ኖላዊ ኄር ዘ-ኦርቶዶክስ
Статистикаዘየአምን ለአማኑኤል በስሙ ፣ ኅቱም በማኅተመ ደሙ ፣ ውኩል በጸሎተ ማርያም እሙ ፣ ወለቅዱሳን ተላዌ ሃይማኖቶሙ ። [ አቤቱ አንተን ለመስማት ያዘነበለ ልብ ስጠን! #ለሃሳብ ለአስተያየት - @Nolawiher1 በ Facebook ይከተሉን https://www.facebook.com/estifanos.dejene.94
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 205
- 1/48двое суток
- 2 526
- 1/72трое суток
- 2 725
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የምታሳርፍ እውነት ፣ የምትመራ ብርሃን ፣ የምታደርስ መንገድ መድኃኔዓለም ሆይ አመሰግንሃለሁ ። ሰምህን ጠርቼ ያላለፍኩት ሰንሰለት ፣ አንተን ተደግፌ ያልነጋልኝ ሌሊት ፣ ፊትህ ወድቄ ያልቀለለኝ ሸክም የለም ። ለሚያሻግር ስምህ ፣ ለሚያፀና ክንድህ አኮቴት ይገባል ። ክብሬ ሆይ! አንተ ብርሃኔ ሆነህ ሌሊቴን ስታነጋ ፣ አንተ ሀኪሜ ሆነህ ነፍሴን ስታለመልም ፣ አንተ መድኃኒቴ ሆነህ የሞተ ሥጋዬን ስትፈወስ ፣ አንተ አፅንተኸው ማዕበሉ ሲረጋልኝ ፣ አንተ ቀድመህበት መንገዴ ሲቀናልኝ አይኃለሁ ። አንተ አይተኸው ያልፈካልኝ ፣ አንተ ይዘኸው ያልቀናልኝ ምን አለ?! ድካሜን ያልቆጠርከው ብርታቴ ፤ ሕመሜን የቆረጥከው ሀኪሜ አንተ አይደለህም ወይ !? ኧረ አንተስ ተመስገን ። ጭንቀቴን የገታኸው አቅሜ ፣ ሸክሜን ያቀለልከው እረፍቴ አንተ አይደለህም ወይ !? ። መድረሻዬን ያየህልኝ ፅናቴ ፣ እንባዬን ያበስክልኝ አባቴ አንተ አይደለህም ወይ !? ። ኧረ አንተስ ተመስገን ። ጌታዬ ሆይ ሸሽጎ ያከመኝ እጅህ መድኃኒቴ ነው ። ሰውሮ ያፅናናኝ ድምፅህ ሰላሜ ነው ። አቅፎ ያባበለኝ ፍቅርህ ደስታዬ ነው ። ሰፍቶ ያሻገረኝ ክንድህ ደሴቴ ነው ። ትላንቴን ያልቆጠረብኝ ልብህ ማረፊያዬ ነው ። ጭንቄን የነቀለ እቅፍህ ሀኪሜ ነው ። ከልሎ የሚያኖር ፣ ደግፎ የሚለውጥ እንደ አንተ ማን አለ ?! ። ኧረ አንተስ ተመስገን ። በሺህ እጥፍ ስርቅህ አንተ ግን በሺህ እጥፍ የቅርቤ ነህ ። ለሚርቁህ ቅርብ ፣ ለሚወዱህ ክብር ስትሆን ዓይኖቼ ያዩኃል ። የማትለወጥ ደስታዬ ፣ የምፈካብህ ፀዳሌ አንተ አይደለህም ወይ ?! ። ኧረ አንተስ ተመስገን ። ስታክመኝ ያዩህ ዓይኖቼ ዛሬ የዓለምን ደስታ ያስሳሉ ። እባክህ ይቅር በለኝ ። በሚያኖር ቸርነትህ ለዘለዓለሙ አሜን! #ዲያቆን #እስጢፋኖስ #ደጀኔ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና (ዘጸ.23÷20-22) በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ጊዜ ብቻ ለሙሴና ለሕዝቡ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን እስከዛሬና ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ !
የገዳዮችን ያክል ለሟች የማያዝን እርሱ ራሱ ገዳይ ነው ። የሌሊቱ አልበቃ ብሎ በቀንም በጎች ከተገደሉ የምንከሰው ገዳዩን ብቻ አይደለም እረኛውንም ጭምር ነው ። በርግጥ በመሪ የማይዳኝ ፣ በእረኛ የማይጠበቅ ምእመን ይዘን ለምን ተገደልን ማለት እንችላለን ወይ ? የሞትነውስ ዛሬ ነው ወይ ? የተሰደድነውስ ዛሬ ነው ወይ ? አዝናለሁ በጣም ። መፍትሔ ከእርሱ ነውና አባቶች ትላንት ተሸሽገው ወደተሻገሩበት እውነተኛ ዳኛ ግን እንዲህ ብዬ እጮኻለሁ አቤቱ አምላኬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! የቅዱሳን ሞገስ ፣ የሰማዕታት አባት አንተን አመሰግንሃለሁ ። ሽንገላና የግፍ ስራ የማይስማማህ እውነተኛ ፈራጅ ሆይ! ዛሬ በዕንባ ሆኜ ወደ አንተ እጮኻለሁ ። ጌታ ሆይ በአርሲ ምድር ላይ ክንድህን ዘርጋ ። ገዳዩን በኃይልህ አስቁመው ። ጌታ ሆይ! ከመሪዎችም ፣ ከእረኞችም ያልታደልን ልጆችህ ስንጠፋ ማየት አይገድህም ወይ ? ያለ ጥፋታቸው ፣ ስለ ስምህና ስለ እምነታቸው የታረዱት ንጹሐን ልጆችህ ደም መሬት ላይ ሲፈስ ማየት አይገድህም ወይ? የሕፃናቱ ልቅሶ፣ የእናቶች ዋይታ፣ የሽማግሌዎች መታረድ ፣ የቤተክርስቲያን መቃጠል አንተን አይገድህም ወይ? የቀደሙት አባቶቻችን በግፍ ሲበደሉ “አቤቱ ፍርድህ አይዘገይም” ብለው እንደጮኹ፣ ዛሬም እኔ ልጅህ በደጅህ ቆሜ በእንባ እጠይቅሃለሁ ። የንጹሐን ደም ካንተ ዘንድ ዋጋ አለውና ። የአቤል ደም ከመሬት ወደ አንተ እንደጮኸች፣ ዛሬም በአርሲ የፈሰሰው የልጆችህ ደም ወደ አንተ ይጮኻል ። አቤቱ ክብርህን ግለጥ! ጠላትን በኃይልህ ገሥጽ ፤ መከራውንም አሳጥር። ለአገርና ለሕዝብ ሰላምን፣ ለሞቱት ወገኖቻችን የሰማዕታትን አክሊል፣ ለቀሩትም መጽናናትን ስጥ ። መከራችንን በኃይልህ ሻረው ። በሚያድነው ስምህ ለዘለዓለሙ አሜን ! #ዲያቆን_እስጢፋኖስ_ደጀኔ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
"እግዚአብሔር በሰናዖር ሜዳ የበታተነው የዓለምን የዓመፅ ቋንቋ በጴራቅሊጦስ ቀን የፍቅር ቋንቋ አድርጎ ሰበሰበው " | ቅዱስ አውግስጢኖስ |
без подписи
#ናልኝ_ጌታ “ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” [ ሐዋርያት 1፥11 ] ። አንተ የሞት መድኅን ፣ አንተ የነፍስ ብርሃን ፣ አንተ የሕይወት ደሴት ፣ አንተ የሁሉ መድኅን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃለሁ ። እሩቅ ነህ አልልህም ዳርቻህ አይመረመርም ። ጥልቀጥትህ የማይደረስበት የቅርቤ ነህ ። ትተኸኛል የማልልህ የማትዝል ብርቱ ነህ ። ቀርበህ ለወደደከኝ ፣ አቅፈህ ላባባልከኝ ለአንተ ምስጋና አኮቴት ይገባል ። በሰማይና በምድር የከበርክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! ለጠፋሁትና ላጠፋሁት ልጅህ ከዙፋንህ ወርደህ ስላዳንከኝ አመሰግንሃለሁ ። የክብር ባለቤት መድኃኔዓለም ሆይ፤ ዛሬ በደቀ መዛሙርትህ ፊት በታላቅ ክብርና በደመና ወደ ሰማይ ያረግህበትን ታላቅ ዕርገትህን በደስታ አስባለሁ ። በዕርገትህ የሰውን ሥጋ ወደ ቀደመ ክብሩ መልሰሃል፤ በሰማያዊው መንበርህም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት ተቀምጠሃልና ለስምህ ምስጋና ይገባል ። ያንተን ዕርገት በድንጋጤና በትኩረት ይመለከቱ ለነበሩት የገሊላ ሰዎች ቅዱሳን መላእክትህ እንደነገሯቸው በክብርና በኃይል ዳግመኛ የምትመጣበትን ያንን የተባረከ ቀን በትጋትና በቅድስና እንድጠባበቅ ክንድህን ዘርጋልኝ ። ጌታ ሆይ ዛሬ ግን ወደ ተረበሸው ልቤ ፣ ወደ ተመሰቃቀለው ኑሮዬ ፣ ወደ ጨለመው ቀኔ ናልኝ ። ወደ ሰማይ የወጣኸው የድል ጌታ ሆይ ! እባክህ ወደ ጓዳዬ ናልኝ ። ያዝሁ ስል የምለቅ ነኝ ፣ አተረፍኩ ስል የምበክን ነኝ እባክህ በበረከትህ ጎብኘኝ ። ልብና አሳቤን በሰማይ ቤትህ አስቀምጥልኝ ። የኔ የሆንከው ጌታ ሆይ ! ሳልጀመር ፍፃሜ ላይ የምንጠለጠለው ልጅህን ይቅር በለኝ ። የመንፈስ ቅዱስን ኃይልና መጽናናት ከዓርያም አፍስስልኝ ። በሚያፀና ድምፅህ ፣ በሚያኖር ምሕረትህ ለዘለዓለሙ አሜን ! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም
без подписи
የቃል መዝገብ ተወለደች የነቢያት ተስፋ ፣ የመለኮት ማደሪያ ፣ የሁሉ እመቤት እመ ብርሃን ሆይ ሰላም እልሻለሁ ። የልደትሽ ብርሃን ፣ የስምሽ መዓዛ ፣ የምስጋናሽ ሀሴት ገፃችንን አፍክቶታል ። አንቺን እናት አድርጎ የሰጠን አምላክ እንዴት ያለ ቸር ነው ። የታተምሽ መዝገብ ሆይ ! ቅድስናሽና ንጽሕናሽ ለሰው ልጅ ሁሉ መመኪያ ሆነ ። አንቺ ስትወለጂ የመርገም ደብዳቤ ተቀደደ ፤ የሞት ድልድይ ተሰበረ ። ድንግል ሆይ ! የሆነብንን የረሳነው አንቺ የማታልቂ ደስታ ሆነሽንልን ነው ። የማትፈፀሚ ደስታችን ሆይ ለልደትሽ ክብር እንዘምራለን ። አንቺን ደስታች አድርጎ የሰጠን ጌታ እንዴት ያለ ግሩም ነው ። ከአዳም ውድቀት በኋላ የሰው ልጅ ተስፋ ያጣበትን ጨለማ ለገፈፈው ልደትሽ ሰላምታ ይገባል ። መንግሥተ ሰማያትን ወደ ልባችን ላቀረበው ልደትሽ ሰላምታ ይገባል ። የሐናን እና የኢያቄምን መካንነት የፈታ ልደትሽ እንደምን ያለ ተዓምር ነው ። የልደትሽ ደስታ የታሰርንበትን ሕመማችንን ፣ የቆሰልንበትን ስብራታችንን ይንቀልልን ። የጥፋት ውኃ የጎረፈባት ምድር በአንቺ ልደት የሰላምን ብርሃን አየች ። መርገም በሰፈነባት ዓለም ውስጥ አንቺ እንደ በረከት ዝናብ ወረድሽልን ። ድንግል ሆይ ! የልደትሽ ዜና ለታሰርነው መፈታትን ፣ ለደከምነው ብርታት ያድለን ። የልደትሽ ብርሃን ለነፍሳችን የሚሆን ምሕረትን፣ ለሥጋችን የሚሆን በረከትን፣ ለሕይወታችን የሚሆን ሰላምን ከጸባዖት ያፍስስልን ። ቃል ሥጋ ሊሆን የመረጣት ታቦት ዛሬ ተወለደች ። የአዳም ተስፋ ፣ የሔዋን እንባ መጥረጊያ የሆነችው መዝገብ ዛሬ ተከፈተች ። ኪሩቤል የሚሸከሙትን ልትሸከም የተመረጠችው የቃል መዝገብ ከሊባኖስ አበበች ። ታወልደውበን የሚያውኩንን መወለድሽ ይሻርልን ። አሜን ! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ ግንቦት 1 ቀን 2018
ነው ስንል የኃጢአትን መንገድ ገስጾ ፣ የልብን ክፋት ገልጦ ወደ ጽድቅ ጎዳና ይመራናል ማለታችን ነው ። በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል ከክፉ ጎዳና ይመልሳል ። ታላቁ ባሕታዊ ማር ይሳቅ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ከመንፈሳዊ ተጋድሎ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲህ ያስረዳል፦ ❝የሕይወት መንገድ መጀመሪያ አእምሮን ዘወትር በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማለማመድ ነው❞። የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ጸሎት አትቅረቡ፤ ❝አቤቱ በቃልህ ውስጥ ያለውን ኃይል አስተውል ዘንድ ፍቀድልኝ❞ ብላችሁ ጸልዩ፤ ምክንያቱም ጸሎት ለቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢር መክፈቻ ቁልፍ ነው ይላል ። የእግዚአብሔር ቃል ማለት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የላከው የፍቅር ፣ የንስሐ እና የድኅነት መዝገብ ነው ። የእግዚአብሔር ቃል ❝የሚመልስ❞ የሚባለው ፣ ሰሚው ቃሉን ተቀብሎ በሕይወቱ ሲተረጉመው ነው ። ይህ ሂደት በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች መከፋፈል እንችላለን ። 1ኛ . ቃሉን መስማት ወይም የልቡና መከፈት መመለስ የሚጀምረው ከመስማት ነው ። ነገር ግን መስማት ሲባል በጆሮ ብቻ ሳይሆን በልብ መሆን አለበት። እግዚአብሔር በቃሉ አማካኝነት "አዳም ሆይ ወዴት ነህ?" ብሎ እንደጠራው፣ ዛሬም በቃሉ ሰውን ይፈልገዋል ። ዓለም ተጠቅማ የጣለቻችሁ ፣ ብቸኝነት የተዛመዳችሁ ፣ ኃጢአት ዘመድ ሆኖ ያጎሳቆላችሁ ፣ የውስጥ ሳላም የራቃችሁ ወገኖቻ እግዚአብሔር ዛሬም በቃሉ ወዴት ናችሁ? ይላችኋል ። ትሰሙት ይሆኝ ? ቃሉን ስንሰማ ማንነታችንን፣ ድካማችንንና ኃጢአታችንን እንረዳለን። ቃሉ እንደ መስታወት ነው፤ የነፍሳችንን እድፍ ያሳየናል። ያዕቆብ 1:123 “ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል”የሚለን ለዚህ ነው ። 2ኛ.የልብ መመለስ ወይም ንስሐ ቃሉን ሰምቶ "ምን ላድርግ?" ብሎ መጠየቅ የመመለስ መጀመሪያ ነው ። እንደ ጠፋው ልጅ "ተነሥቼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ" ብሎ መወሰን ቃሉን ሰምቶ የመመለስ ትልቁ ምሳሌ ነው ። "ቃሉን በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ" (ሐዋ ፪፥፴፯) እንደሚል፣ የእግዚአብሔር ቃል ድንጋዩን ልብ አርጥቦ ለንስሐ ያዘጋጃል ። 3ኛ. ወደ እግዚአብሔር መቅረብ (ፍሬ ማፍራት) መመለስ ማለት ኃጢአትን መተው ብቻ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር መመለስና ከእሱ ጋር መኖር ነው። ቃሉን ሰምቶ የተመለሰ ሰው ቃሉን መኖር ይጀምራል። ያዕቆብ "ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ" የሚለን ለዚህ ነው ። መመለስ ማለት የባሕርይ መለወጥ ነው። ቁጡ የነበረው ታጋሽ፣ ነጣቂ የነበረው መጽዋች (እንደ ዘኬዎስ) የሚሆንበት ተአምራዊ ጉዞ ነው ። ዘኬዎስ ከፍቅረ ንዋይ ወደ ፍቅረ እግዚአብሔር የተመለሰው ፤ ልቡን ከፍቶ ወደ ጌታ ድምፅ አሳቡን ስለመለሰ ነው ። ወገኖቼ ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል እንዳትስሙ ምን ይሆን የጋረዳችሁ ? እንደ ዘኬዎስ ወደ ከፍታው ውጡ ። ዓለም የሸፈነችባችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ አድምጡ ። እንደ ዘኬዎስ ከፍ ብለን የእግዚአብሔር ቃል በግልፅ የምንሰማባት ከፍታችን የመለኮት ማደሪያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት ። ዘኬዎስ ቀራጭና ባለጸጋ ነበር ፤ በሕዝቡም ዘንድ እንደ ኃጢአተኛ ይታይ ነበር። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ❝ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ" አለው (ሉቃስ ፲፱፥፭)። ያ የጌታ የፍቅር ጥሪ የዘኬዎስን ልብ ሰበረው ። ወዲያውኑ ወርዶ ንብረቱን ለድሆች ለመስጠትና የበደለውን አራት እጥፍ ለመመለስ ወሰነ። ቅዱስ ኤፍሬም በጸሎቱ ፦ ❝የእግዚአብሔር ቃል ሆይ፣ የሞተችውን ነፍሴን ታስነሣት ዘንድ ዛሬም ጥራኝ❞ ብሎ የተማጸነው የዘኬዎስን ዕድል ተመኝቶ ይመስለኛል ። ትምህርተ አበውም ፦ ❝ቃሉን ሰምቶ የማይመለስ፣ በውኃ ዳር ሆኖ በጥም እንደሚሞት ሰው ነው❞ ። ይላል ። ቅድስት ማርያም መግደላዊት ከጨለማ ወደ ብርሃን የመጣቸው ቃሉን ሰምታ ነው ። ሰባት አጋንንት ያደሩባትና በሕይወት ተስፋ የቆረጠች ሴት ነበረች ። የጌታን ትምህርት ስትሰማና ይቅርታውን ስታገኝ ሕይወቷ ተለወጠ ። እርሱን ሰምቶ ማይለወጥ ማን አለ ! ከትንሣኤ በኋላም በመቃብር አጠገብ ስታለቅስ ❝ማርያም!❞ ብሎ በስሟ ጠራት ። ያ አንድ ቃል ("ማርያም") ትካዜዋን ወደ ደስታ፣ ሞቷን ወደ ሕይወት መለሰው ። በእግዚአብሔር እንደ መጠራት ምን ሚደንቅ ነገር አለ! ። በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል አጋንንትን የሚነቅል ነፍስን ከባርነት ነፃ የሚያወጣ መሆኑን ከመግደላዊት ማርያም እንማራለን ። ቅዱስ ጴጥሮ ከክህደት ወደ እረኝነት የመጣው ቃሉን ሰምቶ በመመለሱ ነው ። ጴጥሮስ ጌታን ሦስት ጊዜ ከካደ በኋላ ተስፋ ቆርጦ ነበር ። ትንሣኤው ከተከናወነ በኋላ ጌታችን ❝የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?❞ ብሎ ሦስት ጊዜ ጠየቀው (ዮሐንስ ፳፩፥፲፭)። ይህ ጥያቄ (ቃል) ጴጥሮስን ወደ ቀድሞ የሐዋርያነት ክብሩ መለሰው። በደሉን በንስሐ አጥቦ በቃሉ ታደሰ ። የእግዚአብሔር ቃል ወድቀን እንድንቀር አያደርገንም፤ በፍቅር ጠይቆ መልሶ ያቆመናል ። የወደቀውን የሚያነሳ ፣ የበደለውን የሚሾም እንደ እርሱ ማን አለ ? ። ወገኖቼ እነዚህ ሁሉ ቅዱሳን የተመለሱት ቃሉን ሰምተው ብቻ ሳይሆን ለቃሉ ታዝዘው ጭምር ነው ። ቃሉ ለእነሱ የድኅነት ድልድይ ሆኖላቸዋል። የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እኛ የሚመጣ የድኅነት ድልድይ ነው ። ይህ ቃል የደከመች ነፍስ የፀናችበት ዓለት ፣ የቆሰለችውን ነፍስ የፈወሰና ኃጢአተኛውን ወደ ቅድስና የመለሰ ሕያው ቃል ነው። ዛሬም ቢሆን የእግዚአብሔር ቃል በቤተክርስቲያን ቅጽር፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ንባብና በወንጌል ትምህርት አማካኝነት ለእያንዳንዳችን ይነገራል። ቃሉ ❝የሚመልስ❞ የሚሆነው ግን እኛ ጆሯችንን ሰጥተን፣ ልባችንን ከፍተን ስንቀበለው ብቻ ነው። እንደ ዘኬዎስ ከትዕቢት ዛፍ ላይ ወርደን፣ እንደ ማርያም መግደላዊት በንስሐ እንባ እግሩ ስር ወድቀን፣ እንደ ጴጥሮስም ፍቅራችንን ስንገልጥ ቃሉ በሕይወታችን ውስጥ ተአምር መሥራት ይጀምራል ። የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ያለውን የጨለመ ስፍራ እንዲያበራው ፈቃደኞች እንሁን ። ቃሉን መስማት ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባርና ወደ ንስሐ ሕይወት በመለወጥ ከእግዚአብሔር ጋር እንታረቅ ። የተመለስንበትን ቃል ለሌሎችም የመመለሻ ምክንያት እንዲሆን በሕይወታችን እንመስክረው ። የእግዚአብሔር ቃል ነፍሳችንን ወደ ቀድሞ ክብሯ የሚመልስ፣ ልባችንን በሰላም የሚሞላ ዘላለማዊ ስንቃችን ይሁን ። ❝ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ። ❞ (ያዕቆብ ፩፥፳፪) ። የሚመልስ ቃሉን ወደ ልባችሁ ወደ ሕይወታችሁ እግዚአብሔር ይስደድ ። ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጋር እንዲህ ጸልዩ ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የልቤን ዓይኖች አብራ፤ ቃልህን ሰምቼ አስተውል ዘንድ፤ ፈቃድህንም አደርግ ዘንድ ማስተዋሉን ስጠኝ። በምድር ላይ ስደተኛ ነኝና ትዕዛዝህን ከእኔ አትሰውር። ቃልህ ለዓይኖቼ ብርሃን ነውና። አቤቱ፤ የልቤን ዓይኖች አብራ፤ በሕግህ ያለውን ተአምራትህንም አይ ዘንድ። አንተ የነፍሴ ብርሃን ነህና፤ ለዘላለሙ አሜን። ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ Deacon Estifanis Dejene ሚያዝያ 26 ምሽት 2018 የምሕረት ዓመት ተፈፀመ ! ስብሐት ወክብር ለስሉስ ቅዱስ ይደሉ ፤ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስሉስ ዕሩይ ኩሎ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም አሜን ።
አላቸው ። አረጋዊው አባት ፈገግ አሉና መነኩሴውን እንዲህ አሉት፦ ❝ልጄ ሆይ! ያንን የቆሸሸ የቅርጫት ዘንቢል አንሳና ከወንዙ ውኃ ቀድተህ አምጣልኝ❞ ። መነኩሴው ግራ ተጋባ። ቅርጫቱ ቀዳዳ ስለሆነ ውኃ እንደማይይዝ ያውቃል፤ ቢሆንም የታዘዘውን ለማድረግ ወደ ወንዙ ሄደ ። ውኃ ቀድቶ ወደ አባቱ እስኪመለስ ድረስ ውኃው ተንጠባጥቦ ያልቃል። እኚህ ቅዱስ ግን ❝ደግመህ ሂድ❞ ይሉታል። መነኩሴው ሰባት ጊዜ ተመላለሰ ፤ ነገር ግን አንድ ጠብታ ውኃ ለታላቁ አባት ማድረስ አልቻለም ። በመጨረሻም መነኩሴው ደክሞት "አባቴ ሆይ! ቅርጫቱ ውኃ መያዝ ስለማይችል ድካሜ ከንቱ ነው" አላቸው። አረጋዊው አባት ግን ወደ ቅርጫቱ ጠቆሙና እንዲህ አሉት፦ ❝ልጄ ሆይ! ቅርጫቱ ውኃ ባይይዝም እንኳ፣ ደጋግመህ ስትጠልቅበት ግን ምን እንደሆነ ተመልከት❞ ። መነኩሴው ቅርጫቱን ሲመለከት ደነገጠ። ቀደም ሲል በጭቃና በቆሻሻ ተለቅልቆ የነበረው ቅርጫት፣ አሁን ከመደጋገሙ የተነሳ ጸድቶና ነጽቶ ነበር ። አረጋዊው አባትም እንዲህ አሉት፦ ❝የእግዚአብሔር ቃልም እንደዚሁ ነው ። በልባችን ውስጥ ወዲያው ላይቀመጥ ወይም የቃሉ ትርጉም ወዲያው ላይገባን ይችላል። ነገር ግን ቃሉን እንደ መስታወት ስንመለከተውና በልባችን ስናሳልፈው፣ እኛ ባናውቀውም እንኳ ውስጣችንን እየቀየረውና የነፍሳችንን ቆሻሻ እያጠበ ያነጻናል❞። መስታወቱ ቆሻሻችንን እንደሚያሳየን ሁሉ፣ ቃሉም ማንነታችንን እያሳየን ሳናውቀው እንድንቀየር ያደርገናል ብለው አስተማሩት ። አዎ ወገኖቼ የእግዚአብሔር ቃል ውጤቱ ወዲያው ባይታይም፣ ማንነታችንን የማጥራት ስውር ኃይል አለው። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ቃሉ ወደ ውስጥ ገብቶ እንደ መስታወት ድክመታችንን ያሳየናል ፤ ያን ጊዜ ደግሞ ጸጋው ያጥበናል። ❝አልተለወጥኩም❞ ብለን ከቃሉ መራቅ የለብንም ። እራሳችንን ደጋግመን የምናገኝበት ቦታ ማንነታችንን ሊወስነው ይችላል ። እግዚአብሔር ከብዙ ግንኙነትና ከብዙ መንገዶች የመለሰን ያ ቦታ ስለማይመጥነንና የተፈጠርንበትን ዓላማ ሊያስተን ስለሚችል ነው ። እግዚአብሔር ሲመልስ መታዘዝ ይገባል ። እግዚአብሔር ስለመለሳችሁ ነው ዛሬን ለማየት የበቃችሁት ። ደጋግመን የሮጥንባትና የሮጥንላት ዓለም ተጠቅማ ጥላናለች ። በዚህ ዘመን ደጋግመን የምንሮጠው ወደ ቃለ እግዚአብሔር ካልሆነ የምንሆነውና የሆነብንን መሸከም አንችልም ። በርግጥም ደጋግመን የምንጠልቅበት የነፍስ ደሴት የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ወደ እግዚአብሔር ቃል አሳብን ማቅናት ከዚህ ዘመን ሀሩር እራስን መሸሸግ ነው ። ወገኖቼ ይሄን ዘመን የምንሻገረው በእግዚአብሔር ቃል ነው ። የምንሰማው ነገር ደስ አይልም ። የምንመለከተው ነገር አይማርክም ። ጆሮን ጭው የሚያደርግ ዜና የዕለት ምግባችን ሆኗል ። የሀገር ባለውለታዎች በር ተዘግቶባቸው ፤ የሀገር ሸክም በሆኑ ህሊናቢሶች ሀገር ስትታመስ እያየን ነው ። ወጣታችን በቀቢጸ ተስፋ እራሱን እያጠፋ እየተመለከትን ነው ። ይህን ሁሉ ከባድ ነገር እየተመለከትን ዛሬን የኖርነው የእግዚአብሔር ቃል ኃይል ሆኖልን ነው ። ❝ቃሉን ማንበብና ማሰላሰል አእምሮን ከዓለማዊ ሐሳብ ነፃ ያደርገዋል❞። እንዲል ማር ይሳቅ (St. Isaac the Syrian) ፤ የእግዚአብሔር ቃል ብዙ ሸክማችንን አራግፎልን እንጂ እንደሆነውና እንደሆነብን ዛሬን ማየት አንችልም ነበር ። ዓለም ዛሬ የሆነችሁን እኛ ያልሆነው የእግዚአብሔር ቃል ቅጥር ሆኖልን ነው ። የማይጠፋ ብርሃናችን ፣ የማይሰርቁት ሀብታችን የእግዚአብሔር ቃል ነው ። አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ❝ነፍስ ያለ እግዚአብሔር ቃል ልትኖር አትችልም❞ የሚሉት ለዚህ ነው ። እሾህ ይብቀልብሽ ተብላ በተረገመችው በዚህች ምድር ላይ እየኖርን አለመወጋት አንችልም ። የኃጢአት ጦር ዘርግታ ፣ የክፋት ስንቅ ተሸክማ ፣ በጨለምተኝነት ቅጥሯን አስምራ በምትቀበለን ዓለም ውስጥ ይዘን የምንሄደው ጋሻ ቃለ እግዚአብሔርን ነው ። በጸሎት ኃይል ፀንተን ፣ በተጋድሎ ጌጥ አብበን ፣ በቃሉ በረከት ተሸፍነን ካልተዋጋን ዓለሙ ነፍሳችንን ለመንጠቅ ሁሌም ፅኑ ነው ። ለማይተኛልን ዓለም የምንነቃው ቃሉን የነፍስ ጌጥ ስናደርግ ነው ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈውርቅ ❝የእግዚአብሔርን ቃል አለማወቅ የክፋት ሁሉ ምንጭ ነው፤ ያለ መሣሪያ ወደ ጦርነት እንደመግባት ይቆጠራል❞ ብሎ የሚገፅፀን ለዚህ ነው ። ወገኖቼ በመጻሕፍት ቅዱስ ውስጥ ያለው መለኮታዊ ቃል በፍላጎታችን የታቀፍነውን ትዕቢትን የሚያጠፋ፣ የሥጋ ፍላጎትን የሚያበርድና ትዕግሥትን የሚሰጥ የመድኃኒት ማዕከል ነው ። ሁሉን አቀፍ ፈውስ የምናገኘው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው ። የሕይወታችንን መንገድ የሚያቀናውን እግዚአብሔርን እርሱን ላላስቀደምንበት ምርጫችን ምሕረትን ልንለምነው ይገባል ። በምርጫችን ገብተንት ለታመምንበት ፣ ከአሳቡ እርቀን ለሰበርንበት ፣ ከፍቃዱ ሸሽተን ለቆሰልንበት ፣ ከቃሉ እርቀን ለመከንበት ማንነታችን ይቅርታ ልጠይቀው ይገባል ። የእግዚአብሔር ቃል የሚመልስ ቃል ነው ። የእግዚአብሔር ቃል ዝም ብሎ የሚነገር ድምፅ ሳይሆን፣ የጠፋውን የሚመልስ ኃይል ነው ። የእግዚአብሔር ቃል ከምን ይመልሰናል ? አንድ ነጥብ እንመልከት ። ከስህተት መንገድ ይመልሰናል የእግዚአብሔር ቃል ከስህተት መንገድ የሚመልስ ነው ስንል፣ በኃጢአት ወይም ባለማወቅ የጠፋን ሰው ወደ እውነትና ወደ ሕይወት ጎዳና የሚመልስ የብርሃን መመሪያ ነው ማለታችን ነው ። የሰው ልጅ ሳያውቀው ወይም በልምድ ወደ ስህተት ሊገባ ይችላል። የእግዚአብሔር ቃል ግን እንደ መስታወት እውነተኛ ማንነታችንንና ያለንበትን የተሳሳተ አቅጣጫ ያሳየናል ። በሰዎች ሕይወት ላይ ለመወሰን የሚፈጥነው ልባችን ፣ ለሀገርም ለቤተክርስቲያን የማይጠቅመው ድርጊታችን የሚታረመው በቃሉ ነው ። መዝሙረኛው "❝ቃልህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴም ብርሃን ነው❞ ። (መዝሙር 119:105) ያለው ለዚህ ነው ። የእግዚአብሔር ቃል ስህተትን ከመጠቆም ባለፈ፣ ያንን ስህተት እንዴት አርመን ወደ ትክክለኛው መስመር እንደምንመለስ ያስተምረናል። ትክክለኛው የሕይወታችን ኮምፓስ ቃለ እግዚአብሔር ነው ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:16-17 ላይ ❝የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።"❞ የሚለን ለዚህ ነው ። ወገኖቼ ከስህተት መመለስ ማለት ሃሳብን መለወጥና አዲስ ሕይወት መጀመር ነው ። ቃሉ የሰውን ውስጣዊ ማንነት የመለወጥ ኃይል አለው ። ያ ክፉ ጠባያችሁ ከእናንተ ላይ እረግፎ በአዲስ ማንነት በሰውና በእግዚአብሔር ፊት በፍቅር ቆማችሁ ካያቹ ደግፎ ያቆማችሁ ፣ ለውጦ የሰራችሁ የእግዚአብሔር ቃል ነው ። መዝሙረኛው የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።" (መዝሙር 19:7) የሚለን ለዚህ ነው ። የንጉሥ ኢዮስያስ ታሪክ ለዚህ ምስክር ይመስለኛል ። 2ኛ ነገሥት 22፥1-20) ላይ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ሕግ ረስተው ለዘመናት በጣዖት አምልኮና በታላቅ ስህተት ውስጥ ነበሩ ። ቤተ መቅደሱ ሲታደስ የሕጉ መጽሐፍ ተገኘ ። ንጉሡ የቃሉን ንባብ በሰማ ጊዜ ፣ ሕዝቡ ምን ያህል ከመለኮታዊው መንገድ እንደሳተ ተረዳ ። ንጉሡ ልብሱን ቀደደ፤ ንስሐ ገባ፤ ጣዖታትንም ሁሉ አጠፋ ። የጠፋው ሕዝብ በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ወደ ትክክለኛው አምልኮ ተመለሰ ። ወገኖቼ የእግዚአብሔር ቃል ከስህተት የሚመልስ
የሚመልስ ቃል ፍቅደን ለተውናቸው ቅን መንገዶች ፣ ደክመን ለጣልናቸው መልካምነቶች መልሱ እግዚአብሔር ነው ። እግዚአብሔር እንደ አምላክነቱ ባይመራን ፤ እንደ ማሐሪነቱ ባይምረን ያ ክፉ ጠባያችን ያስማሰን ገደል ዛሬ መቀበሪያችን ይሆን ነበር ። እግዚአብሔር እንደ አምላክነቱ ስለመራን ዛሬን ዛሬ ለማለት ብቅተናል ። እግዚአብሔር የንገን ብርሃን የሰወረብን ትላትን እንድንማርበት ዛሬን እንድናመሰግንበት ነው ። ከትላንት ያልተማረ ዛሬን አያመሰግንም ። የዛሬው ምስጋና የትላቱን ሕይወት ካላረመ ላንመለስ ወደ ውድቀት እንነጉዳለን ። ዓለም ጊዚያዊ መቆያ እንደመሆኗ በመጠን መኖር ያስፈልገናል ። ለዚህ ለማይሟላ ኑሮና ለማይመች ዓለም ከእግዚአብሔር እርቆ ወደ ውድቀት መመለስ ሁለት ሞት ነው ። እግዚአብሔር ፊት ለዓለም ብርቱ ለክብሩ ሰነፍ ሆነን መቆም አይገባንም ። ለጽድቅ ካልጨከንን መንፈሳዊነት ይመነምናል ። አሁን በምናሳየው አቋም መንፈሳዊነት የራቀው ፣ የእግዚአብሔር ክብር የማይስበው ፣ የቤተክርስቲያን ጥሪ የማያስደነግጠው ፣ የሊቃውንት ትምህርት የማያውደው ፣ የአባቶች ምክር የማይመልሰው ትውልድ እንዳንፈጥር እሰጋለሁ ። እግዚአብሔር እንደ ሸፋኝነቱ ይህን ትውልድ ከዚህ እንዲጋርድ እለምናለሁ ። ትውልድ እምቢ ያለ ጊዜ ሀገር ትወድማለች ፣ ትውልድ ከእግዚአብሔር የራቀ ጊዜ ፈተና ይበዛል ። እግዚአብሔርን እቢ ብለን እሺ የሚሆንልን ነገር የለም ። እንደ ሐይማኖት አባትነት ፣ እንድ ሀገር መሪነት እግዚአብሔርን እሺ የሚል ትውልድ ለማብዛት ልንሰራ ይገባል ። እንደ ሐይማኖት አበትነት በድክመታችን ፣ እንደ ሀገር መሪነት በእውቀታችን ፣ እንደ ህዝብ በስራችን ከእግዚአብሔር እንርቃለን ። እንደ ሐይማኖት አባት ቤተክርስቲያንን አንፀን ለረሳናቸው ሕንፃ ስላሴዎች ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል ። እንደ ሀገር መሪነት በፖለቲካ ቀመር ሀገር ገንብተን መሠረቱን ለነጠቅነው ትውልድ እግዚአብሔርን ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል ። እንደ ሕዝብ ያኖረንን አምላክ ክደን የመሪዎችን ክንድ ለመደገፋችን እግዚአብሔርን ይቅርታ ልጠይቅ ይገባል ። የሚመሩ ካልተመለሱ የሚከተሉ አይመለሱምና እግዚአብሔር ባስቀመጠን ቦታ ለክብሩ ብለን ልንሰራ ለፍቅሩ ብለን ልንፀና ይገባል ። እግዚአብሔር አምላኩ የሆነተለት ትውልድ ብሩክ ነው ። ዓለም ያለችሁንም ሆነን የወደደን ክርስቶስ ነው ። እርሱ ያለንን መሆን ፤ የመረጠልንን መከተል እርሱን ማክበር ነው ። የሚያፀና ድምፁን ሰምተን ፣ የመረጠልንን ቃሉን ተመግበን መኖር ያስፈልጋል ። ሰዎች ግንኙነታችንን የሚወስኑት ስለ እኛ በተሰማቸው ልክ ነው ። የሰባት የአምስት ዓመት ታሪክ በሁለት ሰከንድ ውሳኔ ሲሻር የምንመለከተው ስሜት ሲያራምድ ትላንትን ስለማያሳይ ነው ። መጽሐፍ ❝ ራስን መግዛት የማይችል ሰው ቅጥር እንደሌለው ከተማ ለጠላት የተጋለጠ ነው❞ ። (ምሳሌ 25፥28) የሚለን ለዚህ ነው ። ስሜት የሚገራው በቃለ እግዚአብሔር ነው ። ከሁሉ በላይ በወድቀታችን ፣ በሐዘናችን ፣ በስብራታችን ፣ ውስጥ የሚመልስና የሚያፅናና ድምፅ ከተሰማን ያ ድምፅ የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ከስሶት ወር በፊት እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የማውቃት አንዲት እሕቴ በጠዋት መልእክት ላከችልኝ ። መልእክቱ ❝ ሀዘን አትደርስም?❞ የሚል ጥያቄ አዘል መልእክት ነበር ። ድንግጥ ብዬ ምን ሆንሽ ለማለትም አቅም አንሶኝ አድራሻ ጠየኳት ። የሰው ሐዘን ለምን አይባልም ። ሐዘን ምክንያት አይጠየቅለትም ። አፅናኙን ጌታ የጠሩበታል እንጂ ሐዘን እንዴት አይባልም ። ክርስቶስ አላዛርን ከማስነሳቱ በፊት ከእነ ማርታ ጋር አልቅሷል ። ካዘኑት ጋር ማዘን ክርስትና ነው ። ወዲያው ራይድ ይዤ ወዳለችኝ ስፍራ አቀናሁ ። ያለችኝ ቦታ ደርሼ ስልክ ደወልኩ ። ወድያው አንድ ወጣት ልጅ ወደ እኔ ቀርቦ እስጢፋኖስ አንተ ነክ ? አለኝ በፈገግታ፤ አዎ አልኩት እሺ ብሎ ከኋላው አስከትሎኝ ወደ ቤቱ አቀናው ። የምንጠብቀውን ነገር መስማት ደስ ይላል ። የምንሻውን ነገር ማየት ያሳርፋል ። ትንሽ እንደተራመድን ያ ወጣት ልጅ አንድ ትልቅ ቤት ያለበትን በር አንኳኳ በሩም በአንድ ወጣት ጠባቂ ተከፈተ ። ወጣቱ ልጅ በፈገግታ ጠባቂው በግርታ ግባ አሉኝ ። ቤቱ አንድ ጠባቂ የሚያንሰው ቀና ብለው ለመጨረስ የሚከብድ ቅንጡ ግቢ ነው ። ውስጥ ገብተን ወደ ሁለተኛ ፎቅ አመራን ። ሁለተኛው ፎቅ ሰሳሎን ውስጥ አንዲት በጥቁር ልብስ የተሸፈነች ብቸኛ ሴት ምንጣፍ ዘርግታ ተቀበለችኝ ። ሰላም ዋላቹ ? አልኩ እዛ ሚያክል ጊቢ ውስጥ ብዙ ሰው ይኖራል ብዬ ። ሐዘን የሰበረው ደረቷን ቀና አድርጋ ፤ ፀፀት ያጦቀረውን አንደበቷን ከፍታ እግዚአብሔር ይመስገን አለች ያቺ ምስኪን ሴት ። ከአንደበቷ ቅልብ አድርጌ አሜን ! አልኩ ። በሐዘን ተሰብሮ ማማስገን ቀላል ነገር አይደለም ። እግዚአብሔር ካልደገፈ ሐዘን ብቻችንን የምንታመምበት ከባድ ሸክም ነው ። ከዚህች እሕት ጋር ትንሽ ካወጋን በኋላ ❝ብርሃን የሌለው ሰው መንገድ እንደሚጠፋው ሁሉ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጨረር የማይበራለት ሰው በጨለማ ውስጥ ይኖራል❞ እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (St. John Chrysostom) ። እኔም እግዚአብሔር ያለምክንያት እዚህ ቤት አላመጣኝም ብዬ መጽሐፍ ቅዱስ ላስተምር ተነሳው ። አስተምሬ ጨረስኩና ቁጭ እንዳልኩ ፤ ያ በሐዘን የተቆለፍው አንደበቷ በፈገግታ ሲሞላ ታየኝ ። በልቤ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ ። የእግዚአብሔር ቃል ከሕዝን ወደ ደስታ ይመልሳል ። የእግዚአብሔር ቃል የጨለመውን ወደ ብርሃን ይመልሳል ። የሕይወት ማዕበላችንን የሚያረጋጋ ፣ የዓለምን ወረት በብርሃኑ የሚያጠፋ እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ያኔ በሐዘናችሁ ወራት ያለማንም ደግፋ ፈገግ ያላችሁት የእግዚአብሔር ቃል ይህን ዓለም ደግፎ ስለያዘ ነው ። በእርግጥም የሚመልስ ቃል ! እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ቃጠሎ የዘረጋልን ካባ ቅዱስ ቃሉን ነው ። ይህ ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ባይበራበት ኖሮ ጨለምተኝነት ይወርሰን ነበር ። የእግዚአብሔር ቃል የተራበች ነፍስ የምትጠግብበት የነፍስ ምግብ ፣ የታመመች የምትፈወስበት መድኃኒት ፤ የጠፋች ነፍስ የምትመራበት ዘላለማዊ የሕይወት ብርሃን ነው ። የዓለሙ በረሀ ሲያጥወልገን ፣ የስብሐት ፀዳል ከፊታችን ሲሰወር ፣ በተረበሸ አእምሮ ሰላማችን ሲታወክ የሚያረጋጋን የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ (St. Basil the Great) ❝መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ነፍስ ራሷን የምታይበት መስታወት ነው፤ በዚያም ውስጥ የራሳችንን ጉድለት አይተን እንድንታረም ይረዳናል❞ ይላል ። እራሳችንን በሰው ውስጥ ለማየት የምንጥር ብዙዎች ነን ። የሥጋን እድፍ በመስታወት አይተን እንደምናሰውግደው ሁሉ የነፍስን እድፍ የምናየው በእግዚአብሔር ቃል ነው ። እርሱ ሰጥቶን ያላተረፍንበት የለም ። እንደ እግዚአብሔር ቃል እራስን የሚያሳይ መስታወት የለም ። ወገኖቼ እራስን ማየት ትልቅ ፀጋ ነው ። ❝በአንድ ወቅት በአስቄጥስ በረሃ የሚኖር አንድ ወጣት መነኩሴ ነበረ ። ይህ መነኩሴ ዘወትር የእግዚአብሔርን ቃል ያነባል ፤ ነገር ግን በሕይወቱ ላይ የሚመጣ ለውጥ ስላልታየው ተስፋ ቆረጠ ። አንድ ቀን ወደ አንዱ ታላቅ አረጋዊ አባት ዘንድ ሄዶ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ ❝አባቴ ሆይ! ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል አነባለሁ፤ ነገር ግን ምንም ትርጉም ያለው ለውጥ በራሴ ላይ አላየሁም ። ቃሉን አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያው እረሳዋለሁ ። ታዲያ ማንበቤ ምን ጥቅም አለው?❞
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
መልእክተ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምዕት ዐሠርቱ ወሰመንቱ ዓመተ ምሕረት "ተሰጥመ ሞት ውስተ ሙኣት፤ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ" ፩ ቆሮ ፲፭፥፶፬ ከሲኦል እጅ ሊታደገን የመጣው ንጉሥ ከሞት ተቤዥቶናል፤ ለዘመናት ሠልጥኖብን የኖረው ሞት ከክርስቶስ በኋላ የእርሱን ስም ሰምቶ መደንገጥ እና መንቀጥቀጥ ግብሩ ሆኗል። የሚያስጨንቀን የነበረው የመቃብር ድንጋይ ከሕይወታችን መንገድ ተወግዷል፤ የምንሻውን የናዝሬቱን ኢየሱስም አግኝተነዋል የሞትን ኃይል ሲደመስሰውም ተመልክተናል። የትንሣኤውን ክብር ይገልጥ ዘንድም ጥቂት ብርሃኑን አውጥቶ የመቃብር ጠባቂዎችን ሲጥላቸው ያየነው እርሱ በመለኮታዊ ብርሃኑ ጨለማን አስወግዶ በብርሃን መርቶናል። ተወዳጆች ሆይ ! በአዳም ያጣነውን ልጅነት በክርስቶስ ኢየሱስ አግኝተነዋል ፣ ከመራቆት በብርሃኑ ተጎናጽፈናል፣ ከስደት ወደ አባታችን ቤት ተመልሰናል፣ ከረሃብና ከመጠማት በሥጋውና በደሙ ጠግበናል፣ ከዲያብሎስ ተገዥነት ወደ ልባችን ደስታ ተጠግተናል፣ ውርደታችን በጌታ ትንሣኤ በክብር ተለውጧል። ስለዚህ በሞት ተጀምሮ በትንሣኤው የተረጋገጠልን የሕይወታችን ነገር እንዲህስ ከሆነ ያከበረንን አምላክ ደስ እናሰኘው ዘንድ ምክንያት አለንና ምን ጊዜም በበጎ ነገር እንጽና፣ የተቸገሩ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እናስባቸው፣ ለሰውና ለፍጥረት ሁሉ መልካሙን እናድርግ፤ የተከፈለልንን ዋጋ መመለለስ እንደማይቻለን ተረድተን የትንሣኤውን ብርሃን ያሳየንን ድንቅ አምላክ እናመስግነው ፤ በመልካም ሥራም እንጽና ! እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! እግዚአብሔር ኢትዮጵያን፣ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካን ይባርክ ! መልካም በዓለ ትንሣኤ + አባ ሄኖክ በኢትዮጵያ እርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ