tgindex

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

описание

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

39 764
подписчиков
Охват к подписчикам
29,7%
ERR
Реакции к просмотрам
0,88%
2 665 на 23 постов
Пересылки к просмотрам
0,12%
367
Постов в день
0,6
всего 23

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 6 авг.✠🌿✠ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሠላም አደረሳችሁ። ✠🌿✠ ⛪ በቀበና ምሥራቀ ፀሐይ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል 📖 የውዳሴ ማርያም እና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ 🗓️ ከሰኞ - ዐርብ 🕟 ከቀኑ 4:30 - 6:00 🗓️ ቅዳሜና እሑድ ⛪ ከቅዳሴ በመቀጠል 🕑 ጠዋት 2:00 ጀምሮ 🎙️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ይተረጎማል። 📡 የቀጥታ ሥርጭት የምታስተላልፉ ሚዲያዎች በተጠቀሰው ሰዓት ተገኝታችሁ ማስተላለፍ የምትችሉ መኾናችኹን እንገልጻለን። ✠🌹 በእመቤታችን ፍቅርና በረከት በሁላችንም ይደር። 🌹✠2,46%
  • 15 авг.без подписи2,26%
  • 14 авг.https://www.youtube.com/live/wFKQlG6y83o?si=XCgk8UZpxMqFrW871,87%
  • 25 июл.[ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል] ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ዶሮዳስ ታደሰ ❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው። ❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡ ❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡ ❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡ ❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል። ❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ዐምስት መቶ ሦስት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ ✔ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡- “እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ ወስምዖ መጥበቤ ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ ለአባልከ ሰላም እቤ” (እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦ “ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ በልደት ንዑስ፤ ንጹሕ ከመ ዕጣን ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡ (በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል) ❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡ (ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨ [የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨ [ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ1,71%
  • 13 авг.https://www.youtube.com/live/uM9l9DcN9uQ?si=ffWs5YIx2Qiav5yX1,64%
  • 7 авг.https://www.youtube.com/live/mLPp6j4HXSA?si=tNaJXt9bFBZJOfFp1,63%
  • 12 авг.https://www.youtube.com/live/DyhhpkSEf9s?si=YuLjw7zWC-yu4mUM1,54%
  • 9 авг.https://www.youtube.com/live/joqVEM2oDNY?si=56R3MZv-H1RuLbGF1,36%
  • 11 авг.https://youtu.be/42nL8RlJ8MY?si=qn0baQSHty4PXuml1,30%
  • 8 авг.https://www.youtube.com/live/RqslEofIb-4?si=8HkRWZ3oaIGFsJx81,19%
  • 11 авг.https://www.youtube.com/live/mfdVdZTbDfM?si=MLL8bKjXxk2qO4mB1,14%
  • 24 июн.без подписи1,09%