- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 46
- 1/48двое суток
- 52
- 1/72трое суток
- 56
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ወላጆች አደራ... ልጆቻችሁን አትራገሙ! አደራችሁን! ቢያጠፉ እንኳ 'ልጅነት ነው፣ ወጣትነት ነው፣ የጉርምስና ግለት ነው' ብላችሁ እለፏቸው እንጂ መጥፎ ቃል አትወርውሩባቸው። ለልጅ የሚገባው ዱዓ ማድረግ እንጂ እርግማን አይደለም!
ከሰዎች ጋር ለመኖር...በርህን ገርበብ አድርገህ ተወው፣የገባ ይግባ፣ የወጣም ይውጣ።በገቡት ብዙ አትደሰት፣በወጡትም ብዙ አትዘን። ሰው ይሄዳል ይመጣል፣የመጣዉን አላህ ነው ያመጣው፣የሄደዉንም አላህ ነው የሸኘው።
~ሞት አፋፍ ላይ ስትደርስ ቀልብ ይዛ የኖረችዉን ብቻ ነው የምትተፋው። የዛሬ የዕለት ተዕለት ዉሎአችን የነገ ኻቲማችን ነው። ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፣ በሞተበት ነገር ላይ ይቀሰቀሳል። አላህ ኻቲማችንን ያሳምርልን!
አላህ ሁለት ልቦችን ማቀራረብ ከሻ፤ በመካከላቸው ያለው ርቀት የሰማይና የምድር ያህል እንኳን ቢሆን ያሰባስባቸዋል፡፡ ዝምብላችሁ ዱዓ አድርጉ!!
ሰዎች ገፍተው ገፍተው ምርር አድርገውት ወደ አላህ እንደሄደ ሰው የታደለ ማን አለ? በደላቸው ወደ አላህ እንድንጠጋ ባደረገን ሰዎች ላይ የአላህ እዝነት ይስፈን!አላህን ካገኙ ወዲህ የሚታጣ ምናለ? (ምንም)
አንቱ ሰው ብቸኝነት ይሰማኛል አላቸው ወጣቱ እሳቸውም ምነው ከጌታህ ተለያየህ ???አሉት አልገባኝም አላቸው የኔ ልጅ በአላህ የተብቃቃ በሰው መምጣት መሄድ አይጎልም ! የኔ ልጅ ብዙ አብሮነቶችን አጣጥመናል ግና ከአሏህ ጋር እንደመሆን በላጭ ጣዕም ያለው አብሮነትን አላገኘንም☝️ አሉት Haq🥺
النجم فَأَعْرِضْ عَن مَّن تَوَلَّى عَن ذِكْرِنَا وَلَمْ يُرِدْ إِلَّا الْحَيَاةَ الدُّنْيَا 29 ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡ ኪታብ (ቁርዐን)
ከጠየቅኩት በላይ ሰጥቶኛል፣ ከጥረቴ በላይ ሸልሞኛል፣ ከለመንኩት በላይ ለግሶኛል። ርቄው አልተወኝም፣ ሸሽቼው አልጣለኝም፣ ረስቼዉም አልረሳኝም። አልሐምዱ ሊላህ!
እንግዳ ተቀባይና አክባሪ ህዝብ… ኢትዮዸያ!! ————————::—————- "ክርስቲያኖች ተሰደው ሲመጡ ተቀበልናቸው" 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በአሕመዲን ጀበል ✅✅✅✅✅ እኛ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ እምነት ተከታዮች ነበርን።ከመካከለኛ ምስራቅ በቅድሚያ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ተሰደው ወደኛ ሲመጡ በእንግድነት ተቀበልናቸው።እነርሱም እምነቱን መስበክ ጀመሩ። ከኛ ዉስጥ ጥቂቶች እምነቱን ተቀበሉ። ቀጥሎም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 ፍሪምናጦስ በተባለ ወጣት መሪነት ጥቂት የሶሪያ ክርስቲያኖች በስደት ወደ አክሱም መጡ። በእንግድነት ተቀበልናቸው። እምነታቸውን እንዲሰብኩ ፈቀድንላቸው።ክርስትናን መስበክ ጀመሩ። የአክሱሙ ንጉሥ ኢዛናን ጨምሮ ከኛ ዉስጥ ጥቂቶች ክርስትናን ተቀበሉ። ወጣት ፍሪምናጦስ ጳጳስ ፍለጋ ወደ ግብጽ አመራ። ንጉሡ ኢዛና ክርስትናን እንዲቀበል እንዳደረገ ገለጸ። ንጉሡን ክርስትና ማስነሳት ከቻልክ አንተኑ ጳጳስ እናድርግህ ብለው "አባ ሰላማ" ብለው ቀቡት። ክርስትናን የተቀበሉት ኢትዮጵያውያን ደግሞ "ከሳቴ ብርሃን" ብለው ሰየሙት። ክርስትና ከ330 እስከ 451 ድረስ የአክሱም ቤተ መንግስት ሃይማኖት እንጂ የአጠቃላዩ ሕዝብ ሃይማኖት መሆን አልቻለም ነበር። በአምስተኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ኢትዮጵያ ክርስትናን ለሕዝቡ የሰበኩትና ‹‹ዘጠኙ ቅዱሳን›› በሚል የሚታወቁት የሃይማኖት አባቶች ሁሉም መጤና የመካከለኛ ምስራቅ ስደተኞች ናቸው። እነዚህ ስደተኞች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ተሰደው የመጡት እ.ኤ.አ በ451 ከተካሄደው ‹‹ቻልኬዶን ጉባዔ›› በኋላ ነበር። ስደተኞቹ የሃይማኖት አባቶች አባ አፍጼ፣ አባ አሌፍ፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጉባ፣ አባ ሊቃኖስ፣ አባ ጴንጤሌዎን፣ አባ ጻሕማ፣ አባ የማታ፣ እና አባ ዘሚካኤል ዓረጋዊ ናቸው። (The Dictionary of Ethiopian Biography, Vol.1, From Early times to the End of the Zagwe Dynasty C.1270 AD, Institute of Ethiopian studies, Addis Ababa University, 1975, Pp. 209-210) ቀጥሎም በ615 ከመካ የኢስላም እምነት ተከታይ ሰሀቦች ተሰደው መጡ። ነጻነት በመስጠት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን በመቀበል በሀገራችን እንዲኖሩ ፈቀድንላቸው። እምነቱን ሰበኩ። ከኛ ዉስጥም ጥቂቶችም ኢስላምን እንደ እምነት ተቀብለው ሙስሊም ሆኑ። በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ጥቂት ስደተኞች በዚሁ ሞተው በትግራይ ተቀበሩ። የተቀሩት ከ15 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ክርስትና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 ወደ አክሱም ሲገባ ኢስላም ደግሞ ክርስትና ወደ አክሱም ከገባ ከ285(ከሁለት መቶ ሰማንያ አምስት) ዓመታት በኋላ ማለት በ615 ነበር የገባው። ከዚያ በኋላ እኛ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ጊዜ በተቀበልናቸው ሃይማኖቶች ምክንያት እምነታችን የተለያየ ሆነ። ከፊሉ አይሁድ፥ ከፊሉ ክርስቲያን፥ ከፊሉ ሙስሊም ሆነ። ቀጥሎም በ16ኛ ክፈለ ዘመን ካቶሊኮች ወደ ሀገራችን ተሰደው መጡ።ተቀበልናቸው። እምነታቸውን መስበክ ጀመሩ። ከኛ መካከል ከፊሎች የካቶሊክ እምነትን ተቀበሉ። ቀጥሎም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መጡ።ተቀበልናቸው።እምነታቸውን እንዲሰብኩ እኛ ኢትዮጵያውያን ፈቀድንላቸው። በዚህ ሁኔታ እኛ ኢትዮጵያውያን እምነታችንን እየቀያየርን ቀጠልን። ከፊላችን ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ወዘተ እየሆንን ቀጠልን። ከላይ በተጠቀሰው መልኩ በመጤ ስደተኞች የተሰበከውን እምነት እየተከተልን ዘለቅን።ነገር ከኛ መካከል በመጤ ስደተኞች የተሰበከው የአንዱ እምነት ከፊል ሰባኪዎች "ሌሎች እንጂ እኛ መጤ አይደለንም።" የሚል እይታ ያዙ።በእርግጥ መጤዎቹ እምነቱን ያመጡልን እንጂ እኛ የተቀበልነው ኢትዮጵያውያን አይደለንም። ከእምነቶቹ መምጣት በፊት ሀገርና ህዝብ ነበር።ዛሬም ሀገራችን የሁላችንም ስለሆነች ሁላችንን በምትመስልና እኩል በምትወክል መልኩ እንገንባት የሚል ጥያቄ ሲነሳ "እኛ ነባር እናንተ መጤ" የሚል የድንቁርና ጫወታ መጫወት ያማራቸውን ታዘብን። እኔም ሀገራችን የሁላችንም ናትና መስተካከል ያለባቸው ነገሮች እንዲስተካከል ሀሳብ ሳነሳ አፍ በማዘጋት ዝም ለማሰኘት ጥቂቶች ተረባረቡ። አክራሪ፣አይ፣ ኤስ፣ወሃቢያ፣ የእጌሌ ተላላኪ፣ ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ አቅደዋል፣ሌላም ሌላም። ያሻችውን ይበሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተሰደው ሲመጡ በመቀበላችን እንደምንኮራው ክርስቲያን ስደተኞችን በመቀበላችን እንኮራከን። ቸር እንሰንብት!
🌹#ፈገግ_በሉልኝ🌹 ታሪኩ በበፊቱ ጊዜ ነው! እናም አራት የ ገጠር ሰዎች በጀመአ አየሰገዱ ነበር። ከዛም ልክ ሩኩእ ሲያረጉ አንዱ ወይኔ ወገቤን አለ😳 ሁለተኛው ደሞ የወገብን ነገር አታንሳው ይለዋል🙆♂ ንግግራችዎን የሰማው ሶስተኛው ሰው ሶላት ላይ አይወራም ይላቸዋል🙊 ከሁሉም የባሰው አራተኛዉ አንተ ራስህ ሶላት ላይ አኮ ነህ ብሎት አርፍ😁 #አውነተኛ_ታሪክ_ነው
▢ አላህ ሆይ! አስደስተን፣ለኛ መደሰት ደፋ ቀና የሚሉትንም አስደስትልን፣ እኛን ማስደሰት ፈልገው ያልሆነላቸዉንም ከመደሰታችን በፊት እነርሱን አስደስትልን፣ ተደስተን ስያዩ ደስ የሚላቸዉንም ደስ እንዲላቸው አድርግልን፡፡ ኢላሂ! መልካም ሀሳብ ያለው ሁሉ ደስታን አይጣ፡፡
۞ وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبًّا جَمًّا ۞ { ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡ } መልዕክቱን ለሌሎችም ያጋሩ 🤝 ✅ -{ قال ﷺ }بلغوا عني ولو آية የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብሏል ከእኔ አንዲትንም አንቀፅ ቢሆን አድርሱ
ዋናው ቁምነገር መሸፈኛ መኖር ብቻ አይደለም፤ ዋናው ቁምነገር መሸፈኛው የሚያስገኘው እውነተኛ ሲትር (እራስን በአግባቡ መሸፈን) ላይ ነው። የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «(በስም) የለበሱ ነገር ግን (በተግባር) እራቁታቸውን የሆኑ፣ (ከትዕዛዝ) ያዘነበሉና (ሌሎችንም ወደ ስህተት) የሚያዘነብሉ፣ ራሶቻቸው ልክ እንደ ዘንበል ባለ የግመል ሻኛ የሆኑ ሴቶች አሉ። እነሱ ጀነት አይገቡም፤ የጀነትንም ጠረን አያገኙም።» ሒጃብ ሲትር ነው። ዛሬ በህይወት እያለሽ ካለበሽው፤ ነገ ስትሞቺ ትከፈኝበታለሽ።
የመስጂድ ስርዕቶች ❶ መስጂድ ከመምጣት በፊት ነጭ ሽንኩርት ከመመገብ መቆጠብ ❷ ሴት ልጅ ሽቶ ከመቀባት መቆጠብ ❸ ወደ መስጂድ ሲኬድ በእርጋታ መራመድ ❹ ወደ መስጂድ ሲኬድ ይህን ዚክር(“አላሁመጅዕል ፊቀልቢ ኑራ ወፊ ሊሳኒ ኑራ ወፊ ሰምዒ ኑራ ወፊ በሰሪ ኑራ ወሚን ፈውቂ ኑራ ወሚን ታህቲ ኑራ ወአን የሚኒ ኑራ ወአን ሺማሊ ኑራ ወሚን አማሚ ኑራ ወሚን ኸልፊ ኑራ ወአእዚምሊ ኑራ ”)ማለት ❺ መስጂድ ሲገባ ቀኝ እግርን ማስቀደም ❻ መስጂድ ሲኬድ ይህን ዚክር(“አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊ ሙሀመድ አላሁመፍታህሊ አብዋበ ራህመቲክ ”)ማለት ❼ ሁለት ረከዕ (ተህየተል መስጂድ) መስገድ ❽ መስጂድ ውስጥ ከመትፋት መጠንቀቅ ❾ መስጂድ ውስጥ ድምፅን ዝቅ ማድረግ ❿ መስጂድ ውስጥ ከመሸጥና ከመግዛት መቆጠብ ❶❶ መስጂድ ውስጥ የጠፋን ነገር አፋልጉኝ ከማለት መጠንቀቅ ❶❷ አዛን ከተደረገ በሆላ ከመስጂድ አለመውጣት ❶❸ ከመስጂድ ሲወጣ ግራ እግርን ማስቀደም ❶❹ ከመስጂድ ሲወጣ ይህን ዚክር (“አላሁመ ዒኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ”)ማለት
አላህ ሲወድህ፣ በአንድ ግንኙነት ውስጥ ብዙ ርቀህ ሳትጎዳ የዚያን ሰው እውነተኛ ማንነት ቀድሞ ያሳይሃል። ሁሉም ነገር ለኸይር ነውና፤ ከእጅህ ባመለጠና በራቀህ ነገር ላይ ሁሉ ትርጉም በሌለው ሐዘን አትብሰልሰል።
ምኞት አየለና ቀደሩን አስረሳን፣ ለጥቂት ቀን ፈተና ሰላምን አጣን። የነገው ሲጨንቀን የዛሬው ሲገፋን፣ የዓለሙ ጌታ መኖሩን ዘነጋን።
ለጊዜው ተሸሽጎ የቆየ ማንነት ፍጻሜው ሲቃረብ መጋለጡ አይቀሬ ነው፤ ጭንብል ተለብሶ ቢኖርም እውነተኛው ባሕሪ አንድ ቀን አፈትልኮ ይወጣል። ሰው በሕይወት ዘመኑ ሲያዘወትረው በነበረው ተግባር ላይ ሕይወቱ ያልፋል፤ በዚያው በለመደው ማንነቱም ለፍርድ ይቀርባል። ስለሆነም፣ የነገውን ውርደት ለማስቀረት ዛሬውኑ ራስን መመርመርና መጥፎ አመሎችን ማረም ብልህነት ነው።
ከስልካችን ጋ እንደምንሆነው ከቁርኣን ጋ ብንሆን ኖሮ..
መጥፎዎች ለመጥፎ፣ ጥሩዎች ለጥሩ ይሄ ነው የጌታህ የትዳር ሚስጥሩ! ቀድመህ ራስህን በኢማን አሳምር፣ ሷሊህ አጋር ይስጥህ እንዲሰምር ትዳር።
እንዲህ የምትሆን ፍጡር ነህኮ ! ኩራቱ ከየት መጣልህ