ዶ/ር ምህረት ደበበ
Статистикаበዚህ ቻናል የተለያዩ የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ሀሳቦች ይነሳሉ፡፡ ✔የሳይኮሎጂ ምክር ✔አጫጭር ታሪኮች ✔የታዋቂ ሰዎች አጫጭር አባባሎች <<...ካመለጠ ትናንት ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል።...>>
- Последний пост
- 8 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://t.me/wallet/start?startapp=v2-b3BlcmF0aW9uPXJld2FyZHNfc3F1YWQmc3F1YWRJZD03MTEyOTQxNzE1NDgxMyZwcm9ncmFtSWQ9MyZjb2RlPVhXMzRBTlRNXzVN
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
💛Happy Mother's Day 💛 💙መልካም የእናቶች ቀን❤
አደራ ይነበብ!!! ታሪኩ ከረጅም ውጊያ በኀላ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ ስለተዘጋጀ አንድ ወታደር ነው ፡፡ ይህ ወታደር በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቹ ቤት ከመሄዱ በፊት ቤተሰቦቹ ጋር ስልክ ደወለ ፡፡ " እማዬ አባዬ ወደ ቤት ልመጣ ነው ፤ ነገር ግን አንድ ነገር እሺ እንድትሉኝ እጠይቃችኀለው ፡፡ ወደ ቤት አብሬ ይዤው መምጣት የምፈልገው ጓደኛ አለኝ ፡፡" ቤተሰቦቹ "ትችላለክ በንተዋወቀው ደስ ይለናል ፡፡" በማለት እሽታቸውን መለሱ ፡፡ ልጅ መናገሩን ቀጠለ "ግን ስለሱ ማወቅ ያለባችሁ ነገር አለ ፤ በወጊያ ላይ እያለ በጣም ተጎድቷል ፡፡ እጅና እግሩን በማጣቱ የቆመው እኔን ተደግፎ ነው ፡፡ እናም የሚሄድበት ስለሌለው ከእኔ ጋር መቶ አብሮን እንዲኖር እፈልጋለው ፡፡ " ቤተሰቦቹ " ይህን በመስማታችን በጣም እናዝናለን ልጄ ፤ ሌላ የሚኖርበት ቦታ በመፈለግ ልንረዳው እንችላለን ፡፡" በማለት መለሱ ፡፡ ልጅ በድጋሚ " አይደለም እማዬ አባዬ ከእኛ ጋር እንዲኖር እፈልጋለው ፡፡" አባት " ግን ልጄ እየጠየከን ያለውን ነገር አላወከውም ፡፡ እንደሱ አይነት አካል ጉዳተኛ ለእኛ ሸክም ነው ሚሆንብን ፡፡ እኛ የምንኖረው የራሳችን ህይወት አለን ፡፡ ስለዚህ እንደዚህ አይነት ነገር ህይወታችን እንዲረብሽ አንወድም ፡፡ ስለዛ ጓደኛክ እረስተክ እቤት መምጣት አለብክ ፡፡" ይህን ከተናገሩ በኀላ ልጅ ስልኩን ዘጋው ፡፡ ከእዛን ቀን በኀላ ቤተሰቦቹ ከልጃቸው ምንም አልሰሙም ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኀላ ቤተሰቦቹ ከፖሊስ ጣቢያ ተደውሎላቸው ልጃቸው ከፎቅ ላይ ወድቆ እንደሞተ ተነገራቸው ፡፡ ፖሊስ እራሱን አጥፍቶ ነው ብሎ አምኗል ፡፡ የልጁ ቤተሰቦች በከተማው ፖሊስ ጣቢያ ወዳለው የሬሳ ማስቀመጫ አመሩ ፡፡ የልጃቸውንም አስከሬን ለይተው አገኙት ፡፡ ነገር ግን ባዩት ነገር በጣም ደነገጡ ፡፡ ያ በልጃቸው እጅና እግር የለውም ተብለው የተነገራቸው ሌላ ሰው የገዛ ልጃቸው ነበር ፡፡ ወደ ቤት ከመሄዱ በፊት ቤተሰቦቹ ለእሱ የሚኖራቸውን አመለካከት ለመፈተሽ ነበር ጓደኛ በማለት የእራሱን አካል ጉዳተኛነት የነገራቸው ፡፡ # _የታሪኩ_መልክት ሁላችንም የሚያምርና ጤነኛ ሰውን ለመውደድ አንቸገርም ፤ ነገር ግን በመልክና ቁመና ደረጃ ለአይን ያልተመቸንን ሰው አንወድም ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከማያምሩ ፣ በጣም አሪፍና ጤነኛ ካልሆኑ ሰዎች እራሳችንን እናርቃለን ፡፡ በህይወት እስካለን ሁሉንም ሰው በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ይሁን ሰው በመሆኑ ብቻ እኩል ለናከብርና ለንወድ ይገባል ፡ 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
видео или голосовое, без подписи
ሃያ ምርጥ የማርቲን ሉተር አባባሎች 1. ‹‹ ሕልም አለኝ! ›› 2. ‹‹ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፡፡ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ፡፡ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ፡፡ ምንም ነገር ስታደርግ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ፡፡ ›› 3. ‹‹ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ጊዜ ሁል ጊዜ ትክክለኛው ሠዓት ነው፡፡ ›› 4. ‹‹ ከፍቅር ጋር ለመጣበቅ ወስኛለሁ፡፡ ምክንያምቱም ጥላቻ ሊሸከሙት የማይችሉ ታላቅ ቀንበር ነውና፡፡ ›› 5. ‹‹ በስተመጨረሻ ከጠላቶቻችን ንግግር ይልቅ የወዳጆቻችንን ዝምታ ነው የምናስታውሠው፡፡ ›› 6. ‹‹ በየትኛውም አካባቢ ያለ ህገወጥነት ለዓለም ፍትህ አደጋ ነው፡፡ ›› 7. ‹‹ እምነት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ›› 8. ‹‹ እውነተኛው የትምህርት ዓላማ አዋቂነት እና መልካም ባህሪን አንድ ላይ ማድረግ ነው፡፡ ›› 9. ‹‹ የማያልቀውን ተስፋ አጥብቀን በመያዝ የበዛውን ውድቀታችንን በፀጋ መቀበል አለብን፡፡ ›› 10. ‹‹ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ጨለማ ጨለማን አይገፍም፡፡ ጥላቻም በጥላቻ አይሸነፍም፡፡ ያን ማድረግ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ›› 11. ‹‹ በዓለም ላይ ከመሃይምነት እና ከጅልነት የበለጠ አደገኛ ነገር የለም፡፡ ›› 12. ‹‹ ጠላትን ጓደኛ ማድረግ የሚችለው ሃያሉ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ›› 13. ‹‹ ማንም ሠው ቢሆን ሕገወጥ ለሆኑ ህጎች ያለመገዛትና ያለመታዘዝ ሞራላዊ ሃላፊነት አለበት፡፡ ›› 14. ‹‹ ሁላችንም አብረን ተስማምተን ለመኖር መማር አለብን፡፡ አልያ ግን ልክ እንደ ጅል እርስበራስ መጨራረስ ሊኖርብን ነው፡፡ ›› 15. ‹‹ ይቅርታ ማድረግ በሆነ ጊዜ ላይ ብቻ የምናደርገው ሳይሆን ቋሚ የሆነ የሁልጊዜ አመለካከት መሆን አለበት፡፡ ›› 16. ‹‹ በዓለም ላይ እንደ ፍቅር ፅኑ እና ቋሚ ሃይል ምንም የለም፡፡ ›› 17. ‹‹ ታሪክ ሠሪዎች ሳንሆን በታሪክ የተሠራን የታሪክ ፍጡራን ነን፡፡ ›› 18. ‹‹ ጥላቻ ጠዪውን አጥፊ ነው፡፡ ›› 19. ‹‹ ነፃነት በጨቋኞች ነቃ ፈቃድ የሚገኝ ሳይሆን በጭቁኖች የሚፈለግና ሚጠየቅ ነው፡፡ ›› 20. ‹‹ ክዋክብቶችን ማየት የሚቻለው በጨለማ ብቻ ነው፡፡ ›› 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
видео или голосовое, без подписи
አንድ ወታደር ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ በውጊያ ሜዳ የወደቀ ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል። አለቃውም "በህይወት መኖሩ ለማይታወቅ ሰው ብለህ ህይወትህን አደጋ ላይ መጣል የለብህም" በማለት ይናገረዋል። ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል ከብዙ ፍለጋ በኋላ እራሱን በሞት ቀጠና ውስጥ መስዋዕት አድርጎ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል። አለቃውም: "ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሰው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ?" በማለት ይጠይቀዋል፤ ወታደሩ ግን ባደረገው ነገር ደስተኛ ስለነበር "አለቃዬ! ይህኮ ምንም ማለት አይደለም"...ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ እያለ ደርሼበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር " አለቃውም "ለመሆኑ ምን አለህ?" ብሎ ሲጠይቀው ወታደሩም እንዲህ ብሎ መለሰ... "እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ" ነበር ያለኝ ሰው ሰውን በአስቸጋሪ ሁኔታ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንደሚመጣለት እርግጠኛ ሆኖ ከጠበቀው እኛስ በምናልፍባቸው የህይወት ውጣ ውረዶች ፈጣሪ እንደሚመጣልን ለምን እርግጠኛ አንሆንም?... .....ይመጣል ይመጣል ይመጣል 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
በአንድ ወቅት ዝሆን ና ዉሻ በተመሳሳይ ጊዜ ላይ #አረገዙ...ከሶስት ወራት በኋላም ዉሻ ስድስት ግልገሎችን ወለደች..ስድስተኛዉ ወር ላይ መልሳ አረገዘች...በድጋሚ ዘጠነኛዉ ወር ላይ ደርዘን ግልገሎችን ወለደች:: አስራስምንተኛዉ ወር ላይ ወደ ዝሆን ጠጋ ብላ <<እኔ ምልሽ ግን እርግጠኛነሽ እርጉዝ ነሽ?.. ↩በተመሳሳይ ጊዜ ነዉ ያረገዝነዉ..ይሄዉ እኔ ብዙ ጊዜ ወልጀ ልጆቸ፡ራሱን የቻለ ትልቅ ዉሻ እየሆኑ ነዉ...አንቺ ግን አሁንም 'ርጉዝ ነሽ....ምንድን ነዉ ነገሩ??>> አለቻት:: ዝሆንም ድምፇን ለስለስ አድርጋ <<አንድ እንዲገባሽ የምፈልገዉ ነገር አለ...አየሽ እኔ ስወልድ የምወልደዉ ግልገል አይደለም..ዝሆን እንጂ!! የምወልደዉ ደሞ በሁለት አመት አንዴ ነዉ..የእኔ ልጂ ምድርን የረገጠ እለት..ምድርም መፈጠሩን ታዉቃለች..የእኔ ልጂ መንገድ ሲያቋርጥ ሰዎች እርምጃቸዉን አቁመዉ በአድናቆት ካሚራቸውን አውጥተው እየቀርፁ ያዩታል.. የእኔ ልጂ ቀልብን የሚሠርቅ ነዉ....እኔ የምወልደዉ ሃያልና ታላቅ ነዉ!!>> አለቻት ↩ስለዚህ ወዳጀ የሌሎች ፀሎት ቶሎ ምላሽ ሲያገኝ የናንተ የዘገየ ቢመስላችሁ እምነት አትጡ..በሌሎች በረከትም አትቅኑ!! የራሳችሁን መባረክ ያላገኛችሁ ቢመስላችሁ..ተስፋ አትቁረጡ..ይልቅ ለራሳችሁ እንዲህ በሉት <<የእኔም ጊዜ እየመጣ ነዉ..ምድርን የረገጠ እለትም..ህዝብ ሁሉ በአድናቆት ይቀበለዋል>> በሉ// አስተማሪ ሁኖ ካገኙት. ሼር ያርጉት 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
ተስፋ መቁረጥ ሲሰማህ ልብህን ወደ ፈጣሪህ አዙርና እንዲህ በል 👇 " አምላኬ ሆይ ችግር በረታብኝ። ፅናቱን ስጠኝ። መከራን የምቋቋምበትን ብርታት ስጠኝ። እኔ አልችልም አንተ ግን ትችላለህ። እኔ ደካማ ነኝ አንተ ብርቱ ነህ። በእኔ ሳይሆን ባንተ መንገድ ውሰደኝ! ያንተ ፍጹምነት ከሰውነቴ ይበልጣል! የሁኔታዎች ሁሉ ባለቤት አንተ ነህ። በተዓምራቶችህ አልጠራጠርም! የጠፋውን ተካልኝ። የተሰበረውን ጠግንልኝ። ተስፋዬን መልስልኝ። ተስፋዬን አለምልምልኝ። አምላኬ ሆይ መከራን የምችልበት አቅም ስጠኝ። ነገዬ አብራልኝ። ነገ ብርሃን ከፊቴ እንዳለ በተስፋህ አግዘኝ። አምላኬ ሆይ ከአጠገቤ አትራቅ። ደካማህን ጠብቀኝ 🙏 አሚን 🙏"
መልካም ስራ የክፉ ቀን ስንቅ ይሆናል! ---ጎጆሽ ይሻላል ንብረትሽ ውብአለም ተመለሺ--------- የአበበ መለሰ - እውነተኛ ገጠመኝ ትልቅ ሰውዬ ናቸው። በናዝሬት አንድ መዝናኛ በር ላይ ቆመው "ልጆቼ ሀገሬ መግቢያ አጥቼ ነው አግዙኝ" እያሉ ይማፀናሉ። ...... በቦታው የነበረው በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ታላቅ ስም ያለው የዜማው ምንጭ አበበ መለሰ ይህንን የሰውየውን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ። በርግጠኝነት ይህንን ድምፅ ያውቀዋል። ....... እናም ለማረጋገጥ እርዳታ ይጠይቁ የነበሩትን ሰውዬ አተኩሮ እያያቸው አባቴ ምን ሆነው ነው ሲል ጠየቃቸው። ሰውየውም ለአንድ ጉዳይ ከሚኖሩበት ቦታ መጥተው አሁን መመለሻ አጥተው እንደተቸገሩ ነገሩት። ......... አበበ አሁን ማን እንደሆኑ እርግጠኛ ሆነ። ይህ ድምፅ የአያ ትርፌ ድምፅ ነው። ወንበር ስቦ ካስቀመጣቸው በኋላ ይጠይቃቸው ጀመር ። አባቴ፦ ስምዎት አያ ትርፌ ነው አይደል? አዎ አሉ ጎጃም ውስጥ የጁቤ አይደል የሚኖሩት? ልክ ነህ ልጄ እኔ አበበ እባላለሁ። ከብዙ አመታት በፊት እርሶ ቤት እመጣ ነበር። አያ ትርፌ አላስታወሱትም ። አበበ ግን በደንብ አውቋቸዋል። እኚህ አሁን ከሀገራቸው ወጥተው መመለሻ በማጣት ሲለምኑ ያገኛቸው ሰው የያኔው የጮማው፣ የቅቤው፣ የእርጎውና የማሩ ጌታ አያ ትርፌ ናቸው። እኚህ ሰው አደለም ለራሳቸው ለሰውም ይተርፉ የነበሩ ሲሆኑ አበበንም ጥብስ ከጥሬ እያበሉ ለወራት እንግዳቸው አድርገውት ነበር። .... ከብዙ አመታት በፊት በ1974 ዓ.ም ላይ የአሁኑ ታዋቂ የያኔው ወጣት አበበ መለሰ የገጠሩን ህብረተሰብ ለማስተማርና ለመርዳት ሲባል ታውጆ በነበረው ዘመቻ ምክንያት ጎጃም ውስጥ የምትገኝ የጁቤ የምትባል የገጠር ከተማ ዘምቶ እያለ ነበር እኚህን ሰው የሚያውቃቸው። ..... አያ ትርፌን የዛኔ ሲያውቃቸው የሞላ ኑሮ ያላቸው ወጣት ከምትባል ሚስታቸው ጋር በፍቅር የሚኖሩ ሰው ወዳጅ ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይመስላቸው ነበሩ ። .... ዛሬ ሀገራቸው መግቢያ አጥተው በችግር ከስተው እና ጠቁረው ፊቱ ቆመው ሲለምኑ ድንገት ያገኛቸው አያትርፌ ያኔ ወዛቸው የሞላ ፡ ደስተኛ ትዳር ፡ ውብ የሆነች ሚስት የነበራቸው ፡ የተከበሩ አባወራ ነበሩ። ...... አበበ ሰውየውን አጠገቡ አስቀምጦ የትና መቼ ያውቃቸው እንደነበር ነገራቸው። ለመሆኑ ለምን መጥተው ነው አይ ታሪኩ ብዙ ነው ልጄ ብለው ይነግሩት ጀመር ፡ አያ ትርፌን ከቀዬያቸው አርቆ ፡ ለችግር የዳረጋቸው የሚወዷት ሚስታቸው ድንገት ከቤት መጥፋት ነበር። ...... ድንገት አንድ ቀን ከእርሻ ውለው ቤት ሲመለሱ ፡ ያቺ ምድጃውን ለኩሳ ፡ ቡና አቅርባ ፡ ቤቱን አሙቃ ትጠብቃቸው የነበረች ሚስታቸው ውባለም የለችም ። ..... ትመጣለች ብለው ጠበቋት ። ..... ውባለም ርቃ ሄዳለች ። ......... ካሁን አሁን ከዛሬ ነገ ትመለሳለች ብለው በር በሩን የሚያዩት አያ ትርፌ የውባለም ወጦ መቅረት እውን ቢሆንባቸው እሳቸውም በራቸውን ዘግተው ፍለጋ ወጡ። ........... አዲስ አበባ ታየች ሲባል አዲስ አበባ ሄደው ውባለሜን አያችሁ ወይ ሲሉ በከንቱ ደከሙ። .... ሀረር ታየች አሏቸው ...... አያትርፌ ፡ ውቧ ሚስታቸው ውባለም ታይታለች ወደተባለበት ሀረር ተጓዙ። .... ሀረርም የለችም። ...... በዚህ መሀልም እህልና ከብቶቻቸውን ሽጠው የያዙት ገንዘብ አለቀ። እንደምንም አዳማ ደረሱ። ... የሞላ ኑሮ የነበራቸውን እኛ የተከበሩ ሰው ችግር አሸንፎ የሰው ፊት እንዲያዩ አደረጋቸው። ..... በዚህ ሁኔታ ልጆቼ ሀገሬ መግቢያ አጥቼ ነው እያሉ ሲለምኑ ከአመታት በፊት መልካም ካደረጉለት ከአበበ መለሰ ጋር ተገናኙ። .... አቤ ይህንን አሳዛኝ ታሪክ ከሰማ በኋላ አያትርፌን ሳንቲም ሰጥቶ አልሸኛቸውም። ይዟቸው ያረፈበት ቦታ ሄደ። ተጎሳቁለው የነበሩት አያ ትርፌ ፡ ሻወር ወሰዱ ፡ ልብሳቸው በአዲስ ተቀየረ። .... ድንገት ሳያስቡት በማያውቁት ሰውና ከተማ ውስጥ አይዞት አባቴ የሚል ሰው አገኙ። በአንድ ወቅት ያደረጉት መልካም ስራ ስንቅ ሆኖ፡ ከዚህ መልካም ሰው ጋር አገናኛቸው። አበበ መለሰ አያ ትርፌን በዚህ ሁኔታ ካስተናገደ በኋላ፡ የትራንስፖርት ብቻ ሳይሆን ኑሯቸውንም ሊደጉም የሚችል ብዙ ገንዘብ ሰጥቶ ልብሳቸውን ቀያይሮ፡ ወደሀገራቸው ሸኛቸው። .......... አበበ መለሰ አያ ትርፌን ወደ ሀገራቸው ከሸኘ በኋላም የሳቸው ነገር ከውስጡ ሊጠፋ አልቻለም። እና ይህንን አሳዛኝ የአያ ትርፌንና የውባለምን የፍቅር ታሪክ በዜማ ለመስራት ተነሳ። እናም ሙዚቃ ለመስራት አብሮት አዳማ የነበረው ድምጻዊ ቴዲ ታደሰ እንዲዘፍነው አንድ ዜማ ሰራ። ..... ይህ ከቴዲ ታደሰ ተወዳጅ ስራዎች መሀከል አንዱ የሆነው ውባለም ናፈቅሽኝ የሚለው ዜማ የተሰራው በዚህ ሙድ ነበር። ሆኖም ይህንን ዜማ የሰራው አቤ፡ ግጥሙን እንዲሰራ ለይልምሽ ሰጠው። ይህ ዜማ ሲወጣ አበበ መለሰ አሁንም በውስጡ ያለው፡ የአያትርፌና የውባለም ነገር በግጥሙ እንዳልተገለፀ ተሰማው። ምክንያቱም አያ ትርፌንም፡ ውባለምንም በአካል የሚያውቀው እሱ ነው። ሌላ ስራ ለመስራት አሰበ ። እናም ኤፍሬም ታምሩ ውባለም ተመለሽ(ጎጆሽ ይሻላል) የሚለውን ስራ ግጥሙንና ዜማውን ሰርቶ ሰጠው። እንግዲህ በፊት በፊት ሙዚቃ የሚሰራው በዚህ መሳይ ጥልቅ ስሜቶች ነበር። ........ የፍቅርን ሀያልነትና ፡መልካም ስራ አንድ ቀን ሊከፍል የሚችል መሆኑን የሚያሳይ ህያው ታሪክ ። ምንጭ ©W.T እንደፃፈው ሀቅ እና ድንቅ 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
አንዳንድ አስቀያሚ የሕይወት ዕውነቶች ◄▸► ◄▸► ◄▸◄ ◄▸◄ ◄▸ ◄▸ ◄▸ 1. አንዳንድ ጓደኞችህ እና ዘመዶችህ ውድቀትህን እና መውደቅህንን በድብቅ እየጠበቁ ናቸው። አንዳንዶች መልካም እየተመኙልህ ሊሆን ይችላል። እና ፣ ጥሩ ስትሰራ ማየት ይፈልጋሉ ።ነገር ግን፣ ከእነሱ የተሻለ እየሰራህ ከሆነ እሱን ላይፈልጉ ይችላል። ስለዚህ ምንም አይነት ነገር ቢደርስብህ መጥፎ ጊዜህን ከጓደኞችህ ወይም ከዘመዶችህ ጋር ቢሆንም በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አታካፍል። 2. ወላጆችህ ካልሆኑ በስተቀር ሕይወትህ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማንም አያስብም። ትግላችሁን ለራሳችሁ አድርጉ እና በህይወት ውስጥ ግፉ። ሰዎች በማማረርህን በአቤቱታህን ሰልችተዋል ነገርግን ለአንተ ላለመናገር መርጠዋል። 3. ብዙ ሰዎች አይለውጡም ግን ያስመስላሉ። ብዙዎች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ይከዱሃል። ነገር ግን ፣ በፍቅር በመውደቅ ወይም ሰዎችን በማመን እራስዎን አይወቅሱ ዝም ብለህ ቀጥል። 4. ሁልጊዜ የምትፈልገውን አታገኝም እና የምትጸልይላቸው አብዛኛዎቹ ነገሮች አይፈጸሙም። ነገር ግን ይህ ከመጸለይ ሊያግድዎት አይገባም ምክንያቱም ጸሎት ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ይሰራል። 5. ደስታ ለዘላለም አይቆይም ሀዘንም ለዘላለም አይቆይም። ሕይወት ለእርስዎ ምንም ያህል ከባድ ወይም ጥሩ ቢሆንም ፣ ለዘላለም እንደማይሆን ያስታውሱ። ደስታ በሀዘን እና ጭንቀትን ይተካል። በተጨማሪም ሀዘን እና ጭንቀት በደስታን ይተካሉ። ይህንን ቀደም ብለው ባወቁ መጠን ህይወትዎ የተሻለ እና ያነሰ ጭንቀት ይሆናል። 6. የቱንም ያህል ቆራጥ፣ ትኩረት ወይም ደፋር ብትሆን ሕይወት በእርግጠኝነት ይሰብርሀል። በህይወት ውስጥ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ትወድቃለህ እና ትበሳጫለህ። የእርስዎ እቅዶች፣ ህልሞች እና ምኞቶች አንዳንድ ጊዜ አይሰሩም። ግን መንቀሳቀስዎን ይቀጥሉ እና የተሻሉ ቀናት እየመጡ መሆኑን ልብ ይበሉ። 7. ሁሉም ሰው ስለ ምንም ስለማያውቀው ነገር አስተያየት አግኝቷል እና ብዙ አላዋቂዎች ሲሆኑ, ብዙ አስተያየቶች ይኖራቸዋል, ምክንያቱም ገደቦች ሁል ጊዜ የሚጣሉት በእውቀት ክፍተቶች ነው። 8. ስሜቶች ከተቆጣጠሩትህ አንተነትህን ቀድመህ አተሀል። ስሜትህ ጠላትዎ ሊሆኑህ ይችላል,። ለስሜት ራስህን ከሰጠህ, እራስህን ታጣለህ, ምክንያቱም ሰውነት ሁል ጊዜ አእምሮን ስለሚከተል። 9. ትልቅ ውሸት ከተናገርክ እና ብትደግመው ሰዎች በመጨረሻ ያምኑታል። ፖለቲከኞችን ጠይቋቸው የተሻለ ይነግሩዎታል። 10. የቱንም ያህል ጠንካራ ብትሆን ደካማ እንድትሆን የሚያደርግህ ሰው አለ። ተጨማሪ ፅሁፎችን ለማግኘት ቴሌግራምችንን ይጓብኙ ብዙ ይማራሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
видео или голосовое, без подписи
ለማሰብ እንፈራገጥ! የትም አገር ብትሄዱ ያልነቃ ሕዝብ መሆን ከባድ ነው። ሕዝብ ለማሰብ ካልተፈራገጠ ከሰል ነው። [የሚሆነው] ከሰል ወጥ ይሰራልጂ ከሚሰራው ወጥ የሚደርሰው(የሚያገኘው) ነገር የለውም! ለማሰብ ያልተፈራገጠ ሕዝብ ያጨበጭባል ለምን? እንደሚያጨበጭብ አያቅም ይኖራል ለምን? እንደሚኖር አያውቅም ለማሰብ እንፈራገጥ! 😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️
😘@mihret_debebe 😘 😍@mihret_debebe 😍 ❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️ 💚💛❤️