ዝክረ ቅዱሳን (ርቱዓነ ሃይማኖት)
Статистикаይህ! ከዕለት ስንክሳር በመውሰድ፡ የነገረ ቅዱሳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት ቤተሰባዊ ምዕላድ ነው። "የቅዱሳንን ዜና ሕይወት(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል- ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/መጽሐፈ ምስጢር)
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 25
- Всего постов
- 44
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 23
- 1/48двое суток
- 26
- 1/72трое суток
- 28
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🍃 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። 🍃 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! +++"ጽንሰታ ለማርያም"+++ ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል። ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም…
የመልካም ነገሮች ሁሉ ጥጉ መጨረሻው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሠላም ቢባል የሠላም ጥግ ሠላማዊ እርሱ ነው። ቸርነት ቢባል የቸርነት ጥግ እርሱ ነው፡፡ ደስታ/ሐሴት ቢባል የደስታ/የሐሴት ጥግ እርሱ ነው። ለዚህም ነው ደስታ ብለን ያሰብናቸው ነገሮች ሁሉ ስንደርስባቸው ጎዶሎ የሚሆኑብን። ይህቺም ጎዶሎ በሁላችንም ውስጥ አለች! እኛም እንሠራለን እናተርፋለን ያኔ ደስተኛ እንሆናለን እንላለን! ነገር ግን ነግደን…
የመልካም ነገሮች ሁሉ ጥጉ መጨረሻው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሠላም ቢባል የሠላም ጥግ ሠላማዊ እርሱ ነው። ቸርነት ቢባል የቸርነት ጥግ እርሱ ነው፡፡ ደስታ/ሐሴት ቢባል የደስታ/የሐሴት ጥግ እርሱ ነው። ለዚህም ነው ደስታ ብለን ያሰብናቸው ነገሮች ሁሉ ስንደርስባቸው ጎዶሎ የሚሆኑብን። ይህቺም ጎዶሎ በሁላችንም ውስጥ አለች! እኛም እንሠራለን እናተርፋለን ያኔ ደስተኛ እንሆናለን እንላለን! ነገር ግን ነግደን አትርፈን ያሰብንበት ስንደርስ የጠበቅነውን ደስታ አናገኝም፡፡ "በቃ! አሪፍ ቤት ልግዛ ያን ጊዜ ደስታዬ ምሉዕ ከሆነ! " እንላለን። ይህም ያው ይሆንብናል። ትዳር ብይዝ ደስተኛ እሆናለውም እንላለን ፡ ትዳር ይዘን ስናየው ግን ያሰብነውን ደስታ እናገኘውም። እስቲ ልጅ እንውለድ ያንግዜ ደስታዬ ምሉዕ ከሆነ! እንላለን። ነገር ግን አሁንም ደስታውን በምልዐት እናገኘውም፡፡ ምክንያቱም ከእያንዳንዱ ደስታችን ጀርባ ሁለን ፀጥ የሚያደርግ እውነተኛ ሠላም እውነተኛ ደስታ/ሐሴት እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና። 💡አላወቅንም እንጂ በዚህ ሁሉ ደስታና ሃሴትን የማግኘት ረሃብና ጥማት፤ ቁፋሮና ፍለጋችን ግን ሁሉም የሚመሩን #ወደ_እርሱ_ነው፡፡ Alexander schememann For the life of the world በተባለ መጽሐፋቸው "Man is a hungry being. But he is hungry for God. Behind all the hunger of our life is God. All desire is finally a desire for Him." ብለዋል።
видео или голосовое, без подписи
“ርኩሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች“
https://youtu.be/OnPI7IQxZTo?si=JnMeDfWYF57WH2hi
видео или голосовое, без подписи
🍃 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። 🍃 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! +++"ጽንሰታ ለማርያም"+++ ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል። ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም…
🍃 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። 🍃 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! +++"ጽንሰታ ለማርያም"+++ ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል። ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ። "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።" (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4) ➫ ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል። 🌷#የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ #ቅዱስ_ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች #ቅድስት_ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር። ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም። የለመኑትን የማይነሳ ጌታችን በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች። ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ። እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ። እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ። ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ። "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች። "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም) +++"ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት"+++ ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ። በዚያም ጌታችን ከእነርሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ። የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር። የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን። ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት። አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው። "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው። ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ። ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ። "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው። እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ። ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ። ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና። በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው። (ማቴ. 16:16) ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ። ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)" ተሰጠው። 🍂 ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ:: ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ" ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም። +++"አፄ ናዖድ ጻድቅ"+++ 🍂 ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት። ከእነዚህ አንዱ ደግሞ #አፄ_ናዖድ ናቸው። ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ። ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል። ➫ ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .) የደረሷት እርሳቸው ናቸው። ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል። ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው። የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (ማርያም ክብራ): ልጆቻቸው (አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ። ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት። እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው። ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመንስ አታድርሺኝ" አሏት። በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን (መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም) ሊገባ እርሳቸው #ነሐሴ_7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል። 🍃 ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን። #ነሐሴ ፯/7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ ፩. #በዓለ_ጽንሰታ_ለእግዝእትነ_ማርያም ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቅዱስ ገብርኤል መበሥር ፬. ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ፭. አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) ፮. ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ) ፯. አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው። ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል። የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል።" (መዝ. ፹፮፥፩-፮) 🍃 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🍃
አኵሱም አቡነ ጰንጠሌዎን ገዳም አጠገብ የሚገኘው የቅድስት ማርያም መግደላዊት ገዳም
видео или голосовое, без подписи
#ነሐሴ_፮/6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ ፩. ቅድስት ማርያም መግደላዊት (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት) ፪. ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት (ዘቂሣርያ) ፫. አባ ዊጻ (የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር) ቅዱሳት እናቶቻችንን ያጸና ቸር አምላካቸው እኛንም በሃይማኖትና በምግባር ያጽናን ፡ ከበረከታቸውም አብዝቶ ያድለን። https://t.me/kidusentony
፨ "ልቡን ለእግዚአብሔር ቤትነት የሰጠ እግዚአብሔርም በመንግሥቱ ለእርሱ ቤት ይሰጠዋል" ፨ (saying of the desert fathers)
በሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት የምዕመናን አያያዝ (ኖላዊነት) ፡ የክህነት እና የምንኲስና አያያዝ ቀንተን ሞትን 'ኮ! 🥹 እኛስ ይህን የምናይ መች ይሆን?! ...
ወደ አንተ እንደተዘረጉ ያረጁ እጆች የተቀደሱ ናቸው።