tgindex
بنت مراد (BINT MURAD)

بنت مراد (BINT MURAD)

Статистика
@bint_muraadарабский

اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
244
−1 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
58
21 постов
Вовлечённость
23,8%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
8
1/48двое суток
9
1/72трое суток
9

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • አላህን መገናኘት ከሚወዱ ሰዎች አላህ ያድርገን።

  • 🔒ጥያቄ ❔ በሱረቱ አል-ከህፍ ውስጥ የተጠቀሰዉ የአስሃቡል ከህፍ ታሪክ ብቻ ነው ? ⚡️የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

  • 🚩 የብሄሬን ካላገባሁ አትበል | ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ #EthioMuslim

  • 2 авг.531из islamic_tube9

    ወደ ሲራው እንመለስ 💫💫💫ክፍል 22💫💫💫💫 «ስለ 3 ነገሮች ጠይቁት ከመለሰላችሁ ነብይ ነው። ካልመለሰ ግን ግደሉት። በጥንት ዘመን ከወገኖቻቸው ተነጥለው ስለወጡ ወጣቶች ምን እንደደረሰባቸው ጠይቁት።አስደናቂ ታሪክ አላቸውና፣ ምድርን ከምስራቅ እስከ መእራብ ድረስ በመዞር ስለሚያስሰው ሰውም ጠይቁት፣ ስለ መንፈስም (ሩህ) ምን እንደሆነች ጠይቁት።»             ነድር ወደ መካ ሲመለስ «የኛንና የሙሀመድን ጉዳይ የምንለይበት ነገር ይዘንላችሁ መጥተናል።» አለና የአይሁድ ሀይማኖት አዋቂዎች ያሉትን ነገራቸው።ቁረይሾች የአላህን መልእክተኛ (ሰዐወ) ስለሶስቱም ጉዳዮች ጠየቁ።ከቀናት በኋላ (ሱረቱል ከህፍ) ወረደ።በዚህ ምእራፍ ውስጥ የነዚህ ወጣቶች ታሪክ ሰፍሯል።አስሀበል ከህፍ (የዋሻው ባለቤቶች) ይባላሉ።   አገር የሚያስሰው ሰው ታሪክም ተወስቷል።እርሱም « ዙል ቀርነይን»ይባላል።መንፈስን በሚመለከትም (በአል ኢስራእ ) ምእራፍ መልስ ተሰጠ።የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እውነተኛ ነብይ መሆናቸውን ቁረይሾች ተረዱ።ግና በዳዮች ክህደትን እንጂ አሻፈረን አሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ የአቡ ጧሊብና የጎሳቸው አቋም ከላይ ያየነው ጣኦታዊያን ይፈፅሙት የነበረውን ነው።አቡ ጧሊብ በበኩላቸው ነብዩን (ሰዐወ) አሳልፈው እንዲሰጡ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀረበላቸው።የቁረይሾች እንቅስቃሴ የርሳቸውን ጥበቃ በመዳፈር ነብዩን (ሰዐወ) ለመግደል መወሰናቸውን ያመለክታል።ዑቅበት ቢን አቢ ሙዐይጥ፣ ዑመር ቢን ኸጧብና አቡ ጀህል ያደረጓቸው የግድያ ሙከራዎች ለአብነት ይጠቀሳሉ።በመሆኑም አቡ ጧሊብ የበኒ ሀሽምና የበኒ ሙጦሊብ ጎሳዎችን በመሰብሰብ ለነብዩ (ሰዐወ) ጥበቃ እንዲያደርጉ ተማፀኗቸው።በዐረብ የጥበቃ ባህል መሰረት ነብዩን (ሰዐወ) ለመጠበቅ ሙስሊሞችም ሙስሊም ያልሆኑትም የዚህ ጎሳ አባላት ፈቃደኛ  ሆኑ። ከካእባ ዘንድ በመሄድም ቃል ኪዳን ተጋቡ።ወንድማቸው አቡ ለሀብ ብቻ ከዚህ ውል ራሱን አግልሎ ከቁረይሾች ጋር ወገነ። ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ አጠቃላይ ማእቀብ የግፍ ሰነድ የቁረይሾች ግራ መጋባት ጨመረ።የሞከሩት ብልሀት ሁሉ አልሰራላቸውም።በኒ ሀሽሞች እና በኒ ሙጦሊቦች የሆነው ቢሆን ነብዩን (ሰዐወ) ከጥቃት ለመከላከል እና ለመጠበቅ ቁርጥ ውሳኔ አድርገው ፀንተዋል።በመሆኑም ቁረይሾች ከ«መኽሰብ»ሸለቆ ውስጥ ከበኒ ኪናናህ መስክ ላይ በመሰባሰብ በበኒ ሀሽምና በበኒ ሙጦሊብ ጎሳዎች ላይ ማህበራዊ ማእቀብ ለመጣል፣ አድማ ለማድረግ ወሰኑ።አድማው ከእነሱ ጋር አለመጋባትን፣አለመገበያየትን፣አለመቀራረብን፣አለመቀላቀልን፣ወደ ቤቶቻቸው አለመግባትን እና አለማናገርን ያጠቃልላል።የአላህን መልእክተኛ (ሰዐወ) ይገድሏቸው ዘንድ አሳልፈው እስከሚሰጧቸው ድረስ ማእቀቡ ይቀጥላል።ውሉን በሰነድ ላይ አሰፈሩት።        ነብዩን (ሰዐወ) ለግድያ አሳልፈው እስኪሰጡ ድረስ ከበኒ ሀሽም ጋር ምንም አይነት የእርቅ ሀሳብ ላይቀበሉ እና ርህራሄም ላይኖራቸው ሰነዱ ላይ አሰፈሩ። ውሉ ተፅፎ ከካእባ መሀል ተንጠለጠለ።የበኑ ሀሽም እና የበኑ ሙጦሊብ ሰዎች አቡ ለሀብ ሲቀር አማኞችም ያላመኑትም በሰባተኛው አመተ ነብይነት በሙሀረም ወር የመጀመሪያ ሌሊት ወደ አቡ ጧሊብ ሸለቆ ውስጥ ሄደው ሰፈሩ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ በአቡ ጧሊብ ሸለቆ ውስጥ ለሶስት አመታት ማእቀቡ በረታ።የሚላስ የሚቀመስ ጠፋ።ጣኦታዊያን ወደ መካ የሚገቡ ምግቦችን ሁሉ ፈጥነው በመግዛት ይቆጣጠሩባቸዋል።ችግሩ በርትቶ ቅጠሎችንና ቆዳዎችን ለመብላት ተገደዱ።እንስቶቻቸው እና ህፃናቶች  ከረሀብ የተነሳ ከሸለቆው ውስጥ ሆነው የሚያሰሙት የሰቆቃ ድምፅ ከሸለቆው ባሻገር  ይሰማ ነበር። በሚስጥር ካልሆነ ምንም ነገር አይደርሳቸውም ነበር።በተከበሩት ወራት (አሽሁረል ሁሩም) ካልሆነ አንዳች ነገር ለመሸመት ከሸለቆው አይወጡም ነበር።ያኔም የሚገዙት ወደ መካ የሚገባውን ቅፍለት ጠብቀው ነው።እርሱንም ቢሆን ቁረይሾች የማይችሉትን ዋጋ በመቆለልና  በመጫረት ይሸምቱባቸዋል። ሀኪም ቢን ሂዛም አልፎ አልፎ ለአክስቱ ለኸዲጃ ስንዴ ይወስድላት ነበር።አንድ ቀን አቡ ጀህል መንገድ ላይ ያዘው።አበል በኽተር ጣልቃ ገብቶ አስለቀቀው።እህሉን ለአክስቱ አደረሰላት። አቡ ጧሊብ ለአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ህይወት በጣም ይፈሩ ነበር።ሰወች ሁሉ ሲተኙ የአላህን መልእክተኛ (ሰዐወ) ከፍራሻቸው ላይ እንዲተኙ ያደርጋሉ።ምን አልባትም ሊገድላቸው የሚመጣ ሰው ካለ በግልፅ ሊያይ በሚችልበት መልኩ።ሰው ሁሉ ከተኛ በኋላ ግን ከልጆቻቸው፣ ከወንድሞቻቸው ወይም ከአጎቶቻቸው ልጆች አንዱን ከርሳቸው ፍራሽ ላይ እንዲተኛ ያዙና እርሳቸው ቦታ ቀይረው እንዲተኙ ያደርጉ ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እና ሙስሊሞች በሀጅ ወቅት እየወጡ ከሰወች ጋር በመገናኘት ወደ ኢስላም ጥሪ ያደርጉ ነበር።አቡ ለሀብ ይፈፅመው የነበረውን መጥፎ ድርጊት ከዚህ ቀደም አይተናል። ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ የውሉ መፍረስ ይ   ቀ     ጥ        ላ          ል እስከ👉 ክፍል 20 👈 እዚህ ሊንክ ላይ ይገኛል። 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

  • 🔒ጥያቄ ❔ በቁርአን ውስጥ የሚገኘው ረጅሟ ሡራ ሡረቱል በቀራህ ናት? ⚡️የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

  • 31 июл.414из islamic_tube9

    اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد ﷺ، وعلى آله وصحبه أجمعين.❤️

  • ወደ ሲራው እንመለስ 💫💫💫ክፍል 20💫💫💫💫 «የወንድሜ ልጅ ሆይ፤ ዘርህና ቤተሰብህ ከእኛ ዘንድ የተከበረ እንደሆነ ታውቃለህ።በወገኖችህ ላይ ከባድ ነገር አምጥተሀል ። ህብረታቸውን በትነሀል።አስተሳሰባቸውን ቂላቂል አድርገሀል።አማልክቶቻቸውን እና ሀይማኖታቸውን አነውረሀል።ከአያት ቅድመ አያት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው እምነት ክደሀል።ስለሆነም በጥሞና አድምጠኝ። ሀሳብ አቀርብልሀለሁ።ምን አልባትም ትቀበለው ይሆናል።» የአላህ መልእክተኛም (ሰዐወ)« አበል ወሊድ ሆይ፤እየሰማውህ ነው »አሉት።እንዲህ አለ፡ «የወንድሜ ልጅ ሆይ፤በዚህ ባመጣህው አዲስ እምነት የምትፈልገው ገንዘብ ከሆነ ከሁላችንም የበለጠ ሀብታም እናደርግሀለን።የምትሻው ልቅናም ከሆነ አለቃችን እናደርግሀለን።ያለ ፈቃድህ ምንም ነገር አንፈፅምም።የምትፈልገው ንግስና ከሆነ ንጉሳችን እናደርግሀለን።ይህ የሚገለፅልህ ነገር ልትቋቋመው የማትችለው በሽታ ከሆነም ሀኪም እንፈልግልሀለን።ከርሱ ትፈወስ ዘንድም ያለንን ገንዘብ ሁሉ  እናወጣለን። » ንግግሩን ሲያጠናቅቅ መልእክተኛው «አበል ወሊድ ሆይ፤ጨረስክን? »አሉት።«አወ» አላቸው።«እንግዲያውስ ስማኝ» አሉት ። «እሽ እየሰማውህ ነው» አላቸው።የሚከተለውን የቁርአን መልእክት አነበቡለት። «حم@ تنزيل من الرحمان الرحيم@ كتاب فصلت ءاياته قرءانا عربيا لقوم يعلمون@ بشيرا ونذيرا فأعرض أكثرهم فهم لا يسمعون@ وقالو قلوبنا فى أكنة مما تدعونا إليه وفى ءاذاننا وقر ومن بيننا وبينك حجاب فاعمل إننا عملون@ (سورة فصلت) » «ሀ፣ሚም።(ቁርአን)እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ ከሆነው (አምላክ) የተወረደ መልእክት ነው።አንቀፆቹ ግልፅ የተደረጉና የተብራሩ የሆነ መፅሀፍ ነው።በዓረበኛ ቋንቋ የወረደ ቁርአን ነው።ለሚያውቁ ሰዎች አብሳሪና አስፈራሪም ነው።ይሁንና አብዛኞቹ (መልእክቱን ከማስተንተን እና ከመተግበር) ሸሽተዋል። እነሱ ፈፅሞ አይሰሙም።«ልቦናችን በመሸፈኛወች ውስጥ ናቸው።ወደርሱ ከምትጠራን እምነት (ተጋርደዋል) ። ከጆሮወቻችንም ውስጥ ድንቁርና አለ።በእኛና በአንተ መካከልም ግርዶ አለ።በመሆኑም አንተ (የምትሻውን)ስራ እኛም (የከጀልነውን) እንሰራለን።አሉ። የአላህ መልእክተኛ(ሰዐወ) ንባባቸውን ቀጠሉ።ዑትበት እጆቹን ወደ ኋላ አድርጎና እነርሱን ተደግፎ የአላህን ቃል በፀጥታ አደመጠ።የአላህ መልእክተኛ(ሰዐወ) ከሰጅዳህ ቦታ ላይ ሲደርሱ ሱጁድ ወረዱ።ከሱጁድ ሲነሱም «አበል ወሊድ ሆይ፤ የሰማኸውን ሰምተሀል።የሚበጅህን ወስን።አሉት።ዑትባህ ወደ ባልንጀሮች ሲሄድ ከፊሎቹ  «በአላህ እንምላለን፤ አበል ወሊድ የተመለሰው በሄደበት ገፅታ አይደለም።»አሉ።ከአጠገባቸው ደርሶ ሲቀመጥ «አበል ወሊድ ሆይ፤ ምን ይዘህ መጣህ?»ሲሉ ጠየቁት።«በአላህ እምላለሁ፤አስደናቂ መልእክት አድምጨ ተመለስኩ።እንዲህ አይነት ቃል ሰምቼ አላውቅም።በአላህ እምላለሁ፤ግጥምም፣ድግምትም፣ጥንቆላም አይደለም።ቁረይሾች ሆይ፤ እባካችሁ ስሙኝ።ለዚህ ሰው እንቅፋት አትሁኑበት ተውት።በአላህ እምላለሁ፤ የሰማሁት ቃል ታላቅ ዜና ሳይሆን አይቀርም።ሌሎቹ አረቦች ካጠቁት ያለናንተ ተሳትፎ የፈለጋችሁት ተፈፀመ።በዓረቦች ላይ የበላይነትን ካገኘ ደግሞ የእርሱ መንገስ የናንተ መንገስ ነው።ክብሩ ክብራችሁ ነው።በርሱ አማካኝነት ከማንም በላይ ደስተኞች ትሆናላችሁ።             «አበል ወሊድ ሆይ፤ በምላሱ ደገመብህ» አሉት። «የእኔ አስተያየት ይህ ነው።እናንተ ግን ያሻችሁን ማድረግ ትችላላችሁ»አለ። በሌላ ዘገባ እንደተወሳው ዑትበት የአላህን መልእክተኛ (ሰዐወ) ንባብ በጥሞና አደመጠ። «ከሸሹ እንደ ዓድና ሰሙድ (ህዝቦች) ያለችን ጩኸት (ጥቃት) አስጠነቅቃችኋለሁ።ከሚለው የአላህ ቃል ላይ ሲደርሱ የማስጠንቀቂያው መቅሰፍት ወዲያውኑ እንዳይከሰት በመፍራት ከተቀመጠበት ፈጥኖ ተነሳና የአላህን መልእክተኛ (ሰዐወ) አፍ በእጁ ይዞ «በአላህና በዝምድና እማፀንሀለሁ»አላቸው።ወደ ወገኖቹ በመመለስም ከላይ የተገለፀውን ቃል ነገራቸው። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ የቁረይሽ ባላባቶች ከመልእክተኛው (ሰዐወ) ጋር መደራደር ስለመፈለጋቸውና አቡ ጀህል ሊገድላቸው ስለማሰቡ ቁረይሾች በመልእክተኛው ምላሽ ተስፋ አልቆረጡም።ምክንያቱም ግልፅ እምቢታ ወይም እሽታ አላዘለም።እናም ባላባቶቹ ከተመካከሩ በኋላ ለመደራደር ወሰኑ።አንድ ቀን ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ከካእባ ጀርባ ላይ ተቀምጠው የአላህን መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲመጡ መልእክት ላኩባቸው።ሲመጡ ዑትበት ያቀረበላቸውን የማባበያ ሀሳብ ደግመው አቀረቡላቸው መልእክተኛውም (ሰዐወ) የዚህ ሰው እንዳልሆኑ፣ የአምላክን መልእክት የሚያደርሱ መሆናቸውን፣ ይህን መልእክት ከተቀበሉ በዚህችም በመጭውም አለም ተጠቃሚወች እንደሚሆኑ፣ አሻፈረን ካሉ ግን አላህ ፍትሃዊ ውሳኔውን እስኪያመጣ ድረስ እንደሚታገሱ አብራሩላቸው። ጣኦታዊያኑም እውነተኛ ነብይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ተአምር ጠየቋቸው።«እናምንህ ዘንድ አምላክህን፣ ተራራውን በመግፋት አገሩን እንዲያሰፋ፣ ወንዞችም እንዲያፈስባት፣ ሙታንንም ህያው እንዲያደርግ ጠይቀው» አሏቸው።የነብዩ (ሰዐወ) ምላሽ ግን ካለፈው የተለየ አልሆነም። ቅጣትም ጠየቋቸው።«ሰማይን ቆርሶ እንዲያወርድ አድርግ»አሏቸው።ነብዩም (ሰዐወ) «ይህ በአላህ እቅድና ፈቃድ የሚሆን ነው። ከፈለገ ይፈፅመዋል።»የሚል ምላሽ ሰጡ።ጣኦታዊያኑ ይህን ምላሽም አልተቀበሉም።ይባስ ብለው ዛቱባቸው።አስጠነቀቋቸው።ነብዩም (ሰዐወ) በሀዘን ስሜት ተሞልተው ተመለሱ። የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ሲመለሱ አቡ ጀህል በትእቢት እንዲህ አለ፡ «ቁረይሾች ሆይ፤ ሙሀመድ እንደምታዩት ሀይማኖታችንን ከማነወርና አባቶቻችንን ከመስደብ፣ አስተሳሰባችንን ከማጣጣልና አማልክቶቻችንን ከማንቋሸሽ ውጭ ሌላ ነገር አሻፈረኝ ብሏል።እኔ በበኩሌ አቅሜ የሚችለውን ያህል ድንጋይ ይዤ እጠብቀውና ሱጁድ ሲያደርግ በርሱ አናቱን እፈጠፍጠዋለሁ።ያኔ አሳልፋችሁ ስጡኝ።ወይም ተከላከሉልኝ።ወገኖቹ በኑ አብዱል መናፍም ያሻቸውን ያድርጉ።» «በአላህ እንምላለን፤ ለክፉ ነገር ፈፅሞ አሳልፈን አንሰጥህም ። ያሰብከውን ፈፅም።»አሉት።በቀጣዩ ቀን ጠዋት አቅሙ የቻለውን ያህል ትልቅ ድንጋይ በመያዝ የአላህን መልእክተኛ(ሰዐወ) ተቀምጦ ይጠብቃቸው ጀመር።የአላህ መልእክተኛ(ሰዐወ) ዘወትር እንደሚያደርጉት ማልደው በመምጣት መስገድ ጀመሩ።ቁረይሾች የአቡ ጀህልን ድርጊት ለመመልከት በጠዋቱ ተሰባስበዋል።መልእክተኛው(ሰዐወ) ሱጁድ ሲወርዱ አቡ ጀህል ድንጋዩን አነሳና ወደ መልእክተኛው(ሰዐወ) አመራ።ከአጠገባቸው ሲደርስ................................... ይ   ቀ     ጥ        ላ          ል

  • 🔒ጥያቄ ❔ በቁርአን ውስጥ የሚገኘው ረጅሟ ሡራ ሡረቱል በቀራህ ናት? ⚡️የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

  • 28 июл.494из ibrahim_furii

    ከማህበራዊ ሚዲያ እብደትና ሱስ ስታገግም... በርካቶች ቀድመውህ የራቀ ጉዞ እንደተጓዙ ታያለህ። አንደኛው ቁርዓን ሲሃፍዝ፣ ሌላው መሠረታዊ የእስልምና እውቀቶችንና ልዩ ልዩ ጥበቦችን ሲቀስም አንተ ግን ስልክህ ላይ እንደተደፋህ ጊዜህ በከንቱ ያልፋል፤ ዕድሜህ ሲነጉድ እንኳ አይሰማህም። በአንተና በመቃብርህ መካከል ግን የቀረችው አንዲት እርምጃ ብቻ ልትሆን ትችላለች! t.me/ibrahim_furii

  • ⭕️ይህ መልዕክት ለሱና ቻናል ባለቤቶች ⭕️ ➲ ቻናላችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ  መልክ ጀምረናል 🛑በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥       ➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች ላላቸው  ⚡️ የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

  • ወደ ሲራው እንመለስ 💫💫💫ክፍል 19💫💫💫💫 በሀይልም ጨመቁት።እንዲህም አሉ።«ዑመር ሆይ ፤አላህ ለወሊድ ቢን ሙጊራህ ያከናነበውን አይነት ውርደት እስኪያከናንብህ ትጠብቃለህን?፣ አላህ ሆይ ዑመር ቢን ኸጧብ እነሆ፣አላህ ሆይ፤እስልምናን በዑመር ቢን ኸጧብ አበርታ።» «ዑመርም ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለና አንተም የአላህ መልእክተኛ መሆንህን እመሰክራለሁ።»በማለት ሰለሙ። በቤቱ ውስጥ የነበሩ ሁሉ ድምፃቸው ከመስጊዱ እስኪሰማ ድረስ ተክቢራ አደረጉ።       ዑመር ማጎብደድ የማያውቁ ብርቱ ሰው  ነበሩ።የእርሳቸው መስለም ጣኦታውያንን ውርደት አከናነባቸው።ለሙስሊሞች ደግሞ ክብርን፣ጉልበትንና ደስታን ጨመረላቸው። ኢብን ኢስሀቅ እንደዘገቡት ዑመር እንዲህ ብለዋል። «በሰለምኩ ጊዜ ከመካ ሰወች መካከል ለአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ይበልጥ ጥላቻ  ያለው ማን እንደሆነ ሳስብ አቡጀህል ሆኖ አገኘሁት።ወደቤቱ ሄድኩና በሩን አንኳኳሁ።ወጣና «ቤት ለእንግዳ ምን አመጣህ» አለኝ ። «በአላህና በመልእክተኛው ሙሀመድ እንዳመንኩ ፣ እሱ ያመጣውን መልእክት እውነት ብየ እንደተቀበልኩ ልነግርህ ነው አመጣጤ» አልኩት።«አላህ ያዋርድህ።ያመጣህውም ነገር የተዋረደ ይሁን።»አለና በሩን ከፊቴ ላይ በሀይል ዘጋብኝ።» ኢብን ሂሻምና ኢብኑል ጀውዚ በዘገቡት በሌላ ዘገባ እንደተወሳው ዑመር በሰለሙ ጊዜ ከጀሚል ቢን መዕመር አልጀመሂ ዘንድ ሄዱና መስለማቸውን ነገሩት።ወሬ  በማሰራጨት ከቁረይሽ ሰወች ይበልጥ ፈጣኑ ነበር።«ኢብነል ኸጧብ ከወገኖቹ ሀይማኖት አፈነገጠ»በማለት ጮሆ ተናገረ።ዑመርም ከኋላው ሆነው «ውሸቱን ነው በእርግጥ ሰልሜአለሁ»አሉ።ተረባረቡባቸው።እስከ እኩለ ቀን ድረስም ሲፋለሙ ዋሉ።በመጨረሻም ዑመር ደከማቸውና ተቀመጡ።ሌሎች እንደቆሙ ነበሩ ዑመር እንዲህ አሉ።«ያሻችሁን ማድረግ ትችላላችሁ ፤በአላህ እምላለሁ፤ቁጥራችን ሶስት መቶ ቢደርስ ወይ እኛ ወይ እናንተ ይቺን ሀገር ለቀን እንሄድ ነበር።»ከዚህ በኋላ ጣኦታዊያን ሊገድሏቸው ወደ ቤታቸው ተመሙ።ቡኻሪ እንደዘገቡት አብደላህ ቢን ዑመር ተከታዩን አስተላልፈዋል።ዑመር ጥቃት እንዳይደርስባቸው በመስጋት ከቤት ውስጥ ተቀምጠው እያለ አል አስ ቢን ዋኢል አሰሀሚ አቡ አምር መጣ።በሀር የተቀመቀመ ልብስ ተጎናፅፏል።የበኒ ሰህም ሰው ነው።በኒ ሰህም በቅድመ ኢስላም አጋሮቻችን ነበሩ።«ምን ሆነህ ነው?» በማለት ዑመርን ጠየቃቸው።«ስለሰለምኩ ወገኖችህ ሊገድሉኝ አስበዋል» አሉት። እርሱም «ማንም አይነካህም።»አላቸው።ሲወጣም በርካታ ሰወችን አገኘና «ወደ የት እየሄዳችሁ ነው?»አላቸው።«ኢብነል ኸጧብ ከወገኖቹ ሀይማኖት አፈንግጧል።»አሉት።«ማንም እንዳይደርስበት» አለ። ሰወች ይሄን ቃሉን ሊጥሱ አልደፈሩም። በጣኦታዊያን በኩል የነበረው ሁኔታ ከላይ የተጠቀሰውን ይመስላል።በሙስሊሞች ወገን በኩል የነበረውን በተመለከተ ሙጃሂድ ኢብን አባስን በመጥቀስ እንደዘገቡት« «አል ፋሩቅ» በሚል ስያሜ የተጠሩት ለምንድን ነው?»ስል ዑመርን ጠየኳቸው።«ሀምዛ ከእኔ ሶስት ቀን ቀደም ብለው ሰለሙ።»በማለት ጀምረው የመስለማቸውን ታሪክ ካወሱ በኋላ በመቋጫው ላይ እንዲህ አሉ። «በሰለምኩ ጊዜ «የአላህ መልእክተኛ ሆይ፤ብንሞትም በህይወት ብንኖርም በእውነት ላይ አይደለንምን?»በማለት ጠየኳቸው።«አወ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ።ብትሞቱም በህይወት ብትኖሩም በእውነት ላይ ናችሁ።»አሉኝ።«ይህ ከሆነ ታዲያ መደበቅ ለምን አስፈለገ?በእውነት በላከህ ጌታ እምላለሁ፤ ይፋ እንወጣለን አልኳቸው።በሁለት ረድፍ ተሰልፈን ሀምዛ አንድኛውን እኔ ደግሞ በሌላኛው ረድፍ እየመራን አደባባይ ወጣን።ወደተከበረው መስጂድም ገባን።ቁረይሾች ከዚያን ቀን በፊት አግኝቷቸው የማያውቅ ሀዘንና ውርደት አገኛቸው።የዚያን ቀን የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) «አል ፋሩቅ» በማለት ሰየሙኝ።» ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ብለዋል።«ዑመር ከመስለማቸው በፊት ካእባ ውስጥ መስገድ አንችልም ነበር።» ሱሀይብ ቢን ሲናን አልሩሚ እንዳስተላለፉት ዑመር በሰለሙ ጊዜ እስልምና ይፋ ሆነ።በይፋ ወደ እርሱ ጥሪ ተደረገ።በአላህ ቤት ዙሪያ ተቀመጥን።ጠዋፍም አደረግን።የሚገላምጠንን ተጋፈጥን።ለተንኮሉም በከፊል ምላሽ መስጠት ቻልን።አብደላህ ቢን መስዑድ እንዲህ ብለዋል «ዑመር ከሰለሙበት እለት አንስቶ የተከበርን ሆነናል።» ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ የቁረይሽ ልዑክ ከአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ዘንድ ሁለቱ ጀግኖች ፣ ማለትም ሀምዛ ቢን አብዱል ሙጦሊብ እና ዑመር ቢን ኸጧብ ከሰለሙ በኋላ ዳመናው ይገፈፍ ጀመር።ጣኦታዊያን በሙስሊሞች ላይ ሰቆቃ ከማዝነብ ስካራቸው በመንቃት ለነብዩ (ሰዐወ) የሚፈልጉትን ሁሉ በመስጠት ጥሪያቸውን ያቆሙ ዘንድ ለመደራደር ወሰኑ።ፀሀይ ብርሀኗን የምትረጭበት አለም ሁሉ ከነብዩ (ሰዐወ) ጥሪ አንፃር የትንኝ ክንፍ ያህል የሚመጥን ዋጋ እንደሌለው እነዚህ ሚስኪኖች አላወቁም ነበር።     ቢን ከእብ ቀረዚን በመጥቀስ ኢብን ኢስሀቅ እንደዘገቡት ዑትበት ቢን ረቢዓህ (ባላባት ነው) አንድ ቀን ከቁረይሾች ጋር እያለ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ብቻቸውን ከመስጂድ ውስጥ በተቀመጡበት «ቁረይሾች ሆይ፤ ከሙሀመድ ዘንድ ሄጄ ምንአልባትም ማባበያወችን አቅርበንለት ያሻውን እንዲወስድና ከጥሪው ይታቀብልን ዘንድ ላናግረውን?»አለ።ይሄ የሆነው ሀምዛ መስለማቸውና የነብዩ ባልደረቦች ቁጥራቸው እየጨመረ መሄዱን ባዩ ጊዜ ነው።«አባ ወሊድ ሆይ፤ ሂድና አናግረው» አሉት።ዑትበት ተነስቶ ሄደና ከመልእክተኛው (ሰዐወ) አጠገብ በመቀመጥ እንዲህ አላቸው..................................... ይ   ቀ     ጥ         ላ            ል

  • አላህ ያየኛል የምትል ሴት እና እነ እገሌ ያዪኛል የምትል   هَلْ يَسْتَوِيَانِ مَثَلًا

  • ከ70አመት ኢባዳ በኋላ አቧራ የሚያስለብስ ስራ ⁉️ መካሪ መስሎ ሸይጧን ስንቱን አክፍሯል❕❕ ማሳሰቢያ 👇👇 ደቂቃው 18:00 ብቻ ነው። t.me/bint_muraad

  • ወደ ሲራው እንመለስ 💫💫💫ክፍል 18💫💫💫💫 ሀምዛ ከአቡ ጀህል ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት ማንንም አላናገሩም።ወደ መስጂድ ሲገቡ አገኙት።ከበላዩ እያንዣበቡ«የወንድሜን ልጅ ትሳደባለህን? እኔ የእርሱን ሀይማኖት ተቀብያለሁ።»አሉና ከግንባሩ ላይ በቀስት ደጋን መተው ክፉኛ ፈነከቱት።ከበኑ መኽዙም የሆኑ ሰወች የአቡ ጀህል ወገኖች ዘለው ተነሱ።የበኑ ሀሽም ሰዎችም የሀምዛ ወገኖች ዘለው ተነሱ።አቡ ጀህል «አቡ አምርን ተውት ፤የወንድሙን ልጅ አስከፊ ስድብ ሰድቤበት ነው።»አለ።         ሀምዛ የሰለሙት ስጋቸው የሆነ ሰው ሲሰደብ እና ሲዋረድ የመጠቃት ስሜት ተሰምቷቸው ቢሆንም አላህ ልባቸውን ለእስልምና ክፍት አደረገው። የማይበጠሰውን የእምነት ገመድ አጥብቀው ያዙ።በርሳቸው መስለም ሙስሊሞች ከፍተኛ ክብርና ብርታት አገኙ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ የዑመር ኢብኑል ኸጧብ መስለም በግፍና በጥመት ጭጋግ በተሸፈነው በዚህ ድባብ ውስጥ ከመጀመሪያው ይበልጥ የደመቀ ብልጭታ ተከሰተ።እርሱም የዑመር ኢብኑል ኸጧብ መስለም ነው።ዑመር የሰለሙት በስድስተኛው አመተ ነብይነት፣ በወርሃ ዙል ሂጃ ፣ ሀምዛ በሰለሙ በሶስተኛው ቀን ነበር።ነብዩ (ሰ ዐ ወ) ዑመር እንዲሰልሙ ዱዓ አድርገው ነበር።ይኸውም  «አላህ ሆይ ፤እስልምናን ከሁለት ዑመሮች መካከል ከአንተ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ በሆነው አበርታው።በኡመር ኢብኑል ኸጧብ ወይም በአቡ ጀህል ኢብኑ ሂሻም።»         ከሁለቱ ሰዎች መካከል ከአላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ዑመር ቢን ኸጧብ መሆናቸው ተረጋገጠ። ዑመር በሀይለኝነትና በጉልበተኝነት ይታወቃሉ።በሙስሊሞቹ ላይ ብዙ እንግልት አድርሰዋል።ከውስጣቸው ሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ይታገሉ ነበር።አንደኛው የአያት ቅድመ አያታቸውን ልምድና ባህል የማከበር ስሜት ሲሆን ፣ ሁለተኛው ሙስሊሞች ለእምነታቸው ሲሉ ያን ሁሉ መከራ መሸከማቸው እና ጥንካሬአቸው የፈጠረባቸው የአድናቆት ስሜት ነበር።በተጨማሪም የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት ከሌሎች ይበልጥ የላቀ እንደሆነ ይሰማቸው ጀምሯል።በዚህ ምክንያት ሲቆጡ ቁጣቸው ብዙ አይቆይም።ወዲያውን ይበርዳሉ።የሰለሙበት ሁኔታ እንደሚከተለው እናቀርባለን። አንድ ቀን ከቤታቸው ውጭ ለማደን አሰቡ።ወደ ተከበረው መስጂድም መጡ።ከካእባ ግርዶ ውስጥም ገቡ።ነብዩ (ሰ ዐ ወ)  በመስገድ ላይ ነበሩ።«አልሀቀህ» የተባለውን ምእራፍ ማንበብ ጀመሩ።ዑመርም ቁርአኑን ያደምጡ ጀመር።የቃላት አወቃቀሩ ፣ የአረፍተ ነገር አሰካኩ አስደመማቸው። ክስተቱን ሲያወሱ እንዲህ ብለዋል።   «ይህ ሰው እውነትም ቁረይሾች እንዳሉት ገጣሚ ነው ስል አሰብኩ።ወዲያው وما هو بقول شاعر قليلا ما تؤمنون (   የገጣሚ ቃል አይደለም። ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ የሚል አንቀፅ አነበቡ።እንግዲያውስ ጠንቋይ ነው።ስል አሰብኩ።ወዲያውም ولا بقول كاهن قليلا ما تذكرون «የጠንቋይ ቃልም አይደለም።ጥቂትን ብቻ ትገሰፃላችሁ ? تنزيل من رب العالمين ከአለማት ጌታ የወረደ መልእክት ነው» የሚለውን አንቀፅ እስከ ምእራፉ መቋጫ ድረስ አነበቡ።በዚህ ጊዜ እስልምና ወደ ልቦናየ መስረፅ ጀመረ።        እስልምና ወደ ልባቸው መስረፅ የጀመረበት የመጀመሪያው ክስተት ይሄ ነበር።ይሁንና የመሀይምነት ዘመን ጭፍን ወገንተኝነት እና ተከታይነት እንደዚሁም በአያት ቅድመ አያት እምነት የመኩራራት ስሜት ወደ ቀልባቸው የሰረፀውን ጥቂት እውነት በማሸነፉ ዑመር ለውስጥ ጥሪያቸው ጆሮ ሳይሰጡ ፀረ ኢስላም ድርጊታቸውን ገፉበት።በባህሪያቸው ሀይለኛና ለአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ)  ያላቸው ጥላቻ እጅግ የበረታ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ቀን ሰይፋቸውን ታጥቀው ነብዩን ለመግደል በማሰብ ወጡ።ኑዐይም ቢን አብደላህ የተባለ ሰው አገኛቸውና «ወደ የት እየሄድክ ነው?»አላቸው።«ሙሀመድን መግደል እፈልጋለሁ።»አሉ።ሰውየውም «ሙሀመድን ገድለህ ከበኒ ሀሽም እና ከበኒ ዘህራእ ብቀላ እንዴት ታመልጣለህ? »አላቸው።«ከወገኖችህ ሀይማኖት ያፈነገጥክ ትመስላለህ? አሉት።«ይበልጥ የሚያስገርምህን ነገር ላመላክትህን?እህትህና ባሏ ከሀይማኖትህ አፈንግጠዋል።»አላቸው።ዑመር ይህን ሲሰሙ በጣም ተቆጡ።ወደ እህታቸውና ወደ ባሏ ገሰገሱ።ኸባብ ቢን አል አረት ከእነርሱ ጋር ነበር።(ጧሀ) የተሰኘው የቁርአን ምእራፍ የተፃፈበትን ገፅ ይዘዋል።እርሱን እያስተማራቸው ነበር።ኸባብ የዑመርን ኮቴ ሲሰማ ተደበቀ። የዑመር እህት ፋጡማ በበኩሏ የቁርአን ፁሁፉን ደበቀችው።ዑመር ወደ ቤቱ ሲቃረቡ የኸባብን የቁርአን ንባብ ሰምተው ኑሯል።ወዲያው እንደገቡ «ይህ የሰማሁት መነባንብ ምንድን ነው?»ሲሉ ጠየቁ።«ወግ እያወጋን ነበር።»በማለት መለሱ።ዑመርም «ከወገኖቻችሁ ሀይማኖት አፈንግጣችሁ እንዳይሆን?»አሉ።እህታቸውም «ዑመር ሆይ እውነቱ ያለው አንተ ካለህበት ሀይማኖት ውጭ ቢሆንስ? »ስትል መለሰች።የዚህን ጊዜ ዑመር የእህታቸውን ባል ዘለው በሀይል ረገጡት እህታቸው መጣችና ከባሏ ልታስለቅቃቸው ሞከረች።በጥፊ መቷት ፊቷ ደማ።በሌላ ዘገባ እንደተወሳው ሲመቷት ተፈነከተች።የዑመር ድርጊት በጣም አበሳጫት።እንዲህ አለች «ዑመር ሆይ ፤እውነቱ ያለው አንተ ከምትከተለው ሀይማኖት ውጭ ነው።ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለ እና ሙሀመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።»አለች።ዑመር ተስፋ ቆረጡ ።ከእህታቸው ፊት ላይ ደም ሲፈስ ሲመለከቱም ተፀፀቱ።ሀፍረትም ተሰማቸው።«ከእናንተ ዘንድ ያለውን ፁሁፍ ስጡኝ እና ላንብበው አሉ።»እህታቸውም «አንተ ቆሻሻ ነህ ። ንፁሀን እንጂ አይነኩትም።ታጥበህ ና» አለቻቸው።ታጥበው ተመለሱ። ፁሁፉን ተቀብለው (በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው) የሚለውን መግቢያ አነበቡና «መልካም ባህሪያት ናቸው»አሉ።ከዚያም «ጧሀ» የሚለውን ምእራፍ «አላህ እኔ ነኝ።ከእኔ ሌላ አምላክ የለም።ስለሆነም አምልከኝ።እኔን ለማስታወስም ሶላትን ደንቧን ጠብቀህ ስገድ።እስከሚለው አንቀፅ ድረስ አነበቡና «እንዴት ያማረ እና የተከበረ ንግግር ነው?ከሙሀመድ ዘንድ ውሰዱኝ አሉ። ኸባብ የዑመርን ንግግር ሲሰማ ከተደበቀበት ወጣና «ዑመር ሆይ፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ሌሊት ያደረጉት ዱዓ ለአንተ እንደደረሰ ተስፋ አደርጋለሁ።አላህ ሆይ፤እስልምናን በዑመር ኢብኑል ኸጧብ ወይም በአቡ ጀህል ኢብኑ ሂሻም አጠንክር።በማለት ዱዓ አድርገው ነበር።አሁን ከሶፋ ስር ከሚገኘው ቤት ውስጥ ናቸው።አለ።         ዑመር ሰይፋቸውን ታጥቀው ወደ ተባለው ቤት ገሰገሱ።በሩንም አንኳኩ።ከሙስሊሞች መካከል አንዱ በቀዳዳ ወደ ውጭ ሲመለከት ዑመር መሆናቸውን አየ።ሰይፍ ታጥቀዋል።ለአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ነገሯቸው።ሰዎች ተሰበሰቡ።ሀምዛም «ምን ሆናችሁ? »ሲሉ ጠየቁ «ዑመር መጣ» አሏቸው ።«በሩን ክፈቱለት።አመጣጡ ለደግ ነገር ከሆነ እንሰጠዋለን።ለክፉ ከሆነ ግን በገዛ ሰይፉ እንገድለዋለን።»አሉ።የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ከውስጥ ወህይ እየወረደላቸው ነበር።ከነበሩበት ወጡና ዑመርን አገኙት።ልብሱን እና የሰይፉን ጫፍ በመያዝ ሳቡት።በሀይልም ጨመቁት። ከዚያም................................. ይ   ቀ     ጥ         ላ           ል

  • ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። ጥያቄ 1 💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?

  • ወደ ሲራው እንመለስ 💫💫💫ክፍል 17💫💫💫💫 ስቃይን የበለጠ ማበርታት እና በነብዩ (ሰ.ዐ. ወ) ላይ የግድያ ሙከራ ቁረይሾች ስደተኞችን ለመመለስ ያደረጉት ሙከራ ሲከሽፍባቸው እጅግ ተቆጡ።በቀሪ ሙስሊሞች ላይም የቅጣት መአት አዘነቡ።ወደ አላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) የክፋት እጃቸውን ዘረጉ።እንቅልፍ ከነሳቸው ሙግት ለመገላገል ሲሉ የአላህን መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)  ለመግደል አስበው እንደነበር ድርጊቶቻቸው ያስረዳሉ።          ሙስሊሞችን በተመለከተ መካ ውስጥ የቀሩት በጣም ጥቂቶች ነበሩ።እነርሱም አንድም የተከበሩና የሚከላከልላቸው ወገን ያላቸው አልያም የተከበረ ወገን ጥበቃ የተቸራቸው ናቸው።ይህም ሆኖ እስልምናቸውን ይደብቁ ነበር።በተቻለ መጠንም ከግፍ አራማጆች አይን ለመሰወር ይጥሩ ነበር።ሆኖም ግን ይህን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረጉ ግን ከጉዳት እና ከግፍ አላመለጡም። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በበኩላቸው ከግፈኞች ፊት አላህን ያመልኩ ነበር።ይህን ከማድረግ ምንም ነገር አያቅባቸውም።ምክንያቱም «የታዘዝከውን ግለፅ፣ከጣኦታዊያንም ራስህን አግልል» የሚለውን የአላህን ትእዛዝ የመተግበር እና መልእክታቸውን የማድረስ አካል ነውና።ይህም በመሆኑ ጣኦታዊያን ባሻቸው ጊዜ በርሳቸው ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ነበር።         የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሞገሳማ፣ አቡጧሊብም የታፈሩና የተፈሩ ሰው ከመሆናቸው ውጭ ፣ እንደዚሁም በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ አንዳች መጥፎ ነገር ቢያደርሱ ፍፃሜው ጥሩ እንደማይሆንና የበኒ ሀሽም ጎሳ በአንድ ሊያብርባቸው እንደሚችል ከመስጋታቸው ውጭ ላይ ላዩን ሲታይ በመልእክተኛው ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ የሚያቅባቸው ምንም ነገር አልነበረም።ይሁንና ጣኦታዊ ስርአታቸው እየፈራረሰ እንደሆነ የሀይማኖት መሪነታቸውም አደጋ ላይ እንደወደቀ ሲሰማቸው እነዚህን ሁሉ ነገሮች ወደጎን በመተው እርሳቸውን መዳፈር ጀመሩ።       የታሪክ ምሁራን እንዳወሱት አንድ ቀን ዑተይባህ ቢን አቢ ለሀብ ከመልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና በነብይነታቸው መካዱን ገለፀ።ተተናኮላቸውም።ልብሳቸውንም ቀዶ ከፊታቸው ላይ ተፋባቸው።ግና ምራቁ ከእርሳቸው ላይ አልወደቀም።በዚህ ጊዜ «አላህ ሆይ፤ ከውሾችህ አንዱን ላክበት» በማለት ዱዓ አደረጉበት።የመልእክተኛውም (ሰ.ዐ.ወ) ዱዓ ተቀባይነት አገኘ።ዑትባህ አንድ ቀን ከተወሰኑ የቁረይሽ ሰዎች ጋር ሆኖ ጉዞ ወጣ።ሻም ውስጥ ዘርቃእ ከተባለ ቦታም ሰፈሩ።የዚያን ቀን ሌሊት አንበሳ ሲዞራቸው አመሸ።ዑትባህም «ወዮልኝ፤ በአላህ እምላለሁ፤ይህን አንበሳ የላከብኝ ሙሀመድ ነው።እኔን ለይቶ ይበላኛል።እርሱ መካ ውስጥ እኔ ሻም ውስጥ ሆነን ገደለኝ።»አለ።አንበሳውም ከሰዎች መሀል እርሱን ለይቶ አጠቃው።አንገቱን ይዞ ገደለው።የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ቀን ሱጁድ ላይ እያሉ ዑቅበት ቢን አቢ ሙኢጥ የተከበረ አንገታቸውን ረገጠው።አይኖቻቸው ከጉድጓዶቻቸው ተጎልጉለው እስኪወጡ ድረስም አስጨነቃቸው።             ግፈኞች ሊገድሏቸው አስበው እንደነበር ከሚያሳዩ ክስተቶች መካከል አንዱ የሚከተለው ነው።አብደላህ ቢን አምር ቢን አል አስ እንዲህ ይለናል። «የጣኦታውያን መሪዎች በአላህ ቤት ውስጥ ተሰብስበው እያለ መጣሁ።የአላህን መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጉዳይ አወሩ።«እንደዚህ ሰው ጉዳይ ምንም ነገር አልታገስንም።ያመጣብንን ጉድ ታግሰናል።» ተባባሉ።ይህን እያሉ እያለ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጡ።ሰዎችን አልፈው ሩክኑን (የተከበረውን መስጂድ ምሶሶ) ሳሙ።መስጂዱን እየጎበኙም በአጠገባቸው አለፉ።በንግግር እንደወጓቸው ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ገፅታ ተረዳሁ።ለሁለተኛ ጊዜም ሲያልፉ እንደዚሁ እንደሰደቧቸው ከገፅታቸው ተረዳሁ።ለሶስተኛ ጊዜ ሲያልፉ ሰደቧቸው።ቆሙና እንዲህ አሉ።«ቁረይሾች ሆይ፤ትሰማላችሁን?ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ፤በአደጋ አስጠነቅቃችኋለሁ።»ንግግራቸውን ሲሰሙ ሁሉም በራሪ ከአናቶቻቸው ላይ ያረፈች ይመስል አንገታቸውን ደፉ።ከመካከላቸው ብርቱው እንደምንም ወኔውን ሰብስቦ «አበል ቃሲም ሆይ፤ሂድ በአላህ እምላለሁ፤ አንተ መሀይም አይደለህም።»በማለት አባበላቸው።            በቀጣዩ ቀን ጠዋትም እንደዚሁ ተሰብስበው ስለርሳቸው ጉዳይ በመነጋገር ላይ እያሉ ሲመጡ ሁሉም በአንድነት ዘለሉና ከበቧቸው።አንደኛው የኩታቸውን ጫፍ ያዘ።አቡበክርም እያለቀሱ «አላህ አምላኬ ነው ስላለ ትገድሉታላችሁን?»በማለት ለመከላከል ሞከሩ።እነርሱም ከአጠገባቸው ተበተኑ።»ኢብን አምር እንዲህ ብለዋል። «ቁረይሾች የአላህን መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለመጉዳት ካደረጓቸው ጥረቶች ሁሉ በከፍተኛ ሁኔታ ተሳክቶላቸው ያየሁት ይህን ብቻ ነው። ቡኻሪ እንደዘገቡት ዑርወት ቢን ዙበይር እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል። ቢን አምር ቢን አልአስን «ጣኦታዊያን በነብዩ ላይ የፈፀሙት በጣም አስከፊ ነገር ምን እንደሆነ ንገረኝ።»በማለት ጠየኩት።እንዲህ አለ። «የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)  ካእባ ውስጥ በመስገድ ላይ እያሉ ዑቅበት ቢን አቢ ሙኢጥ ወደ እርሳቸው ሄደና ልብሱን በአንገታቸው ላይ አደረገ።በጣምም አነቃቸው።አቡበክር ትከሻውን ያዙና ገፍትረው አስለቀቁት።«አምላኬ አላህ ብቻ ነው ስላለ ትገድሉታላችሁን? »ሲሉም ተናገሩ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ የሀምዛ መስለም በግፍና በጠላትነት ጭጋግ በተሸፈነው በዚህ ሁኔታ መሀል መንገዱን በብርሀን የሞላ ብልጭታ ተከሰተ።እርሱም የሀምዛ ቢን አብዱል ሙጦሊብ መስለም ነው።ሀምዛ የሰለሙት በስድስተኛው ዓመተ ነብይነት ነው። ሀምዛ የሰለሙበት ምክንያት እነሆ፤ አንድ ቀን አቡጀህል በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አጠገብ አለፈ።ሶፋ ከተባለው ኮረብታ ላይ ነበሩ።አወካቸው።ሰደባቸው።የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አልመለሱለትም።ከራሳቸው ላይ በዲንጋይ ፈነከታቸው።ደማቸው ፈሰሰ።አቡጀህልም ከርሳቸው በመለየት ከካእባ አጠገብ ከቁረይሽ ስብስብ መሀል ገብቶ ተቀመጠ።የአብደላህ ቢን ጀድአን አገልጋይ ሶፋ ላይ ካለ ቤቱ ውስጥ ሁና ትእይንቱን ትከታተል ነበር።ሀምዛ ከአደን ሲመለሱ ያየችውን ነገረቻቸው።ሙሉ የአደን ትጥቅ ታጥቀዋል።በጣም ተቆጡ እጅግ የተከበሩና የታፈሩ ብርቱ ወጣት ነበሩ።ፍጥነታቸውን ጨምረው ገሰገሱ። አቡጀህል ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት ማንንም አላናገሩም።ወደ መስጂዱ ሲገቡ አገኙት።በጣም ተናደው .......................................... ይ   ቀ     ጥ         ላ            ል

  • 22 июл.39из ahmedadem

    без подписи

  • ወደ ሲራው እንመለስ 💫💫💫ክፍል 16💫💫💫💫 ሁለተኛው የሀበሻ ስደት ነጃሽ ስደተኛ ሙስሊሞችን በመልካም ሁኔታ ማስተናገዱን ቁረይሾች መስማታቸው አንገበገባቸው።በሙስሊሞች ላይ የሚፈፅሙት ግፍ ፣ የሚያደርሱት ስቃይም በረታ።እናም የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሀቦቻቸውን ወደ ሀበሻ እንዲሰደዱ በድጋሚ ማዘዝ ግድ ሆነባቸው።ሁለተኛው ስደት ከመጀመሪያው ይበልጥ አስቸጋሪ ነበር።ምክንያቱም ቁረይሾች መረጃ ደርሷቸው ስለነበር ስደቱን ለማክሸፍ ተሰናድተው በንቃት ይጠብቁ ነበር። በአንፃሩ ሙስሊሞች በፍጥነት ከተማዋን  ለቀው መውጣት ነበረባቸው።አላህ ጉዞውን ገር አደረገላቸው።ጠላቶቻቸው ሳያገኟቸው በፊት ከመካ ወጥተው ወደ ሀበሻ ተጓዙ።ከነጃሺ ዘንድም በሰላም ደረሱ።የዚህ ስደት ተሳታፊዎች ቁጥር አማር ከመካከላቸው ካለ 83 ወንዶችና 18 ወይም 19 ሴቶች ነበሩ።ግና የአማር አብሮ መሰደድ በምሁራን ዘንድ በአጠራጣሪነት የተመዘገበ ነው። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ በሀበሻ ስደተኞች ላይ የቁረይሾች ሴራ ስደተኞች እምነታቸውን በነፃነት የሚያራምዱበት ጥላ ከለላ ማግኘታቸው ለቁረይሾች የሚዋጥ አልሆነም።እናም ሁለት ብልህና ጠንካራ ሰወችን በመምረጥ ለነጃሺና ለቀሳውስቱ ዳጎስ ያለ ስጦታ አስይዘው ወደ ሀበሻ ላኳቸው።እነዚህ መልእክተኞች አምር ቢን አልዓስ እና አብደላህ ቢን ረቢዓህ ይባላሉ።ሁለቱም በኋላ ላይ ሰልመዋል።            ሁለቱ መልእክተኞች ሀበሻ ከገቡ በኋላ መጀመሪያ ለቀሳውስቱ ስጦታቸውን በማደል ነጃሺ ስደተኛ ሙስሊሞችን ከሀገሩ እንዲያባርር መነሻ የሚሆኑ ምክንያቶችን አብራሩላቸው። ቀሳውስቱም ለነጃሺ ይህንኑ ምክር እንደሚለግሱ ከተስማሙ በኋላ ከነጃሽ ዘንድ በመቅረብ ስጦታውን አቀረቡለት።እንዲህ ሲሉም አናገሩት። «ንጉስ ሆይ፤ ወደ እርስዎ  ሀገር ቂላቂል ወጣቶች መጥተዋል።እነዚህ ወጣቶች ከወገኖቻቸው ሀይማኖት ያፈነገጡ ሲሆኑ ወደ እርስዎ ሀይማኖትም አልገቡም።እርስዎም እኛም የማናውቀው አዲስ ሀይማኖት አምጥተዋል።የተከበሩ አባቶቻቸው፣  አያቶቻቸው እና ጎሳወቻቸው እነዚህን ወጣቶች ወደ መጡበት እንዲመልሱ ከእርስዎ ዘንድ ልከውናል።የእነርሱን ጥፋት ወገኖቻቸው ከማንም በላይ ያውቃሉ።»ቀሳውስቱም «ንጉስ ሆይ፤እውነት ነው።  ለእነርሱ ያስረክቧቸው።ወደ ወገኖቻቸው፣ ወደ ሀገራቸው ይመልሷቸው።በማለት ድጋፋቸውን ገለፁ። ግና ነጃሺ ግራ ቀኙን በመስማት ጉዳዩን ለማጣራት በመወሰን ሙስሊሞችን አስጠሯቸው።መጡ።እነርሱ በበኩላቸው የሆነው ቢሆን እውነት ብቻ ለመናገር ተስማምተዋል።ነጃሺ፡ «ከወገኖቻችሁ እምነት በማፈንገጥ ከእኔ ወይም ከሌሎች ከሚታወቁ ሀይማኖቶች ሳትገቡ አዲስ የምትከተሉት  ሀይማኖት ምንድን ነው?»ሲሉ ጠየቋቸው። በዚያን ጊዜ ሙስሊሞችን ወክሎ እንዲናገር የተመረጠው ጀዕፈር ኢብኑ አቡ ጧሊብ እንዲህ በማለት ዘመን ተሻጋሪ እና ታሪካዊ ንግግር ተናገረ። «ንጉስ ሆይ፤ መሀይማን ህዝቦች ነበርን።ጣኦታትን እናመልካለን።በክት እንመገባለን።ፀያፍ ድርጊቶችን እንፈፅማለን።ዝምድናን እንቆርጣለን።በጎረቤት ላይ ክፉ እንውላለን።ከመካከላችን ጠንካራው ደካማውን ይበላል።በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እያለን አላህ ዘሩን፣እውነተኛነቱን፣ታማኝነቱንና ንፅህናውን የምናውቀውን መልእክተኛ አስነሳልን።ይህ መልእክተኛ አላህን በብቸኝነት እንድናመልክና እኛም ሆንን ወገኖቻችን ከአላህ ውጭ እናመልካቸው የነበሩትን ድንጋዮችና ጣኦታት ማምለክ እንድናቆም አስተማረን።እውነት እንድንናገር፣አደራን እንድናደርስ፣ዝምድናን እንድንቀጥል፣ጉርብትናን እንድናሳምር፣የሰውን ክብርና ደም እንድንጠነቀቅ አዘዘን።ከእኩይ ድርጊት፣ሀሰት ከመናገር፣የየቲምን ገንዘብ ያለ አግባብ ከመብላት፣ የንፁሀን ሴቶችን ስም በዝሙት ከማጥፋት እንድንቆጠብ አዘዘን።አላህን ብቻ እንድናመልክ፣ከእርሱ ጋር ሌላን አካል እንዳናጋራ አዘዘን።ሶላት እንድንሰግድ፣ዘካ እንድንሰጥ፣ፆም እንድንፆም  አዘዘን።ትምህርቱን አመንንበት። ይዞልን የመጣውን የአላህ ሀይማኖት ተቀብለን ተከተልነው።እናም አላህን በብቸኝነት አመለክን።ከእርሱ ጋር ምንንም ነገር ማጋራት አቆምን።እርም ያደረጋቸውን ነገር ታቀብን።የፈቀደልንን ብቻ ተጠቀምን።በዚህም ምክንያት ወገኖቻችን በጠላትነት ተሰየሙብን፣ቀጡን፣ከእምነታችን በሀይል ሊያስወጡን ታገሉ።ከአላህ አምልኮ ወደ ጣኦት አምልኮና ድሮ እንፈፅማቸው የነበሩ እኩይ ድርጊቶችን ወደ መፈፀም ሊመልሱን ጣሩ።በጨቆኑን፣በበደሉን እና መውጫ መግቢያ ባሳጡን ጊዜ በእኛና በሀይማኖታችን መካከል ግርዶ ባደረጉ ጊዜ ከሌሎች ሁሉ እርስዎን በመምረጥ ወደ ሀገርዎ ተሰደድን።ንጉስ ሆይ፤ከእርስዎ ዘንድ እንደማንበደል ተስፋ አደረግን።» ነጃሺም «ከአላህ ዘንድ የመጣ መልእክት አለህን?»ሲሉ ጠየቁ።ጀዕፈርም «አዎ» በማለት የመርየምን ምእራፍ የመጀመሪያ አናቅፅ አነበበ።በዚህ ጊዜ ነጃሺ ፂማቸው በእንባ እስኪርስ ድረስ አለቀሱ።ቀሳውስቱም የተነበበላቸውን የቁርአን መልእክት ሲሰሙ መፅሀፍቶቻቸው በእንባ እስኪርሱ ድረስ አለቀሱ።በመቀጠልም ነጃሺ ለአምር ቢን አልአስና ለባለንጀሮቹ «በአላህ እምላለሁ፤ይህ እና ኢሳ (እየሱስ) ይዞት የመጣው መልእክት ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ናቸው።ሂዱ በአላህ እምላለሁ አሳልፌ አልሰጣችሁም። »አሉ።መልእክተኞቹ ወጡ።አምርም ለአብደላህ ቢን ረቢዓህ «በአላህ እምላለሁ፤ነገ ጉዳቸውን የሚያጋልጥ ነገር እናገራለሁ።»አለ አብደላህ ቢን ረቢዓህም «እንዲህስ አታድርግ።ምንም እንኳ በእምነት ብንለያይም ወገኖቻችን ናቸው።»አለ።አምር ግን በውሳኔው ፀና። በቀጣዩ ቀን ጠዋት ለነጃሺ እንዲህ አላቸው።«ንጉስ ሆይ ፤ስለ እየሱስ ሊናገሩት የሚከብድ ነገር ይናገራሉ።»ነጃሺ ወደ ሙስሊሞች «ስለ እየሱስ ምን ትላላችሁ?» በማለት መልእክት ላኩባቸው።ሙስሊሞች ደነገጡ።ቢሆንም ግን የሆነው ቢሆን እውነቱን ለመናገር ተስማሙ።ወዲያው ከንጉሱ ዘንድ እንደገቡ ንጉሱ ፈጥነው ጠየቋቸው።ጃዕፈርም «ስለ እየሱስ የምናምነው ነብያችን የነገሩንን ነው።ይኸውም ኢሳ የአላህ ባሪያና መልእክተኛ ፣መንፈስና ወደ ድንግላዊት ማርያም ያኖረው ቃሉ ነው።»አለ።ነጃሺ ከመሬት ስንጥብ እንጨት አነሱና እንዲህ አሉ። «በአላህ እምላለሁ፤እየሱስ አሁን ከተናገርከው የዚችን እንጨት ታክል የተለየ አይደለም።»በዚህ ጊዜ ቀሳውስቱ አጉተመተሙ።ነጃሺም «ብታጉተመትሙም እውነቱ ይህ ነው።»አለ። ለሙስሊሞችም «ሂዱ በሀገሬ ውስጥ በሰላም ተቀመጡ።የሰደባችሁ ይቀጣል።የሰደባችሁ ይቀጣል።የሰደባችሁ ይቀጣል።ከእናንተ በአንዳችሁ ላይ ጉዳት አድርሼ ጋራ የሚያክል ወርቅ ባገኝ የምወድ አይደለሁም።»አሏቸው። ከዚያም ለባለሟሎቻቸው «ስጦታውን ለመልእክተኞቹ መልሱላቸው።አልፈልገውም።በአላህ እምላለሁ፤እኔ በዚህ ጉዳይ ጉቦ እቀበል ዘንድ አምላክ ንግስናየን ሲመልስልኝ ከኔ ጉቦ አልተቀበለም።ሰወችን በእርሱ ጉዳይ እታዘዝ ዘንድ እርሱ በኔ ጉዳይ ማንንም አልታዘዘም» አለ። ይህን ታሪክ የተረከችው ኡሙ ሰለማህ እንዲህ ትላለች።«መልእክተኞቹ ያመጡትን ስጦታ ተሸክመው በውርደት ተመለሱ።እኛም ከነጃሺ ዘንድ በሰላም ተቀመጥን።ጥሩ ጎረቤትም ሆኑን።⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ስቃይን የበለጠ ማበርታት እና በነብዩ (ሰ.ዐ. ወ) ላይ የግድያ ሙከራ............................................ ይ   ቀ     ጥ        ላ           ል

  • ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። ጥያቄ 1 💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?