The Christian News
описание
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW
5 310
подписчиков
Охват к подписчикам
22,3%
ERR
Реакции к просмотрам
0,83%
564 на 50 постов
Пересылки к просмотрам
0,10%
67
Постов в день
0,4
всего 133
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 5 авг.4627 ሰዎች ወደ #ጌታ መንግስት ተጨምረዋል። "መልካም ወጣት ደማስቆ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን የሚዘጋጀው የ2018 ዓ.ም መልካም ወጣት መረሃ ግብር ከተጀመረ 4ኛ ሳምንቱ ላይ ደርሷል። እያንዳንዱ ስልጠናዎች አንድ ሳምንትን የሚፈጅ ሲሆን አሁን 4ኛው ዙር ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዙር ብቻ 1336 ሰዎች ከአለም ለማምለጥ እና ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ለመግባት መወሰናቸውን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች። ባለፉት 3ዙሮች በ1ኛው ዙር 940 ሰዎች በ2ኛው ዙር 1143 ሰዎች በ3ኛው ዙር 1208 ሰዎች ጌታን ለመቀበል የወሰኑ ሲሆን በአጠቃላይ በ4ዙሮች ብቻ 4627 ጌታን ለመቀበል ወስነዋል። #እግዚአብሔር ይመስገን!2,38%
- 12 авг.#ሰው ግን ምን ያክል በቀለኛ ሊሆን ይችላል ? የበቀል መጨረሻውስ ምን ይሁን ? የፓስተር ጻድቁ አብዶ "በቀል በቀለኛውን ያጠፋል" የተሰኘው መጽሀፍ በአፋን ኦሮምኛ እና በትግረኛ እየመጣ ነው። በእንግሊዘኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ አሁን ደግሞ በሁለት ቋንቋዎች በዝግጅት ላይ እንደሆነ ፓስተር ጻዲቁ ተናግረዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ ከሲና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰኔ 8 / 2017 ዓ.ም ከአንድ ዓመት በፊት ተመርቆ ለንባብ የበቃው መጽሀፍ በአሁኑ ሰዓት ለብዙዎች እንዲደርስ በአፋን ኦሮምኛ እና በትግረኛ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ከ50 አመት በላይ ያገለገሉ #እና የሙሉ #ወንጌል ሴሚናሪን 9 ዓመታት የሙሉ ወንጌልን ቤተክርስቲያንን ደግሞ በዋና ጸሐፊነት 8 አመታት የመሩ እና በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት የሆኑት ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ይህ መጽሀፍ ከ17 ዓመት በላይ ያስተማሩትን ትምህርት ወደ መጽሀፍ የተቀየረ ነው። #ትንቢተ አብድዩ መጽሃፍ ላይ ተንተርሶ በመንታ ወንድማማቾ ስር በሰደደ ጸብ ምክንያት አንዱ ሞተ አንዱ ተሰደደ በትውልዳቸው ጥላቻ ስር ሰደደ። ይህን #ድንቅ ታሪክ ለሁሉም ሊሆን በሚችል መልክ ተርከውታል። ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ https://www.youtube.com/watch?v=sU79nt70EYg&t=2463s2,16%
- 13 авг.የኢትዮጵያ አማኑኤል ሕብረት ቤተክርቲያን የመሪዎች ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደች ነው። በጉዲና ቱምሳ የስልጠና ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘው ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሃምሌ 7 እና 8 የሚካሄድ ሲሆን በጉባኤው የ2018 ዓ.ም የስራ ሪፖርት እና የ2019 ዕቅድ ጨምሮ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።2,10%
- 23 дек.без подписи2,04%
- 8 авг."እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም" ፓስተር ታምራት ሀይሌ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የዝማሬ አገልግሎት ብዙዎችን የባረኩት እና ከአንጋፋ አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ፓስተር ታምራት ከሰሞኑ በካናዳ ስለተደረገላቸው ድንገተኛ ሰርፕራይዝ ምስጋናቸው አቅርበዋል። በማህበራዊ ድህረገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የመላ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት "ለኅብረት ተጠርተናል" በሚል በቶሮንቶ ከተማ ባዘጋጁት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ እንድናገለግል በተጠራንበት፣ በኮንፈረንሱ መጨረሻ ላይ "የአገልግሎትህን 50ኛ ዓመት" በሚል በድንገት ሰርፕራይዝ አደረጉን። "ብርሃነ ወንጌል" በተሰኘች ቤተክርስቲያን በመዘምራን ቡድን የተሰለፍኩበት ዓመት ተጨምሮ ሲሰላ በእርግጥም 50 ዓመት መሙላቱን ያስተዋልኩት በኋላ ነው። እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም። የምንኖርባት ምድር ጠፍጣፋ (Flat) ብቻ ሳትሆን ወጣገባ እንደሆነች ሁሉ፣ ሕይወትም እንዲሁ ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም ቅሉ፣ ጌታን ለመከተል የመጀመሪያዋን እርምጃ እግሬን ካንሳሁበት ዕለት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ በማንከስም፣ በዳዴም ሆነ በሩጫ ዘመን እጄን ይዞ የመራኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፣ ይህን የሰማ ሁሉ ያመስግንልኝ። ወንድሜ ሸዋዬ ዳምጤ እንዳዜመው፣ "ቀሪ ዘመኔን" እንዲባርክልኝ እለምነዋለሁ፣ እናንተም ለምኑልኝ። "ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ" (ዘፍ. 35:3) "አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና። ተጨማሪ ለማንበብ Facebook1,81%
- 2 апр.без подписи1,77%
- 26 янв.без подписи1,32%
- 7 авг.#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ #የቄስ ጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ የኢትዮጵያወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ እና የቄስ ጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ። “እነርሱም አንድ እንዲሆኑ” የሚለውን የዮሃንስ ወንጌል 17 መሰረት በማድረግ በአዲስ አበባ ቦሌ ኢላሜ ኮንቬንሽን ሴንተር በተካሄደው ፕሮግራም የቄስ ጉዲና ቱምሳን የአገልግሎት እና የህይወት ሌጋሲ ማውሳት እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ ጽሁፎች ቀርበዋል ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ የጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን መስራች እና መሪ እንዲሁም የቄስ ጉዲና ልጅ ወ/ሮ ሌንሳ ጉዲና ተጋባዥ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ሲሉ ተቀብለዋል። በመድረኩ ቄስ ዶ/ር ሳሙኤል ደረሳ፣ ዶ/ር ተካልኝ ነጋ እና ዶ/ር ለማ ደገፋ ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበዋል። ዶ/ር ምህረት ደበበ የእለቱ ተናጋሪ መልዕክት አስተላላፊ ነበሩ። ቄስ ሃረገወይን ቃለ እግዚአብሔር ያቀረቡ ሲሆን፣ ቄስ ገመቺስ ደስታ (ፕሮፌሰር) እና ሃዋርያው ታምራት ታረቀኝ በጸሎት አገልግለዋል። ዘማሪ መስፍን ጉቱ፣ ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ፣ ዘማሪት ራሄል ተፈራ እና ዘማሪ ጉቱ ሽፈራው በዝማሬ ያገለገሉ ሲሆን የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ታዳጊዎች “አንድ ነን” የተስኘ ኬሮግራፊ አቅርበዋል። በኦቦሌሳ አዶላ1,25%
- 24 дек.без подписи1,19%
- 20 июл.ኮይኖኒያ የተሃድሶ ሚሲዮናዊት #ቤተክርስቲያን የምስጋና መረሃ ግብር አካሄደች። ቤተክርስቲያኒቱ በጎተራ አከባቢ ያላት አጥቢያ ሕጋዊነትን ለማስከበር ከአመታት በላይ የተሰራ ሲሆን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ካርታ በመገኘቱ የምስጋና እውቅና የመስጠት መረሃ ግብር የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው መሪዎች እኛ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል። እጅግ ተስፋ በሚያስቆርጥ አድካሚ እና ውጣ ውረድ የበዛበት ጉዞ ነበር ነገር ግን ተዓምራዊ በሆነ መንገድ መሬቱን ሙሉ በሙሉ መረከብ ችለናል ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ መሪ የሆኑት መጋቢ መራዊ ንቡሴ ናቸው። መጋቢ መጋዊ ከክርስቲያን ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ በእለቱ የተዘጋጀው መረሃ ግብር አንድም የምስጋና አንድም በሂደቱ ውስጥ የነበሩ አካላትን እውቅና ለመስጠት እና በቀጣይ ቤተክርስቲያን ለመስራት ያሰበቻቸውን እቅዶች በጋራ ለመወያየት እንደሆነ ተናግረዋል። ከተመሰረተች ከ30 ዓመት በላይ እንደሆናት የሚነገረው ኮይኖኒያ የተሃድሶ ሚሲዮናዊት ቤተክርስቲያን ባለፉት ሶስት አስርት አመታት የምስራቹን ወንጌል ለትውልድ ለማድረስ እየተጋች እንደነበረ በመድረኩ ተገልጿል። ቤተክርስቲያን በቀጣይ የእግዚአብሔር ቃል በታማኝነት ለብዙዎች ለመድረስ የምትተጋ ቤተክርስቲያን እንደሆነች መጋቢ መራዊ ንጉሴ አክለው ለክርስቲያን ዜና ተናግረዋል። በዮሐንስ ግርማ1,19%
- 5 маябез подписи1,18%
- 23 дек.без подписи1,14%