ዓምደ ተዋሕዶ
Статистикаሠላም✋ 🙏 እንኳን ደህና መጡ 🙏 ሠላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን ይህ በፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓምደ ተዋህዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ገጽ ነው በዚህ ይፋዊ ገጽ ላይ :- #መንፈሳዊ ትምህርቶች #መንፈሳዊ ዝማሬዎች #መንፈሳዊ መጽሐፍቶች # ገድሎች #ምስባክ # የእለት ስንክ ሳር 👉እና ሌሎችም የቤተክርስትያንን ቀኖና የጠበቁ ሀሳቦች የሚቀርቡበት ገጽ ነው። 🙏share🙏
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 64
- 1/48двое суток
- 73
- 1/72трое суток
- 79
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ፍልሰታ ምን ማለት ነው? ፍልሰታ ማለት ‹ፈለሰ – ተሰደደ› ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡›› 'ፍልሰታ ለማርያም' የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ሐዋርያት ኹለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡ እንኳን አደረሳችሁ !
ክፍል ፪ ሱባኤ ለመግባት መደረግ ያለበት ዝግጅት ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት ኣስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡ ቅድመ ዝግጅት ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/ በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኣንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት ኣለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሓ ኣባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በኣባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ ኣባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኣንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሓ ኣባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡ ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ ኣቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው ኣንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዓቅምንና ችሎታን ኣገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡ ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኣብዛኛው ሱባዔ የሚገባው ኣጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን ኣለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በኣጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሓራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በኣጽዋማት ወቅት ብዙ ኣባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከኣባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ ኣይያዝም» የሚል ኣቋም ለመያዝ ኣይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ካጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ ኣያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና ኣድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡ ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/ በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል። መዝ 5:3፤ መዝ 133:2፤ ዮሐ 11:41 ።
ክፍል ፩ 🍁🌿✨🍁🌿✨🍁🌿✨🍁🌿✨🍁🌿✨ ሱባዔና ሥርዓቱ 🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩 ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡ ሱባዔ ምንድን ነው? ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ሱባዔ መቼ ተጀመረ? ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡ ሱባዔ ለምን? የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡ 🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩 በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡ ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡ እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡ 🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩 ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ 🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩 አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡ ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡ ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡ #ይቀጥላል🟢 በቀጣይ ክፍል ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ?
без подписи
ምክረ አበው 🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐 'ስለ ሌላው ሰው ከመፍረድህ በፊት፣ በእርሱ ጫማ ውስጥ ገብተህ ለመራመድ ሞክር። ያኔ መፍረድ ትተህ መጸለይ ትጀምራለህ።" አባ ሙሴ ጸሊም 🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐 "እግዚአብሔር አንተን ሲፈጥርር ዓለም አላሰፈለጋትም ነበር እርሱ ግን አስፈልገኸዋል አሁንም አንተ ባትፈልገው እንኳ እርሱ ይፈልግሃል'' ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐 "ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት ለማስተካከል በነገው ቀን አትተማመን፤ ነገ ያንተ አይደለምና። ጠላት ሰይጣን በኋላ ታደርገዋለህ እያለ እሁንህን ሊሰርቅህ ይወዳል፡፡ ዛሬ ለመውደድ፣ ይቅርለማለትና ንሰሐ ለመግባት ያለህ የመጨረሻው ዕድል እንደሆነ አድርገህ ኑር፡፡'' አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐 ጸሎት ክፋ ሀሳብ ከውስጣችን የሚወገድበት መንገድ ነው። ከጨለማ ኃይላት ርቆ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መግባት የሚቻለውም በጸሎት ነው። አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐 “በደልህን ይቅር የሚልህ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ የሰውን በደል ይቅር ማለት ደግሞ የአንተ ድርሻ ነው።" አባ ሙሴ ጸሊም
እንኳን #ለመርባስ ከሚባል አገር ሰዎች ለሆኑ #ለቅዱሳን_ዮሐንስና_ለአባቱ_ወንድም_ልጅ_ለስምዖን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና #ለእስክንድርያ_ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ ለሆነው #ሊቀ ጳጳሳት_ለቅዱስ_ለአባ_ገብርኤል ለዕረፍቱ በዓል በሰላሞ አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ በአስቄጥስ ገዳም ከነበረው ከቅዱስ አባት ኢሳይያስና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
ስምዖን ቀለዮጳ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክንድርያ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ከላድያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት መላእክት ይጎበኙት ለነበረ ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ለነበረ ለአባ ብስንዳ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከምትታሰበው፦ ከሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) አብራ ሰማዕትነት ከተቀበለች ከቅድስት ቴዎና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን።
እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለኢትዮጵያዊው_ለጻድቁ ለአባታችን #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ በዐባይ ባሕር ውስጥ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ #ለዘጠኝ_ዓመት ከጸለዩ በኋላ #ከጌታችን_ቃል ኪዳን_ለተቀበሉበት_ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን #ጌታችን_በአረጀ_መነኲሴ አምሳል ለተገለጸላቸ በጀርባቸው ላዘሉት የሚነድ መለኮት በከንፈራቸው ለሳሙ ለአባታችን #ለአቡነ_ኪሮስ ለዓመታዊ ለዕረፍታቸው በዓላቸው፣ አባ ኪሮስ ለቀበረው ለንጉሥ ልጅ ድኃ ለነበረው #ለአባ_ሚሳኤል ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልእግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም አባ_ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሥሉስ ቅዱስ በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና:: ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ:: ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል:: አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው:: ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና:: ሐምሌ 7 ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም የተገለጠለት በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው።
እንኳን እንደ እርሱ ያሉ #ኤልያስና_ኄኖክ ወደ አሉበት ብሔረ ሕያዋን ለተሰወረው #ለነቢዩ_ለቅዱስ_ዕዝራ_ሱቱኤል_ለዕርገቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስና ለቅዱስ ጳውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ሐምሌ ፭ ቀን የቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች፣ የዓለም ብርሃናትና የቅዱስ ወንጌል ፋናዎች እንዲሁም ዋነኞቹ ሐዋርያት የሆኑት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ያረፉበት ታላቅ ዕለት ነው። ሁለቱም ሐዋርያት በተመሳሳይ ዕለት በሮም ከተማ በግፈኛው ንጉሥ ኔሮን እጅ የክብርን አክሊል ተቀዳጅተዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ (የሐዋርያት አለቃ) ጥሪውና አገልግሎቱ፦ ቀድሞ ስሙ ስምዖን ይባል ነበር፤ ጌታችን ደግሞ "ጴጥሮስ (አለት)" አለው። የገሊላ ባሕር ዓሣ አጥማጅ የነበረው ጴጥሮስ፣ የጌታችንን ጥሪ ተከትሎ "ሰዎችን አጥማጅ" ሆነ። ክብሩ፦ የሐዋርያት መሪና የቁልፍ ጠባቂ ተብሎ የተሾመ፣ በደበረ ታቦር የጌታን መለኮታዊ ክብር ካዩት ሦስት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው። በጥላው ድውያንን ይፈውስ፣ ሙታንንም ያስነሳ ነበር። ሰማዕትነት በሮም ከተማ ወንጌልን ሲሰብክ በሰማዕትነት እንዲሞት ተፈረደበት። ነገር ግን "ከጌታዬ እኩል ቀጥ ብዬ ልሰቀል አይገባኝም" በማለት በትሕትና ራሱን ዘቅዝቆ እንዲሰቅሉት አድርጓል፤ በዚህም የሰማዕትነት አክሊልን አግኝቷል። ቅዱስ ጳውሎስ (የአሕዛብ ሐዋርያ) መለወጡ ቀድሞ ሳውል በሚል ስሙ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ጸሐፊና ፈሪሳዊ ነበር። ወደ ደማስቆ ሲጓዝ ጌታችን በታላቅ ብርሃን ተገልጦ "ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?" ካለው በኋላ ተለውጦ ታላቅ ሐዋርያ ሆነ። አገልግሎቱ ለአሕዛብ ወንጌልን ለማድረስ ሦስት ታላላቅ የጉዞ ስብከቶችን አድርጓል፤ 14 መልእክታትንም በመጻፍ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በግርፋት፣ በስደትና በብዙ መከራ ውስጥ አልፏል። ሰማዕትነት ልክ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁሉ በሮም ከተማ በሰማዕትነት ያረፈ ሲሆን፣ እርሱ ግን የሮም ዜግነት ስለነበረው በሰይፍ ራሱን በመቀላት የሰማዕትነት ፍጻሜውን አግኝቷል። እነዚህ ሁለት ቅዱሳን ምንም እንኳን አስተዳደጋቸው፣ ጥሪያቸውና የአገልግሎት መንገዳቸው የተለያየ ቢሆንም፣ በክርስቶስ ፍቅር አንድ ሆነው ለወንጌል እውነት ሕይወታቸውን ሰጥተዋል። ጴጥሮስ ለአይሁድ፣ ጳውሎስ ለአሕዛብ ወንጌልን በመስበክ የክርስትና መሠረት ሆነዋል። "መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፥ ሩጫውን ጨርሻለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል..." (2ኛ ጢሞ. 4፡7) የቅዱሳን ሐዋርያት በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን። "አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት፣ ወንጌለ መንግሥት አወፈዮሙ፤ ሰንበተ ክርስቲያን ለዕረፍት ሠርዐ ሎሙ፤ ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ፤ ወከመ ጽንሐሕ መሥዋዕት ተወክፎሙ አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት። ትርጉም፦ ሐዋርያትን በሰማያት ሸለማቸው፤ ገነት መንግሥተ ሰማያት የምታስገባ ወንጌልን ሰጣቸው፤ ሰንበተ ክርስቲያንን ሠራላቸው (ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጀላቸው)፤ እንደ ወርቅ በእሳት ፈተናቸው፤ ወይም ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን በመከራ ፈተናቸው፤ እንደ ጽና መሥዋዕት (እንደ ተወደደ የመሥዋዕት መዐዛ) ተቀበላቸው፤ በሰማያትም ሸለማቸው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
እንኳን #ለብርሃናተ_ዓለም_ለቅዱስ_ጴጥሮስ፣ #ቅዱስ_ጳውሎስ_በጫካኙ ንጉሥ በኔሮን ቄሳር እጅ #ሰማትነት_ለተቀበሉበት_ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_ሳቁኤል_ለበዓሉ_መታሰቢያ፣ #ለሰባ_ሁለቱ_አርድእት_ለመታሰቢያቸው_በዓላቸው፣ #ለአባታችን_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸውና ለሐዋርያት (ለሰኔ) ፆም ፍቺ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ፡በዚች ከሚታሰቡ፦ በጋዛ ሰማዕት ከሆነ #ከይስሐቅና_ከደብረ_ዓሣ_ጻድቃንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ አራት በዚህች ቀን #የቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ፣ #የነቢዩ_ሶፎንያስ እረፍት ነው፣ የዐሥራ ሁለቱ #ደቂቀ_ነቢያት መታሰቢያቸው ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ ሐምሌ አራት በዚች ቀን የቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ። ይህም እንዲህ ነው እሊህ ቅዱሳን የካቲት ስድስት ቀን ሰማዕታት ሆነው በሞቱ ጊዜ ምእመናን ሥጋቸውን ተሸክመው ወስደው በእስክንድርያ ከተማ በስተሰሜን ባለች በቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥውር አኖሩዋቸው እስከ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ዘመንም በዚያ ኖሩ። የእግዚአብሔር መልአክም ለቅዱስ ቄርሎስ ተገለጸለት ወደ ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ሔዶ የቅዱሳን የአቡቂርንና የዮሐንስን ሥጋቸውን አውጥቶ እንዲሸከም አዘዘው። እርሱም ተነሥቶ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ሕዝቦች ነበሩ በደረሱም ጊዜ ጸለዩ ምድሩንም ሲቆፍሩ ሥጋቸው በውስጡ ያለበት ቦታ ተገለጠላቸው በባሕር ዳርቻ ወደ አለች ወደ ሌላዪቱም የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ተሸክመው አድርሰው በዚያ አኖሩ። በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው በዚችም ቀን ታላቅ በዓል አደረጉ ከሥጋዎቻቸውም ድንቆች ተአምራት ተገለጡ አረማውያንም ተሰበሰቡ ይህንንም ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ትተው ክርስቲያኖች ሆኑ። በዚያቺም የጣዖቶች ቤት አሸዋ በላይዋ ተከመረባት ታላቅ ኮረብታም ሆነ። የቅዱሳንም ሥጋቸው ታምራትንና ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስን ያደርጋል። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ነቢዩ_ሶፎንያስ በዚህችም ቀን ደግሞ የአማርያ ልጅ፣ የሴዴቅያስ ልጅ፣ የጎዶልያ ልጅ፣ የኩሲ ልጅ የሶፎንያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እርሱም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ትንቢት ተናገረ። እንዲህም አለ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ፈጽመው ይጠፋሉ አለ ከብቶችና ሰዎች ያልቃሉ። የባሕር ዓሣዎችና በሰማይ የሚበሩ አዕዋፍም ያልቃሉ። ዳግመኛም ስለሞአብ እንዲህ አለ ስለዚህ ሞአብ እንደ ሰዶም ትሆናለች የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ልጆች ይሆናሉ ደማስቆም እንደ እህል ታልቃለች። እርሱ እንደ ተነበየው እነዚያ አገሮች በናቡከደነጾር ምርኮ ይጠፋሉና። ዳግመኛም ስለ ፋርስና ስለ ነነዌ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ የፋርስን ሰዎች አጠፋቸዋለሁ ነነዌንም ፍርስራሽና ውኃ እንደሌለባት ምድረ በዳ አድርጋታለሁ መንጋዎችም በመካከሏ ይሠማሩባታል። ይህቺም ከተማ በመቄዶናዊው እስክንድር እጅ ጠፍታለች። ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ መምጣት እንዲህ ተናገረ። ያን ጊዜም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራ ዘንድ በአንድ ሕግም ይገዙልኝ ዘንድ የአሕዛብን ሁሉ አንደበት ወደ ሕግ እመልሳለሁ። ደግሞም እንዲህ አለ ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ መሥዋዕቴን ያመጡልኛል። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ደቂቀ_ነቢያት ዳግመኛም በዚች ቀን ስለ ክርስቶስ ትንቢታቸውን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያጐረፉ የዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት መታሰቢያቸው ነው። ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው፡፡ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት የሚባሉት፡- ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ኢዩኤል፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ እንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ዋና (ዓበይት) ነቢያት የሚባሉት አራት ሲሆኑ እነርሱም ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤልና ዳንኤል ናቸው፡፡ ከሆሴዕ እስከ ሚልክያስ ድረስ ያሉት ነቢያት ‹‹ደቂቀ ነቢያት›› የተባሉት ምክንያት አንድም የነቢያት ልጆች በመሆናቸው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የጻፏቸው ትንቢቶቻቸው ዓበይት ነቢያቱ ከጻፏቸው ጋር በንፅፅር ሲታይ አነሥተኛ ስለሆነ ነው፡፡ 'ነቢይ' ማለት እግዚአብሔር የመረጠውና የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ የሚያስተላልፍ ብሎም የተሠወረውንና የሚመጣውን ሁሉ በግልጽ የሚመለከት ማለት ነው፡፡ ነቢያት ሲባሉ በአጠቃላይ ምግባር ሃይማኖታቸው ያማረ፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው የሰመረ ነውና አካሄዳቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቄርሎስ አረፈ፣ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ክልስቲያኖስ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ቄርሎ ስ ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ቄርሎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላ*ካውያት የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው። ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርቱን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው። ከዚህም በኋላ ሁልጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር በሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው። ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር። አባ ቴዎፍሎስም ከአረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስ*ጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ። ይህን አባት ቄርሎስንም መርጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት። ንስጥ*ሮስንም ተከራከረው ስሕተ*ቱንም ገለጠለት። ከስሕ*ተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግ*ዘው ከመንበረ ሢመቱ አሳደ*ዱት። ይህም አባት ቄርሎስ ዐሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ ከእነርሱ በኋላ ግን ብዙዎች ድርሳናትን ተግሣጻትንና መልእክቶችን ደረሰ። እሊህም በሁሉ ቦታ በምእመናን እጆች ይገኛሉ። ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትስብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራው ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ አስረዳ። ይህም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስን ወደ ሁለት የሚከፍሉትን መናፍ*ቃንን ሁሉንም አው*ግዞ ለያቸው። በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነ ሥራውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ክልስቲያ ኖስ በዚህችም ቀን ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ የነበረ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ክልስቲያኖስ አረፈ። ይህ አባ ዮናክንዲኖስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዱሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ ብሎ አዘዘው። ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲኖስ ባረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፋንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በዚያን ወራት ደግ ንጉሥ አኖሬዎስ ነበረ። ከርሱም በኋላ ዐመ*ፀኛ ሉልያኖስ ነገሠ ። እርሱም ክልስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መና*ፍቁ ንስ*ጥርስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክልስቲያኖስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድ*ለውም ይሻ ነበር። እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር። ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሔደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ሩፋኤልም ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው በዚያም ኑር አለው። ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድ*ልህ ዘንድ በልቡ አስቧልና። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱ ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ። ወደ እንጾኪያም ከተማ ደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስን አገኘው ከዐመፀኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው። ከዚህም በኋላ ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲኖስ በሌሊት ራእይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋር የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበረ። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ። ንጉሥም ጌታዬ ምን ላድርግ አለው እነዚያም ሁለቱ አባቶች በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን ብለው መለሱለት እኔ አምናለሁ አላቸው ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስን ወደ መንበሩ መልሰው አሉት። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ ድምትርያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሢመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን ለመልእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሃለሁ። መልክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት። በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደኅና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች። የንስጥሮስም ክህ*ደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምክንያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ። ይህ አባት ክልስቲያኖስም በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደጉባኤው መምጣት አልተቻለውም ነገር ግን ንስ*ጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋራ ሁለት ቀሳውስትን ላከ። ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲኖስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርቶሃልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው ተኵላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ። ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ እንነሣና እንሒድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው። በዚችም ሰዓት ከዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን ሀገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው። ይህንንም ብሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
እንደ ለመነውም አደረገለት የሃይማኖትንም ሕግ አስተምሮ የክርስትናን ጥምቀትም አጠመቀው ሥጋውንና ደሙንም አቀበለው ሁሉንም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከዚህ በኋላ ከዚያ ወጣ በሰላምም ሸኙት በብዙ አገሮችም ውስጥ ገብቶ ሰበከ ከአይሁድና ከአረማውያንም መከራ ደረሰበት። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
#ሐምሌ_2 #ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሁለት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላያቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። አንድ ቀንም ወደ ሶርያ ከተማ ሲጓዝ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ በሚአምር ጐልማሳ አምሳል ለእርሱ ተገልጦ ወዳጄ ታዴዎስ ቸር አለህን አትፍራ እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አለው ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። ወደ ከተማውም በቀረበ ጊዜ ከእርሱ ጋራ አባት ጴጥሮስ ነበረ ማሳ የሚያርስ ሽማግሌ ሰውን አዩ ሐዋርያትም ሰላምታ ሰጡትና ሽማግሌ ሆይ የምንበላው እንጀራ ስጠን አሉት። እርሱም ከዚህ የለም ግን አመጣላችኋለሁ እናንተም ከበሮቹ ዘንድ ተቀመጡ አላቸው እነርሱም እንዳልክ አሉት። ያ ሽማግሌም ከሔደ በኋላ ሐዋርያ ከበሮች ጋር ያለ ሥራ በከንቱ መቀመጥ ለኔ ኅፍረት ነው ያ ሽማግሌ ለእኛ በጎ ሊሠራ ሒዷልና አለ። ይህንንም ብሎ ተነሥቶ እርፉን ይዞ በበሮቹ ላይ ድምፅ አሰማና ያርስ ጀመረ በዚያም ከርሱ ጋራ የሥንዴ ዘር ነበረና ያን ጊዜ ዘሩንና ማሳውን ባርኮ የሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእርሻው ላይ ዘራ ሠላሳ ትልሞችንም አረሰ። የተዘራው ዘርም ወዲያውኑ በቀለና አደገ እሸትም ሆነ ያ ሽማግሌም በተመለሰ ጊዜ ሐዋርያት ያደረጉትን ተመልክቶ ደነገጠ። ከእግራቸውም በታች ወድቆ ሰገደ እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን አላቸው እነርሱም እኛ የቸሩ አምላክ ባሮቹ ነን እንጂ አማልክት አይደለንም አሉት ደግሞ እንዲህ አላቸው ስለ አደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ሁሉ ልከተላችሁን። ይህን ልታደርግ አይገባም ነገር ግን በሮቹን ለጌታቸው ወስደህ መልስ ቤትህንም አዘጋጅልን የምንበላውንም ታዘጋጅልን ዘንድ ለሚስትህ ንገራት። እኛም ወደዚች ከተማ ልንገባና እግዚአብሔር እስከ ጠራን ድረስ በውስጧ ለመኖር እንሻለን አሉት። ከዚህም በኋላ ያ ሰው ከዚያ እርሻ እሸት ቆርጦ ተሸከመ በሮቹንም እየነዳ ሔደ የከተማው ሰዎችም የተሸከመውን እሸት አይተው አሁን የእርሻ ወቅት አይደለምን ይህን ከወዴት አገኘህ አሉት ቃልንም አልመለሰላቸውም። በሮቹንም ለጌታቸው መለሰ ወደ ቤቱም ሔዶ ለሐዋርያት ቦታን አዘጋጀ ራትንም እንድታዘጋጅላቸው ለሚስቱ ነገራት። ወሬውም ወደ ከተማው መኳንንት ደረሰ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ይህን እሸት ከወዴት እንዳገኘህ ንገረን ብለው ወደርሱ ላኩ። ይህንም በሰማ ጊዜ ከእኔ ጋራ ሕይወት ሳለ ሞትን አልፈራም አለ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው። ሒደህ ወደእኛ አምጣቸው አሉት እርሱም ጥቂት ቆዩ እነርሱ ወደእኔ ቤት ይመጣሉ በመጡም ጊዜ በዐይኖቻችሁ ታይዋቸዋላችሁ አላቸው። ሰይጣንም የከተማ መኳንንቱን ልቡና ለውጦ አከፋ እኒህ አይሁድ ከሰቀሉት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ወገኖች ውስጥ ከሆኑ ወዮልን እንድንገድላቸውም ተዘጋጁ አሉ። እኩሌቶቹም ልንገድላቸው አንችልም አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማው መግቢያ በር ራቁቷን እናስቀምጣት በአዩዋትም ጊዜ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ወደ ከተማችንም አይገቡም አሉ። እንዲሁም አደረጉ ሴትዮዋንም አራቁተው በከተማው መግቢያ በር ላይ አስቀመጧት። ሐዋርያው ታዴዎስም በአያት ጊዜ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ በራሷ ጠጉር በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ላክልን አለ። በዚያን ጊዜም ተሰቀለች የከተማዋ ስዎችም አዮዋት ያቺ ሴትም ከከተማዋ መኳንንቶች አቤቱ ፍረድልኝ እያለች ጮኸች ነገር ግን የሐዋርያትን ቃል ወደ መቀበል አልተመለሱም ሰይጣን የሰዎችን ልብ አጽንቷልና ። ከዚህም በኋላ ወዲያውኑ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ወረደና የከተማው ሰዎችን ልቡና የማረኩ መናፍስት ርኩሳንን አስወጥቶ ስደዳቸው ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ያን ጊዜም ሐዋርያው ታዴዎስ ያቺን በአየር ላይ የተሰቀለችውን ሴት አወረዳት። ከዚህ በኋላም ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ያቺንም ተሰቅላ የነበረች ሴት ለቤተ ክርስቲያን የምትላላክ ዲያቆናዊት አደረጋት። በሐዋርያትም እጆች ብዙ ድንቅና ተአምር ተደረገ ዕውሮች አዩ ሐንካሶችም በትክክል ሔዱ ዲዳዎች ተናገሩ ደንቆሮዎች ሰሙ ለምጻሞች ነጹ አጋንንትም ከሰው እየወጡ ተሰደዱ የከተማው ሰዎችም ሁሉ በጌታችን እስኪያምኑ ሙታን ተነሡ። ሰይጣንም የከተማው ሰዎች ሁሉም በጌታችን እንዳመኑ በአየ ጊዜ ተቆጣ በአንድ ገንዘብ በሚወድ ጎልማሳ ባለጸጋ ልብ አድሮም በሐዋርያው ታዴዎስ ላይ አነሣሣው ወደርሱም መጥቶ ሰገደለትና እንዲህ አለው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እኔ ብዙ ገንዘብ አለኝ እድን ዘንድ ምን ላድርግ አለው። ሐዋርያውም ጎልማሳውን ፈጣሪህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ኃይልህ ውደደው አትግደል አትስረቅ አታመንዝር በአንተ ሊያደርጉብህ የማትሻውን በሌላው ላይ አታድርግ ደግሞም ገንዘብህን ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ስጥ በሰማያትም ለዘላለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ አለው። ይህንንም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተመልቶ ሐዋርያው ታዴዎስን ይገድለው ዘንድ አነቀው። የእግዚአብሔርም ኃይል ከዚህ ሐዋርያ ጋር ባይኖር ኖሮ ከመታነቁ ጽናት የተነሣ ዐይኖቹ ተመዝዘው በወጡ ነበር። አባት ጴጥሮስም የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ አለው ያን ጊዜም ተወው ሐዋርያው ታዴዎስም ጌታችን እንዳንተ ላለው ሀብታም ባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ገመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ብሎ በእውነት ተናገረ አለው። ጐልማሳው ባለጸጋም ይህ ነገር ትክክል አይደለም እንዴት ሊሆን ይችላል አለ። በዚያን ጊዜም በዚያ ጐዳና ሊያልፍ ባለ ገመል መጣ ሐዋርያው ታዴዎስም ጠርቶ አስቆመውና መርፌ ከሚሸጥ ዘንድ መርፌን ፈለገ። መርፌ የሚሸጠው ግን ሐዋርያውን ሊረዳው ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የሆነ መርፌ አመጣለት ሐዋርያውም እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ነገር ግን በዚች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የሆነ መርፌ አምጣልን አለው። .ከዚህ በኋላ ባለ መርፌው ቀዳዳው ጠባብ የሆነውን መርፌ ባቀረበለት ጊዜ ኃይልህን ግለጥ ብሎ ወደ ጌታችን ጸለየ እጁንም ዘርግቶ ባለ ገመሉን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንተ ከገመልህ ጋራ በመርፌ ቀዳዳ ውስጥ ግባና እለፍ አለው ገብቶም አለፈ ሕዝቡ የፈጣሪያችን የክርስቶስን ኃይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ አለው ባለ ገመሉም በመርፌው ቀዳዳ ሦስት ጊዜ ከገመሉ ጋራ አልፎ ሔደ። ሕዝቡም አይተው ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ። ያም ጐልማሳ ባለጸጋ መጥቶ ከሐዋርያው እግር በታች ወድቆ ሰገደና ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ ገንዘቤንም ሁሉ ወስደህ ለድኆችና ለምስኪኖች አከፋፍል አለው።
без подписи
አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ታአምር ተገለጠ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳን_ብዮክና_ብንያሚን በዚህችም ቀን ቅዱሳን መስተጋድላን ብዮክና ብንያሚን አረፉ። እሊህም ቅዱሳን በግብጽ ደቡብ በቴዎዳ አውራጃ ቱና በሚባል አገር የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ነበሩ። እነርሱም ወንድማማች ነበሩ። አባታቸውም የቤተ ክርስቲያን ሹም የሆነ ደግና የዋህ ሰው ነበረ እሊህም ሁለቱ ልጆቹ በእግዚአብሔር ጸጋና በቅድስና ፍጹማን ነበሩ። እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ተአምራትን ያደርግ ነበር በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር እነርሱም ከቤተ ክርስቲያኑ የጉድጓድ ውኃ ቀድተው በሽተኞችን ያጥቧቸዋል ወዲያውኑም ከበሽታቸው ይድኑ ነበር። የአባታቸው የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ በዚያን ሰዓት ቀሲስ ብንያሚን ቍርባን ያሳርግ ዘንድ የቅዳሴ ልብስ ለብሶ በቤተ መቅደስ ነበረ መልዕክተኞችም መጥተው አባቱ ለመሞት እንደ ተቃረበ እርሱንም እንደሚፈልገው ነገሩት። ብንያሚንም የቍርባኑን ሥርዓት ሳልፈጽም ልብሰ ተክህኖውን አላወልቅም ከመሞቱ በፊት እንዳየው እግዚአብሔር ከፈቀደ ይቆየኛል ካልሆነም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን አለ። አባቱም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ላከ አባ ብንያሚን ግን የቍርባኑን ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ወደ አባቱ ሔደ ሙቶም አገኘው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ንዋየ ቅድሳትም እጅግ አዘነ እነርሱ በእርሱ ዘንድ እየኖሩ ዕቃዎችን ያኖረበትን ቦታ አላመለከታቸውም ነበርና። ወንድሙ ብዮክም አባታቸው ስለ አስቀመጠው ንዋየ ቅድሳት ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ ቅዱሳን አረጋውያን ሒዶ እንዲጠይቅ መከረው። አባ ብንያሚንም በሔደ ጊዜ የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት አባ ዳንኤልን አገኘው አባ ዳንኤልም ስለርሱ የመጣበትን ሥራ ሁሉ ነገረው ነገር ግን ወደ አንድ ጻድቅ ሰው እንዲሔድ አዘዘው እርሱም ንዋየ ቅድሳቱ ያለበትን እንደሚያስረዳው ነገረው። በሔደም ጊዜ እንደ አመለከተው ያንን ጻድቅ ሰው አገኘው። እርሱም ገልጾ አስረዳው በተመለሰም ጊዜ እንዳስረዳው አገኘው። ከዚህም በኋላ በመልካም ገድል ሁሉ ከወንድሙ ጋራ ተጠምዶ ኖረ። ለሕሙማን ነፍሳችው ሳትወጣ ያቀብሏቸው ዘንድ ከቅዱስ ቍርባን ከፍለው በሣጥን የማኖር ሥርዓት ነበራቸው ሰይጣንም ከይሲን አነሣሣውና ሣጥኑን ቀድዶ ከዚያ ከቅዱስ ቍርባኑ በላ። ብዮክና ብንያሚንም ይህን ባወቁ ጊዜ እጅግ አዘኑ ከይሲውንም ገደሉት ከዚህም በኋላ የተቀደሰውን ቍርባን ስለ በላ ከይሲውን ይበሉት ዘንድ ተማከሩ ፈቃዱም ከሆነ እንዲያስረዳቸው እግዚአብሔርን ለመኑት የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጸላቸውና ያን ከይሲ ይበሉት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም በሉት። ከበሉትም በኋላ አረፉ። እግዚአብሔርም ሥራቸውንና ገድላቸውን ለአንዲት ድንግል ሴት ገለጸ እርሷም የእሊህን ቅዱሳን ገድል ለሕዝብ ተናገረች እነርሱም የአማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ተአምርን አደረገ። ሥራ የሚሠራ አንድ ጎልማሳ ነበር ከሐዋርያው ቶማስም እጅ የተባረከ እንጀራ ከሕዝብ ጋራ ተቀበለ። ወደ አፉም ሊጨምረው በወደደ ጊዜ እጆቹ ደረቁ። ያዩት ሰዎች ግን በዚህ ሰው ላይ የሆነውን ለሐዋርያው ነገሩት። ሐዋርያው ቶማስም ጠራው ልጄ ሆይ አትፈር ንገረኝ የእግዚአብሔር ቸርነት በግልጽ ዘልፎሃልና አለው። ያም ሰው ከሐዋርያው እግር በታች ሰገደ መልካም ሥራ የሠራሁ መስሎኝ ክፉ ሥራን ሠርቻለሁ አንዲት የጠጅ አበዛ ሴት ነበረች አስቀድሞ ወደርሷ እኔ እገባ ነበር። አንተም በንጽሕና እንድንኖር አስተማርከን ያችም ሴት ከእርሷ ጋራ እተኛ ዘንድ ነዘነዘችኝ ስለዚህም ሰይፍ አንሥቼ አረድኳት ሐዋርያውም እንዴት እንዲህ ያለ ቁጣና የአውሬ ሥራን ሠራህ አለው። ከዚህ በኋላም ውኃ ያመጡ ዘንድ ሐዋርያው አዘዘና በውኃው ላይ ጸለየ ጐልማሳውንም በእግዚአብሔር ታምነህ እጆችህን ታጠብ አለው ሲታጠብም ዳነ። ከዚህም በኋላ የዚያች ሴት በድን ወደ አለበት ና ምራኝ አለው ያም ጐልማሳ መርቶ ወደ ቦታዋ አደረሰው በደረሰም ጊዜ አይቷት እጅግ አዘነ። ወደ ውጭም አውጥተው በዐልጋ ላይ ያኖሯት ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ እጁንም በላይዋ ጭኖ ጸለየ። ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጐልማሳውን ሒድ እጇን ይዘህ እኔ ቀድሞ በእጄ ገደልኩሽ አሁን ግን በሃይማኖት በእኔ እጅ ክርስቶስ ያስነሣሽ በላት አለው። እርሱም እንዳዘዘው አደረገ እጇንም ይዞ ሳባት ፈጥናም ተነሣች ሐዋርያውንም አየችው ዐልጋዋንም ትታ ከሐዋርያ ቶማስ እግር በታች ሰገደች የልብሱንም ጫፍ ይዛ በአንተ ዘንድ አደራ ያስጠበቀኝ ባልንጀራህ ወዴት አለ አለችው። ሐዋርያም ወደየት ደርሰሽ ነበር ንገሪኝ አላት እርሷም አንተ ከእኔ ጋራ እያለህ እንዴት ንገሪኝ ትለኛለህ አለችው ያየሽውን ንገሪ አላት። ከሥጋዬ በተለየሁ ጊዜ አንድ ልብሱ የቆሸሸ ሽታውም የሚከረፋ ጠቋራ ተቀበለኝ የእሳት ጉድጓድና የእሳት መንኰራኵር ወደአለበት ቦታ ወሰደኝ ደግሞም እድፍንና ትልን የተመላ ጉድጓድን አየሁ ነፍሳትም በውስጡ ይንከባለላሉ። በዚያም በምላሳቸው የተንጠለጠሉ አሉ በጠጉራቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በእጆቻቸውም በእግሮቻቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በላያቸውም ድኝ ይጤስባቸዋል ያስጨንቋቸዋልም። ያ የሚመራኝም እኒህ ነገረ ሰሪዎች፣ ሐሰተኞች፣ አመንዝራዎችና ቀማኞች፣ ሌቦች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ድኆችንና በሽተኞችን የማይጐበኙ፣ የእግዚአብሔርንም ሕግ የማያስታውሱ ናቸው ስለዚህ እንደ ሥራቸው ይቀጣሉ አለኝ አለች። ሐዋርያው ቶማስም ከዚያ የነበሩትን ይቺ ሴት የምትለውን ሰማችሁን ያለው ሥቃይ ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ከዚህ የሚከፋ አለ እናንተም የኃጢአትን ሥራና ክፉ አሳብን ትታችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። ትሕትናን፣ የዋህነትንና ፍቅርን፣ ንጽሕናንም ጠብቁ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ጸጋን ትቀበላላችሁ አላቸው። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ሕዝብ አመኑ ለድኆችም ምጽዋትን ሊሰጡ ብዙ ገንዘብ ሰብስበው አመጡ ለድኆች ምጽዋት መስጠት ለሐዋርያው ልማዱ ነበርና። ወሬውም በየሀገሩ ሁሉ ደርሶ በሽተኞችን ሁሉ አጋንንት የያዟቸውንም አምጥተው በጎዳና ዳር አኖራአቸው ሁሉንም በእግዚአብሔር ኃይል አዳናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ_እና_ታኅሣሥ)
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ አንድ በዚህችም ቀን #ቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው፣ ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች #ቅድስት_ቅፍሮንያ ሰማዕት ሆነች፣ #ቅዱሳን_ብዮክና_ብንያሚን አረፉ፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_ቶማስ በመሸታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ተአምርን አደረገ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ ሐምሌ አንድ በዚችም ቀን የሊቀ ጳጳሳቱ የአግናጥዮስ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙሩ ነው በስብከተ ወንጌልም በማገልገል ከእርሱ ጋር ብዙ አገሮችን ዙሮ አስተምሮአል ከዚህም በኋላ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው በውስጥዋመሰ ሕይወተሰ የሆነ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ብዙዎችንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በትምህርቱም ልቡናቸውን አበራላቸው። ከዚህም በኋላ ጣዖትን ለሚያመልኩ ስሕተቻተውን በገለጠላቸው ጊዜ ተቆጡ። ወደ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጠራብዮስ ሔደው ከሰሱት እንዲህም አሉት "አግናጥዮስ የአማልክቶችህን አምልከሸ ይሽራል እኮን ሰዎችንም እያስተማረ ክርስቶስን ወደ ማመን ያስገባቸዋል"። በዚያንም ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስመጣውና "አግናጥዮስ ሆይ ለምን ይህን አደረግህ የአማልክቶቼን አምልኮስ ለምን ሻርክ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ አስገብተሃቸዋልና" አለው። አግናጥዮስም "ንጉሥ ሆይ ቢቻለኝስ ያክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ባስገባሁህ ነበር" አለው ንጉሡም "ይህን ነገር ትተህ ለአማልክቶቼ ሠዋ አለዚያ በታላቅ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። "በእኔ ላይ የምትሻውን አድርግ እኔ ግን ለረከሱ አማልክቶችህ አልሠዋም ሥቃይህንም እሳትም ቢሆን አንበሳንም ቢሆን አልፈራም ከሕያው ንጉሥ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው። ይህንንም ሲሰማ ንጉሡ ተቆጣ ያሠቃዩትም ዘንድ አዘዘ በተለያዩ በብዙ ሥቃዮችም አሠቀሠዩት በእጆቹም ውስጥ እሳት አድርገወሰ ከእጆቹ ጋር በጉጠት ይዘው አቃጠሉት። ከዚህም በኋላ በዲንና በቅባት እያነደዱ ጎኖቹን አቃጠሉ በሾተሎችም ሥጋውን ሠነጠቁ። ከማሠቃየትም በደከሙ ጊዜ የሚያደርጉበትን እስከመክሩ ድረስ ከወህኒ ቤት ጨመሩት ብዙ ቀኖችም በዚያ ኖረ። ከዚህም በኋላ አስታውሱት ከወህኒቤትም አውጥተው በንጉሡ ፊት አቆሙት ንጉሡም "አግናጥዮስ ሆይ አማልክቶቼን ብታያቸው ውበታቸው ባማረህ ነበር" አለው። ቅዱሱም "ንጉሥ ሆይ አንተ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ብታምን ሙታኖችን የምታሥነሣቸው በሽተኞችንም የምትፈውሳቸው ባደረገህ ነበር"። ንጉሡም "ለፀሐይ ከመስገድ የተሻለ የለም" አለ የከበረ አግናጥዮስም "መንግሥቱ የማያልቀውን ፈጣሪ ትተህ ለተፈጠረ ፀሐይ ትሰግዳለህን?" ብሎ መለሰ ንጉሡም "ለራስህ መልካም አልክ ግን በመተላለፍ የአንጾኪያና የሶርያን ሰዎች ስበሕ ወደ ክርስቶስ አምልኮት አስገባሃቸው እንጂ" አለው። የከበረ አግናጥዮስም ተቆጥቶ "ንጉሥ ሆይ ከንቱ የሆነ ጣዖትን ከማምለክ ሰዎችን ስለሳብኳቸውና ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ስለአስገባኋቸው በእኔ ላይ ትቆጣለህን ለረከሱ ጣዖቶችህስ እንድሠዋ ታዘኛለህን እኔ ግን ቃልህን ተቀብዬ ለሰይጣናት አልሠዋም ለእውነተኛ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሠዋለሁ እንጂ" አለው። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ተቆጣ ከሥጋው ምንም ምን ሳያስቀሩ ይበሉት ዘንድ ሁለት የተራቡ አንበሶችን በላዩ እንዲሰዱ አዘዘ። የከበረ አግናጥዮስም አንበሶች ወደርሱ ሲቀርቡ በአያቸው ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሕዝብን እንዲህ አላቸው "ከዚህ የተሰበሰባችሁ እናንተ የሮሜ ሰዎች ቃሌን ስሙ እወቁም እኔ ይህን ሥቃይ የታገሥኩት በትዕቢትና በትምክህት አይደለም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እንጂ። አሁንም እኒህ አንበሶች እንደ ሥንዴ ይፈጩኝ ዘንድ ነፍሴ ወደደች የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ልትሔድ ነፍሴ ሽታለችና"። ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ አደነቀ ድንጋጤ አድሮበት እንዲህ አለ "የክርስቲያኖች ትዕግሥታቸው ምን ይብዛ ስለ አምልኮት ከአረማውያን በእንዲህ ያለ ሥቃይ ላይ የሚታገሥ ማን ነው" አለ። እነዚያ አንበሶችም ወደ ቅዱሱ ቀረብ ብለው ደንግጠው ቆሙ። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ እጁን ዘርግቶ አንገቱን ያዘው በዚያንም ጊዜ ደስ ብሎት ነፍሱን በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ ልመናውንም ፈጸመለት። ለእነዚያ አንበሶችም ሥጋውን ይዳስሡት ዘንድ አልተቻላቸውም የክብር ባለቤት ክርስቶስ ዳግመኛ እስከ ሚመጣ የተጠበቀ ሆነ እንጂ ከዚህም በኋላ በክብር በምስጋና ከከተማ ውጭ ቀበሩት እንደዚህም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመልካም ተጋድሎ ምስክርነቱን ፈጸመ ለምእመናንም ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ገድሉን ጻፉ የበዓሉንም መታሰቢያ አደረጉለት። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ቅፍሮንያ በዚህች ቀን ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች ቅድስት ድንግልና መስተጋድልት ቅፍሮንያ ሰማዕት ሆነች። እርሷም በደናግል ገዳም ቁጥራቸው ሃምሳ ለሆኑ ለደናግሉ እመ ምኔት እኅት ነበረች። የእመ ምኔትዋም ስሟ ኦርያና ነው። ይህችንም ቅድስት በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደገቻት። በትሩፋት ሥራ ተጋዳሊት እስከሆነችም ድረስ አምላካውያት የሆኑ መጻሕፍትን አስተማረቻት። ከዚህም በኋላ ፍጹም ገድልን ጀመረች በየሁለት ቀኑ ትጾም ነበር ብዙ ጸሎታትንም ትጸልይ ነበር። ያቺም እመ ምኔት ሥራዋ ያማረ በሃይማኖቷም የጸናች ነበረች። በበጎ ሥራ ሁሉ እንዲጸኑ ወገኖቿን ታስተምራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ሰዎች ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልኩ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በአዘዘ ጊዜ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ይዘው አሠቃዩአቸው ሰማዕታትም ሆኑ። እሊያ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ከገዳም ወጥተው ሸሽተው ተሠወሩ። እመ ምኔቷ ግን ከዚች ቅድስት ቅፍሮንያ ጋራ ብቻዋን ቀረች። በማግሥቱም የንጉሡ መልክተኞች ወደ ዚያ ገዳም በመጡ ጊዜ እመ ምኔቷን አግኝተው ያዟት ሌሎችንም ደናግል ፈለጓቸው ግን አላገኟቸውም። ቅድስት ቅፍሮንያም በእርሷ ፈንታ እኔን ውሰዱኝ ይቺንም አሮጊት ተውዋት አለቻቸው። እነርሱም ያዟት በብረት ሰንሰለትም አሠሩዋት መኰንኑ ወደአለበትም ከተማ ወሰዱዋት እመ ምኔቷም እያለቀሰች ተከተለቻቸው። ወደ መኰንኑም በአደረሷት ጊዜ ለአማልክት ሠዊ አላት ብዙ ቃል ኪዳንም ገባላት እርስዋ ግን ቃል ኪዳኖቹን አቃለለች ትእዛዙንም አልተቀበለችም እንዲደበድቧትም አዘዘና በበትሮች ደበደቧት። ዳግመኛም ልብሷን ገፍፈው ሥጋዋን ግልጥ እንዲያደርጉ አዘዘ እመ ምኔቷ ኦሪያናም አንተ ከሀዲ ይቺን ታናሽ ብላቴና እንዳጐሳቈልሃት እግዚአብሔር ያጐሳቍልህ ዘንድ አለው ብላ ጮኸች። መኰንኑም እጅግ ተቈጥቶ ይህቺን ቅድስት ቅፍሮንያን አሥረው በመንኰራኵር ውስጥ እንዲያሠቃዩዋት በብረት መጋዝም እንዲሠነጥቋት አዘዘ ሁሉንም አደረጉ ይህንም ሁሉ ፈጸሙባት እርሷም ርዳታን ሽታ ወደ እግዚአብሔር ጮኸች ወዲያውኑ ከሕመሟ ሁሉ ድና ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ሆነች። ከዚህም በኋላ ደግሞ ምላሷንና ሕዋሳቷን ሁሉ ቆረጡ ጥርሶቿንም ሰበሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ሕማም አስነሣት። መኰንኑም እሷን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች።