ጦር ሜዳ
Статистикаምክንያቱም ተጋድሎአችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን -ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ -ከሥልጣናትና ከኀይላት -እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው። ኤፌ 6:12 *ጦር ሜዳ ውስጥ መሆኑን ያላወቀ ሰው ለውግያ የተዘጋጀ አይደለም፡፡ ሁሌ የተማረከ እና የተሸነፈ ነው፡፡ ሰለዚህ "የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ ኤፈ 6:13.... ... አስተያየት ካላችሁ @endyab
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 30
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 72
- 1/48двое суток
- 82
- 1/72трое суток
- 88
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19:21
видео или голосовое, без подписи
አቤቱ በህዝብህ ሞገስ አስበን ******* አቤቱ በህዝብህ ሞገስ አስበን በመድሃኒትህም ጐብኘን ህዝብህ ለአርባ አመታት ሲጓዝ ምድረ በዳ ሞገስ ስለሆንከው ከቶ ሳይጐዳ እያዘነብክለት ከሰማያት መና ስትጠብቅ ስትመራው በእሳት በደመና ሞገስህን አግኝቶ ህዝብህም በርትቶ ድል በድል አድርጓል ጠላቶቹን ረግጦ ህዝብህን ባሰብክበት ሞገስህ አስበን ማምለጥ እንድንችል ከከበበን ነገር አዝ፦ በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x) በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x) ያየ የጋለው ፍቅርህ የቀድሞው ሕይወታችን ዛሬ ቀስሞብናል ቀዝቅዟል ልባችን አንድነት ሲጠፋ መለያየት በዝቶ ስም ብቻ ሆነናል ሕይወታችን ሞቶ ዛሬ ግን ጌታ ሆይ ጐብኘን በ??? ባሰብክበት ምህረት ልክ እንደህዝቦችህ እጆቿን ወደ አንተ ኢትዮጵያም ትዘርጋ ጊዜው አሁን ይሁን ሞገስህ ይብዛና አዝ፦ በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x) በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x) በአንደበት ፍቅር የለበጥ አንድነት ቤትህን አረግነው ተንኮል የሞላበት በአፋችን ሌላ በልባችን ሌላ የያዝነውን እምነት አረግነው ደካማ መግባባት ይኑረን ቃላችን አንድ ይሁን እንደተናገርነው እንዲሁ እንድንኖር ዛሬ ለውጥን ስጠን ጌታ ለሁላችን በሞገስህ አስበን ይቀየር ልባችን አዝ፦ በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x) በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x) @btlfld
ኢየሱስ ካለማ ***** ገዢና ተገዢ መኳንንት ሹማምንት የአገሬው ህዝብ ሁሉ የተሳተፉበት እምቢልታ መሰንቆ በገናና ዋሽንት ሁሉም ተሰለፎ ለአንድ ሰው ትዕቢት አቤት ትዕቢት (፪x) የአንድ ንጉሥ ትዕቢት አገር ሲያሰግድ ህዝቡን ሲያንቀጠቅጥ ሶስት ደፋር ሰዎች ጣዖት ያለመዱ አንሰግድም ሲሉ በዓል አበላሹ ንጉሡም ሲሰማ በትዕቢት ተቆጣ እቶኑን ጨመረው እጥፍ እንዲነድ ሌላ ጉድ ፈላ አንሰግድም ያሉ በትዕቢት በጋለ እቶን ውስጥ ተጣሉ ወድቀው ተቃጥለው አረው ተኮማትረው መች ቀሩ መች ቀሩ ምንም ቢታሰሩ ተፈታ ገመዱ እያለ አዳኙ ጭራሽ ወዲህ ወዲያ ይራመዱ ጀመር የተስማማ እስኪመስል እንዴትስ አይመች እንዴትስ አይድላ ኢየሱስ ካለማ (፪x) ትዕቢቱ ተመታ የንጉሡ ሲበለሻሽ በት ድግሱ ሶስት ሰዎችን ጥሎ አራት ሲሆኑበት ነገር ግራ ሆነበት ንጉሱም እንዲህ አለ አዋጁን ቀየረ እየደነገጠ እነዚያን ብሩካን አውጧቸው ከእሳት እናምልከው በቃ የእነርሱን አምላክ (፪x) ሁሉም ሰው ያምልከው ይስገድለት ፊቱ ያስደንቃልና የማዳን ጉልበቱ እንደፋ ፊቱ እስቲ ጐምበስ (፪x) ይባልለት ይሰገድለት እስቲ ጐምበስ (፪x) ይባልለት ይሰገድለት አያልቅበት (፪x) ማዳኑ አያልቅበት አያልቅበት መታደጉ አያልቅበት አያልቅበት ምህረቱ አያልቅበት እስቲ ጐምበስ (፪x) ይባልለት ይሰገድለት እስቲ ጐምበስ (፪x) ይባልለት ይሰገድለት (፪x) @btlfld
መስቀልህ ስር ***** ተስፋ ቆርጬ ወደኋላዬ አልልም በጥቂቱ ዝዬ አልመለስም ብትገድለኝም ብታድነኝም ብትሰጠኝም ብትነሳኝም እጅህን እጠብቃለሁ ከፊትህ አልሄድም አንተን የለመነህ በፊትህ ጠብቆ ሁሉን እንደምትችል እንደምትሰጥ አውቆ ጊዜውን ብታረዝምም እምነቱን ልትፈትን እርሱን የጠበቀው መች አጣው ባርኮቱን አግኝቷል ከጌታ አጽንቶ እምነቱን እኔም መስቀልህ ስር ሆኜ እጠብቃለሁ ምን እንደምትሰራ እጅህን አያለሁ ጉልበቴን በፊትህ አምበረክካለሁ ቃሌንም በቤትህ ዝም አሰኘዋለሁ አንተ ምትሰራውን በሙሉ አያለሁ አንዲት ከነአናዊት ሴት ወደ ኢየሱስ መጥታ 'የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ ልጄ በእርኩስ መንፈስ ተይዛ ትስቃያለችና እባክህ እራራልኝ' እያለች ጮኸች እርሱ ግን አንድም ቃል ሳይመልስላት ዝም አለ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረብ ብለው 'ይሂች ሴት እየተከተለችን ስለምትጮህ እባክህ አሰናብታት' ሲሉ ለመኑት እርሱም 'እኔ የተላኩት ከእስራኤል ቤት እንደበጐች ለጠፉት ብቻ ነው' ሲል መለሰ። ሴትዬዋ ግን ቀርባ በእግሩ ስር ተንበረከከችና 'ጌታ ሆይ እባክህ እርዳኝ አለችው'። ኢየሱስም 'የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መጣል የተገባ አይደለም' አለ። እርሷም 'ጌታ ሆይ እርግጥ ነው። ነገር ግን ውሾችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዐድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ' አለችው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ 'አንቺ ሴት እምነትች ትልቅ ነው። ስለዚህ እንደፍላጐትሽ ይሁንልሽ አላት'። የሴትየዋም ልጅ በዚያን ሰዓት ዳነች። በለእርሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል ከጌታው ሚጠብቅ እርሱ ደግሞ ይከብራል እኔም ከአንተ ብቻ እጠብቃለሁኝ የአማረውን ፍሬ ለመብላት ጓጓሁኝ አይቀርም አንድ ቀን ደግሞ እከብራለሁኝ ብትሰጠኝም ብትነሳኝም እጅህን እጠብቃለሁ ከፊትህ አልሄድም ቃሌንም በቤትህ ዝም አሰኘዋለሁ አንተ ምትሰራውን በሙሉ አያለሁ @btlfld
እስቲ ልለምነው ጌታዬን ********* እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለህዝቤ የራሴን የግሌን ነገር ትቼ እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለምድሬ የራሴን የጸሎት ርዕስ ትቼ ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች (፪x) የአገሬ መፍትሄዋ የእንቆቅልሿ መፍቻዋ ቁልፉ ያለው ሰው ጋር አይደል ታዲያ ማንም አይታለል ስለእልቂቷ ወሬን ትቼ ስንበረከክ ተደፍቼ ይሰማኛል አምነዋለሁ ከዚም በፊት አይቻለሁ ሁሉም ነገር ያበጀዋል ዝብርቅርቁን ያሳምራል አዝ፦ እስቲ ልለምነው ጌታዬን ...... ለሹማምንት .... በችግሯ ከምሳለቅ ይልቅ እኔ ፊቱ ልውደቅ ባለምነው ባልጠይቀው እዳው በእኔ ጫና ላይ ነው መፍትሄ ላይሆን ወሬን ትቼ ልንበረከክ ፊቱን ሽቼ ሰሚ አምላክ እያመንኩኝ ለምን መፍትሄ አጣለሁኝ እትልቅም ለውጥ አመጣለሁ ለምድሬም ፈውስ እሆናለሁ አዝ፦ እስቲ ልለምነው ጌታዬን ...... ለሹማምንት ..... ብለምነው ስለአገሬ ሸክም ቢኖረኝ ለምድሬ ያለባትን ችግር ሁሉ ይዤ ብቀርብ ከመስቀሉ ጌታዬ እኮ ያደምጠኛል እንደሃሳቡ ይመልሳል ሳልታክት ፊቱ እቀርባለሁ ቃሉም ይላል ጸልያለሁ ሸክሟን ሳሳየው የምድሬን ይፈውሳታል አገሬን አዝ፦ እስቲ ልለምነው ጌታዬን .... ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች (፪x) ኢትዮጵያን ግብኛት ተመልከታት በቃል ኪዳንህ አስባት (፬x) @btlfld
አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ******** ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እምበረከካለሁ" አዝ፦ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ዙፋንህ ካለበት እምበረከካለሁ ጉልበቴ ይታጠፋል ሸክሜ ይራገፋል (፪x) የሕይወቴንና የኑሮዬን ሸክም ቀኑን ሙሉ ይዤው አልመላለስም ጠዋት ተነስቼ ስደፋ በፊቱ ሸክሜ ተራግፎልኝ እሆናለሁ ብርቱ ያለምክንያት አይደል የምምበረከከው ሰምቶ የሚመልስ አምላክ ስላለኝ ነው (፪x) አዝ፦ አባትነት ........... ያለኝን የልቤን ለማውራት በፊቱ ከእግሩ በቀር??? ስሆን ይመጣል መንፈሱ መልስ እንኪመጣልኝ በፊቱ ያለ እረፍት??? መንፈሱ ያግዘኛል ከልቤ??? እንድቃትር??? አምናለሁ ይራገፋል በእኔ እያለው ሸክም በፊቱ ወድቄ ያለ መልስ አልሄድም (፪x) አዝ፦ አባትነት ...... አባቴ ነውና ይሰማኛል ብዬ ልጠይቅ ልረዳ ያለኝን ከልቤ ፊቱ ስንበረከክ ደስታን አሞላለሁ ለጠየቅሁት ሁሉ መልስን አገኛለሁ እንዲሁ አይደለም በፊቱ መውደቄ ማንነቱን በደምብ ገብቶኝ ነው አውቄ (፪x) አዝ፦ አባትነት ...... ተነስ የእኔ ጌታ ስራ እንደቀድሞ ይብቃ ይህ ድካሜ ይወገድ ፈጽሞ ከከበበኝ ነገር መፍትሄ እንድትሆነኝ ወደ አንተ እጣራለሁ ኢየሱሴ ምትሰማኝ ልጥራህ በማለዳ ልጥራህ በጠዋቱ (፪x) ዛሬም ምታድሰኝ ኢየሱስ የናዝሬቱ ኢየሱስ የጥንቱ (፪x) @btlfld
በግ የሆነከው ******* በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ስለ እራሴ ስለ ግሌ ስለ ቤቴ ስለ አገሬ ስለ ኑሮ ስለ ሕይወት ስለ ያዝኩት አገልግሎት የማዋይህ አለኝና ልምበርከክ ፊትህ እንደገና የማዋይህ አለኝና ልምበርከክ ፊትህ እንደገና (፪x) የእግዚአብሔር በግ የሆንከው ልቤን በፍቅርህ ያደስከው ጓዴ/ጌታ ኢየሱስ እስቲ ና የማዋይህ አለኝና (፪x) *"ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ አንድ ሰው እስኪነጋ ድረስ ይታገለው ነበር እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሽሉዳ??? ነካው ያዕቆብም የጭኑን ??? ሲታገለው ደነዘዘ እንዲህም አለው 'ሊነጋ አቅላልቷልና ልቀቀኝ' እርሱም 'ካልባረከኝ አለቅህም' አለው እንዲህም አለው 'ስምህ ማነው?' እርሱም 'ያዕቆብ ነኝ' አለው ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባላል እንጂ ያዕቆብ አይባልም' በዚያም ስፍራ ባረከው።" በረከትህን ልጥራ በእኔ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ በቤቴ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ በአገሬ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ቤተሰቤን ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ስራዬ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ትምህርቴ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ትዳሬ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ በእኔነቴ በዚህ ማለዳ ካልባረከኝ አለቅህም (፬x) ካልዳሰስከኝ አለቅህም (፪x) ካልፈወስከኝ አለቅህም (፪x) ካለወጥከኝ አለቅህም (፪x) ካላደስከኝ አለቅህም (፪x) ካልባረከኝ አለቅህም (፪x) @btlfld
ማሳዘን አልፈልግም አንተን *************** ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x) ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x) ላሳዝንህ አልፈልግም አንተን (፪x) ላስቀይምህ አልፈልግም አንተን (፪x) ብዙ ውለታ አለብኝ ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x) ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x) ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x) ብዙ ውለታ አለብኝ ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x) የሞላኸው አለ ጐድሎብኝ የጠገንከውም አለ ተሰብሮብኝ የአደስክልኝ ብዙ ነው አርጅቶብኝ የመለስከውም አለ ግራ ገብቶኝ ይሄ ሁሉ በዝቶልኝ ላሳዝንህ አልፈልግም ይከብደኛል ሌላው ቢቀር ዘመኖቼ /ዕድሜዬ ይመሰክሩልኛል አዝ:- ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x) ... ብዙ ውለታ አለብኝ ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x) ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x) ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x) ብዙ ውለታ አለብኝ ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x) ለሃዘን ቀን ለደስታ ቀን ለፍርድ ቀን ለምጽዓት ቀን የታተምኩበት የአንተ ማኅተም የእርስቴ መያዣ ምጽናናበት ኀጢአትን ባደርግ የምወቀስበት ስለሰማዩ ሚስጥር የምረዳበት መንፈስ ቅዱስ እርሱ ነው ምጽናናበት የቀረ ይቀራል እንጂ (፫x) አሳዝኜው አልወጣም/አልርቅም ከእርሱ እጅ (፬x) አዝ፦ ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x) .... ብዙ ውለታ አለብኝ ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x) ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x) ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x) ብዙ ውለታ አለብኝ ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x) @btlfld
አቤቱ መተላለፌን ደምስስ ****************** አቤቱ እንደቸርነትህ ብዛት እንደ ምህረትህ ብዛት መተላለፌን ደምስሳት (፬x) እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ከቶ አልክድም ፊትህ በደሌም ሁልጊዜ በፊትህ ነው አንሳኝ በምህረትህ እንድትመራኝ ብዬ መጣሁ እጠበኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ (፪x) አዝ፦ አቤቱ እንደቸርነትህ ብዛት እንደ ምህረትህ ብዛት መተላለፌን ደምስሳት (፬x) ለበደሌ ክርክር አላቀርብም እኔ አልሟገትም መናዘዝ እንጂ እያልኩኝ ኀጢአተኛ ነኝ ሌላ ምን ምርጫ አለኝ ስለዚህ በሂሶብ??? እርጨኝና እጠበኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ (፪x) አዝ፦ አቤቱ እንደቸርነትህ ብዛት እንደ ምህረትህ ብዛት መተላለፌን ደምስሳት (፪x) "ጌታ ሆይ ቅዱስ መንፈስህ ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ" ቅዱስ መንፈስህን (፪x) ከእኔ ላይ (፪x) ኧረ አትውሰድብኝ (፪x) ቅዱስ መንፈስህን (፪x) ከእኔ ላይ (፪x) ኧረ አትውሰድብኝ (፪x) ታድያ እኔ ማነኝ ይህን ታላቅ ስም ልጠራ ታዲያ እኔ ማነኝ ፊትህ ለማቅረብ ምሥጋና ግን ፊትህ ለመቆም ሞገስ/ምህረት ከአገኘሁ ምሥጋናን ምሥጋና ምሥጋናን እሰዋለሁ ምሥጋናን ምሥጋና ምሥጋናን እሰዋለሁ (፪x) ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x) "እግዚአብሔር መሃሪና ይቅር ባይ ነው ከቁጣ የራቀ ምህረቱም የበዛ ሁልጊዜ አይቀስፍም ለዘለዓለምም አይቆጣ እንደኀጢአታችን አላደረገብንም እንደበደላችንም አልከፈለንም ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል እንዲሁ እግዚአብሔር ምህረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ ቸር እንደሆነ ምህረቱ ለዘለዓለም እንደሆነች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይናገሩ" ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) @btlfld
እጸልያለሁ - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ** ሌሊቱ ሲነጋ ጐህ ሲቀድ አእዋፍ ሲንጫጩ በአንድነት በዜማ ፈጣሪን ለማምለክ ሲወጡ ሁሉም ከያሉበት እኔ ግን መኝታዬ ሞቀኝ ዝምብለሽ ተኚ ተኚ ቢለኝ መኝታዬን ወዲያ ገፍፌ ለጸሎት ነቃሁኝ ከእንቅልፌ ለጸሎት መንፈሴ ሲነቃ ሥጋዬ ባይደሰት ቢከፋ ሳይወድ በግዱ ያብርና መጸለዬ ይቀጥላል ገና ስሙን ስጠራው የጌታዬን ያድሰዋል ደካማው ጐኔን ቅባቱ መፍሰስ ይጀምራል ለጸሎት ጉልበቴን ያድሳል እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መች አፍሬ አውቃለሁ እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ ድልን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መልስን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ እንደሚሰማ አምናለሁ አንዳንዴ ውስጤ ጸልይ ሲለኝ ስጋዬ ግን ሲያታልለኝ ቆይ ትጸልያለህ በኋላ እያለ ጊዜዬን ሊበላ ግን ዳንኤልን ጉድጓድ ያስጣለው አትጸልይ የሚል ህግ ነው ቢያስመርጡት ከምንም ነገር ጸሎት ነው ለእርሱ ትልቅ ነገር ይህንን ሳስታውስ እነቃለሁ ስጋዬን ተወኝ እለዋለሁ ስታዘዝ ለነቃው መንፈሴ ለጸሎት ተጋልኝ ጉልበቴ ጸሎት ትልቅ መሳሪያዬ ነው ሰይጣንም ይሄ ስለገባው እንዳልጸልይ ቢታገለኝም ምክኒያትን ለሥጋዬ አልሰጥም አዝ፦ እጸልያለሁ (፫x) ግራ ሲገባኝ በሕይወቴ መምበርከክ ሲያቅተው ጉልበቴ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ስሞላ መፍትሄ መልስን ሳጣ መላ ከመጸለይ ይልቅ በፊቱ ሳወራ ላገኘሁት ሁሉ ይባባስብኛል ችግሬ ያጐብጠኛል ያ ጠብቆ ቀምበሬ ግን በሬን ዘግቼ ስገባ የውስጤን ሁሉ ወደ ሚረዳ በጸሎት ዙፋኑ ስር ስወድቅ ይታደሳል ውስጤ በድንገት ያልወጣሁት ችግር ጸልዬ ፍፁም የለምና በሕይወቴ ባልጸልይ እራሴን እጐዳለሁ ይህንን በተግባር አውቃለሁ አዝ፦ እጸልያለሁ (፫x) * ጦር ሜዳ:-https://t.me/btlfld
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ - የ11ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ
የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ--kingdom sound cover orginal ተስፋዬ ጋብሶ ******************** ሰማይን የሰራ የምድርም ፈጣሪ በዘለዓለም ዙፋን ለዘለዓለም ኗሪ ገናናነትህን ሰማያት ያውቃሉ ምድርና ሞላዋም ይመሰክራሉ። የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ። የተዳፈሩህን የተነሱብህን ልክህን ሳያውቁ የታጠቁብህን እየቀጣሃቸው ተረቶች ሆነዋል ተፈርተህ ተከብረህ አንተ ግን ኖረሃል። የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ። x2
ክፍል 5 – ሮድሪጌስ ከአንጎላ (በሦስተኛ ወገን የተነገረ ምስክርነት) ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ይህ ምስክርነት ለብዙ ዓመታት በጨለማው ዓለም ሰይጣንን በማገልገል ስላሳለፈች እና አሁን ግን በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ሕይወቷን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥታ ከጨለማው እስራት ነጻ ስለሆነች ስለ ሮድሪጌስ ነው። በእንግሊዝኛ የተጻፈውን ለማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩን ከታች አስቀምጥላችኋለሁ። 👉 https://www.mcreveil.org/Anglais/witchcraft/rodrigues_en.php ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሌሎች በዚህ ገጽ (Page) ያሉትን መልዕክቶች ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 👉 @btlfld
ክፍል 4 – ሮድሪጌስ ከአንጎላ (በሦስተኛ ወገን የተነገረ ምስክርነት) ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ይህ ምስክርነት ለብዙ ዓመታት በጨለማው ዓለም ሰይጣንን በማገልገል ስላሳለፈች እና አሁን ግን በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ሕይወቷን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥታ ከጨለማው እስራት ነጻ ስለሆነች ስለ ሮድሪጌስ ነው። በእንግሊዝኛ የተጻፈውን ለማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩን ከታች አስቀምጥላችኋለሁ። 👉 https://www.mcreveil.org/Anglais/witchcraft/rodrigues_en.php ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሌሎች በዚህ ገጽ (Page) ያሉትን መልዕክቶች ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 👉 @btlfld
ክፍል 3 – ሮድሪጌስ ከአንጎላ (በሦስተኛ ወገን የተነገረ ምስክርነት) ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ይህ ምስክርነት ለብዙ ዓመታት በጨለማው ዓለም ሰይጣንን በማገልገል ስላሳለፈች እና አሁን ግን በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ሕይወቷን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥታ ከጨለማው እስራት ነጻ ስለሆነች ስለ ሮድሪጌስ ነው። በእንግሊዝኛ የተጻፈውን ለማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩን ከታች አስቀምጥላችኋለሁ። 👉 https://www.mcreveil.org/Anglais/witchcraft/rodrigues_en.php ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሌሎች በዚህ ገጽ (Page) ያሉትን መልዕክቶች ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 👉 @btlfld
ክፍል 2 – ሮድሪጌስ ከአንጎላ (በሦስተኛ ወገን የተነገረ ምስክርነት) ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ይህ ምስክርነት ለብዙ ዓመታት በጨለማው ዓለም ሰይጣንን በማገልገል ስላሳለፈች እና አሁን ግን በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ሕይወቷን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥታ ከጨለማው እስራት ነጻ ስለሆነች ስለ ሮድሪጌስ ነው። በእንግሊዝኛ የተጻፈውን ለማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩን ከታች አስቀምጥላችኋለሁ። 👉 https://www.mcreveil.org/Anglais/witchcraft/rodrigues_en.php ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሌሎች በዚህ ገጽ (Page) ያሉትን መልዕክቶች ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 👉 @btlfld
ክፍል 1 – ሮድሪጌስ ከአንጎላ (በሦስተኛ ወገን የተነገረ ምስክርነት) ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ይህ ምስክርነት ለብዙ ዓመታት በጨለማው ዓለም ሰይጣንን በማገልገል ስላሳለፈች እና አሁን ግን በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ሕይወቷን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥታ ከጨለማው እስራት ነጻ ስለሆነች ስለ ሮድሪጌስ ነው። በእንግሊዝኛ የተጻፈውን ለማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩን ከታች አስቀምጥላችኋለሁ። 👉 https://www.mcreveil.org/Anglais/witchcraft/rodrigues_en.php ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሌሎች በዚህ ገጽ (Page) ያሉትን መልዕክቶች ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 👉 @btlfld
በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። ማቴዎስ 7:13-14