HONEST WCU Counseling
СтатистикаThis channel belongs to WCU(Evangelical Christian students fellowship) Counseling Department. Share to other @WUCounseling
- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 265
- 1/48двое суток
- 303
- 1/72трое суток
- 327
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ክፍል - 2 ስቀልድ ነው! ወዳጆቼ መቼስ ስለቀልድ በቁም ነገር ባወራችሁ በመከራ ቀጥ አድርጌ ያቆምኩትን "ቁም ነገሬን" ቁጭ እንዳታደርጉብኝ ስል ስለ ቀልድ ከማንሳት ይልቅ ስለ መለኪያ ማንሳቱን መርጭያለሁ። አሁን ስቀልድ አይደለም ! እንደ አማኝ ለንግግሮቻችን መለኪያ ይኖረን ይሁን? "አዎን" ከሆነ መልሳችን የትኛው ነው መለኪያችን? ግልጽ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስርዓትና ግብ አበጅተንለትስ ይሁን? ወይስ እንደ አለማውያኑ ልቅ ሆነን ይሁን? ለመሆኑ በዘመናችን ዐይንና ጆሯችንን ሞልተው በምላሳችን የሚፈሱ ቀልዶች በርግጥ ማሳቅ ብቻ ነው ዓላማቸው? እስቲ ትንሽ ፈልቀቅ እናርጋቸውና ልጠቅልል። እኚህን አስተውሉ። በብዙ አስቂኝ ቀልዶች ውስጥ :- ☑️እውነትን ማደብዘዝ ☑️ቅድስናን ማቅለል ☑️መንፈሳዊ ግለትን ማብረድና መንፈሳዊነትን ሰዋዊ ማድረግ ☑️ወኔን ሸርሽሮ ትጋትን ማሳጣት ☑️ለተግሳጽ ዋጋ ማሳነስ ☑️ቁም ነገርን ማሳጣት እና እንዲጠላ ማድረግ ☑️ስድብን እና ጸያፍ ንግግርን ማስለመድ ☑️ሀሜትን ማስፋፋት ☑️ክብር ለሚገባው ክብርን መከልከል .....ወ.ዘ.ተ እናንተም መጥቀስ ትችሉ ይሆናል። ወዳጆቼ ልብ ብላችሁ ቀልዶቻችንን ካስተዋላችሁ እና ከፈለቀቃችሁ እነዚህን ማግኘታችሁ በርግጥ የማይቀር ነው። መቼስ ዘንድሮ ጓዳ ሚባል ነገር ስለሌለ በማህበራዊ ሜዳ በጣቶቻችን ስንፋንን ሆነ በቡና ያወራረድናቸው ንግግሮቻችን እና ቀልዶቻችን መለኪያ አላቸውን? በእርግጥ ለጸሎት፣ ለዝማሬ፣ ለስብከት የምንጠቀማቸው እነዚያው ቃላት አይደሉምን "ኧረ ስቀልድ ነው!" ስንል የምንጠቀማቸው? ያሻንን ካልን በኋላ ከተጠያቂነት እና ከጥፋተኝነት ለመሸሽ ስንል "ስቀልድ ነው!" ማለትስ ተቀባይነት አለውን? የተሰጠንስ ዕድሜና የመኖር ዓላማ ቀልድን ታሳቢ ያደረገ ይመስላችኋልን? በእርግጥ አሁን ላለንበት ለዘብተኝነት እና ድንበሩ ለደበዘዘ ክርስቲያናዊነት ቀልድ እና ቀልደኝንት ብሎም ልጓም የለሽ ንግግራችን ድርሻው የጎላ አይደለምን? እነዚህን ጥያቄዎች በማስተዋል ራሳችንን እንጠይቅ እና ለንግግራችን ለከት እናኑር። በቀልድ ሰበብ ያጣናቸውን ነገሮች እንመልስ። ከላይ ያለውን ሀሳብ በእነዚህ ክፍሎች በጥልቀት ማየት ይቻላል ! መዝ 116:85 1 ጢሞ 4:7 , 6:20 2 ጢሞ 2:16, 4:4 ያዕ 5:3-12 የአንደበት ቅድስና ለእግዚአብሔር 🙏 @WUCounseling
ክፍል - 1 ስቀልድ ነው! ዋሽቶ ማስታረቅ እንደ እርቅ፣ ዘርፎ ስዕለት ማድረስ እንደ ቅዱስ ምስጋና፣ ሰርቆ ማጉረስ እንደ ቸርነት በሚቆጠርበት ሀገር ባህል እና ሀይማኖት፣ መርህ አልባ አደራረግ፣ ከስሁት መረዳት የሚመነጭ ልምምድ፣ ትናንትናን እና ነገን ባጡ የአፍታ ዕድሜ በማይኖራቸው ግላዊ ስምምነቶች ላይ በሚመሠረቱ ምክንያቶች የተገነቡ ነጽረተ ዓለሞች በሞሉበት ህዝብ መካከል ተወልዶ እያደገ ያለ ሰው ቀልድና ቁምነገር ለምን አልለየም? ብል ራሱ ... ስቀልድ ነው¡ መለክያ በሌለበት ልክን ማወቅ ፈታኝ ነው። ያሉንን መለኪያዎችም ልክነታቸውን መለካት ሌላ ማይለካ ፍጹም መለኪያ ያሻዋል። እነሱ በፍጹም መለኪያ እስካልተለኩ ድረስ በልኬታቸው የተለካ ሁሉ ልኩ ልክ አለመሆኑ ነው እንግዲህ። ስለዚህ መለኪያውም የተለካውም እኩል ሌላ መለኪያ ያሻቸዋል። ይህ ምን ማለት ነው? ልክ የለም ማለት ነው። አወሳሰብኩባችሁ? 🤔 ስቀልድ ነው ባካችሁ! 😁 ይሁን እንጂ እኚህ በስንኩል መለኪያ የተለኩም ሆኑ ጭራሽ ያልተለኩም እሳቤዎች፣ ንግግሮች ሆኑ ግብሮች ገበያቸው የደራ ነው። በስፋትም በአይነትም ገበያውን የሞሉት እነሱ ናቸው። እሽቅድድሙም እነሱ ላይ ለመውደቅ ነው። ስለዚህ ይህ ምን ያሳያል? ሻጩም ሸማቹም ፍጹም ልኬት የላቸውም። ባጭሩ ገበያው ልክ፣ ሻጩ ገዢውም መለኪያ የላቸውም። ሲያቀብጥህ "ፍጹም መለኪያ አለኝ" እያልክ ገበያ ብትገባ በገበያተኛው ብሎም በብዙሃኑ ተለክተህ ማሰብያክ ልክ እንዳልሆነ ተነግሮህ አንተ ስሁት እነሱ ልክ ሆነው ትወጣለህ። ይሁንና መለኪያቸው ልክ አለመሆኑን ማሳየት አሁንም ያንተ ድርሻ ነውና መንገድ እየዘየድክ መታገሉ አማራጭ አይኖረውም። ካልሆነ እዛው አለኝ ያልከውን ፍጹም መለኪያ በስንኩል መለኪያ ለውጠህ ተከባብረህ ለመኖር ትገደዳለህ። ስቀልድ ነው 😁 እኔም እንግዲህ ያሻኝን ሁሉ ባስብ ፣ብናገር ፣ ብጽፍ ፣ ባደርግ ገበያው ይቀበለኝ እንጂ እኔንም ያርካኝ እንጂ ስጨርስ ስጨርስ "ስቀልድ ነው!" ብል ማንስ ምን ይለኛል?! ቢበዛ "እሱ ጎበዝ ቀላጅ ነው መድረክ አያያዝ ያውቃል እሱ ይጋበዝ" የሱን ቻናል እንከታተል "አንተ? ሲሰብክ የሚጠቀማቸው ቀልዶቹ ኡኡኡ .... ሲጽፍ ባየህ ..... በአካል ብታገኘውማ ጥርስህ እስኪጠቁር ነው የምትስቀው" ብባል ነው። https://t.me/WUCounseling
ቀልዶቻችን ይመዘኑ ቀልድ ማለት ሰዎችን ለማሳቅ😁 ወይም ደስታ😂 ለመፍጠር የሚነገር ወይም የሚደረግ ነገር ነው። ጤናማ ቀልድ ግንኙነትን🤝 ያሳድጋል፣ ጭንቀት🤕ን ይቀንሳል፣ ፍቅርንና መቀራረብን🥰 ያጠናክራል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በወሬያችንና በጨዋታችን መካከል፦ “ይሄን የገለጠልኝ መንፈስ ነው…” “አሜን የእግዚአብሔር ሰው…” “በመንፈሴ አየዋለሁ…” ....ወዘ ተረፍ የሚሉ ንግግሮችን ለቀልድና ለማሳቂያ እንጠቀማለን። ግን እነዚህ ስሞችና ቃላት ተራ የጨዋታ ቃላት አይደሉም። የአምላክን ስም፣ መንፈሳዊ ነገሮችንና የተቀደሱ ቃላትን የያዙ ናቸው። እነሱ ክብር ያላቸው፣ የተለዩና በፍርሃት ሊጠሩ የሚገባቸው ናቸው። የአምላክ ስም የተቀደሰ ነው፤ የክብር ስም ነው፤ ከሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው። ታዲያ እንዴት ለቀልድ ማድመቂያ እና ለወሬ ማዋዣ እናደርገዋለን? እንዴትስ ከአፋችን በቀላሉ ይወጣል? የምናከብራቸውን ሰዎች ስም እንኳ ለመቀለድ እንፈራለን። በዓለም ስርዓት ያሉ ባለስልጣናትን ስም እየጠራን ለማሳቂያ አንጠቀምበትም። ምክኒያቱም እንፈራለን። ታዲያ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እንደፍራለን? ምናልባት እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ስለሆነ ፍርሃታችን ቀንሶ ይሆን ይሆናል!? ነገር ግን መሐሪነቱ ክብሩን እንድናቀልል አያደርገንም። እንዲህ ይላል፦ “የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ።”ዘፅዓት 20:7 እንዲሁም፦ “የማይገባ ንግግርና የሰነፎች ቀልድ አይገባችሁም።” ኤፌሶን 5:4 ስለዚህ ወሬያችን፣ ቀልዳችንና ንግግራችን በእግዚአብሔር ፍርሃት የተሞላ ይሁን። ምክንያቱም ቃላችን ማንነታችንን ያሳያል፤ ልባችንም በአፋችን ይገለጣል። “ቀልድ” በመሆኑ ብቻ ሁሉም ነገር ተገቢ አይሆንም። የአምላክን ስም በክብር እንጥራ፤ በፍርሃትም እንኑር። መታሰቢያነቱ እንደ እኔ ብዙ ጊዜ በዚህ መሰልጠን በሚመስል ያለማወቅ ድንዛዜ ውስጥ ለነበራቹ እና ላላቹ ይሁን🤗 ጌታ ያለማወቅ ሽንቁራችንን በምህረቱ ይሸፍን በመንፈሱ እውቀት ይሙላን👐 @WUCounseling
ውዶች እንዴት አላችሁ? ሰሞኑን ሁላችን በሚባል ቁጥር አብዛኛዎቻችን የአመቱ መዝጊያ እና የሴሚስተሩ መቋጫ ወደ ሆነው ፋይናል ፈተና ደርሰናል። መቼስ ፋይናል ፋይናል ነው። አይለመድም 😁 አንድአንድ ነገሮችን ልበላችሁ 1. በእግዚአብሔር ታመኑ እምነታችሁ፤ መታመናችሁ፤ መደገፊያችሁ እግ/ር ብቻ ይሁን። ራሳችሁን፣ ያላችሁን ንብረት(አጥሬራ፣ ስልክ 😉..)፣ ሰዎች፣ ሁኔታዎች ... አይሁኑ። ሁሉን ማድረግ በሚችል አምላክና አባታችሁ ላይ እምነታችሁን አድርጉ። እርሱ ሰላምንና ጤናን ከእድሜ ጋ ስሰጥ ነው መድረስ የሚቻለው። አድርሶ መስራትን እንችል ዘንድ ማስተዋልንና እውቀትን የሚያበዛው ራሱ አባታችን ነው። 2. በፍጹም መረጋጋት አትረበሹ፣ አትጨነቁ፣ አትፍሩ፣ ተስፋ አትቁረጡ። ከፈተና በፊት አትጨነቁ፣ በፈተና ጊዜ አትረበሹ፤ ተረጋጉ እና ከፈተና በኋላ ተስፋ አትቁረጡ። የውጊያው ሜዳ የፈተናው አዳራሽ ሳይሆን አእምሮአችሁና ልባችሁ ነውና። ለክፉ ልጅ ራሳችሁን አትስጡ። በመረበሽ የሚጠፋን ጊዜና ጉልበት ለማንበብ፣ ለፀሎታችሁ እና ለቃሉ አውሉ። 3. ከሀጢአት ተጠበቁ ቀላል እና ኖርማል ከሚመስሉ ግን እግዚአብሔር አጥብቆ ከሚቃወም ሀጢአት ጋ በማመቻመች እንዳትተባሩ። የማንኮርጀው፤ የማናስኮርጀው ሞራል ስላልሆነ ሳይሆን እግዚአብሔር የማይከብርበት ሀጢአት ስለሆነ ነው። (እናንተ በዚህ አትጠረጠሩም 😊) 4. ጊዜአችሁን ጠብቁ እንዳትባክኑ ያላችሁን ጊዜ በአግባቡ ተጠቀሙ። በፈተና ሰዓት ያላችሁን ጊዜ ለእግ/ር እና ለትምህርታችሁ ብቻ አውሉ። ከዚህ በፊት አላነበበኩም በሚል ስንፍና የቀራችሁን ጊዜ እንዳታባክኑ። ጨርሻለሁ ብላችሁም እንዳትዘናጉ። 5. በእጃችሁ ያዙ ወደ እግዚአብሔር እንድባርክ ከመቅረባችሁ በፊት በእጃችሁ ሁለት ዓሳ እና አምስት እንጀራ መያዛችሁን እርግጠኞች ሁኑ። ያነበባችሁትን የቻላችሁትን ይዛችሁ ወደ አባታችሁ ቅረቡ እርሱ የበረከት አምላክ ነውና። 6. አመሰጋኝነት ምስጋናህን ትልቅ የሚያደርገው ጩኸትህ አይደለም፤ ምክንያትህ ነው። በተሳካው ባልተሳካው፣ በስብራት በጠገን፣ በመውደቅ መነሳት፣ .... ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ። "በሁሉ አመስግኑ" ይለ የለ ቃሉ? ብቻ አመስግኑ አመላክ በምስጋና ውስጥ መንገድ አለው። 7. ፀጋውን ፍለጋ [ተግባሬ] ቢሳካልኝ ፥ አመሰግነዋለሁ ፤ ሳይሳካ ቢቀር ፥ ፀጋውን ፍለጋ እገሠግሣለው ። __ ማክስ ሉካዶ በየተኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ከፀጋው ዙፋን ስር አትታጡ። በዛ ለነፍሳችሁ እረፍት፣ ለመንፈሳችሁ ብርታትን፣ ለልባችሁ ደግፎትን እና ለስጋችሁ ጠገንን ታገኛላችሁ። እንግድህ ተወዳጆች ሆይ በሚኖራችሁ የፈተና ቆይታ ሁሉ እግዚአብሔርን ብቻ ደስ ታሰኙ ዘንድ እንድትተጉ፤ በዙሪያችሁ የከበበውን አለም እንዳትመስሉ ትቆረጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እግዚአብሔር ህይወታችሁን፣ ትምህርታችሁን፣ ጤናችሁን፣ ጓዳችሁን፣ አደባባያችሁን ሁሉ ይጠበቅ፣ ይባረክ። የለፋችሁበትን እግዚአብሔር ያስፋላችሁ። በምስጋና ነዶ ፈተናችሁን ጨረሱ። እግዚአብሔር በፍሬ ይባርካችሁ። ህይወታችሁ፣ ቀናችሁ ሳምንታችሁ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተቀጠረ ይሁን። የክፋት አደራረግ ሁሉ አያግኛችሁ። አምልጡ፣ ተሻገሩ። ሁሌም ትወደዳላችሁ 🥰🥰 መልካም ፈተና @WUCounseling
#ቀን_አምስት 💥ፍለጋውን መፈለግ 💥 ሚክያስ 6:8 [8] ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ✨የሰው ልብ የሚፈልገውን/የፈለገውን ይፈልጋል፤ይህም የልብን ምኞት መሰረት ያደረገ ነው። ሌላው ደግሞ የሚያስፈልገውን መፈለግ ሲሆን ይህ ከባለአዕምሮነት እና ከአስተዋይነት ይመነጫል። ✨ክርስቲያኖች ልባችን ከሚፈልገው፣ ደግሞም ከሚያስፈልገን ይልቅ የሚበልጠው እና የሚሻለው እግዚአብሔር የሚፈልገውን መፈለጋችን ነው። ✨እግዚአብሔር ከእኛ ምን ይፈልጋል? ከእኛ ህይወት፣ ከእኛ አገልግሎት፣ ከእኛ የግልና ማህበራዊ መስተጋብር፣ ከትምህርታችን፣ .... እግዚአብሔር ምን ይፈልጋል? ......ሁሌም እኛ የምንፈልገው ነገር ከእኛ የሚፈልገው ነገር አለ። እኛ እግዚአብሔርን ስንፈልግ እግዚአብሔርም ከእኛ እንደዛው። ያንን መፈለግ ደግሞ ለተጠራንበት ህይወት ብርቱ መሠረት ነው። እግዚአብሔር በሰጥቶ መቀበል መርህ የሚመራ አምላክ አይደለም። ስላደረጉልኝ አደርጋለሁ አይልም። ነገር ግን ከእኛ መልስን፣ መታዘዝን እና ፈቃዳችንን ማስገዛት ይፈልጋል። ሲወደን ከእኛ አንዳችን ነገር ጠብቆ አይደለም ፤ስለወደደን መልሰን እንድንወደው እንጂ። ✨ከእያንዳንዱ ክርስቲያን እግዚአብሔር ሚፈልገው ነገር አለ። እግዚአብሔርን ስንፈልግ እርሱ የሚፈለገውን እንድንፈልግ ፣ እንድንተው የሚፈልገውን እንድንተው፣ የሚወደውን እንድንወድ፣ የሚጠላውን እንድንጠላ፣ ያከበረውን እንድናከብር፣ የናቀውን እንድንንቅ ይፈልጋል። ✨ በዘመናችን፣ በዙሪያችን ካለው ከበባ እና በልባችን ከሞላው ቅጥ ያጣ ፍላጎት ገለል ብለን፣ እየገሰገሰን ካለንበት አቅጣጫ የሳተ ጉዞአችንን ገታ አድርገን እግዚአብሔር ከእኔ ምን ይፈልጋል? ብለን እንጠይቅ። ......የዛኔ ብዙ ያከበርናቸው ነገሮች ውርደታቸው፣ የወደድናቸው ነገሮች ወጥመድ መሆናቸው፣ ደስታ የመሰሉ ሀዘኖች፣ ብርሃን የመሰሉ ጽልመቶች፣ ያለንበት ስፍራ የቆምንበት ማጥ፣ የያዝናቸው መደላድሎች መሠረተ አልባነታቸው፣ የተላበስናቸው ባህሪያት፣ የኮረጅናቸው ባህሎች ሁሉ ትክክል እንዳልሆኑ እንረዳለን። ከዛ እግዚአብሔር ወደ ሚፈለገው ህይወት ጥራት እንድንኖር ይኼም:- እውነተኛ(ህጸጽ የሌለበት)፣ የነገር ሁሉ(የህይወታችንም ጭምር) መለኪያ እና የመጨረሻ ባለሥልጣን ወደ ሆነው ቃሉ፤ ህይወታችን ተፈትሾ ስተን እንደሆነ መመለስ እና በእውነተኛው መሠረት ላይ መጽናት። ጨምረን ደግሞ ለእርሱ ክብር እና ደስታ በሚሆን አኗኗር እንድንኖር ። 👆👆👆ይህንን እግዚአብሔር ከእኛ ይፈልጋል! ✨ፍለጋውን እንፈልግ!! 👇👇👇👇👇👇👇 @WUCounseling
видео или голосовое, без подписи
💥ፍለጋውን መፈለግ💥 ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? —ሚክያስ 6:8 በመማክርት ህብረት የተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም 🗓አርብ ⏰ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ 📍አንቢቾ MKC ⚠️ባለማርፈድ እንትገኙ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን!!!! 📌ማስታወሻ🖊️ እና መፅሐፍ ቅዱስ📖 መያዝ እንዳይረሳ! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል🤗 #Counseling_Night
#ቀን_አራት 💥ምግባረ - ክርስትና💥 1 ዮሐንስ 2:6 [6] ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል። ማንም ክርስቲያን በእግዚአብሔር መንግስት ሲኖር የሚኖርበት የህይወት ዘይቤ፣ የአኗኗር ባህል፣ የንጽረተ-አለም ቅኝት፣ ባህሪይ፣ የህይወት አላማ፣ .... አለው። በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ክርስቲያኖች እንዲመላለሱበት እና እንዲኖሩበት የተሰጠ መተዳደሪያ እና የሚገለጡበት የህይወት አይነት አለ። የክርስቲያን ምግባሩ የሚቀዳው ከራሱ ከእግዚአብሔር ነው። ደግሞም መለኪያው እራሱ እግዚአብሔር ነው። ክርስቲያን እንደ ልቡ ፈቃድ ለመኖር፣ ለስጋው ደስታ፣ የፈለገውን ለማድረግ፣ ... ለማድረግ አልተጠራም። ደግሞም አልተፈቀደም፤ ሀጢአት ነው። እንድንከተለው እና እንድንመስለው የተጠራነው ፍለጋውን እንድንከተል ምሳሌ የተወለንን ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው የሆነው ወልድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። ከጨለማ፣ ከአለም ከራሳችንም ጭምር ስዋጀን የመጣንበትን አለም እንድንመስል፣ በቀደመው የህይወት ምልልስ እንድንኖር አይደለም። በክርስትና ዓለም ከምልሰት በኀላ የሚኖር ሕይወት አለ። ኢየሱስን እንድንመስል። እርሱን እንድንከተል ተጠርተናል። በምልልሳችን፣ በማህበራዊ እና በግል ህይወታችን፣ በትምህርታችን፣ በመንፈሳዊ ህይወታችን፣ በአገልግሎታችን፣ በስውር በጓዳ፣ በግልጥ በአደባባይ፣.... ሁሉ ነባራዊ የሆነ ነው የክርስቲያን ምግባር። ሁኔታዎች፣ ሰዎች፣ ዘመኑ የማይቀይረው መርህ። በማይዋዥቅ ወጥ የሆነ ምግባር። በቅድስና መኖር ልቡ የተለወጠ ክርስቲያን የልዩነት ምልክቱ ነው። የልብ መለወጥ ደግሞ የዳነ ሰው ምልክት ነው። የዳኑ ሰዎች የሚታወቁት በዕሁዱ ጉባኤ ሳይሆን በቅዳሜው ገበያ ነው። በዝማሬ ቅላፄያቸው ሳይሆን በማይሻቅብ ሚዛናቸው ነው። የእውነተኛ ክርስትና መገለጫው ጥሩ ማሰብ እና ማድረግ ሳይሆን እንደ ኢየሱስ ማሰብ እና ማድረግ ነዉ::ኢየሱስን እንድንመስል ነው የተጠራነው::የእግዚአብሔር ፍለጋ ኮቴውን እንከተል ዘንድ ነዉ! ✨ፍለጋውን መፈለግ! 👇👇👇👇👇👇 @WUCounseling
видео или голосовое, без подписи
HONEST WCU Counseling pinned «https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeg_zhhbazJi1rc_2k8A2dySqWWdOzmWBp04l9AN_2NQ7PLow/viewform?usp=publish-editor 💥💥ይህ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች በCounseling ህብረት የተዘጋጀ የመረጃ ማሰባሰቢያ ቅፅ ነው። ይህን ቅፅ ሲሞሉ ማንነታችሁ ስለማይታወቅ፣ በዚህ ፎርም ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች በግልፀኝነትና በታማኝነት…»
#ቀን_ሶስት ✨ምልሰት!!✨ “ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ፥ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።” — ኤርምያስ 3፥22 አንድ በእግዚአብሔር ቤት የሳተ እና ከቤት ውጭ ወጥቶ የጠፋ ሰዉ ወደ እግዚአብሔር መመለሱ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ነገር ግን የመመለስ ጅማሮው ያለበትን ማወቅ፣ መጥፋቱን/መሳቱን ማመን ነው። ጥፋትን ማመን ታክሞ እንደገና በሕይወት ለመኖር የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥቶ በጥፋት ለተመላለሰው የሰው ልጅ እንደገና በሕይወት መኖር ጥፋትን በማመን እና ለመመለስ በመወሰን የአቅጣጫ ለውጥ ማድረግ ከበሽታው ለመዳን የሚደረግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ወቀሳ(መፀፀት) የልብ ጉዳይ ሲሆን፤ ባለማስተዋል ወይም በድፍረት ከእግዚአብሔር ሃሳብ ርቆ የተጓዘ ሰው እንደበደለ በማወቅ ራሱን እና ያለበትን በማስተዋል የሚመለከትበት ሁኔታ ነው። “ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።” — ሉቃስ 15፥17 ነገር ግን ወቀሳ(መፀፀት) ብቻውን በራሱ ምንም የሚያደርግልን ነገር የለውም። መፀፀት ወደ እውነተኛ ንሰሀ እና መመለስ ሊያመራን ይገባል። ካለሆነ ስሜትን ማንፀባረቅ ነው። እውነተኛ ንሰሐ ከልብ መታደስ የሚመነጭ ወደ እውነተኛው መሠረት፣ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነዉ። (“እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ ...” — ሉቃስ 3፥8) ንሰሐ በጓዳ ከእግዚአብሔር ጋር በልብ ለውጥ፣ በመንፈስ መታደስ የሚመጣ፤ ፍሬው በአደባባይ የሚታይ እና የሚገለጥ የህይወት ለውጥ ነው። ሀጢአቱን የሚናዘዝ ብቻ ሳይሆን የሚተዋት ነው የተመለሰ። ሰው ለበደሉ ምህረትን እንዳገኘ፣ እግዚአብሔር በለውጥ መንገዱ እርዳታን እንደሚያደርግለት እና ኪዳኑን እንዳደሰለት በማመን የዘመኑን የእግዚአብሔር ሃሳብ ለማከናወን በአምላኩ ፊት ሞገስ አግኝቶ የሚኖርበት ሕይወት ይኖረዋል። የመመለስ ህይወት የውሳኔ ህይወት ነው። ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ለመሆን ራስን ለፈቃዱ ማስገዛት፤ ከሀጢአትና ከመጥፋት በፀጋው ሀይል በማምለጥ በእቅፉ መኖር። ✨ በዘመናት መካከል እግዚአብሔር ወደ እርሱ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለመመለስ የሚፈልጉትን ከቶ የማይጠላ፣ እጁን ዘርግቶ የሚጠብቅ እውነተኛ አባት ነው። እንመለስ ዘንድ ይፈልጋልና ኑ እንመለስ!! “ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።” — ሉቃስ 15፥2 ፍለጋውን መፈለግ!💥 👇👇👇👇👇 @WUCounseling
видео или голосовое, без подписи
✨ጠፍተን - አለን! የሰማይና የምድር ጌታ ከልጆቹ ሊግባባ ሲፈልግ ቃሉን ሰጠ! ለሙሴ በድንጋይ ጽላተ ላይ ሲቀርጽ፣ ለእኛ ደግሞ በልባችን ጽላት ከትቦ ሊቀርበን ወደደ። እንዲሁም ደግሞ በክርስቶስ ደም ታርቆን፣ የልጅና የአባትን ህብረት መሠረተ። እኛን ለመቅረብ መለኮት ረጅም ርቀት ተጓዘ! ብቻውን መኖር የሚችል ጌታ ብቻችንን ለማንችል ለኛ ብቻውን ዋጋ ከፈለ! ታድያ እኛስ!? ልጅነት-ከአባት ጋር በፍቅር የተገመደ፣ የልብ አንድነት ያለበት፣ እጅግ የጠለቀ የነፍስ ትስስር ነው። የኛ ኑሮና አካሄድ ደግሞ ከዚህ እውነት የራቀ ሆኗል። “ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና” — ኢሳይያስ 29፥13 በአካል በቤቱ አለን፣ በከንፈራችንም እሱን ከማክበር አልጎደልንም፤ በልባችን ግን ከሀሳቡና ከፈቃዱ ኮብልለን ከማዶ ከትመናል። ቤተክርስቲያን መመላለሱ፣ ማገልገሉ፣ ሙቀቱ፣ስለ እግዚአብሔር የሰበሰብነው መረጃ..... አለን ብለን እንድንቀጥል አድርጎናል። ልባችን ግን ለጌታ ከመሆን ይልቅ መከፈልን መርጧልና። በውስጡ መዓት ጢሻ አለ። በሀጢአት መሰንበት፣ የመንፈስ ቅዱስን ወቀሳ ረግጦ መመላለስ፣ የልቦና መደንደን፣ የህሊናን ክስ ችላ ማለት፣ ጓዳን ጥሎ አደባባይ መሰጣት፣ ከልብ ባልሆነ መንፈሳዊ በሚመስል ጭምብል መሸፈን፣ ወደ ጌታ ለመመለስ አለመፈለግ፣መሀል ሰፋሪ፣ ለብ ያለ ህይወት፤ ከአንዱ ጥግ ያለሆነ! "በጌታ ቤት ነን፣ በፊቱም አለን" እያልን ነገር ግን የያዝነው ስልክ ፀሎት ካስተወን፣ ቃሉን ካስጣለን፣ ርሀባችንን ከነጠቀን፣ ሀጢአትን ከተለማመድን፣ ከአለማዊያን መግጠም ከቀለለን፣ በርኩሰት ከተዝናናን፣ በውድቀት ከጸናን፣ከተገበዝን..... መጥፋታችን አይደለምን?......ጠፍተን-አለን ከቤቱ ሳይሆን ከልቡ ያለን ርቀት ነው“አለን"ም “ጠፍተናል"ም የሚያስብለን።በልብ ተራርቆ በአንደበት መቅረብ፣ የነፍስ ትስስር በሌለበት በስጋ መገኘት፣የደጅ ርቀት እንጂ እውነተኛ ህብረት አይደለም። እርሱ የሚሻው የልቡን እንድንረዳለት እንጂ የልባችንን እንድናደርግ አይደለም።እርሱን የሚያጠግበው የማርታ ገበታ ሳይሆን የማርያም ልብ ነው። በቃሉ መስታወት ሕይወታችንን እንመዝን ወደ ልባችን ተመልሰን መጥፋታችንን እንገንዘብ! ✨ፍለጋውን መፈለግ 👇👇👇👇 @WUCounseling
видео или голосовое, без подписи
💥ቃለ-እግዚአብሔር💥 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥...... የልብንም ስሜትና ሀሳብ ይመረምራል፤” — ዕብራውያን 4፥12 ✨መጽሐፍ ቅዱስ ምንም እንኳን በሰው ቋንቋ፣ በሰው ባህል እና በሰው እጅ ቢጻፍም የእግዚአብሔር ቃል መሆኑንና ኃይሉን በፍጹም አይለውጠውም፡፡ ምክንያቱም ፃሐፊዎቹ የፃፉት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው እንጅ እንደማንኛውም ድርሳናት ከራሳቸው አይደለም ።2ኛጴጥሮስ 1:20 ✨መፅሐፍ ቅዱስ ትናንትናም ዛሬም ለወደፊትም የሚሰራና የታመነ ነዉ ::ዮሐንስ 5፥47 የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ባለቤቱ እራሱ እግዚአብሔር ነው! “..... የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ...." 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17። ✨መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቅድስና፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ እና የእግዚአብሔርን ፍትሕ በማሳየት አባት ለሚወደው ልጁ የጻፈለት ውድ የፍቅር ደብዳቤ ነው፡፡እንዲሁም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያዘጋጀውን የደህንነት መንገድ ግልጽ አድርጎ የማሳየት ዓላማን የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ ✨ቤተክርስቲያን ሕዝብን የምትመራበት ምሪት እና መተዳደሪያ ደንብ የተቀበለችው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው ፤መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሲኖሩ የሚመሩበት የመጨረሻ ባለስልጣን ነዉ!ይህ መፅሐፍ እውነት ሲሆን የመፅሐፉ እውነት ደግሞ ነባራዊ እውነት እንጂ አንፃራዊ አይደለም! ✨አንድ ሰው ጠዋት ተነስቶ ራሱን በመስተዋት እንደሚመለከተው እንደዛው ራሳችንን ለመመልከቻ ይሆነን ዘንድ እግዚአብሔር ከወዴት እንደወደቅን እናውቅ እና አካሄዳችንን ማስተካከል እንችል ዘንድ ራሳችንን ቁልጭ አድርጎ ያለግብዝነት የሚገልጥ እና የሚያሳየን ዋና መለኪያችን ነዉ! ብሎም በሽታችን ታክሞ በሕይወት መኖር እንችል ዘንድ መድሃኒቱን የሚጠቁም እና የሚያክም ነዉ። ✨ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ስንመለከት ምንያህል እንደሳትን እናውቃለን መመዘኛችን ነውና::ወደ ቃሉ እንመለስ ቃሉን ዋናችን እናድርገው::እግዚአብሔር ከኛ ቅዱስ ቃሉ ላይ የተመሰረተ ሕይወት እንዲኖረን ይፈልጋል! ፍለጋውን እንፈልግ!🙏🙏
видео или голосовое, без подписи
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeg_zhhbazJi1rc_2k8A2dySqWWdOzmWBp04l9AN_2NQ7PLow/viewform?usp=publish-editor 💥💥ይህ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች በCounseling ህብረት የተዘጋጀ የመረጃ ማሰባሰቢያ ቅፅ ነው። ይህን ቅፅ ሲሞሉ ማንነታችሁ ስለማይታወቅ፣ በዚህ ፎርም ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች በግልፀኝነትና በታማኝነት አንድ ጊዜ እራሳችሁ ከሞላችሁ በኃላ ሌሎችን ደግሞ እንድታስሞሉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን:: ተባርኩ! ማሳሰቢያ:ይህ ቅፅ/ form ውስጥ የሚሳተፈው የዋቻሞ followship አባል ሊሆን ይገባል
"ስንቅ" ብቻውን ምድረ-በዳ እንደ ሚሰደድ ሰው፥ ከቤተሰብ እና ማህበረሰብ ተለይተን ወደ ጊቢ(university) ስንገባ፥ ሁሉ ነገር አዲስ በአንዴም የማይጨበጥ ይሆናል። አዲስ ኑሮ፣ አዲስ ህይወት፣ አዲስ ማህበር፣ አዲስ ብሒል... ብዙ ብዙ። ታዲያ ወደዚህ ተቋም ከገባን ኋላ ምንም እንኳ ቤተሰብ ከጎናችን የሚቆም ቢሆንም ራሳችን የራሳችን አስተዳዳሪ እንሆናለን። ለመከራው ፣ ለብቸኝነቱ፣ ለሚገጥሙን ብርቱ ፈተናዎች በሙሉ ፊት የምንሆነውም እኛው እንሆናለን። በዚህ ሁሉ መኃል አንድ ክርስቲያን ተማሪ ከዚህ ተቋም ትምህርቱንና ራሱን ጠብቆ እንዴት በሰላም ሊወጣ ይችላል? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ጥያቄ ይሆናል። የሚገጥሙን ፈተናዎች አያሌ በመሆናቸው ለውድቀት ሊዳርጉን ፣ ከጌታውም እውነት ሊያጎድሉን ፣ ቅድስናችንን ሊያሳጡን ፣ ልንሆን ከሚገባን ትክክል ላይ ሊያወዱን አቅም አላቸው። ስለዚህ ከስር የምናስቀምጥላችሁ የyoutube አጭር podcast አንድ ክርስቲያን ተማሪ በጊቢ ቆይታው በምን አይነት መልኩና በምን አይነት መንገድ ራሱን ማሰማራት እንዳለበት ያስተምረናል። ታዲያ ሁላችሁም መስፈንጠሪያውን በመጫን የዚህ በረከት ተካፋዮች ሁኑ። በዛሬ ብርሃን ጨለማውን ነገ አንመልከትና ከወዲሁ እንሰናዳ ! https://youtu.be/v6K6ViHMjL8?si=dW42OfKXcZXqUhFl Join us 👉@WUCounseling
አለባበስ እናት ሔዋን ቅጠል እየሰፋች ሌጦ እየለበጠች፣ ጥራ ተጣጥራ እርቃኗን ሸፈነች። ልጅ ሔዋን አደገች፣ ቅጠሉን ገለጠች፣ ጨርቋን ቀዳደደች፣ ሌጦዋን አንስታ እርቃኗን ገለጠች። ✍️✍️✍️ በአሁኑ ዘመን አለባበስ እንደ ትውልድ የምንቸገርበት ጉዳይ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። ቃሉ የሚያስተምረን ነገርና እኛ በራሳችን የመረጥነው እንደ ቃሉ ያልሆነ አካሄድ ገላጋይ ያጡ ይመስላል።ይህም የመጣው አንድ በተለምዶ ምንለው ከፊል እውነትን ከውሸት ጋር የያዘ አባባልን ሙሉ ለሙሉ መቀበላችን ነው «ጌታ ልቤን እንጂ ልብሴን አያይም » እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ገላችንን የምንሸፍንበት ልብሳችን ስለ እኛ የሚናገረው ብዙ ነገር መኖሩ ነው። 🤔የምር ሰዎች አለባበሳችንን አይተው ምን ያስቡ ይሆን? 🤔የተገላለጠ ገላችን ስለኛ ምን ይናገር ይሆን? 🤔አሁን አሁን የጌታ ቤት የfashion ማሳያ መሆኑ ምክንያቱ ባይገባኝም ምናልባት ግን church ውስጥ camera መግባቱ ይሁን .......እንጃ🤷♀️🤷♂️ “ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 8፥13 ✍️ሰዉ ወደጌታ ሲቀርብ ከራሱ ይልቅ አጠገቡ ላለ ወንድም ያስባል፤ አደለም ሚለብሰውን ሚበላውን እስኪተው:: ✍️የእኛ ምቾት በደሙ ቤዛነት ከተዛመድናቸው ወንድምና እህትቶቻችን አይበልጥምና እጠንቀቅላቸው! መፅሐፍ ሲናገር “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።” ይላል — 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥31 ✨ አለባበሳችን በሁለንተና እግዚአብሔርን ለማክበር ለተጠራነው ጥሪ ምላሽ የምንሰጥበት አንዱ መንገድ ነውና ለምንለብሰው ነገር ትኩረት እንስጥ!🙏 ✍️በWCU COUNSELING TEAM Join 👉 @WUCounseling
HONEST WCU Counseling pinned a photo