Amex Den
СтатистикаChristian Views; Life Experiences & Stories; Funny stuff; Book Reviews; … and more
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 16
- Всего постов
- 52
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 38
- 1/48двое суток
- 43
- 1/72трое суток
- 46
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Jemal Abdulaziz አቶ ልዑልሰገድ ኩምሳ አቶ ልዑልሰገድ ኩምሳ በኢትዮጵያ በጋዜጠኝነት እና በተለይም በእንግሊዝኛ ዜና አንባቢነት ታዋቂ እና ትልቅ አሻራ ያሳረፉ አንጋፋ ባለሙያ ናቸው። አቶ ልዑልሰገድ የቋንቋ እና የኮሙኒኬሽን ክህሎታቸውን በትምህርት ካዳበሩ በኋላ ወደ ጋዜጠኝነት ሙያ ተቀላቀሉ። የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው፣ አነባበባቸው (pronunciation) እና የድምፅ አወጣጥ ችሎታቸው የሚስብና በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈ ነበር። አቶ ልዑልሰገድ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ / አሁን ኢቢሲ) እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ በዋናነት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ክፍል ውስጥ ለብዙ ዓመታት አገልግለዋል። ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዜናዎችን፣ አበይት ኩነቶችን እና የክብር እንግዶች ጉብኝቶችን በከፍተኛ ትኩረት እና ሙያዊ ብቃት ያስተላልፉ ነበር። የነበራቸው ግልጽ፣ ማራኪ እና የሚስብ የእንግሊዝኛ ድምፅ በወቅቱ የቴሌቪዥን ተመልካቾች እና የሬዲዮ አዳማጮች ዘንድ የእንግሊዝኛ ዜና ዋና መለያ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አቶ ልዑልሰገድ ለብዙ ታዳጊዎች እና የጋዜጠኝነት ተማሪዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀም እና በዜና አቀራረብ ረገድ ትልቅ አርአያ (role model) ሆነዋል። በጋዜጠኝነት ዘመናቸው ለሙያው የነበራቸው ታማኝነት፣ ታታሪነት እና ስነ-ምግባር በስራ ባልደረቦቻቸው እና በህዝብ ዘንድ ትልቅ ክብርን አትርፎላቸዋል። በአጠቃላይ አቶ ልዑልሰገድ ኩምሳ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ውስጥ ከነበሩት ምርጥ የእንግሊዝኛ ዜና አቀራረብ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ሆነው ሁልጊዜ ይታወሳሉ።
видео или голосовое, без подписи
Tab Amex ምስኪኗ H: እግዚአብሔር ፈቅዶና ወድዶኝ በዚህች አጭር ሕይወቴ ብዙ ሰዎችን ተዋውቄያለሁ። ለቁጥር ባለፈ ከመልካም ከወንዶችም ከሴቶችም ጋር ተቀራርቤያለሁ። በወጣትነቴ በመልካቸው ዐይንን ከሚስቡ፥ በባሕርይ ልብን ከሚያስደነግጡ እጅግ መልካም ጥቂት ልጃገረዶችም ጋር ጣፋጭ ጊዜያትን አሳልፌ አውቃለሁ። እስከ አሁን ድረስ ሴት ልጅን ለመጠቀሚያ ወይም ለሌላ ነገር ሆን ብዬ ስላልበደልኩኝ፣ ጥበቃና ምሕረቱን ያበዛልኝን የእስራኤል አምላክ እጅግ በጣም አመሰግነዋለሁ። ከኮሌጅ ምርቃት በኋላ የመጀመሪያ ሥራ በተቀጠርኩት ከጥቂት (ምናልባትም 2-3) ዓመታት በኋላ፣ አንዲት ውብ ወጣት ለዲፓርትመታችን ሴክሬታሪነት ተቀጠረች። ለጥቂት ጊዜም ጋር አብሬያት እሠራ ነበር። “H” ማለት ምንም የማይጎድላት ሴት የምትባል አይነት ነበረች። እያጋነንኩኝ አይደለም። ቡጉር ጣል ጣል ያደረገባት ጠይም ፊቷ፥ አጠር ያለ ቁመቷና እጅግ የሚያምረው ብዙና ረጅም ጠጉሯ! ዋው ያስብላል። ጠባይና ትሕትናዋ በጣም ልዩ ነው። ከአፏ ማር የሚንጠባጠብ የምትባል አይነት በጣም የምታምር ውብ ልጅ ነበረች። ከተራ ወሬዎችና በጣም ጥቂት ጊዜ አብሮ ሻይ ቡና ከማለት ያለፈ ነገር አልነበረንም። የትውልድና የጊዜውን ግለ ታሪኳን በጥቂቱ ነግራኝ ነበር። H. እኔ ከመውጣቴ በፊት ወደ አሜሪካን አገር ሄደች። ከአንድ ወይ ሁለት ዓመታት በኋላ እኔም ከአገር ወጣሁ። ከወደ ሁለት ዓመታት በኋላ: ——— አገር ቤት ተመለስኩኝ። ከጥቂት ቀናት በኋላም የድሮ መሥሪያ ቤቴ ብቅ አልኩኝ። ከዚያም ከውቧ H. ጋር አብራ ትሠራ የነበረችውን M. አገኘኋት። “M. ስለ H. ትሰሚያሽ? ደኅና ናት?” ብዬ ጠየቅኋት። M. እጅግ አሳዛኝ ነገርን ነገረችኝ። H. የሄደችበት አገር በወሊድ እንደሞተች አረዳችኝ! — “H.” ምስኪኗ ነፍስ !
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
TABLETALK (September 2026) ______ #መሪ_ርዕስ: “Assurance of Salvation” - (፩- Assurance of Salvation in Scripture and the Spirit’s Witness (p.4) - (፪ The Ultimate Ground of Assurance (p.9) - (፫- The Fruit of Faith and the Evidence of Grace (p.12) - (፬- Assurance Distortions (p.17) - (፭- Why Christians Struggle with Assurance (p.23) - (፮- Growing in Assurance Through the Means of Grace (26) ___ ቀጣይ እትም: #እምነትና_ሥራ
видео или голосовое, без подписи
Jemal Abdulaziz የሒሳብ ሊቅ ዶ/ር ሙላቱ ለማ ዶ/ር ሙላቱ ለማ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ ትምህርት ያጠናቀቁ ሲሆን፣ የዶክትሬት (Ph.D.) ዲግሪያቸውን ደግሞ በአሜሪካ ከሚገኘው 'Kent State University' አግኝተዋል። ዶ/ር ሙላቱ በአሜሪካ ጆርጂያ በሚገኘው 'Savannah State University' በፕሮፌሰርነት እና በምርምር ዘርፍ ለበርካታ አስርት ዓመታት አገልግለዋል/እያገለገሉ ይገኛሉ። የሒሳብ ቀመሮች እና ግኝቶች (Mathematical Contributions)፤ ዶ/ር ሙላቱ በሒሳብ ምርምር ዘርፍ በርካታ ሳይንሳዊ ጽሁፎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ በስማቸው የሚጠሩ አዳዲስ የሒሳብ ቀመሮችን እና ንድፈ-ሃሳቦችን (Mathematical Patterns/Formulas) አፍልቀዋል። በተለይም በ'Number Theory' እና 'Fibonacci Numbers' ዙሪያ ባደረጓቸው ጥናቶች ይታወቃሉ። የሽልማትና የእውቅና ማዕረጎች፤ በወጣቶች ትምህርት እና በሒሳብ ማሳደግ ላይ ባሳዩት ላቀ መሪነት እና አደራጅነት በርካታ ታዋቂ ሽልማቶችን አግኝተዋል፦ • የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሽልማት (Presidential Award for Excellence in Science, Mathematics and Engineering Mentoring) – በሳይንስ፣ ሒሳብ እና ምህንድስና ዘርፍ ወጣቶችን በማብቃትና በማስተማር ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከ'ኋይት ሐውስ' የሚሰጠውን ታላቅ ሽልማት ተጎናጽፈዋል። • ማስታወሻ፦ ዶ/ር ሙላቱ እ.ኤ.አ በ2011 በስማቸው የተሰየመ "የሙላቱ ቁጥር" የተሰኘ የሒሳብ ቀመር ለዓለም አስተዋውቀዋል።
Jemal Abdulaziz «ኢትዮጵያ አገርህ በእውነት ትልቅ ሳትሆንና ወንድሞችህም ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሳይደላቸው አንተ ብቻህን የምታገኘው ደስታ ገንዘብና ተድላ በሕልም እንደተገኘ ወርቅ መና ባዶ ሆኖ የሚቀር መሆኑን ልብህ አይዘንጋው።» ∞ ∞ «ፀሐይ ጥዋት ጥዋት የምትወጣው የሱን ድምጥ ሰምታ እየመሰለው በልቡ ሲኮራ የሚኖር እንዳንድ አውራ ዶሮ አለ ይባላል። በሕዝብም መካከል እንደዚሁ ሊሰሩት የማይችሉትን ትልቅ ሥራ የሰሩ እየመሰላቸው በከንቱ ሲመኩ የሚታዩ ሰዎች ይገኛሉ።»
በዮናስ ቀንቻለሁ፤ ግን አድንቄዋለሁም ________ https://www.bbc.com/amharic/articles/czrj14x5j08o
የገዛችው እሙዬ ያመጡት ኤንዲ/ተዜ ይመሰገናሉ። በብዙ ተባረኩልኝ 🙏❤️
видео или голосовое, без подписи
Jemal Abdulaziz o͏d͏t͏e͏o͏S͏s͏r͏n͏p͏c͏l͏a͏9͏9͏g͏m͏c͏0͏1͏3͏4͏t͏1͏a͏6͏3͏c͏c͏5͏h͏i͏0͏4͏8͏c͏t͏4͏3͏i͏5͏5͏i͏2͏4͏2͏6͏m͏0͏i͏0͏5͏c͏0͏1͏9͏6͏9͏i͏c͏ ፕሮፌሰር አቻምየለህ ደበላ ዶ/ር አቻምየለህ የተወለዱት በ1949 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት እና በናይጄሪያ ከሚገኘው አህማዱ ቤሎ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። በበለፀገው ትምህርታቸው ከሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ በሙዚየም ጥናትና የኪነ-ጥበብ ታሪክ (MA) እንዲሁም ከሜሪላንድ ኢንስትቲዩት ኮሌጅ ኦፍ አርት በሥዕል ሙያ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን (MFA) አግኝተዋል። በተጨማሪም በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በዲጂታል አርትስና ኮምፒውተር ግራፊክስ የዶክትሬት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በአዲስ አበባ ሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት በታዋቂዎቹ አርቲስቶች አለፈለገ ሰላም፣ ገብረክርስቶስ ደስታ እና እስክንድር በጎሲያን ስር ተምረዋል። ፕሮፌሰር አቻ በኮምፒውተርና ዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥነ-ጥበብን በመፍጠር ረገድ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት የአፍሪካ አርቲስቶች አንዱ ናቸው። በሥራዎቻቸው ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥበብን፣ የባህል ምልክቶችን፣ የቀለም አጠቃቀምን እና አፍሪካዊ-አሜሪካዊ የታሪክ ትረካዎችን ከዘመናዊ ዲጂታል ቴክኒኮች ጋር አዋህደው ያቀርባሉ። ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ባዘጋጇቸው ንድፎች (Designs) የ11ኛው እና 12ኛው ክፍለ ዘመን የቤተክርስቲያን ሕንፃዎችን በማስተዋወቅ በዩኔስኮ (UNESCO) እና ዩኒሴፍ (UNICEF) እውቅና አግኝተዋል። ፕሮፌሰር አቻምየለህ በሰሜን ካሮላይና ሴንትራል ዩኒቨርሲቲ (NCCU) ከ30 ዓመታት በላይ በፕሮፌሰርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን
ወይ አካውንቲንግ! (ፌብሩዋሪ አጋማሽ ላይ የተላከልኝ የ$1.00 ቼክ ነው። ገርሞኝ አስቀምጬው ነበር ማለት ነው)
#ፍቅር! ከዓመታት በፊት አንድ ፓስተር፣ ኢየሱስ መስቀል ላይ ሆኖ “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ባለበት ዙሪያ ሲያስተምር፤ አብ ዝም እንዳለ ተናገረ። አያይዞም፣ (am paraphrasing) ልጁ መስቀል ላይ መሞቱ የግድ መሆኑን ካስታወቀ በኋላ፤ አብ፣ “አለበለዚያ እኔና አንተ አልኖርናትም! ምርጫ የለም!” በማለት ጨመረበት። “ወጣት” ክርስቲያን ብሆንም፣ ይህ አባባል ይኸው እስከዛሬ እንደቆረቆረቆረኝ አለ። እግዚአብሔር ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት አሳልፎ የሰጠው ለእኛ ብሎ እንጂ፣ ለራሱ ወይም ለልጁ “መኖር” ብሎ አይደለም። በፍጹም! የሥነ መለኮት ሊቃውንት፣ እግዚአብሔርን “Self-Existent” እና “Self-Sufficient” ነው በሚል ይገልጡታል። እንዲህ የሆነው እርሱና እርሱ ብቻ ነው። ይህ ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጥ የሚያስተምሩት ነገር ነው። እግዚአብሔር ልጁን ለሞት አሳልፎ የሰጠው፣ መድኃኒትና ድነት እንዲሆነን ብሎ ነው። የእኛ መኖር ወይም አለመኖር ለእግዚአብሔር የሚጨምረው የሚቀንሰውም ነገር የለም። የፈጠረን እኛ ፈልገን ሳይሆን በራሱ ፈቃድና ጥበብ ነው። በመልኩና በአምሳሉ ልዩ አድርጎ ለፈጠረን ከጸጋውና ከሕይወቱ ሊያካፍለን ወደደ። ነገር ግን፣ በእሱና እኛ በመኻል ኃጢአት የሚባል ነገር ገባና ለያየን። እርሱ ቅዱስ ስለሆነ፥ እኛ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ከኃጢአታችን መንጻት አለብን። ራሳችንን ማንጻት ስለማንችል፤ እግዚአብሔር ራሱ የድነት መፍትሔን አዘጋጀ። በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በኩል በነጻ ሰጠን። ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል የሞተው የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም ነው። ነፍሱን አሳልፎ የሰጠውም ወዶና በፈቃዱ ነው። እግዚአብሔር አባት ልጁን ወደ ዓለም የላከው ለእኛ ካለው ትልቅ ፍቅር የተነሣ እንጂ፤ እርሱ አንዳች ጎሎበት አይደለም።
#መዝሙር 62 ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ________ መዝሙር 62:1 ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና። 2 እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ እጅግም አልታወክም። 3 እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ፡ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ። 4 ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ ሐሰትንም ይወድዳሉ፤ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ። 5 ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና። 6 እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው፤ አልታወክም። 7 መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው። 8 የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው። 9 ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፤ በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው። 10 ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ። 11 እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥ 12 አቤቱ፥ ምሕረትም ያንተ ነው፤ አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ፍዳውን ትሰጣለህና።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Supersensitiveness~ ወገኖች፣ማካበድ በጣም በዝቷል
https://youtu.be/YtNx9i-fN3U?is=pAhvMC6Yp_2Jpfeo