SEBAT INSTITUTE
Статистикаሰባት ኢንስቲተዩት በሁለንተናዊ አቋሙ የተስተካከለ እና ኢስላምን ወደተሻለ እርከን ከፍ የሚያደርግ ትዉልድን ቀርፆ ለሙስሊሙ ኡማ ለማበርከት እየተንቀሳቀሰ ያለ ህጋዊ ተቋም ነዉ ። @SEBAT_INSTITUTE
- Последний пост
- 1 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 37
- 1/48двое суток
- 42
- 1/72трое суток
- 45
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ለ12ኛ ክፍል ተመራቂዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉 የማይረሳ የምረቃ ቀንዎን ከእኛ ጋር ያክብሩ! በፕሮግራሙ የሚጠብቋችሁ፦ 📍የጋራ የፎቶ ፕሮግራም 📍ለተመራቂዎች የተዘጋጁ ልዩ ስጦታዎችና ሰርፕራይዞች 📍 ሰርተፊኬት እና ሽልማቶች 📍 በMS League የሚዘጋጁ ስልጠናዎችና ፕሮጀክቶች ላይ የመሳተፍ ዕድል 📍የመድረክ ፕሮግራም 📍በMS League የሚዘጋጁ የስኮላርሺፕ ናቪጌሽን ፕሮግራሞች ላይ የመሳተፍ ዕድል 🎪አራዳ ፓርክ 🗓️ነሐሴ 3 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ 🔗 የምዝገባ ሊንክ https://msleague.org/f/kglqdt0zo8xtvo 📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0962333331 / 0962333332
اللهم صل وسلم على نبينا محمد 🍃 ❤️🩹
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
اللهم صل وسلم على نبينا محمد ❤️🩹🍃
የዐሹራእ ፆም . ሙሐረም 10 ነብዩላህ ሙሳ(ዓ.ሰ) ከአንባገነኑ የፊርዓውን ጭቆና ነፃ የወጡበት ቀን ነው:: ይህን ቀን አንድ ቀን ቀደም ተብሎ ሙሐረም 9 አልያ ሙሐረም 11ን በማስከተል መፆም ይወደዳል:: ረሱል ስለ አሹራ ፆም ሲናገሩ "ምናልባት ለሚቀጥለው አመት በህይወት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም እፆማለሁ ብለዋል (ሶሒሁ ሙስሊም 1134) ሙሐረም 10 የአሹራ ቀን የፊታችን ሐሙስ ሰኔ 18 (Jun 25)ነው:: ይህን ቀን መፆም የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ) "የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል (ሶሒሁ ሙስሊም 1163) ቤተሰባችንንም ሌላውንም ይህን መልዕክት እናስታውስ!
видео или голосовое, без подписи
اللهم صل وسلم على نبينا محمد 🍃 ❤️🩹
☆☆ እንኳን ለ1448 ሂጅራ አመት በሰላም አደረሰን☆☆ ሂጅራ ታሪካዊ ቀን ነዉ::ተአምራዊ ሽግግር የተደረገበት ክስተትም ነዉ-ታላቁ ነብይ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)ከግለሰብ ሙስሊም ግንባታ ወደ ሙስሊም ማህበረሰብ የተሸጋገሩበት አስደማሚ ክንዉን::ለሙስሊም አገር ግንባታ መሠረት የተኖረበትም ጭምር!!! በዐረበኛ ቋንቋ ሂጅራ የሚለዉ ቃል አንድን ሃሳብ,ባህሪይ,ማህበረሰብ,አከባቢ,ነባራዊ ሁኔታን መተዉ መራቅ መሸሽን ያመላክታል:: በሸሪዐዊ ትርጓሜዉ ደግሞ ወደ ተሻለ ሃሳብ: ወደ ላቀ ባህሪ ና ከባቢ: ባጠቃላይ ከፍ ወዳለ ሁኔታና ማንነት ማደግ መላቅ ና መሽጋገርን ይጨምራል:: በመሆኑም ኸሊፋዉ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ(ረ.ዐ)"የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)ስደት እዉነት ከዉሸት ተብጠርጥሮ የተለየባት እለት በመሆኗ ለሙስሊሞች ቀን መቁጠሪያ መነሻ አድርጓት"በማለት የኛ ቀን መቁጠሪያ(ካላንደር) ትሆን ዘንድ ሃሳቡን አፀኑ::እነሆ 1448 ሆነን:: አልሐምዱሊላህ!!! አዲሱ አመት ከጥፋት ወደ ልማት,ከኃጢአት ወደ ተዉበት,ከችኩልነት ወደ ስክነት,ከስሜት ወደ እዉቀት,ከክስረት ወደ ክብረት የምንሸጋገርበት ይሁንልን!!! የተሻለ ያቀድንበት ና የላቀ ዉጤት የምናሳካበት የፍትህ የበረካ የስኬት አመት ያርግልን!!! አገራችንን,አህጉራችንን,ዓለማችንን አማን እኛንም እዉነተኛ አማኝ ያድርገን!!! ዒባዳ የሚጣፍጠን የሚፍናቀን :ወንጀል የሚጎመዝዘን የሚርቀን:የእዉነት ባንዲራ ከፍ ብሎ የሚዉለበለብበት:መቼም የማይወርድበትአመት ይሁንልን!!! ﴿ ثُمَّ يَأْتِي مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ عَامٌ فِيهِ يُغَاثُ النَّاسُ} ከዚያም(የችግር አመታት)በኃላ ሠዎች የሚዘነቡበት(የሚረዱበት,የሚታገዙበት) አመት ይመጣል. ሱረቱ ዩሱፍ 49 አያ ወንድማችሁ ዐብዱረሕማን መሐመድ የመሐመድ አባት
اللهم صل وسلم على نبينا محمد 🍃 ❤️🩹
After a long period of absence and silence, Sebat is back — bringing fresh ideas, renewed energy, and a commitment to uplift and serve the community. With new initiatives and a spirit of dedication, Sebat steps forward once again to inspire growth, strengthen bonds, and contribute meaningfully to the collective journey. Take Back Ctrl of Your Time is a one‑time interactive workshop that teaches students how to make the best out of their summer break by reclaiming control of their time. The session combines practical time‑management techniques with an Islamic touch, inspiring discipline, balance, and purposeful living. Objectives: - Help students plan and use summer productively - Teach practical time‑management strategies - Encourage balance between rest, study, and spiritual growth - Motivate students to set meaningful goals -Help them become agents of change and shape their era. https://forms.gle/zdSyy5WqDrkhRkk99 @sebat_institute
видео или голосовое, без подписи
የዶ/ር አብዱልቃድር አደም በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ በተራ ቁጥር 12 ይገኛሉ። እባክዎ ይህንን መልክት ለሚያውቋቸው ሰዎች ይላኩ።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲን ነው እኔ የምመርጠው። ብእር
🕋 የዓመቱ ምርጥ ቀን‼ =============== (የዐረፋ ቀን ልዩ ሚስጥር እና ወርቃማው ዕድል!) || ✍️ ዱንያ በሙሉ እንደ ዐረፋ ቀን የምትደምቅበት፣ አላህ በባሮቹ የሚመካበት፣ እዝነት እንደ ዝናብ የሚዘንብበት እና ወንጀል እንደ ቅጠል የሚረግፍበት ሌላ ቀን የለም! ✅አዎ! ዛሬ ማክሰኞ የዙል-ሒጃ 9ኛው ቀን (የዐረፋህ ቀን) ነው። ይህ ቀን እንዲሁ ተራ ቀን አይደለም፤ በውስጡ አዕምሮን የሚያስደምሙ፣ ልብን በናፍቆትና በተስፋ የሚሞሉ ታላላቅ ሚስጥሮች አሉት። ✅ እስኪ ይህን ቀን ታላቅ የሚያደርጉትን 6 አስገራሚ ምክንያቶች በሐዲሥና በቁርኣን መነፅር እንመልከት፦ 1⃣ የዓመቱ ምርጥ ቀን መሆኑ! ነብዩ ﷺ በግልጽ አዋጅ እንዲህ ብለዋል፦ «أفضل الأيام يوم عرفة» «ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ነው!» (ኢብኑ ሒባን)። አላህ ከፈጠራቸው ቀናቶች ሁሉ (ከጁሙዓም፣ ከረመዿንም ቀናት) በላጩ ይህ ቀን ነው። አላህ የዚህን ቀን ታላቅነት ለማሳየት በሱረቱል ፉጅር ውስጥ "ወል-ወትር" (በነጠላው እምላለሁ) በማለት ምሎበታል! ታዲያ የዓመቱን ምርጥ ቀን በዝንጋቴ ማሳለፍ እንዴት ይገባል? 2⃣ ዲን ሙሉ የሆነበት ታሪካዊ ቀን! 🎀 አንድ አይሁዳዊ ወደ ዑመር ኢብኑል ኸጥጧብ መጥቶ፦ «እናንተ ሙስሊሞች በቁርኣናችሁ የምትቀሯት አንዲት አያት አለች፤ እሷ አያት እኛ አይሁዶች ላይ ወርዳ ቢሆን ኖሮ፣ የወረደችበትን ቀን 'በዓል' አድርገን እናከብረው ነበር!« አለው። ዑመርም፦ "የቷ አያት ናት?" ሲሉት፣ አይሁዳዊው ይህችን አንቀፅ አነበበ፦ ﴿الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا﴾ «ዛሬ ኃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ኢስላምንም ለእናንተ ከኃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡» [አል-ማኢዳህ፡ 3] ዑመርም መለሱለት፦ «ይህች አንቀፅ የወረደችበትን ቀን እና ቦታ ጠንቅቀን እናውቃለን፤ ነብዩ ﷺ ዐረፋ ሜዳ ላይ ቆመው፣ ዕለቱ ጁሙዓ በነበረበት ቀን ነው የወረደችው!» [ቡኻሪና ሙስሊም] አዎ! ዐረፋ የእስልምና የሙሉነት ማህተም የተመታበት ቀን ነው! 3⃣ የሁለት ዓመት ወንጀል የሚታበስበት ፆም! 🎀 አላህ የዚህን ቀን ፆም አጅር ያደረገው እጅግ በሚያስገርም የሒሳብ ስሌት ነው። አንድ ቀን በመፆም ብቻ የ730 ቀናት (የ2 ዓመት) ወንጀል ይታጠባል! ነብዩ ﷺ ተጠየቁና እንዲህ አሉ፦ «صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ» «የዐረፋን ቀን መፆም ያለፈውን አንድ ዓመት እና የሚመጣውን አንድ ዓመት ወንጀል እንደሚያብስልኝ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ።» [ሙስሊም፡ 1162] 📌 አስገራሚው ነጥብ፦ ያለፈውን ወንጀል አላህ መማሩ ይታወቃል؛ ነገር ግን «የሚመጣውንም አመት ወንጀል ያብሳል» ማለት ምን ማለት ነው? ዑለማዎች ሲያብራሩት፦ «አንደኛ፡ አላህ በሚመጣው ዓመት ትልልቅ ወንጀል ከመሥራት ይጠብቅሃል (ይጋርድሃል)። ሁለተኛ፡ ብትሳሳት እንኳን፣ አስቀድሞ ይህን ፆምህን ሰበብ አድርጎ ወንጀልህን ይምረሃል!» ይላሉ። ሱብሐነል'ሏህ! ይህን ዕድል የሚተው ሙስሊም አለ? 4⃣ አላህ ራሱ «እኔን ለማየት ኑ» ብሎ በባሮቹ የሚመካበት ቀን! 🎀 ይህ ትዕይንት ልብን ያቀልጣል! በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሑጃጆች ፀሀይ እየመታቸው፣ አቧራ ለብሰው ዐረፋህ ሜዳ ላይ ሲቆሙ... አላህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርድና መላእክቶቹን ሰብስቦ እንዲህ ይላል፦ «يَا مَلَائِكَتِي، انْظُرُوا إِلَى عِبَادِي أَتَوْنِي شُعْثًا غُبْرًا ضَاحِينَ مِنْ كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ...» «መላእክቶቼ ሆይ! እስኪ ወደ ባሮቼ ተመልከቱ፤ ጸጉራቸው ተንጨባርሮ፣ አቧራ ለብሰው፣ ፀሐይ እየመታቸው ከየሩቅ መንገዱ ሁሉ ወደኔ መጡ። ወንጀላቸውን እንደማርኩላቸው አስመሰክራችኋለሁ!» [አሕመድ እንደዘገቡት!] 5⃣ ጀሀነም ባዶ የምትቀርበት ቀን! 🎀 ከዚህ ቀን የበለጠ አላህ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም! እናታችን ዓኢሻ ባስተላለፈችው ሐዲሥ ነብዩ ﷺ፦ «مَا مِنْ يَوْمٍ أَكْثَرَ مِنْ أَنْ يُعْتِقَ اللَّهُ فِيهِ عَبْدًا مِنَ النَّارِ مِنْ يَوْمِ عَرَفَةَ...» «አላህ ከዐረፋህ ቀን የበለጠ ብዙ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ምንም ቀን የለም!» ብለዋል። =ሙስሊም፡ 1348] አላህ ነፃ ከሚያወጣቸው ውስጥ እኛንም እንዲያካትተን ዱዓእ እናብዛ! 6⃣ ከዱዓዎች ሁሉ ምርጡ ዱዓእ! 🎀 የዐረፋህ ቀን ዱዓእ ተቀባይነት በማግኘት ወደር የለውም። ነብዩ ﷺ ይህን ሚስጥር ሲነግሩን፦ «خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي...» «ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋህ ቀን ዱዓእ ነው። እኔም ሆንኩ ከእኔ በፊት የነበሩ ነቢያት ካሉት ቃል ሁሉ ምርጡ ደግሞ፡- ‹ላ ኢላሀ ኢለ-ልሏሁ፣ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር› ማለት ነው።» [ቲርሚዚ፡ 3585] ⚠️ ወሳኝ ማሳሰቢያዎች ለነገው (ማክሰኞ) የፆም ዕለት፦ 1️⃣ ማን ይፁም? የዐረፋን ቀን መፆም ሱንና (የተወደደ) የሚሆነው ሐጅ ላላደረገ (ቤት ለዋለ) ሰው ብቻ ነው። ዐረፋህ ሜዳ ላይ ለቆመ ሑጃጅ ግን መፆም አይወደድለትም ነብዩም ﷺ እዚያ ቦታ ላይ ሆነው አልፆሙም፤ ምክንያቱም ፆሙ አቅም አሳጥቶት ከዱዓና ከዚክር እንዳያዘናጋው ነው። 2️⃣ ከዚህ በፊት ያለፉትን 8 ቀናት ላልፆመ ሰው፦ ከዙል-ሒጃ መግቢያ ጀምሮ እስካሁን ምንም ላልፆመ ሰው ቢሆን፣ ነገ 9ኛውን ቀን (የዐረፋን ቀን) ብቻ ነጥሎ መፆም ይቻላል! ምንም ችግር የለውም፤ አጅሩንም ያገኛል። 3️⃣ ቀዿ ያለበት ሰው፦ የረመዿን ቀዿ ያለበት ሰው፣ ነገ የዐረፋን ቀን «በዐረፋ ፆምም፣ በቀዿ ፆምም ኒያ አጣምሮ መፆም ይችላል። (ይህም የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች ፈትዋ ነው)። 4️⃣ ከነጋ በኋላ ኒያ ማድረግ፦ ማታ ኒያ ያላደረገ ሰው፣ ከነጋ በኋላ ምንም ምግብና መጠጥ ካልቀመሰ፣ «ዛሬ የዐረፋን ቀን ልፁም» ብሎ በቀልቡ ነይቶ መፆም ይችላል። ነገር ግን ምንዳው የሚሰላው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው። ⬅️ ውድ ወንድምና እህቶቼ! የነገው ቀን የህይወታችን ወሳኝ የለውጥ ቀን ነው። ነገን በፌስቡክ፣ በቲክቶክ እና በእንቅልፍ አናሳልፈው። አፍረን፣ አልቅሰን፣ ዱዓእ አድርገን፣ ጌታችንን የምንለምንበት ቀን ነው። ሰለፎች ወሳኝ ሐጃቸውን «የዐረፋህ ቀን ይድረስና ዱዓእ አደርግበታለሁ!» ብሎ ቀኒቱን በጉጉት ይጠባበቋት ነበር። ያ ረብ! በዛሬው ዕለት ከእሳት ነፃ ከሚወጡት፣ ወንጀላቸው ከሚማርላቸው፣ እና በዱንያም በአኺራም የልባቸውን ሐጃ ከምታወጣላቸው ምርጥ ባሮችህ መካከል አድርገን! አሚን! 🤲 (ይህንን ወርቃማ እና ህይወት ቀያሪ መልዕክት ለምትወዷቸው ሁሉ ሼር በማድረግ የኸይር ሥራው ተካፋይ ሁኑ!)
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
اللهم صل وسلم على نبينا محمد 🍃 ❤️🩹
видео или голосовое, без подписи