cloudss™
СтатистикаA little reminder: Don't forget to pray before you sleep..🙂 There is No such thing as original ተመስገን🙏 ......@ende_thought ......@or_deal ......@fewash_thoughts ......@sabawitt ......@idiDitBeZeNeZeNa1 ......@d_e_v_1_2 @PityTruth @gkvii7 March 22
- Последний пост
- 20 дек.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አእምሮ የሕይወት መሸፈኛ ሳይሆን ሕይወትን ነጻ የማውጫ መንገድ ነው፡፡ አሁን አሁን በሄድክበት ሁሉ ሰዎች “አእምሮህን መቆጣጠር አለብህ” ይላሉ፡፡ አእምሮህ ግን የሚያስፈልገው ነፃ መውጣት እንጂ ቁጥጥር ሊደረግበት አይደለም፡፡ አእምሮ እንቅፋት ሳይሆን፣ ትልቅ ዕድል ነው... አእምሮ እንቅፋት የመሆኑ ችግር የሚፈጠረው የአእምሮን መሰረታዊ ባህሪይ ሳትረዳና ሳታውቅ፣ ልትመራው ስትሞክር ነው፡፡ ዋነኛው የአእምሮ ችግር ሥነ ምግባር ነው፡፡ ሌላኛው ትልቁ ችግር ደግሞ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ትክክልና ስህተት የሚባሉት ነገሮች በአእምሮ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ እና መጥፎ የሆነ የሚለውን ሀሳብ አስተምረውሃል፡፡ ጥሩና መጥፎ በጣም ጠንካራ የሆኑ የማንነት ነጥቦች ናቸው፡፡ ስለሆነም ጥሩ ነው ብለህ በምትቆጥረው ትለያለህ፣ መጥፎ ብለህ ከምትቆጥረው ትርቃለህ፡፡ የሆነን ነገር መጥላትና ወደ ሌላ ነገር መሳብ የመለያው መሰረት ይሆናል፡፡ የምትጠላው ሁሉ በአእምሮህ ላይ የበላይ ለመሆን ይሞክራል፡፡ የአእምሮ አፈጣጠር አንድን ነገር “አልፈልግም” ስትል፣ ያ ነገር አእምሮህ ውስጥ መከሰት የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ በአእምሮ ውስጥ መደመርና ማባዛት ብቻ እንጂ መቀነስና ማካፈል የለም፡፡ ከአእምሮ ውስጥ ምንም ነገር በኃይል መውሰድ አትችልም፡፡ ይህን ለመረዳት ደግሞ ምንም መገለጥ አያስፈልገውም፡፡ 📓የሕይወት ኬሚስትሪ
ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ከድሮም ጀምሮ የምታውቀው ሰው ሳይሆን ፀባይህ ሲቀየር አብሮህ የሚቀረው ነው፣ ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ጮክ ያለውን ሳቅህን ሳይሆን የረዘመውን ዝምታህን ሚያስተውለው ነው፣ ለማይፈልግህ ሰው ደስታ ስትለፋ የተረዳህ ሰው ነው ጓደኛ ማለት፣ ያለ ምላሽ እንደምትሰጥ እና ወድቀህ እንደምትነሳ ያስተዋለህ ነው ጓደኛ ማለት፣ ማብራሪያም ሆነ ማስረጃም አይፈልግም የውስጥህን ለመረዳት፣ ምክንያቱም እሱ ካንተ ሚጠብቀው አሪፍ እንድትሆን ሳይሆን እራስህን እንድትሆን ነው ሚፈልገው፣ ንግግርም ቀንሶ በህይወት ውጣ ወረድ ጊዜም ስታጣ አይርቅህም፣ እዛው አብሮህ ይሆናል፣ ሁሌም ባያወራህም ሁሌም ባያይህም ያስብሃል ይጨነቅልሃል፣ ሳታወሩ ቀናቶች ሊያልፋ ይችላሉ ከዛም ምንም እንዳልተፈጠረ ታወራላቹ፣ ምክንያቱም አንዳንድ ጓደኝነቶች ሚለኩት በቆዩት ጊዜ አይደለም በጥንካሬው እና በመቀራረብ እንጂ።
አንዳንዴ ለእኛ ከቀረቡት ሰዎች ይልቅ የራቁን ሰዎች አሳምረው ያውቁናል። ከአንድ እናት ተወልደው በአንድ ጣሪያ ሥር ከአደጉ ወንድምና እኅት በላይ አራምባና ቆቦ ያሉ ሰዎች ይሳሳባሉ። ልብ ለልብ ይግባባሉ። እንጀራ ጠቅልለን የምናጎርሰውን ሰው ሆድ አናውቅም። አንዳችን የአንዳችንን ልብስ ለብሰን ስንሳሳቅ የምንተዋወቅ እንመስላለን። እንደ ወንድምና እኅት የወረስናቸው ዓይኖችና ጆሮዎች ተመሳሳይ ናቸው። እርስ በእርስ ግን አንተያይም። አንሰማማም። ዓይኖቻችን የሩቅ ሰው ያያሉ። ጆሮዎቻችን ባይተዋሩን ያደምጣሉ። በሥጋ እንጂ በመንፈስ አልተዛመድንም። 📓ትዝታሽን : ለእኔ ትዝታዬ : ለአንቺ
ተስፋ መቁረጥ የሀዘን የቅርብ ጓደኛ ነው። ይህ ተስፋ መቁረጥ ግን የአንድ ነገር አለመሳካት አይደለም፤ ከሱም በላይ ነው። የሕልውናን ትርጉም መካድ፣ የሁሉም ነገር ከንቱ መሆን ስሜት ነው። ከፊታችን ያለው ዓለም ባዶ መድረክ ይመስለናል፣ አኛም በጨለማ ውስጥ ተደብቀን በዝምታ ብቸኝነታችንን የምንመለከትበት ተመልካች ነን። ይህ ስሜት ማንኛውንም ደስታ ወይም ብርሃን የማየት ችሎታን ያደበዝዛል፣ ሁሉንም ነገር ግራጫ ያደርገዋል። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን ፍርሃት ይጨመራል የሚመጣውን ሳይሆን አሁን ያለውን የሀዘን ዘላለማዊነት ፍርሃት። ይህ ስሜት መቼም ቢሆን ላይለቀን እንደሚችል ማሰብ ሌላኛው አስፈሪ ነገር ነው። ይህ ህመም የራስህ የሕይወት አካል ሆኖ ሌላ ማንኛውንም ስሜት እንዳንቀምስ የሚገታ የባርነት ቀንበር ነው መጨረሻ የሌለው፣ እፎይታ የሌለው የነፍስ እስር ቤት።
አንዳንዴ ህይወት ውስጥ እንዲህ ያጋጥማል እንዳሰብከው ሳይሆን አንተ እንደጠበከው ፍፁም ተቃራኒ ሆኖ ነው ሚገኘው ከጎንህ ላለው በርቶ ላንተ ይጨልማል ሌት ከቀን እየጣርክ ትርፍህ ድካም ሆኗል ያቀድከው ያለምከው አልሳካ ብሎህ መጣ ያልከው ቀርቶ ደግ ያልከው ከፍቶብህ የኔ ያልከው ወዳጅ የሩቅ ሰው ሆኖብህ ውስጥህ ብቸኝነት ተሞልቶ ባዶነት ድንግርግር ብሎህ ትርጉሙ የህይወት በቃ ሁሉም ነገር ስልችት ብሎሀል ከተስፋ መቁረጥ ስር ካፍፉ ቆመሀል ልብ በሉ ህይወት ይቀጥላል ጨለማን ባናውቅ ኖሮ እኮ የብርሀንን ዋጋ ባልተገነዘብን ነበር ማጣትን ባናይ ኖሮም የማግኛት ትርጉም በቅጡ ባልገባን ነበር የደግ ሰዎችን ግምት አንድታቅ የሚያደርጉህም የክፉወች መኖር ነው አይደል ሁሉም የሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው አያችሁ የህይወት ገፆች ብዙና የተለያዩ ናቸው ሁሉም ገፆች መልካምና ጥሩ እንዲሆኑ ግን መጠበቅ የለብህም የንጋቱዋን ፀሀይ ለመሞቅ የለሊቱን ጨለማ በትግስት ማሳለፍ ግድ ነው እናም ምን ለማለት ነው ባንተ መቆም የሚቆም ባንተ መኖር የሚኖር ቢያንስ አንድ ሰው አለ ስለዚህ የፈለገውን ያክል ነገሮች አሰልቺ ቢሆኑብህ እንኳን ተስፋ መቁረጥን የመጨረሻ ምርጫህ እንኳን አታድርገው ከፈጣሪህ አትራቅ ዛሬ ላይ ማድረግ ያለብህን ካንተ የሚጠበቀውን እያደረክ ነገን መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርግ ማን ያውቃል ባልጠበከውና ባላሰብከው መንገድ ህይወት በራሷ የተቃናች ትሆን ይሆናል ምክንያቱም ህይወት ይቀጥላል ።
ረጃጅም ህንጻዎች ትናንሽ ትግስቶች፣ ሰፋፊ መንገዶች፣ ጠባብ አመለካከቶች፣ የምናወጣው ብዙ የሚኖረን ጥቂት፣ብዙ እንገዛለን ጥቂት እንደሰታለን፣ ትላልቅ ቤቶች ትናንሽ ቤተሰቦች፣ የተሻለ ምቾት ጥቂት ጊዜ፣ ብዙ ዲግሪ ትንሽ ማመዛዘን(ግንዛቤ)፣ ብዙ እውቀት ትንሽ ጥበብ፣ ብዙ አዋቂነት ብዙ ችግሮች፣ ብዙ መድኃኒት ትንሽ ጤነኝነት ስለ ጥሩ አኗኗር ተምረናል እንዴት እንዴት እንደሚኖር ግን አልተማርንም ለህይወት እድሜ ጨምረንለታል ለእድሜ ግን ህይወት አልጨመርንበትም መከባበር በመናናቅ መተዛዘን በመጠፋፋት ህሊና በሆድ ተተኩ ጨረቃ ላይ ደርሰን ተመለስን ግርግዳ የሚለየውን አዲሱ ጎረቤታችንን መተዋወቅ አቀበት ሆነብን ከምድራችን ውጪ ያለውን ህዋ ተቆጣጠርን በውስጣችን የሚገኘውን ትንሽ ቦታ ግን አልተቆጣጠርንም ትላልቅ ችግሮችን እንጂ የተሻሉ ነገሮችን አልሰራንም አካባቢያችንን እያፀዳን ነፍሳችንን ግን እየበከልን ነው አቶምን ሰነጠቅን መሰረተቢስ ጥላቻዎቻችንንና ቅራኔዎቻችንን ግን አልፈታንም ብዙ እናነባለን ትንሽ እንለወጣለን ብዙ እናቅዳለን ጥቂት እናደርጋለን መቸኮል እንጂ መጠበቅ አልተማርንም የተሻለ ገቢ እንጂ ያደገ ስነ ምግባር የለንም። ብዙ መረጃ የሚይዝና ብዙ ስራ ባጭር ጊዜ የሚያከናውነውን ኮንፒዮተር ፈጠርን እንጂ በመካከላችን ግን ብዙ መግባት አልተፈጠረም በብዛት ብዙ ሄደናል በጥራት ግን ወደ ኋላ ተጎትተናል። ጊዜው እንዲህ ሆነ ሰው በሁለት ገቢ የሚተዳደርበት ትዳር ግን የሚበተንበት የተሰነጣጠቁ ቤተሰቦች የሚኖሩባቸው ግን የተዋቡ መኖርያዎች። ወቅቱ ፈጣን ጉዞ የሚደረግበት ለአንድ ሌሊት ትዳር የሚወጣበትና ግብረ-ገብነት ተሽቀንጥሮ የተጣለበት ዘመን።
አእምሮ የሕይወት መሸፈኛ ሳይሆን ሕይወትን ነጻ የማውጫ መንገድ ነው፡፡ አሁን አሁን በሄድክበት ሁሉ ሰዎች “አእምሮህን መቆጣጠር አለብህ” ይላሉ፡፡ አእምሮህ ግን የሚያስፈልገው ነፃ መውጣት እንጂ ቁጥጥር ሊደረግበት አይደለም፡፡ አእምሮ እንቅፋት ሳይሆን፣ ትልቅ ዕድል ነው... አእምሮ እንቅፋት የመሆኑ ችግር የሚፈጠረው የአእምሮን መሰረታዊ ባህሪይ ሳትረዳና ሳታውቅ፣ ልትመራው ስትሞክር ነው፡፡ ዋነኛው የአእምሮ ችግር ሥነ ምግባር ነው፡፡ ሌላኛው ትልቁ ችግር ደግሞ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ትክክልና ስህተት የሚባሉት ነገሮች በአእምሮ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ እና መጥፎ የሆነ የሚለውን ሀሳብ አስተምረውሃል፡፡ ጥሩና መጥፎ በጣም ጠንካራ የሆኑ የማንነት ነጥቦች ናቸው፡፡ ስለሆነም ጥሩ ነው ብለህ በምትቆጥረው ትለያለህ፣ መጥፎ ብለህ ከምትቆጥረው ትርቃለህ፡፡ የሆነን ነገር መጥላትና ወደ ሌላ ነገር መሳብ የመለያው መሰረት ይሆናል፡፡ የምትጠላው ሁሉ በአእምሮህ ላይ የበላይ ለመሆን ይሞክራል፡፡ የአእምሮ አፈጣጠር አንድን ነገር “አልፈልግም” ስትል፣ ያ ነገር አእምሮህ ውስጥ መከሰት የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ በአእምሮ ውስጥ መደመርና ማባዛት ብቻ እንጂ መቀነስና ማካፈል የለም፡፡ ከአእምሮ ውስጥ ምንም ነገር በኃይል መውሰድ አትችልም፡፡ ይህን ለመረዳት ደግሞ ምንም መገለጥ አያስፈልገውም፡፡ 📓የሕይወት ኬሚስትሪ
እግዚአብሔር ጸሎታችን አይዘነጋም ግን it might take some times የጠየቅነውን እስኪሰጠን ወይም ከሆነ አመታት በፊት እግዚአብሔርን የጠየቅነው ጥያቄ ይኖራል ያ ጥያቄ ደግሞ mindset understanding and maturity level ይጠይቃል እነዚህ ነገሮች ደግሞ ዝምብለን በቀልድ የምናልፈው ሳይሆን Hustle እና ብዙ መውጣት መወረድ ይኖረዋል እግዚአብሔር በዛ ውስጥ ሲያሳልፈን ደግሞ እየሰራን ነው ማለት ነው ለጸሎታችን መልስ ሊሰጠን እያዘጋጀን ነው ! እኛን ለጥያቄዎቻችን መሸከም የምንችልበት ጥንካሬ ሊሰጠን ስለሚፈልግ ነው ነገሮች የሚዘገዩት or የዘገዩ የሚመስሉን እንጂ እንደጠየቅነው ወዲያው ቢሰጠን ወይ ልንጠፋበት እንችላለን ወይ ልናጠፋው እንችላለን because we are not matured enough or strong enough for that prayer እሱ ከእኛ የበለጠ ለእኛ ያስባልና እሱን መጠበቅ መልካም ነው።
ምንምን መናገር.. አንዳንድ ነገሮች ምስክር አያስፈልጋቸውም ማንም ማረጋገጫ አይስጥበት ብቻህን ታመመው ከመጀመሪያው ያልነበሩ ሰዎች ናቸው አሁን ላንተ ምስቅልቅል መፍትሄ አይሉት ፍርድ እየሰጡ የተቸገርከው.. እነሱም ልክ ናቸው አንተም የራስህን ነገር አድርግ ሰላምን እንጂ ፍፁምነትን አትፈልግ, ፍፁምነትን ሳታገኝ ሰላምህን ደሞ ላታገኝ ይሆንና ግራ ይገባሃል ያኔ ነው የመኖር ምክንያት የሚሉት ከባድ ጥያቄ የሚፈጠረው.. ማሰብ መልካም ማሰላሰል ጥሩ ሆነው ሳለ አንተ የያዝከው ጭንቀት ግን ተመችቶሃል.. ያርግልህ ባሻዬ ይመችህ.. ያለህበትን ምስቅልቅል ተቀብሎ የሚያኖርህ ቤት ካለህ እድለኛ ነህ ከሌለህ ደሞ መቃብርህን ስትናፍቅ ጊዜ ይቆጠራል.. የሄደ አይመጣም ያለ ደሞ ይሄዳል.. ይኼንን ስታይ ኖረሃል እሱም ይቀጥላል..
እንዲህ ነው ወይ....? ህይወት ልክ እንደ ትራፊክ መብራት እና መብራቱን ከበው መስቀልኛ መንገድ ላይ እንደቆሙ መኪኖች ናት። ህይወት በሆነ አጋጣሚ ያገናኘህ አንተ ቀይ ላይ ሆነሆ ለሱ አረንጓዴ ሲበራ ጥሎህ ይሄዳል። ቀይ የበራብን ግን ባለንበት ቋመን አለን.... አዎን አብሮህ ጎንለጎን እየተጓዘ የነበረ ወዳጅህ ለሱ አረንጓዴ በርቶ አንተን ቀይ መብራት ውስጥ ያለኸውን የሚጠብቅበት ምክኒያት የለም
በነገራችን ላይ ሰው ማጣትን ወይ ደሞ ከዜሮ መጀመርን አደለም ሰው ምን ይለኛል ትላንት አግኝቶ አጣ እባላለሁ ትላንት ሳረጋቸው የነበሩ የቅንጦት ነገሮች ሲቀሩ በሰዎች ዘንድ እታማለው ሚለውን ነው ሚፈራው ግን አንዳንዴ አጥቶ መመለስም ትልቅ ትምህርት ነው በአገኘንበት ጊዜ የሰራናቸው ስህተቶች ግልፅ ሁነው እናገኛቸዋለን በአገኘንበት ጊዜ መጥሮ የሆንበት እና ለውድቀታችን መነሻ የሆነውን ስህተት እንረዳዋለን መልሰን ብናገኝ እንኳን የአጣንበት ጊዜ ቀጥቶ አስተምሮናል እና ድጋሚ ያንን ስራ አንደግመውን ህይወት ፈትና ነው ምታስተምረው
ሁሉም እስካልረሰበት ድረስ አያውቀውም... የሰው ህመም የሚገባህ በቦታው ሆነህ ስታየው ብቻ ነው! ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል እንዲሉ አበው ከዳር ሆኖ መፍረድ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ እየተዝናናህ በአጠገብህ የአምቡላንስ ጩኸት ስትሰማ 'ለምን ያደነቁረናል' ብለህ ትናደዳለህ አንድ ቀን ግን የአንተ የሆነን ሰው ሲጭን "እባክህ ጥሩንባውን አስጩኽና መንገድ አስከፍት ቶሎ እንድረስ' ብለህ ትማፀናለህ....የሃዘን ቤት ምስር ይጣፍጣል ነው ያልከኝ? ልክ ነህ ይጣፍጣል..ጣዕም አልባ መሆኑ የሚገባህ አንተ ቤት ውስጥ ሲሰራ ነው!
ዕድሜህ በሄደ ቁጥር በዚህች ዓለም ሕይወት ላይ ያዘንክባቸው ነገሮች ሁሉ ያን ያህል ዋጋ ሊሠጣቸው እንደማይገባ ትረዳለህ። ህይወት እንዲሁ ናት። ታሸንፋለህ ትሸነፋለህ፣ ታዝናለህ ትስቃለህ፣ ታገኛለህ ታጣለህ፣ እድል ይመጣል ይሄዳል፣ ሰው ይሄዳል ይተካል፣ ምድር ላይ ለዘላለሙ አብሮህ የሚዘልቅ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የለም። የነገሮች መወለድና መሞት ያለ ነዉና ብዙ አትገረም።
መናገር ፈልገን ብዙ የያዝናቸው ነገሮች አሉ.... መናገር ፈልገን ብዙ የያዝናቸው ነገሮች አሉ፣ አንድም የሚረዳን አተን፣ አንድም ሰው ላለማስቸገር ብዙ ጣጣ ያለው ሰው ነው ወይም ደሞ ችግር አያጣውም ላለመባል ብዙ ነገር በውስጣችን አምቀን ተቀምጠናል፣ ደሞ ለአንድ ሰው ሚሰማንን ህመም በምን ምክንያት እንደሚሰማን ስንነግረው ያ ሰው እኛን ሚቀየመን ወይም ደሞ እኛ ላይ ሚፈርድበት ሰዓት ይኖራል፣ ሰው እኮ ወዶ አይደለም ደህና ነህ ወይ ብለህ ስትጠይቀው አይኑ በእምባም ተሞልቶ ይሁን እያለቀሰም ቢሆን ደህና ነኝ ብሎ ሚመልሰው፣ ደህና አይደለሁም ብንል ቀጣዩ ጥያቄ "ምን ሆነህ ነው ምን ተፈጥሮ ነው" ነው ሚሆነው ታድያ ሙሉ የውጣችንን እና የተፈጠረውን ሙሉ ዘርዝረን ተናግረን ሚረዳም ስለሌለ ነው፣ ብዙዎቻችን በራሳችን ዝምታ ውስጥ እየተሰቃየን ነው ወይ ጠይቃቹ ሲነገራቹ ተረዱን ወይ ደሞ ዝም በሉ አታሳቁን።
ሁላችንም ተፈላጊ የምንሆነው ዋጋችን ሲጨምር ብቻ ነው ለዚህ ደግሞ great example ዮሴፍ ነው።.... የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እሱ ተመልሰው የመጡት እሱ ጋር የሚያስመጣ ነገር ስለያዛቸው ብቻ እንጂማ ረስተውት ነበር እኮ። ዮሴፍ በወንድሞቹ ከተጠላበት ነገር አንዱ በህልሙ ነበር። ህልም ለሰው ሲነገር ሁሌ ያስቃል ሲፈታ ነው ትርጉም ያለው እና what i understand is that ህልማቹ እስኪፈታ ድረስ ሁሌም ሰዎች አያጨበጭቡላችሁም ሰዎች እንዲስቁባቹ የሚያደርግ ይሆናል your dreams ግን when the time comes and when you made it everyone will adore the dream so ቁም ነገሩ ምንድን ነው until our time comes በጸሎት መበርታቱ is the only option. የዮሴፍ መጨረሻ ያማረው አረማመዱ ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበር ነው። life passing by እያደረጋቹ ከመሰላቹ pray like this "ጌታ ሆይ የእኔ ተራ እስኪደርስ የምጠብቅበትን ትዕግሥት ስጠኝ ትዕግሥት እና ማስተዋልን አድለኝ" and work on your dreams it will come true.
አንዳንዴ መከራ እና ፈተናህ ሲበዛ ፈጣሪ አምላክ የተሻለ ነገር ሊሰጥህ ወይ ለጥሩ የወደፊት ሕይወት ዛሬ እያዘጋጀህ ብቻ አይሆንም.. ጊዜህ ደርሶ ልትሞትም ትችላለህ አትሸወድ.. ቢሆንም ግን.... ምናልባት የዚኛው ዓለም ትግል እና መከራ የሚያዘጋጀን ለቀጣዩ ለማያልፈው ዓለም ቢሆንስ ባሻዬ.. የመከራ እና ትግል ውጤት ፅናት ወይ ተስፋ መቁረጥ አይደል.. የምድርም የሰማይም ሞት ደሞ ተስፋ መቁረጥ ነው, ፅናታችን ደሞ ለማያልፈው ዓለም ዝግጅት ቢሆንስ.. በሥጋ ሳይሆን በነፍስ..
ባዶ የምንሆነው ራሳችንን ያጣን ቀን ነው.. ባዶነትን የምንተረጉምበት አውድ ይለያይ ይሆናል እንጂ ትልቁ ባዶነት ራስን ማጣት ነው.. አብዛኞቻችን የጠፋውን ራሳችንን ስንፈልግ ይመሽብናል.. አንዳንዶቻችን ደሞ ራሳችንን ማግኘት ስለማንፈልግ.. ባዶነታችንን በማስመሰል ሸፍነን ስንጓዝ ይመሻል.. ራስን ማጣት አይደለም ችግሩ አለመፈለግ እንጂ.. ማንም ሰዉ ባዶ የሆነ ቢመስለው ራሱን ፈልጎ ቢያገኝ ግማሽ ያህሉ የሕይወት ጥያቄዎቹ ይመለሱለታል.. ባያገኝ እና ባይሳካለት እንኳን ቢያንስ ህይወቱን በማስመሰል ስላልኖረ.. ማንነቱን በውሸት ስላልገፋው.. የመጣበትን ሳይረሳ ያለበትን ያውቃል.. አይደል መሰለኝ ብቻ አስቡበት...
ምንም አደረግን ምን እኛ ብቻ ትክክል እኛ ብቻ እውነተኛ እንደሆንን የሚሰማን ግብዞች.. ስህተትን ማመን እና ይቅርታ መጠየቅ ሽንፈት አይደለም.. ሽንፈቱ ስህተቱን መስራት ነው.. አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ስንሳሳት ተሸንፈናል አለቀ ምንም ማስተባበያ የለውም.. ትልቁ ማሸነፍ ደሞ ይቅርታ መጠየቅ አይደለም.. ስህተትን አለመድገም እንጂ.. አንድ ስህተት ላይ 3ቴ ከተገኘን ደሞ ምርጫችን ነው ወይም ፈልገነዋል ማለት ነው.. ስለዚህ አጉል ተጎጂ እና ተበዳይነቱን ትተን የመረጥነውን ማንነት ይዘን እንቀጥል.. ሰው ፃድቅ አይደለም ማለት እኛም አይደለንም ማለት ነው.. በጥፋታችን ላይ ኩርፊያ እና ሽሽት ጨምረን.. ከ 7 ዓመት ሕፃን የማይጠበቅ ባህሪ አናሳይ.. ማደግ በጭንቅላት ነው እንኳን አድርገነው ሳናደርገው የምንወነጀልበት ዓለም ላይ ራስን ብቻ ንፁህ አድርጎ መሄድ አይቻልም አትሸወዱ..
በጣም ከሚያስቸግሩኝ ነገሮች ውስጥ ሰው የተባለውን ፍጥረት መረዳት ነው እውነት የሰው ልጅን እንደመረዳት የሚያስቸግር እና ችሎታ ሚጠይቅ ነገር የለም። ውስጡ ሌላ ውጭው ሌላ። በአሁኑ ጊዜ አንድን ሰው አውቀዋለሁ ማለት ዘበት ነው እንኳን ትንሽ ጊዜ አውርተኸው አውቀዋለሁ ልትል ቀርቶ እድሜ ልክህን አብረኸው ብትኖር ራሱ ሰውን ማወቅ አይቻልም። በአንድ ሰው ውስጥ የሁለት ሰው ባህሪ ትመለከታለህ ለካስ ለሰው ሞት አነሰው የተባለው እውነት ሳይሆን አይቀርም... እናም ደግሞ ሁሌም ከሚያስደንቁኝ እና ከሚያስገርሙኝ ነገር ውስጥም ሰው ነው ለምን እንደሆነ በማላውቀው ሁኔታ ሰዎች ከእንስሳ የተሻለ አስተሳሰብ አላቸው ይላሉ እኔ ግን ይህን ሀሳብ አልደግፈውም ምክንያቱም ይሄ አስተሳሰብ የተባለው ነገር ካልተጠቀሙበት ከእንስሳ እንደማይሻል እና ሲጠቀሙበት በአግባቡ ካልሆነ ምኑን ከእንስሳ ተሻሉ? ተባለ እነዚህ ሰው የተባሉ ፍጥረታት ሲበዛ ራሳቸውን አጉልተው ማሳየት ይፈልጋሉ ይህ ባህሪያቸውን ስመለከት የሚያደርጉት ድርጊት ለሳቅ የሚጋብዝ እና በተቃራኒው ደሞ "ውይ ሰው መሆኔ" የሚያስብል ነው.... ስለ ሰው ተወርቶ አያልቅም በእውነቱ አንዱን ሀሳቤን ልፅፍ ስነሳ ሌላኛው ካልተፃፍኩ ብሎ ቁም ስቅሌን ያሳየኛል ሌላኛው ሀሳብ ይመጣና ካልፃፍሺኝ እጠፋለሁ የሚለኝ ይመስለኛል...
እየተዋደዱ መለያየት እንደ መለያየት ክፉ ነገር የለም። ማንም ልቤ ደንዳና ነው ባይ ከተላመደው ሰውም ሆነ ቦታ ሲለያይ ልብን የሚያሸብር፤ሆድን የሚያስብስ፤አንጀትን የሚበላ ስሜት ይሰማዋል። በህይወት አጋጣሚ ከሰዎች ጋር አለመገናኘት አለመተዋወቅ ነገሮችን እና ስሜቶችን አለመጋራት አይቻልም። እናም እነዚህን ትስስሮችን በቀላሉ ከሚበጣጥሱ ነገሮች አንዱ በአካል መራራቅ ነው። አማራጭ የለም እዚህ ምድር ላይ አንዳንድ ግዜ እየተዋደዱም እየተፈላለጉም መለያየት ግድ ነው። የህይወት ጉዞ መንገዳችን ሁሉን ጥለን እንድንሄድ ያስገድደናልና። ያንን ገመድ ድጋሚ አጥብቆ ለማስተሳሰር እና ያንን ግዜ ለመድገም አይቻልም። የዚያን ግዜ ሁሉም የማይቻል ይሆናል። መራራቅ ግዴታችን ይሆናል።