tgindex
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

Статистика

@Tewahdo27 ✞ በየጊዜው አዳዲስ መንፈሳዊ † ➢ ፅሁፎች ➢ መዝሙሮች ➢ ኦርቶዶክሳዊ መልእክቶች ➢ መንፈሳዊ ነገሮችን ሁሉንም ለማግኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞ ለአስተያየቶ @Tewahdo27 ይጠቀሙ ➢ ሁሉም እንዲያነበው SHARE ያርጉ ! እናመሰግናለን !

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
107
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 830
+3 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
586
40 постов
Вовлечённость
20,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 107
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
299
1/48двое суток
342
1/72трое суток
369

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ጾም በሰላም አደረሳችሁ❕ ​ጾመ ፍልሰታ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅርና በረከት በሁላችንም ላይ የሚፈስስበት፤ በተለይም የሕጻናትን ልብ በቅዱስ ደስታና በየዋህነት የሚሞላ የተቀደሰ ወቅት ነው። ​ሕጻናት በነጭ ነጠላ ተሸፋፍነው በጠዋት ወደ ቤተክርስቲያን ሲገሰግሱ፣ ታቦት ሰርተው በደስታ ሲዘምሩና ምጽዋት ሲካፈሉ ማየት የፍልሰታን በረከት ልዩ ያደርገዋል። ​እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት ያድርግልን፤ የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን❕ ​መልካም ወሬንና መንፈሳዊ በረከትን ማካፈል ትልቅ በጎነት ነው❕ ይህንን የተባረከ የመልካም ምኞት መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ (Share) በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ያድርጓቸው።    ​❖═ @Ortodox_27 ═❖ ❖══ @Ortodox_27 ══❖    ❖═ @Ortodox_27 ═❖

  • https://youtube.com/shorts/WjrYbctx_8M?si=itntmc3b5RAxdQQv

  • ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና። ማቴዎስ 7፥12 አንዳንድ ነገሮች ብዙ ማብራራት አያስፈልጋቸውም። የሚያስፈልጋቸው ይበልጥ በሕይወታችን ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ነው። ዐብረን እንድናደርግ እጋብዛችኋለሁ፦ ከሌሎች ጋራ ራሳችንን በምናገኝበት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ወርቃማውን ሕግ ለመፈጸም እንትጋ! https://kedusbible.com

  • ስለዚህ ከቶ ዝም አልልም፤ በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፤ በነፍሴም ምሬት አጕረመርማለሁ። ኢዮብ 7፥11 አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን ስለምናመነታባቸው ነገሮች በግልጽ ከርሱ ጋራ ለመነጋገር በጣም ደካማ፣ የራቀ ወይም ለመናገር የማይፈልግ እንደ ሆነ አድርገን እናስባለን። ሌሎች ደግሞ መቼም በእግዚአብሔር ላይ ጥርጣሬ፣ ንዴት ወይም ሐዘን ያለባቸው ሰዎች ሆነው መቅረብ አይፈልጉም። ኢዮብ ግን ስሜቱን ለመግለጽ ዐይናፋር አልነበረም። በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ንዴት፣ ሕመምና ሐዘን አልካደም ነበር። እግዚአብሔርን ከሚያከብርና ደስ በሚያሰኘውም መልኩ ከኖረ ሕይወት በመነጨ፣ እውነቱን ተናገረ (ኢዮብ 1፥1)። ምንም ብንደክም፣ ግራ ብንጋባም ወይም ምንም ዐይነት ወጀብ ውስጥ ብንሆን፣ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ያለንን ግንኙነት እንድንጠብቅ እንደሚፈልግ ኢዮብ ትልቅ ማስታወሻችን ነው። በትግሎቻችሁ ውስጥ ምንም ዐይነት ስፍራ ላይ ብትሆኑ፣ ለእግዚአብሔር ግልጽ ሁኑ። ስለ ስሜቶቻችሁ ግልጽ ሆናችሁ እርሱን አውሩት። አሁን ስላላችሁበት የሕይወት ምዕራፍ ግልጽ ሆናችሁ፣ ለሚሰማችሁ ሕመምና ሐዘን ዕውቅና ስጡ። እውነተኛ ሕመማችሁን፣ የጠለቀውን ጭንቀታችሁንና ትልቁን ፍርሀታችሁን እንዲያውቅና እንዲያገለግላችሁ ፍቀዱለት። የመዝሙር መጽሐፍ ለእግዚአብሔር ብዙ የጥያቄና የግራ መጋባት ጩኸቶችን ያስቀምጣል። ኢዮብ ስለ መከራውና ስለ ሕይወት ኢፍትሓዊነት በግልጽ ተናግሯል። ስለዚህ እናንተም፣ ለእግዚአብሔር ግልጽ መሆን ትችላላችሁ። ለልባችሁ እውነት ያልሆኑ ያማሩና የተስተካከሉ ቃላትን አለመጠቀም ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስ ቃላቶቻችሁን ሊያነጻና የማይነገሩ የልቦቻችሁን ስሜቶች ሊገልጽ ስለ እናንተ ይማልዳል (ሮሜ 8፥26-27)። ዝም አትበሉ፣ የመንፈሳችሁን ጭንቀትና የነፍሳችሁን ምሬት ለሚያዳምጣችሁና ለስሜታችሁ ለሚጠነቀቅላችሁ ለአባታችሁ ንገሩት። https://kedusbible.com

  • ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና። መዝሙር 7፥9 የተቀናጁ ወንጀሎች፣ ሙሰኛ መሪዎች፣ ሰው አዘዋዋሪዎች፣ ወሲባዊ ጥቃት የሚያደርሱ፣ ሽፍታዎች በበዙበት ዓለም ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ብዙ የምንሠራው ሥራ አለ። የምንኖርበት ባህል የሚከተለውን ጨቋኝ መንገድ መቀየር አለብን። ይህን የምንጀምርበት ቦታ ደግሞ በአብ ፊት ተንበርክከን፣ በዚህ ዐመፅ በሞላበት ዓለም ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንድንችል እንዲረዳን በመለመን ነው! በዘመናችን ከተለያዩ የዜና አውታሮች ዐመፆችን ስንሰማ ተንበርክከን ዳዊት በመዝሙረ ዳዊት 7 ላይ የጸለየውን ጸሎት እንጸልይ፤ ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና። https://kedusbible.com

  • 8 июл.4681из Orthodox_Tewahdo22

    без подписи

  • አሁን ግን ቀድሞ ጠፍሮ አስሮን ለነበረው ሞተን፣ ከሕግ ነጻ ወጥተናል፤ ይህም አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ አዲስ በሆነው በመንፈስ መንገድ እንድናገለግል ነው። ሮሜ 7፥6 ጽድቅን ለማግኘት ሕግን ከመጠበቅ ነጻ ወጥተናል! ይህ ማለት ሕግ አልባ ነን ማለት ነውን? በፍጹም! ከሕግ ነጻ ያወጣን ጸጋ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስም በውስጣችን ዐብሮን እንዲኖር አድርጓል። መንፈሱ በራሳችን ፈጽሞ ልናደርግ የማንችለውን ማድረግ እንድንችል ኀይል ሊሰጠን ይችላል (ኤፌሶን 3፥14-21)። መንፈሱ በድካማችን ወቅት በልበ ሙሉነትና በመታመን መጸለይ እንድንችል ያግዘናል (ሮሜ 8፥26-27)። በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ፣ በእግዚአብሔር ጸጋና በክርስቶስ መንፈስ የተያያዙ ኀላፊነት የሚወስዱ ጓደኞች ያሉበት ኅብረት ውስጥ ገብተናል። የመንፈስ ፍሬዎች የሆኑት ማለትም ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት (ገላትያ 5፡22-23) እናዳብር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳን እርስ በርስ መበረታታት እንችላለን። ኢየሱስን ስንፈልግና በሕይወታችን ስንገልጠው፣ እርሱን ይበልጥ እንመስላለን (2 ቆሮንቶስ 3፥17-18)። ቅድስናና ፍቅር በሚያስፈልግበት ዓለም ውስጥ በቅድስና እንድንኖር ይህን "አዲስ መንገድ" ስለ ሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን! https://kedusbible.com

  • መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣ መጻተኛውንና ድኻ አደጉን፣ መበለቲቱንም ባትጨቍኑ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም ባታፈስሱ፣ የሚጐዷችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣ ለአባቶቻችሁ ለዘላለም ርስት አድርጌ በሰጠኋቸው ምድር፣ በዚህ ስፍራ አኖራችኋለሁ። ኤርምያስ 7፥5-7 የባሕርያችን ትክክለኛ መለኪያ ምንድን ነው? "ቤተ ክርስቲያን" ወይም እንደ እኛ ባሉ ሰዎች ፊት የምናሳየው ባሕርይ አይደለም። ባሕርያችንን ወይም እውነተኛ መንፈሳዊነታችን የሚፈትነው በሰማይ ካለው አባታችን ጋራ ያለን ግንኙነትና እርሱ የጠፉትን፣ የተረሱትን፣ የተዋረዱትንና የተሰበሩትን በማዳኑ ሥራ ላይ ያለውን መተባበር ነው። በዚህ ቊጥር ላይ ደግሞ፣ "መጻተኛውንና ድኻ አደጉን፣ መበለቲቱንም" በማለት ይገልጻል። ለራሳችን ብቻ ስንኖርና "የሌላቸውን" ሰዎች ደግሞ ፍቅር፣ ፍትሕና ምሕረት መስጠት ብናቆም የምንኖርበት ባህልና ማኅበረ ሰብ ይፈርሳል። ምክንያቱም ለተረሱና ብቸኛ ለሆኑ የሚሆነውን የእግዚአብሔር ልብ አይኖረንም። በተጨማሪም፣ "የሌላቸው" ሰዎች ውስጥ ቅንአትና ቂም ያድራል፤ "ያላቸው" ደግሞ የበላይነት ስለሚሰማቸው ማኅበረ ሰቡ እንደ ማኅበረ ሰብ መቀጠል አይችልም! የባሕርያችን እውነተኛ መለኪያ፣ በዙሪያችን ያሉ የተቸገሩትን ሰዎች የምንወድበትን መንገድ ነው። https://kedusbible.com

  • የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ። ኤርምያስ 7፥3 ብዙ ጊዜ ያለንን ነገር፣ የምንኖርበት ቦታ፣ በሕይወታችን በረከት የሆኑልንን ጓደኞች፣ እንድናደግና የቤተኛነት ስሜትን የሰጡን ቤተ ሰቦች እንዲያው የመጡ ይመስለናል፤ ዋጋም አንሰጣቸውም። እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን ስጦታዎች ናቸው። የሚገቡንም አይደሉም። መለኮታዊ መብት አልያም ከዘራችን የተነሣ የሚገቡን ወይም የእኛ አይደሉም። እነዚህን በረከቶች ሠርተን አናመጣቸውም፤ ነገር ግን ልናጠፋቸው እንችላለን። እግዚአብሔር እርሱን እንድናስደስት ብቻ ሳይሆን ራሳችንና የምንወድዳቸውን ሰዎች መጠበቅ እንችል ዘንድ እንድንታዘዘው ይፈልጋል። ስለዚህ ለራሳችን ሳይሆን ለኢየሱስ ለመኖር ድርጊታችንን እናድስ። https://kedusbible.com

  • ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል። ምሳሌ 10፥2 ሀብት፣ በተለይ ደግሞ በራስ ወዳድነትና በክፉ መንገድ የተገኘ ሀብት ዘላቂ ዋጋ የለውም። ይህ ዐይነቱ ሀብት ልብን ያበላሻል። እንዲህ ዐይነቱ ሀብት በመጨረሻም ከመሞት አያድነንም። ነገር ጽድቅ ከሀብት በላይ የከበረ ነው። እውነተኛ ጽድቅ ከእግዚአብሔር ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የተቀበልነው የጸጋ ስጦታ ነው። ይህ ዐይነቱ ጽድቅ ከእኛ ሟችነት የሚያልፍ ነው። ጽድቅ ከምናከማቸውም የገንዘብ ሀብትም ይልቃል። ነፍሳችንንም ከሞት ያድናል። https://kedusbible.com

  • እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም መዝሙር 7፥1 የሚያሳድዳችሁ ምንድን ነው? በፊት የሠራችሁት ስሕተት ነው? የድሮ ጠላት ነው? ወደ ኋላ የሚጐትታችሁ ሱስ ነው? ኅሊናችሁ ነው? የጥፋተኝነት ስሜት ነው? እናንተ ላይ አካላዊ ጕዳት ማድረስ የሚፈልግ ሰው ነው? አካላዊ ሕመም ነው? ስለ ወደፊቱ ስታስቡ ርግጠኛ ያለመሆን አልያም የመፍራት ስሜት ነው? ብዙ የሚሰሙንና የምንፈራቸው ነገሮች አሉ፤ እነዚህ ነገሮችም እንደሚያሳድዱንም ይሰማናል። ስለዚህ ትልቁ ጥያቄ ይህ ነው፤ በሕይወት ማዕበል ውስጥ ሰላምንና ደኅንነትን ለማግኘት የምንሄደው ወዴት ነው? እውነተኛና ዘላቂ መሸሸጊያ አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም፣ እግዚአብሔር አምላክ ነው! ይህ ጌታም በርሱ ዘንድ ከተሸሸግን ነጻ ሊያወጣንና ሊያድነን ይፈልጋል! https://kedusbible.com

  • ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው። ዮሐንስ 6፥29 "ሥራህ ምንድን ነው?" ይህ በብዙ ባህል ውስጥ የሚጠየቅ ጥያቄ ነው። እርስ በርሳችን በላቀ መልኩ ዋጋችንን የምንተምነው በምንሠራው ሥራ ነው። ነገር ግን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋችን የሚተመነው ከርሱ ፍቅርና በኢየሱስ ላይ ካለን እምነት የተነሣ ነው። እግዚአብሔር እንድናሳካ የሚፈልገው ሥራ ወይም እንደ እርሱ ደቀ መዝሙር ሥራችን፣ በኢየሱስ ላይ ሙሉ ለሙሉ መተማመንና ሌሎችንም በኢየሱስ ላይ ያላቸው እምነት እንዲያድግ ማገዝ ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደ ላከው ማመን የሕይወታችን አንዱ አካል ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በሕይወታችን ያለው ሥራ ነው። https://kedusbible.com

  • የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩ። ሉቃስ 6፥28 ኢየሱስ ምሳሌ ባይሆንልን ኖሮ፣ ይህ ትእዛዝ ምንም ትርጕም አይሰጠንም ነበር። ነገር ግን ዕጣ ፈንታችንን በአምላካችንና በአባታችን እጅ የመተውን አስፈላጊነት ያሳየናል። በድንገት፣ ይህ ትርጕም ይሰጣል። ጠላትን የማሸነፍ ምርጡ መንገድ ምንድን ነው? በርግጠኝነት ያንን ሰው መምታት ወይም መግደል አይደለም። ጠላቶቻችንን የምናሸንፍበት ምርጡ መንገድ የኢየሱስ ጸጋ ልባቸውን እንዲያሸንፍና ባሕርያቸው የንጉሣችንን መስሎ ከእኛ ጋራ ለጌታ እንዲኖሩ ስናደርግ ነው! ጠላቶቻችንን የምናሸንፍበት መንገድ ይህ ነው፤ ወደ ኢየሱስ እናመጣቸዋለን፤ በክርስቶስ ያሉ ወንድሞችና እኅቶች ይሆኑናል። https://kedusbible.com

  • “በማንኛውም የመንግሥቴ ግዛት ሰው ሁሉ፣ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር ይህን ዐዋጅ አውጥቻለሁ። “እርሱ ለዘላለም የሚኖር፣ ሕያው አምላክ ነውና፣ መንግሥቱ አይጠፋም፤ ለግዛቱም መጨረሻ የለውም። እርሱ ይታደጋል፤ ያድናልም፤ በሰማይና በምድር፣ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋል፤ ዳንኤልን፣ ከአንበሶች አፍ አድኖታል።” ዳንኤል 6፥26-27 እግዚአብሔር ለአበቦች ውበትን፣ ለሳሮች ደግሞ ሕይወትን ሰጥቷል። ከትላልቅ እውነቶችና መዋቅሮች ተነሥተን ካሰብን፣ እነዚህ ነገሮች ጊዜያዊና ኢምንት ናቸው። እንዲያድነን ልጁን ከሰማይ ላከልን፤ ስለዚህ ወደቤታችን ሄደን ከርሱ ጋራ እስክንኖር ድረስ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ይሰጠናል! እግዚአብሔር የፈጠረውን ውበት ተመልክተን ከእነርሱ በላይ እንደሚወድደን፣ እንደሚመግበንና ወደ ቤቱም ሊወስደን ቃል እንደ ገባ እናስታውስ! https://kedusbible.com

  • 26 июн.610из ortodox_27

    https://youtu.be/4JfRYDAjD6w?si=BCPN1BP7XKsS-wHC

  • https://youtube.com/shorts/VL7WV13ymIM?si=fNTzW8s0Il0ad7FV

  • በሞቱ ከርሱ ጋራ እንደዚህ ከተባበርን፣ በትንሣኤው ደግሞ በርግጥ ከእርሱ ጋራ እንተባበራለን። ሮሜ 6፥5 ስለዚህ ትልቁ ዜና ይህ ነው፤ በእምነትና በጥምቀት በኩል ከክርስቶስ ጋራ ከሞትን፣ አስፈላጊውንና ዋናውን ሞት ሞተናል። ሕይወታችን ከክርስቶስ ሕይወት ጋራ ተሳስሯል፤ ስለዚህም፣ ዳግም ሲመለስ የጌታን ክብር ዐብረን እንደምንጋራው ርግጠኞች መሆን እንችላለን (ቈላስይስ 3፥1-4)። ሞት እንኳ በሕይወታችን ውስጥ ያለውን የኢየሱስን ህልውና ሊወስድብን አይችልም (ሮሜ 8፥35-39)። ምክንያቱም፣ በጌታችን በኢየሱስ በኩል በሞት ላይ ድል ተሰጥቶናል (1 ቆሮንቶስ 15፥55-57)። የሚመጣውን ፍርድና ሁለተኛው ሞት ሊያስፈራን አይገባም። ምክንያቱም፣ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግረናል (ዮሐንስ 5፥24)። ጳውሎስ በርግጠኛነት እንዲህ ይላል፤ "በሞቱ ከርሱ ጋራ እንደዚህ ከተባበርን፣ በትንሣኤው ደግሞ በርግጥ ከርሱ ጋራ እንተባበራለን።" https://kedusbible.com

  • አባቶች ሆይ፤ እናንተም ልጆቻችሁን አታስቈጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና ተግሣጽ አሳድጓቸው። ኤፌሶን 6፥4 በሚልክያስ 4፥6 በሚመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች እንደሚመልስ ይናገራል። ይህን ልጆቻችንን በመንከባከብና በመገሠጽ በቤታችን እውን እናድርገው። በእንክብካቤና በተግሣጽ መካከል ያለውንም ሚዛን እንጠብቅ። ልጆቻችን እንደምንወድዳቸውና በእነርሱ ደስ እንደሚለን መረዳት እስከሚከብዳቸው ድረስ ለመታዘዝ በሚከብዱ ሕጎችና ሥርዐቶች ቤታችንን አንሙላ! የሞራል ምስቅልቅል በበዛበት ዓለም ውስጥ እንዴት መኖር እንዳለባቸው ግራ እስኪገባቸውና ችላ የመባል ስሜት እስከሚሰማቸውም ድረስ ነጻነት አንስጣቸው። ልባችንን ወደ እነርሱ አድርገን፣ እግዚአብሔር የልጆቻችንን ልብ ወደ ቤታቸውና በሰማይ ወዳለው አባታቸው እንዲያደርጉ እንጸልይ! https://kedusbible.com

  • 4 июн.691из Orthodox_Tewahdo22

    https://www.tiktok.com/@danu_daniel_27?_r=1&_t=ZS-96vdmsRUjzQ

  • без подписи