tgindex
𝑻𝒓𝒆𝒆𝒑𝒍

𝑻𝒓𝒆𝒆𝒑𝒍

Статистика

መማር ከፈለክ ቀኖች ሁሉ አስተማሪ ናቸው። https://t.me/treeplh2 ለጥያቄና ለአስተያየት @yisakor24

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
988
−5 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,10%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
466
22 постов
Вовлечённость
47,2%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
56
1/48двое суток
64
1/72трое суток
69

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሰዎች በድብቅ ይጠሉኛል፤ እኔ በግልጽ ችላ እላቸዋለሁ...!!🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2

  • 7 авг.202141

    የምሽቱን መንገድ ዝናብ የቀላቀለ ካፊያና ከየስራው ወደቤቱ የሚገሰግስ  የመኪና ጋጋታ ሞልቶታል።  ይሳቅ በካፌው ጥግ ባለው ወንበር ላይ ተቀምጦ፣ ከፊት ለፊቱ ፊቷን በእጆቿ ደግፋ በመስኮት ወደ ውጭ የምትመለከተውን ማህሌትን በዝምታ ይመለከታል። ፊቷ ላይ ያለው ሰላም እና እርጋታ ያስቀናል። የይሳቅ ልብ ግን በሃሳብ ይናወጣል። ባለፉት ጊዜ ያጠፋቸውን ጥፋቶች፣ በብስጭት የተናገራቸውን አስቀያሚ ቃላት፣ የዋሻቸውኝ እውነታዎች እና ያመከነውን ጊዜ እያሰበ ራሱን ይወቅሳል። እንዴት ከነዚህ ሁሉ ጉድለቶቼ ልትወደኝ ቻለች? ብሎ በልቡ ራሱን ጠየቀ። ማንነቱን፣ የውስጡን እድፍ፣ ውድቀቱን እና ድካሙን ከማንም በላይ ጠንቅቆ ያውቀዋል። አንዳንዴ እሱ ራሱ ራሱን መሸከም ሲከብደውና ራሱን ሲጠላ፣ እሷ ግን ምንም ሳትል፣ ሳትፈርድበት፣ በዚያች በማይነጥፍ ፈገግታዋ እና ርህራሄዋ ታቅፈዋለች። ይህ እኮ ለእኔ አይገባኝም... እሷ ከዚህ የተሻለ፣ ንፁህ የሆነ ሰው ይገባታል... የሚለው ሐሳብ ዘወትር አእምሮውን ይሞግተዋል። ከሀሳቡ ነቅቶ ቀስ ብሎ ጉንጮቿ የተደገፋንን እጇን ወደ ራሱ ሳበው እና ያዘው። ከምትመለከተው ግርግር አይኖቿን ወደ እርሱ መልሳ ፈገግ እያለች ጣቶቹን አጥብቃ ጨበጠች። ምን ሆንክብኝ የኔ ጌታ? በሀሳብ ርቀህ ሄድክ እኮ? አለችው የካፌውን ጫጫታ በሚያሸንፍ ለስላሳ ድምፅ። ምንም... ዝም ብዬ እያየሁሽ ነው። አንቺ ግን...  ቃላቶች ጉሮሮው ላይ እየተሰባበረ ...ከነጥፋቴ፣ ከነድካሜ እንዴት ልትወጂኝ ቻለሽ? እንዴት አልሰለችሽም?" አላት፣ ዝግ ባለ ድምፅ። አይኑን በፍቅር እያየች እጁን ይበልጥ አጥብቃ ያዘችው እና፣ ፍቅር ማለት እኮ ንፁህ እና ያልተበላሸ ገፅ ላይ አንድ ነገር መፃፍ ብቻ አይደለም ። ፍቅር ማለት የተበላሸውን ገፅ አብሮ ማስተካከል፣ የወደቀውን ማንሳት፣ የቆሸሸውን ማጠብ ነው። እኔ ያንተን ጥፋት ሳይሆን፣ በጥፋትህ ጀርባ ያለውን ደጉን እና የተሰበረውን ልብህን ነው የማየው፣ አለችው። ከነድካምህ ሰው ሲወድህ ፣ እንዴት ደስ ይላል? ከነ ሀጢአትህ  ከነጥፋትህ ፣ ሰው ሲያፈቅርህ፣እንዴት ደስ የሚል ስሜት አለው? ማንነትህን አይተህ ይህ እኮ ለእኔ አይገባኝም??...... እያልክ ፣ ግን ምንም  ሳይል ፣ ዝም ብሎ ሚወድህ ሰው ስታገኝ ፣ ከዚህ በላይ ምን መታደል  አለ?      ሰናይ ለሊት❤️ @treeplh2 @treeplh2

  • የሰው ልጅ የማሰብ  ችሎታው ሲጨምር ጓደኛ ይቀንሳል!! በስነ-ልቦናው ዓለም አንድ ታዋቂ አባባል አለ፦ ትልልቅ አእምሮዎች ስለ ሀሳብ ይወያያሉ፣ መካከለኛ አእምሮዎች ስለ ድርጊት ይወያያሉ፣ ትናንሽ አእምሮዎች ደግሞ ስለ ሰው ይወያያሉ። አንድ ሰው የማሰብ አቅሙ ሲጨምር፤ ለሐሜት፣ ለሰዎች የግል ህይወት ትንተና፣ እና ለትርጉም አልባ ጭቅጭቆች ያለው ትዕግስት እጅግ በጣም ይቀንሳል። በመሆኑም እነዚህን ነገሮች ከሚያዘወትሩ ሰዎች ራሱን እያገለለ ይመጣል። @treeplh2 @treeplh2

  • መጽሐፈ ምሳሌ 26:20-24 (NASV) •••••••••• ²⁰ ዕንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ አሾክሻኪ ከሌለም ጠብ ይበርዳል። ²¹ ከሰል ፍምን፣ ዕንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ አዋኪ ሰውም ጠብን ያባብሳል። ²² የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል። ²³ ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣ በብር ፈሳሽ እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው። ²⁴ ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤ በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል። ከሀሜተኛ ይሰውረን🚶‍♂❤️ @treeplh2 @treeplh2

  • ቡናዋን በዝግታ እያማሰለች መስኮት አሻግራ ትመለከታለች፤ ከውጪ የሚዘንበው ዝናብ የመንገዱን እንቅስቃሴ አቁሞታል። የኔ ትኩረት ግን ሙሉ በሙሉ እሷ ላይ ብቻ ነበር። የተገናኘንበትን ጉዳይ በስሱ ማውራት ጀመርኩኝ በጭራሽ አትገመትም፣ ታደርገዋለች ብሎ ማሰብ ዘበት እስኪመስል ድረስ ሀሳቧና ፍላጎቷ አይታወቅም፤ በውስጤ እያሰላሰልኩ ትኩር ብዬ ተመለከትኳት። አብሬያት የቆየሁባቸውን ጊዜያት ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስብ፣ ገፆቿ ያልተፃፉባት መፅሐፍ ሆና ነው የምትታየኝ። የሰው ልጅ በባህሪው ሲቀረብ ሚስጥሩ ይገረጣል፤ በርሷ ዘንድ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ያወቅኋት የመሰለኝ ቀን፣ አለማወቄ ይጎላል፤ ዛሬ አንድ እርምጃ ወደ ልቧ የተጠጋሁ ሲመስለኝ፣ ነገ በማይታይ የርቀት ግድግዳ ታጥረቀኛለች። እንደ ሌላው ሰው በድንገተኛ ነገሮች አትደነግጥም፣ በደስታ አትቦርቅም፣ በሀዘንም አትሰበርም። ዓይኖቿ ውስጥ ጥልቅ የሆነ እርጋታ እና ለመፍታት የሚያዳግት ዝምታ ብቻ ነው ያለው። ከዚህ በፊት ህይወትን የኖረችው ይመስል ብዙም ነገሮች አይገርሟትም። ምን ያህል ህይወት ቢገባት ነው እንዲህ ደመ-ቀዝቃዛ የሆነችው?!" ስል ራሴን ጠየቅሁ። የዓለምን ጫጫታ ሁሉ አልፋ፣ የሰውን ልጅ ስሜት ሁሉ አሟጥጣ የጨረሰች እና ወደ ሌላ የመንፈስ ከፍታ የወጣች ትመስላለች። ዝምታው በመሀከላችን ሲረዝም፣ ዞር ብላ አየችኝ። ከንፈሯን በስሱ እንደመሳቅ ለጠጠችው። ወሬ ለማስቀጠል ያህል፣ ሀሳቧ ከኔ ጋር የነበረ ለማስመሰል፤ "ይገርማል..." አለችኝ። እኔ ግን የልቧን ምት አውቀዋለሁ። አስባበት እና አሰላስላ እንጂ ተሰምቷት እንዳልሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የሷ ፈገግታ የውስጥ ደስታ መግለጫ ሳይሆን፣ ለእኔ ስትል የለገሰችኝ ምላሽ ነበረች። ያቺ ሰው ሰራሽ ፈገግታዋ እና የዓይኗ እርጋታ ተዳምረው ሊሸውዱኝ አልቻሉም፤ አጠገቤ ተቀምጣ ሳለ፣ የርቀቷ ልክ ተሰማኝ። በምሽት በቀስታ እንደሚነፍስ ነፋስ አይነት ቅዝቃዜ በአጥንቴ ሰርፆ ገባ። ይህች ሴት የራሷ የተለየች ዓለም አላት። እኔ ደግሞ በዚያች ዓለም ደጃፍ ላይ የቆምኩ፣ መቼም ቢሆን ወደ ውስጥ ገብቼ እውነተኛ ማንነቷን ማግኘት የማልችል ምፃተኛ መሆኔን ተረዳሁ፤ ነገር ግን ደግሞ ትቻት መሄድ ያቃተኝ የራሴ እስረኛ ነኝ። የነፍሷን ጥልቅ ባህር እንደ ሙሴ በትር ከፍዬ ለመረዳት መሞከር፣ በሬ ይወልዳል ብሎ እንደመጠበቅ ሆነብኝ........ @treeplh2 @treeplh2

  • የውስጣችንን ስሜት ሁሉ አውጥተን ብንዘረግፈው ዙሪያችንን እንደ እሳት ያቃጥላል ፤ አምቀን ዝም ብንል ደግሞ የገዛ የራሳችንን አንጀት ይበላል። መናገር የውጭ ጦርነት ነው፤ ዝምታ ደግሞ የውስጥ ጦርነት። የሕይወት ትልቁ ጥበብ፣ ራስን በማያደማ ዝምታ እና ሌላውን በማያቆስል እውነት መሀል መንገድ መፈለግ ነው። አንዳንዴ ለዚህ መፍትሄው ለሁሉም ሰው ከመናገር ይልቅ፣ ሀሳባችንን ያለፍርድ ለሚሰማን ለአንድ እውነተኛ ወዳጅ ማካፈል፣ ወይም ደግሞ ስሜታችንን በወረቀት ላይ መፃፍ የውስጥን ሸክም ያቀላል። @treeplh2 @treeplh2

  • ለሁለት ነገሮች አልታገልም....... 1 ለእውነተኛ ፍቅር 2 ለእውነተኛ ጓደኞች በሕይወታችን ውስጥ በላብ፣ በድካም እና በግዴታ ልናገኛቸው የማንችላቸው ውድ ነገሮች ቢኖሩ የልብ ትስስሮች ናቸው። እነዚህ ሁለት ፀጋዎች ልክ እንደ ንጋት ፀሀይ በራሳቸው ጊዜ ፈንጥቀው የሚወጡ እንጂ፣ ታግለን የምናመጣቸው አይደሉም። @treeplh2 @treeplh2

  • የህይወት ጎዳናህ የአንተ እና የአንተ ብቻ ነው። በጉዞህ ላይ ሰዎች አብረውህ ሊጓዙ መንገድህን ሊያደምቁት ወይም ድካምህን ሊያካፍሉህ ይችላሉ፤ ነገር ግን ማንም ያንተን ጫማ አጥልቆ ላንተ ሊራመድልህ፣ ወይም ህይወትህን ተክቶ ሊኖርልህ አይችልም። የእርምጃውም ሆነ የመድረሻው ባለቤት አንተው ራስህ ነህ። @treeplh2 @treeplh2

  • አንዳንዴ ወደ ህይወትህ ዳግም እንዲመለሱ ሳትፈልግ ያሳለፋችሁትን ጊዜ መናፈቅህ አንዳችም ክፋት የለውም። አብራችሁ የፈጠራችኋቸውን ውብ ትዝታዎች ወደኋላ መለስ ብለህ እያሰብክ ብትናፍቅም ተፈጥሯዊ ነው። ዛሬ ላይ አጠገብህ ሊሆኑ የማይችሉበትን እውነተኛ ምክንያት ስታስታውስ፣ ልብህ በሀዘን ቢከበድም አሁንም ችግር የለውም። አብራችሁ ያሳለፋችሁት ያ ቆንጆ ጊዜ ስላመለጠህ ወይም ትዝታው ስላንሰፈሰፈህ፣ ያንን ሰው ዛሬም በህይወትህ ዳግም ትፈልገዋለህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ የምንናፍቀው ሰዎቹን ሳይሆን፣ ከእነሱ ጋር የነበረንን ያንን ጣፋጭ ጊዜ ነው። ስለዚህ ያለፈውን ማሰብ፣ መናፈቅ እና ማዘን የሰው ልጅ ጤናማ ስሜት እንጂ፣ ወደተዘጋ በር የመመለስ ፍላጎት አይደለም። @treeplh2 @treeplh2

  • 2 июл.569201

    ከህይወት አንድ ነገር ተምሬያለሁ ፥ ለአንድ ሰው አስፈላጊ መሆን ትችላለህ ነገር ግን ለራሱ ጥቅም ሲሆን ብቻ ነው ።🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2

  • ሰዎች በአንተ ውስጥ ምንም መልካም ነገር ማየት እንደማይችሉ ሲናገሩ፤ እቅፍ አድርገህ ሕይወት ለዓይነ ስውራን አስቸጋሪ እንደሆነች ንገራቸው።😁 @treeplh2

  • ማንም ሰው በውለታ እንዲያስርህ አትፍቀድልት ፤ ገደል መግባት ይችላሉ ከነውለታቸው ።🚶‍♂ እድሜና ጤና ይስጥህ እጥፉን ትመልሳለህ እያደርን❤️ @treeplh2 @treeplh2

  • 8 июн.689131

    ሁሉንም አክብር ነገር ግን ማንንም አትፍራ። @treeplh2 @treeplh2

  • በሙት አይቀለድም እንጂ የሚቀጥለው አመት ምርጫ ላይ አስክሬን መረጠ ይሉናል። ከንቱ ሀገር🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2

  • 31 мая654161

    ብዙ ነገር ልታገስ እችላለሁ ፤ ንቀትን ግን መቼም አልታገስም። ሞቴን እመርጣለሁ!!😎 @treeplh2 @treeplh2

  • ብዙ ጊዜ በሕይወታችን ስንወድቅ ወይም መድረስ ያለብን ቦታ አልደረስንም ብለን ስንቆጭ ራሳችንን የምንቀጣው፣ ፍጹም ለመሆን ስለምንሞክር ነው። መላእክትን እንኳ ሳይቀር ስንፍና እንደሚከሳቸው በቅዱስ ቃሉ ተጽፏል፤ ፍጹም እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህንን እውነት ሲገባን ራሳችንን ከማይቻል የጭንቀት ቀንበር ነፃ እናወጣለን። መሳሳትና መውደቅ የሰው ልጅ ተፈጥሮ አካል መሆኑን ስንቀበልም፣ ውድቀትን እንደ መጨረሻ ሳይሆን እንደ መማሪያ ክፍል ማየት እንጀምራለን። ሰውን እውነተኛ ሰው የሚያደርገው ይህ ነው፤ እንደ እንስሳ ፍጹም ጨካኝና ሕሊና ቢስ አይደለም፣ እንደ መላእክትም ፍጹም ረቂቅ አይደለም። ሰው ማለት መውደቅና መነሳት የሚችል፣ ከስህተቱ በንስሐና በጸጸት ታጥቦ የሚቀደስ ድንቅ ፍጡር ነው። ውድቀት በራሱ ጨለማ ቢሆንም፣ ከጀርባው ግን “ተነስ! ገና ሰዓት አለህ፤ የጀመርከው ሕልም አለህ!”የሚል የፈጣሪ የቸርነት ሹክሹክታ አለ። ያንን ድምፅ ሰምቶ፣ አቧራውን አራግፎ መነሳት መቻል እሱ ነው የብልሆችና የጽኑዓን ሰዎች ትልቁ ጥበብ።🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2

  • ሰው በተስፋ መጠበቅ ያለበት እርግጠኛ የሆነበት ነገርን ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ ። አንዳንድ ነገር ላይ ያለን እይታ በሰማይ ላይ እንዳለ ደመና ነው፤ ተስፋ ግን መሬት ላይ የምትተክለው ዘር ነው። እርግጠኛ ባልሆንክበትና ባላመንክበት ነገር ላይ ሀሳብህን የመቀየር ሙሉ መብት አለህ። @treeplh2 @treeplh2

  • 23 мая643184

    አንዳንዶች በሰዎች አስተያየት፣ ክህደት ወይም መለወጥ ምክንያት ተስፋ ሲቆርጡና ሕይወታቸውን ሲያጨልሙ ማየት በእውነት ያስገርማል። ትላንት ወደ ሕይወትህ የመጣ፣ ታሪክህን የማያውቅ ባዕድ ሰው ዛሬ እንዴት ሙሉ ሕይወትህን የመወሰን፣ የመቆጣጠር ሥልጣን ይኖረዋል? በዚህች ምድር ላይ ሁሉም ነገር "ኮንትራት" ነው። ማንም ሰውና ምንም ነገር ለዘለዓለም አብሮህ እንዲኖር አልተፈጠረም። ከእናትህ ማኅፀን ጀምሮ አብሮ የተወለደ የለም፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ሕይወትህ የሚመጣው ለተወሰነ ምዕራፍ፣ ለአንድ የተለየ ምክንያትና ለጊዜያዊ ኮንትራት ብቻ ነው። ጊዜው ሲያበቃ ደግሞ ጥሎህ መሄዱ የማይቀር ሀቅ ነው። የወደደህ አብሮህ ይቀጥላል ፤ የደበረው ደግሞ ይሄዳል። ስለዚህ በሰዎች መምጣትና መሄድ ውስጥ ልብህን አታስጨንቅ። ራስህን ቻል፤ በገዛ እግርህ ላይ ብቻ ቁም። ማንም ሰው ያንተን ሰላም እንዲሰርቅህ አትፍቀድ። የሕይወትህ ድልድይ የሚሠራው በላብህና በጥረትህ እንጂ በሰዎች ቃልኪዳን አይደለም። አንተ ሹፌሩ ነህ ሌላው ተሳፋሪ ነው ፤ በጉዞ ላይ ደግሞ ተሳፋሪም ወራጅም አለ ሹፌሩ ከነተሳፋሪው ቤቱ ገብቶ አያውቅም።🚶‍♂ ሰላም እደሩልኝ❤️ @treeplh2 @treeplh2

  • 12 мая706153

    እንኳን ሰው ጊዜም ጊዜያዊ ነው ፤ በጊዜያቸው ይመጣሉ ፣ ጊዜያቸው ሲያበቃ ይሄዳሉ። @treeplh2 @treeplh2

𝑻𝒓𝒆𝒆𝒑𝒍 — tgindex