A+ Tutorials Free
Статистикаይሄ ቻናል ፍሬሽ ማን ተማሪዎች ሁሉንም ትምህርቶች A+ እንዲያመጡ ለማገዝ ታስቦ የተከፈተ ነው ✨ ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ @Aplusowner በኩል ማስተላለፍ ይችላሉ ይሄን ዕድል ሌሎች ቤተሰቦች ሼር በማድረግ የትምህርቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ተባበሩን🙏
- Последний пост
- 24 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 70
- 1/48двое суток
- 80
- 1/72трое суток
- 86
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://t.me/SkillEarn1_bot/skillearn1?startapp=ref_3AF424AC
#geographic Geographic chapter 1 👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1962 #logic Logic chapter 1 👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1973 #psychology Psychology chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1951 #economic Economic chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1989 #inclusiveness Inclusiveness chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/2007 #Global_Trend Global Trend chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/2036 📌ቀጣይ ምን ትምህርት ይጨመር❓ ✅ለFresh_Man ተማሪዎች ሼር አድርጉላቸው‼️ Join now 👇👇👇 @aplusfree @aplusfree @aplusfree
GPA 4⃣ ላለማምጣት ሰበብ መደርደር ቀረ ከ Aplus VIP Class ጋር ይህም ይቻላል። 🔝 ይህን የመሰለ ጥርት ያለ Material በአማርኛም በ እንግሊዘኛም ለ ሁሉም Course የተዘጋጀውን የ Aplus VIP Class ማጥኛ Note አንብቦ Exam አለመድፈን አይቻልም💯 📌በእርግጠኝነት እንደሚጠቅማቹ አንጠራጠርም ለምን ከተባለ እዛው በ English የምታነቡት ሀሳብ ካልገባቹ በቋንቋቹ ቀለል ባለ መልኩ ስለተዘጋጀ ይረዳቹሀል። 🖥ይህ ሁሉ ⭐️ፅድት ያሉ Notes ⭐️ማብራርያ Videos ⭐️በየምእራፉ መጨረሻ ጥያቄዎች ⭐️ ሳምንታዊ Voice Chat ምን አለፋቹ ሁሉንም በአንድ ላይ በ Aplus VIP Class በ 150 ብር ብቻ ታገኛላቹ። 👀ታዲያ ምን እየጠበቃቹ ነው ከወዲሁ ዝግጁ እንድትሆኑ በማሰብ ሰኞ ዝግጅት ይጀመራል። ⚠️እስካሁን ካልተመዘገባቹ አሁንም ለመቀላቀል እድሉ አላቹ ✔️ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎችክ ከታች ባለው username ብቻ ይመዝገቡ 👇👇 @aplusowner @aplusowner 🙀 መልካም የፍሬሽማን ጉዞ ይሁንላችሁ🥰 ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 JOIN: @aplusfree ✅ JOIN: @aplusfree ✅
👨🏫👩🏫 ለ 2018 የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች። ⏲ የፍሬሽማን ካሪኩለም በ 2013 ሲመሰረት ፥ አብሮ ተመስርቷል። የፍሬሽማን ኮርስን ለ ተከታታይ አራት አመታት የማስተማር ልምድ ያካበተ ቀዳሚው ቲቶርያል ነው - A+ Tutorial Class❗️ 👨🏫👩🏫 በርካታ የ 2018 ዓም የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመመዝገብ ላይ ሲሆኑ ፥ ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ የሆኑ የፍሬሽማን ቲቶርያሎችን በመማር ላይ ይገኛሉ። 📚 በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሰረት ሁሉንም የፍሽማን ኮርስ ለሁሉም የፍሬሽማን ተማሪዎች ለመረዳች ምቹ ና ጊዜን በሚቆጥብ መልኩ በአማርኛ እንግሊዝኛ በተብራራ ኖት ፤ በቪዲዮ ፤ በቮይስ ና በ Diagram ትምህርቶቹ ይቀርባሉ። 📚ለ Mid exam ና Final exam ፈተናችሁ እንዲረዳችሁ ታሳቢ በማድረግ ከቲቶርያሎቹ በተጨማሪ ከግቢ ፈተናዎች ጋ በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው በአንድ ኮርስ በርካታ ጥያቄዎችን በእያንዳንዱ Topic ና በእያንዳንዱ ምዕራፍ ከበቂ ና ግልፅ ማብራሪያዎች ጋ ይቀርባሉ ፤ በእያንዳንዱ ቻፕተር worked solution ተዘጋጅቶ ይቀርባል ፥ ያለፉ አመታት የግቢዎች mid exam ና final exam ተብራርተው ይሰራሉ። 👨🏫👩🏫 ይመዝገቡ ወደሚፈልጉት ዲፓርትመንት ለመግባት ትግልዎን ያቃሉ። 💵 ክፍያው 150 👉100 ብር ብቻ 🛑ማሳሰቢያ ቅናሹ ለ3 ቀን ብቻ ነው የሚቆየው ለመመዝገብ ከታች ባለው username ያናግሩን 👇 @Aplusowner @Aplusowner ©A+ Tutorial Class.
🎓 የግቢ ውስጥ ፈተናዎች 1.ፋይናንስ:- ያዩትን ሁሉ መግዛት፤የጓደኛ ጫና አላስፈላጊ፣መገባበዞች 2.ጊዜ :-ለClass ቀድሞ መሄድ፤ከClass በኋላ ተሰባስቦ ገደብ የሌለው ወሬ፣ሁሉ ነገር የሚጠቅም መስሎ መታየት፤ ምንጩ ባልታወቀ መረጃ መሸበር፤የማይተገበር የጥናት መርሀ ግብር፡፡ 3.ሌባ:- የልብስ ፤የፒሲ፣ የስልክ.. 4.ምግብ፦ የግቢው ምግብ ከቤት አንጻር፤ የመመገቢያ ሰዓት፤ 5.መኖሪያ :-ለብቻ መኖር የለመደ ሰው የሰው ጋጋት ሲበዛ፤ሀይማኖታዊ ሢዓቶችን ለማከናወን መቸገር፤ የእንቅልፍ መርሀ ግብር ከዶርም አጋሮች ጋር አለመጣጣም፤የጸባይ ልዩነት፡ሻወር እና ልብስ ፤በጧት መነሳት፤ 6.ጓደኝነት:-የሚሳያስቴሽን😁፤የሚያነቃቃ፤ የሚያደናቅፍ፤ የሚመክር፤ ቡድን መስርቶ መንቀሳቀስ፤ሱሰኞች 7.የትምህርቱ ስርዓት:-ሁሉን ለማወቅ መጣር፤አላስፈላጊ የሪፈረንስ ጋጋታ ፤ በስላይድ ብዛት እና በ አስተማሪዎች መደናገጥ፤ ኮሚኒኬሽን ጋፕ፤ፍርሀት 8.የGrade System :- የተሳሳተ ፈተና፤ የመምህራን ከተለያየ ቦታ መምጣት፤ 9.ዲፓርትመንት መረጣ:- በጓደኛ ፤በቤተሰብ ጫና ላይ መመስረት፤ ለመላመድ ጊዜ መውሰድ፤ 10.Tension:- የmid እና የfinal ሰሞን 🌀መፍትሄ፡ ቶሎ adapt ማድረግ ፤ ከተሻሉ ሲኔሮች ጋር መላመድ፤ Prioritization ፤Schedule አወጣጥ፤ቀደም ብሎ ማጥናት ፤ራስን ማዳመጥ፤ራስን መቆጣጠር:: በተረፈ በቻልነው አቅም እኛም እናግዛቿለን😊 JOIN US🔽 @APLUSFREE @APLUSFREE
🚨 ሰበር ዜና በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል። በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል። 🚨 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስትሩ አስታውቋል። በነዚህ ሽርፍራፊ ነጥቦች ቀርቶባችሁ የነበረ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። 😀 Like👍 Share 📱 𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 @aplusfree ⭐️ @aplusfree ⭐️
🗨️ ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አብዛኛው ተማሪ የማይነግራቹን ወሳኝ ምክር እንንገራቹ። በተለይ ዘንድሮ ወደ University የምትገቡ የ Freshman Course የምትወስዱ ልጆች ይህን በአስተውሎት አንብቡት። 🚸አብዛኛው ተማሪ የጊቢን ህይወት Life መቅጫ መዝናኛ ነው ፈታ እንበል እያለ ጊዜያቹን ገንዘባቹን ያላቹን ነገር በሙሉ ይወስድባቹሀል። አስተዉሉ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ የ Freshman Season ወሳኝ ነው። ለምን መሰላቹ ✅ የ Freshman ውጤታቹ የምትፈልጉትን Department የማግኘት እድላቹን ይወስናል። ✅በ University ቆይታቹ Freshman ላይ የምታስመዘግቡት ውጤት እስከመጨረሻው ድረስ Effect አለው። ይህን በደንብ እንዴት እንደሆነ ከዚህ ቡሀላ የምናስረዳቹ ይሆናል። ✅የነገ የስራ አለም ህይወታቹ ራዕያቹ በሙሉ የሚመሰረተው መጀመርያ በምትሄዱት መንገድ በመሆኑ። ⚠️ብቻ ምን አለፋቹ Freshman ላይ ከቀለዳቹ አለቀ ሙሉ የ University ቆይታቹ እንደሚበላሽ 101% እርግጠኛ ሁኑ። በአንፃሩ Freshman ላይ በጥሩ ሁኔታ Perform ካደረጋቹ እና ጥሩ ውጤት ካመጣቹ ህልማቹ የመሳካት እድሉ ሰፊ እና በቀጣይ በምትገቡት department ዉስጥ ጫናዎችን ይቀንስላቿል። 🎁እንደ Campus Material Team ደግሞ በቀደሙት አመታቶች እንዳደረግነው እናንተን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለመርዳት ዝግጁ ነን። ከዚህ በፊት ከኛ ጋር የነበሩ ልጆች ህልማቸው እውን ሆኖ አሁን የ 3ተኛ 4ተኛ አመት ተማሪዎች ናቸው። ✅በመሆኑም በዚህም አመት Support ማድረጋችን እንዲሁም እገዛችን ስለማያቆም እናንተን ለማገዝ ብቻ ታስቦ የተከፈተውን ለ Campus ተማሪዎች ብቻ የታሰበውን ቻናል ከታች Join በማድረግ እንዲሁም ለሌሎች በማጋራት ከኛ ጋር ይሁኑ። 𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 @aplusfree @aplusfree
☕️ ማጥናት ጀምር! ➡️ከፈተና በኋላ እንዳይቆጭህ ከፈለክ አሁን በደምብ አጥና፣ ጥያቄ ስራ። እስካሁን አልጀመርኩም ካልክ አሁን ጀምር! የምትችለውን ሁሉ አድርግ🙂 🖱አለበለዚያ Mid and Final Exam ቶሎ ይደርሳል፤ ውጤት ሲመጣ ታዝናለህ! በትምህርት እስከቀጠልክ ድረስ የወደፊት ህይወትህ የሚወሰነው በ Freshman year ነው፤ ያንተን ስኬት የሚጠብቁ ጥግ ድረስ የሚወዱህ አባት፣ እናት ወይ ቤተሰቦች አሉ! ብቻህን አይደለህም አሁኑኑ ተነስና ማጥናት ጀምር😇 ✨መልካም እለተ ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏 🌐 @aplusfree🔂
#geographic Geographic chapter 1 👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1962 #logic Logic chapter 1 👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1973 #psychology Psychology chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1951 #economic Economic chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/1989 #inclusiveness Inclusiveness chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/2007 #Global_Trend Global Trend chapter 1 👇👇👇👇 https://t.me/aplusfree/2036 📌ቀጣይ ምን ትምህርት ይጨመር❓ ✅ለFresh_Man ተማሪዎች ሼር አድርጉላቸው‼️ Join now 👇👇👇 @aplusfree @aplusfree @aplusfree
A+ Tutorials Free pinned Deleted message
🙌አያችሁ ኣ Constructvism " በአለም አቀፍ ደረጃ ግለሰቦች ከ ግለሰቦች የሚያደርጉት አለምአቀፋዊ ግንኙነቶች ትልቅ እሴት ና ጥቅም አላቸው ብለው ያምናሉ። አበበ ከ ዴቪስ ጋር ፤ ጆርዲ ከ ኦዶንካራ ጋር ወዘተ የሚያደርጉትን ግንኙነት Constructvism ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። 👨💼 Alexander Wendt ✓ described the relationship between agents (individuals) and structures (such as the state) ✓ His famous phrase “anarchy is what states make of it”.(ያዙት ለፈተና) 📚 አሌክሳንደር Wendt ✓ በወኪሎች (ግለሰቦች) መካከል ያለውን ግንኙነት ገልጿል። እንዲሁም በመዋቅሮች (እንደ መንግስት ያሉ) መካከል ያለውን ግንኙነት ገልጿል። የ Alexander Wendt ዝነኛ አባባል👇 "ስርአት አልበኝነትን የሚፈጥሩት መንግስታት ናቸው" 📚 the core of constructivism, is that the essence of international relations exists in the interactions between people. ❖After all, states do not interact; it is agents of those states, such as politicians and diplomats, who interact. 🎯 የ Constructivism ዋና አስተሳሰብ👇 " የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ይዘት በሰዎች መካከል ባለው ግንኙነት ውስጥ ነው።" ይላል። በሌላ አባባል👇 😁 ሀገራት አለም አቀፍ ግንኙነት አያደርጉም; የሚገናኙት እንደ ፖለቲከኞች እና ዲፕሎማቶች ያሉ የነዚያ ሀገራት ወኪሎች ናቸው። Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 🙄ገብቷችሗል ኣ። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋ ግንኙነት ስታደርግ ፤ ግንኙነት የሚያደርጉት ኢትዮጵያን ና ቻይና ን ወክለው ፖለቲከኞች ና ዲፕሎማቶች ናቸው ፤ እነዚህ ፖለቲከኞች ና ዲፕሎማቶች ደግሞ ሰው ናቸው። 😁ተራራው ወንዙ ሸለቆው ግምቡ ወዘተ ግንኙነት አያደርጉም በሌላ አባባል ሀገራት ግንኙነት አያደርጉም ነገር ግን ሀገራቱን የሚውክሉ ባለስልጣናት ና አምባሳደሮች ናቸው ግንኙነት የሚያደርጉት። ስለዚህ እንደ Constructivism አስተሳሰብ አለም አቀፍ ግንኙነት የሚካሔደው በሀገራት(states) መካከል ሳይሆን በሰዎች(people) መካከል ነው። 📚 International anarchy could even be replaced with a different system if a critical mass of other individuals (and by proxy the states they represent) accepted the idea. 🎯 እንደ Constructivism ገለፃ ፤ ሌሎች በርካታ ግለሰቦች (እና በግንኙነቱ ሀገራቱን የሚወክሉት ግለሰቦች) ሀሳቡን ከተቀበሉ ዓለም አቀፍ ሥርዓት አልበኝነት በሌላ ሥርዓት ሊተካ ይችላል። 📚 International Relations is, then, a never-ending journey of change chronicling the accumulation of the accepted norms of the past and the emerging norms of the future. As such, constructivists seek to study this process. 🎯 ዓለም አቀፍ ግንኙነት እንግዲህ ያለፈው ዘመን ተቀባይነት ያላቸው ደንቦችና እየወጡ ያሉትን የወደፊቱን መመዘኛዎች መከማቸትን የሚዘግብ ማለቂያ የሌለው የለውጥ ጉዞ ሒደት ነው። Constructivism ምም ይህንን ሂደት ለማጥናት ይፈልጋሉ። 🙌ስለ Constructivism ይህን ካልን ይበቃናል። Critical Theories ን እናንተ አንብቡት። © A+ Tutorial Class.
📌 Marxism ትኩረት የሚያደርገው የ Capitalism ስርአት በአለም አቀፍ ግንኙነት ደረጃ ፣ ድሀ ሀገራት በ ሀብታም ሀገራት ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋል ፣ በዚህም ምክንያት ሀብታም ሀገራት የድሀ ሀገራትን የተፈጥሮ ሀብት ና የሰው ሀብት እንዲበዘብዙ(exploitation) ያደርጋል ሲል ይሞግታል ፤ እንዲሁም Marxism በአለም አቀፍ የስራ ክፍፍል ላይ ያተኮረ ሲሆን ጥገኝነት ፤ ብዝበዛ ና ኢ - ፍትሐዊ የስራ ክፍፍል አብዛኛው የአለም ህዝብ ወደ ድህነት ጫፍ እንዲሸጋገር ያደርገዋል ሲል Karl Marx ይሞግታል። 😍😍 እንደኔ Marxism የተመቼው እስኪ🙌... Capitalism ግን😏😏 ተመልከቱ የ Capitalism ን ግፍ👇 📌ለምሳሌ አንዲት ወጣት ልጃገረድ ሴትን እንመልከት ፤ ይቺ ወጣት ልጃገረድ አፍላ ተማሪ ናት ስራ የላትም አባቷ ሙቷል እናቷ በሽተኛ ናት። ይቺ ልጃ ገረድ ሴት ሁለት ታንሽ ወንድም ና አንድ እህት አላት። ቤተሰቦቿ የዕለት ጉርስ ተቸግረዋል። ይህን ድህነቷን ያዩ ሀብታም ሰዎች ብር እየሰጡ ልጃገረዷን ሴት ስጋዊ መሻታቸውን ይፈፅሙባታል፤ በብራቸው ይበዘብዟታል። 😏ተመልከቱ ሀብታም ሀገራትም በኢኮኖሚ የበላይነት ብድር እርዳታ በመስጠት ድሀ ሀገራትን ልክ እንደ ልጃገረዷ ሴት ይበዘብዛሉ❗️። የሀገራችን ባህል አልተቀየረምን❓እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ ፤ ስርአት ያለው ትውልድ እያፈራን ነውን❓Capitalism ን ከ 666 አስተሳሰብ ለይቼ አላየውም🙌ይህ የእኔ የዳኒ ምልከታ ነው። ለማንኛውም👇 📚 As many in this tradition argued, most states were not free they were subjugated by the political, ideological and social consequences of economic forces. Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 🎯እንደ Marxism ገለፃ ፣ አብዛኞቹ የአለም ሀገራት(ድሆቹ) ነፃ አልነበሩም፣ በኢኮኖሚ የበታችነት ምክንያት የ ሀብታም ሀገራትን የ ፖለቲካዊ፣ የ ርዕዮተ ዓለም እና የ ማኅበራዊ አስተሳሰብ ውጤቶችን በእጅ አዙር ለመቀበል ተገደዱ ፤ በአጭሩ ባርነት ማለት ነው። 🤔 የአለም ሀገራት ለምን አንዳንዶቹ የናጠጡ ሀብታም ሆኑ❓ሌሎቹስ ለምን ድሀ ጨርቃም ሆኑ❓እንደ Marxism አስተሳሰብ መልሱ ይኸው👇 📚 The basis of such manifest inequality was the capitalist structure of the international system which accrued benefits to some while causing, through unequal exchange relations, the impoverishment of the vast majority of others. 🎯 ለእንዲህ ዓይነቱ አንፀባራቂ ኢ-እኩልነት መሰረቱ ለአንዳንዶች ጥቅም ያስገኘ የአለም አቀፍ ስርአት ካፒታሊዝም መዋቅር ሲሆን እኩል ባልሆነ የንግድ ፥ የቴክኖሎጂ ፥ የሀብት ወዘተ ልውውጥ ብዙዎች ሀገሮችን ለ ድህነት ዳርጓል። 😁 እንደ Marxism አስተሳሰብ አንዳንዶቹ ሀገራት ሀብታም የሆኑት ሌሎቹ ሀገራት ደግሞ ድሀ የሆኑበት ዋናው ምክንያት ና ተጠያቂ Capitalism ነው ይላል። 🙌በነገራችን ላይ ትልቁ የመጨረሻው የ Capitalism የአስተሳሰብ ደረጃ ና ስርአት pluralism ይባላል። 🙌Pluralism ማለት የተለያየ ባህል ዘር እምነት ያላቸው ማህበረሰቦች ተቻችለው የመኖር ሁኔታ ማለት ነው። ወደ አለም አቀፍ ስርአት ሲመጣ ደግሞ Pluralism ማለት የተለያዩ ሀገራት የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ወዘተ ትብብር የመፍጠር ሁኔታ ማለት ነው። 😁😂ግን ለይስሙላ ለራስ ጥቅም ነው ትብብሩ ከልብ የመነጨ አይደለም።🤔ስለ Liberalism ስንማር ታስታውሳላችሁ ኣ Cooperation የሚል ነገር ተምረናል። ስለዚህ Pluralism ከ Liberalism ጋ የሚያገናኛቸው ነገር አለ ማለት ነው። 📚 pluralism and its liberal associations had viewed networks of economic interdependence as a basis of increasing international cooperation founded on trade and financial interactions. 🎯 ብዝሃነት(pluralism) እና የሊበራሊዝም ማህበሮች በንግድ እና በፋይናንሺያል መስተጋብር ላይ የተመሰረተውን ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ የኢኮኖሚ ትስስር አውታረ መረቦችን ይፈጥሩ ያስፋፉ ነበር። 🙌ዘመናዊ የተሻሻለው የ Marxism አስተሳሰብ ደግሞ Neo Marxism ይባላል። ታዲያ Neo Marxism ከላይ ያየንውን የ Pluralism ና የ Liberalism አስተሳሰብን ይቃወማል👇 📚 neo-Marxist structuralism viewed these processes as the basis of ✅ inequality ✅ the debt burden ✅ violence and instability. 📌 በ ሀብታም ና በድሀ ሀገራት መካከል እኩልነት እንዳይኖር ፤ የ ዕዳ ወይም ብድር ጫና እንዲሁም ብጥብጥና አለመረጋጋት እንዲኖር የ Pluralism አስተሳሰብ ዋነኛ ምክንያት ነው ሲል Neo-Marxism ይሞግታል። 🙌በ ትብብር ስም 🙉🙉የተበደርንው ገንዘብ የትውልድ ዕዳ ነው😒 ። 🙌ለማንኛውም Marxism እዚህ ላይ ጨርሰናል። ወደ Constructivism እናምራ። © A+ Tutorial Class. > Elda: 📚 #Global Trends. 📚 Constructivism. 🙌እስካሁን ባለው ትምህርታችን ስለ Liberalism, Realism ና Marxism ተምረናል። አሁን ደግሞ አራተኛውን የ አለም አቀፍ ግንኙነት ርዕዮት አለም እንማራለን እርሱም Constructivism ይባላል። 📚 Constructivism commonly viewed as a middle ground between mainstream theories and the critical theories. 😁 Constructivism የአማርኛ ጥሬ ትርጉሙ "ገንቢነት" ማለት ነው። ለማንኛውም Mainstream Theories የሚባሉት Liberalism, Realism ና Marxism ናቸው። Critical Theories ደግሞ ለ Mainstream Theory ዎች በተለይም ደግሞ ለ Liberalism ና Realism አፀፋዊ ምላሽ ተቃርኖ ሙግት የሚሰጡ ናቸው። ስለዚህ Mainstream theories ና Critical Theories ተቃራኒ ናቸው። በሁለቱ ማለትም በ Mainstream theories ና በ critical theories መካከል የሚገኘው ና እንደ መካከለኛ የሚቆጠረው Constructvism ይባላል። ከሁለቱ ወገን አይደለም ግን በሁለቱ መካከል ነው። 📚 constructivists highlight the importance of values and shared interests between individuals who interact on the global stage. 🎯 Constructivism "በዓለም አቀፍ ደረጃ መስተጋብር ግንኙነት በሚፈጥሩ ግለሰቦች(individuals) መካከል ያለውን የእሴቶችን እና የጋራ ፍላጎቶችን አስፈላጊነት ያጎላሉ አፅንኦት ይሰጣሉ።
2ኛ) የፋብሪካ ባለቤቶች - እነዚህ የፋብሪካ ባለቤቶች በቁጥር ትንሽ የሆኑ ሀብታሞች ናቸው ፣ ለቀጠሯቸው ሰራተኞች ደሞዝ በጣም ጥቂት ብር እየሰጡ እነሱ በጣም ከፍተኛ ትርፍ ነው የሚያገኙት። 🙌ስለዚህ በዚህ የ Capitalism ስርአት የ ሰው ልጆች በኢኮኖሚ ደረጃ ለሁለት ተከፈሉ። በጣም ሀብታም የሆኑ በቁጥር አናሳ የሆኑ የፋብሪካ ባለቤቶች ና በጣም ድሀ የሆኑ በቁጥር ብዙ የሆኑ ተቀጣሪ ሰራተኞቹ። 🙌ስለዚህ Capitalism የተባለው የ ኢኮኖሚ ስርአት ንብረት ያላቸው ሀብት ያላቸው ባለለብቶች ድሀውን ማህበረሰብ በትንሽ ብር ጉልበቱን የሚበዘብዝ ስርአት ነው። 👿አሁን ላይ almost ሁሉም የአለም ሀገራት ይህን ስርአት ይጠቀሙታል። 😁 በ 2ሺ ብር ደሞዝ የኛ ሀገር። 🙌ታዲያ Karl Marx የተባለው ጀርመናዊው ኢኮኖሚስት ይህንን የ Capitalism ኢኮኖሚያዊ ስርአት በመቃወም Marxism የተባለ የፖለቲካ አስተሳሰብ መሰረተ። 📚 Marxism is an ideology that argues that a capitalist society is divided into two contradictory classes – the business class (the bourgeoisie) and the working class (the proletariat). Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 📚 The proletariats are at the mercy of the bourgeoisie who control their wages and therefore their standard of living. Marx hoped for an eventual end to the class society and overthrow of the bourgeoisie by the proletariat. 📌 የካፒታሊስት ማህበረሰብ በሁለት እርስ በርሱ የሚቃረኑ ፣ የሚጋጩ ክፍሎች ማለትም የቢዝነስ መደብ (ቡርጂዮዚ ፣ ባለአባቶች ፤ ባለሀብቶች) እና የሰራተኛ መደብ (ፕሮሌታሪያት) የተከፈለ ነው በማለት የሚሞግት ርዕዮተ ዓለም Marxism ይባላል። ተመልከቱ👇 እንደ Marxism አስተሳሰብ የ Capitalism ስርአትን የሚያራምድ ሀገር ሁለት መደቦች አሉት። እነርሱም👇 📌1ኛ) ባለሀብቶች ወይም የቢዝነስ አንቀሳቃሾች ባለቤቶች ሲሆኑ እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች bourgeoisie ተብለው ይጠራሉ። 📌 2ኛ) የ ባለሀብቶቹ ድርጅት ወይም ፋብሪካ ላይ በጣም በትንሽ ክፍያ ተቀጥረው የሚሰሩ የማህበረሰብ ክፍሎች እነርሱም proletariat ተብለው ይጠራሉ። 😁ተመልኩት አንደኛው ቡድን በጣም ሀብታም ነው ቅንጡ ኑሮ ይኖራል ፤ ሌላኛው ቡድን ደግሞ በጣም ድሀ ነው በትንሽ ብር የባለጠጎች ፋብሪካ ላይ ይሰራል ፤ ባለሀብቶች ጉልበቱን ይበዘብዙታል። 📌ስለዚህ ሁለቱ መደቦች ፍፁም ለየቅል የሆነ ተቃራኒ የአኗኗር ዘይቤ ና ደረጃን ያስተናግዳሉ ፤ በአንድ አብሮ በሚኖር ማህበረሰብ ውስጥ ሁለት ተቃራኒ ማህበረሰብ ን Capitalism ፈጠረ። ይህን የ Capitalism ስርአት የተቃወመ የተቸ ና ለመጣል የተጋለው ርዕዮተ አለም ደግሞ Marxism ይባላል። 📚 እንደ Marxism አስተሳሰብ ፕሮሌታሪያቶች(ተቀጣሪ ሰራተኞች) ደሞዛቸውን እና የኑሮ ደረጃቸውን በሚቆጣጠሩት ቡርጂዮዚዎች(ባለአባቶች) መዳፍ ላይ የወደቁ ናቸው ፤ ጀርመናዊው Mark የመደብ ማህበረሰብ(capitalism) እንደሚያከትም እና ቡርጂዮይስን በፕሮሌታሪያት እንደሚገለበጥ ተስፋ በማድረግ ታግሏል። 😁ይህ የ Capitalism ስርአት እንዲያከትም Mark በወቅቱ የመፍትሔ ሀሳብ ያቀረበው ተቀጣሪ ሰራተኞች በመንግስት ና በባለጠጎች ላይ እንዲያምፁ ድብልቅልቅ ያለ አብዮት እንዲያስነሱ ነበር።(ያዙት ለፈተና) 🤔የኛ ሀገር በ አፄ ሀይለ ስላሴ ዘመን ፤ ወጣት ተማሪዎች መሬት ለአራሹ(Land to The Tiller) የሚል ከባድ አመፅ ና አብዮት አስነስተው የአፄውን ወንበር ገልብጠዋል።ይህ አመፅ ና አብዮት ምንጩ ማን ነው❓ Marxism ነው። ትምህርታችን ስለ አለም አቀፍ ግንኙነት ና ዐውድ ነው። ታዲያ የ Marxism ርዕዮተ አለም ከ አለም አቀፍ ግንኙነት(IR) ጋ ምን ቁርኝነት ና አስተሳሰብ አለው ❓ 😎ቅድም ከላይ የነገርኳችሁ የ ካፒታሊዝም ሁለቱ መደቦች ማለትም ባለሀብቶች(Bourgeois) ና ተቀጣሪ ሰራተኞች(proletariats) ናቸው። እነዚህ መደቦች ወደ አለም ሀገራት እንውሰደው ፤ እነርሱም ሀብታም ሀገሮች ና ድሀ ሀገሮች፤ ስንዴና ዘይት😂እያደሉ የተፈጥሮ ሀብታችንን የሚበዘብዙ። Marxism ስለ International Realtion ምን አለ❓👇 📚 Marxism concentrated on the inequalities that exist within the international system, inequalities of wealth between the rich "North" or the "First World" and the poor “"South" or the "Third World" > Elda: 👉 ሀብታም ሀገራት በሌላ ስማቸው "ሰሜን ወይም የመጀመሪያው አለም(North or the first world)" ተብለው ይጠራሉ። 👉 ድሀ ሀገራት ደግሞ በሌላ ስማቸው "ደቡብ ወይም ሶስተኛው አለም(South or third world)" ተብለው ይጠራሉ። 😁እኛ ስንተኛው አለም ነን? 😂ሾሽተኛው። 📚 ታዲያ ከአለም አቀፍ ግንኙነት አንፃር ማርክሲዝም(Marxism) የሚያተኩረው "በአለም አቀፍ ስርአት ውስጥ ባለው የ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ና ልዩነት ላይ ነው ፣ እርሱም በ ሀብታም ሀገራት ማለትም 'ሰሜን' ወይም 'በመጀመሪያው አለም' እና በድሀ ሀገራት ማለትም 'ደቡብ' ወይም 'በሶስተኛው አለም' መካከል ያለው የሀብት እኩልነት አለመመጣጠን ላይ ነው።" ተመልከቱ👇 📌 የአለማችን ሀብታም ሀገራት ሰሜን(North) ወይም የመጀመሪያው አለም ይባላሉ ፤ ለምሳሌ እነ አሜሪካ ፤ ቻይና ፤ ሳዑዲ አረቢያ ወዘተ። 📌 የአለማችን ድሀ ሀገራት ደቡብ ወይም የ ሶስተኛው አለም ተብለው ይጠራሉ ፤ ለምሳሌ አብዛኞቹ የአፍሪካ ፣ የኤስያ ና የ ላቲን አሜሪካ ሀገራት። 🙄አያችሁ ኣ Capitalism ስግብግብ የሆነ ስርአት ነው። 📚 በ አለማችን ሀብታም ና ድሀ ሀገራት መካከል ያለው የዕድገት ና የሀብት አለመመጣጠን Marxism ን ያሳስበዋል ይቃወማልም። ምንድን ነው ያሳሰበው ና የሚቃወመው ነገር❓ 🎯 the structuralist paradigm focused on dependency, exploitation and the international division of labor which relegated the vast majority of the global population to the extremes of poverty, often with the complicities of elite groups within these societies. 😎 Structutalist paradigm ማለት የ Marxism(structuralism) የ አስተሳሰብ ዘይቤ ማለት ነው። እርሱም👇
Realist ቶች አለም ጦርነት እና ግጭት የተለመዱበት እና የሰላም ጊዜያት የሚኖረው ወይም የሰላም ጊዜ የሚባለው መንግስታት ለወደፊት ግጭት የሚዘጋጁበት ጊዜ ብቻ😂 እንደሆነ ይገልፃሉ። 👀የዚህን ያክል ስለ ሰላም ያላቸው አመለካከት ጨለምተኛ ነው ፤ ትክክል ናቸው እውነታው እንደዛ ነው። 📚 Another point to keep in mind is that each of the overarching approaches in IR possesses a different perspective on the nature of the state. Both liberalism and realism consider the state to be the dominant actor in IR, although liberalism does add a role for non-state actors such as international organizations. 📌 ሁለቱም Liberalism እና Realism በ አለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ መንግስት(State) ን እንደ ዋና ተዋናይ(actor) አድርገው ይቆጥሩታል፣ ነገር ግን ሊበራሊዝም መንግስታዊ ላልሆኑ ለምሳሌ አለም አቀፍ ተቋማት ና ግለሰቦችም ዋና ተዋናዮች ናቸው ይላል። ስለዚህ Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 👉 በ Liberalism አመለካከት Actors of international relations የሚባሉት "States, international cooperations ና individuals" ናቸው። 👉 በ Realism አመለካከት ደግሞ Actors of international relations የሚባሉት "States" ብቻ ናቸው። 👆 ያዙት ለፈተና። 📚 Nevertheless, within both theories states themselves are typically regarded as possessing ultimate power. This includes the capacity to enforce decisions, such as declaring war on another nation, or conversely treaties that may bind states to certain agreements. 🎯በ Liberalism ና Realism የፖለቲካ አስተሳሰብ መሰረት "መንግስታት(States) ትልቁ የስልጣን የሀይል ባለቤት" እንደሆኑ ይገልፃሉ። ለምሳሌ በሌላ ሀገር ላይ ጦርነት የማወጅ ስልጣን ወይም በተቃራኒው ከ ሌላ ሀገር ጋር የሚያስተሳስራቸውን ስምምነት ውል የመዋዋል ስልጣን ያላቸው መንግስታት ናቸው። 📚In terms of liberalism, its proponents argue that organizations are valuable in assisting states in formulating decisions and helping to formalize cooperation that leads to peaceful outcomes. 📌 እንደ ሊበራሊዝም አስተሳሰብ ፣ አለም አቀፍ ድርጅቶች(ተቋማቶች) ውሳኔዎችን በማዘጋጀት እና ወደ ሰላም የሚያመጣ ትብብርን በማዘጋጀት ፤ ሀገራትን(መንግስታትን) በመርዳት ጠቃሚ ናቸው። ነገር ግን👇 📚 Realists on the other hand believe states partake in international organizations only when it is in their self-interest to do so. 📌 እንደ Realist ቶች አመለካከት ግን መንግስታት በአለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሳተፉት ለራሳቸው ጥቅም ሲያስቡ ብቻ ነው ብለው ያምናሉ😁። ይመቹኛል Realist ቶች ነጭ ነጯን ሀቅ ሀቁን(real) ነው የሚናገሩት። 😁አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ። በ Liberalism ና በ Realism አመለካከት ለአለም ሰላም በምን መልኩ ይመጣል ብለው ያስባሉ❓ በ Liberalism አስተሳሰብ ዘላቂ ሰላም አለም ላይ የሚመጣው ፤ ሀገራት ሲተባበሩ ሲተጋገዙ አንድ የሚያደርጋቸው አለም አቀፍ ተቋም ሲኖራቸው ነው ይላል።(International cooperation and collective security) በ Realism አስተሳሰብ ግን ዘላቂ ሰላም አለም ላይ የሚመጣው ፤ ሀገራት የወታደራዊ አቅማቸውን ሲያዳብሩ ፣ ጡንቻቸውን ሲያፈረጥሙ መሳሪያ ሲታጠቁ ፤ በሀገራት መካከል የሀይል መመጣጠን ሲኖር ነው ይላል(Balance of power)።ለምን? እናንተ መልሱት ተምረንዋል። 🙌በነገራችን ላይ Neo Liberalism ና Neo Realism ማለት ምን ማለት ነው❓ Neo Liberalism ማለት የተሻሻለው ዘመናዊው የ Liberalism አስተሳሰብ ነው። Neo Realism ማለት የተሻሻለው ዘመናዊው የ Realism አስተሳሰብ ነው። 🙌 ዋና ሀሳቡን ብቻ ያዙ ለፈተና። © A+ Tutorial Class. > Elda: 📚 #Global Trends. 📚 Chapter One - Understanding International Relations. 📚 Theories of International Relations. 📕 Structuralism / Marxism. 📌 ካሁን በፊት በነበረው ትምህርታችን ስለ Liberalism ና Realism ተምረናል። አሁን ደግሞ ስለ Structuralism ወይም Marxism እንማራለን። ልክ እንደ Realism ፤ Marxism ም ለአለም አቀፍ ግንኙነት ጨለምተኛ አመለካከት ነው ያለው ፤ እስኪ እንማረው። 🙌ስለ Marxism ከመማራችን በፊት ስለ Capitalism ትንሽ ነገር ማወቅ አለብን፤ ምክንያቱም Marxism የተመሰረተው Capitalism ምን በመቃወም ስለሆነ። ለመሆኑ Capitalism ምንድን ነው🤔❓ 📚 Capitalism is an economic system based on the private ownership of the means of production and their operation for profit. 📌በአሁኑ ዘመን ከ 90% በላይ የሆኑት የአለም ሀገራት የ Capitalism ስርአት አራማጅ ናቸው ፤ የ Capitalism ሀሳብ በ ኢንዱትስሪ አብዮት(industrial revolution) ዘመን የተመሰረተ ነው ፤ የኢንዱስትሪ አብዮት ማለት ደግሞ በአለማችን ላይ ፋብሪካዎች የተስፋፉበት ዘመን ነው ፤ ከ ኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን በፊት ማንኛውም ዜጋ መሬት ነበረው ፤ መሬቱን ያርሳል ከብቶቹን ያረባል ወዘተ። 📚 ነገር ግን በ ኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን በርካታ ፋብሪካዎች ና ኢንዱስትሪዎች ስለተገነቡ ፤ ፋብሪካዎቹ ጋ ተቀጥሮ የሚሰራ የጉልበት ሰራተኛ በጣም ያስፈልግ ነበር። ስለዚህ በወቅቱ የነበሩት መንግስታት ያደረጉት አንድ ነገር ነበር እርሱም ዜጎች መሬታቸው እየተቀማ ከ ገጠር ወደ ከተማ እንዲሰደዱ ማድረግ ፤ መሬታቸውን ተቀምተዋል ከተማ ሔደው የገቢ ምንጭ የላቸውም። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ፋብሪካ ውስጥ ገብተው የጉልበት ሰራተኛ መሆን ነበር። 📚 ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩት የጉልበት ሰራተኛዎች Proletariats ይባሉ ነበር ፤ የፋብሪካ ባለቤቶች ደግሞ Bourgeois ይባሉ ነበር። ስለዚህ Capitalism ሁለት የማህበረሰብ ክፍሎችን ይዟል👇 1ኛ) ተቀጣሪ ሰራተኞች(proletariats) - እነዚህ ተቀጣሪ ሰራተኞች አብዛሀኛው የማህበረሰብ ክፍል ወይም ድሀው ማህበረሰብ ነው በቁጥር በርካታ ናቸው ፤ የሚያገኙት ደሞዝ በጣም በጣም አናሳ ነበር ፤ ተገቢ የሆነ ህይወት ሊያስኖራቸው የማይችል ነበር።
📚 As no such contract exists internationally and there is no sovereign in charge of the world, disorder and fear rules international relations. That is why war seems more common than peace to realists indeed they see war as inevitable. 🙌 ነገር ግን እንዴ Kenneth Waltz Realism ገለፃ መሰረት "በአለም አቀፍ ደረጃ እንደዚህ አይነት ውል ስለሌለ እና አለምን የሚቆጣጠር ሉዓላዊ የሆነ አካል ስለሌለ፣ ስርዓት አልበኝነት እና ፍርሃት የአለም አቀፍ ግንኙነቶችን ይገዛል። ለዚያም ነው ጦርነት ከሰላም የበለጠ የተለመደ የሚመስለው። ስለዚህ Realists በእርግጥ ጦርነትን የማይቀር(inevitable) ነው ይላሉ። 📌 When they examine history they see a world that may change in shape, but is always characterized by a system of what they call "international anarchy" as the world has no sovereign to give it order. Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 😁የ Realism አቀንቃኞች ታሪክን አጠኑና በጥናታቸው አለም ቅርጿ ሊለወጥ እንደሚችል ተገነዘቡ። አለም አቀፍ ስርአት ግን መቼም አይለወጥ አሉ ፤ ማለትም አለም አቀፉ ስርአት "ስርአት አልበኝነቱን(International anarchy)" መቼም አይለውጥም አሉ። 🙄አስባችሁታል የአለም ቅርፅ(shape) መቀየር በጣምምምምምምምምምምምም ከባድ ነው ፤ ክብ የሆነችውን አለም ወደ ሌላ ቅርፅ መቀየር ከባድ ነው ፤ በተአምር የማይታሰብ ነው። ግን Realists የአለምን ቅርፅ መቀየር ይቀላል ፤ ስርአት አልበኝነት(ጦርነት የተሞላበትን) አለም አቀፋዊ ስርአት ከመቀየር ይልቅ የአለምን ቅርፅ መቀየር ይቀላል አሉ😂። በሌላ አባባል ጦርነት አይቀሬ ነው ይላሉ ምክንያቱም የሰው ልጅ ራስ ወዳድ(ego) ና ጥቅም ተኮር(self interested) ስለሆነ። Liberalism ግን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ጥሩ(innately good) ነው ይላል ፤ ሰዎች ጦርነት አይፈልጉም በተፈጥሯቸው ሰላም ወዳድ ናቸው ስለዚህ ጦርነትን ማስቀረት ና ዘላለማዊ ሰላም(perpetual peace) ማምጣት ይቻላል ይላሉ Liberalist ቶች። በአንፃሩ ግን👇 📌 Realists believe conflict is unavoidable and perpetual and so war is common and inherent to humankind. 📌 Realist ቶች ግን "ግጭት የማይቀር እና ዘላለማዊ ነው ብለው ያምናሉ ፤ ስለዚህ ጦርነት ለሰው ልጆች የተለመደ እና ተፈጥሯዊ ነው።" ይላሉ። 👁 ገባችሁ ኣ ፣ Liberalism አለም ዘላለማዊ ሰላም(perpetual peace) መሆን ትችላለች ይላል፤ Realism ግን አለም ዘላለማዊ ጦርነት(perpetual war) መገለጫዋ ነው ይላል። 😂Realism ነጭ ነጯን Real የሆነውን ነው የሚናገረው። 📚 Hans Morgenthau, a prominent realist, is known for his famous statement "all politics is a struggle for power" (Morgenthau 1948). This demonstrates the typical realist view that politics is primarily about domination as opposed to cooperation between states. 🎯 ታዋቂው የ Realism አቀንቃኝ ሀንስ ሞርጀንቱ "ሁሉም ፖለቲካ ለስልጣን የሚደረግ ትግል ነው(all politics is a struggle for power" በሚል በ 1948 በሰጠው መግለጫው ይታወቃል። ይህ የሚያሳየው ፤ ፖለቲካ በዋነኛነት በሀገራት መካከል ካለው ትብብር ይልቅ በተቃራኒ ስለ የበላይነት ነው ትግሉ ፤ Realist ቶች በዚህ አቋማቸው ይታወቃሉ። በአለም ላይ ያሉ መንግስታት የሀይል የስልጣን የበላይነት ነው ቀዳሚ አላማቸው ስለዚህ ጦርነት አይቀሬ ነው ይላሉ። 📚 Liberals share an optimistic view of International Relations, believing that world order can be improved, with peace and progress gradually replacing war. They may not agree on the details, but this optimistic view generally unites them. > Elda: Liberalism የተባለውን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎች ወይም ሙህራኖች Liberals(Liberalist) ሲባሉ ፤ Realism የተባለውን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎች ወይም ሙህራኖች ደግሞ Realist ይባላሉ። ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ፤ ሁሉም Liberalist ቶች ተመሳሳይ አንድ አይነት ሀሳብ ያላቸው ይመስሏችሗል❓የላቸውም። በዝርዝር የማይስማሙባቸው ጉዳዮች አሉ ግን Generally የሚስማሙባቸው ሀሳቦች ና መርሆዎች አሏቸው። Realist ቶችም እንዲሁ። ታዲያ👇 🎯 ሊበራሊስቶች የዓለምን ሥርዓት ማሻሻል እንደሚቻል በማመን ሰላምና መሻሻል ቀስ በቀስ ጦርነትን በመተካት ስለ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ብሩህ(optimist) አመለካከት ይጋራሉ። በዝርዝሮቹ ላይ ላይስማሙ ይችላሉ, ነገር ግን ይህ ብሩህ አመለካከት በአጠቃላይ አንድ ያደርጋቸዋል። በተቃራኒው ግን Realist ቶች👇 📚 Conversely, realists tend to dismiss optimism as a form of misplaced idealism and instead they arrive at a more pessimistic view. This is due to their focus on the centrality of the state and its need for security and survival in an anarchical system where it can only truly rely on itself. 📚 As a result, realists reach an array of accounts that describe IR as a system where war and conflict is common and periods of peace are merely times when states are preparing for future conflict. 🎯 በተገላቢጦሽ፣ Realist ቶች የ ሊበራሊስቶችን ብሩህ ተስፋ(optimistic view) ን የተሳሳተ የርዕዮተ ዓለም ዓይነት አድርገው ይቆጥራሉ ፤ ይልቁኑ ወደ ተስፋ አስቆራጭ ጨለምተኛ(pessimist) እይታ ይደርሳሉ። Realist ቶች አለም ጦርነት የራቀባት ሰላምን የሰፈነባት መሆን አትችልም የሚል የተስፋ መቁረጥ እሳቤ እንዲኖራቸው ያደረገው ምክንያት Realist ቶች በሀገራት የግዛት ማዕከላዊነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን የሀገራት የደኅንነት እና የህልውና ፍላጎት በራሳቸው ላይ ብቻ በሚተማመኑበት ሥርዓተ-አልባነት ላይ በማተኮር ነው። ገብቷችሗል ኣ ፤ ሀገራት የሚተማመኑበት አስተማማኝ አለም አቀፍ ስርአት ና ተቋም የለም ፤ በዚህም ምክንያት ሀገራት ራሳቸውን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ በወታደራዊ ቁመና ይፈረጥማሉ ፤ ወደ ጦርነት ይገባሉ ፤ በአጭሩ ስርአት አልበኝነት የተጠናወተው ስለሆነ IR system ሙ ፤ ጦርነት ግድ ነው ይላሉ።
📚 እንደ ሞርጀንቱ አስተሳሰብ "ሀይል ወይም ስልጣን(power) በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው።" ይላል። ግን ይህን አስተሳሰቡን እስከ መጨረሻው ትክክለኛ አስተሳሰብ ነው አላለም። በ Liberalism አስተሳሰብ Morality ነው በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው። በ Realism ደግሞ ሀይል ስልጣን(Power) ነው። 😁ግን የቱ ይመስላችሗል ትክክል❓ ነጭ ነጯን(real) መነጋገር ጥሩ ነው ፤ ሀይል ነው ተቀባይነት ያለው ፤ እናንተ ራሱ ክብደት በማንሳት ጡንቻ በማፈርጠም ታምኑ የለ😂። 📚 Morgenthau‘s text starts with the assumption that there are objective laws which have universal applicability, "international politics, like all politics, is a struggle for power". 🎯 የ Morgenthau ጽሑፍ የሚጀምረው ሁለንተናዊ ተፈጻሚነት ያላቸው ተጨባጭ ሕጎች እንዳሉ በማሰብ ነው፣ “ዓለም አቀፍ ፖለቲካ፣ ልክ እንደ ሁሉም ፖለቲካ፣ የሥልጣን ትግል ነው”። የሚል ነው። Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 📚 Thomas Hobbes is often mentioned in discussions of realism due to his description of the brutality of life during the English Civil War of 1642–1651. Hobbes described human beings as living in an order-less "state of nature" that he perceived as a war of all against all. 🎯 ቶማስ ሆብስ የ Realism አንዱ መስራች ሲሆን ከ 1642-1651 በእንግሊዝ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ስለነበረው የህይወት ጭካኔ በሰጠው መግለጫ በ Realism ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። የሰው ልጆች እርስ በርሳቸው በመጣላት በመገዳደል በመጠፋፋት ሥርዓት በሌለው “የተፈጥሮ ሁኔታ” ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል ሆብስ። 📌 To remedy this, he proposed that a "social contract" was required between a ruler and the people of a state to maintain relative order. 🎯 ስርአት አልበኝነትን ለማስተካከል ቶማስ ሁበስ በወቅቱ አንድ ሀሳብ አቅርቦ ነበር " አንጻራዊ ጸጥታን ለማስጠበቅ በ ገዥ ና በሕዝብ ወይም በተገዢ መካከል “ማህበራዊ ውል(Social Contract)” እንደሚያስፈልግ አቅርቧል ፤ Civics ቻፕተር 4 ላይ በስፋት አለ እንማረዋለን። 📚 Kenneth Waltz‘s "Man, the State and War"(1959) and his later "Theory of International Politics"(1979) define a neo-realist agenda and absolutely dominated the discipline and some would argue do so to the present day. 🎯 ኬኔት ዋልትስ በ 1959 "ሰው፣ መንግስት እና ጦርነት" እና በኋላም በ 1979 "Theory of International Politics" የሚሉ ሁለት መፅሀፎችን ፅፏል። መፅሀፎቹ የ Neo-Realism አጀንዳን ይገልፃሉ ፤ የ Kenneth Waltz የ Realism ፅሁፎች በወቅቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ነበሩ። አንዳንዶች እስከ ዛሬ ድረስ የሱን የ Neo Realism ሀሳብ ደግፈው ይከራከራሉ። ለመሆኑ Neo Realism ምንድን ነው❓Neo Realism ማለት የተሻሻለው የ Realism አስተሳሰብ ማለት ነው ፤ ለተጨማሪ መረዳት Google አድርጉት። 📚 Where Morgenthau‘s realism concentrates on the attributes and behavior of states within the international system, Waltz focuses on the international system itself and seeks to provide a structuralist account of its dynamics and the constraints it imposes on state behavior. 🙌 የ ሞርጀንቱ(የሞርገንሃው) የ Realism አስተሳሰብ "በአለም አቀፉ ስርአት ውስጥ ባሉ መንግስታት(states) ባህሪያት ላይ ያተኮረ" ሲሆን የ Kenneth Waltz የ Realism አስተሳሰብ ደግሞ " በራሱ በአለም አቀፉ ስርአቱ ላይ ያተኩራል እንዲሁም ስለ አለም አቀፉ ስርአት ተለዋዋጭ ባህሪያት እና አለም አቀፉ ስርአት በመንግስታቶች(states) ላይ ስለሚያደርሰው ጫና ይዘግባል። 🤔 ገብቷችሗል ኣ። የ ሞርጀንቱ Realism ዋና ትኩረቱ በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ናቸው ፤ ለጦርነት መነሳትም ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው የሚል ሀሳብ አለው። የ ዋልት Realism ደግሞ ዋና ትኩረቱ ራሱ አለም አቀፉ ስርአት ነው ፤ ለጦርነት መነሳትም ተጠያቂው አለም አቀፉ ስርአት ነው ብሎ ያምናል። 🙌በነገራችን ላይ ለፈተና ይህን ሁሉ መያዝ አይጠበቅባችሁም ፤ ፈተና ላይ የምትጠየቁት ዋና ሀሳቡን ነው። ማለትም 👇 👉 የ Liberalim የ Realism የፖለቲካ አመለካከትን መያዝ። 👉 Liberalism ና Realism ለ አለም አቀፉ ስርአት(IR System) ያላቸው አመለካከት ምን እንደሆነ መያዝ። 👉 በ Liberalism ና Realism መካከል ያለው መሰረታዊ ልዩነት ምን እንደሆነ መያዝ። በቃ ፈተናው ከዚህ አይዘልም ፤ እነዚህን ደግሞ እየተማርናቸው ነው። እንቀጥል ወደ ትምህርቱ። 📚 The international system is, for Waltz, anarchical and hence perpetually threatening and conflictual. What is of interest to Waltz is not the set of motives which may determine state behavior, but the imperatives of the international system and the distribution of capabilities within it. > Elda: 📚 Each leader or "sovereign" (a monarch, or a parliament for example) sets the rules and establishes a system of punishments for those who break them. We accept this in our respective states so that our lives can function with a sense of security and order. It may not be ideal, but it is better than a state of nature. 🎯 እያንዳንዱ መሪ ወይም “ሉዓላዊ” (ንጉሠ ነገሥት ወይም ፓርላማ ለምሳሌ) ደንቦቹን ያዘጋጃል እና ለጣሱ ሰዎች የቅጣት ሥርዓት ይዘረጋል ፤ ዜጎች በሰላም እና በስርዓት እንዲኖሩ ሀገራት ህግን ያስከብራሉ። ገብቷችሗል ኣ ፤ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹን ሲያስተዳድር በሀገሪቱ ሰላም ና መረጋጋት ለማስፈን ሲባል በዜጎች ና በመንግስት መካከል ገዢ ውል(ህግ) አለ ፤ ይህን ውል መንግስትም ዜጎችም ያከበሩታል ፤ ውሉን(ህጉን) የሚያፈርስ አካል ቅጣት ይጠብቀዋል ፤ ስለዚህ ሀገራት ሰላማቸውን ጠብቀው በዚህ መልክ ይኖራሉ እንደ Kenneth Waltz Realism ገለፃ መሰረት። ነገር ግን👇
📌Realists አንድ ዋና መከራከሪያ ሀሳብ አላቸው። እርሱም ስነ ምግባር(morality) እንደ ሁኔታው እንደ አውዱ በራስ ፍላጎት የሚወሰን ነው ይላሉ ስለዚህ Morality ከሰው ሰው ይለያያል ይላሉ። ያ ማለት የ ሩሲያ መሪ የፑቲን Morality የፑቲንን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ፤ የአሜሪካው መሪ ጆ ባይደን ሞራሊቲ የ ባይደንን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው። ለዛ ነው Morality is context bound ነው የሚለው realism። የባይደን ና የፑቲን ፍላጎት አለመጣጣም ጦርነትን ይጋብዛል ፤ ይህ ደግሞ Conflict of interest(የጥቅም ግጭት) ይባላል። Ralist ቶች ፤ አሁን(present) ያለው ሁኔታ የሚወሰነው ባለፉት ታሪካዊ ሒደቶች ወይም ክስተቶች ነው ብለው ያምናሉ። ለምን ይመስላችሗል የ ፑቲን ና የባይደን ፍላጎት የተለያየው❓ከ 60 አመት በፊት በሩሲያ(ሶቭየት ህብረት) ና በአሜሪካ መካከል ጦርነት ተኳሒዶ ነበር ፤ ያ ጦርነት አሁን ላይ ለሩሲያ ና ለአሜሪካ ቁርሾ ነው። ለዛም ነው "The present condition are determined by historical process" ብለው የሚያምኑት realist ቶች። Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 😁 Liberalist ቶች ግን morality ከ ሰው ሰው አይለያይም ፤ Morality አለም አቀፍ የሆነ መመሪያ ዶግማ ነው ይላሉ ፤ እርሱም ሰዎች በተፈጥሯቸው መልካም ናቸው ሌሎችን የመጉዳት ሀሳብ የላቸውም የሚል ነው። 😁 ያ ማለት የ ፑቲን ና የባይደን ፤ የ አብይ አህመድ ና የደብረፅዮን ወዘተ የሞራሊት አስተሳሰብ ተመሳሳይ ነው😁።ስለዚህ ጦርነቱ አይኖርም። 📌 The formative assumptions of realism as a school of thought centre on the view that the international system is "anarchic", in the sense that it is devoid of an all-encompassing authority. 🎯 የ Realism ዋና የፖለቲካ አስተሳሰቡ👇 " ዓለም አቀፉ ስርአቱ 'ስርአት አልበኛ(anarchic)' ነው ፤ ማለትም አለም አቀፉ ስርአቱ አንድ ወጥ የሆነ አስተዳዳሪ ገዢ ተቋም የለውም ፤ ፈርጣማ ሀገራት እንደልባቸው ይፈነጫሉ ድሀ ሀገራት ደግሞ ተጨቁነው ይኖራሉ። 🤔 ስርአት አልበኝነት(Anarchy) ምን ማለት እንደሆነ ገብቶችሗል❓ ሀገራት እርስ በርስ ከልብ አይከባበሩም ፣ ሁሉንም የአለም ሀገራት በእኩልነት በፍትሐዊነት የሚገዛ የሚያስተዳድር ፣ ሁሉም የአለም ሀገራት የሚያከብሩት የሚታዘዙለት አለም አቀፍ ስርአት ና ተቋም አለመኖር ማለት ነው Anarchy ማለት። ለምሳሌ ፤ በአሁኑ ሰአት አለም አቀፍ ተቋም የተባበሩት መንግስታት(UN) ነው አይደል። ግን ይህን ተቋም የሚያከብር የሚሰማ ለህጉ የሚታዘዝ ሀገር አለ❓የለም በተለይ ሀይል ያላቸው እነ አሜሪካ ሩሲያ ቻይና ወዘተ መስሚያቸው ጥጥ ነው። ተቋሙ ራሱ ሁሉንም ሀገር በእኩል አይን ያስተናግዳል❓እንደው በሞቴ ኢትዮጵያን ና አሜሪካን እኩል ያያል❓😂😂 ይህ ነው Anarchy ማለት ፤ ሁሉን አቀፍ ስልጣን የለሽ ማለት ነው። 📚 Where domestic society is ruled by a single system of government, the international system of states lacks such a basis and renders inter-national law non-binding and ultimately ineffectual in the regulation of relations between states. Conflict is hence an inevitable and continual feature of inter-national relations. 🎯 አንድ ሀገር በ ሀገሪቱ መንግስት ይመራል ይተዳደራል አይደል። ለምሳሌ ኢትዮጵያ በብልፅግና መንግስት እየተመራች ነው። አለምስ በማን ነው የምትመራው የምትተዳደረው❓አለምን የሚያስተዳድራት አለም አቀፋዊ መንግስት ወይም ተቋም የለም። የተባበሩት መንግስታት(UN) በርግጥ አለም አቀፋዊ ተቋም ነው። ግን ይህ ተቋም ከስም በዘለለ ትርጉም ያለው ስራ እየሰራ አይደለም ፤ ስለዚህ በአለም ላይ ያሉ ሀገራትን ግንኙነት የሚመራ የሚቆጣጠር አለም አቀፋዊ ስልጣን ያለው አካል የለም። በዚህም ምክንያት ጦርነት የማይቀር(inevitable) ና ቀጣይነት ያለው የብሔራዊ ግንኙነት መገለጫ ነው ይለናል Realism። በ Liberalism አስተሳሰብ ግን ጦርነት inevitable አይደለም ወይም ጦርነት መቅረት ይችላል። 📚 As liberal internationalism sought foundations in the Enlightenment and the birth of reason so realism locates its roots further back, citing Thucydides, Machiavelli and Hobbes as its founding voices. 🙌Liberalism በ እነ John Locke ና Immanuel Kant አማካኝነት በ Enlightenment ዘመን ነበር የተመሰረተው። Realism ደግሞ በእነ Thucydides, Machiavelli ና Hobbes አማካኝነት ነው የተመሰረተው። 📚 Thucydides and his account of the Peloponnesian War is read as the formative paradigmatic text in that it covers themes such as power, intrigue, conquest, alliance-building and the intricacies of bargaining. Here we see portrayed a system of city states, the units or members of which are self-reliant and independent, with war breaking out in 431 BC. 🎯 Thucydides የፔሎፖኔዥያ ጦርነትን ዘግቧል። ዘገባው እንደ ሃይል፣ ሴራ፣ ድል፣ ህብረት እና የድርድር ውስብስብ ጉዳዮችን ስለሚሸፍን እንደ መደበኛ ምሳሌያዊ ጽሁፍ ይነበባል። 😁Realism እየተጠነሰሰ ነው ማለት ነው። > Elda: 📚 Hans Morgenthau, whose Politics among Nations(1948) leads the realist perspective, points to a clear line of descent from Thucydides when he asserts that "realism" assumes that its key concept of interest defined as power is an objective category which is universally valid, but it does not endow that concept with a meaning that is fixed once and for all. ከ Thucydides በመቀጠል የመጣው Hans Morgenthau ይባላል ፤ የ Hans Morgenthau የ Realism አስተሳሰብ በ 1948 አካባቢ አብዛሀኞቹ ሀገራት ተቀብለውታል። የ Hans Morgenthau(ሃንስ ሞርጀንቱ) የ Realism አስተሳሰብ ምንድን ነው❓
👀 ተመልከቱ ፣ Liberalism በአለም ላይ ዘላቂ ሰላም ማምጣት ይቻላል ጦርነትን ከአለም ፈፅሞ ማስወገድ ይቻላል ይላል ፤ ጦርነትን ለማስወገድ ደግሞ አለም አቀፋዊ ተቋም(international law) መመስረት የተሻለ ነው ይላል። Realism ግን በአለም ላይ ዘላቂ ሰላም ማምጣት አይቻልም ጦርነት አይቀሬ(inevitable) ነው ይላል ምክንያቱም የሰው ልጅ ራስ ወዳድ ነው ፤ በሀይሉ በወታደራዊ አቅሙ የተነሳ አለም አቀፍ ህግን(international law) ን አያከብርም ፣ ሌሎችን ጨቁኖ ሌሎችን ረግጦ እርሱ የበላይ መሆን ስለሚፈልግ። 😁 በዚህ context የሰው ልጅ ስንል በስልጣን ላይ ያሉ መሪ የሆኑ የሰው ልጆችን ነው ፤ እነ ሒትለር አብይ አህመድ ኦባማ ፑቲን ወዘተ። Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 😁ስለዚህ የ Realism የፖለቲካ አስተሳሰብ ገብቷችሗል ኣ። ጦርነት በአለም ላይ የማይቀር ነው ምክንያቱም ሰዎች(መሪዎች) ራስ ወዳድ ስለሆኑ ፤ ሌሎችን በመጨቆን በሀይል በመርገጥ ፤ በመበዝበዝ የራሳቸውን ሀገር ጥቅም ማስጠበቅ ስለሚፈልጉ ፤ ሁሉም የአለም ሀገራት የሚያከብሩት በሁሉም የአለም ሀገራት ተሰሚነት ያለው አለምአቀፋዊ ተቋም ባለመኖሩ አለም ለጦርነት ተጋላጭ ናት። እስኪ ከታሪካዊ አመጣጡ ጀምረን እንመልከተው። 📚 Though liberal internationalist ideals are now recognized for their significant contribution in the development of normative approaches to the subject, they seemed, at the outset of the 1930s and ultimately the outbreak of the Second World War, futile and utopian. Thus it was that the subject matter of international relations, dominated as it had been by international law and diplomatic history, was transformed to an intellectual agenda which placed power and self-interest at the forefront of concern. Futile ማለት ዋጋ ቢስ ማለት ነው። Utopian ማለት ደግሞ ሀሳባዊ(ideal) ተግባራዊ መሆን ያልቻለ ማለት ነው። ተመልከቱ👇 🎯 ምንም እንኳን የ Liberalism ፅንሰ-ሀሳቦች ለ Theories of IR መመስረት ና ማደግ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅዖ እውቅና ቢያገኙም ፤ በ1930ዎቹ ጦርነት መካሔድ እና በመጨረሻም የ2ኛው የዓለም ጦርነት ፍንዳታ የ Liberalism የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲወድቅ ፤ ዋጋ ቢስ(futile) እና ሀሳባዊ ፥ በተጨባጭ ተግባራዊ መሆን የማይችል(utopian) እንዲሆን ምክንያት ሆነ። Liberalism ወድቆ Realism የተባለ የፖለቲካ አስተሳሰብ ተተካ። ስለዚህም የዓለም አቀፍ ግንኙነት ርዕሰ ጉዳይ፣ ከ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ሕግ ፣ ወደ ምሁራዊ አጀንዳነት(intellectual agenda) የተሸጋገረ ሲሆን ይህም በ Realism አስተሳሰብ ሥልጣንን እና የግል ጥቅም የአለም የስጋት ቀዳሚ ምንጭ ሁነው ተነሱ። 🤔 ለምንድን ነው የ2ኛው የአለም ጦርነት ለ Liberalism መውደቅ ምክንያት የሆነው❓ 🌐 ካስታወሳችሁ ባለፈው ስለ Liberalism ስንማር ፤ በ Liberalism የፖለቲካ አስተሳሰብ ፤ የሰው ልጆች በተፈጥሯቸው መልካም(innantely good) ስለሆኑ ጦርነት ከአለም ላይ ሙሉ ሙሉ ማጥፋት ይቻላል ፤ አለማችን ጦርነት የማይጎሰምባት ፍፁም ሰላማዊ ምድር(ገነት) ማድረግ ይቻላል። ለዚህም ደግሞ አለምአቀፋዊ ህግ(international law) ና አለምአቀፋዊ ተቋም ና ህብረት(international cooperation) መመስረት ያስፈልጋል ብለው መሰረቱ። 😁ነገር ግን ይህ የ Liberalism አስተሳሰብ ና በሱ አማካኝነት የተመሰረቱት እነ League of Nation የተባሉ አለም አቀፍ ተቋማት አለምን ከጦርነት ማዳን አልቻሉም። ይልቁንም እጅግ አውዳሚ የሆኑ የአለም ጦርነቶች ተካሔዱ። በዚህም ምክንያት👇 💉 የሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሳት የ Liberalism የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲወድቅ ሆነ ፤ Realism የሚባለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ማቆጥቆጥ ጀመረ። ፈተና ላይ ለምሳሌ👇 Of the following, which one can be a reason for the failure of Liberalism and emergence of Realism? A) The effective arbitration of League of Nations. B) The outbreak of World War II(WWII). C) The End of Cold War. D) The emergence of UN. 😁እንደዚህ ብትየጠቁ። መልሱ B ይሆናል ማለት ነው ፤ አደራችሁን መሉውን ነው መረዳት ያለባችሁ እንዳትሸመድዱ። 📌ስለዚህ ሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሳት የአለም የፖለቲካ ርዕዮት ከ Liberslism ወደ Realism ተሸጋገረ። የ Liberalism ዋና አጀንዳው አለም አቀፋዊ ዘላቂ ሰላም የሚመጣው አለምአቀፍ ህብረት ፤ ተቋም ና ህግ በመመስረት ነው ይል ነበር። Realism ደግሞ ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸው ሀገራት የራስ ጥቅምን በበላይነት ለማስጠበቅ ሲሉ በሀይላቸው በወታደራዊ አቅማቸው አለም አቀፍ ተቋም ና ህግን ይሽራሉ ይላል። > Elda: League of Nations የሚባል አለምአቀፍ ተቋም ነበር ይህን ተቋም ና ህጉን ጥሰው ለዛም ነው ሁለተኛው የአለም ጦርነት ሀገራት የጀመሩት ይላል። ስለዚህ ከ Liberalism ወደ Realism ተሸጋገረ ማለት ከ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ሕግ ፣ ወደ ምሁራዊ አጀንዳነት(intellectual agenda) ተሸጋገረ ማለት ሲሆን ይህም ሥልጣንን እና የግል ጥቅም የስጋት ቀዳሚ ምንጭ ሁነው ተነሱ። ማለትም የስልጣን የበላይነት ለማግኘት ና የግል ጥቅምን ለማጋበስ ሲባል ሀገራት የሚያደርጉት ፉክክር ለአለም ስጋት ና ችግር ደቀነ። 😍በቃ ይህ ነው የ Realism ዋነኛ የፖለቲካ አስተሳሰብ መሰረቱ። 📚 Realists argue that values are context bound, that morality is determined by interest, and that the conditions of the present are determined by historical processes. Where idealism sought a universally applicable doctrine, Carr‘s call is for a historical analysis of the contingent frameworks which determine politics. 🎯 የ Realism የፖለቲካ አስተሳሰብን የሚያራምዱ ሰዎች Realists ተብለው ይጠራሉ።
📌 international law performs two different functions.(አለም አቀፍ ህግ ሁለት መሰረታዊ ተግባራት አሉት።) እነርሱም👇 1) provides mechanisms for cross-border interactions. (ለድንበር ተሻጋሪ ግንኙነቶች ወይም በሀገራት መካከል ለሚደረጉ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ዘዴዎችን ና ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።) ይህ የ አለም አቀፍ ህግ ተግባር ፤ Operating System ተብሎ ይጠራል። Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 2) shape the values and goals these interactions are pursuing. (ለድንበር ተሻጋሪ ግንኙነቶች ወይም በሀገራት መካከል ለሚደረጉ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ፣ ግንኙነቶቹ መከተል ማድረግ ያለባቸውን እሴቶች እና ግቦች ይቀርጻል። ይህ ሁለተኛው የአለም አቀፍ ህግ ተግባር Normative System ተብሎ ይጠራል። 🤔በአጭሩ የአለም አቀፍ ሕግ ዋና አላማው(purpose) ወይም ተግባሩ ምን ይመስላችሗል❓ 😌 ኢንጂነር ሚጢሻዬ መልሺ እስኪ። እነ ሶሪያ ሊቢያ አፍጋኒስታን ሲወድሙ ይህ የአለም አቀፍ ህግ ምን እየሰራ ነበር❓ > Elda: #Global 📌 The purpose of international law is thus to regulate the conducts of governments and the behaviors of individuals within states. 📚 የአለም አቀፍ ህግ አላማ በአለም ላይ የሚገኙ ሀገራትን(መንግስትን) አሰራራቸው ላይ ቁጥጥር ማስተካከያ ማድረግ እና በሀገራት ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን ባህሪ መቆጣጠር ነው። 🙌ግን እውነት አለምአቀፍ ሕግ ከስም ና ቢሮ ከማሞቅ ስብሰባ ከመሰብሰብ የዘለለ በተግበር ትርጉም ያለው ስራ ለአለም ህዝብ ለሰው ልጅ እየሰራ ነውን❓😏😏እእእ ቱሪናፋ ብቻ። 📚 However, the legal standing of international law is a contentious issue among scholars. There are three competing views on this matter. (ሆኖም የአለም አቀፍ ህግ ህጋዊ አቋም በምሁራን መካከል አከራካሪ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ሦስት ተፎካካሪ አመለካከቶች አሉ።) እነርሱም👇 1) Some scholars say international law is not a law at all but a branch of international morality.(አንዳንድ ሊቃውንት አለም አቀፍ ህግ በፍፁም ህግ ሳይሆን የአለም አቀፋዊ የስነምግባር ክፍል ነው ይላሉ። በአጭሩ ፦ህግ(law) ሳይሆን Ethics ነው ይላሉ።) 2) Others say it is a law in all senses of the term. ( ሌሎች ደግሞ በሁሉም የቃሉ ፍቺዎች ህግ ነው ይላሉ።) 3) Yet, others say it is a matter of definition. As a result, the operating system of international law functions in some ways as a constitution does in a domestic legal system and not as law proper-i.e it does nothing beyond setting out the consensus of its constituent actors on distribution of authority, rights and responsibilities for governance within the international system.(ሌሎች ግን የፍቺ ጉዳይ ነው ይላሉ። በ አንድ አገር ውስጥ ያለ ህገ መንግስት አጠቃላይ የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮችን እንደሚዳስስ ሁሉ አለም አቀፍ ህግም እንዲሁ ነው። ማለትም እንደ ህግ ሳይሆን በስልጣን ክፍፍል፣ መብትና ግዴታዎች ላይ ያላቸውን ስምምነት ከማስቀመጥ የዘለለ ምንም ነገር አላደረገም። 🙌 ስለ Liberalism ከዚህ ላይ እናቁም። ከ Liberalism የፖለቲካ አስተሳሰብ ምን ተረዳችሁ🤔❓ደካማ ና ጠንካራ ጎኑ ምን ይመስላችሗል❓ይህን የፖለቲካ አስተሳሰብ ወዳችሁታልን❓ 🙌እኔ አንድ ነገር ልናገር ከተረዳሁት። እንዴ Liberalism አመለካከት "Individuals(ግለሰቦች) ፣ ሀገራት(States) ፣ አለም አቀፍ ተቋማት(institutions) በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ ዋና ተዋናዮች(actors) ናቸው" ስለዚህ በአለም ላይ ሰላም ለማምጣት የሶስቱን ደህንነት ማስጠበቅ አለብን" 🙌Liberalism ለሰዎች የሚያዝን ና ለሰው ልጅ በጎ አመለካከት ያለው ይመስላል ፤ ለሰዎችም ልክ የሆነ ነፃነት ይሰጣል። ዲሞክራሲያዊ ስርአት ን ይመርጣል ከንጉሳዊ ና ከአምባገነናዊ ስርአት። 🤔ግን እውነት Liberalism በተግባር ለሰው ልጅ ቀና አመለካከት አለው❓አዬዬዬዬ እነ አሜሪካ እእ እንጅ በጣም ያስባሉ ህህህህህህ😏😏። አሁን ደግሞ Realism ን እናያለን። © A+ Tutorial Class. > Elda: 📚 #Global Trends 📚 Chapter One - Understanding International Relations. 📚 Theories of International Relations. 📌 Realism 🙌በቅድሙ ትምህርታችን ስለ Liberalism ወይም Idealism የፖለቲካ ርዕዮት ና የሞራል ፍልስፍና አይተናል። አሁን ደግሞ ስለ Realism የፖለቲካ ርዕዮት ና የሞራል ፍልስፍና እናያለን። በ Liberalism ና በ Realism መካከል ያለውን የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳስሳለን። 🤔Realism የፖለቲካ አስተሳሰቡ ምንድን ነው❓ Realism በነገራችን ላይ Real ከሚለው ቃል የተወሰደ ነው ፤ Real ማለት ደግሞ እውነታ ፥ ሀቅ ማለት ነው። 📚 Realism is a theory that claims to explain the reality of international politics. Realism emphasises the constraints on politics that result from humankind's egoistic nature and the absence of a central authority above the state. 🎯 Realism የአለም አቀፍ ፖለቲካን እውነታ(ሀቅ) የሚገልፅ ቲዎሪ ነው። የአለም ፖለቲካ በተግባር ምን ይመስላል? "በሰው ልጅ የራስ ወዳድነት ና የስግብግብነት (ego) ባህሪ ምክንያት ስላለው የአለም ሀገራት የፖለቲካ ነፃነት ማጣት እና በአለም ላይ ካሉ መንግስታት በላይ የሆነ የአለም መንግስታትን የሚዳኝ የሚገዛ ፤ አንድ አለም አቀፋዊ ማዕከላዊ ተቋም ባለመኖሩ ለአለም ፖለቲካ መባለግ መበላሸት ምክንያት ነው" ይላል Realism። 👀ተመልከቱ ፣ Liberalism የሰው ልጆች በተፈጥሯቸው መልካም(innately good) ናቸው ይላል ፤ Realism ግን የሰው ልጆች ራስ ወዳድ( Ego, selfish, self-interested) ናቸው ይላል።
📚 With foundations in the Enlightenment and the eighteenth century, liberal internationalism, as Scott Burchill points out, suggested that "the prospects for the elimination of war lay with a preference for democracy over aristocracy, free trade over autarky, and collective security over the balance of power system". Nathan🐾, [11/26/2024 3:17 AM] 😒ስለ Enlightenment እኔ አላስረዳችሁም። Liberal internationalism(liberalism) የተመሰረተው በ Enlightenment ዘመን ነበር። Scott Burchill የተባለው ፀሀፊ በ Enlightenment ዘመን የተመሰረተውን Liberal Internationalism ን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል👇። > Elda: ጦርነትን የማስወገጃ መንገዶች👇 👉 ከባላባታዊ(aristocracy) ሥርዓት ይልቅ ለ ዴሞክራሲ ቅድሚያ ቦታ ሲሰጥ ተመራጭ ሲሆን ፣ 👉 በቁጥጥር ከተመሰረተ የንግድ ልውውጥ (autarky) ይልቅ ለ ነፃ የንግድ ልውውጥ(free trade) ቅድሚ ቦታ ሲሰጥ ፣ 👉 ከ ሓይል ሚዛን(balance of power) ይልቅ ለጋራ ደህንነት(collective security) ቅድሚያ ቦታ ሲሰጥ ተመራጭ ሲሆን ፤ 👆ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስቱን ነገሮች ማድረግ ጦርነትን ለማስወገድ ወይም በአለም ላይ ሰላምን ለማምጣት ይረዳሉ ይላል Liberal internationalism። 🤔ፈተና ላይ እንዲህ ተብላችሁ ብትጠየቁስ❓👇 In liberalist thinking, which one is preferable to bring international peace? A) Balance of power B) Economic Power C) Military Might D) Collective Security 😌አያችሁ ኣ ለፈተና ስትዘጋጁ በዚህ መልኩ ነው። ስለዚህ መልሱ D ነው። 📚 The two formative pillars of liberal internationalism, democracy and free trade, required the establishment of international relations which would promote collectivist aspirations in place of the conflictual relations which formed the basis of balance-of-power thinking. 🙌 የ Liberal internationalism ምሰሶዎች(pillars) ሁለት ናቸው እነርሱም ዲሞክራሲ ና ነፃ ንግድ ናቸው። በ liberalism አስተሳሰብ የሓይል ሚዛን (balance of power) በአለም ላይ ጦርነት እንዲፈጠር ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። ስለዚህ የሓይል ሚዛን(balance of power) ተወግዶ ፣ በሱ ቦታ በ democracy ና free trade የአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ መርህ መሆን አለባቸው ሲል ይከራከራል። ገብቷችሗል ኣ ዲሞክራሲ መሆኑ ዲሞክራሲያዊ ሀገር ከዲሞክራሲያዊ ሀገር ጋ ጦርነት አይገጥሙም ብለው ስለሚያስቡ ነው እነ kant። free trade መሆኑ በ ሀገሮች መካከል የ ኢኮኖሚ የበላይነት እንዳይኖር ያደርጋል ፣ የ ኢኮኖሚ የበላይነት ከሌለ ደግሞ የሓይል ሚዛንም አይኖርም። 📚 For it was just such thinking, based as it was on the premise that relations between states are determined solely by the pursuit of power, which led to violations of international law and ultimately to the outbreak of war in 1914. A system of "collective security" was advocated to replace antagonistic alliance systems with an international. Liberalism እንዲህ ሲል ይከራከራል " በሀገሮች መካከል ሲደረግ የነበረው ግንኙነት 'የበላይ ለመሆን ሀይልን ማፈርጠም ሀይልን ማጎልበት(pursuit of power) ፣ በቡድን ተከፋፍለው ህብረት መፍጠር ና ተቀናቃኝ መሆን' ላይ የተመሰረተ ነበር። ይህ ደግሞ አለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ ለአንደኛው የአለም ጦርነት መጀመር ምክንያት ነው ፣ ምክንያቱም ሀገራት ከ ህግ ይልቅ የነበራቸው ወታደራዊ ቁመና ላይ ስለሚተማመኑ። ስለዚህ እንደዚህ አይነት ተቀናቃኝ ህብረቶች(antagonistic alliance) ን አስወግዶ ፤ የጋራ ደህንነት(collective security) ስርአትን በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ መተግበር ያስፈልጋል ይላል።" 🙌ምን ብለናል ቅድም❓በ Liberalism የፖለቲካ አስተሳሰብ መሰረት አለም ሰላማዊ እንድትሆን ወይም ከአለም ላይ ጦርነትን ለማስወገድ አለም አቀፍ ማህበር(ተቋም) መመስረት ያስፈልጋል። ይህ አለም አቀፍ ማህበር(ተቋም) የሚያወጣቸው ህጎች ና ደንቦች ደግሞ አለም አቀፍ ህግ(international law) ይባላል። ተመልከተቱ👇 ኸረ ደስ የሚል ትምህርት ነው😁 📚 Liberals also argue that international law offers a mechanism by which cooperation among states is made possible. 🎯 Liberalist ቶች "ዓለም አቀፍ ሕግ(International Law) በ ሀገራት በመንግስታት መካከል ትብብር እንዲኖር የሚያስችል ዘዴ ይሰጣል" ብለው ይከራከራሉ ያምናሉ። ለመሆኑ ዓለም አቀፍ ሕግ(International Law) ምንድን ነው❓ይኸው👇 📚 International law refers to the body of customary and conventional rules which are binding on civilized states in their intercourse with each other. 🎯 አለም አቀፍ ህግ(International Law) ማለት "ሀገራት(መንግስታት) እርስበርስ በሚያደርጉት ግንኙነት ላይ ለሀገራቱ ገዢ አስማሚ(binding) የሆኑት ባህላዊ(customary) እና የተለመዱ(conventional) ህጎች ማለት ነው። customary ና conventional rule ማለት ማህበረሰቡ የሚተዳደርባቸው እሴቶች 📚 international law provides the normative framework for political discourse among members of the international system. The framework does not guarantee consensus, but it does foster the discourse and participation needed to provide conceptual clarity in developing legal obligations and gaining their acceptance. 🎯 ዓለም አቀፍ ሕግ በዓለም አገራት መካከል የፖለቲካ ንግግር ና ውይይይት እንዲደረግ ፤ መወያያ መድረኩ ሁኖ ያገልግላል። መድረኩ የጋራ መግባባትን አያረጋግጥም ነገር ግን ህጎችን ለማዳበር እና የህጎችን ተቀባይነትን ለማግኘት ፤ ግልጽ የሆኑ ሀሳቦችን በማቅረብ በሀገራት መካከል ንግግሮች እና ተሳትፎችን ያበረታታል ያሳልጣል።