የ 12ኛ ክፍል የጥናት ቡድን
Статистика- Последний пост
- 20 мар.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
“የሕይወት ተፈራ ዓድዋ” ክብር በማማ የዐፄ ምኒልክ የክተት አዋጅ በተለያየ የጦር አካዳሚ የሚጠና ሲሆን፤ “የዓለማችን አጭሩ የክተት ዓዋጅ” ተብሎ ይጠራል። አብዛኛው የጦር አዋጅ ከሃያ ገጽ እስከ መቶ ገጽ እንደ ሚፈጅ ልብ ይሏል። የምኒልክ ወርቃማው የክተት ዐዋጅ አንድ ገጽ ባትሞላም፥ ብዙ የሚፈከርበትና በብዙ እንደምታ የሚታይ ሲኾን ከዋናው ነጥብ ላለመራቅ፥ መለኮት-ተኮር (theocentric) እና ሰው ተኮር (anthropocentric) ጎኖች አሉት ብሎ ጥቁምታ ሰጥቶ ማለፉ ይበጃል። “አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም” … በሚልና … “ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ!” በሚል ይቀነበባል። ይመር የተሰኘው ገጸሰብ ይሄን ዐዋጅ የሰማው “ታይሞስ” በተሰኘው ዕውቅና እና ክብር ፈላጊው በኾነው የነፍስ ክፍል ውስጥ ባለው ጆሮ በኩል ነበር። ክብረ-ነክ የሆኑ ጥቃቶች ለሀገራት የኃይል ምንጮች እንደሆኑ ፍራንሲስ ፉኩያማ ‹Identity› በተሰኘ መጽሐፉ ያትታል። በኛ ሀገር ግን ከኃይል ምንጭነትም ይሻገራል። የእናት ሀገር ክብር ሲነካ ሕዝቡ ያብራል። አንድያ ነፍሱን ይገብራል። ይመር የተሰኘው አዝማሪው ገጸባሕርይ ግን አሪስቶክራት ኅብረተሰብ ዘንድ እንዳሉት ሜጋሎቲሚያ (ከሌሎች እንደሚልቁ እውቅናን የሚሹ)፤ ክብርን ፈልጎ ነበር ሊዘምት የወጠነው። የአርስቶትል ሪፐብሊክ ላይ እንደተጠቀሰው፥ “ታይሞስ” በተሰኘው የዕውቅናን ክብር የሚፈልገው የነፍስ ክፍል ገፍቶት ነው፣ ከሞት አፍንጫ ሥር ለመርመስመስ ልቡ የተነሳሳው። ለዚህ ነው ሰዒድ የተሰኘው ወዳጁ፤ “ጃኖይ ዐይን እንዲትገባ ቀዴም ቀዴም ማለት አለብህ” ያለው ትዝ የሚለው። ለዚያ ነው “ አቤቱ ፈጣሪየ … የልቤን ቁስል ምታቅ አንተ ብቻ ነህ። ተወረይሉ ወጥቸ … ተሰው ተቆጥሬ … ተከብሬ … ምመኘው እሱን ብቻ ነው” እያለ ከራሱ ጋር የሚነጋገረው። የኋላ ኋላ ግን ከወረኢሉ ተነስተው፥ የደሴን እንቆቅልሽ ፈትተው፥ የአላማጣን መንታ አልፈው፥ የመቀሌን የስሜት ገበታን ተወጥተው፥ ይሐ ላይ አኮብኩበው፥ የዐድዋ የገድል አክሊል ዘንድ ሲደርሱ የወረኢሉው ይመር በዐድዋው ይመር ይተካል። የይመር “ታይሞስ” ይሟሽሻል። አሰቃቂውን ጦርነት ከተካፈለ በኋላ፣ “ያንን ሰፊ የጦር አውድማ፣ ያንን ገላጣ መሬት የከበቡትን ተራሮች አንድ በአንድ አየና ግዝፈታቸው አስፈራው፣ ግርማ ሞገሳቸው አክብሮት፣ አድናቆትና ፍርሐት ጫሩበት። በነሱ ፊት ከሰናፍጭ ያነሰ መሆኑ ታወቀው። “ተይመር ወዲያ” የሚለው ፈሊጡ ብልጭ አለለት፤ ልኩን አለማወቁን ጠቆመው። ”ተራሮቹ“ በእናት ሀገርህ ክብር ውስጥ ነው የአንተም ክብር ያለው!” ሲሉ ሰበኩት። ጃንሆይ ፊት ቀርቦ መሞገስ፣ መወደስ ውጥኑ የነበረው ይመር እያለ ሚስቱ ዘውዴ ምርኮዋን ይዛ ስታልፍ ንጉሠ ነገሥቱ እጅ ነሷት። ወለፈንዴ ብሎ ዝም! ይመር የዴቪድ ሊቨንግስተን ወንድም የጣለውን ካርታም አይደል ያነሳው? ታዋቂ መኾን የሚፈልገው የዴቪድ ሊቪንግስተን ወንድም የሚታወቀው፥ የዴቪድ ሊቨንግስተን ወንድም በሚል ቀጭንዬ መስመርም አይደል? ተጨማሪ ያንብቡ https://t.ly/JyOt7
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።
Enkuan Aderesen
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#MoE በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል። በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል። ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔ መሠረት 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑን ተረድተናል። Via @tikvahuniversity
видео или голосовое, без подписи
የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ፈተናን በወረቀት ለሚፈተኑ ተፈታኞች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀድሞው የተሻሻለ የመልስ መስጫ ወረቀት ለተፈታኞች ምቹ በሆነ ዲዛይን በአዲስ መልክ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ተፈታኞች ማድረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ማስገንዘብ በማስፈለጉ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ✅ተፈታኞች ማድረግ ያለባቸው ነገሮች 👉ክረምት ከመሆኑ አኳያ በሚፈጠር እርጥበት፣ የምትፈተኑበት ጠረጴዛ ላይ ባለ ፈሳሽ ነገርም ይሁን በሙቀት በሚፈጠር የእጅ ላብ ወረቀቱ እንዳይረጥብ እና እንዳይቀደድ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። 👉ሙሉ ስማቸውን የሚፈተኑትን የት/ት ዓይነት እና የተማሩበትን ት/ቤት በcapital letter ሊነበብ በሚችል መልኩ በተቀመጠው ጠቋሚ መሰረት ነጭ ቦታው ላይ ብቻ ይፃፉ፡፡ የሚጽፉትን ከአድሚሽን ካርዳቸው ጋ ማግኘት ይችላሉ። 👉የመፈተኛ መለያ ቁጥራቸውን(ከአድሚሽን ካርዳቸው) የት/ቤት መለያ ቁጥራቸውን(ከአድሚሽን ካርዳቸው) የሚፈተኑትን የጥያቄ ወረቀት መለያ ቁጥር(hጥያቄ ወረቀቱ )እና የት/ት ዓይነቱን መለያ ቁጥር ከአድሚሽን ካርዳቸው ወይም ከጥያቄ ወረቀቱ) በመውስድ በትክክል በቦታው ላይ መፃፍ እና በተፃፈው ትይዩ ወደታች የፃፉትን ቁጥርበተሰጠው የአጠቋቆር መግለጫ መሰረት በትክክል ሙሉ ክቡን ማጥቆር ግዴታ ነው። 👉ፈታኙ የፃፈውን እና ተፈታኙ ፅፈው ያጠቆሩትን የጥያቄ ወረቀት መለያ ቁጥር ተመሳሳይመሆኑን ማረጋገጥ። 👉በሚፈተኑት የት/ት ዓይነት የጥያቄ ቁጥር ብዛት መሰረት እና በተሰጠው የአጠቋቆርመግለጫ መሰረት ከአራቱ አማራጮች ውስጥ መልስ ነው ብለው ያመኑበትን አንድ ፊደል 👉መልሱን ሲያጠቁሩ ተሳስተውም ይሁን መልስ ቀይረው ለማስተካከል ከፈለጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን መልስ እርሳሱ እስኪለቅ ድረስ በደንብ ማጥፋት ግዴታ ነው። 🙅♂️ተፈታኞች ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች 👉ፈሳሽ ያለበት ነገር ላይም ይሁን እርጥበት ያለበት ቦታ ላይ የመልስ ወረቀቱን ማስነካት ወይም ማስቀመት በፍጡም የተከለከለ ነው። 👉መፃፍም ይሁን ማጥቆር ከሚገባቸው ቦታ ውጪ የመልስ ወረቀቱ detect mark guide (5ቱ ክቦች)፣ ከመስሪያ ቦታው ውጪ ባሉ አራቱም ህዳጎች እንዲሁም ከመልስ ወረቀቱ ጀርባ ላይ በምንም አይነት መልኩ የእርሳስም ይሁን የሌላ ነገር ምልክት መተው በፍፁም የተከለከለ ነው። 👉ከአንድ በላይ መልስ ማጥቆር 👉ምንም መልስ ሳያጠቁሩ ማለፍ 📌ማጠቃለያ 👉መኮረጅም ይሁን ማስኮረጅ ሙሉ ውጤትን እስከመሰረዝ ድረስ ያስቀጣል። 👉ከአንድ በላይ መልስ ማጥቆር ውጤት አያሰጥም። 👉ምንም መልስ አለማጥቆር ውጤት አያሰጥም። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ? ➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ? ➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም #Ethiopia #NationalExam #Grade12 #TikvahEthiopiaFamily TIKVAH-ETH
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи