tgindex
Mulualem’s View

Mulualem’s View

Статистика

በውሳኔ አሰጣጥ፣ በስትራቴጂ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና በክርስትና ሃይማኖት ዙሪያ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሠረተ እምነት ላይ በመመሥረት) ሃሳቦችን አጋራለሁ።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 189
+4 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
924
21 постов
Вовлечённость
42,2%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
391
1/48двое суток
448
1/72трое суток
483

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • “ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ፤ ኀጥኣን ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ ግን ሰው ይሸሸጋል።”ምሳሌ 28፥13።

  • ሙሴ በዜግነት ግብጻዊ፤ ያውም በግብጽ ምድር በፈርዖን ቤተመንግስት በክብር ያደገ፤ ሕይወቱንም ግብጻዊ ልዕልት ያዳነችው ቢሆንም ፥ ሲያድግ ግን የፈርዖን የልጅ ልጅ ከመባል ይልቅ ከሚገፉት ወገኖቹ እስራኤላዊ ጋር መቆጠርን መረጠ። ፈርዖን ቤተመንግስት እየዋለ እና እያደረ ፥ እየወጣ ግን የወገኖቹን መከራ ያይ እና በክንዱም ሊረዳቸው ይጥር ነበር። ከሚገፉት ግፍዖን ጋር መቆም፣ ዜጎች የሆንም ቢሆን ትላንት የዚህ ዛሬ የሚሰቃየው ስደተኛ ታሪክ ተካፋዮች ነበር እና ፥ እንደ ሙሴ የመቆርቆር ልባችንን እንዳናጣ። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የተገፉት አምላክ ተብሎ ለመጠራት የሚወድ ነው። ዜግነት ከሚሰጠን የውሸት የደህንነት ስሜት (sense of safety) ይልቅ የስደተኞች ስቃይ ተካፋይ መሆን በእጅጉ ይልቃል። ይሄ መከራ ደግሞ ይቆማል። እንዴት የሚለውን ባናዋቅም።

  • እሥራኤላውያን ወደ ግብጽ ተሰደው ከሄዱ በኋላ አራት መሠረታዊ ሂደቶችን ተሻግረዋል፤ (ምን አልባት ስደት ላይ ያሉ ሰዎች ከእነዚህ ሂደቶች ዓይኖችን አለመንቀል ጥሩ ነው)። 1) ግብጾች በደስታ ተቀበሏቸው። እስራኤሎችም ጠንክረው ሰሩ፣ ተባዙም፥ አጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱንም ሞሏት፤ 2) እሥራኤሎች ለግብጽ በዮሴፍ በኩል ያደረጉትን ታሪክ የማያቅ፣ እስራኤሎች መብዛታቸው እና መጽናታቸው ብቻ የታየው ትውልድ ተነሳ። ይሄም ትውልድ ሊወርሱን ይችላሉ ብሎ ፈራ። በዚህም ብዙ መከራ አበዙባቸው። ሁሉንም ነገር አከበዱባቸው። ባሮች አደረጓቸው። ነገር ግን እስራኤሎች አሁንም በዙ። ጠነከሩ። 3) ይሄ የባርነት ፖሊሲ ለውጥ ሳያመጣ ሲቀር፤ የግብጽ ንጉስ በድብቅ አዋላጆችን ጠርቶ የድብቅ የዘር ማጥፋት እንዲካሄድ አዘዘ። ይሄም አልተሳካም። ዘጸዓት ምዕራፍ አንድ እንደሚነግረን፤ የእስራኤል የመባዛት ፍጥነት ከግብጾች በብዙ እጥፍ ፈጣን ነበር። 4) በመጨረሻ ድብቁ ሳይሰራ ሲቀር፤ ይፋ የሆነ የዘር ማጥፋት ታወጀ። ሁሉም ግብጾች የሚያስፈጽሙት ፖሊሲ ወጣ። ከድብቅ ወደ ይፋ።

  • ሁለት ግብዣ አውቃለሁ። አንደኛው ከአመጹ ጋር እንድንተባበር፣ ከክህደቱ ከሚመነጭ ፍሬ ጋር ማዕዱን እንድንቆርስ ጋብዞናል። ምክንያቱም አመጽ እንኳ የሌሎች ተካፋይነት ሲኖረው ደስ ይለዋል። ክህደቱን ሌሎች ሲቋደሱት ደስታውን ይጨምርለታል። ሌላኛው ግብዣ ግን እኛ ላይ ያተኮረ ነው። የዘላለማዊው ደስታው ተካፋይ እንድንሆን ጠራን። በእርሱ፣ በአባቱ እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለውን ልዩ ፍቅር ለኛም ሊያካፍለን በመካከላችን ተገኘ። ያለ መቀናናት በመካከላቸው ያለው ፍቅር እና ሕብረት ተካፋይ እንድንሆን ሞትን ሳይቀር ስለ እኛ ተቀበለ። የዚህ ግብዣ ተካፋይ ለመሆን እሻለሁ። ንጹሁ ነውና በንጽህና ብቻ መቅረብ የሚቻለው ግብዣ ጋር እቀርብ ዘንድ የእርሱን ምህረት እሻለሁ። እጠበኝ እነጻለሁ።

  • 7 авг.898641

    እሳት የሆነውን በሆድ ያቀፈች፣ ፈጣሪን ለዘጠኝ ወር በጠባብ ማሕጸን የተሸከመች ፥ ፍጡር፤ ኦ ጌታ እኮ ነው ብለው ሐዋርያት የተደነቁበትን አልፋና ኦሜጋን ሥጋዋን ያጋራች ድንግል ማርያምን በጸሎት በጾም ለምታስቡ ሁሉ መልካም የፍልሰታ ጾም።

  • 7 авг.855162

    በስቶክ ማርኬት ውስጥ ትልቁ ልዩነት (በስኬት እና በውድቀት መካከል) ትዕግስት ነው ይላሉ እንደ ወረን በፌት ያሉ አዋቂዎች። ለብዙ ጊዜ ይሄ ትዕግስት ቀናት ወይም ቢበዛ ወራት ነበር የሚመስለኝ። በኋላ ስረዳው ግን ይሄ ትዕግስት ለካ የጊዜ ብቻ አይደለም። አንዴ ጥሩ ነው ብላችሁ የገዛችሁት ቢዝነስ ሲወድቅ፣ አሁንም ሲወድቅ፣ አሁንም ሲወድቅ ዝም ብሎ የመመልከትም ትዕግስት ነው። ከዛ አንድ ቀን ከወራትም ሆነ ከዓመት ወይም ሁለት ዓመት በኋላ በእጥፍ አድጎ ታይቷሏችሁ። ከዛ እንደ ገና በእጥፍ። ከዛ አሁንም በሚገርም እጥፍ አድጎ። ሌላኛው ትዕግስትም በዚህ ሰዓት ነው። ተቻኩሎ ያለመሸጥ ትዕግስት። ድሮ ሲወድቅ ስላያችሁት አሁን ትንሽ ከፍ ሲል ፈጥናችሁ ያለመሸጥ ትዕግስት። ዋናው ሥራ ትክክለኛውን ቢዝነስ መምረጥ ብቻ ነው። ከዛ ትዕግስት ሥራውን ይሰራል። ይሄ ሀሳብ እውነት ቢሆንም፣ የኔ ዓላማ ግን ስለ ስቶክ ማርኬት መጻፍ አይደለም። የዛ ትዕግስት ጥበብ እንዴት በሌላው የየዕለት ሕይወታችን ውስጥ እንደሚሰራ ማሳየት እንጂ። ግፍ ሲሰራ ታያላችሁ። ከዛ አቤት ትላላችሁ። ግፍ የሚሰራ ግን አሁንም በግፍ ላይ ግፍ እየጨመረ፣ ምንም አለመከሰቱ ደግሞ የበለጠ ሞራል እየሰጠው ይቀጥላል። የክፋት አለመሸነፍን የሚያዩ ሰዎች በዚህ ሰዓት ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። እንደውም እጅ ሊሰጡ እና ከክፋት ጋር ሊተባበሩ ይችላሉ። ከዛ ያቺ አንድ ቀን ከተፍ ትላለች። እጅግ ጥቂቶች ብቻ በጽናት የጠበቋት። ከዛ ያ መውደቅ ቀስ እያለ ይጀምራል። ያ ቀስ እያለ መውደቅ የጀመረው የግፍ ተራራ ከዛ ባንዴ ይደረመሳል። በዚህ ሰዓትም ሌላ ትግስት ያስፈልጋል። ናፖሊዮ እንዲህ ብሎ የተናገረለት ትግስት “Never interrupt your enemy when he is making a mistake"

  • 6 авг.753171

    "እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገር ልጅ ይሁንላችሁ፥ እርሱንም እንደ ራስ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።" ኦሪት ዘሌዋውያን 19፥34። ይሄ በብሉይ ኪዳን ለአይሁድ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው። ፍቅርን አስመልክቶ አዲስ ኪዳን ደግሞ እንዲህ ይላል "እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።" 1ኛ ዮሐ 3፥16። (ሚኒሶታ ውስጥ ነፍሳቸውን ለስደተኞች አሳልፈው የሰጡትን እንዳየነው።) አይሁዶች በግብጽ መጻተኛ ሆነው ነበር። ስደተኞች ነበሩ ለአራት መቶ ዓመታት። እናንተ የስደተን መራራነት፣ ባይተዋርነት ታውቃላችሁ እና ሌሎች ሰዎች ተሰደው ወደ እናንተ ሲመጡ ልክ እንደ ሀገር ልጅ ቁጠሩት። እርሱ ብቻ ግን አይደለም የተባሉት። "እንደ ራሳች ሁም ውደዱት" ጭምር እንጂ። ክርስቲያን ነኝ ብሎ ፥ ስደተኛን እንደ ራሱ የማይወድ ፥ መጤን እንደ ራሱ ወገን የማያይ ለብሉይ ኪዳን የበቃ አይሁድ እንኳን አይደለም ክርስቲያን ሊሆን ይቅርና። ይሄ ቃል ዛሬ ራሳቸውን አይሁድ ነን ብለው ሌሎችን ግን ከመሬት የሚያፈናቅሉ፣ በግፍም የሚገዱሉትን ሁሉ እናንተ አይሁድ አይደላችሁም ብሎ ይከሳቸዋል። በዩሐንስ ራዕይ "አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ " እንደሚለው ፥ ይሄን የኦሪትን ትዕዛዝ ያልጠበቀ፣ በግብጽ የነበረውን ስደት እና መከራ አስቦ፣ በእነርሱ ላይ በጀርመን ናዚዎች የተፈጸመባቸውን፣ በብዙ ክፉ ነገስታት የደረሰባቸውን መከራ አስበው ይሄን በሌሎች ላይ ላለማድረግ የማይጠነቀቁ ሰዎች አይሁድ ነን ቢሉ ራሱ አይሁድ አይደሉም። እነዚህ ትዕዛዞች ሁሉ አንድ ሰው ተሰዶ በመጣበት ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ሊሰጡት የሚገባውን ክብር እና ጥበቃ የሚገልጹ ናቸው። ዛሬ መጤዎች ከሀገራችን እስከ አሜሪካ በስም ክርስቲያን ነን በሚሉ ክርስቲያን ግን ባልሆኑ ሰዎች የሚደርስባቸውን ግፍ እያየን ነው። እግዚአብሔር ይሄን ያያል። ማንም የዘራውንም ያንኑ ያጭዳል።

  • 5 авг.6802810

    ነጻነት ማለት የአንተ ግብረ መልስ በሌሎች ላይ ሳይወሰን (depend ሳይሆን) ሲቀር ነው። ለምሳሌ አንድን ሰው የምትወደው ስለሚወድህ ብቻ ከሆነ ፥ የመውደድ ነጻነት የለህም ማለት ነው። ምክንያቱም ያንተን መውደድ የሚቆጣጠረው ሌላኛው ሰው ነው። እርሱ ለአንተ መልካም እስከሆነ ድረስ ብቻ ነውና መልካም የሆንከው አንተ የእርሱ ባሪያ ነህ። እርሱ በተለወጠ ሰዓት አንተም ስለምትለወጥ የአንተን ባህሪ አንተ ሳይሆን ሌላኛው ሰው ነው እየተቆጣጠረው ያለው። ስለዚህ ነጻነት የለህም። ስሜቶችህ ለሌሎች ባሪያ ናቸው። አዕምሮ የሌሎች ባሪያ ነው። ለዚህ ነው ነጻነት በሕግ ብቻ የሚቆመው። ለምሳሌ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ" (You shall love your neighbor) የሚለው ሕግ ትዕዛዝ ነው። ሕግ ነው (You Shall)። በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውስጥ ያለው መውደድ የታዘዝነው ሕግ ነው። በዚህም ይሄ ትልቅ ነጻነት ነው። እንዴት? ምክንያቱም አንድ ሰው ቢጠላህም ትወደዋለህ። ቢወድህም ትወደዋለህ። ቢገልህም ትወደዋለህ። የሌላ ሰው ግብረ መልስ፣ ለአንተ የሚሰጠው መልስ አይደለም እንድትወደው የሚያደርግህ። ሕጉ እንጂ። አንተ ከሌላ ሰው ስሜትም ሆነ ከራስህ ፍላጎት ነጻ ነህ። በዚህ ሕግ ምክንያት ፍጹም ነጻነት ተጎናጸፍክ። ያም ነጻነት ለሁኔታዎች ያለመገዛት ነው። ሌሎች አሁን አንተን በፍጹም ሊቆጣጠሩህ አይችሉም። ምንም ቢያደርጉህ ባልጀራህን ውደድ በሚለው መሠረት ትወዳቸዋለህ። ያም ከእነሱ ነጻ አወጣህ። በተመሳሳይ በማህበራዊ ሕይወት ተሳትፏችሁ ሕግ ካላችሁ ነጻ ትሆናላችሁ። ያም ነጻነት ሰዎች ምንም ቢሰድቧችሁ ክፋትን በክፋት አለመመለስ ነው። ስድብን በስድብ አለመመለስ። ባርነት ማለት ለሌሎች ስሜት መገዛት ብቻ አይደለም፣ መልካም ያልከውን ባህሪ በሌሎች የክፋት ባህሪ ምክንያት መለወጥም ነው። የጠላትህ ትልቁ ስኬት እርሱን መምሰል ነው ይባላል። የሌሎችን ባህሪ መቆጣጠር አትችሉም። የራሳችሁንም ባህሪ ለሁኔታዎች አሳልፋችሁ ከሰጣችሁ ፥ የሁኔታዎች ባሪያ ትሆናላችሁ። ከዚህ የሚያድነን ሕግ ነው። ለምሳሌ ሕጉ "ክፋትን በክፋት አትመልስ" የሚል ከሆነ ፥ "ለዚህ ሰው ምን ልመልስለት?" የሚል ጭንቀት ውስጥ እንኳ አትገቡም። ባሪያ ልትሆኑ ይቅራና ፥ ጭንቀት ራሱ አይኖርባችሁም።

  • አንድን ነገር የምትፈትነው ሊወድቅ ይችላል ብለህ ካሰብክህ ብቻ ነው። እንደማይወድቅ የምታውቀውን ነገር አትፈትነውም። እንደሚወድቅም እርግጠኛ የሆንክበትን ነገር ለአንተ አትፈትነውም። ምን አልባት ተፈታኙን ከጠቀመው ብለህ ካልሆነ( ያለበትን ደረጃ እንዲያውቅ ካልፈተንከው በቀር)።ለዚህ ነው ፍጹም ያመንከውን የማትፈትነው። የተጠራጠርከውን ብቻ ነው የምትፈትነው።

  • 4 авг.756171

    ብዙ ጊዜ ሰዎች ሕግን ከባርነት እና ጭቆና ጋር ያያይዙታል። ወይም ነጻነት ማለት የሕግ ወይም የገደብ አለመኖር ይመስላቸዋል። ይሄን ስል ግን ትክክለኛ ወይም ለክፋት ያልቆመን ሕግ ማለቴ ነው። እውነታው ግን ሕግ ነው ነጻነት። ሕግ በሌለበት ነጻነት የለም። ለምሳሌ ለምንድነው አሜሪካን የነጻነት አገር የምንላት? ምክንያቱም ሕግ ስለሚከበርባት ነው። የሕግ በሁሉም ላይ መከበር ነው አሜሪካንን በአንጻራዊነት የነጻነት አገር እንድንል ያስቻለን። ሕግ ነው በሕግ ፊት ሁላችንንም እኩል ያደረገን። ወይም ናችሁ ያለን። በሕግ ፊት እኩል መሆንን ያጎናጸፈን ራሱ ሕግ ነው። ሕግ በሌለበት ያለው ባርነት ነው። ያውም አረመኔያዊ።

  • https://x.com/NBCNews/status/2084414060037095599

  • 3 авг.848263

    ሰዎች በማስመሰል ብዙ ሊያልፉ ይፈልጋሉ። እውነተኛ ፍቅር ከሌለህ በቃላት እና በቴክኒካል ንግግሮች ለማለፍ ትጥራለህ። እውነተኛ እውቀት ከሌለህ በማነብነብ እና በሽምደዳ ለማለፍ ትጥራለህ። እውነተኛ ርጋታ ከሌለህ በብልጭልጭ ነገሮች ለማለፍ ትጥራለህ። እውነተኛ መንፈሳዊነት ከሌለህ በመቅለስለስ ለማለፍ ትጥራለህ። እውነተኛ ጀግንነት ከሌለህ በፉከራ ለማለፍ ትጥራለህ። ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል "ጐለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።" በተመሳሳይም እኔም ጐለመስሁ ፥ ይሄንንም አየው ከእውነተኛ ፍቅር፣ እውቀት፣ ርጋታ፣ መንፈሳዊነት፣ ጀግነንት በላይ ማስመሰል በጣም አድካሚ ነው። ማስመሰል የሚፈልገው ኃይል፣ ማስመሰል የሚያሶጣን ኢነርጂ እውነተኛ ከመሆን በላይ ነው።

  • 2 авг.892231

    አንድ በጣም የተሳሳተ ትምህርት አለ። በክርስቲያኖች ዘንድ። ለምሳሌ ከዚህ በታች ያለውን ዜና ተመልከቱ። ይሄን አመለካከት ብዙ ክርስቲያኖች ሳይቀሩ ይጋሩታል። ብዙ ክርስቲያኖች ሳይቀር እንዲህ ሊያምኑ ይችላሉ። ምንም እንኳ ከአይሁድ ወገን የሆነው ቅዱስ ጳውሎስ አይደለም በአይሁድ እና በአሕዛብ መካከል ይቅርና፣ በሴት እና በወንድ መካከል እንኳ በክርስቶስ ልዪነት የለም። ሁሉም በእርሱ አንድ ናቸው። ቢልም። ገላትያ 3፥28። የሚገርመው በብልዩ ኪዳን ዘመን (ድህረ ክርስቶስ) ሳይቀር የዚህ እስራኤላዊ ትምህርት ስህተት ነው። በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር ልክ ሊሆን ይችላል። እስራኤላዊያን በእግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው። የቃል ኪዳኑ ሕዝቦች ናቸው። ነገር ግን አይደለም በአዲስ ኪዳን በብልዩ ኪዳን ሳይቀር ከእግዚአብሔር ርቀው ክፋት ባደረጉ ሰዓት እግዚአብሔር ለፍጹም ጨካኞች አሳልፎ ሰጥቷቸዋል። በአዲስ ኪዳን ደግሞ ክርስቶስን ያላመነ በሙሉ ባለማመኑ ተፈርዶበታል። ይሄ ለሁሉም የሚሰራ ነው። ትልቁ ነጥብ ግን አምልኮተ እግዚአብሔርን ከእስራኤል ውጪ ማስፋፋት ባልታዘዘበት ዘመነ ብሉይ ሳይቀር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሚራራ መሆኑን በግልጽ በትንቢተ ዮናስ ተጽፎ አለ።ዮናስ የአይሁድ ነቢይ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ሰዎች ይቅርታን ከጠየቁት የሚምር አምላክ መሆኑን ያውቅ ነበር። እነዛ ሰዎች አሕዛብ ቢሆኑ እንኳን። በትንቢተ ዮናስ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ እንዴት የሚራራ የፍቅር አምላክ መሆኑን ለዮናስ ነግሮታል። በአዲስ ኪዳን ደግሞ ይሄ የበለጠ ነው። ምክንያቱም ሞቶልናል። በደሙ ነው የጠራን። ስለዚህ የዚህ እስራኤላዊ ትምህርት በሁለቱም ዘመናት ፍጹም ስህተት ነው።

  • Integrity, Love, and the Knowledge of God!

  • 29 июл.1 299282

    መንፈሰ ብርቱ የሆነ ሰው ሁሉን ይችላል። መንፈሱ የተሰበረን ግን ማን ያጸናዋል? ምሳ 18፥14።

  • 24 июл.1 702131

    “…but in heaven it is of course the case that no work wins approval unless it is a work of love.”

  • 23 июл.1 777151

    የኃይሌ ገብረሥላሴን የፕሮፐርቲ ታክስ (property tax) ንግግር ስሰማ አሜሪካ እንዴት ከፌዴራሊዝም ተጠቃሚ እንደሆነች ማሳየት ፈለኩኝ። የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ ወቅቶች ከወሰኗቸው ምርጥ ውሳኔዎች ውስጥ አሜሪካ የተዋቀረችው ከፍተኛ ነጻነት እና በብዙ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን ባላቸው ስቴቶች ነው የሚል ነው። ይሄም አሜሪካንን የብዙ ጉዳዮች መሞከሪያ አድርጓታል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይሄን የሀሳቦች ላብራቶሪ ይለዋል። ለምሳሌ በአሁን ሰዓት አሜሪካ ውስጥ ሶሻሊዝም እየተሞከረ ነው። በኒው ዮርክ ከተማ። በተመሳሳይ ደግሞ እንደ ቴክሳስ እና ፍሎሪዳ ያሉ ስቴቶች ጥብቅ የሆነ የነጻ ኢኮኖሚ መርሕን እየተከተሉ ነው። ካሊፎርኒያ በቢሊየነሮች ላይ ታክስ ለመጣል ሕግ አርቅቃ ለሕዝበ ውሳኔ ተቀጥሯል። ፕሮፐርቲ ታክስ ያላቸው ስቴቶች አሉ። ፕሮፐርቲ ታክስ በጣም ዝቅተኛ ወይም ምንም የሆነባቸው ስቴቶች አሉ። ለምሳሌ ለብዙ ጊዜ የደቡቡ የአሜሪካ ክፍል በጣም ወግ አጥባቂ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ፖሊሲዎችን ተከተለ። ይሄም ለጊዜው ጥሩ ነው ተብሎ ባንዳንድ ነጮች ተወደሰ። ከሠላሳ እና ሃያ ዓመት በኋላ ግን ኢስት እና ዌስት ኮስቱ (ሊብራል የሆኑት) በኢኮኖሚ ሲመነደጉ፣ ደቡቡ በጣም ደሃ ሆኖ ቀረ። ዛሬ ድረስ በብዙ የደቡቡ ስቴቶች ዝቅተኛው ደሞዝ ሰባት ወይም አምስት ዶላር ነው በሰዓት። ካሊፎርኒያ እና ሌሎች ሊብራል ስቴቶች ወደ ሃያ ዶላር የተጠጋ ወይም ከዛ በላይ ሲሆን። ከሃያ ዓመታት በኋላ ኒውዮርክ ወይም ቴክሳስ ትክክል ሆነው እናገኛቸዋለን። ግን አሁን ሁለት ጽንፍ ፖሊሲዎችን እያየን ነው። አሜሪካ ግን በዚህ ትጠቀማለች። ምክንያቱም ዓየር ላይ ባለ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ሳይሆን መሬት ላይ የመሞከርን ዕድል ይሰጣል። ለሀገራችንም ይሄን ነው የምመኘው። የፌዴራል ክልሎች ትልቅ ስልጣን (autonomy) እንዲያገኙ ማድረግ ጥሩ ነው። ኦሮሚያ እና ሲዳማ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ነድፈው፣ ባለሀብቶች የሚያዋጣቸው ጋር በመጨረሻ ይሄዳሉ። ከሃያ ዓመት በኋላ የትኛው ፖሊሲ አዋጭ እንደሆነ እናያለን። ለምሳሌ ዝቀተኛ ደሞዝ ያደረጉ የደቡቡ ስቴቶች ካምፓኒዎችን የጠቀሙ መስሏቸው ነበር። ግን ከነዛ ስቴቶች ታለንት (ሙያ) በገፍ ተሰደደ። በዚህም ካምፓኒዎች የሚመሰረቱት ታለንት ያለባቸው ስቴቶች ሆነ። ምንአልባት የማምዳኒ ኒውዮርክ ከውጪ ሲያዩት ሶሻሊስት ሊመስል ይችላል። ግን የማህበረሰቡ ጤና፣ የወንጀል መጠን መቀነስ፣ ለኢሚግራንት ምቹ መሆን፣ ለኑሮ ተስማሚነቱ ከፍ ካለ ፥ ኒውዮርክን ተመራጭ ሊያደርጋት ይችላል። ይሄን በጊዜ ሂደት ብቻ ነው ፈትነን ማወቅ የምንችለው። አሁን ፍልስፍና ተኮር (የፖለቲካ ውግንና ላይ አተኩረን) ክርክር ነው የምናደርገው። በርግጥ ይሄን የአሜሪካ ፌዴራሊዝም ስናገር ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የፖለቲካ ባህል እና የሰላም እጦት አንጻር ማወራው ቅንጦት ሊመስል ይችላል። ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ክልሎች የበለጠ ስልጣን ወደ ማግኘት ሊሄዱ የመቻላቸው ዕድል አሁን እንደውም የበለጠ ይታየኛል። ትግራይ ለፌዴራል መንግስቱ አልታዘዝም ማለት ወደፊት አሁን አሜሪካ ላይ የምናየው ዓይነት ነጻነት (የክልል autonomy) ሊያመጣ ይችላል። ከዛ ከክልሎ ጋር የሚኖረው ትስስር ኢኮኖሚያዊ የመሆን እድሉ እየበረታ እና በክልሎች መኃል ጠንካራ ውድድር ሊፈጥር ይችላል።

  • 23 июл.1 238252

    “ጐለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።”መዝ 37:25

  • 22 июл.1 389531

    ክርስትና ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ እጅግ ብዙ ሰማዕታት አሰቃቂ ዋጋ ከፍለዋል። ቤተክርስቲያን ፊት ስትቆሙ በሰላም ለመቆም እና ዛሬ በድፍረት ክርስቲያን ብለን ለመጠራት ያስቻሉንን እነዛን ሰማዕታት አንርሳ። በጣም ታላቅ በሆነ የደም ክፍያ ላይ ቆመን ነው ዛሬ በነጻነት ማምለክ የቻልነው።

  • 21 июл.1 528201

    ብዙዎቻችን በዓለም ያለው ነገር በነጠላ (without synergy) የሚንቀሳቀስ ይመስለናል። ዊልሰን ኮንሲሊየንስ በሚለው መጽሐፉ "በዚህ ዓለም ውስጥ ሁላችን የተለያየ ነጠላ እውቀት ስላለን ወይም ሙያችን አንድ ብቻ ስለሆነ የነገሮች ትስስር አይታየንም" ይላል። ለምሳሌ ስድስት እውር ሰዎች አንድን ዝሆን ቢነኩት፣ የዝሆኑን ጆሮ የነካው ትልቅ ቅጠል ወይም ፋን ሊመስለው ይችላል። ኩንቢውን የነካው ዛፍ፣ ጭራውን የነካው ገመድ እና ሁሉም የየራሳቸው ምልከታ እና ትርጉም ሊኖራቸው ይችላሉ። ምክንያቱም ማየት አይችሉም። ዝሆን ከዚህ በፊት አያውቁም። እኛም በዚህ ዓለም ላይ ባብዛኛው እንደዚህ ነን። አንዱ ነገር ከአንዱ ጋር ያለው ዝምድና አይታየንም። "የኳስ ጌም ውጤት ከፖለቲካ ጋር ምን ያገናኘዋል?" ልትሉ ትችላላቹ፣ ወይም "አማዞን ላይ ያለው ቃጠሎ ሀዋሳ ላይ ካለው ዝናብ ጋር ምን ትስስር አለው?" ልትሉ ትችላላቹ። ምን አልባት ክርስቶስ በተሰቀለ ሰዓት የሰማዩ መጥቆር ብራዚል ያለው ማህበረሰብ ሌላ ትርጉም ሰጥቶት ነበር። እንጂ አንድ ሰው በግፍ በእስራኤል ምድር ስለተሰቀለ ነው ሰማዩ የጠቆረው፣ ከዋክብት የረገፉት የሚል ላይኖር ይችላል። ቢኖርስ ማን ሰምቶት። ጅል ከመባል በቀር። ዊልሰን በዚህ ምድር ላይ ብዙዎቻችን እንደ ዕውሮች ነን የሚለው ለዚህ ነው። "ይሄ ዓለም በሚገርም ስምረት እና ሕግ ነው የሚተዳደረው" ይላል ይሄ ባይሎጂስት። ለኛ ለእውሮች ይሄ ዓለም ተራ ቀውስ (chaos) ነው የሚመስለን፤ በአይዛክ ኒውተን ዘመን የነበሩ ሰዎች መብረቅን እግዚአብሔር ሲቆጣ ብቻ የሚልከው ነው ብለው ነበር የተረዱት። ኒውተን ግን ሲቪላይዜሽንን የቀየረ ጥያቄ አነሳ። "ምንአልባት ይሄ መብረቅ የሆነ የተፈጥሮን ሕግ እየተከተለ ቢሆንስ?" ማለትም ከቀውሱ በታች ሥርዓት እና በአግባቡ የሚሰራ ሕግ ታየው። ዊልሰን እንዲህ ይላል በኢንላይትመንት ዘመን የነበሩ ሰዎች ትልቁ ልዩነታቸው "Reality makes sense" ማለት መጀመራቸው ነበር ወይም የእውነታው ዓለም የሚገዛለት ሕግ እና ሥርዓት እንዳለው መረዳት መጀመራቸው ነው ይላል። ዊልሰን አንድን ነገር እስከ ፍጻሜ ካጠናነው ሁሉንም ነገር የማወቅ አቅማችንያሳድጋል ይላል። (ሁሉንም እናውቃለን አይደለም ከፍ ይላል እንጂ)። በዚህ ዓለም ያለ እውቀት ትልቅ ተራራ እንደ ከፈለው ወንዝ ነው። ወንዙ ከተከፈለ በኋላ አንዱ ወደ ምዕራብ አንዱ ወደ ምስራቅ ይጓዛሉ። በመጨረሻም፣ ከመቶዎች ማይሎች በኋላ፣ ሸለቆ እና ቁልቁለት አቋርጠው ሁለቱም የተራራው ሌላ ጫፍ ላይ ይገናኙ እና ባህር ውስጥ አንድ ሆነው ይገባሉ። ዊልሰን "እውቀት ልክ እንደ ዛ" ነው ይላል። አንድን ትምህርት ስትጀምሩ ከሌላው የእውቀት ዘርፍ ጋር ምንም የተገናኘ አይመስልም። እስከ መጨረሻው ከገፋችሁበት፣ እስከ ጥግ ከሄዳችሁ ግን ሌሎችንም ነገሮች ማወቅ ትችላላችሁ። ምክንያቱም ሁለቱም በአንድ ወጥ ሕግ ነውና የሚተዳደሩት። (But if we follow them deeply enough, they begin converging because they describe the same underlying reality from different perspectives.) ለዚህ ነው ስለብዙ ነገር ትንሽ ከሚያውቅ ይልቅ ስለ አንድ ነገር በጥልቀት የሚያውቅ ሰው ስለ ብዙ ነገር በትንሹ ካጠናው በላይ ስለ ብዙ የእውቀት ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ የሚኖረው። ዊልሰን ለቻርሊ መንገር (የዋረን ባፌት ወዳጅ እና የቢዝነስ አጋር) አስተሳሰብ ትልቅ ተጽዕኖ ያለው ግለሰብ ነበር።

Mulualem’s View — tgindex