tgindex
Grace Commission

Grace Commission

Статистика

የታረቀ ማኅበረ ሰብ _ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥20

Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 540
+3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 101
20 постов
Вовлечённость
82,7%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
345
1/48двое суток
395
1/72трое суток
426

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በዚህ ሊንክ ገብተው ድምፅ ይስጡ! https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZMqmGgXJMRGUIvi6ZrTucv_j4H8vTTTe1vt-hpvod4AHvnQ/viewform

  • видео или голосовое, без подписи

  • Grace Commission pinned a photo

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ጌታ እንዴት ቸር ነው? የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ለ2018 ዓ.ም. ለሚያደርገው የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት፣ የራሴ መጽሐፍ እና ኹለት አርትዖት የሠራሁላቸው መጻሕፍት በዕጩነት ቀርበዋል። እነዚኽን መጻሕፍት አንብባችሁ ከተጠቀማችሁ ድምፅ በመስጠት እንድታበረታቱን እጠይቃለኹ። 👉 የእኔ እና የእኅት ኤልሳ ጀንበሬ መጽሐፍ በመንፈሳዊ እድገት ዘርፍ ዕጩ ኾኖ ቀርቧል፦ 👉 የፓስተር መኳንንት ዓለሙ ደግሞ በተግባራዊ ነገረ መለኮት ዘርፍ ዕጩ ኾነው ቀርበዋል። 👇 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZMqmGgXJMRGUIvi6ZrTucv_j4H8vTTTe1vt-hpvod4AHvnQ/viewform

  • "ስለ ነገሮች የምናውቀው ዕውቀት እጅግ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም፣ ማን መሆናችንን ማወቅ በጣም የላቀ ዕውቀት ነው። ምክንያቱም፣ ማንነትን ማወቅ ራስን ማወቅ ነው፤ ራስን ማወቅ የተፈጠርንለትን ዐላማ ማወቅ ነው፤ የተፈጠርንለትን ዐላማ ማወቅ አካሂያዳችንን ማሳመር ነው" _ብሬኒ ብራውን

  • 30 июн.1 2816

    #ወንጌል ለሁሉም፤ ሁሉም #ለወንጌል!

  • 29 июн.1 551208

    የልጁ መልክ የክርስትና ዋና ግብ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን መምሰል ነው። ይህ የእግዚአብሔር ዐላማ፣ ከመፈጠራችን በፊት የታቀደ ነው። እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና።" ሮሜ 8፥26 እንዴት ያለ ድንቅ ውሳኔ ነው! ይህን ዘላለማዊ ዐላማ እውን ለማድረግ፣ እግዚአብሔር ዛሬም እየሠራ ነው፤ በክርስቶስ በኲል በእኛ ውስጥ የጀመረው ሥራ ገና አልተጠናቀቀምና። ሕይወታችን በምንም ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ፣ እግዚአብሔር ዐላማውን አይተውም። በምናልፍበት በእያንዳንዱ ሁኔታ፣ የራሱን ዕቅድ እየፈጸመ ነው። ሁሉንም ነገር፣ ሁሉንም አጋጣሚ ወደ አንድ ክቡር ፍጻሜ ለማምራት ይጠቀምበታል። እኛ ዝም ያለ በሚመስለን ጊዜም እንኳ፣ ርሱ ያለማቋረጥ እየሠራ ነው። ስለዚህ ልጁን የማይመስል ነገር ሁሉ ከሕይወታችን እየጠረበ ይወገዳል። ክርስቶስም በሕይወታችን በሁሉ ነገር ቀዳሚ ስፍራውን እንዲይዝ ያደርጋል። አሜን! ኢየሱስን የማይመስል ማንኛውም ባሕርይ፣ አስተሳሰብ እና አኗኗር ከእኛ ላይ፣ ደረቅ ቅጠል ከዛፍ ላይ እንደሚረግፍ ይርገፍ! የክርስቶስ መልክ ግን በእኛ ውስጥ ዕለት ዕለት ይገለጥ። አሜን! * ከላይ ያለው ታሪክ የተወሰደው፣ ሮናልድ ደን "ሰማዩ ዝም ሲል" በሚል ርእስ ከጻፈው መጽሐፉ ነው።

  • መንፈሳዊ ነገሮችን፣ ለምሳሌ፦ መጸለይ፣ ስብከት ማዘጋጀት፣ ዝማሬ መጻፍ፣ መጽሐፍ መጻፍ፣ ወንጌል መናገር፣ ለሌሎች ማካፈል፣ ... በቀላሉ ማንቀሳቀስ የሚቻለው፣ የእግዚአብሔርን ቃል በወጥነት እና በቋሚነት በማንበብ ነው!

  • "ስለ ኢየሱስ የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዝ ከእግዚአብሔር ጋራ የተስተካከለ ሕይወት መምራት አይቻልም" _ ዋረን

  • ቤተ ክርስቲያን በወጥነት በመስቀሉ ቃል ትርክት ውስጥ መኖር አለባት!

  • በነገራችን ላይ እውነትን በዐመፅ (በተንኮል ወይም በአለመታዘዝ) በሚያፍኑ (በሚያድበሰብሱ) ሰዎች ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ይገለጣል! (ሮሜ 1፥18)

  • መሆን ወይም አለመሆን! ታላቁ እስክንድር፣ በአንድ ወቅት በርሱ ስም የሚጠራ ወታደር ሲሸሽ ተመልክቶ፣ "ወይ ተዋጋ፤ ወይ ስምህን ቀይር" አለው።

  • "እግዚአብሔር ከምን እንዳዳነን ብቻ ሳይሆን፣ ለምን እንዳዳነን በቅጡ ልንገነዘብ ይገባል።" ማርቆስ ዘ/ብርሃን (ዶ/ር)

  • የዮሴፍ እና የወንድሞቹ ፍጻሜ ለምን ተለያዬ? ዮሴፍ እና ወንድሞቹ [ቤተ-ሰቦቹ] ወደ ግብፅ የገቡበት መንገድ [ምክንያት] ይለያያል። ዮሴፍ ተሽጦ፣ እነርሱ ተቸግረው። ዮሴፍ እንደ ባሪያ፣ እነርሱ እንደ ነጋዴ። ርሱ ተገዝቶ፣ እነርሱ እህል ሊገዙ። ዮሴፍ ተገዶ፣ ወንድሞቹ ወደው። ዮሴፍ ወደ ግብፅ ባሪያ ሆኖ ቢገባም፣ ገዥ [ለመፍትሒ የሚፈለግ ሰው] ሆኖ ኖሯል። ወንድሞቹ በዮሴፍ ምክንያት ለጊዜው ቢከበሩም፣ ከርሱ መሞት በኋላ በግብፅ ባሪያዎች ሆነዋል። ለ430 ዓመታት ያህል አስከፊ የባርነት ጊዜ አሳልፈዋል። የዮሴፍን መሸጥ ሦስት ውጤቶች አምጥቷል። 1) ዮሴፍን ራእይ አካል አስይዟል። (ለራሱ) 2) ቤተ-ሰቡን ከራብ አድኗል። (ለቤተ-ሰቡ) 3) የግብፅን ሕዝብ ከራብ አትርፏል። (አስተዳደራዊ መፍትሔ) የዮሴፍ እና የወንድሞቹ ፍጻሜ ለምን ተለያዬ? ምናልባት ወንድሞቹ የዘሩትን አጭደው ይሆን? በሁለቱ መካከል ልዩነት ያመጣው፣ ራእይ እና ምልልስ ይሆናል። ዮሴፍ የሆነውን የሆነው በተቀበለው ራእይ፣ በአምላኩ ሞገስ እና በንጹሕ ምልልሱ ምክንያት ነበረ።

  • #መንገዳችን ይለያያል! ዮሴፍና ሙሴ ወደ ቤተ መንግሥት የገቡበት መንገድ ይለያያል። ዮሴፍ ሕልም ፈትቶ [ምክረ ሐሳብ አቅርቦ] ሲሆን ሙሴ ግን በንጉሡ ሴት ልጅ ፊት ምገስ አግኝቶ ነው። ዮሴፍ በሌላ ስፍራ ተሠራ፥ ሙሴ በቤተ መንግሥት እየተሠራ አደገ። ዮሴፍ በግብፅ ነግሷል። ሙሴ ግን ቤተ መንግሥቱን ትቶ ሄዷል። ዮሴፍ በግብፅ መንገሡ፣ ሙሴም ንግሥናን መተዉ ሁለቱም ግብ ነበረው። የዮሴፍ መንገሥ፣ በዋናነት ለግብፃውያን ነበረ። የሙሴ ንግሥናን መተው ደግሞ ለእስራኤላውያን ነጻ መውጣት ነበረ። የሁላችንም መንገድ የግድ አንድ ዐይነት መሆን አይጠበቅበትም። ዋናው ነገር፣ ኑሯችን የመለኮት ዐላማና ቅኝት ይኑረው!

  • #የብቻዎች (Sola) መርሕ #ለኦርቶዶክስ "ብቻ" የሚለው ቃል፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አስተምህሮ ቅቡል (Acceptable) አይደለም። ቃሉን ባንወደውም፣ ግዴታ፣ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ አለ። በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለበትን ሁኔታዎች እንመልከት፦ 1) የእግዚአብሔርን አምላክነት ለመግለጽ “አሁንም እኔ ብቻዬን* እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር* አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ ከእጄም የሚያድን የለም።” — ዘዳግም 32፥39 “ብቻውን* አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 “አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ*፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።” — ነሀምያ 9፥6 እነዚህ ክፍሎች፣ የእግዚአብሔርን ብቻነት [ርሱ ብቻ አምላክ እንደ ሆነ] ያመለክታሉ። 2) የእግዚአብሔርን መፍጠርና ማዳን በሚመለከት “እርሱ ብቻውን* ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤” — መዝሙር 136፥4 “ብቻውን* ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤” — መዝሙር 136፥7 “እግዚአብሔር ብቻውን* መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።” — ዘዳግም 32፥12 እነዚህ ቁጥሮች ደግሞ፣ እግዚአብሔር ያለ ማንም ድጋፍ ብቻውን ስላደረጋቸው ነገሮች [መፍጠር፣ መጠበቅ፣ ማዳን] ይናገራሉ። ብቻ (Only, Alone) የሚለው ቃል፣ የግድ ጥቅም ላይ እንደሚውል መስማማት ይጠበቅብናል! ኦርቶዶክስ ወደ #መሠረቷ እንድትመለስ እና የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲከናወንባት፣ የግድ አንዳንድ ብቻዎችን [ሶላዎችን] መቀበል ይኖርባታል። ለምሳሌ፦ _ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ (sola scriptura) _ ክርስቶስ ብቻ (solus Christus)፣ _ ጸጋ ብቻ (sola gratia)፣ _ እምነት ብቻ (sola fide) እና _ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ (soli Deo gloria) እነዚህ ብቻዎች (only, alone) የሉተር ተሐድሶ ምሰሶዎች መሆናቸው ይታወቃል። በወቅቱ የነበረውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የአስተምህሮ ችግሮች፣ ለመፍታት የቀረቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመፍትሔ ሐሳቦች ነበሩ። እነዚህ ብቻዎች፣ በእኛ ሁኔታና #ዐውድ (context) አሁንም መደገም እንዳለባቸው አምናለሁ። ጥቂት ትንታኔ፦ 1_ "የእግዚአብሔር ቃል ብቻ" (sola scriptura)፦ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሲባል፣ አዋልድ መጻሕፍት ነፍሳችን ውስጥ ይጋፋሉ። በዚህ ጉዳይ ሁለት ነገሮች ልጠቁም፦ የመጀመሪያው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማለት፦ የእግዚአብሔርን ሙሉ ምክር ለመረዳት፣ [የመዳንን እውቀት ለማግኘት፣  ለትምህርት፣ ለተግሳጽ  ወዘተ.] መጽሐፍ ቅዱስ በቂ እና ብቁ ነው ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ፣ ስልጣን (Authority) ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ማለት ነው። ሌሎች አዋልድ መጻሕፍት፣ ባለሥልጣናት አይደሉም። ሌላው አንድ ኦርቶዶክስ የሆነ ሰው ማድረግ ያለበት፣ አዋልድ መጻሕፍት የምር የመጽሐፍ ቅዱሱ ልጆች መሆናቸው አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ነው።  ይህን ሲያደርግ፣ መጽሐፍ ቅዱሱን የትምህርት መመዘኛ እና የቀኖና መስፈሪያ ማድረግ ይኖርበታል። 2_ "ክርስቶስ ብቻ" (solus Christus)፦ ይህን ሐሳብ ከመዳን አንጻር መመልከት ተገቢ ነው። የሰው ልጆች መዳን፣ የሥላሴ ምክርና ፈቃድ ቢሆንም፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሱታፌ ቢኖራቸውም፤ የተሰቀለው፣ የሞተው እና የተነሣው አዳኙ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። በዚህ ምክንያት፣ መዳን በርሱ ብቻ መሆኑ በቃሉ ውስጥ ተገልጿል፦ “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” — ሐዋርያት 4፥12 “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ሲባል፣ ወደ አእምሯችን የሚመጡ ሌሎች አዳኞች መኖር የለባቸውም። አዳኙ አንድ ነው፤ አንድየ እንደምንለው። 3_ "ጸጋ ብቻ" (sola gratia)፦ "ጸጋ ብቻ" ማለት የመዳናችን ጉዳይ ከክርስቶስ ሥራ ጋራ ብቻ የተገናኘ መሆኑን ያሳያል! "ጸጋ ብቻ" ማለት፣ መዳን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ያሳያል። መዳን ሠርተን የምናገኘው አይደለም! መዳን ሠርተን ወደ ፊት የምንሸለመው አይደለም! (ሮሜ፣ ኤፌሶን እና ገላትያ ይነበቡ) 4_ "እምነት ብቻ" (sola fide)፦ ይህ የሚያሳየው መዳንን ለመቀበል መሥራት እንደማይጠበቅብን ነው። ማመን፣ አዳኙን የእግዚአብሔር ጸጋ፣ መቀበል ማለት ነው። (ገላትያ 2፥16 ኤፌሶን 1፥13) ለመዳን ምንም ዐይነት ሥራ መሥራት፣ ምንም ዐይነት ምስጢራት መፈጸም አያስፈልግም! ጸጋና እምነት፣ እንዴት አብረው እንደሚሠሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ያስረዳል፦ "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።" (ኤፌሶን 2፥8_9) የመልካም ሥራ ጉዳይ፣ ኤፌሶን 2፥10 ላይ ተገልጿል። ለመዳን ሳይሆን ስለዳንን የምናደርገው ነው! ውጤቱ ደግሞ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥10 ላይ ይታያል! 5_ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ (soli Deo gloria)፦ ክብር በዚህ ዐውድ አምልኮን ገላጭ ነው። ለአምላክ የሚገባውን ክብር፣ ውዳሴ፣ ዝማሬ፣ ምስጋና፣ አምልኮ እና ቅኔ፣ ለሌሎች መስጠት የለብንም! ብዙ ኦርቶዶክሳውያን፣ እግዚአብሔርን ብቻ እናመልካለን ብለው ያምናሉ። አንዱን እና እውነተኛውን አምላክ የምናመልክ ከሆነ፣ የሚዘመርለት መልአክ፣ ጻድቅ፣ ቅዱስ፣ ሰማዕት ሊኖር አይችልም! #ብቻዎችን (Sola) #ለኦርቶዶክስ እንደ መፍትሔ ማሰብ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የተሐድሶ መንገድ መከተል ነው! #በርናባስ #ዘመነ

  • ኢየሱስን #ከእምነት #ተቋምህ በላይ ትወደዋለህ? ምንአልባት ኦርቶዶክስ ትሆናለህ፤ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት በላይ፣ ኢየሱስን ትወደዋለህ? ካቶሊክም ከሆንህ፣ ከእምነትህ ተቋም በላይ ኢየሱስን ትወደዋለህ? ወንጌል አማኝም ከሆንህ፣ ኅብረት ከምታደርግበት አጥቢያ በላይ ኢየሱስን ትወደዋለህ? አንዳንድ ሰዎች ከኢየሱስ ይልቅ ለሃይማኖታቸው ከፍ ያለ ቅናት አላቸው። ለዚያም ነው ኢየሱስን ትተው #ተቋም #ለማስቀጠል ሁሉንም ዋጋ የሚከፍሉት። እንደ እግዚአብሔር ቃል የታነጹ ተቋማት፣ እጅግ በጣም ያስፈልጋሉ። በልባችን የኢየሱስን ያህል ስፍራ ግን አይገባቸውም። #የትኛውም #ነገር ለኢየሱስ ያለንን ''ንጽሕና እና ቅንነት" ከለወጠ ከእግዚአብሔር አይደለም! #ኢየሱስ ከተቋማቱ በፊት ነበረ! የእኛ ጌታ #ከተቋማቱ በኋላም ይኖራል!

  • <<ክርስቶስ እንዲከብርና እንዲመሰገን የሚፈልግ ሰው የሚከብርበትን መንገድ መምረጥ አይችልም።>> ምኒልክ አስፋው

Grace Commission — tgindex