በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የAI ከፍተኛ ተጠቃሚዎች መካከል፦ ◉ አነስተኛ የንግድ ባለቤቶች፣ ◉ የፍሪላንስ ሾል የሚሰሩ ሰዎች፣ ◉ የተለያዩ የማህበራዊ የይዘት ፈጣሪዎች፣ ◉ አስተማሪዎች፣ ◉ የንግድ እና ማህበራዊ ሳይንስ አማካሪዎች፣ ◉ ተማሪዎች ወዘተረፈ ......ይገኙበታል ችግሩ አብዛኛው ሰው AI የሚመስለው ChatGPT ብቻ ነው! እናም ብዙዎች ChatGPT ላይ የዘፈቀደ ጥያቄዎችን (Random Questions) መጠየቅ ወይም የማህበራዊ ይዘት መፍጠርን እንደ ትልቅ ሾል ይቆጥሩታል። ሌሎች በAI ስኬትን የተሸናጁ ሰዎች ግን የ AI ስርዓቶችን (AI systems) እየገነቡ ነው፤ ይህንንም ስርአት በመጠቀም፦ ◉ የደንበኞች አገልግሎትን ማዘመን ◉ ድረ-ገጾችን መፍጠር ◉ የኦን-ላይን (Online) ትምህርቶችን መገንባት ◉ አዳዲስ የንግድ ስልቶችን ማመንጨት እንዲሁም አጠቃላይ ስኬታማ የማህበራዊ ገፅ መስተጋብሮችን ማስኬድ ችለዋል። ይህም AI ጥያቄዎችን ከመመለስ ባሻገር የስኬት ማስፈፀሚያ መሳሪያ (Success Tool) መሆኑን ማሳያ ነው። እንግዲህ ወሳኙ እና ትክክለኛው ጥያቄ ❓እኛስ AIን እንዴት እየተጠቀምንበት ነው? 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ትክክለኛ ቦታችን የት ነው? እኛ የምንጠቅመው በትክክለኛው ቦታችን ላይ ስንገኝ ብቻ ነው። ዶሮ በዓመት 300 እንቁላሎችን ትጥላለች፣ ንስር ደግሞ 3 እንቁላሎችን ብቻ ትጥላለች። ነገር ግን በዶሮ እንቁላሎች መሃል የተጣለ የንስር እንቁላል ጫጩት ሁኖ ቢፈለፈል ጭሮ የሚበላ እንጂ በሮ የሚያድን መሆን ይሳነዋል። እናም ይህንን እንማር ...ክህሎታችን፣ እውቀታችን፣ ችሎታችን እና ልምዳችን የሚጠቅመን በትክክለኛው ቦታ ላይ ስንጠቀመው ብቻ ነው። 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ!      - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • መልስ ለመስጠት ሳይሆን ነገሩን ለመረዳት ማድመጥ! ይህኛው ዘመን ስለፈለግነው ጉዳይ በቀላሉ ብዙ መረጃ ማግኘት እየቻልን በጥቂት ጥራዝ ነጠቅ እውቀት ላይ በእርግጠኛነት ውሳኔ ይመንወስንበት ዘመን ሁኗል። ለምሳሌ ይህንን ፅሁፍ ብዙ ሰው Read More....የሚለውን ተጭኖ ጠቅላላ የፅሁፍን ይዘት ላያነበው ይችላል። ❓እርሰዎስ? .........እያነበቡ ከሆነ ልቀጥል በቀደመው ዘመን አንድ ሰው ሾለ ሮም ማወቅ ከፈለገ ሮም መሄድ ነበረበት በዚህኛው ዘመን ግን ባለንበት ሁነን በእጃችን በያዝነው ስልካችን ማወቅ እና መረዳት ስለምንፈልገው ጉዳይ በዝርዝር እና በጥልቀት የፈለግነውን መረጃ ማግኘት እንችላለን። ነገር ግን ችግሩ መረጃ እና ማስረጃዎቹን የመመርመር እና በአግባቡ የመረዳት ጉዳይ ነው። በዚህኛው ዘመን አብዛኞቻችን ተቃራኒ ርዕዮተ ዓለሞችን በመግባባት ሳይሆን በመሸናነፍ ለመፍታት ስንተጋ እንገኛለን። የሚፎካከሩ ፍላጎቶች በመቻቻል ሳይሆን በመበላለጥ ጉልበተኝነት ላይ የተመሰረተ እየሆነ ነው። የሰሉ ትችቶች፣ ጠንካራ አስተያየቶች የተሻለውን ለመፍጠር ሳይሆን የሚሞክረውን ለመሾር ከሆነ ዋል አደር ብሏል። በጥቅሉ ይህኛው ዘመን......የራስ ፍላጎትን፣ ውስጣዊ ስሜትን፣ ልዩነቶችን ጮክ ብሎ በመናገር፣ በፍጥነት በመከላከል፣ የበለጠ በኃይል በማረጋገጥ መፍታት ይቻላል የሚል እምነት የነገሰበት ነው። ሆኖም ግን የጋራ መግባባት እና እድገት ባልተግባብቶም ሽቅድድም ውስጥ ሳይሆን በመተሳሰብ ውስጥ ይነግሳል። እመኑኝ  መልስ ለመስጠት ሳይሆን ነገሩን ከስረ መሰረቱ ለመረዳት ማዳመጥ ስንጀምር ያኔ ነገሮች መሾመር መያዝ ይጀምራሉ። ማዳመጥ ግምቶችን ያስቀራል። ማዳመጥ የአክብሮት ምልክት ነው። ማዳመጥ እምነትን ይገነባል። ማዳመጥ ለሌላው ሰው ከንግግራችን በላይ ብዙ ሀሳብን ይነግራል። እናም ሐቀኛ ውይይቶች በመናገር ሳይሆን በመደማመጥ ውስጥ ይገነባሉ። ተነጋግሮ ለመተማመን ቁንፅል ሀሳብ ይዞ መከራከር ማለት አይደለም፤ በክርክር ውስጥ ድል የለም። ለማስረዳት ከመሽቀዳደማችን በፊት ነገሩን በጥልቀት ለመረዳት በትኩረት እና ዲሲፕሊን በአፅንዖት እናድምጥ። መናገር ካለብን ንግግራችን ውስን ይሁን...ምክንያቱም አንድ ጊዜ ብዙ መናገር መግባባትን ይገድላል....አብዝቶ ማዳመጥ ግን እምነትን ይገነባል። 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ!      - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • 16 мар.1 280414

    የምናልመው ሕይወት በአጋጣሚ አይመጣም! ይልቀንስ ጠንካራ፣ ብልህ እና የበለጠ ዲሲፕሊን ያለውን ማንነታችንን ይፈልጋል። ያ ደግሞ በአንድ ጀምበር አይፈጠርም.....በእያንዳንዱ ቀን በሚኖረን ትጋት እና ጥረት በገነባናቸው ከትላንት የተሻሉ ልማዶች፣ ከውድቀት እና ስህተቶቻችን መማር በቻልንበት ከፍታ እንዲሁም እራሳችንን በራሳችን ለማሳደግ በግል የእድገት ጉዞ በጓዳችን እራሳችን ላይ በሰራነው ማንነት ላይ ይመሰረታል። ዛሬ የምናደርጋቸው እያንዳንዱ ትናንሽ ውሳኔ ነገ የምንሆነውን ማንነት ቀስ በቀስ እየቀረጸው ይሄዳል። ማልደን ጠዋት ነቅተን የሚኖረን የቀኑ ዝግጅት፣ ለዛሬው ምቾት ሳይሆን ለነገው እድገት ብለን የምንወስዳቸው አስቸጋሪ ምርጫዎች፣ ማንም በማይመለከትበትን ጊዜ ለራስ መርህ ተገዝተን በዲሲፕሊን የምናደርገው መሻሻል፣ ነገሮች አስቸጋሪ በሚመስሉበት ጊዜ ለመቀጠል የሚያስችል እቅም የፈጠርንበት ልኬት፣ ሁሉም የተሻለውን የወደፊቱን ማንነት እንድንገነባ ይረዱናል፤ ስለዚህ ፍጹም የሆነውን ጊዜ፣ ምርጡን አንድ ዕድል ወይም ጠንካራውን ተነሳሽነት በፍፁም አንጠብቅ። ዛሬ ያንን ሰው ባለን ነገር መገንባት እንጀምር...በትለቁ ሳይሆን በትንሹ ለትልቅ ውጤት እንትጋ....ዛሬ የምንጀምረው አንድ ልማድ፣ አንድ አዲስ እወቀት፣ አንድ እርምጃ ላይ ትኩረታችንን እናድርግ። ይህንን ማድረግ ከቻልን ሌላ ሰው ሳይሆን የነገው ማንነታችን ያመሰግነናል! 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • 🇪🇹 አደዋ 🇪🇹 የጥቁር አናብስት የድል አንባ፣ የትንኩኝ ባዬች አርማ፣ የእብሪተኞች መቃብር፣ የፅናት ልክ የድል በር፣ የአምባገነኖች መደምሰሻ፣ የክፉዎች ሸር መርከሻ፣ የመሪ ጥበብ ውጤት ማሳያ፣ የህዝብ እምነት መለኪያ፣ ባቀለሉት ልክ የማይቀል፣ ባረከሱት ልክ የማይፈርስ፣ የክብራችን የሞገሳችን ወጋ፣ የባርነትን ጨለማ በነፃነት ፋና ያነጋ፣ ያለመበረዛችን....ያለመከለሳችን ምህኒያት፣ የታሪካችን ሁሉ ቁንጮ አደዋ ናት - ሣሙኤል ተክለየሱስ

  • አንዳንድ ጊዜ...ዝ'ም እንበል! አንዳንድ ጊዜ መናገር የምንፈልገውን ነገር ሳንናገር ብንቀር ይሻላል! አንዳንድ ጊዜ የውስጣችን ስሜት፣ የሀሳባችን፣ የፍላጎታችን በንግግራችን ሳይሆን በልተነገሩ ቃላትችን ውስጥ ይገለጣሉ። አንዳንድ ጊዜ እውነት በማስረዳት ውስጥ ሳይሆን በዝምታችን ውስጥ ትነግሳለች። አንዳንድ ጊዜ ከንግግሮች ሁሉ በላይ ዝምታችን ለአንድ ሰው ያለንን ጥልቅ ስሜት አብዝቶ ይናገራል። አንዳንድ ጊዜ ለምንወደው ሰው መልካም ምኞት ከመመኘት በላይ ለልሾ የተያዘ የዝምታ ፀሎት ዋጋ አለው። አንዳንድ ጊዜ ሌሎች እንዲሁኑ የፈለግነውን ሌሎች ከሚያውቁት ይልቅ እግዚአብሔር ብቻ ቢያውቀው ይሻላል። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ብዙ ከመናገር ተቆጥበን አብዝተን ዝም እንበል! 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ሁሉም ሰው.... 1.ሁሉም ሰው ነገሮች እንደሚሻሻሉ ተስፋ ያደርጋል፣ ነገር ግን የተሻለ እንዲሆን የተሻለ መስራት አለብን፣ 2. ሁሉም ሰው እውቀት እንዲኖረው ይፈልጋል፣ ነገር ግን እውቀትን ለማግኘት ማንበብ እና መማር ያስፈልጋል፣ 3. ሁሉም ሰው ስኬታማ ለመሆን ተስፋ ያደርጋል፣ ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን በወጥነት፣ በዲሲፕሊን እና በፅናት መትጋትን ይጠይቃል፣ 4. ሁሉም ሰው ደስተኛ ለመሆን ይመኛል፣ ነገር ግን በሁለቱም አጋጣሚ አመስጋኝ መሆን እና ከሁሉ በላይ የራስ ሰላምን መምረጥ ያስፈልጋል፣ 5. ሁሉም ሰው አንድ ቀን ሀብታም እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋል፣ ነገር ግን ሀብትን ለማግኝ ዛሬ መቆጠብ፣ በእቅድ ላይ የተመሰረተ ኢንቨስት ማድረግ አለብን፣ 6. ሁሉም ሰው ሌሎች እንዲወዱት ይፈለጋል፣ ነገር ግን ተወዳጅ ለመሆን መጀመሪያ ያለስስት ፍቅርን መስጠት ይጠይቃል፣ 7. ሁሉም ሰው ክብርን ይመኛል፣ ነገር ግን በታማኝነት እና ሌሎችን በማክበር መኖር ያስፈልጋል፣ 8. ሁሉም ሰው ጥሩ የወደፊት ሕይወት እንዲኖረው ተስፋ ያደርጋል፣ ነገር ግን ዛሬ ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ ማድረግ ይጠይቃል፣ 9. ሁሉም ሰው ነፃ ህይወትን ተስፋ ያደርጋል፣ ነገር ግን ከመጥፎ ልማዶች ባርነት መላቀቅ አለብን፣ 10.ሁሉም ሰው በታሪክ እንዲታወስ ይፈልጋል፣ ነገር ግን ተጽዕኖ የሚያሳድር ሕይወትን ዛሬ መኖር ይጠይቃል፣ ............ይቀጥላል 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • እየሞከርክ ነው? ግን በመጀመሪያው ሙከራህ አታሸንፍም! የመጀመሪያው ሙከራህ ሳይሳካ ሲቀር ድል አኔ ጋር አይደለችም ብልህ ተስፋ እንዳትቆርጥ....ብቻ ሙከራህን ቀጥል። ምናልባት የመጀመሪያውን ድል ለማጣጣም ደጋግሞ መሞከር ያስፈልጋል.......ይህ የጭንቅ ምጥህ ደግሞ አንድ ቀን እድልን ይውልዳል.... ያቺ አንድ ቀን ግን በጭራሽ በቀላሉ አትገኝም...... የንተን የየቀን ትጋት፣ የአንተን የየቀን ልፍት፣ የአንተን የየቀን በፅናት ተስፋ ሳይቆርጡ መሞከር ትሻለች። በእዚያች በመጨረሻዋ ሰዓት በስኬታማነትህ ስትወደስ ከድልህ ባሻገር ያለውን ስቃይ ግን ሰዎች አይመለከቱትም .....ግን አንድ ነገር እወቅ በጓዳህ የተዋደቅከውና ያሳለፍከው እልክ አስጨራሽ ትግልህ ምንጊዜም ለአዳባባዩ ስኬትህ መሰረት ነው። ከብዙ ሙከራህ በኋላ ያንተ የሚሆነው ስኬትህ እንቅልፍ ያጡት አይኖችህ፣ የገረጣው የፊትህ ቆዳና የደነደነው መዳፍህ ውጤት ነው። ስለዚህ ሀልጊዜም ይህንን አትዘንጋ ወደ ፊት በምታደርገው ጉዞ ከፊትህ ሊያደናቅፉህ ከኋላህ ደግሞ ሊጠልፉህ የሚሞከሩ  አይጠፍምና በፅናት እና በትዕግስ እለፋቸው። 'እፍ' ብለው ሊያጠፉህና ብርሃንህን ሊያደበዝዙት ቢፈልጉም ይልቁንስ የበለጠ ደምቀህ ብሩህ ሆነህ ማብራትህን ቀጥል። ......አዎ ሞክር....አንዴ ሳይሆን ደጋግመህ ሞክር እመነኝ በዚህ ሁሉ እልህ አስጨራሽ ፈተና ውስጥ ይህን ሁሉ የምታደርገው ደግሞ ስለምትችል ሳይሆን መሆን ስላለበት ነው! እናም ሞ ክ ር! ከወደቅክ....ለመነሳት ሞክር ከቆምክ ....ለመራመድ ሞክር ከተራመድክ....ለመገስገስ ሞክር እየገሰገስክ ከሆነ.....ለመሮጥ ሞክር ከሮጥክ....ለመብረር ሞክር ብቻ ተስፋ ሳትቆርጥ፣ በፅናት ሞክር! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ህይወታችንን ለምን እናወሳስበዋለን? ያልገባን ጉዳይ ካለ - እንጠይቅ ያልተመቸን እና ያልወደድነው ጉዳይካለ - እንናገር የሚያስፈልገንን ነገር - እንጠይቅ የናፈቀን ሰው ካለ - እንደውልለት መገናኘት የፈለግነው ሰው ካለ- እንጋብዘው ሌሎች እንዲረዱን ከፈለግን - ነገሩን እናብራራው ብቻ አንድ ህይወት ነው ያለን... ቀላል እናድርገው! 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ፍቅር ያሸንፋል! ፍቅር መስዋእትነት ነው፤ ፍቅር አመስጋኝ ነው፤ ፍቅር ይቅር ባይ ነው፤ ፍቅር ራስን መስጠት ነው፤ ፍቅር መተማመን ነው፤ ፍቅር መከባበር ነው፤ ፍቅር ማስተዋል ነው፤ ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ፍቅር ቁርጠኝነት ነው፤ ፍቅር ታማኝ ነው፤ ፍቅር ደጋፊ ነው፤ ፍቅር ከራስ ወዳድነት ነፃ መሆን ነው፤ ❤️ፍቅር ሁሌም አሸናፊ ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • https://youtu.be/-efAJ3KIh94?si=gIwtK93_99rgazrc

  • ሶስት ጠቃሚ ምክሮች:- ❶ ጥቂት እንናገር፤ ከምንም በላይ ውጤቶቻችን ይናገሩ፣ ❷ የበለጠ እናድምጥ፤ ካልሰማን መማር አንችልም፤ ካልተማርን ደግሞ ማደግ አንችልም፣ ❸ ትኩረት ይኑረን፤ ነገሩን በትኩረት ስንመለከተው... ያኔ ሁኔታው ​​​​ይበልጥ ግልጽ ይሆንልናል። 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • ምላጭ ምን ስለታም ቢሆን ዛፍን መቁረጥ አይችልም፤ መጥረቢያ ምን ጠንካራ ቢሆን ግን ፀጉር መቁረጥ አይችልም። ሁሉም በቦታው እና በጊዜው ሲሆን የተሻለ አቅምን ይፈጥራል! ጌዜ ለኩሉ! 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • የስሜት ብስለት (Emotional Intelligence) ያለው ሰው መገለጫዎች፦ ❶ ቅድሚያ በሚሰጣቸው እና በአለም ፍላጎቶች መካከል ያለውን ልዩነት አበጥሮ ይለያል፣ ❷ ከትላንት ስህተቶቹ ተምሮ በራስ መተማመን እና ጽናትን በመሻሻል ይገነባ፣ ❸ በይቅርታ ያምናል፣ ከሁሉ በላይ ለልሹ ይቅር ይላል፣ ❚ እንዴት ተስፋ እና አመስጋኝ መሆን እንዳለበት ያውቃል፣ ❺ ጉድለቶቹን አውቆ አጥብቆ ልሹ ላይ ይሰራል፣ ❻ በቀን ተቀን ሰርክ ህይወቱ ትርጉም የሚሰጡ ጉዳዬች ላይ ብቻ ለማተኮር ጊዜውን ይሸልማል፣ ❼ አሳዛኝ፣ ተስፋ አሰቆራጭ የህልውና መዋቅሩን አፍርሶ ተስፈኛ፣ የፅና ማንነትን ይገነባል፣ ❽ ፍቅር ክህሎት እንጂ ስሜት እንዳልሆነ ይገነዘባል እናም መተማመንን፣ ግልፅነትን፣ ልግስና እና ጾታዊ ግንዛቤ ጠንቅቆ ያውቃል፣ ❞ ከሁሉ ነገር በላይ ሰው መሆንን ያስቀድማል። 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ

  • ትልቅ ህልም + ሼል = ስኬት ትልቅ ህልም + ስንፍና = ባዶ ቅዠት ትላልቅ ግቦች ስላሉን ወይም በትልቁ ስላለምን ብቻ ሳይሆን ህልማችን ላይ የምንደምረው ትጋት በትልቁ ውጤታማ እንድንሆን ያስችለናል። 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • 8 ማስተካከል የሚገቡን ጉዳዬች፡- 1. ለራሳችን ቃል እና መርህ ታማኝ መሆን፤ 2. አዋቂ ለመምሰል ከመታገል ይልቅ ያልገባንን እና ያልተረዳነውን በመጠየቅ መማር፤ 3. በቀላሉ ትኩረታችንን ከሚከፋፍሉ ነገሮች መራቅ፤ 4. ነገሮች ወደፊት ቀላል ይሆናሉ ብሎ ለይደር ከማስቀመጥ ይልቅ ዛሬ እና አሁን ነገሩን መጀመር፤ 5. መሰረታዊ ነገሮችን መረዳት እና መሰረታዊ ነገሮችን ማድረግ አንድ አድርጎ ማመንን መተው፤ 6. እርዳታ መጠየቅ ማለት አቅመ ቢስ መሆን ነው ከሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ወጥተን መተጋገዝን መልመድ፤ 7. ብዙ ነገር ጀምሮ አንዱንም ካለመጨረስ ይልቅ አንድ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተን ማከናወንን መልመድ፤ 8. ለተፈጠረው የህይወታችንን ምስቅልቅል ሌሎችን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ለልሾ ሀላፊነት መውሰድ፤ ❓እርሶስ ማስተካከል አለብን የሚሉት አንድ ወሳኝ ነገር ምንድን ነው? በ Comment መስጫው ላይ ያጋሩን! 🙏 ይሔው ነው! #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! - Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

  • "5 ወሳኝ የስኬታማ ሰዎች መገለጫዎች" 1. በትልቁ ማሰብ፦  ስኬት የሚለካው በጅማሬው ሳይሆን ፀንተን በተጓዝንበት ርቀት ልክ ነው። በትልቅ ማሰብ፣ ነገርግን በትንሹ መጀመር፣ አናም ደግሞ ውጥኑ እስኪሳካ መፅናት የስኬታማነት ቁልፍ ነው። 2. እንቅፋት ሳይሆን እድሎች፦ ተግዳሮቶችን እንደ እንቅፋት ሳይሆን እንደ አጋጣሚዎች መመልከት መቻል፤ የነቃ አስተሳሰብን ካጎለበትን ተግዳሮቶችን (Challenges) እንደችግር ሳይሆን መፍትሄዎችን በማፍለቅ የጋራ ተጠቃሚነትን (Mutual Benefits) መፍጥር የምንችልበትን አጋጣሚ ይፈጥርልናል። 3. እራስ ላይ ኢንቨስት ማድረግ፦ ወጥነት ባለው እራስን የማነፅ ጉዞ ለስኬታማነት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ዕውቀትና ክህሎቶችን እራሳችን ላይ ኢንቨስት ማድረግ ከቻልን ሁሌም በመሻሻል ውስጥ እንሆናለን። 4. ከምቾት ቀጠና መውጣት፦ የምንፈልገውን ለማግኘት የማንፈልገውን መስራት የግድ ነው፤ በአደባባይ ለመሸለም ደግሞ በጓዳ መልፋት አይቀሬ ነው። 5. አሁን መጀመር፦ ጊዜ በጣም ውድ የሆነው ሀብት ነው። ያሰብነውን ለመጀመር ዛሬ ከነገ በእጅጉ የተሻለ ነው እና ትኩረታችን የነገውን ስኬት በዛሬ መጀመር ውስጥ መሆን አለበት። #ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ! -Samuel Tekleyesus (የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)