tgindex
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ💒❤️‍🩹

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ💒❤️‍🩹

Статистика

"ለነፍሴነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና እንዳልጠፋ አምናለው ያንቺ ልጅ ነኝና">>>> ✅ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ✅መዝሙሮች እንዲሁም ግጥምና መልዕክቶችን ✅እናስተላልፍበታለን... ✅የቅዱሳን ታሪኮች ✅መንፈሳዊ መፀሀፍቶች ወዘተ... መሳደብ ፣ የማይሆን ቃል መናገርና መልቀቅ ❌ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 622
+3 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,06%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
267
24 постов
Вовлечённость
16,5%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
135
1/48двое суток
154
1/72трое суток
166

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 7 авг.301151

    የበረከት ፆም ያድርግልን ❤️

  • ጾመ ፍልሰታ Today - ነሐሴ 1, 2018 || ጾመ ፍልሰታ ከነሐሴ 1-15 ቀን የሚጾም የድንግል ማርያም ፍልሰታ ዋዜማ ጾም ነው። ይህ ጾም የ15 ቀናት ሲሆን ሐዋርያት የድንግል ማርያምን ማረፍና ትንሣኤ ለማየት በጾምና በጸሎት ያሳለፉበትን ወቅት ያስታውሳል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❣ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/        🌺ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡   🌺ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡   🌺ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤  እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡   🌺የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡   🌺ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡   🌺ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡   🌺በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ 💛የጾሙ እና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤ አሜን💛

  • видео или голосовое, без подписи

  • ✨የዛሬን ብቻ አዉጣኝ /ይቅር በለኝ / እንጂ ከዚህ በኋላ ስህተት አልሰራም እያልን ስንት ስህተት እየሰራን እዚህ ደርሰናል። እግዚአብሔር ግን ታጋሽ በምሕረቱም ባለጠጋ ነውና ስሙ ለዘለአለም የተመሰገነ ይሁን🙏

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሰላም እንዴት አደራችሁ ተወዳጆች በዚህ በማለዳ አንድ ነገር ልበል ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል ሸክማችሁን ሁሉ እሱ ላይ አራግፋችሁ ኑሩ ከዛ ባለፈ እመኑት እንደሚያኖራችሁ እንደሚያበላችሁ እመኑት "ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላልና" እግዚአብሔር ደግሞ እንደሚችል ማሳያ ያድርጋችሁ ዛሬን ያሻገራችሁ ነገንም እንደሚያሻግራችሁ እመኑ ! እግዚአብሔር እንደሚችል ማሳያ ያድርጋችሁ ! መልካም ቀን ቅዱስ አማኑኤል ሰላም ያውላችሁ ቀኝ ያውላችሁ ❤️

  • ፊልጵስዩስ 4 ⁴ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ⁵ ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ⁶ ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።

  • видео или голосовое, без подписи

  • የመድኃኔዓለም መምጫው አይታወቅም !

  • ሐምሌ 26 ዕረፍቱ ለዮሴፍ ጻድቅ ሰዉ ሁሉ ባወቀዉ ታማኝነትህን      ኢየሱስ ክርስቶስ ቸሩ ፈጣሪህ     ከደጋጎች ሁሉ አንተኑ መርጦህ    ድንግል ወላዲቷን አደራ ሰጠህ    አረጋዊ ዮሴፍ አንተስ ብጹዕ ነህ

  • ✝ ወደ ክርስቶስ መገስገስ የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ "ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው ፡፡"

  • ❝ትላንት ያሳለፈንን አማልካችንን ትተን በሰዎች መመካት ስንጀምር ውድቀታችን ያኔ ይጀምራል !

  • видео или голосовое, без подписи

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ💒❤️‍🩹 — tgindex