tgindex

cloudss™

описание

A little reminder: Don't forget to pray before you sleep..🙂 There is No such thing as original ተመስገን🙏 ......@ende_thought ......@or_deal ......@fewash_thoughts ......@sabawitt ......@idiDitBeZeNeZeNa1 ......@d_e_v_1_2 @PityTruth @gkvii7 March 22

200
подписчиков
Охват к подписчикам
53,5%
ERR
Реакции к просмотрам
17,88%
381 на 20 постов
Пересылки к просмотрам
0,23%
5
Постов в день
0,0
всего 20

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 9 дек.አንዳንዴ ለእኛ ከቀረቡት ሰዎች ይልቅ የራቁን ሰዎች አሳምረው ያውቁናል። ከአንድ እናት ተወልደው በአንድ ጣሪያ ሥር ከአደጉ ወንድምና እኅት በላይ አራምባና ቆቦ ያሉ ሰዎች ይሳሳባሉ። ልብ ለልብ ይግባባሉ። እንጀራ ጠቅልለን የምናጎርሰውን ሰው ሆድ አናውቅም። አንዳችን የአንዳችንን ልብስ ለብሰን ስንሳሳቅ የምንተዋወቅ እንመስላለን። እንደ ወንድምና እኅት የወረስናቸው ዓይኖችና ጆሮዎች ተመሳሳይ ናቸው። እርስ በእርስ ግን አንተያይም። አንሰማማም። ዓይኖቻችን የሩቅ ሰው ያያሉ። ጆሮዎቻችን ባይተዋሩን ያደምጣሉ። በሥጋ እንጂ በመንፈስ አልተዛመድንም። 📓ትዝታሽን : ለእኔ ትዝታዬ : ለአንቺ32,76%
  • 4 авг. 2025 г.ሁላችንም ተፈላጊ የምንሆነው ዋጋችን ሲጨምር ብቻ ነው ለዚህ ደግሞ great example ዮሴፍ ነው።.... የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እሱ ተመልሰው የመጡት እሱ ጋር የሚያስመጣ ነገር ስለያዛቸው ብቻ እንጂማ ረስተውት ነበር እኮ። ዮሴፍ በወንድሞቹ ከተጠላበት ነገር አንዱ በህልሙ ነበር። ህልም ለሰው ሲነገር ሁሌ ያስቃል ሲፈታ ነው ትርጉም ያለው እና what i understand is that ህልማቹ እስኪፈታ ድረስ ሁሌም ሰዎች አያጨበጭቡላችሁም ሰዎች እንዲስቁባቹ የሚያደርግ ይሆናል your dreams ግን when the time comes and when you made it everyone will adore the dream so ቁም ነገሩ ምንድን ነው until our time comes በጸሎት መበርታቱ is the only option. የዮሴፍ መጨረሻ ያማረው አረማመዱ ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበር ነው። life passing by እያደረጋቹ ከመሰላቹ pray like this "ጌታ ሆይ የእኔ ተራ እስኪደርስ የምጠብቅበትን ትዕግሥት ስጠኝ ትዕግሥት እና ማስተዋልን አድለኝ" and work on your dreams it will come true.23,42%
  • 10 окт. 2025 г.አእምሮ የሕይወት መሸፈኛ ሳይሆን ሕይወትን ነጻ የማውጫ መንገድ ነው፡፡ አሁን አሁን በሄድክበት ሁሉ ሰዎች “አእምሮህን መቆጣጠር አለብህ” ይላሉ፡፡ አእምሮህ ግን የሚያስፈልገው ነፃ መውጣት እንጂ ቁጥጥር ሊደረግበት አይደለም፡፡ አእምሮ እንቅፋት ሳይሆን፣ ትልቅ ዕድል ነው... አእምሮ እንቅፋት የመሆኑ ችግር የሚፈጠረው የአእምሮን መሰረታዊ ባህሪይ ሳትረዳና ሳታውቅ፣ ልትመራው ስትሞክር ነው፡፡ ዋነኛው የአእምሮ ችግር ሥነ ምግባር ነው፡፡ ሌላኛው ትልቁ ችግር ደግሞ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ትክክልና ስህተት የሚባሉት ነገሮች በአእምሮ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ እና መጥፎ የሆነ የሚለውን ሀሳብ አስተምረውሃል፡፡ ጥሩና መጥፎ በጣም ጠንካራ የሆኑ የማንነት ነጥቦች ናቸው፡፡ ስለሆነም ጥሩ ነው ብለህ በምትቆጥረው ትለያለህ፣ መጥፎ ብለህ ከምትቆጥረው ትርቃለህ፡፡ የሆነን ነገር መጥላትና ወደ ሌላ ነገር መሳብ የመለያው መሰረት ይሆናል፡፡ የምትጠላው ሁሉ በአእምሮህ ላይ የበላይ ለመሆን ይሞክራል፡፡ የአእምሮ አፈጣጠር አንድን ነገር “አልፈልግም” ስትል፣ ያ ነገር አእምሮህ ውስጥ መከሰት የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ በአእምሮ ውስጥ መደመርና ማባዛት ብቻ እንጂ መቀነስና ማካፈል የለም፡፡ ከአእምሮ ውስጥ ምንም ነገር በኃይል መውሰድ አትችልም፡፡ ይህን ለመረዳት ደግሞ ምንም መገለጥ አያስፈልገውም፡፡ 📓የሕይወት ኬሚስትሪ22,73%
  • 20 дек.አእምሮ የሕይወት መሸፈኛ ሳይሆን ሕይወትን ነጻ የማውጫ መንገድ ነው፡፡ አሁን አሁን በሄድክበት ሁሉ ሰዎች “አእምሮህን መቆጣጠር አለብህ” ይላሉ፡፡ አእምሮህ ግን የሚያስፈልገው ነፃ መውጣት እንጂ ቁጥጥር ሊደረግበት አይደለም፡፡ አእምሮ እንቅፋት ሳይሆን፣ ትልቅ ዕድል ነው... አእምሮ እንቅፋት የመሆኑ ችግር የሚፈጠረው የአእምሮን መሰረታዊ ባህሪይ ሳትረዳና ሳታውቅ፣ ልትመራው ስትሞክር ነው፡፡ ዋነኛው የአእምሮ ችግር ሥነ ምግባር ነው፡፡ ሌላኛው ትልቁ ችግር ደግሞ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ትክክልና ስህተት የሚባሉት ነገሮች በአእምሮ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ እና መጥፎ የሆነ የሚለውን ሀሳብ አስተምረውሃል፡፡ ጥሩና መጥፎ በጣም ጠንካራ የሆኑ የማንነት ነጥቦች ናቸው፡፡ ስለሆነም ጥሩ ነው ብለህ በምትቆጥረው ትለያለህ፣ መጥፎ ብለህ ከምትቆጥረው ትርቃለህ፡፡ የሆነን ነገር መጥላትና ወደ ሌላ ነገር መሳብ የመለያው መሰረት ይሆናል፡፡ የምትጠላው ሁሉ በአእምሮህ ላይ የበላይ ለመሆን ይሞክራል፡፡ የአእምሮ አፈጣጠር አንድን ነገር “አልፈልግም” ስትል፣ ያ ነገር አእምሮህ ውስጥ መከሰት የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ በአእምሮ ውስጥ መደመርና ማባዛት ብቻ እንጂ መቀነስና ማካፈል የለም፡፡ ከአእምሮ ውስጥ ምንም ነገር በኃይል መውሰድ አትችልም፡፡ ይህን ለመረዳት ደግሞ ምንም መገለጥ አያስፈልገውም፡፡ 📓የሕይወት ኬሚስትሪ22,37%
  • 13 окт. 2025 г.ረጃጅም ህንጻዎች ትናንሽ ትግስቶች፣ ሰፋፊ መንገዶች፣ ጠባብ አመለካከቶች፣ የምናወጣው ብዙ የሚኖረን ጥቂት፣ብዙ እንገዛለን ጥቂት እንደሰታለን፣ ትላልቅ ቤቶች ትናንሽ ቤተሰቦች፣ የተሻለ ምቾት ጥቂት ጊዜ፣ ብዙ ዲግሪ ትንሽ ማመዛዘን(ግንዛቤ)፣ ብዙ እውቀት ትንሽ ጥበብ፣ ብዙ አዋቂነት ብዙ ችግሮች፣ ብዙ መድኃኒት ትንሽ ጤነኝነት ስለ ጥሩ አኗኗር ተምረናል እንዴት እንዴት እንደሚኖር ግን አልተማርንም ለህይወት እድሜ ጨምረንለታል ለእድሜ ግን ህይወት አልጨመርንበትም መከባበር በመናናቅ መተዛዘን በመጠፋፋት ህሊና በሆድ ተተኩ ጨረቃ ላይ ደርሰን ተመለስን ግርግዳ የሚለየውን አዲሱ ጎረቤታችንን መተዋወቅ አቀበት ሆነብን ከምድራችን ውጪ ያለውን ህዋ ተቆጣጠርን በውስጣችን የሚገኘውን ትንሽ ቦታ ግን አልተቆጣጠርንም ትላልቅ ችግሮችን እንጂ የተሻሉ ነገሮችን አልሰራንም አካባቢያችንን እያፀዳን ነፍሳችንን ግን እየበከልን ነው አቶምን ሰነጠቅን መሰረተቢስ ጥላቻዎቻችንንና ቅራኔዎቻችንን ግን አልፈታንም ብዙ እናነባለን ትንሽ እንለወጣለን ብዙ እናቅዳለን ጥቂት እናደርጋለን መቸኮል እንጂ መጠበቅ አልተማርንም የተሻለ ገቢ እንጂ ያደገ ስነ ምግባር የለንም። ብዙ መረጃ የሚይዝና ብዙ ስራ ባጭር ጊዜ የሚያከናውነውን ኮንፒዮተር ፈጠርን እንጂ በመካከላችን ግን ብዙ መግባት አልተፈጠረም በብዛት ብዙ ሄደናል በጥራት ግን ወደ ኋላ ተጎትተናል። ጊዜው እንዲህ ሆነ ሰው በሁለት ገቢ የሚተዳደርበት ትዳር ግን የሚበተንበት የተሰነጣጠቁ ቤተሰቦች የሚኖሩባቸው ግን የተዋቡ መኖርያዎች። ወቅቱ ፈጣን ጉዞ የሚደረግበት ለአንድ ሌሊት ትዳር የሚወጣበትና ግብረ-ገብነት ተሽቀንጥሮ የተጣለበት ዘመን።21,25%
  • 10 авг. 2025 г.ሁሉም እስካልረሰበት ድረስ አያውቀውም... የሰው ህመም የሚገባህ በቦታው ሆነህ ስታየው ብቻ ነው! ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል እንዲሉ አበው ከዳር ሆኖ መፍረድ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ እየተዝናናህ በአጠገብህ የአምቡላንስ ጩኸት ስትሰማ 'ለምን ያደነቁረናል' ብለህ ትናደዳለህ አንድ ቀን ግን የአንተ የሆነን ሰው ሲጭን "እባክህ ጥሩንባውን አስጩኽና መንገድ አስከፍት ቶሎ እንድረስ' ብለህ ትማፀናለህ....የሃዘን ቤት ምስር ይጣፍጣል ነው ያልከኝ? ልክ ነህ ይጣፍጣል..ጣዕም አልባ መሆኑ የሚገባህ አንተ ቤት ውስጥ ሲሰራ ነው!20,79%
  • 23 нояб.ተስፋ መቁረጥ የሀዘን የቅርብ ጓደኛ ነው። ይህ ተስፋ መቁረጥ ግን የአንድ ነገር አለመሳካት አይደለም፤ ከሱም በላይ ነው። የሕልውናን ትርጉም መካድ፣ የሁሉም ነገር ከንቱ መሆን ስሜት ነው። ከፊታችን ያለው ዓለም ባዶ መድረክ ይመስለናል፣ አኛም በጨለማ ውስጥ ተደብቀን በዝምታ ብቸኝነታችንን የምንመለከትበት ተመልካች ነን። ይህ ስሜት ማንኛውንም ደስታ ወይም ብርሃን የማየት ችሎታን ያደበዝዛል፣ ሁሉንም ነገር ግራጫ ያደርገዋል። ​በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን ፍርሃት ይጨመራል የሚመጣውን ሳይሆን አሁን ያለውን የሀዘን ዘላለማዊነት ፍርሃት። ይህ ስሜት መቼም ቢሆን ላይለቀን እንደሚችል ማሰብ ሌላኛው አስፈሪ ነገር ነው። ይህ ህመም የራስህ የሕይወት አካል ሆኖ ሌላ ማንኛውንም ስሜት እንዳንቀምስ የሚገታ የባርነት ቀንበር ነው መጨረሻ የሌለው፣ እፎይታ የሌለው የነፍስ እስር ቤት።20,00%
  • 10 дек.ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ከድሮም ጀምሮ የምታውቀው ሰው ሳይሆን ፀባይህ ሲቀየር አብሮህ የሚቀረው ነው፣ ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ጮክ ያለውን ሳቅህን ሳይሆን የረዘመውን ዝምታህን ሚያስተውለው ነው፣ ለማይፈልግህ ሰው ደስታ ስትለፋ የተረዳህ ሰው ነው ጓደኛ ማለት፣ ያለ ምላሽ እንደምትሰጥ እና ወድቀህ እንደምትነሳ ያስተዋለህ ነው ጓደኛ ማለት፣ ማብራሪያም ሆነ ማስረጃም አይፈልግም የውስጥህን ለመረዳት፣ ምክንያቱም እሱ ካንተ ሚጠብቀው አሪፍ እንድትሆን ሳይሆን እራስህን እንድትሆን ነው ሚፈልገው፣ ንግግርም ቀንሶ በህይወት ውጣ ወረድ ጊዜም ስታጣ አይርቅህም፣ እዛው አብሮህ ይሆናል፣ ሁሌም ባያወራህም ሁሌም ባያይህም ያስብሃል ይጨነቅልሃል፣ ሳታወሩ ቀናቶች ሊያልፋ ይችላሉ ከዛም ምንም እንዳልተፈጠረ ታወራላቹ፣ ምክንያቱም አንዳንድ ጓደኝነቶች ሚለኩት በቆዩት ጊዜ አይደለም በጥንካሬው እና በመቀራረብ እንጂ።19,74%
  • 9 авг. 2025 г.ዕድሜህ በሄደ ቁጥር በዚህች ዓለም ሕይወት ላይ ያዘንክባቸው ነገሮች ሁሉ ያን ያህል ዋጋ ሊሠጣቸው እንደማይገባ ትረዳለህ። ህይወት እንዲሁ ናት። ታሸንፋለህ ትሸነፋለህ፣ ታዝናለህ ትስቃለህ፣ ታገኛለህ ታጣለህ፣ እድል ይመጣል ይሄዳል፣ ሰው ይሄዳል ይተካል፣ ምድር ላይ ለዘላለሙ አብሮህ የሚዘልቅ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የለም። የነገሮች መወለድና መሞት ያለ ነዉና ብዙ አትገረም።19,23%
  • 7 авг. 2025 г.መናገር ፈልገን ብዙ የያዝናቸው ነገሮች አሉ.... መናገር ፈልገን ብዙ የያዝናቸው ነገሮች አሉ፣ አንድም የሚረዳን አተን፣ አንድም ሰው ላለማስቸገር ብዙ ጣጣ ያለው ሰው ነው ወይም ደሞ ችግር አያጣውም ላለመባል ብዙ ነገር በውስጣችን አምቀን ተቀምጠናል፣ ደሞ ለአንድ ሰው ሚሰማንን ህመም በምን ምክንያት እንደሚሰማን ስንነግረው ያ ሰው እኛን ሚቀየመን ወይም ደሞ እኛ ላይ ሚፈርድበት ሰዓት ይኖራል፣ ሰው እኮ ወዶ አይደለም ደህና ነህ ወይ ብለህ ስትጠይቀው አይኑ በእምባም ተሞልቶ ይሁን እያለቀሰም ቢሆን ደህና ነኝ ብሎ ሚመልሰው፣ ደህና አይደለሁም ብንል ቀጣዩ ጥያቄ "ምን ሆነህ ነው ምን ተፈጥሮ ነው" ነው ሚሆነው ታድያ ሙሉ የውጣችንን እና የተፈጠረውን ሙሉ ዘርዝረን ተናግረን ሚረዳም ስለሌለ ነው፣ ብዙዎቻችን በራሳችን ዝምታ ውስጥ እየተሰቃየን ነው ወይ ጠይቃቹ ሲነገራቹ ተረዱን ወይ ደሞ ዝም በሉ አታሳቁን።19,13%
  • 11 авг. 2025 г.በነገራችን ላይ ሰው ማጣትን ወይ ደሞ ከዜሮ መጀመርን አደለም ሰው ምን ይለኛል ትላንት አግኝቶ አጣ እባላለሁ ትላንት ሳረጋቸው የነበሩ የቅንጦት ነገሮች ሲቀሩ በሰዎች ዘንድ እታማለው ሚለውን ነው ሚፈራው ግን አንዳንዴ አጥቶ መመለስም ትልቅ ትምህርት ነው በአገኘንበት ጊዜ የሰራናቸው ስህተቶች ግልፅ ሁነው እናገኛቸዋለን በአገኘንበት ጊዜ መጥሮ የሆንበት እና ለውድቀታችን መነሻ የሆነውን ስህተት እንረዳዋለን መልሰን ብናገኝ እንኳን የአጣንበት ጊዜ ቀጥቶ አስተምሮናል እና ድጋሚ ያንን ስራ አንደግመውን ህይወት ፈትና ነው ምታስተምረው18,64%
  • 12 авг. 2025 г.እንዲህ ነው ወይ....? ህይወት ልክ እንደ ትራፊክ መብራት እና መብራቱን ከበው መስቀልኛ መንገድ ላይ እንደቆሙ መኪኖች ናት። ህይወት በሆነ አጋጣሚ ያገናኘህ አንተ ቀይ ላይ ሆነሆ ለሱ አረንጓዴ ሲበራ ጥሎህ ይሄዳል። ቀይ የበራብን ግን ባለንበት ቋመን አለን.... አዎን አብሮህ ጎንለጎን እየተጓዘ የነበረ ወዳጅህ ለሱ አረንጓዴ በርቶ አንተን ቀይ መብራት ውስጥ ያለኸውን የሚጠብቅበት ምክኒያት የለም17,60%