Biruk H. 🦋 የከበረ ነፃነት
СтатистикаI am here to 𝐄𝐦𝐩𝐨𝐰𝐞𝐫 𝐏𝐞𝐨𝐩𝐥𝐞 𝐟𝐨𝐫 𝐆𝐥𝐨𝐫𝐢𝐨𝐮𝐬 𝐅𝐫𝐞𝐞𝐝𝐨𝐦 @BirukHailemichael
- Последний пост
- 30 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- турецкий
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 94
- 1/48двое суток
- 107
- 1/72трое суток
- 116
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Right prayer and fasting https://youtu.be/xNgNn6SG2Gc?si=8FJMwOm1lRzuTxvS
High level prayer 🔥 https://youtu.be/Jf8ErAhYmaE?si=kdaFwpCJS6fnviUT
ሴላ
The last episode of audiobook has been released. This is my favorite episode. I invite you to listen to it. 25 minutes is enough to refresh your mind into the mind of God. For a short while, I’ll get away from media. Until then, shalom. መጽሐፍ በኢሳይያስ 53፡11 ላይ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “ጻድቅ ባሪያዬ በእውቀቱ ብዙዎችን ያጸድቃል” ይላል። እዚሁ ክፍል ላይ ወረድ እያልክ ስታነብ “ዘሩን ያያል እድሜውም ይረዝማል” ይላል። ይህ ዘር ሰዎችን በእውቀቱ የሚያጸድቀው የኢየሱስ ዘር ነው። ይህ እውቀት የአባትህ እውቀት ነው። የአባትህ እውቀት ብዙዎችን ለማጽደቅና ነጻ ለማውጣት ለአንተ ተሰጥቶሃል። 🥏Don't forget to Subscriber the channel https://youtu.be/IOxtRAn4UfA?si=hpQFW1enYUSeXOro
видео или голосовое, без подписи
"ኢየሱስ “ወደ አለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” ብሏል። (ማር16፡15) የምንሰብከው ሰዎች ከያዙት የተሳሳተ እውቀት እንዲድኑ ነው። ወንጌል ለድነት መደረግ ያለባቸው ነገሮች ስብከት አይደለም። ወንጌል ማስፈራሪያ አይደለም። ወንጌል በክርስቶስ የተገለጠውን እግዚአብሔርን ለሰዎች በማስረዳት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲጀምሩ ማድረግ ነው። ወንጌል የመዳኛ ቅድመ ሁኔታ ዝርዝር አይደለም። ኢየሱስ የሞተው ሊያድነን ነው ካልክ በኋላ ኢየሱስን ብትቀበል ትድናለህ የሚሉ ሁለት አረፍተ ነገሮች አንድ ላይ መሄድ አይችሉም። ኢየሱስን ወደ ልብህ ብትጋብዘው፣ እግዚአብሔርን ብትከተል፣ በፍጹም ልብህ ወስነህ ወደ እርሱ ብትመለስና ከሲኦል ጥፋት ትድናለህ… ዳግመኛ ትወለዳለህ… የእግዚአብሔር ልጅ ትሆናለህ… አዲስ ፍጥረት ትሆናለህ… ምርጥ ትውልድ ትሆናለህ ወዘተ የሚሉ ስብከቶች ወንጌል ሳይሆኑ ህግ ናቸው። በእርግጥ በዚህ አይነት ስብከት ውስጥ ወንጌል አለ? በፍጹም። ይህ ወንጌል ሳይሆን ሙሴ እንዳስቀመጠው አይነት የመዳኛ ቅድመ ሁኔታ ነው። ወንጌል የሚለው የግሪክ ቃል “ኢዩዋንጌልዮን” (euangelion) ሲሆን የምስራች፣ መልካም ዜና፣ ደስ የሚያሰኝ መልዕክት፣ የድል አዋጅ ማለት ነው። ወንጌል እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሰው ልጆች የፈጸመው መልካም ዜና ነው። ወንጌል ውስጥ መጠይቅ ካለ ወንጌል አይደለም። ወንጌል ውስጥ ማስፈራሪያ ካለ ወንጌል አይደለም። ወንጌል ገሃነም እና ሲኦልን ማስተዋወቂያ አይደለም ነገር ግን የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር ማወጃ ነው። ወንጌል የሚናገረው በክርስቶስ መስቀል ምክንያት ለሰው ልጆች ምን ሆነ የሚለውን ነው። ወንጌል ከመጀመሪያውኑ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆናችን እውነት መልዕክት ነው።" - የከበረ ነፃነት
ይህ የሰጪነት ባህሪ አንዳች ሳይቀነስና ሳይጨመር በአንተ ውስጥ አለ። አሁን በኑሮህ ላይ የምታየው ማንኛውም የመሰሰት ባህሪ የአንተ ሳይሆን የውሸት አባት ነው። በአዕምሮህ ውስጥ ያለ ለእኔ ብቻ የሚል ማነኛውም ሃሳብ የቀደመው እባቡ ነው። ብዙዎች እግዚአብሔርን የማይመስል ሕይወት ነፍሰ ገዳይነትና ዝሙት ብቻ ይመስላቸዋል። ቃሉ መሰሰት ከሌሎቹ ክፉ ባህሪያት እንደ አንዱ ያስቀምጠዋል። (ኤፌ5፡3) subscriber ያላደረጋችሁ አድርጉ https://youtu.be/o1R1NGFhBRk?si=0Tq1C8ylg8VTsjge
ኢየሱስ እና እግዚአብሔር እየተጨቃጨቁ ነው?😏 የተቆጣ እግዚአብሔር አብ እና አፍቃሪ ኢየሱስን ከማምለክ የግራ መጋባት ክልል ውስጥ እንድትወጡ በክብር እጋብዛችኃለሁ። እግዚአብሔር ሊያጠፍን የሚፈልግ አካል ኢየሱስ ደግሞ ከእግዚአብሔር ሊያድነን የሚፈልግ አካል አድርገን ከማሰብ መመለስ አለብን። በክርስቶስ ላይ ለሰው ሁሉ በቃልና በተግባር ተገልጦ ያየነው ፍቅር የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። የተቆጣ እግዚአብሔርን ከሰው ጋር ለማስታረቅ መሀል ላይ የገባ ሶስተኛ ልዩ አካል የለም። ሰውን ከራሱ ጋር ለማስታረቅ ስጋ በለበሰው ክርስቶስ ውስጥ የተገለጠው ራሱ እግዚአብሔር ነው። 2ቆሮ5:18/ቆላ1:20 በሰማይ የዙፍን ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር ወልድ በአንተ አጀንዳ እንደ ዳኛና ጠበቃ እየተከራከሩ እንደሆነ ማሰብ አቁም። አብና ወልድ በሀሳብ ተለያይተው አያውቁም። እግዚአብሔር አባት ከሁኔታ ውጪ ስለሚወድህ ኢየሱስም ይወድሃል። ኢየሱስ የሚያደርገው አባቱ የሚያደርገውን ብቻ ነው። አንተ በመለኮት አለም ውስጥ ግን በሌለው ሊገለፅ በማይችል ጥልቅ ፍቅር የተወደድክ ነህ። በዙፍን ክፍል ውስጥ ስለ አንተ የሚነሳው ሀሳብ የሰላም፣ የፍቅር፣ የክብር ነው። የእግዚአብሔር አዕምሮ የተወደድክ ልጁ መሆንህ ላይ አንዳች ማመንታት የለበትም። 😍😍😍 - የከበረ ነፃነት
መጥመቁ ዮሐንስ እንዳወጀው ኢየሱስ "የአለም ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ነው። የአለምን ማለት የጴንጤዎችን ማለት አይደለም። የአለምን ማለት የአማኞችን ማለት አይደለም። የአለምን ማለት በአለም ውስጥ ያሉ የሰው ዘሮች በሙሉ ማለት ነው። ኢየሱስ የመጣበትን አላማ ፈፅሟል። ተሳክቶለታል። ኃጢያትን በማያዳግም ሁኔታ ደምስሶ አስወግዶታል። እግዚአብሔር ከኃጢአት ጋር የሚመለከተው አንድ ሰው እንኳን አለም ላይ የለም። ሃሌሉያ ለተሰቀለው ክርስቶስ 🙏
የኢየሱስ ደም ለምን? የኢየሱስ ደም እግዚአብሔር እኛን የሚያይበትን መንገድ በመግነጢሳዊ ሀይል ከጥላቻ ወደ ፍቅር አይለውጥም። የደሙ ሀይል የታጨቀው ለእኛ በሚነግረን የእግዚአብሔር የፍቅር ወንጌል እውነት ውስጥ ነው። የፈሰሰው የኢየሱስ ደም የሰውን አዕምሮ እግዚአብሔር ይጠላኛል ከሚል አስተሳሰብ ወደ ይወደኛል ያመጣዋል። ደሙ በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ያለንን ጥርጣሬ ሁሉ ያመክናል። ደሙን በተመለከትን ቁጥር ከኃጢአት የመንፃታችንን ጉዳይ ከማነኛውም ጥያቄ ውጪ ይሆናል። የከበረ ነፃነት
ይቅርታ ማድረግ ማለት ያጠፋውን ሰው ትክክል እንዳደረገ መቁጠር አይደለም። ማንም በተሳሳተ እኔነት እንዳይቀጥል ሲያጠፋ ሊገሰጽ ይገባዋል። መገሰጽ ማለት በተሳሳተ ማንነት ውስጥ ላለ ሰው ትክክለኛ ማንነቱን እንዲቀበል ተጽዕኖ ማድረግ ነው። መገሰጽ ያጠፋ ሰው ላይ እየጮሁ መሳደብ ወይም በአደባባይ ማሳፈር ማለት አይደለም። (ማቴ18፡15) መጽሐፍ “ወንድምህ ቢበድልህ ገስጸው ቢጸጸት ይቅር በለው” ይላል። (ሉቃ17፡3) #Subscriber https://youtu.be/xRRhBK5dzFI?si=64yHo46DVkd6cPLT
✅ከውስጥ ወደ ውጪ የሚፈስ የሰውነት ምሕንድስና ስጋ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረው የመንፈስ ፍቃድ ተገዥ ሆኖ እንዲኖር የተሰራ ነው። ስጋ የምንኖርለት ሰውነታችን ሳይሆን የምንኖርበት ሰውነታችን ነው። የምንኖረው ሰውነታችን እንደ እግዚአብሔር አርዓያ የተሰራው መንፈሳችን ነው። ስጋ መንፈሳችንን በምድር የምንኖርበት ቤት ነው። ስጋ መኖሪያችን በመሆኑ እኛን በሚመጥን መልኩ በክብር ሊጠበቅ ይገባዋል። ነገር ግን ስጋ ከውስጥ ማንነታችን በተቃረነ መልኩ ከውጪ በአዕምሮ የተገነባውን ማንነት እንድንኖርበት ሊፈልግ ይችላል። የሚዳሰሰው ስጋ (Soma) ላይ ተንተርሶ የሚመጣ ከመንፈስ ፍቃድ ተቃራኒ የሆነ የስጋ ፍላጎት (sarx) ሁሉ በመንፈስ ግዛት ውስጥ እንዲወድቅ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ሰው ከውስጥ ወደ ውጪ በሚፈስ የሰውነት ምሕንድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረ ፍጥረት ነው። 🥏የከበረ ነፃነት መፅሐፍ - ገፅ 25
" በጠንካራ የዘረኝነት አስተሳሰብ የተገነባችው ሰማርያዊቷ ሴት ውሃ ስጪኝ ያላትን ኢየሱስ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ እኔን ሳምራዊቷን እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትላለህ” ስትለው ታያለህ። (ዮሐ4፡9) ይህ ንግግሯ በአይሁድና በሳምራዊያን ዘሮች መካከል የጠለቀ ችግር እንዳለ ዮሐንስ ይነግረናል። ያኛው ዘር ጠላታችን ነው፣ የኛ ዘር ይህንን አያደርግም፣ የእኛ ዘር ከሌላ አያገባም። የኛ ዘር ተጨቁኗል፣ የእኛ ዘር ታላቅ ነው፣ የእኛ ዘር ደካማ ነውና በመሳሰሉት ትምህርቶች ትውልዱን ይገነባሉ። የዚህ አይነት ትምህርት ክፍ ፍሬን ያፈራባት ይህቺ ሴት ፊት ለፊቷ ላለው ውሃ የተጠማ ሰው አይደለም ውሃን ለመስጠት ውሃ ስጪኝ ብሎ በመጠየቁ ስትናደድ ትመለከታለህ። ይሁን እንጅ በእዚች ሴት ውስጥ ያለው የቡድነኝነት አስተሳስብ በውሸት በውስጧ የተሰራ ማንነት እንጂ እሷ ከተፈጥሮ ክፉ አይደለችም።" ቀጣይ ክፍል ተለቋል 👇👇👇😍😍😍 #subscriber እያደረግን ከዘረኝነት ነቅለን እየወጣን ወደ ፍቅር 🚶♂️ https://youtu.be/qaPNUc8geV8?si=1-ZAi9XxIUQcYksP
በአዲስ አመት አዲስ አስተሳስብ (ወደ ፍቅር) Please Subscriber my channel " ጴጥሮስ በጸጋው እውነት ድኖ እንኳን ቡድነኝነት የሚያስቸግረው ሰው ነበር። ይህንን አይነት የሃይማኖተኝነት ባህሪውን እንዲተው ጳውሎስ እንደገሰጸው ነግሮናል። (ገላ2፡11-14) ጴጥሮስ ይህንን አይነት አስተሳሰብ እንዲተው አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ተነግሮት ነበር። “እግዚአብሔር ንጹህ ያደረገውን አንተ እንደ እርኩስ አትቁጠረው” (ሐዋ10፡15) የሰውን ቡድን፣ ተግባር፣ ንግግር፣ አለባበስ እና ሁኔታ በማየት ሰውን እንደ ኃጢያተኛ ዝቅ አድርጎ መመልከት የሃይማኖተኞች መታወቂያ ነው። ክርስቶስ በሁሉም ውስጥ ነው። (ገላ3፡28፣ ቆላ3፡11)" https://youtu.be/Kqc8mCo4ZnU?si=jkwaoTpFWm5lIJHa
ምንድነው የምናምነው? እምነት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነው። የምናምነው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምነውን ነው። የምናምነው ማንነታችን ለህይወት በሚሆነው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተሰራ መሆኑን ነው። የምናምነው ስሪታችን ልጅነት መሆኑን ነው። የምናምነው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአባታችን የተወደድን መሆናችንን ነው። የምናምነው ከአዳም የወረስነው የማንነት እውቀት ሁሉ ውሸት መሆኑን ነው። የምናምነው አንድን ውጤት ለማምጣት ሳይሆን በክርስቶስ መገለጥ ወደ ብርሀን የወጣውን ውጤት ነው። የምናምነው በክርስቶስ መገለጥ ኃጢአትን እንደተወገደ እንጂ ስናምን ጠብቆ እንዲያስወግድልን አይደለም። የምናምነው በእግዚአብሔር ዘንድ ለመወደድ ሳይሆን ተወዳጅ እንደሆንን ነው።
ላለፉት 6 ዓመታት የቻናሌ ቤተሰቦች ሆናችሁ የቆያችሁ እና አዲስ የመጣችሁ ሁሉ መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ። 🏵️
የምናደርጋቸው ነገሮች ከከንቱነት የሚድኑት በፍቅር ብቻ ነው። (1ቆሮ. 13፡1-2) ፍቅር የሰው ልጅ ሕይወት ትክክለኛ ትርጉም ነው። እግዚአብሔር ከክፉ መናፍስቶችና ከዚህ ዓለም ገዢዎች የለየው ሃይለኛ መሆኑ ሳይሆን ፍቅር መሆኑ ነው። የምታደርገው ፍቅር ላይ ያልተመሰረተ ማንኛውም ነገር ብታምንም ባታምንም ከእግዚአብሔር አይደለም። Please #Subscriber አድርጉ and share አድርጉላቸው🔥 https://youtu.be/kHCCuyU_DXw?si=pKddPJwa0LIU36yP
🥏የሚያስፈልገው ፀሎት ነው! 🥏ከኢየሱስ ህይወት ስለ ፀሎት የምንማረው 🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗 ቀጣዩ ተለቋል Please subscriber and shares https://youtu.be/uxNH2F98w7g?si=btN3TfeL7G6PNhdE
የተፈጠርነው በእግዚአብሔር አይነት ተፈጥሮ ነው። "ኃጢያተኛ ተፈጥሮ" የሚባለው ነገር በመፅሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎችና አስተማሪዎች የተሰጠን አስተሳሰብ እንጂ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። በአዳም ምክንያት የተፈጠረው ችግር "ተፈጥሮአችን" ላይ ሳይሆን ስለ ተፈጥሮአችን ያለን "አመለካከት" ላይ ነው። ተፈጥሮአችን ሊበላሽ የማይችለው የእግዚአብሔር መልክ ነው። ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ፃድቅ ተፈጥሮ ነው። 🤩😍😃 ➢We are created with the same nature as God. The concept of "sinful nature" is not in the Bible, it is a concept given to us by Bible translators and teachers. The problem caused by Adam is not in our "nature" but in our view of our nature. Our nature is the incorruptible "image of God." It is the righteous nature that we have received from God.
ለስጋዊ ፍላጎትህ ብለህ ልጅነትህን አትጣል። ለተራበው ሆድህ ብለህ ብኩርናህን አትሽጥ። አንበሳ የጻድቅ ሰው ምሳሌ ነው። አንበሳ የሚበላው ስጋ ስላጣ ብቻ ሳር አይበላም። እርቦት ሆዱ ሊጣበቅ ይችላል ነገር ግን ሳር አይበላም። ምክንያቱም ሲፈጠር ሳር መብላት ማንነቱ አይደለም። ለስጋህ ሳይሆን ለማንነትህ ለመኖር ተወልደሃል። (1ጢሞ. 4፡8) ቀጣዩ ክፍል ተለቋል subscriber ማድረግ አትርሱ https://youtu.be/PolWfMRyQu4?si=1brUWvSo4mSSjm5R