tgindex
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥናትና ምርምር መጽሔት ስራዎች

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥናትና ምርምር መጽሔት ስራዎች

Статистика

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥናት እና ምርምር ጽሁፎች የታተሙ ያልታተሙ ጆርናሎች ችግር ፈቺ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ዳሰሳዎች መጽሐፎች ይቀርቡበታል

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
27
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 399
−3 за 3 дн.
Сутки
−2
−0,06%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
389
27 постов
Вовлечённость
11,4%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 27
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
105
1/48двое суток
120
1/72трое суток
129

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • ዲያቆናዊቷ ቅድስት ፌበን 🤗 በጥንቷ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያለ ድምፅና ያለ እውቅና ፍለጋ አምላካቸውን በታማኝነት ካገለገሉ ታላላቅ ሴቶች መካከል ፌበን በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች። ፌበን በጥንቷ ግሪክ በቆሮንቶስ ከተማ በስተምሥራቅ ይገኝ የነበረ ክንክራኦስ በተባለች ጥንታዊ የወደብ ከተማ ባለች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ እና ዲያቆናዊት ናት። ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ ስለ እሷ ሲመሰክር “በክንክሬኦስ ያለች የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እህታችንን ፌበንን አደራ ብያችኋለሁ” በማለት በታላቅ አክብሮት ያስተዋውቃታል [ሮሜ 16፥1]። ፌበን በሀብቷና በማህበራዊ ተፅዕኖዋ አገልጋዮችንና ተቸጋሪዎችን ትደግፍ ነበር። ጳውሎስም ይህንኑ በጎነቷን ሲገልፅ “እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና” በማለት ምስክርነቱን ይሰጣል [ሮሜ 16፥2] የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ የተላከውንም መልእክት ያደረሰችው ከቆሮንቶስ ተነስታ ወደ ሮም ክርስቲያኖች ያደረሰችው እሷ ነች። በዚያ ዘመን ከቆሮንቶስ ተነስተው በሜዲተራኒያን ባህር አቋርጦ ወደ ሮም መጓዝ በባህር ላይ ከሚነሳ ማዕበል እስከ ወንበዴዎች አደጋ ድረስ ከፍተኛ ስጋት የነበረበት መንገድ ነበር። ፌበን ግን እግዚአብሔርን በሚፈራ ልቧና በወንጌል ፍቅር ተሞልታ የሐዋርያው ጳውሎስን ታላቅ የሮሜ መልእክት በአደራ ተሸክማ የሮምን አፈር ረገጠች። ጳውሎስም ለሮሜ አማኞች ሲጽፍ “ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።” በማለት በታላቅ አክብሮት አደራ ብሏቸዋል [ሮሜ 16፥2] በጥንቷ ቤተክርስቲያን ትውፊት መሠረት ደብዳቤ ይዞ የሚሄድ መልእክተኛ ደብዳቤውን ለጉባኤው ከማንበቡም በላይ የአንባቢዎችን ጥያቄ የመመለስና የተጻፈውን ትምህርት የማብራራት ኃላፊነት ነበረበት። ይህም ፌበን እጅግ ጥልቅ የሆነውን የጽድቅና የእምነት ትምህርት [የሮሜን መልእክት] በደንብ የተረዳች በመንፈሳዊ እውቀት የበሰለችና የታመነች አስተማሪ እንደነበረች እንመለከታለን ። የምዕራቡ ታሪክ ተመራማሪው ቤን ቪተሪንግተን Women in the Earliest Churches በተሰኘው ጥናታዊ መጽሐፉ ላይ ስለ ፌበን ሲገልጽ “ጳውሎስ ስለ ፌበን የተጠቀመበት ‘ፕሮስታቲስ’ [Prostatis] የሚለው ቃል በሮማውያን ባህል ውስጥ ከፍተኛ ማህበራዊና ቁሳቁሳዊ አቅም ያላቸውን ደጋፊዎች [Patrons] ለማመልከት የሚያገለግል ነው። ፌበን በባህር ወደብ ከተማ በሆነችው በክንክሬኦስ በራሷ ንግድ የምትተዳደር፣ ሀብታምና ያላትን ንብረት የወንጌል አገልጋዮችና ስደተኞችን ለመጠበቅና ለመደገፍ ያዋለች ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት ነበረች።” በማለት ሲያስቀምጥ፤ እንዲሁ በ3ኛው እና 4ኛው ክፍለ ዘመን የተሰበሰበው በጥንቷ ቤተክርስቲያን የስርዓትና የታሪክ ሰነድ[apostolic constitutions] ውስጥ የሴቶች ሚና በሚገለሰጸው በተለይ ስለ [ዲያቆናዊት] አገልግሎት ፌበንን እንደ ዋና መነሻ ይጠቅሳታል፦ “በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ፌበን እንደመሰከረው በጥንቷ ቤተክርስቲያን ያሉ አገልጋይ ሴቶች (ዲያቆናዊት) በንጽህና፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ ለተቸገሩት መጠጊያ በመሆንና የጥምቀት ስርዓትን በማግዝ የቤተክርስቲያንን አካል በታማኝነት ያገለግላሉ።” በማለት ያስቀምጣል። አሁን ዘመን ላለን ክርስቲያኖችም የእናታችን ፌበን ሕይወት የሚያስተምረን እውነት እግዚአብሔር ሰፊና ጥልቅ የሆነውን የወንጌል አደራ የሚሰጠው ታማኝ፣ ደፋርና ለቃሉ የተገዙ ልቦች ላሏቸው አገልጋዮቹ መሆኑን ነው። ዛሬም ቢሆን የተሰጠንን ጸጋና ሀብት ለጌታ ዓላማ በማዋል የፌበንን አርዓያነት መከተል እንችላለን። ¹-Ben Witherington III, "Women in the Earliest Churches" (1988) ²-Apostolic Constitutions, Book III, Section 15 https://t.me/orthodox_chrstianity

  • “አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ችግረኛና ምስኪን ነኝና።ቅዱስ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ፤ አምላኬ ሆይ፥ አንተን የታመነውን ባሪያህን አድነው። አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ማረኝ።የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።” መዝ 86፥1-4

  • "ሳይወሰን በማኅፀን ተወሰነ ሳይሰበሰብ በማኅፀን አደረ ሥጋዊ ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ እርሱ በማኅፀን ኖረ፡፡ በኪሩቤል ላይ የሚኖር እርሱ በሥጋ ወተት አደረ፡፡ የሚያቃጥል እሳት እርሱ ሥጋን ተዋሐደ ከሥውር በግልጽ ተወለደ በማኅፀንም ሕፃናትን የሚፈጥራቸው እርሱ ሕፃን ሆነ ብርሃንን የሚጐናጸፍ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፡፡ እንደ ምስኪን በድሃ ቤት አደረ እንደ ንጉሥ እጅ መንሻን ከርቀት ያመጡለት ዘንድ ሐዋርያትን ላከ፡፡ ላህም ጌታውን እንዲያውቅ የሚያደርገው እርሱ በበረት ተኛው፡፡ እንደ ሕፃን አደገ የሁሉ ጌታ እንደ መሆኑ ሰገዱለት፡፡ እንደ እግዚአብሔርነቱ እየሠራ እንደ ሰው ተመላለሰ፡፡"    ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ

  • https://youtu.be/4ISQ9W2Qi-0?si=9cyVmuH_yDD_zvGO

  • “ወጽአ እምድረ ካራን: ወቦአ ብሔረ ከነዓን: ተአመነ አብርሃም በእግዚአብሔር: እንበይነዝ ጽድቀ ኮኖ፡፡” በስመ ሥላሴ እየቀጠቅጥ ከይሴ እንኳን አደረሰን

  • 8 июл.491411

    + + + ማግባት ለሚሹ ወጣቶች + + + #የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦"ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡ ስለዚህ ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ፦ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊነቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡ አባቶች ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡ እናቶች ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡ እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡ እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡ የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡

  • ✝ስለ እርሱ አንብቡ ! እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለ እርሱ አብዝታችሁ አንብቡ 🌱 ▸እርሱን ለማወቅ ስለ እርሱ አንብቡ ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ ❓ ▸ ስለ እርሱ አንብቡ ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለ እርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ ። ነገር ግን ወደ #እርሱ_ጥልቀት_ለመግባት ወይም እርሱ #ወደ_እናንተ_ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ .. ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ ። ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ ❗️ በጽሑፎች ውስጥ ስለ እርሱ " ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል ..." [ መዝ 44*2]  የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት☀️ ታውቁ ዘንድ አንብቡ ። ▸ #እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለ እርሱ አንብቡ ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ ። ▸ ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰለሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "...እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው " [ መኃ 5*16] ትላላችሁ ። ▸ ከወደዳችሁት ስለ እርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ ። እግዚአብሔር ስለ እርሱ የሚያነቡትን ስለ እርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል ። ስለ እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ #እንደምትወዱት🥰 ታውቃላችሁ ። "      አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ☀️

  • በቲክቶካ ያግኙን https://www.tiktok.com/@bahiretibebat0?_r=1&_t=ZS-97amFLHdTZh

  • ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ይሰማኛል "ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ 😢 ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ። ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን ባዶነቴና ብቸኝነቴ ያስጨንቀኛል። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።" ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ

  • “እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት።እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ #ነፍስህንም ይጠብቃታል። ከዛሬ ጀምሮ #እስከ_ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።” መዝ 121 ፥5

  • ማለም አይከለከልም😊 👉 በጥራት እና በውበት የተገነባ የመኖርያ አፓርታማ 👉 ኦርቶክሳዊ ማኅበረሰብእ የመኖርበት ግቢ 👉 ሰርክ 2 ሰዐት ማታ የማኅበር ጸሎት ማድረጊያ አዳራሽ 👉 ለህፃናት በመንፈሳዊ ነገሮች እየታነፁ የሚቆዩበት ማቆያ day care 👉 የአፓርታማዎቹ የብሎክ ስያሜ በአስተማሪ ትርጉም ይዘት ባላቸው 👉 24/7 የከርሰምድር ውሃ መብራት የማይቋረጥበት 👉 ለአዋቂዎች እና ልጆች መንፈሳዊና አለማዊ መጻሕፍት የያዘ ላይብረፘ መጫወቻ የተሟላለት 👉 የበገና አብነት ት/ት መማርያ የተሟላለት 👉 የነዋሪውን መረጃ ዳታ ከDigital id ጋር አሰላስሎ የሚይዝ በAI የታገዘ security 👉 አንድ ኦርቶዶክሳዊ የማኅበረሰብእ ኮምፓውንድ 👉 … ጨምሩበት እንደዚ እንገንባ እንዴ 😄

  • 1 ዜና መዋዕል 16:36 “ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤ እግዚአብሔር ይመስገን” አሉ። “

  • #1ሺህ221_ሁለንተናዊ_አስተዋፅኦዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገርና ለዓለም ሥልጣኔ ያበረከተቻቸውን 1,221 ሁለንተናዊ አስተዋፅኦዎች ። PDF➠https://t.me/Ayuzeyesus/87 ይህ ባለ #402_ገጽ_መጽሐፍ የተዘጋጀው በቅርቡ በመንግሥት በኩል በፓርላማም ሆነ በተለያዩ መድረኮች ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሀገርን ወደኋላ እንዳስቀረች ተደርጎ ለቀረበውና በተለይም ከፕሮቴስታንት ምሁራን ለተሰነዘሩ እውቀታዊ ያልሆኑ ሀሳቦችና የሀሰት ትረካዎች ቀጥተኛ፣ ሳይንሳዊና ታሪካዊ ምላሽ ለመስጠት ነው። መጽሐፉ ስሜታዊነትን አስወግዶ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከዩኔስኮ (UNESCO) እና ከዓለም አቀፍ የአካዳሚክ ዳታቤዞች (እንደ JSTOR እና Google Scholar) በተገኙ ይፋዊ ስታቲስቲክሶችና የውሂብ ማህደሮች ላይ የተመሰረተ ነው። የሀሰት ትረካን የሚሰብሩት 13ቱ የምርምር ምሰሶዎች (The 13 Pillars) ​ምሰሶ ፩➠ምህንድስና፣ ስነ-ህንጻና ከተማ ምስረታ (95 ነጥቦች) ​የምህንድስና ጥበብና ከተማ ምስረታን በተመለከተ በሀገሪቱ ያሉ የዋሻና የውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሲታነጹ የመሬት ስበትን፣ የድንጋዩን ጥንካሬና የርዝመት መለኪያዎችን (የቤተክርስቲያን ክንድ እና ስንዝር) ለማስላት የተጠቀሙበት የጂኦሜትሪና የስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ ስሌት ሙሉ በሙሉ ከገዳማት የፈለቀ ነው። ​የከተማና የከተሜነት መሠረትን በማስመልከት አንድን አገር አገር የሚያደርጉት ከተማ ምስረታ፣ የሕግና የሥርዓት መሠረቶች በአንድ ጀምበር የተፈጠሩ ሳይሆኑ በቤተ ክርስቲያን ማሕፀን ውስጥ ተኮትኩተው ያደጉ መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ ያሳያል። ​ምሰሶ ፪➠ህክምና፣ ስነ-አእምሮና የዕፅዋት ሳይንስ (90 ነጥቦች) ​ሀገር በቀል የሕክምና ሳይንስን በምናይበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖታዊ አገልግሎት ባለፈ በሰው ኃይል ልማት እና በሕክምና ዘርፍ የራሷ የሆነ ጥልቅ አሻራ አላት። በጥንታውያን የብራና መጽሐፍት ውስጥ የተመዘገቡ የዕፅዋት ሳይንስ (Botany) እውቀቶች ለማኅበረሰቡ አካላዊና ስነ-አእምሯዊ ፈውስ ሲሰጡ የኖሩ ሳይንሳዊ እሴቶች ናቸው። ​ምሰሶ ፫➠ ኢኮኖሚ፣ ፋይናንስና ማክሮ-ተቋማት (100 ነጥቦች) ​የመጀመሪያው የማይክሮ-ፋይናንስ መሠረትን በሚመለከት በቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚመሠረቱት ማኅበራትና ሰንበቴዎች፣ አባላቶቻቸው በየወሩ የሚሰበስቡትን ንብረትና ገንዘብ የሚመዘግቡበትና ለችግረኛ የሚያከፍሉበት የራሳቸው የሒሳብ ሥርዓት ነበራቸው። ​የፋይናንስ አስተዳደርና መዝገበ ሒሳብን በአውድ ደረጃ ስንመረምር እንደ አካሱም ጽዮንና ላሊበላ ያሉ ታላላቅ አድባራት ለነገሥታቱ የግብር፣ የርስትና የንብረት ቁጥጥር የሚያገለግሉ "የመዝገበ ሒሳብ" Accounting Ledger አሠራሮችን በመቅረጽ የመጀመሪያውን የተደራጀ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት ዘርግተዋል። ​ምሰሶ ፬➠ ህግ፣ ፍትህና ህገ-መንግስታዊ አስተዳደር (95 ነጥቦች) ​የተጻፈ ሕግና የፍትሕ ሥርዓትን (ፍትሐ ነገሥት) በተመለከተ አውሮፓውያን የዌስትፋሊያ ስምምነትን ከመፈራረማቸውና ፕሮቴስታንቲዝም ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት፣ ሀገሪቱ በፍትሐ ነገሥት አማካኝነት የዳበረ የፍትሐ-ብሔርና የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የነበራት ሲሆን "የመጽሐፍ ቤት" ሊቃውንትም የመጀመሪያዎቹ የሕግ ፋኩልቲዎች ነበሩ። ​ሕገ-መንግሥታዊ መሠረቶችና የቢሮክራሲ ባህልን በማስመልከት "ሥርዓተ መንግሥት" እና "ክብረ ነገሥት" የነገሥታትን ሥልጣንና ሹመት የሚወስኑ ጥንታዊ የአስተዳደር ሕጎች ሲሆኑ፣ "ጸሐፌ ትእዛዝ" የተሰኘው መዋቅር ደግሞ የዳበረ የመንግሥት ቢሮክራሲ መኖሩን ያረጋግጣል። ከዚህም በላይ የንጉሡን ፍጹም አምባገነንነት የሚገታ "መብራተ መንግሥት" እና የዳኝነት ነፃነትን የሚያረጋግጡ ሕጎች ነበሩ። ​ሰብዓዊ መብቶችና የመማጸኛ ቦታዎችን በምናይበት ጊዜ ምዕራባውያን ባርነትን በሕግ በምስራቅና ምዕራብ በሚያጸኑበት ዘመን፣ ፍትሐ ነገሥት የባሪያዎችን ሰብዓዊ ክብርና ነፃ መውጫ ድንጋጌዎችን ያስቀመጠ ሲሆን ገዳማትና አድባራት ደግሞ ጥንታዊው የጥገኝነት መብት (Right to Asylum) የሚከበርባቸው "የማማጸኛ ቦታዎች" ነበሩ። ​ምሰሶ ፭➠ ስነ-ምህዳር፣ የአካባቢ ጥበቃና ግብርና (95 ነጥቦች) ​የአየር ንብረት ትንበያና ሜትሮሎጂን በሚመለከት ሊቃውንቱ አራቱን የንፋስ አቅጣጫዎችና የአየር ባህሪያት ከዓመቱ ወቅቶችና ከባሕረ-ሐሳብ ቀመር ጋር በማጣመር ገበሬው መቼ መዝራትና ማጨድ እንዳለበት መመሪያ ይሰጡ የነበረ ሲሆን ይህም የመጀመሪያው የግብርና ካላንደር ነው። ​የውኃ ዑደት (Hydrology) ትንተናን በተመለከተ "መጽሐፈ አክሲማሮስ" ውኃ ከምድር ተንኖ እንዴት ደመና እንደሚሆን፣ በዝናብ መልክ ተመልሶ ምድርን እንዴት እንደሚያረካና ወንዞች ወደ ባህር እንዴት እንደሚፈሱ የሚተነትን ፍጹም የተፈጥሮ ሳይንስ እውቀትን ይዟል። ​ምሰሶ ፮➠ ትምህርት፣ ስነ-ልሳንና የሰው ሃይል ልማት (100 ነጥቦች) ​የእውቀትና የትምህርት ተቋም መሠረትን በማስመልከት ሳይቋረጥ ከሊቅ ወደ ደቀ-መዝሙር ለሁለት ሺህ ዓመታት የተላለፈው የአብነት ትምህርት ሥርዓት፣ ሀገሪቱ ጠንካራና የማይናወጥ የትምህርት ተቋም እንደነበራት ትልቅ ማረጋገጫ ነው። ​ስነ-ልሳንና የግዕዝ ፊደላት ድንቅ መዋቅርን በምናይበት ጊዜ ኢትዮጵያ የራሷ ፊደልና የዳበረ የቋንቋ መዋቅር ባለቤት እንድትሆን ያደረገችው ቤተ ክርስቲያን ስትሆን፣ ሰባቱ ድምፆች ከሰው ልጅ የድምፅ መውጫና ከድምፅ ሞገድ ፊዚክስ ጋር ፍጹም የተገናኙ ናቸው። ምሰሶ ፯➠ የቁጥር ሳይንስ፣ ስነ-ኮከብና የዘመን አቆጣጠር (85 ነጥቦች) ​ባሕረ ሐሳብና አገር በቀል ሒሳብን በተመለከተ በ፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተቀረጸውና እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ምንም ስህተት የሚሠራው "ባሕረ ሐሳብ" ረቂቅ የሒሳብና የሥነ-ፈለክ ቀመር መኖሩን ትልቅ ማረጋገጫ ሲሆን፣ ተማሪዎች ያለምንም ካልኩሌተር ረቂቅ አሃዞችን በአእምሮአቸው የማስላት (Mental Mathematics) ብቃት አላቸው። ​የ፲፫ቱ ወራትና የፀሐይ ዑደት ቀመርን በማስመልከት ሊቃውንቱ የፀሐይን ዑደት በ365 ቀናት ከ6 ሰዓት በመከፋፈል፣ ትርፏን 6 ሰዓት በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በጳጉሜን ወር ላይ 6ኛ ቀን አድርገው በመደመር የወራትን ዑደት ሳያዛባ ሁልጊዜ መስከረም ፩ ላይ እንዲጸና ያደረጉ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን በዓለም ላይ የራሷ Calendar ያላት ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር አድርጓታል። ​የሰማይ አካላት ምደባና የግርዶሽ ትንበያን በምናይበት ጊዜ "አቡሻህር" በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ አማካኝነት ምዕራባውያን ቴሌስኮፕን ሳያውቁ በፊት የከዋክብትን ጉዞ በመገመት "ፅኑዓት" እና "ከርታቲ" በማለት ፈርጀዋል፤ የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰትበትን ጊዜም አስቀድመው ይተነብዩ ነበር። ​የግዕዝ ቁጥሮች ፍጹም ሳይንሳዊ መዋቅርን በሚመለከት ከሮማን ቁጥሮች በተሻለ መልኩ በአሥርዮሽ መደብ (Base-10 System) ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ለረቂቅ የሒሳብ ስሌቶችና ዛሬ ለዘመናዊው ኮምፒውተር ኮዲንግ (Unicode) እጅግ አመቺ ናቸው። ​ምሰሶ ፰➠ ዲፕሎማሲ፣ ስነ-ልቦናና ብሄራዊ ሉዓላዊነት (95 ነጥቦች)

  • ​ሉዓላዊነትና ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በሚመለከት ኢትዮጵያ ከግብፅ፣ ከሮም፣ ከፖርቱጋልና ከኢየሩሳሌም መንግሥታት ጋር ያደረገቻቸው የዲፕሎማሲ ደብዳቤዎችና ስምምነቶች በገዳማት ተጠብቀው የኖሩ ሲሆን፣ የውጭ መልእክተኞች ሰብዓዊና ሕጋዊ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚደነግገው ሕግ ጥንታዊው የዲፕሎማሲ መብት (Diplomatic Immunity) መተግበሪያ ነበር። ​የሰላም ዲፕሎማሲና ዕርቅን በተመለከተ በተለያዩ የጦር መሪዎችና ጎሳዎች መካከል ግጭት ሲነሳ የገዳማት አባቶች መስቀልና ታቦት ይዘው በመካከላቸው በመግባት ደም መፋሰስን ያስቆሙና ዘላቂ ሰላም ያወርዱ ነበር። ​ምሰሶ ፱➠ ፍልስፍና፣ ስነ-ምግባርና ስነ-ማህበረሰብ (90 ነጥቦች) ​ጥልቅ የፍልስፍና ድርሳናትን በማስመልከት "መጽሐፈ ፊሎን" የሰማይና የምድርን ፍጥረት ውበት ከሒሳብና ከጂኦሜትሪ ሕግጋት ጋር በማገናኘት የሰውን ልጅ የማሰብ አድማስ የሚያሰፋ ጥልቅ የፍልስፍና ድርሳን ሲሆን፣ "አውደ ነገሥት" ደግሞ የሰዎችን ባህሪ ከተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች ጋር በማገናኘት የሚተነትን ጥንታዊ የስነ-ልቦና እውቀትን ይዟል። ​ምሰሶ ፲➠ ስነ-ፅሁፍ፣ ታሪክና ማኑስክሪፕቶግራፊ (100 ነጥቦች) ​ታሪካዊ ቅደም-ተከተልና ሜታዳታ (Metadata) አወቃቀርን በምናይበት ጊዜ መጻሕፍት መቼ፣ በማን ዘመንና በየትኛው የከዋክብት ዑደት እንደተጻፉ መጨረሻቸው ላይ የማስፈር ባህል ዛሬ በኮምፒውተር ሳይንስ "Metadata" የሚባለው መረጃን የማደራጀት የላቀ ሥርዓት ጥንታዊ ማሳያ ነው። ​ምሰሶ ፲፩➠ ኪነ-ጥበብ፣ ስነ-ስዕልና ውበት ሳይንስ (85 ነጥቦች) ​የማይክሮ ግራፊና የጂኦሜትሪ ውሕደትን በተመለከተ በብራና መጻሕፍት ዳርና ዳር ላይ የሚሰሩት ረቂቅ የንድፍ ቅርጾችና ስዕሎች ዝም ብለው ለጌጥ የተሰሩ ሳይሆኑ፣ ፍጹም የሆነ የጂኦሜትሪ ስሌትና የሒሳብ መለኪያዎችን የተከተሉ የውበት ሳይንስ መገለጫዎች ናቸው። ​ምሰሶ ፲፪➠ የዜማ ሳይንስ፣ ኦዲዮ-አኮስቲክስና ስነ-ግጥም (96 ነጥቦች) ​የቅዱስ ያሬድ የዜማ ሳይንስን በማስመልከት የያሬድ ዜማ (ግዕዝ፣ ዕዝል፣ አራራይ) ዝም ብሎ ድምፅ ሳይሆን ጥብቅ የሆነ የሒሳብ ምትና ስልት (Rhythm and Metric System) ያለው ሲሆን የዜማ ምልክቶቹም (ይዘት፣ ርክረክ፣ ሒደት…) የድምፅን መውረድና መውጣት የሚወስኑ የጂኦሜትሪ ምልክቶች (የሙዚቃ ኖታ) ናቸው። ​የበገና ክርና የሞገድ ሒሳብን በምናይበት ጊዜ የበገና አስሩ ክሮች የሚታሰሩበትና የሚቃኙበት ስልት ፍጹም የድምፅ ሞገድ ሒሳብን (Audio Acoustics) የተከተለ መሆኑን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ያረጋግጣሉ። ​ምሰሶ ፲፫➠ አለም አቀፋዊው የኢትዮጵያዊነት ንቅናቄ (100 ነጥቦች) ​የዓለም ሳይንስ መጋቢነትን (መጽሐፈ ሄኖክ) በተመለከተ በዓለም ላይ ሙሉ ይዘቱ በግዕዝ ቋንቋ ብቻ ተጠብቆ የቆየው ጥንታዊው የሄኖክ መጽሐፍ ስለ ሰማይ አካላት ብርሃንና ስለ አጽናፈ-ዓለም መስፋፋት የሚተነትን የሥነ-ፈለክ ድርሳን ሲሆን፣ ዛሬም የዓለም ሳይንቲስቶች ይህንን ለማጥናት ወደ ገዳማት ይመጣሉ። ​ፍጹም የሥልጣኔ ባለቤትነትን በማስመልከት ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል፣ የራሷ ቁጥርና የራሷ የዘመን አቆጣጠር ካላንደር ያላት ብቸኛ ጥቁር አገር እንድትሆን ያደረገችው ይህንን ሥልጣኔ ከከዋክብት እሰከ ምድር ጠብቃ ያቆየችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት። PDF➠https://t.me/Ayuzeyesus/87

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • በሆነ ሽግግር ወቅት የሚደርሱ ግ*ድ*ያ*ዎች እንደ አጋጣሚ (incident) ሊታዩ ይችላሉ። በቋሚነት ከሆነ ግን ሥርዓታዊ (systemic) ሆኗል። የአርሲ ሰቆቃ በአፈጻጸሙም በአያያዙም ወገን የለየ የሥርዓታዊ ጥቃት ማሳያ የው።የተለመደ አቀራረብ (trend)ም አለው። ፩. ኦርቶዶክሳውያን በግፍ ይወድቃሉ። ፪ ምዕመኑ ቁጣውን ያሰማል። ይቆጫል። ይናገራል። ከመንግሥትና ቤተ ክህነት በኩል ፀጥ። ፀጥ። ድፍጥ። ድፍጥ። ፫. ከዚያ ቤተክህነቱ ተጎትጉቶ ለዘብተኛ መግለጫ ያወጣል። ፬. የሃይማኖት ተቋማት "በሁሉም ወገን" ለተጎዱት "ኀዘኑን" ገልጾ አጣሪ ልዑክ ልኬያለሁ/እልካለሁ ይላል። ፭. ስለጉዳዩ "መረጃ የሌለው" የዞኑ መንግሥት "ባልተፈጸመ ነገር የዞኑን ስም በሚያጠፉ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ" በቲክቶከር ጎብኝዎች ታጅቦ መግለጫ ይሰጣል። ያስፈራራል። ይረሳሳል። እንዝላለን። በዚህ መካከል ሌላ ዙር ተገፍዖ ይመጣል። አዙሪት! ሥርዓታዊ አዙሪት! የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን የሰቆቃ አዙሪት! መፍትሔውም ከልብ የሆነ የመንግሥታዊ አስተዳደር መዋቅሩን የፈተሸ ሥርዓታዊ ምላሽ ነው። እንደ መንግሥት፥ማድፈጥና ለአፍ ማላቀቂያ የሚሆን false equivalence እስኪገኝ ሸምቆ መቆየት አይደለም።

  • без подписи