The Christian News
Статистикаይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 133
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 533
- 1/48двое суток
- 610
- 1/72трое суток
- 658
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኢትዮጵያ አማኑኤል ሕብረት ቤተክርቲያን የመሪዎች ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደች ነው። በጉዲና ቱምሳ የስልጠና ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘው ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሃምሌ 7 እና 8 የሚካሄድ ሲሆን በጉባኤው የ2018 ዓ.ም የስራ ሪፖርት እና የ2019 ዕቅድ ጨምሮ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።
ያልተነገሩ ነገር ግን የተኖሩ እውነተኛ የህይወት ምስክርነቶች እና አስተማሪ መልዕክቶች እንዳያመልጣችሁ። በክርስቲያን ዜና እየተዘጋጀ በየሳምንቱ የሚቀርበውን ተወዳጅ ሲና የተሰኘውን ፕሮግራም አጫጭር መልዕክቶች ከInstagram ይመልከቱ! follow ማድረጋችሁን አትርሱ። https://www.instagram.com/sinapodcast26?igsh=aWdrNGdqcTAxcWV6
#ሰው ግን ምን ያክል በቀለኛ ሊሆን ይችላል ? የበቀል መጨረሻውስ ምን ይሁን ? የፓስተር ጻድቁ አብዶ "በቀል በቀለኛውን ያጠፋል" የተሰኘው መጽሀፍ በአፋን ኦሮምኛ እና በትግረኛ እየመጣ ነው። በእንግሊዘኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ አሁን ደግሞ በሁለት ቋንቋዎች በዝግጅት ላይ እንደሆነ ፓስተር ጻዲቁ ተናግረዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ ከሲና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰኔ 8 / 2017 ዓ.ም ከአንድ ዓመት በፊት ተመርቆ ለንባብ የበቃው መጽሀፍ በአሁኑ ሰዓት ለብዙዎች እንዲደርስ በአፋን ኦሮምኛ እና በትግረኛ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ከ50 አመት በላይ ያገለገሉ #እና የሙሉ #ወንጌል ሴሚናሪን 9 ዓመታት የሙሉ ወንጌልን ቤተክርስቲያንን ደግሞ በዋና ጸሐፊነት 8 አመታት የመሩ እና በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት የሆኑት ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ይህ መጽሀፍ ከ17 ዓመት በላይ ያስተማሩትን ትምህርት ወደ መጽሀፍ የተቀየረ ነው። #ትንቢተ አብድዩ መጽሃፍ ላይ ተንተርሶ በመንታ ወንድማማቾ ስር በሰደደ ጸብ ምክንያት አንዱ ሞተ አንዱ ተሰደደ በትውልዳቸው ጥላቻ ስር ሰደደ። ይህን #ድንቅ ታሪክ ለሁሉም ሊሆን በሚችል መልክ ተርከውታል። ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ https://www.youtube.com/watch?v=sU79nt70EYg&t=2463s
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን 31ኛ ጠቅላላ ጉባኤው በምዕራብ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል ተከናወነ። በመረሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ም/ፕሬዝደንት መጋቢ ሰንበቶ ባሼ እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ም/ፕሬዝደንት ፓስተር ታሪኩን ጨምሮ እና የተለያዩ እህት ቤተእምነቶች እና ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል። የቤተክርስቲያኒቱ ብሔራዊ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀንካራ ሀርቃ ጉባኤውን በኦፊሴሉ ያስጀመሩት ሲሆን የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ እንግዶችን ተቀብለዋል። ብሔራዊ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀንካራ ሀርቃ በመክፈቻ ንግግራቸው በበጀት አመቱ ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የወንጌሉን የምስራች መስማታቸውን እና ከ36ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ጌታ ኢየሱስን የግል አዳኛቸው አድርገው መቀበላቸውን ጠቅሰው ከ23ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የውሀ ጥምቀት ወስደዋል ሲሉ ተናግረዋል። በጉባኤው በክልሉ የተገነባውን (ሂሊዮ አካዳሚ) የሚል መጠሪያ ያለውን ትምህርት ቤት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። በምርቃቱ ላይ በትምህርት ቤቱ ግንባታ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለሊዮ እና ሂልካ ሪንታኒያሚ ቤተእምነቷ ዕውቅና የሰጠች ሲሆን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ውስጥ ካገለገሉ እና ቀደምት አባቶች መካከል አንዱ የሆኑት ሄኪ ፔንትነን በስፍራው ተገኝተው “በቤተክርስቲያኒቱ እድገት መደሰታቸውን እና አሁንም በዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ወንጌልን መስራታችሁን ቀጥሉ” ሲሉ መልዕክታቸውም አስተላልፈዋል። ተጨማሪ ዝርዝር ለማንበብ Facebook ገፃችንን ይመልከቱ
እሳቸው የሕብረቱ መሪ በነበሩበት 10 ዓመታት እንደ ሕብረት ብቻ ሳይሆን እንደሀገር እጅግ በብዙ ጭንቅ ውስጥ የታለፈበት ጊዜ ነበር። ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ወደ ሃላፊነት ከመጡ ጀምሮ በተግዳሮት ውስጥ ያለፈውን ሃላፊነታቸውን በታማኝነት አስረክበዋል። ነገር ግን ከዚህ ቀደም ያልተሰሙ እና ያለፉባቸውን ተግዳሮቶችን ግን አጫውተውናል። ይህ ከአንጋፋው የወንጌላውያን መሪ ከሆኑት ፓስተር ጻዲቁ ጋር የተደረገ ቆይታ የመጨረሻው ክፍል ነው። 🛑🛑 Sina Podcast ላይ ያለውን ቆይታ ተመልክታችሁ ሃሳባችሁን እንድታጋሩን ግብዣችን ነው። https://youtu.be/sU79nt70EYg
ብዙዎች እረኛቸውን ትተው ሄዱ! 🚶♂️➡️🚶♂️➡️🚶♂️➡️ ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜ በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ሙሉ ትምህርቱን ኮሜንት ስር ያገኙታል።
"እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም" ፓስተር ታምራት ሀይሌ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የዝማሬ አገልግሎት ብዙዎችን የባረኩት እና ከአንጋፋ አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ፓስተር ታምራት ከሰሞኑ በካናዳ ስለተደረገላቸው ድንገተኛ ሰርፕራይዝ ምስጋናቸው አቅርበዋል። በማህበራዊ ድህረገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የመላ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት "ለኅብረት ተጠርተናል" በሚል በቶሮንቶ ከተማ ባዘጋጁት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ እንድናገለግል በተጠራንበት፣ በኮንፈረንሱ መጨረሻ ላይ "የአገልግሎትህን 50ኛ ዓመት" በሚል በድንገት ሰርፕራይዝ አደረጉን። "ብርሃነ ወንጌል" በተሰኘች ቤተክርስቲያን በመዘምራን ቡድን የተሰለፍኩበት ዓመት ተጨምሮ ሲሰላ በእርግጥም 50 ዓመት መሙላቱን ያስተዋልኩት በኋላ ነው። እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም። የምንኖርባት ምድር ጠፍጣፋ (Flat) ብቻ ሳትሆን ወጣገባ እንደሆነች ሁሉ፣ ሕይወትም እንዲሁ ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም ቅሉ፣ ጌታን ለመከተል የመጀመሪያዋን እርምጃ እግሬን ካንሳሁበት ዕለት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ በማንከስም፣ በዳዴም ሆነ በሩጫ ዘመን እጄን ይዞ የመራኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፣ ይህን የሰማ ሁሉ ያመስግንልኝ። ወንድሜ ሸዋዬ ዳምጤ እንዳዜመው፣ "ቀሪ ዘመኔን" እንዲባርክልኝ እለምነዋለሁ፣ እናንተም ለምኑልኝ። "ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ" (ዘፍ. 35:3) "አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና። ተጨማሪ ለማንበብ Facebook
#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ #የቄስ ጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ የኢትዮጵያወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ እና የቄስ ጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ። “እነርሱም አንድ እንዲሆኑ” የሚለውን የዮሃንስ ወንጌል 17 መሰረት በማድረግ በአዲስ አበባ ቦሌ ኢላሜ ኮንቬንሽን ሴንተር በተካሄደው ፕሮግራም የቄስ ጉዲና ቱምሳን የአገልግሎት እና የህይወት ሌጋሲ ማውሳት እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ ጽሁፎች ቀርበዋል ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ የጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን መስራች እና መሪ እንዲሁም የቄስ ጉዲና ልጅ ወ/ሮ ሌንሳ ጉዲና ተጋባዥ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ሲሉ ተቀብለዋል። በመድረኩ ቄስ ዶ/ር ሳሙኤል ደረሳ፣ ዶ/ር ተካልኝ ነጋ እና ዶ/ር ለማ ደገፋ ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበዋል። ዶ/ር ምህረት ደበበ የእለቱ ተናጋሪ መልዕክት አስተላላፊ ነበሩ። ቄስ ሃረገወይን ቃለ እግዚአብሔር ያቀረቡ ሲሆን፣ ቄስ ገመቺስ ደስታ (ፕሮፌሰር) እና ሃዋርያው ታምራት ታረቀኝ በጸሎት አገልግለዋል። ዘማሪ መስፍን ጉቱ፣ ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ፣ ዘማሪት ራሄል ተፈራ እና ዘማሪ ጉቱ ሽፈራው በዝማሬ ያገለገሉ ሲሆን የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ታዳጊዎች “አንድ ነን” የተስኘ ኬሮግራፊ አቅርበዋል። በኦቦሌሳ አዶላ
እኔ ጠይቄ እምቢ ቢሉኝስ የሚል ፍርሃት ነበረኝ / መጀመሪያ ለትዳር ሲጠየቁ ያለቀሱ ነበሩ 😁 የፓስተር ጻዲቁ አዝናኝ የፍቅር ጉዞ https://youtu.be/6-A-b_jNuGs
4627 ሰዎች ወደ #ጌታ መንግስት ተጨምረዋል። "መልካም ወጣት ደማስቆ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን የሚዘጋጀው የ2018 ዓ.ም መልካም ወጣት መረሃ ግብር ከተጀመረ 4ኛ ሳምንቱ ላይ ደርሷል። እያንዳንዱ ስልጠናዎች አንድ ሳምንትን የሚፈጅ ሲሆን አሁን 4ኛው ዙር ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዙር ብቻ 1336 ሰዎች ከአለም ለማምለጥ እና ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ለመግባት መወሰናቸውን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች። ባለፉት 3ዙሮች በ1ኛው ዙር 940 ሰዎች በ2ኛው ዙር 1143 ሰዎች በ3ኛው ዙር 1208 ሰዎች ጌታን ለመቀበል የወሰኑ ሲሆን በአጠቃላይ በ4ዙሮች ብቻ 4627 ጌታን ለመቀበል ወስነዋል። #እግዚአብሔር ይመስገን!
ተለቀቀ 🛑🛑 ፓስተር ጻዲቁ መድረክ ላይ እና እቤት ውስጥ ምን ይመስላል ? ያልተሰሙ ድንቅ ምስክርነቶች እና የሕይወት ምስክርነት ከፓስተር ጻዲቁ ጋር የተደረገ ድንቅ ቆይታ ተለቀቀ። https://www.youtube.com/watch?v=mCu_r96TKv4&t=146s
"ለአንድ ሀገር ዘላቂ መረጋጋትና ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ መሠረት በሚሆኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ በሰለጠነ መንገድ ሐሳብ እየተለዋወጥን ነው" ፓስተር ጻዲቁ አብዶ የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ከሰሞኑ እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዙሪያ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው። ፓስተር ጻዲቁ የምክክር ሂደቱ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህልን የሚያጎለብትና ለትውልድ የሚሻገር ሰላምን የሚገነባ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዋናው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል። በጉባኤው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በመሰባሰብ በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት እየተመካከሩ እንደሚገኙ የኢዜአ ዘገባ የሚጠቁም ሲሆን ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች፤ የምክክር ሂደቱ አሳታፊ፣ አካታችና ነፃ ሆኖ መካሄዱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባትና ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ተስፋ ሰጪ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን አክሎ ዘግቧል።
ህገ ወጥ መንገደኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ 🚓 🚓 🚓 ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜ በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ሙሉ ትምህርቱን ኮሜንት ስር ያገኙታል።
ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ የሃይማኖት ተቋማት የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ ቀረበ። "አከባቢን መጠበቅ ፈጣሪን ማክበር ነው።" ሲሉ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጽሐፊ መጋቢ ታምራታ አበጋዝ የሃይማኖት መሪዎች፣ አገልጋዮች፣ ምዕመናን እና መላው የከተማችን ነዋሪዎች አከባቢ ጥበቃ የእያንዳንዱ ዜጋ እና የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን እንዲሳተፉ ጥሪ አቀበዋል። አካባቢያችንን መጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን መንከባከብ እና ለመጪው ትውልድ አረንጓዴና ጤናማ አካባቢ ማስተላለፍ የሁላችንም የሞራልና የመንፈሳዊ ግዴታ ነው ያሉት መጋቢ ታምራት እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ጠቅሰው በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በአንድ ጀምበር አንድ ሚልዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት የተጠናቀቀ በመሆኑ በዚህ ታላቅ ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ዘመቻ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ምዕመናን በመርሀ ግብሩ በንቃት እንዲሳትፉ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን ብለዋል። እያንዳንዱ የሚተከሉ ችግኞች ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ፣ ለንጹህ አየር፣ ለተሻለ አካባቢ እና ለዘላቂ ልማት የሚደረግ ዋጋ ያለው አስተዋፅኦ በመሆኑ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ አገልጋዮች ምዕመናንና ምዕመናት የአከባቢ ጥበቃን እንደ መንፈሳዊ ኃላፊነት በመቁጠር፣ በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ከተማ አቀፍ ተግባር በንቃት እንዲሳተፉ በድጋሚ በጉባኤያችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። "ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፣ ነገ ለልጆቻችን የምንሰጠው ተስፋ ነው።" እንተክል! እንጠብቅ! አረንጓዴ ኢትዮጵያን አዲስ አበባን በጋራ እንገንባ! ሲሉ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#ቅዳሜ #ምሽት ይጠብቁን!! 🛑🛑 ከአመራርነት ውጪ ያሉ ያልተሰሙ #ድንቅ የግል ምስክርነቶች የያዘ እጅግ ተወዳጅ ፕሮግራም የክርስቲያን ዜና ይዞላችሁ መጥቷል። የክርስቲያን ዜና እጅግ ተወዳጅ የሆኑ አገልጋዮች እና መሪዎች ቀርበው የምንመካከርበት በይዘት እና በአቀራረብ ለየት ያለ #Sina የተሰኘ #podcast #አዲስ ፕሮግራም ይዘንላችሁ መጥተናል። የፕሮግራማችን የመጀመሪያ እንግዳ የቀድሞ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መሪ ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ሲሆን ያልተሰሙ እና አዳዲስ የሕይወታቸውን ታሪክ አካፍለውናል። ቅዳሜ ምሽት በThe Christian News ቻናላችን ብቻ ይጠብቁን!! ቻናላችንን ለማግኘት YouTube
የቤተክርስቲያን አባላት አሻራቸውን አሳርፈዋል። ኤቨርላስቲንግ ክራይስት ሪቮሊሽን ቸርች መሪዎች አመታዊ የአገልጋዮች የአንድነት ቀን አከናውናለች። የ2018 ዓ.ም የአርንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ‘‘ተስፋን እንትከል’’ በሚል መሪ ሀሳብ በመላው ሀገሪቱ እየተከናወነ ይገኛል።
የጳውሎስ ልመና ወይን ፀሎት ምንድነው? 🙏🧎♂️➡️🙏🧎♂️➡️🙏🧎♂️➡️ ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜ በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ሙሉ ትምህርቱን ኮሜንት ስር ያገኙታል።
ጌታ እኮ ነው! 🙌🙌🙌 ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜ በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ሙሉ ትምህርቱን ያገኙታል። https://youtu.be/hGs61vQUdfw?si=mW5TeeUePTTSa6yb
ኮይኖኒያ የተሃድሶ ሚሲዮናዊት #ቤተክርስቲያን የምስጋና መረሃ ግብር አካሄደች። ቤተክርስቲያኒቱ በጎተራ አከባቢ ያላት አጥቢያ ሕጋዊነትን ለማስከበር ከአመታት በላይ የተሰራ ሲሆን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ካርታ በመገኘቱ የምስጋና እውቅና የመስጠት መረሃ ግብር የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው መሪዎች እኛ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል። እጅግ ተስፋ በሚያስቆርጥ አድካሚ እና ውጣ ውረድ የበዛበት ጉዞ ነበር ነገር ግን ተዓምራዊ በሆነ መንገድ መሬቱን ሙሉ በሙሉ መረከብ ችለናል ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ መሪ የሆኑት መጋቢ መራዊ ንቡሴ ናቸው። መጋቢ መጋዊ ከክርስቲያን ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ በእለቱ የተዘጋጀው መረሃ ግብር አንድም የምስጋና አንድም በሂደቱ ውስጥ የነበሩ አካላትን እውቅና ለመስጠት እና በቀጣይ ቤተክርስቲያን ለመስራት ያሰበቻቸውን እቅዶች በጋራ ለመወያየት እንደሆነ ተናግረዋል። ከተመሰረተች ከ30 ዓመት በላይ እንደሆናት የሚነገረው ኮይኖኒያ የተሃድሶ ሚሲዮናዊት ቤተክርስቲያን ባለፉት ሶስት አስርት አመታት የምስራቹን ወንጌል ለትውልድ ለማድረስ እየተጋች እንደነበረ በመድረኩ ተገልጿል። ቤተክርስቲያን በቀጣይ የእግዚአብሔር ቃል በታማኝነት ለብዙዎች ለመድረስ የምትተጋ ቤተክርስቲያን እንደሆነች መጋቢ መራዊ ንጉሴ አክለው ለክርስቲያን ዜና ተናግረዋል። በዮሐንስ ግርማ
ኤልሻዳይ ቴሌቭዢን ኔትወርክ 19 አመታት ኤልሻዳይ ዮች ከ19 አመታት በፊት ፕሮግራሞችን ከቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና፣ ሐዋርያው ዳንኤል መኮንን፣ መጋቢ ሐንፍሬ አሊጋዝ እና መጋቢ መስፍን ሸለመ ጋር በመሆን አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖችን ለማገልገል የ1 ሰዓት አየር ሰዓት በመከራየት ተጀመረ። ጥንዶቹ መጋቢ አበራ ሐብቴ እና መጋቢ በለጡ ሐብቴ ከ19 አመታት በፊት ኤልሻዳይ ብዙዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ያፈለሰ ተወዳጅ የወንጌል ድምጽ በመሆን እንዲያገለግል የተጀመረ መሆኑን ያስታውሳሉ። ከምስረታው አንስቶ፣ ቅዱሳንን እና ቤተ ክርስቲያንን ያነጸ ፋና ወጊ የአገልጋዮች ድምጽ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል። “እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የአለምን ደካሞች መረጠ እንደሚል የእግዚአብሄር ቃል፣ ዛሬ ኤልሻዳይ በእኛ ችሎታና አቅም ሳይሆን በእግዚአብሔር ድንቅና ተዓምራት እዚህ ደርሷል፣ ስለዚህ ይሄንን ውለታ አንረሳም” ብለዋል ፓስተር አበራ ሐብቴ። “እግዚአብሔር ከለንደን ከዛች ትንሽ ቤት ኤልሻዳይን ከየት እንዳነሳን እናስታውሳለን! ስለዚህ እግዚአብሄርን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ብለዋል” ፓስተር በለጡ ሃብቴ። ዘወትር አርብ ምሽት በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን በሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ 19ኛ አመት ክብረ በዓሉን ያከበረው ኤልሻዳይ፣ ጥሪ ከተደረገላቸው መሪዎች እና አገልጋዮች ጋር በመሆን የተመሰረተበትን 19ኛ አመት ክብረ በዓል አክብሯል። ኤልሻዳይ ቴሌቭዢን ኔትወርክ፣ መጋቢ አበራ ሐብቴ እና መጋቢ በለጡ ሐብቴ እንኳን ጌታ ረዳችሁ፣ ስለ ከበረ አገልግሎታችሁ እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ! በኦቦሌሳ አዶላ