አ/ም ሰንበት ት/ቤት ትምህርት ክፍል official channel
Статистикаይህ በቦሌ ሰ/ም/ፀ/ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/አርሴማ ቤተ ክርስቲያን አንቀፀ ምስራቅ ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን እንዲሁም ወቅታዊ የቤተ-ክርስቲያን መረጃዎችን የምንለቅበት የቴሌግራም ገፃችን ነው።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 137
- 1/48двое суток
- 157
- 1/72трое суток
- 169
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለእግዝትነ ማርያም በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች። የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄምና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም:- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ፤ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች። እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ሃናም አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፤ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም "7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ" አየሁ አላት፤ ሃናም እኔም አየሁ አለችው ምን አየሽ ቢላት "ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ" አለች። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡ እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡፡ ምልጃዋ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን፡፡
ነገረ ሰብእ በዲ/ን አቤል ካሳሁን 📅 ነሐሴ 10 | 🕒 3:00 ሰዓት (ጠዋት) 📍 ቦታ፦ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ "ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!"
ማሳሰቢያ ፦የነገ የቅዳሴ ተረኞች ልብሰ ስብሐት የመልበስ እና በሰዓቱ የመገኘት ግዴታ አለብን።
ማሳሰቢያ ፦የነገ የቅዳሴ ተረኞች ልብሰ ስብሐት የመልበስ እና በሰዓቱ የመገኘት ግዴታ አለብን።
ለነገው ሥልጠና ማሳሰቢያ! ነገ ነሐሴ 3 የእምነታችንን መሠረት የምንረዳበት የንፅፅራዊ ነገረ መለኮት (Comparative Theology) ሥልጠና ተዘጋጅቶአል። አደራ፦ ማንም ቀሪ እንዳይኖር! ሁላችንም ተቀሳቅሰን እንገኝ፤ ሌሎችንም መጋበዝ አይርሱ። በእግዚአብሔር ስም ተጠርታችኋል!
ለሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት ዛሬ ቅዳሜና እሁድ ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።
видео или голосовое, без подписи
1.የንጽጽራዊ ነገረ መለኮት ትምህርት ዋና ጥቅሞች ምንድን ናቸው? የራስን እምነት ጠንቅቆ ለማወቅ የሌላውን እምነት ማወቅ ለምን አስፈለገ? 2.የሌላ እምነት ተከታዮችን አስተምህሮ ስናነጻጽር ልናደርጋቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች። እነዚህ ጥንቃቄዎች በውይይት ወቅት ለምን ወሳኝ ይሆናሉ? 3.በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና በይሁዲነት (Judaism) መካከል መሠረታዊ ልዩነት ከሚፈጥሩ ነጥቦች አንዱ "ስለ መሢሑ" ያለው እይታ ነው። ይህን ልዩነት በዝርዝር ግለጹ። 4.ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በሚደረግ የነገረ መለኮት ውይይት (ተዋሥኦ) ላይ "የጋራ መከራከሪያ መጽሐፍ የለንም" የሚባለው ለምንድን ነው? 5.የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከካቶሊክ እና ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ (Eastern Orthodox) አብያተ ክርስቲያናት ጋር በኬልቄዶን ጉባኤ እና በክርስቶስ ባሕርይ ዙሪያ ያላት መሠረታዊ ልዩነት ምንድን ነው? 6.በፕሮቴስታንት እምነት እና በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መካከል "ለመጽደቅ" የሚያስፈልጉ ነገሮች ላይ ያለው ልዩነት እንዴት ይገለጻል? 7.የፕሮቴስታንት እምነት 66 መጻሕፍትን ብቻ ሲቀበል፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ግን ተጨማሪ መጻሕፍትን (አዋልድ/ዲዩትሮካኖኒካል) ትቀበላለች። ይህ በውይይት ወቅት ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ፍልሰታ ምን ማለት ነው? ፍልሰታ ማለት ‹ፈለሰ – ተሰደደ› ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡›› 'ፍልሰታ ለማርያም' የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ሐዋርያት ኹለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡ ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ። ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐሥራት አገር በመኾኗ እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው፤፡፡ ይቆየን ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን
видео или голосовое, без подписи
📢 ልዩ የሥልጠና ጥሪ! ሰሚት ምሥራቅ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስና ቅ/አርሴማ ቤ/ክ አንቀጸ ምሥራቅ ሰንበት ትምህርት ቤት 📋 ርዕስ፦ ንፅፅራዊ ነገረ መለኮት 🎙 አሰልጣኝ፦ መምህር ወንዶሰን "ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ" — (1ኛ ጴጥ 3፡15) 📅 ቀን፦ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም 🕒 ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ 📍 ቦታ፦ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ 👥 የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት፣ የደብሩ ምዕመናን እንዲሁም መንፈሳዊ ዕውቀቱን ማሳደግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በክብር ተጋብዟል። እንዳያመልጥዎት!
እንዴት አመሻችሁ ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የ4ኛ ,8ኛ ,10ኛ ክፍል የሀገረ ስብከት ተፈታኞች እንዲሁም ወላጆች መልእክት እንደተናገሩት ለልጆቹ የሀገረ ስብከቱ ማጠቃለያ ፈተና በነገው እለት ይሰጣል። ጠዋት 1:00-1:30 ሰዓት ሁላችሁም ተፈታኞች ሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ። ሁሉም ተማሪዎች በአንድ ላይ ነው ወደ ፈተና ጣቢያው የሚሄዱት ወላጆች ልጆች እንዳያረፍዱ በጊዜ ላኳቸው። ማሳሰቢያ ‼️‼️‼️ ሁሉም ተማሪዎች እርሳስ እና ላጲስ ይዛችሁ ተገኙ መልካም ምሽት🙏🙏🙏🙏
"ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።" ትን.ዮና. 3÷8 🕯ሳምንታዊው የአርብ ጸሎት🕯 👉 ውዳሴ ማርያም 👉 መሐረነ አብ 👉 መዝሙረ ዳዊት 👉ስንክሳር 🗓 ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ⏰ ከቀኑ 12:00ሰዓት ጀምሮ 💒 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ኑ በህብረት ስለ ሀገራችንና ስለ ቤተክርስቲያናችን ሰላም እና አንድነት ወደ ፈጣሪያችን በጋራ እንጸልይ‼ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አንዱ እና ዋነኛው መረሐ ግብር የጸሎት ፕሮግራም ስለሆነ ማንም እንዳይቀር አባላት እባካችሁ አትቅሩ አታርፍዱ በጊዜ ተገኝተን በጊዜ ወደየቤታችን እንድንመለስ
ሰላም ውድ የአንቀጸ ምስራቅ ሰንበት ት/ቤት አባላት እንዴት አመሻችሁ? ይህን መልዕክት በትኩረት እንድትመለከቱት ስንል በጥብቅ እናሳስባለን ሌሎችም የምታዩትም ወንድም እህቶች ለጓደኞቻችሁ አጋሩላቸው። የ8ኛ እና የ10ኛ ክፍል በመማር ያሳለፋችሁ ተፈታኞች ተማሪዎች 👉 የፈተና ቦታ እና ሰዓት፦ ሐምሌ 26 ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ''ሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ '' መገኘት ይኖርባችኋል። 👉ቅዳሜ 11 ሰዓት ላይ ሁላችሁም ተገኝታችሁ የሚሰጠውን መልዕክት(orientation) መከታተል ይኖርባችኋል። 👉የመፈተኛም ኮድም ቅዳሜ ስለሚሰጥ በጊዜ ተገኙ። 👉የመፈተኛው ቀን ፈተናው በማጥቆር ስለሆነ ላጲስ እና እርሳስ ይዛችሁ እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን። ‼️‼️‼️‼️‼️ ማሳሰቢያ፡ መልዕክቱንም እንድታነቡ እና ቴሌግራም መጠቀም ለማይችሉ ወንድም እህቶቻችሁ እየደወላችሁ እንድታሳውቁ ስንል እንጠይቃለን።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи