tgindex
Hamere Tewahedo Media - ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

Hamere Tewahedo Media - ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

Статистика
@hameretewahedoитальянский

http://facebook.com/eastdiocese https://www.youtube.com/channel/UCosQ9gywx0VAqiUm80oJ3rA

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
итальянский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 836
−1 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
688
21 постов
Вовлечённость
37,5%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
136
1/48двое суток
155
1/72трое суток
168

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • https://www.youtube.com/live/3JWyN_e0ZEs?si=yPQJaglGBp-W-AQ4

  • https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid0DcRx9FKXwwMQ4ZLGanCsMJzGBjkvGS9arVqiSdfLcALvhwpitZe4RQ1DtrAJm62Tl/?

  • #ዜና_ዕረፍት የኔታ መ/ር አንለይ እግዜሩ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። ጥበበኞችም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይበራሉ፤" — ትንቢተ ዳንኤል 12፥3 #ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም [#ሐመረ_ተዋሕዶ_ሚዲያ] #አዳማ — በአዳማ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ቦታው ከተመሠረተበት ጀምሮ የደብሩ መምህር በመሆን፣ ሌሊትና ቀን ሳይታክቱ ለረጅም ዓመታት በታማኝነትና በቅንነት ያገለገሉት ታላቁና አንጋፋው ሊቅ የኔታ መ/ር አንለይ እግዜሩ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል። ዕድሜያቸውን ሙሉ ለፈጣሪና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰጡት የኔታ እስከ ዕረፍታቸው ዕለት ድረስ በጽናት፣ በፍቅርና በትሕትና ሲያገለግሉ የቆዩ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ እረኛና አባት ነበሩ። በተለይም በአዳማ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደብር የመጽሐፍ መምህር ሆነው በነበሩበት ረጅም የአገልግሎት ዘመናቸው፤ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር በመተርጎም፣ ጉባኤ ዘርግተው ሕፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ደቀ መዛሙርት በትጋት በማፍራት ተተኪ የሌለው መንፈሳዊ አገልግሎት አበርክተዋል። የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በየኔታ መ/ር አንለይ እግዜሩ ዕረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፣ ፈጣሪ የአባታችንንና የሊቁን ነፍስ በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ አሳርፎ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርሳቸው፣ ለሥጋ ዘመዶቻቸው፣ ለደቀ መዛሙርቶቻቸውና ለመላው ምዕመናን መጽናናትን ይመኛል።

  • ❖ Ayyaana Waggaa Qulqulluu Mikaa'elaa Waxabajjii Kudha Lamaa ❖ Waxabajjii 12 galanni isaa akka dammaa kan mi'aawu, jajjabaafi kabajamaa kan ta'e hogganaa Ergamootaa Qulqulluu Mikaa'elaa, Mana Amantaa Ortodoksii Tawaahidoo Itoophiyaa bakka Taaboonni Waadaa jirutti ayyaana waggaa nigiisii haala ho'aa ta'een ni kabajju. https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid02zG6pQNETXfUBkngbNUbS1bHxfRGZtGz94HD2HAtSYt9KFUS96RwZdgUcTgCKezNzl/

  • ❖ ሰኔ ዐሥራ ሁለት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ❖ ሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፣ ንዑድ ክቡር የሆነው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም የመልአኩ የቃልኪዳኑ ታቦት ባለበት ሁሉ የንግሥ በዓሉን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች። https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid022Zfb3TAzMibk6nxQghkhV6XEd7LcqER9nvXpTSJbVCcxgz3ZrcfPdid4ec6z7L7Jl/

  • Waamicha Kabaja Ayyaana Guddichaa fi Argannaa Eebbaa! "Ani Gabri'eel isa Waaqayyo duras dhaabbatudha" (Luq. 1:19). Kawaala bakka jirtanitti ta'uun gargaaruuf: 1000019399161 (Baankiidhaan daldalaa Itoophiyaa) https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid0fju5Z6NNLAfQ4aogiRV6rnN2h1J8qQWEbfD1JjVkDspJiFoY4QWf4KyT9odSGYYsl/

  • የታላቅ ክብረ በዓል እና የበረከት ጥሪ! "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" (ሉቃ.፩፥፲፱)። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንጋፋና ታዋቂ ከሆኑት ገዳማትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው፣ የባቱ (ዝዋይ) ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር ኮሌጅ አንዱ ነው ። በጥቅምት 4 ቀን 1997 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘበኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (ሣልሳይ) አባታዊ መመሪያን መሠረት በማድረግ፣ ያለምንም ሕንጻ አሰሪ በራሳቸው በገዳማውያኑ ብቻ ከሃያ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት በውብ ኪነ ሕንጻ ተሠራ። ሕንጻ ቤተ መቅደሱ ታንጾ ከ9 ዓመታት በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ.ም ተባርኮ ተመርቋል ግንቦት 24 ቀኑም ቅዳሴ ቤቱ ከብሯል። እነሆ የዚህ የታላቁ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ከተመረቀ ዘንድሮ 12 ዓመታትን አስቆጥሮ ነገ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ገዳማውያን አበው መነኮሳት፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የባቱ ከተማና የአካባቢው ምዕመናን በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። እርስዎም ከመላው ቤተሰብዎ ጋር በመሆን በበዓሉ ላይ ተገኝተው ከመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በረከት ይሳተፉ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም በታላቅ አክብሮት ተጠርተዋል።

  • ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (ካልዕ) የሥነ-ጽሑፍ ሀብቶች በባቱ/ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሥር እንዲጠበቁ ወሰነ። ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም [ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ] #አዳማ— የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትላንትናው ዕለት ባከናወነው የርክበ ካህናት ጉባዔ ሁለተኛ ቀን ውሎ፣ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ለሚገኘው የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ትልቅ ትርጉም ያለው ውሳኔ አሳልፏል። ሙሉ መጃውን ለመከታተል https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid02M3ebiacRriWUiF1SJ2xn9o4c3wU9GX2T1VkuXGMoqAnMbvDhnjvkH3dMure16iphl/

  • 6 апр.1 1461

    ሰሙነ ሕማማትና ዕለተ ሰኑይ ❖ ሰሙነ ሕማማት የሚባለው ወቅት ከዐቢይ ጾም ማብቂያ ከሆሣዕና ሠርክ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ባሉት ቀናት ውስጥ ያለው ሳምንት ሲሆን ነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸከመ” ብሎ አስቀድሞ እንደተነበየው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል በፈቃዱ መከራ መስቀልን የተቀበለበትና ነፍሱን ለሞት አሳልፎ የሰጠበት ታላቅ ሳምንት ነው። ይህ ሳምንት በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት አዳምና ሔዋን በኃጢአት ምክንያት ለ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የኖሩበትን የመከራና የሥቃይ ዘመን የምናስብበት ሲሆን ጌታችን ለአዳም ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ መጥቼ አድንሃለሁ ባለው ቃል መሠረት መጥቶ ያዳነበትን ምሥጢር እንዘክራለን። የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያ ዕለት ሰኞ ወይም ዕለተ ሰኑይ በሁለት ዓበይት ድርጊቶች ይታሰባል፤ https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid02DwUNB51rmWeEC5WoCs77HUv56rE4YY5Bjt8uTFjVRTbGbyYK2pt9amSCaHquJryQl/

  • 3 апр.1 0492

    ❖ ባለ ሁለት ሰይፉ ቅዱስ መርቆሬዎስ ❖ መርቆሬዎስ ማለት “የአብ ወዳጅ” ወይም “የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ” ማለት ሲሆን፣ ቀድሞ ስሙ ፒሉፓዴር ይባል ነበር። በሮም ግዛት የጦር መኮንን ሳለ፣ ከበርበር ሰዎች ጋር በነበረው ታላቅ ጦርነት የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የሚነበልበል ሰማያዊ ሰይፍ ሰጥቶት ድልን ተቀዳጅቷል። በዚህም ምክንያት ከምድራዊ ሰይፉ በተጨማሪ ሰማያዊ ሰይፍ ስላለው “ባለ ሁለት ሰይፉ ሰማዕት” ተብሎ ይጠራል። ቅዱስ መርቆሬዎስ በድል ከተመለሰ በኋላ ንጉሡ ዳክዮስ ለጣዖታት እንዲሰግድ ባዘዘው ጊዜ፣ ምድራዊ ማዕረጉንና ትጥቁን በመጣል “እኔ የክርስቶስ ወታደር ነኝ” በማለት በድፍረት እውነተኛውን አምላክ መስክሯል። በዚህም ምክንያት ልዩ ልዩ አሰቃቂ መከራዎችንና ስቃዮችን የተቀበለ ቢሆንም፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየተገለጠለት አጽናንቶታል። በመጨረሻም ኅዳር ፳፭ ቀን አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ የሰማዕትነትን አክሊል ደፍቷል። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተገደለ በኋላም ቢሆን በሥዕሉ አማካኝነት ከሃዲውን ዑልያኖስን በመግደልና በበረሃ የጠፋውን ወጣት ወደ ክርስትና በመመለስ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል። ዛሬም በቃል ኪዳኑ ለሚማጸኑት ፈጣን ተራዳኢና አማላጅ ነው። የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት፣ በረከትና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን። በቃል ኪዳኑ ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከክፉ ሁሉ ይጠብቅልን፤ ሰላሟንና አንድነቷን ያጽናልን። አሜን!!

  • ❖ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ❖ “ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያበባል፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል” (መዝ. ፺፩፥፲፪) መጋቢት ፳፬ (24) ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያዊውን ጻድቅ፣ የሐዋርያውንና የባሕታዊውን የአባታችንን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል አስባ ትውላለች። የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ረድኤትና በረከት፣ የቃል ኪዳናቸው ጥበቃና ምልጃ በሁላችን ላይ ይደር።

  • በመካከላችን የማይነካ ሰላምንና የማይፈርስ አንድነትን ያጽናልን። ❖ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ዳንኤል ❖ “አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ” (ዳን. ፮፥፳፪) መጋቢት ፳፫ (23) ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከዐበይት ነቢያት አንዱ የሆነውን የቅዱስ ዳንኤልን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል ታስባለች። በዚህች ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወርኃዊ መታሰቢያም ነው። ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር የተወደደች ሀገራችንን ኢትዮጵያን መሐሏን ገነት አድርጎ፣ ዳር ድንበሯን ደግሞ በመለኮታዊ እሳት ይጠብቅልን። በመካከላችን የማይነካ ሰላምንና የማይፈርስ አንድነትን ያጽናልን። ለሁላችንም ከክፋት የምንርቅበትና ወደ እርሱ የምንቀርብበትን የዕድሜ ባለጸግነትና የንስሐ ዘመንን ይስጠን። ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን፣ በሰማያዊት ኢየሩሳሌም የመንግሥቱ ወራሾች፣ የዘለዓለማዊ ክብሩም ቀዳሾች ያድርገን። በቅዱሳን ነቢያትና በሰማዕታት ጸሎት ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክልን። የአንበሶቹን አፍ የዘጋና ቅዱሳኑን በፈተና መካከል ያጸና አምላክ እኛንም ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይጠብቀን፤ አሜን

  • без подписи

  • ❖“ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤” ❖ (ሉቃ. ፩፥፵፰) ዛሬ መጋቢት ፳፩ (21) ቀን የዓለም ሁሉ መመኪያ፣ የድኅነታችን ምክንያትና የአምላክ እናት  የቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና የቃል ኪዳኗ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። እመቤታችን በምልጃዋ ከልጇ ታስታርቀን። በንስሓ ታጥበን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን የአባቶቻችን አምላክ ይርዳን፤ አሜን!!

  • ወር በገባ በ፳ (20) ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት (ሕንፀታ ቤታ)፣የታላቁ ነቢይ የቅዱስ ኤልሳዕ፣ የቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር፣  እንዲሁም የሰማዕቱ የቅዱስ በብኑዳ ወርኃዊ የመታሰቢያ በዓል ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ፣ የጻድቃን ምልጃ፣ የሰማዕታት በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን። አምላካችን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና አማላጅነት ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይጠብቀን፤ በሃይማኖትና በምግባር አጽንቶ ለክብሩ መንግሥት ያብቃን። አሜን!!

  • Niqoodimoos" torbaffaa Sooma Guddaa https://www.facebook.com/100085509522860/posts/pfbid02dsxwNCgMpbSfGM1pUh8mykHe4UEB6DMxGFrzbsxBZ9oeNzBmFhc9txnqqhXtimqZl/

  • ❖ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ❖ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” (ሉቃ. ፩፥፲፱) ዛሬ መጋቢት ፲፱ (19) ቀን የምሥራች ነጋሪውንና የእግዚአብሔር ባለሟል የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ወርኃዊ መታሰቢያ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ስሙ ትርጓሜው 'አምላክና ሰው' ማለት ሲሆን፣ እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን በወደደ ጊዜ የድኅነታችንን የምሥራች ለድንግል ማርያም ያበሰረ ታማኝ መልእክተኛ ነው። ይህ ቅዱስ መልአክ በብሉይ ኪዳን ዘመን የአምላክን ትእዛዝ ንቀው ለጣዖት አንሰግድም ያሉትን ሠለስቱ ደቂቅን (ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎን) ከነበልባሉ እሳት መካከል ወርዶ ያዳነና እሳቱን ወደ ቀዝቃዛ ጠል የለወጠ የኃይል መልአክ ነው። እንዲሁም ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስት ጉድጓድ የታደገ፣ ለዘካርያስ የዮሐንስን መወለድ ያበሰረና በቅዱሳን ተጋድሎ ሁሉ ረዳት ሆኖ የሚቆም በመሆኑ 'የምሥራች ሰባኪ' ተብሎ ይጠራል። ቅዱስ ገብርኤል ለሰው ልጆች ሁሉ የደስታና የድል መልእክት ይዞ የሚመጣ በመሆኑ፣ ምእመናን በጸሎታቸውና በመማጸናቸው ተራዳኢነቱን ያገኛሉ። በቅዱሳት መጻሕፍትና በድርሳነ ገብርኤል ላይ እንደተጠቀሰው፣ ይህ መልአክ በእግዚአብሔር ፊት ከሚቆሙ ታላላቅ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚማጸኑ ሁሉ ፈጣን ረድኤቱን ይሰጣል። የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ በሁላችንም ላይ ይደር። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ፣ የጻድቃን ምልጃ፣ የሰማዕታት በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን። ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶነ እሳት ያዳነ መልአክ እኛንም በመልአኩ ፈጣን አማላጅነት ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይጠብቀን፤ በሃይማኖትና በምግባር አጽንቶ ለክብሩ መንግሥት ያብቃን። አሜን!!

  • ❖ ኒቆዲሞስ ❖ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) “ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ ፫፥፭ ቅዱስ ያሬድም ብሉያትን ከሐዲሳት እያስማማ ለጆሮ የሚስማማና ሕሊናን የሚመስጥ ድንቅ ዜማ ባዘጋጀልን መሠረት የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ ተብሎ ይጠራል።

  • ❖ ጻድቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ከፋሌ ባሕር) ❖ "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።                                               ያዕቆብ 5፥16 መጋቢት ፲፰ (18) ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ፣ የጻድቃን ምልጃ፣ የሰማዕታት በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን። ጻድቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ከባሕር ማዕበል ያዳነና በሰላም ያሻገረ አምላክ እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና አማላጅነት ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይጠብቀን፤ በሃይማኖትና በምግባር አጽንቶ ለክብሩ መንግሥት ያብቃን። አሜን!!