የሄኖክ አሸብር ግጥሞች እና ወጎች
Статистика- Последний пост
- 9 июн.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 32
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
📌📌📌ይሄን ዕድል ይጠቀሙ!! #በPdf_ያግኙ!! 👉 1 መጽሐፍ ገዝተው 👉 2 መጽሐፍ በነጻ ያግኙ!! "ኤል-ሃሌል" የግጥም መድብልን በPdf በመግዛት "መማጸኛ ከተማዬ" እና "የቀራንዮ የፍቅር ጭማቂ" በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ🙏🙏🙏 "ኤል-ሃሌል" 👉 350 ብር 1000401587407 CBE 👉Henok Ashebir #ሄኖክ_አሸብር
#ሀገር_ውስጥም ሆነ #ከሀገር_ውጭም ላላችሁ ባላችሁበት ሀገር ሆናችሁ መማር ትችላላችሁ!! ትምህርቱን 👉 በቪዲዮ 👉 በኦዲዮ 👉 በPdf ያገኛሉ!! የመዝሙር ግጥም አጻጻፍ መማር የምትፈልጉ ዘማሪዎችና ገጣሚዎች መመዝገብ ትችላላችሁ!! ኑ ወዳጃችን ኢየሱስ በውስጣችን ያስቀመጠውን የግጥምና የዝማሬ ጸጋ እንዴት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትና በስነጽሑፋዊ እውቀት ለመግለጥና ለማገልገል ፤ ስለኢየሱስ ያማረ ቅኔ እንድንቀኝና እንድንጽፍ እንማር። 👉 ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ የመዝሙር ግጥም አጻጻፍ መማር ትችላላችሁ!! ለበለጠ መረጃ እና ለመመዝገብ +251906114984 በቴሌግራም ያግኙኝ የመዝሙር ግጥም አጻጻፍ ትምህርት #ሄኖክ_አሸብር
የሚሠራም ይኾናል። ለሰዎችም የመታነጽና የመዳን ምክንያት ይኾናል። እንግዲህ፥ ይህንን የመሰለውን ቅዱሱን መጽሐፍ እንዴት አለ ማንበብ እንችላለን? መጽሐፉን አንብቡት። መጽሐፉን ውደዱት። መጽሐፉን አፍቅሩት። መጽሐፉን አክብሩት። መጽሐፉን ታዘዙት። መጽሐፉ አገልግሉት። መጽሐፉን ያዙት። መጽሐፉን ተጣበቁትም። መጽሐፉን ውረሱት። መጽሐፉን ለልጅ ልጅ አውርሱት። 🙏 መጽሐፉን- መጽሐፉን- መጽሐፉን! 🙏 2ኛ ጢሞቴዎስ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ አንተ ግን በተማርኸውና በተረዳኸው ጽና፤ ይህን ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ¹⁵ ከሕፃንነትህም ጀምረህ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል። ¹⁶ ቅዱሳት መጻሕፍት ኹሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ¹⁷ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ኹሉ ብቁ ኾኖ እንዲገኝ ነው።
"ግብዝነት የሌለበት እምነት መገለጫ" ግብዝነት የሌለበት እምነት መገለጫ "በተማሩትና በተረዱት የእግዚአብሔር ትምህርት" መሠረት ላይ ጸንቶ መቆም ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቤተ መጻሕፍት(library) ናቸው። እግዚአብሔርን ያወቅነው በመጽሐፉ ውስጥ ነው። መጽሐፉ የፈላስፋዎቹ ወይም የነገሥታቱ፥ የሃይማኖተኞቹ ወይም የመደዴው ሰዎች አይደለም። መጽሐፉ የእግዚአብሔር ነው። መጽሐፉ ለሰው ልጆች በሙሉ የተሰጠ አፊዎተ እግዚአብሔር ይኸውም እስትንፋሰ መለኮት ነው። በእግዚአብሔር የተተነፈሰ ማለት ነው። እያንዳንዱ ታሪኮች ውስጥ እግዚአብሔር "እርሱነቱን" ተንፍሷል ማለት ነው። መጽሐፉ ውስጥ እንዲያው የገባ ታሪክ የለም። ታሪኮቹ ኹሉ አንዱን ባለ ታሪክ ያጎሉታል። በሚያስደንቅ ኹኔታ፥ ባለ ታሪኩ እግዚአብሔር ኹሉንም ታሪኮች በአንዲት ሥላሴያዊ ምክር አቀናጅቶ፥ ወደ ክርስቶስ ይመራዋል። ቅዱሳት መጻሕፍት ኹሉ የእግዚአብሔርን ልጅ ይጠቁማሉ። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ስድስት ነገሮችን ይነግረናል። -> የመጀመሪያው፥ ቅዱሳት መጻሕፍት ኢየሱስን በማመን መዳን ስለሚገኝበት የእግዚአብሔር ጥበብ ይነግሩናል። በዘፍጥረት ጅማሮው ላይ የምናየው ውቡ ዓለም በኀጢአት መዶሻ እንክትክቱ ቢወጣም፥ እንደ ተሰባበረ ግን አልቀረም። ተሰብሮለት የሚጠግነው መጥቷል። በደዌና በሕማም ደቅቆ ከድቀታችን የሚያድነን ተገልጧል። የእኛን ሥቅየት ጨልጦ ከኀጢአት ውድመት የሚገላግለን ቤዛ ስለ እኛ ሞቷል። የትኛውም የዓለም መጽሐፍ ውስጥ ይሄ ብርሃን የለም። በርግጥ ስለ ኢየሱስ ሞትና አሟሟት የታሪክ ድርሳናት አሉ። ስለ ማዳን ጥበቡ ግን በአንዳቸውም የለም። መጽሐፉ ውስጥ ግን አለ። መጽሐፉ አዳኙን ይተርክልናል። አምላክ ሰው መኾኑን፥ ሞት ራሱ መሞቱን፥ ኀጢአት መወገዱን፥ መንገደ ሰማይ ተከፍቶ "በሰላም ግቡ" መባሉን የትኞቹ መጻሕፍት ናቸው የተሸከሙት? መጽሐፉ አይደለምን? ቅዱሳት የእግዚአብሔር መጻሕፍት አይደሉምን? ለዚህ ነው መጽሐፉን በማንበብ መትጋት ያለብን። መጽሐፉን በእምነት ማንበብ፥ የእግዚአብሔርን ልብ በእምነት ማንበብ ነው። የእግዚአብሔር የልቡ ትርታ ደግሞ ክርስቶስና ቤዝዎተ-ዓለም ነው። እናማ፥ መጽሐፉን አንብቡት! -> ኹለተኛው፥ ቅዱሳት መጻሕፍት ለመማርና ለማስተማር ይጠቅማሉ። እግዚአብሔር ልናውቅ የሚገቡንንና የሚያስፈልጉንን ነገሮች ኹሉ በመጽሐፉ ውስጥ አኑሮታል። ለኹሉም ዐይነት ጥያቄዎች መጽሐፉ መልስ አለው። ሳይንስ እንኳን ደፍሮ የማይነካቸውን ድንበሮች መጽሐፉ ይረማመድባቸው። መጽሐፉ ስለ እግዚአብሔር ሲነግረን ሳያመቻምችና በሙሉነት ነው። "እግዚአብሔር ነበር" ብሎን ይጀምርና "እግዚአብሔር ይኖራል" ብሎን ይጨርሳል። እውነቱን ኹሉ ፍርጥርጥ አድርጎ ይነግረናል። አምላክ ሰው ኾነ ሲለን እንኳን ያለመሳቀቅ ነው። መጽሐፉ እውነትና እውነት ብቻ ነው። የሚማር ልቡና ላላቸው ኹሉ መጽሐፉ የእግዚአብሔር ትምህርት ነው። ስለ ኹሉም ነገር መልስ አለው። መልስ የለም ለምንላቸው ነገሮች እንኳን እግዚአብሔር መልስ ነው ይለናል። መጽሐፉ መልስ በመልስ፥ ሕይወት በሕይወት፥ እውነት በእውነት ነው። እናማ፥ መጽሐፉን አንብቡት! -> ሦስተኛው፥ ቅዱሳት መጻሕፍት ለመገሠጽ ይጠቅማሉ። ግሣጼ እርማት ነው። ግሣጼ የተበላሸን ነገር በአባታዊ ቅጣት ማስተካከል ነው። ግሣጼ ከመንገድ የወጣን ነገር መልሶ ማስገባት ነው። በዚህ ፈራሽ ሥጋ ውስጥ ስንመላለስ ከብዙ ድካሞች ጋር የምንታገል ነን። በኀይሉ ብዛት እየተደገፍን እንቀጥላለን እንጂ እንደ ሸክላ ዕቃዎች ተሰባሪዎች ነን። እግዚአብሔርም ቢኾን የከበረ መዝገቡን ያኖረው በሸክላነታችን ውስጥ ነው። ብረት ለበሶች አይደለንም። እንደ ናስ የጠነከሩ ዐምዶችም አይደለንም። ሸክላዎች ነን። ከዚህም የተነሣ እንፍገመገማለን፤ እንንሸራተታለን፤ እንሰበራለን። መንገድ እንስታለን። መኼድ በማይገባን ጐዳና እንርመሰመሳለን። የተተውን ግን አይደለንም። የሚረዳንና የሚያግዘን የሌለን አይደለንም። የሰማዩ አባታችን እግዚአብሔር በትምህርቱ ይገሥጸናል። በመጽሐፉ ይወቅሰናል። ያለንበትን እንድናስተውል፥ እንደገና እንድንጠገን የቃሉን ወጌሻ ይልክልናል። "ቃሉን ላከ፥ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።"(መዝ 107፥ 20) እንደሚል፥ በቃሉ ከስብራታችን ይጠግነናል። ጤናማ ካልኾነ መንገዳችንም ይመልሰናል። እንግዲህ ዋናው ጥያቄ፥ መጽሐፉን እናነበዋለን ወይ? የሚለው ነው። የሚጠግነን በቃሉ ከኾነ፥ ቃሉን የማናነብ ከኾነ፥ ታዲያ እንዴት እንጠገናለን? በምንስ እንገሠጻለን? ኹለተኛው ጥያቄ ደግሞ "ቃሉን እንታዘዛለን ወይ?" የሚለው ነው። ቃሉን መስማት ብቻውን ሙሉ አይደለም። ሙሉው ነገር መስማትና ማድረግ ነው። ሰምተን ስንታዘዝና ለግሣጼው በጎ ምላሽ ስንሰጥ ከድካማችን እንወጣና እግዚአብሔር በሸክላነታችን ውስጥ የከበረ ኀይሉን ለኹሉ ይገልጠዋል። እናማ፥ መጽሐፉን አንብቡት፥ ታዘዙትም! -> አራተኛው፥ ቅዱሳት መጻሕፍት ለማቅናት ይጠቅማሉ። ማቅናት አንድም መመለስ ሲኾን ኹለትም ደግሞ ምቹ አድርጐ ማቅረብ ነው። መመለስ የመጀመሪያው መንገድ ሲኾን ምቹ አድርጐ ማቅረብ ደግሞ ቀጣዩ መንገድ ነው። እግዚአብሔር የክፋት መንገዳችንን እንድንተው ብቻ ሳይኾን ለእርሱ የሚመቹ ኾነን እንድንቀርብለትም ይፈልጋል። መተውና ማቅረብ ተያያዥ ነገሮች ናቸው። በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርትና ተግሣጽ ስንቃና ያለፈ ጥፋታቸውን የተዉ፥ የእግዚአብሔር ምቹ ዕቃዎች እንኾናለን። መቃናት፥ ምቹ ዕቃ መኾን ነው። መጽሐፉ ምቹ አድርጐ ይሠራናል። እናም፥ ሊሠራን ላለው ቅዱስ መጽሐፍ እጅ ሰጥተን፥ በመታዘዝ አሸብርቀን፥ በተቃና ልብ፥ ለእግዚአብሔር ራሳችንን እናቅርብ። -> አምስተኛው፥ ቅዱሳት መጻሕፍት በጽድቅ መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ። ለቁጥር እስኪያታክቱ ድረስ በዓለም ላይ ብዙ መጻሕፍት አሉ። መልካም የኾኑ ትምህርቶችን ሊያስገነዝቡ የሚችሉ ጽሑፎች ከኢአማንያን እስከ አማንያን፥ ከአይሁድ ፈላስፋዎች እስከ አሕዛባውያን ፈላስፋዎች ተበርክተዋል። የቱንም ያኽል ቢኾኑ ግን፥ የእግዚአብሔርን መጽሐፍ የሚያኽል ትምህርትና ምክር የላቸውም። በሰው ፊት መቆም የሚያስችል የሥነ ምግባር መርሖ ይኖራቸው ይኾናል። በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚያስችል ትምህርት ያለው ግን መጽሐፉ ብቻ ነው። መጽሐፉ ከጅምሩ "ጽድቅን" ያስተዋውቀናል። በክርስቶስ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በጸጋ "እንካችሁ" ይለናል። እንካችሁ ካለን በኋላም ይቀጥልና፥ የጽድቅን መንገድ ምክር ይሰጠናል። መጽሐፉ ጽድቅን ከነምግባሩ ነው የሚያስተምረን። ጽድቅን ብቻ ወይንም ምግባሩን ብቻ የሚል ትምህርት የመጽሐፉ አይደለም። መጽሐፉ የጽድቅ ፍሬ መምህር ነው። እናም፥ በመጽሐፉ መንገድ ስንመላለስ፥ በጽድቅ መንገድ ያለው ምክር በልባችን ይመላለሳል። ምክሩ በልባችን ሲመላለስም በጽድቅ መንገድ ላይ እንመላለሳለን። እናማ፥ በመጽሐፉ መንገድ ላይ ተመላለሱ! -> ስድስተኛውና የመጨረሻው ደግሞ፥ ቅዱሳት መጻሕፍት "የእግዚአብሔር ሰው" በመኾን ለመልካም ሥራ ኹሉ ብቁ መኾንን ለመለማመድ ይጠቅሙናል። የተጻፉት ኹሉ ለጥቅማችንና ለትምህርታችን ተጽፈዋል። መጽሐፉ የእግዚአብሔርን መንገድና ትዕዛዛት ኹሉ ስለ ተሸከመ፥ በቃሉ መንገድ የሚመላለስ ሰው፥ "የእግዚአብሔር ሰው" ይኾናል። የእግዚአብሔር ሰው ደግሞ "ለመልካም ሥራ ኹሉ ብቁ ኾኖ" ይገኛል። ብቁ የኾነ ሰው ደግሞ በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ የታመነ ምስክርነት ይኖረዋል። ለእግዚአብሔር ክብርና ደስታ ተግቶ
✍️ ሞቴን እንዳምን እርዳኝ ******* እኔማ ጸሎቴ ላይኔ መብራት ስጠው ፣ የቃልህ ፍች ይብራ አሻግረህ ከማዶ ወዳየኸው ትውልድ ፣ አፏጭ በ'ኔ ጥራ እንዳሳብህ መጠን እንደፍላጎትህ ፣ እንደልብህ መሻት ላፈንግጥ የሚልን እኔነቴን ደቁስ ፣ ነፍሴን በቃል እሻት በመውደድህ ትርካ በፍቅርህ መቃጠል ፣ በንዳድ ትንገብገብ አብዝታ መፈለግ አንተን አንተን ማለት ፣ አለመጥገብ ትጥገብ ድርቀት ከተሞላ መንፈስህ ከሌለው ፣ መንፈሳዊ ቃላት በስምህ ከሆነ ስምህን ከማይገልጥ ፣ ልምምድ ስርዓት ከብዙ ማስመሰል ከከንቱ ትወና ፣ ከረብ አልባ ትጋት ከባዶ መሟሟቅ ከውሸት መጋጋል ፣ ጎሰም አ'ርገህ አንቃት ትዕቢት በት'ትና አይቆጣጠረኝ ፣ የእኔነት ማዕበል ለሰው ተገብዞ ከንፈሬ "ታይ" ብሎህ ፣ ልቤ "ልታይ" አይበል በዓይኖቼ ተመልከት በአፌ ተናገር ፣ በ'ግሮቼ ተራመድ ፈጽም አላማህን ወደምትወደው ፣ እየወጣህ ውረድ በ'ኔ ያየኸውን አንድ ሳይቀር አርገው ፣ ገደቤን ገድበው በጥቂት ጭብጨባ ተወጣሪ ልቤን ፣ ቀጥቅጠህ አርግበው እኔማ ጸሎቴ ስቅለቴ ካንተ ጋ ፣ እንደተካሄደ አሮጌው አዳሜ ፣ እንደተወገደ ተሰብኬ አምኜ አምኜ ሰብኬ ፣ አዋቂ ለመባል ጥቅስ ሰባስቤ ሸካክፌ እንዳልዞር ፣ግብር የሌለው ቃል ሰው አይቶኝ እንዲያህ ፊቴ ላይ እንዲያውቅህ ፣ ሳወራ እንዲያደምጥህ ምልልሴ ሁሉ መግባቴ መውጣቴ ፣ ኑሮዬ እንዲገልጥህ ላክ ሞቴን አስታዋሽ ላክ መርዶ ነጋሪ ፣ በየ'ለት በየ'ለት በ'ኔ በኩል ያንተን መገለጥ 'ሚጠብቅ ፣ አለህና ፍጥረት አሁን አንተ አትኖርም "ሙተሃል" እያልከኝ ፣ በየማለዳ አርዳኝ ያለሁ ያለሁ መስሎኝ መኖር እንዳልሞክር ፣ ሞቴን እንዳምን እርዳኝ #ሄኖክ_አሸብር
✍ ኃይማኖት የለኝም!! * ወዳጄ ሆይ.......በክርስቶስ ነህ ወይስ ጴንጤ ነህ? ✍ እኔ በጌታ ነኝ ስል........ምን ማለቴ ነው? 👉 "በጌታ ነኝ" ትልቅ እና ጥልቅ ትርጉም ያለው ቃል እንደሆነ ታስተውሉ ዘንድ እወዳለሁ!! ✍ በጌታ ነኝ ስል ጴንጤ ነኝ እያልኩ ሳይሆን በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነኝ ማለቴ ነው!! 📌 በጌታ ነኝ ስል ፕሮቴስታንት ነኝ እያልኩ ሳይሆን በክርስቶስ ጻድቅ ነኝ ማለቴ ነው!! ✍ በጌታ ነኝ ስል ጴንጤ የሚባል ኃይማኖት አለኝ እያልኩ ሳይሆን ኢየሱስ የሚባል ሕይወት አለኝ ማለቴ ነው!! 📌 በጌታ ነኝ ስል የታቀፍኩበት የኃይማኖት ድርጅት አለኝ እያልኩ ሳይሆን ያቀፈኝ የሕይወት ራስ አለኝ ማለቴ ነው!! ✍ በጌታ ነኝ ስል የኃይማኖት ስርዓት ለመፈጸም የምተጋ ነኝ እያልኩ ሳይሆን ክርስቶስ በፈጸመልኝ ያለቀ ሥራ ላይ ተደላድዬ ያረፍኩ ነኝ ማለቴ ነው!! 📌 ባጭር ቃል በጌታ ነኝ ስል በክርስቶስ ውስጥ ነኝ ማለቴ እንጂ ጴንጤ ነኝ ማለቴ አይደለም!! ወዳጆቼ፦ ✍ እገሌኮ በጌታ ነው የምትሉት ጫት አንደማይቅም ለመግለጽ ነው ወይስ በክርስቶስ መጽደቁን ለመግለጽ? 📌 እገሊትኮ በጌታ ናት ስትሉ ጉቦ እንደማትቀበል ለመግለጽ ነው ወይስ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኗን ለመግለጽ? ✍ እኔኮ በጌታ ነኝ ስትሉ መጠጥ እንደማትጠጡ ለመግለጽ ነው ወይስ በክርስቶስ ኃጢአት ፣ ነውር ፣ ኩነኔ ፣ ዕድፍ ፣ በደል ፣ ዕዳ ፣ ክስ ፣ ፍርድ ፣ ሞት እንደሌለባችሁ ለመግለጽ? 📌 በክርስቶስ ነኝ ስትሉ ምን ማለታችሁ ነው? 📌 ክርስቶስ የሞተልህ ጴንጤ እንድትሆን ሳይሆን በክርስቶስ እንድትሆን ነው!! ✍ እግዚአብሔር በክርስቶስ መሆንህን እንጂ ጴንጤነትህን አያውቀውም!! 📌 በክርስቶስ ሆነህ እንጂ ጴንጤ ሆነህ ባለመፍትሄ አትሆንም!! ✍ እግዚአብሔር ሁሉን በልጁ የማድረግ እንጂ ሁሉን ጴንጤ የማድረግ ሀሳብ የለውም!! 📌 በክርስቶስ በመሆንህ ሕይወት ይኖርሃል ጴንጤ በመሆንህ ኃይማኖት ይኖርሃል!! ✍️ ወልድ ያለው ሕይወት እንጂ ኃይማኖት የለውም!! 📌 የወንጌል እንቅፋትና የሰው ትልቁ ጥላት ኃይማኖት ነው!! ✍️ ኃይማኖት ነፍስ የወንጌሉን ብርሃን እንዳትረዳ የሚጋርድ ጥልቅ ጨለማ ነው!! 📌 ክርስቶስ ሕይወትን እንጂ ኃይማኖትን አልሰጠም!! ✍️ በኃይማኖት ነፃነት በክርስቶስ ባርነት የለም!! 📌 በኃይማኖት ዳንኩ የሚል በክርስቶስ ጠፋሁ የሚል የለም!! ✍️ በኃይማኖት መፅደቁ የሚሰማው በክርስቶስ ኩነኔ የሚሰማው የለም!! 📌 በኃይማኖት እርሱ ማለት በክርስቶስ እኔ ማለት የለም!! ✍️ በኃይማኖት የሚያርፍ በክርስቶስ የሚቅበዘበዝ የለም!! 📌 በኃይማኖት ድፍረት በክርስቶስ ፍርሀት የለም!! ✍ ኢየሱስ የእምነታችን ራስና ፈጻሚ እንጂ የክርስትና ኃይማኖት መስራች አይደለም!! 📌 ያመኑበትን ሁሉ ሕይወት ሰጣቸው እንጂ ኃይማኖት አልሰጣቸውም!! ✍️ ሕይወት ያለው ኃይማኖት የለውም!!..............ሕይወት ክርስቶስ ነው!! 📌 ጴንጤ መሆንህ በክርስቶስ የመሆንህ ዋስትና አይደለም!! ✍ ኃይማኖት ኑሮህ ኃይማኖተኛ አለመሆን አትችልም!! 📌 ኃይማኖት ርዕስህን ከኢየሱስ ውጭ እንድታደርግ ትኩረትህን ይነጥቅሀል!! እናልህ ወዳጄ በክርስቶስ ነህ ወይስ ጴንጤ ነህ? Fyi 👉 መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኃይማኖት የሚል ቃል ካገኘህ እምነት(Faith) ለማለት ነው!! #በክርስቶስ_ነኝ!! #In_Christ!! #ሄኖክ_አሸብር
https://www.facebook.com/share/1aHegDAeYp/
1ኛ ጢሞቴዎስ 6 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋር ትልቅ ትርፍ ነው። ⁷ ምክንያቱም ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለም፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም። ⁸ ነገር ግን ምግብና ልብስ ካለን፣ ያ ይበቃናል። ⁹ ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ። ¹⁰ ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው፤ አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጒጒት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል። 5, በክርስትና ሕይወት ውስጥ መሸሽና መከታተል የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታዎች ናቸው። መሸሽ ብቻውን ትርጕም አያመጣም። መሸሽ በመከታተል ብርሃን ካልደመቀ፥ ቀድሞውኑስ ምኑን ሸሸነው? እናም ሐዋርያው የኹለቱን ሚዛናዊነት በመጠበቅ ጢሞቴዎስን "ሽሽ ግን ተከታተል"፥ "ራቅ ግን እምነትህን አጥብቀህ ያዝ" በማለት ይመክረዋል። መልእክቱ ለእኛም ያለው ምክርና ትምህርት ይሄ ነው። "ጽድቅን፥ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን" ልንከታተል ይገባናል። እነዚህን ነገሮች እያዘወተርናቸው በኼድን ቁጥር እግዚአብሔርን የመምሰል ልምምዳችንም ዐብሮ ከፍ እያለ መምጣቱ አይቀሬ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6 (ዐ. መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል። ¹² መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ። በነገር ኹሉ የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይኹን!🙏🙏
ክፍል 3(የቀጠለ) የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ልምምድ ተጨማሪ ገጽታዎች 1, ምንም እንኳን ምክሩ በቀጥታ የተሰጠው ከመበለቶች ጋር ተያይዞ ቢኾንም፥ በውስጥ ዐዋቂነት ለኹሉም አማኞች የሚኾን መልእክት እንዳለው አያጠያይቅም። ቅዱስ ጳውሎስ "እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር" በሚል ቁልፍ ሐረግ እምነትን በተግባር መግለጥ ወይም እውነተኛው መንፈሳዊ ሕይወት የማይቋረጥ የዕለት ተዕለት ትምህርት መኾኑን አስረግጦ ያስተምረናል። እምነትን መኖር የማያልቅ ትምህርት ነው። ብቻም ሳይኾን እምነትን መኖር በመማር የሚመጣ መንፈሳዊ ምግባርም ነው። በመማር ስንልም ሰዋዊ በኾነ የሥጋ ዕውቀትና ፍልስፍና ሳይኾን ከቅዱስ ቃሉ በሚቀዳ የእግዚአብሔር ትምህርት ነው። ትምህርቱ በቃኝ፥ ጨረስሁ፥ አወቅሁኝ ማለት የለውም። ትምህርቱ የየቀንና የኹሌ ነው። ስለዚህ፥ ያመንነውን እምነታችንን በተግባር ለማሳየት መትጋትን የየዕለት ልማዳችን ልናደርገው ይገባናል። ቃሉን ሰምቶ ማድረግም የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ኹነኛው መግለጫ ነው። በዚህም እግዚአብሔርን ወደ መምሰል እናድጋለን። እምነትን በተግባር ለማሳየት የእግዚአብሔር የኾነው ትምህርት እንዳለ ኾኖ በጸሎት መትጋትም እምነትን በተግባር የመግለጥን ዐቅምና ጥበብ የመስጠት ሚና አለው። በቃሉ ትምህርትና በጸሎት ትጋት የተሞላ ሰው፥ እምነቱን በተግባር በመግለጥ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና መኾኑ የማያጠያይቅ ሐቅ ነው። ስለዚህ እምነታችን መልካም ምስክርነት ያለው እንዲኾን በቃሉ ትምህርትም በጸሎት ልምምድም በእግዚአብሔር ፊት ማዘውተራችንን አንዘንጋ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ አንዲት መበለት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሯት፣ እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ቤተ ሰብ በመርዳትና ለወላጆቻቸውም ብድራትን በመመለስ ከሁሉ በፊት እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር ይገባቸዋል፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነውና። ⁵ በርግጥ መበለት የሆነች፣ ብቻዋንም የምትኖር ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ ታደርጋለች፤ ለጸሎትና የእግዚአብሔርን ርዳታ ለመለመን ሌሊትና ቀን ትተጋለች። … ¹⁰ ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለበጎ ምግባር ሁሉ ራሷን በመስጠት በመልካም ሥራም የተመሰከረላት መሆን አለባት። 2, ከሐሳብ እስከ ተግባር፥ ከንግግር እስከ ድርጊት የምንነቀፍበት ነገር ይኖር ይኾን? "ውይ እሱማ'ኮ... ውይ እሷማ'ኮ" የምንባልባቸው ነገሮች ይኖሩን ይኾን? በውጪ ያሉቱ ሰዎች፥ በውስጥም ያሉቱ ወንድሞችና እህቶቻችን የሚነቅፉብን ነገር ይኖራቸው ይኾን? በዚህም ምክንያት እናምነዋለን ያልነው ጌታና የወንጌል ትምህርት ተነቅፎ ይኾን? መልቀቅና መተው ያልፈለግናቸው ነገሮች ይኖሩን ይኾን?... እንግዲህ እናስተውል። ራሳችንንም እንጠይቅ። የት እንዳለንም እንፈትሽ። ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ማንም የሚነቀፍበት ነገር እንዳይኖር" ይላል። ክርስትና፥ በነጻነት ሽፋን እንደ ፈለግን ተለቅቀን የምንኖርበት ሳይኾን የሚነቀፍ ነገር እንዳይገኝብን በታላቅ ጥንቃቄ የምንመላለስበት ሕይወት ነው። ጥንቃቄውም መብትን፥ የግል ነጻነትን፥ እኔነትን መጣልን ይጠይቃል። ስለ ሌላው ምን አገባኝ? የሚል አስተሳሰብ ይዘን፥ ነቀፋ የሌለበትን ሕይወት መኖር አይታሰብም። ሰውም ኾነ ሰይጣን የሚነቅፍብን ነገር እንዳያገኙ፥ በእግዚአብሔር ትምህርት በአግባቡ ልንመላለስ ይገባናል። ከስማችን ይልቅ ለእግዚአብሔር ስም፥ ከእኛ ምቾት ይልቅ ለእግዚአብሔር ፈቃድና ክብር በመቆርቆር ዘወትር ስንመላለስ "እውነተኛው መንፈሳዊ ሕይወት" እያደር እየወረሰን ይመጣል። “ማንም የሚነቀፍበት ነገር እንዳይኖር፣ ይህንም ትእዛዝ ለሕዝቡ ስጥ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥7 (አዲሱ መ.ት) “ስለዚህ ባል የሞተባቸው ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ፣ ልጆች እንዲወልዱ፣ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ጠላትም የሚነቅፍባቸውን ነገር እንዳያገኝ እመክራለሁ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥14 (አዲሱ መ.ት) 3, አብዛኞቻችንን ሊያጠቁን ከሚችሉት ነገሮች መካከል ዋነኛው ይሉኝታ ነው። ይሉኝታ ማለት ለሌሎች ሲሉ ማለት ነው። ለሌሎች ሲሉ ራስን መለዋወጥ፥ አቋምን መቀያየር፥ አንዴ እንዲህ፥ አንዴ እንዲያ መኾን ይሉኝታ ነው። ይሉኝታ እሺ እንጂ እምቢ አያውቅም። በይሉኝታ ፊት አቋም ዐቅም የለውም። ከዚህም የተነሣ አብዛኛውን ጊዜ ለሌሎች ስንል የማንፈልገው ድካም ውስጥ እንገባለን። ጓደኞቻችንን ላለማሳዘንና እንዳይደብራቸው በሚል ጤና ቢስ ፍርሃት የያዝነውን ዕንቁ ሀብት እንደ ተራ ነገር ለግብዣ ስናቀርበው እንገኛለን። ብዙ ሰው ጽድቅን ሽጦ ዐመፅን፥ እውነቱን ጥሎ ስሜትን፥ ብርሃንን ለውጦ ጨለማን የሚገዛው በይሉኝታ ተተብትቦ ነው። እንግዲህ፥ የይሉኝታ ዐቅም ይህን ያኽል መኾኑን ከተረዳን፥ ታዲያ ለምንድነው ከዚህ እስራት ነጻ የማንወጣው? ለምንድነው ተስማምቶን የቀጠልነው? ሐዋርያው "አትቸኵል፥ አትተባበር፥ ጠብቅ" ያላቸውን ቃላት በማስተዋል የመረመርን እንደኾነ ጥልቅ መልእክትን የተሸከሙ ናቸው። ይሉኝታን መስበሪያና እውነተኛውን ሕይወት መኖሪያ መርሖዎች ጭምር ናቸው። ለፍርድና ለኵነኔ ባልቸኰልን ቁጥር፥ ከሌሎች ኀጢአት ጋር ለመተባበር ባለመፍቀድ በጽድቅ እምቢ እያልን ስንመጣ፥ ራሳችንን በንጽሕና መጠበቅና እግዚአብሔርን መምሰላችንን ማሳደግ እንጀምራለን። 1ኛ ጢሞቴዎስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²² በማንም ላይ እጅ ለመጫን አትቸኵል፤ ከሌሎችም ጋር በኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ። … ²⁴ የአንዳንድ ሰዎች ኀጢአት ግልጽ ነው፤ ከእነርሱም ቀድሞ ፍርድ ቦታ ይደርሳል፤ ሌሎችን ግን ኀጢአታቸው ይከተላቸዋል። ²⁵ መልካም ሥራም እንደዚሁ ግልጽ ነው፤ ግልጽ ያልሆነ ቢኖርም እንኳ ተሰውሮ አይቀርም። ከዚህ ጋር ተያይዞ ጠቢቡ ሰሎሞን ያስተማረንንም ምክር እዚህ ጋር መጥቀስ አስፈላጊ ነው። የጠቢቡ ምክር "እምቢ ማለት" የሚል ነው። ስለዚህ፥ እውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት የምንለሚመድው እምቢ በማለትም ነው። ያለ እምቢ፥ ጽድቅን በቁርጠኛነት መኖር የሚባል ነገር የለም። እምቢ፥ አልኼድም፥ አልፈልግም፥ አላደርግም ማለትን እንለማመድ። ምሳሌ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ እሺ አትበላቸው፤ ¹¹ “ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤ ¹² እንደ መቃብር፣ ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው እንዳሉ እንዋጣቸው፤ ¹³ ውድ የኾኑ ነገሮችን ኹሉ በያይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤ ¹⁴ ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣ ¹⁵ ልጄ ሆይ፤ አብረሃቸው አትሂድ፤ በሚኼዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ። 4, ምንም ቢከትቱበት የማይጠረቃውን ሆድ ለመሙላት ሲሉ፥ ቀን ከሌት ገንዘብን እያሳደዱ በማይረካ ሕይወት ውስጥ መመላለስ የመንፈሳዊው ሕይወታችን ኹነኛው ድክመት ነው። ባለንና በምናገኘው ነገር ላይ(ጥቂትም ኾነ ብዙ) በእግዚአብሔር መርካትን መለማመድ ይገባናል። ልክ ስለ እምቢታ እንዳወራነው ርካታም የእግዚአብሔርን ሕይወት በአግባቡ ለመኖር ወሳኙ ግብዓት ነው።
የሄኖክ አሸብር ግጥሞች እና ወጎች pinned «Join and Share በማለት የአገልግሎቱ ተካፋይና አካፋይ እንድትኾኑ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ።»
ክፍል 2(የቀጠለ) የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ልምምድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አማኞች በየቀኑ ሊለማመዷቸው ስለ ሚገቧቸው ኹለት ልምምዶች ወይም ሥልጠናዎች ይናገራል። የመጀመሪያው "የሥጋን ሥራ ይኸውም የዐሮጌው ሰው ኀጢአተኛን ዝንባሌዎችን" በመንፈስ ቅድስ ሳይሳሱ የመግደል ልምምድ ሲኾን ኹለተኛው ደግሞ እግዚአብሔርን የመምሰል ይኸውም እውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት ለመኖር ራስን የማሰልጠን ልምምድ ነው። አንዱ የመግደል፥ ሌላኛው ደግሞ የመኖር ልምምድ ነው። አንዱ ለዚህ ክፉ ዓለም የመሞት ሥልጠና(training) ሲኾን፥ ሌላኛው ደግሞ ለክርስቶስ ዓለም ሕያው ኾኖ የመኖር ልምምድ ነው። “እንደ ሥጋ ብትኖሩ ትሞታላችሁና፤ ክፉ የኾነውን የሥጋ ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ ግን፣ በሕይወት ትኖራላችሁ፤” — ሮሜ 8፥13 (አዲሱ መ.ት) 1ኛ ጢሞቴዎስ 4 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ እግዚአብሔርን ከማያከብር ርባናቢስ አፈ ታሪክና ከአሮጊቶች ተረታ ተረት ራቅ፤ ይልቁንም ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን። ⁸ የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤ ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአኹኑም ኾነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለኹለቱም ይጠቅማል። የሚገርመው ነገር፥ ሐዋርያው የእውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት ልምምድ ያያያዘው ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር ነው። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚፈለገውን ለውጥ እንዲያመጣና አካል(ሰውነት) ጠንክሮ እንዲጐለብት ሳይቋረጥ መደረግና መሠራት አለበት። ይሄ የስፓርት ዓለሙ ሕግ ነው። የስፓርቱ ዓለም ብቻም ሳይኾን የመንፈሳዊውም ሕይወት የዕድገትና የብስለት ሕግ ነው። አንድ body builder ሳይቋርጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባዘወተረ ቁጥር እየጠነከረና እየጐለበተ እንደሚኼድ ኹሉ፥ አማኞችም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ምልልስ ውስጥ እውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖሩ "ራሳቸውን ማሠልጠንና ማለማመድ" ይጠብቅባቸዋል። አኹን ዋናው ጥያቄ የሚኾነው፥ የሥጋን ሥራ እየገደልን፥ ለዚህ ዐይነቱ አኗኗር እንዴት ራሳችንን እናሠልጥን? የሚለው ነው። ለመኾኑ፥ እንዴት ነው ራሳችንን የምናሠለጥነው? 1, ለሚያምኑት ወንድሞችና እህቶቻችንን በሙሉ፥ አርኣያ(መልካም ምሳሌ) መኾን እንድንችል፥ በተግባራዊ አኗኗራችን ይኸውም(በንግግርና በኑሮ) ፍቅርን፥ እምነትና ንጽሕናን በየቀኑ በመለማመድ መንፈሳዊውን ብስለት ማምጣት ይቻላል። “ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ኹንላቸው።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥12 (አዲሱ መ.ት) 2, ልክ በስፓርቱ ዓለም Gym ቤት የኼዱ ሰዎች ሰውነታቸው እንዲገነባ በቤቱ ካሉት የብረት ዕቃዎች እያነሡ እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ቅዱስ ቃሉን በየቀኑ፥ በትጋት፥ በናፍቆት በማንበብ፥ ካነበብነው በማካፈል፥ ያነበብነውን በመኖርና በማስተማር መንፈሳዊውን ብስለት ማምጣት ይቻላል። ቃሉን ከማንበብ እየራቁ ግን መንፈሳዊ ሕይወትና እግዚአብሔርን መምሰል የሚባል ነገር የለም። “እኔ እስክመጣ ድረስ ለማንበብ፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥13 (አዲሱ መ.ት) 3, በውስጣችን የተቀመጠውን፥ በዐደራ መልክ የተሰጠንን የጸጋ ስጦታ ቸል ሳንል፥ ሰዎች ኹሉ ማደጋችንን ያዩ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ታማኝና ትጉህ ሠራተኞች አድርገን ስናቀርብ፥ መንፈሳዊውን ብስለት እየኖርነው እንመጣለን። በተሰጠን ስንታመንና የተሰጠን ላይ አተኵረን ስንሠራ፥ በእግዚአብሔር ፊት እየከበርን(መልካም ምስክርነት እያተረፍን) እንመጣለን። ይህም የእውነተኛው መንፈሳዊ ሕይወት ልምምድ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 4 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል። ¹⁵ ሰው ኹሉ ማደግህን ያይ ዘንድ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኵር፤ በትጋትም ፈጽማቸው። 4, ለምንሰማውና ለምናሰማው ነገር፥ ለምናምነውና ለምንናገረው ጉዳይ፥ ለምንማረውና ለምናስተምረው ትምህርት፥ ለምንሸምተው ዕውቀት አብልጠን በመጠንቀቅ፥ መንገዳችንን ከጥፋት ገበያ ማቀብና መንፈሳዊውን ብስለት መቀዳጀት እንችላለን። በፋንታው ደግሞ ለደራው የዕውቀት ገበያ፥ እሺ ያበዛንና፥ ኹሉን በሞኝነት እየቃረምን የገበየን እንደው፥ ያልጠየቅንና ያልፈተሽን እንደው፥ ገበያው ደርቶ ደርቶ እኛንም መዋጡ አይቀሬ ነው። ስለዚህ እኛም ኾንን የሚሰሙን እንዲድኑና እንዲጠበቁ ከፈለግን ለመንገዳችንና በማየት ወይም በመስማት ወይም በማንበብ ለምንሰብስበው ዕውቀት መጠንቀቅ አለብን። የምንሰማውንና የምናምነውን በጥንቃቄ መምረጥ የእውነተኛው መንፈሳዊ ሕይወት የማይቋረጠው ልምምድ ወይም የየዕለቱ ሥልጠና ነው። “ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥16 (አዲሱ መ.ት) እንግዲህ፥ የእግዚአብሔር ሰዎች የኾንን ኹላችን ይህንን የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ልምምድ ከአኹን ጀምሮ ማዘውተር እንጀምር። ቃሉን ማንበብ፥ ለቃሉ መታዘዝ፥ በቃሉ መኖር፥ ሥጋዊነትን በመንፈስ እየገደሉ ለፈቃደ እግዚአብሔር መገዛት የሕይወት መርሓችን ይኹን!🙏🙏 ክፍል 3... ይቀጥላል....
✍️ ስቃዩን ብቻ አትስበኩን!! ** ✍️ ኢየሱስን ከማይሰብኩ አገልጋዮች ብቻ ሳይሆን የኢየሱስን ስቃይ ብቻ ከሚሰብኩ አገልጋዮችም ተጠበቁ!! 👉 አማኞች ለኢየሱስ እስኪያዝኑ ድረስ ስቃዩን የምትተነትኑ አገልጋዮች ሆይ 📌 ስለእኛ ኃጢአት መደረጉንና እኛ በእርሱ የእግዚአብሔር ጽድቅ መደረጋችንን ንገሩን!! 📌 መጠላቱን ብቻ ሳይሆን በእርሱ መወደዳችንን ንገሩን!! 📌 የተናቀ መሆኑን ብቻ ሳይሆን በእርሱ መክበራችንን ንገሩን!! 📌 ራሱን ባዶ ማድረጉን ብቻ ሳይሆን በእርሱ ሙሉ መደረጋችንን ንገሩን!! ✍️ የጅራፉንና የሚስማሩን አይነት አውቀን በሞቱና በትንሳዔው ያገኘነውን በረከት ካላወቅን ምን ይጠቅመናል🙏🙏🙏 ✍️ መገለጥ ማለት የጅራፉንና የሚስማሩን አይነት ማወቅ ሳይሆን ክርስቶስ በመከራው ይዞን የገባበትን ክብር ማወቅ ነው!! ✍️ የክርስቶስ የመስቀል ሥራ አላማ ስቃዩን እያሰብን ከንፈር እንድንመጥ ሳይሆን ከከንፈሮቻችን ምስጋና እንዲወጡ ነው!! 📌 እርሱ ብላችሁ አትቁሙ በእርሱ ምን ሆንን? 📌 እርሱ ብላችሁ አትዝጉት ከእርሱ ጋር ምን ሆንን? 📌 እርሱ ብላችሁ አትደምድሙ ለእርሱ ምን ሆንን? ✍️ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ ሀዘን የተቀመጠች ሳትሆን በክርስቶስ ስራ ከእርሱ ጋር በአብ ቀኝ የተቀመጠች ናት!! 📌 የኢየሱስ ስቃይ ብቻውን ወንጌል አይደለም!! ✍️ እሰከ መቼ ስቃዩ ላይ ትቆያላችሁ? #ሄኖክ_አሸብር https://t.me/Henokashebir
✍ገና አልደርስም 👉 ደርሻለሁ!! **** 👉 በክርስቶስ ኢየሱስ ዘላለማዊ ሥራ....... 👇👇👇👇👇 ✍ ወደ ጽዮን ተራራ ደርሻለሁ!! ✍ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሻለሁ!! ✍ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም ደርሻለሁ!! ✍ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት ደርሻለሁ!! ✍ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር ደርሻለሁ!! ✍ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር ደርሻለሁ!! ✍ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች ደርሻለሁ!! ✍ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ ደርሻለሁ!! ✍ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሻለሁ!! 📌📌📌 #የመድረስ_ስጋት_የሌለብኝ_ከመድረስ_ስለጀመርኩ_ነው!! ✍ የደረስኩ እንጂ የምደርስ አይደለሁም!! ✍ ኢየሱስን የለበስኩ እንጂ ገና ኢየሱስን የምለብስ አይደለሁም!! ✍ በክርስቶስ የተሰወርኩ እንጂ ገና በክርስቶስ የምሰወር አይደለሁም!! 📌 በአብ ቀኝ የተቀመጥኩ እንጂ ገና በአብ ቀኝ የምቀመጥ አይደለሁም!! 📌 ያረፍኩ እንጂ ገና የማርፍ አይደለሁም!! 📌 የረካሁ እንጂ ገና የምረካ አይደለሁም!! 📌 የተረፍኩ እንጂ ገና የምተርፍ አይደለሁም!! 📌 የወረስኩ እንጂ ገና የምወርስ አይደለሁም!! 📌 ሕይወት ያገኘሁ እንጂ ገና ሕይወት የማገኝ አይደለሁም!! 📌 ጽዮን የደረስኩ እንጂ ገና ጽዮን የምደርስ አይደለሁም!! 📌📌📌 ምድር ላይ ያለሁት የተቀበልኩትን ጣፋጭ ዘላለማዊ ሕይወት ለሌሎች ለማካፈል እንጂ ወደ ጽዮን ለመጓዝ አይደለም!! ✍ የሆነውን ሁሉ ያደረገኝ የሆንኩትን ሁሉ ሆኖ ነው!! ✍ አሁን ያለሁት በአብ ቀኝ ነው!! ✍ አሁን ያለሁት በአባቴ እቅፍ ውስጥ ነው!! ✍ አሁን ያለሁት አፍቃሪዬ ጋር ነው!! ✍ አሁን ያለሁት ፍጹም ሰላም ውስጥ ነው!! ✍ አሁን ያለሁት የማያቋርጥ ደስታ እና እፎይታ ውስጥ ነው!! ✍ አሁን ያለሁት የዘላለም ሰንበት ውስጥ ነው!! ✍ 0% ስጋት!! ✍ ስጋት free ሕይወት!! ✍ወዳጆች ሆይ ማን እንዳለን ተመልከቱ፦ ❝ለእኛስ ነገር ሁሉ #ከእርሱ የሆነ እኛም #ለእርሱ የሆንን #አንድ_አምላክ_አብ_አለን፥ ነገር ሁሉም #በእርሱ በኩል የሆነ እኛም #በእርሱ በኩል የሆንን #አንድ_ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_አለን።❞ —1ኛ ቆሮንቶስ 8: 6 ♥ሁሉ ከእርሱ ከእግዚአብሔር፣ ሁሉ በእርሱ በክርስቶስ፣ ሁሉ ደሞ ለእርሱ ለእግዚአብሔር ነውና፣ ለእርሱ ለእግዚአብሔር ለዘላለም ክብር ይሁን!! https://t.me/joinchat/RrbSCabYHAXQ6nx7 #ሄኖክ_አሸብር
"የሕይወት ምስክርነታችን ምን ይመስላል?" በቤት ውስጥ ያሉ ቅዱሳን፥ በውጪ ያሉ ያላመኑ ሰዎች፥ እግዚአብሔር ራሱ ስለ እኛ ምን ይመሰክራሉ? ምንድናቸው ይሉናል? ስለ እኛ ተናገሩ ቢባሉ የሚናገሩት ምንድነው? እስቲ ኹላችንም ራሳችንን እንጠይቅ? ሐዋርያው ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ቅዱሳን በጻፈላቸው የመጀመሪያው መልእክቱ ላይ "ስለ ሕይወት ምስክርነት" አጽንዖት ሰጥቶ እንዲህ ይነግረናል። 1ኛ ተሰሎንቄ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ ከዚህም የተነሣ በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ ምእመናን መልካም ምሳሌ ሆናችኋል። … ⁹ በእንዴት ያለ አቀባበል እንደ ተቀበላችሁንና ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደ ተመለሳችሁ እነርሱ ራሳቸው ይናገራሉ፤ ¹⁰ ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ። የተሰሎንቄ ምዕመናን የሕይወት ምስክርነት፦ -> መልካም ምሳሌነት ያለው -> ሐዋርያቱን እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ በሚገባ የተቀበሉ -> ሕያው እግዚአብሔርን ለማገልገል ከጣዖታት ዘወር ያሉ -> ኢየሱስ ክርስቶስ በናፍቆት የሚጠባበቁ.... የሚል ምስክርነት ያለበት ነው። እንዲህ ይመሰከርልናል ወይ? የቤቱ ሰዎችም የውጪ ሰዎችም ስለ እኛ እንዲህ ይናገራሉ ወይ? “በእናንተ በምታምኑት መካከል ሳለን እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅ እንዲሁም ያለ ነቀፋ ሆነን እንደኖርን እናንተም እግዚአብሔርም ምስክሮች ናችሁ።” — 1ኛ ተሰሎንቄ 2፥10 (አዲሱ መ.ት) ከተሰሎንቄ ሰዎችም ባሻገር፥ ሐዋርያው ራሱ፥ "የራሱን የሕይወት ምስክርነት" ምስክሮችን እየጠቀሰ በሙሉነት ይናገራል። ከምስክሮቹም መኻል "እግዚአብሔር"ን ይጠቅሳል። አስባችሁታል? እግዚአብሔር ስለእናንተ እንዲህ ሲመሰክር? በርግጥ ይህ ኹኔታ፥ እግዚአብሔር በዕለት ተዕለት አኗኗራችን ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዳለው የሚያሳይ ነው። እርሱ እኛን ኹሌ ጊዜ ይከታተለናል። በየት በኩል እየኼድን፥ ምን ምን እየሠራን እንዳለ፥ ምን እንደ ምንመስል ጠንቅቆ ይመለከታል። ምስክርነትም ይሰጠናል። ወሳኙ ጥያቄ፥ ምን ይመሰክርልናል? የሚለው ነው። ሐዋርያው ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ስላለው ምስክርነት ሲናገር፥ "በቅድስና፥ በጽድቅና ያለ ነቀፋ ስለ መኖሩ" ይናገራል። እንግዲህ፥ በቤት ውስጥ ባለቱ ዘንድ፥ በውጭም ባሉቱ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ ሊኖረን ስለ ሚችለው ምስክርነት ልንጠነቀቅ ይገባናል። መልካም ምስክርነት ያለው ሕይወት መኖር እንድንችል መንገዳችንን ልናስተውል፥ ሰማያዊውን ጥበብ ልንለምን፥ በጸጋው ልንደገፍ ይገባናል።🙏 እግዚአብሔር፥ መልካም ምስክርነት ያለው የማይነቀፍ ሕይወት ይስጣችሁ!🙏
ይህን የናታን በርገና አገልግሎት ሲኾን፥ ከፍቅሩ ተነሣሽነት- በጸጋው ምሕረት- ለክብሩ ምስጋና መጠራታቸውን በመገንዘብ በኑሯቸው ኹሉ ለእግዚአብሔር ደስታ መኖር እንዲችሉ ክርስቲያኖችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት እንዲጎለብቱ መትጋትን በዐላማነት አንግቧል። https://t.me/NatanBergena
ይህን የናታን በርገና አገልግሎት ሲኾን፥ ከፍቅሩ ተነሣሽነት- በጸጋው ምሕረት- ለክብሩ ምስጋና መጠራታቸውን በመገንዘብ በኑሯቸው ኹሉ ለእግዚአብሔር ደስታ መኖር እንዲችሉ ክርስቲያኖችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት እንዲጎለብቱ መትጋትን በዐላማነት አንግቧል። https://t.me/NatanBergena
ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ከክርስቶስ ጋር ካላችሁ አንድነት የተነሣ የትኛውም መበረታታት፣ ከፍቅር የሆነ መጽናናት፣ የመንፈስ ኅብረት፣ ምሕረትና ርኅራኄ ካላችሁ፣ ² በአንድ ሐሳብ፣ በአንድ ፍቅር፣ በአንድ መንፈስና በአንድ ዐላማ በመሆን፣ ደስታ ዬን ፍጹም አድርጉልኝ። ³ ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትሕትና ቊጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ። ⁴ እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ። ⁵ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤ ⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ⁸ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ⁹ ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤ ¹⁰ ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣ ¹¹ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ያ አስተሳሰብ" ሲል mindset(የልቡና ውቅር) ይሰጠናል። ምንና እንዴት ማሰብ እንዳለብን፥ ልንኖርበት ስለሚገባን የአኗኗር ቅኝት፥ አእምሯችን ውስጥ በሙላት ሊከማች ስለሚገባው "አስተሳሰብ" ይነግረናል። "ያ" በማለት የገለጸው አስተሳሰብ "በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የነበረው" ነው። ክርስቶስ የኖረበት፥ የተመላለሰበት፥ even ሰውን ኾኖ ወደ ምድር የመጣበት፥ አባቱን የታዘዘበት "አስተሳሰብ" የእኛም እንዲኾን ነው የሐዋርያው ምክሩ። እስቲ እንደው ዛሬ ራሳችሁን ጠይቁ! ቆም ብላችሁ ራሳችሁን ፈትሹ! በርግጥ "ያ አስተሳሰብ" በእኛ ውስጥ አለ? የምናስበው ክርስቶስ እንዳሰበው ነው ወይስ እኛና እርሱ ተራርቀናል? በእርሱ ያለው- በእናንተም ይኑር ከተባለ፥ ክርስቶሳዊው መርሑም ይኼ ከኾነ፥ ታዲያ እኛ የት ነው ያለነው? ልባችንንና አእምሯችንን የሞሉት አስተሳሰቦችስ የትኞቹ ናቸው? በርግጥ "ያ አስተሳሰብ" የእኛም ነውን? "ያ አስተሳሰብ" በዝቶና ተትረፍርፎ በእኛም እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ በጥበብ፥ በአእምሮና በማስተዋል ኹሉ ይብዛልን! አሜን!🙏🙏🙏
እንግዲህ በምስጋና፥ በመንበርከክ፥ ያለማቋረጥ፥ ኹል ጊዜ፥ በመንፈስ ቅዱስ ጸልዩ!🙏🙏🙏 የእግዚአብሔር ጸጋ ይብዛላችሁ!🙏