የቃ/መ/ብ/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ሐመረ ሕይወት ሰ/ት/ቤት
Статистика- Последний пост
- 14 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ውድ የሰ/ት/ቤታችን አባላት ሰንበት ትምህርት ቤታችን በቀጣይ ለሚያደርጋቸው መንፈሳዊ ጉዞዎች ለጉዞ የሚሆን መሪ ቃል በቋሚነት ስያሜ ለመስጠት ተፈልጓል። ስለሆነም ለምናከናውነው መንፈሳዊ ጉዞ ይሆናል የምትሉትን መሪ ቃል በዚሁ ግሩፕ ላይ እንድታኖሩልን ስንል እንጠይቃችኋለን ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
"ባንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደሆነው መሰብሰባችንን አንተው እርስ በእርሳችን እንመካከር እንጂ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።" -ዕብራውያን 10:25- የ፳፻፲፰ የታህሳስ ወር ፫ተኛ ዙር የተልዕኮ (የርቀት)ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ትምህርት የተከናወነ መርሐ ግብር በፎቶ ይህን ይመስላል:- የቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ሐመረ ሕይወት ሰ/ት/ቤት የተልዕኮ ት/ት ክፍል ታህሳስ ፳፮/፬/፳፻፲፰ዓ/ም
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ሐመረ ሕይወት በአይነቱ ለየት ያለ መርኃ ግብብር አዘጋጅታለች እርሶዎም ያለወቁትን በማሳወቅ የመርኃ ግብሩ ታዳሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል https://vm.tiktok.com/ZMDLGJ1u7/ https://youtube.com/@hamerehiwetmedia19?si=vGbhqXqC26C7m_wz
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ሐመረ ሕይወት በአይነቱ ለየት ያለ መርኃ ግብብር አዘጋጅታለች እርሶዎም ያለወቁትን በማሳወቅ የመርኃ ግብሩ ታዳሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል https://vm.tiktok.com/ZMDLGJ1u7/ https://youtube.com/@hamerehiwetmedia19?si=vGbhqXqC26C7m_wz
የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በ2017ዓ.ም የሥርአተ ትምህርት ትግበራ አፈጻጸም ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች አንደኛ መውጠቱን አስመልክቶ ከብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ እና ሐድያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ እጅ የዋንጫውን ሽልማት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመገኘት ተረክቧል። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጥቅምት 30/2018ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ከ164ገዳማት እና አድባራት ምዘና የወሰዱ እና ወደቀጣይ እርከን የተዘዋወሩ ከ11,885ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር መከናወኑ ይታወሳል። በእለቱ ተመራቂ ተማሪዎች በብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ቡራኬ የተቀበሉ ሲሆን ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች እና ሰንበት ት/ቤቶች ከብጹአን አባቶች እጅ ሽልማት ተቀብለዋል። ከየክፍለ ከተማው ከአንደኛ እሰከ3ኛ የወጡ ሰንበት ት/ቤቶች በቅደም ተከተል ከልደታ ቂርቆስ አዲስከተማ ክፍለከተማ 1ኛ ቅድስት ልደታ ለማርያም ተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት 84% 2ተኛ መካነ ሰማእት ቅዱስ ቂርቆስ ሰት/ቤት 83% 3ተኛብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰንበት ት/ቤት 76% አራዳ እና ጉለሌ ክፍለከተማ 1ኛ ቅ.ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፍቁረ እግዚ ሰ/ት/ቤት 84% 2ኛደብረ ሲና ቅ/እግዚአብሔር አብ እጸጳጦስ ሰ/ት/ቤት 81% 3ኛ እንጦጦ መንበረ መንግስት ቁስቋም ማርያም 79% ንፋስ ስልክ ላፍቶክፍለከተማ 1ኛ ጀሞ መድኃኔ ዓለም ሰ/ት/ቤት 85% 2ተኛ ጽርሐ ንግስት ቅድስት ሐና ሰ/ት/ቤት 83% 3ኛ ላፍቶ ደብረ ትጉሀንቅ.ሚካኤል 79% ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ 1ኛ ሰዋሰው ብርሃን ቅ/ጳውሎስ 82% 2ኛ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ፍኖተ ሰላም ሰ/ት/ቤት73% 3ኛአስኮ ደብረ ገነት ቅ/ገብርኤል ሐመረ ብርሃን ሰ/ት/ቤት 69% አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 1ኛ አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔ ዓለም ሰ/ት/ቤት82% 2ኛቃሊቲ መካነ ብርሃንቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት79% 3ኛሳሪስ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም ሰ/ት/ቤት 77% ቦሌ ክፍለከተማ 1ኛደብረ ምጥማቅ ቅድስት ሰአሊተ ምህረት እና ቅ/አርሴማ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት 94.5% 2ኛ ቦሌ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት78% 3ኛየቦሌ ደብረ ሳሌምመድኃኔዓለም መጥምቀ መለኮትቅዱስዮሐንስካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት 69% የካ ክፍለ ከተማ 1ኛኮተቤ ደብረ ልዳ ቅ/ጊዮርጊስ እናቅ/ኪዳነ ምህረት ሰ/ት/ቤት 72% 2ኛ ኮተቤ ዳግማዊ ቁልቢቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት71% 3ኛፈረንሳይ ፈለገ ሕይወት አቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰ/ቴ/ቤት 65% ለሚኩራ ክፍለከተማ 1ኛ ሲኤም ሲ ቅዱስ ሚካኤል ሰ/ት/ቤት 82% 2ኛሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔ ዓለምሰ/ት/ቤት76% 3ኛ ካራ አሎ ደ/ም/ደ/ቀ መድኃኔዓለም እና የጻድቁ አቡነ ገሪማ ገዳም70% በማምጣት በክፍለ ከተማ ከአንድ እሰከ ሶሶት የወጡ ሲሆን የሰንበት ት/ቤቶችን የውድድር መስፈርት 1- የትምህርት ጥራት 50 በመቶ 2የትምህርት ተደራሽነት 50በመቶ ሲሆን የትምህርት ጥራትን በተመለከተ አንድ ሰንበት ት/ቤት ጠቅላላ ያስፈተነው ተማሪ ውጤት ተደምሮ ለጠቅላላ ተፈታኝ ተማሪ ብዛት ሲካፈል 50ከመቶ የትምህርት ጥራት መለኪያ ። የትምህርት ተደራሽነትን በተመለከተ ለሁለት ተከፍሎ ሶስቱንም እርከን ያስፈተነ 20ከመቶ ። የተፈታኝ ተማሪ ብዛት 30ከመቶ በድምሩ የትምህርት ተደራሽነት 50%ተይዟል። በዚህ ውድድር በአጠቃላይ ከአዲስ አበባ ከሚገኙ 248ሰንበት ትቤቶች ከቦሌ ክፍለ ከተማ የደብረ ምጥማቅ ቅድስት ሰአሊተ ምህረት ማርያም እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት 94.5%በማምጣት አንደኛ ። ሁለተኛ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ጀሞ መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት በ 85% በማምጣት። በሶስተኝነት ከልደታ ቂርቆስ አዲስከተማ ክፍለ ከተማ ቅድስት ልደታ ለማሪያም ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት እና ከአራዳ እና ጉለሌ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፍቁረ እግዚ ሰንበት ት/ቤቶች ሁለቱም እኩል 84% በማምጣት ሦሥተኛ በመውጣት ከአዲስ አበባ የተሻለ አፈጻጸም አሳይተዋል። በዚህ አጋጣሚ በሚሊኒየም አዳራሽ በነበረው የዋንጫ ሽልማት ስነስርአት የደብረ ምጥማቅ ቅድስት ሰአሊተ ምህረት እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤትጋር ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አሳውቋል።
видео или голосовое, без подписи
በአጫብር ስም በሰንበት ት/ቤቶች የሚሰጥ ስልጠናን እግድ እንዳልተነሳ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አስታወቀ። በ16 /3 /2018ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 1/545/2018ዓ.ም ከመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የወጣውን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ በአጫብር ስም በሰንበት ት/ቤቶች የሚደረግ ጥናቶችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ እንደተሻረ አድርገው አንድ አንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ የሐሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል። የአንድነቱን ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ተከትሎ መጋቤ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ ነሐሴ 26/2017ዓ.ም ለጠቅላይ ቤተክህነት ባሰገቡት ማመልከቻ መነሻነት በትምህርት እና ስልጠና ማሰልጠኛ መምሪያ በኩል የማጣራት ስራ ተከናውኗል ። በሂደቱም የትምህርት እና ማስልጠኛ መምሪያ ኃላፊዎች መጋቤ ሃይማኖት ዲበ ኩሉ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ፣ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት ተወካዮች እና ሌሎች በርዕሰ ጉዳዩን ለመከታተል የመጡ አባቶች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ የተነሱ ጭብጦች በቅድስት ቤተክርስትያን አጫብርን እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው መጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ በአዲስ አበባ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ሰንበት ት/ቤቶች ጥናት እንዲያቆሙ የተላለፈው ውሳኔ እሳቸውን ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚል ሲሆን በውይይቱም አሁን ያለው በአጫብር ስም የሚደረገው ጥናት እና ትእይንት በከፍተኛ መልኩ ቤተክርስትያንን እያስተቸ የሚገኝ መሆኑ እና እግዱ ተገቢ መሆኑንን በውይይቱ ላይ የተሳተፋ አካላት በሙሉ የተስማሙበት ሲሆን በተለይም መጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኅየሰ እኔም በማየው ነገር አዝናለሁ አጫብር እንዳስጠና ቅዱስ ሲኖዶስ የፈቀደው ለእኔ ብቻ ነው ። ከዛ ውጪ የሚደረገውን ጥናት እኔም እቃወማለሁ የኔ ጥያቄ ለምን መስመር የሳተው ነገር ታገደ አይደለም እኔ የተፈቀደልኝ ሆኖ እያለ ለማስጠናት ስላልቻልኩ እሱ እንዲስተካከልልኝ ነው በሚል በሰንበት ት/ቤቶችም ሆነ በሌሎች ባልተፈቀደላቸው አስጠኝዎች የሚደረገውን እቃወማለሁ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋርም በጋራ እሰራለሁ በሚል ሀሳባቸውን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች በኩል የጉዳዩ መስመር መልቀቅ እና ተጠያቂነት በሌለው መልኩ በየቦታው ምንም አይነት ፈቃድ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሰጣቸው በአጫብር ስም የሚደረጉ ጥናቶች የሚቀርቡ ወረቦች ቤተክርስትያንን በከፍተኛ መልኩ እያስተቹ መሆኑን አጽኖት ሰጥቶ ያቀረቡ ሲሆን በወቅቱም ሁሉም ተወያይ አካላት በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ የተስማማ ሲሆን ለቀጣይ መፍትሔ ጥናት እንደሚያስፈልግ ከስምምነት ላይ የተደርሷል። መጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉኀየሰ የሚሰጡትን ጥናት በተመለከተ አንድነቱ በአጫብር ስም የሚደረግ እንጂ ቤተክርስትያን የፈቀደችላቸውን አባት አይመለከትም ፣ ነገር ግን አካሄድላይ በተመለከተ ሰንበት ት/ቤት ለማስጠናት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በማያውቀው መልኩ ሁለተኛ አደረጃጀት መፍጠር ስህተት መሆኑን እና የትኛውንም ትክክለኛ ጥናት ከማደራጃው እና ከአንድነቱ ጋር ብቻ በመናበብ እንዲቀጥል በወቅቱ በነበረው ውይይት ከስምምነት ተደርሷል። በዚህም መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ደብዳቤ ለመጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ ማስጠናት የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ እና ይህንንም ሲፈጽሙ ከማደራጃ መምሪያው እና ከአዲስ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ተናበው መሆን እንዳለበት የሚገልጽ እንጂ በአጫብር ስም በሰንበት ት/ቤቶች የሚሰጥ ስልጠናን የሚመለከት አለመሆኑንን የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አሳውቋል። አሁንም በጠቅላላጉባኤው ውሳኔ መሠረት ማንም ሰንበት ት/ቤት በአጫብር ስም የሚደረግ ስልጠና የተከለከለ ሲሆን በመጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ በኩል የሚሰጠው ስልጠና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የአዲስ አበባ ሰንበት ትቤቶች አንድነት ጋር በመመካከር ሲፈቀድ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን ሲል የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አስታውቋል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи