Dire Soccer
СтатистикаThe Voice of Ethiopian Football Telegram : https://t.me/DireSoccer Facebook : https://m.facebook.com/diresoccer
- Последний пост
- 29 июл.
- Последнее чтение
- 19:59
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Спорт
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 406
- 1/48двое суток
- 465
- 1/72трое суток
- 501
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
“ ታዳጊ ቡድኑ በፍቃዱ ጠፍቷል “ ፖሊስ “ የጠፉት ታዳጊዎች የሄዱት በራሳቸው ጥረት ነው በፌዴሬሽኑ አልተላኩም ” የኢ/እ ፌዴሬሽን በስዊድን በተካሄደ የታዳጊዎች ውድድር ' ጎቲያ ካፕ ' ላይ ለመካፈል ያቀኑ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች መጥፋታቸው ተገልጿል። ወደ ስፍራው የተጓዙ ሀያ ተጨዋቾች እና የቡድን መሪዎቹ መጥፋታቸውን የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል። የአካባቢው ፖሊስ የውድድሩ አዘጋጆች በደረሰው ጥቆማ የቡድኑን መጥፋት እንዳረጋገጠ ይፋ አድርጓል። በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን “ በታዳጊዎቹ መጥፋት አዝነናል “ ብሏል። ፌዴሬሽኑ አክሎም “ ታዳጊ ቡድኖች በመሰል ውድድሮች ላይ በራሳቸው ጥረት በሚያገኙት እድል ወደ ውድድሩ የሚያመሩ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የወከሉ አለመሆኑን እንገልፃለን " ብሏል። SHARE || @DireSoccer
🚨 ትውልደ ኢትዮጵያዊው ካናዳዊ ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው ! በዘንድሮው የ2026ቱ የአለም ዋንጫ በካናዳ ብሔራዊ ቡድን ምርጥ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሊ አህመድ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እንደሚመጣ ተነግሯል። አሊ አህመድ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ የታዳጊ እና ወጣት ስፖርተኞችን ተሳትፎ ማበረታትት እና በኢትዮጵያ የስፖርት ልማት ላይ አዎንታዊ አሻራ ለማሳረፍ ፍላጎት ማሳየቱ ተገልጿል። ተጫዋቹ በቀጣይ ሳምንት የሚኖረው የጉብኝት ጊዜ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የሚያንጸባርቅ ተምሳሌት መሆኑን በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። [ ሳምሶን አበበ ] SHARE || @DireSoccer
ኡርጂ ቀፊራ ነጥብ ተጋርቷል ! የ2018 የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ውጤት ! ኡርጂ ቀፊራ 0-0 መንቆረር @DireSoccer
ለገሀሬ ሽንፈት አስተናግዷል ! የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ውጤት አራዳ ክ/ከተማ 3-1 ለገሀሬ 38' ሚኪያስ ደምሴ / 90+5' አብዱላሂ አህመድ 75' ሚኪያስ ደምሴ 90+3' ፀጋዬ ፈለቀ @DireSoccer
ሁለቱ የድሬዳዋ ከተማ ተወካዮች ሽንፈት አስተናግደዋል ! የ2018 የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ሳቢያን ሕብረት 0-2 ባምባሲ ቤል ሚሊ 45+1' ሌታ ደነቦ 89' ኢብራሂም ያሲን ታይዋን 0-2 ጉለሌ ክ/ከተማ 22' ቅዱስ ጥሩነህ 69' ንኩት ባንግ @DireSoccer
የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የሦስተኛ ቀን ጨዋታ መርሐ ግብር ማክሰኞ ሐምሌ 7 2:00 ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከ አሳኢታ ወረዳ (መከላከያ ሜዳ) 2:00 ሽራሮ ከተማ ከ ስርጢ ከተማ (ሳቢያን ሜዳ) 2:00 ሐረር ዩናይትድ ከ ቡርታ ከተማ (ዩኒቨርሲቲ ሜዳ) 4:00 ሁፃ ቆላ ገረአልታ ከ ብሎድ ግሉ ዙባራ (መከላከያ ሜዳ) 4:00 አርባምንጭ ዙርያ ከ ሸዋ ሮቢት (ሳቢያን ሜዳ) 4:00 አጄ ከተማ ከ ቴፒ ከተማ (ዩኒቨርሲቲ ሜዳ) 10:00 ወሊሶ ከተማ ራማ አዴ አርባዕተ (ሳቢያን ሜዳ) 10:00 ጊምቦ ዳዲበን ከ ኬሌ ከተማ (ዩኒቨርሲቲ ሜዳ) SHARE || @DireSoccer
የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ውጤቶች አራዳ ክ/ከተማ 1-0 ዲክሲስ 4' ያሬድ ሙሉጌታ ሁርጂ ቀፊራ 2-1 ቃኘው 21' ማርሲላስ ወንድማገኝ / 12' ናትናኤል ዘለቀ 48' ሮቤል ጉዑሽ ጊምቢ ከተማ 1 - 1 ወረኢሉ ከተማ 61"በሀይሉ ፍሰሀ 16" ብርሃኑ ገ/እየሱስ መንቆረር 1-1 ቦረና ከተማ 45' አለባቸው ተስፋሁን / 29' ስንታየሁ ተስፋዬ ባምባሲ ቤላ አገሩ 0-1 መቱ ከተማ 59' ጋሪዊች ማሉድ ቂርቆስ 2-0 ምዕራብ ዓባያ 12' ቅዱስ ገብረ 90+1' ናትናኤል ቢንያም አዲስ አበባ ፖሊስ 0 - 1 ትግራይ ዋልታ ፖሊስ 2' ዙብር አህመድ SHARE || @DireSoccer
🇪🇹የ2018 የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ⌚️ የሙሉ ሰዓት ውጤት ኡርጂ ቀፊራ 2-1 ቃኘው 21' ማርሲላስ ወንድማገኝ 12' ናትናኤል ዘለቀ 48' ሮቤል ጉዕሽ SHARE || @DireSoccer
የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የ2018 ውድድር በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም በድምቀት ጅማሮውን አድርጓል። በመክፈቻው ሥነ ስርዓት ተሳታፊ ክለቦች የመጡበትን ክልል ባህላዊ አለባበስና ጭፈራ ያስተዋወቁ ሲሆን በመርሐ ግብሩም የድሬደዋ ም/ከንቲባ የተከበሩ ሃርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ ዋና አዛዥና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ፣ የኢ/እ/ፌ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሸረፋ ዴሌቾ፣ የኢ/እ/ፌ ውድድር ዳሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ፣ የድሬዳዋ እ/ፌ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ውድድርና ስነስርአት ሰብሳቢ አቶ ኤርምያስ ኃይሉ እንዲሁም የድ/ዳ/ከ/አ/ወ/ስ/ኮ የስፖርት ማስፋፋና ማልማት/ደ/ዳሪክተር አቶ ኢብሳ ዱሪ ተገኝተዋል። የዛሬ ጨዋታ ውጤት ለገሀሬ 2-0 ገሱባ ከተማ 57' ናትናኤል አየለ 66' ካሌብ አበበ (ፍ) የነገ ጨዋታዎች 2:00 አራዳ ክ/ከተማ ከ ዲክሲስ ከተማ (ሳቢያን) 2:00 ቂርቆስ ክ/ከተማ ከ ምዕራብ አባያ (ዩኒቨርሲቲ) 2:00 ሁርጁ ቀፊራ ከ ቃኘው (መከላከያ ሜዳ) 4:00 ባንባሲ ቤላ አገሩ ከ መቱ ከተማ (ዩኒቨርሲቲ) 4:00 መንቆረር ከ ቦረና ከተማ (መከላከያ ሜዳ) 4:00 ጊምቢ ከተማ ከ ወረኢሉ ከተማ (ሳቢያን) 10:00 አዲስ አበባ ፖሊስ ከ ትግራይ ዋልታ ፖሊስ (ሳቢያን) SHARE || @DireSoccer
የ2018 የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ⌚️የሙሉ ሰዓት ውጤት' ለገሃሬ 2-0 ገሱባ ከተማ 57' ናትናኤል አየለ 66' ካሌብ በየነ (ፍ) @DireSoccer
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል። አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በሁለት ዓመት ውል አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ በይፋ ተሹመዋል። ©Dagu Sport
የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፕዮና ውድድሩ ምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል። SHARE || @DireSoccer
የቦታ ለውጥ ! የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ አስቀድሞ እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት ከነበረው አበበ ቢቂላ ስታዲየም የቦታ ለውጥ ተደርጎበታል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 5፡00 ይካሄዳል። በሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓ/ዩ መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት በሳተላይት እና ኦንላይን አማራጮች ይተላለፋል። SHARE @DireSoccer
ኤንሪኬ የባሕር ዳርቻ ተሰየመላቸው ! ስፔናዊው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በትውልድ ስፍራቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በስፔን ሂሆን ከተማ በስማቸው የተሰየመውን የባህር ዳርቻ መርቀዋል። ሉዊስ ኤንሪኬ በስፍራው ስለ ቤተሰባቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ስሜታዊ ሆነውም ታይተዋል። ስለ ስፔን የአለም ዋንጫ ጉዞ የተጠየቁት ኤንሪኬ “ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከባድ ናቸው ቡድኞች አጥብቀው ይከላከላሉ “ ብለዋል። አክለውም ጥሩ እየተጓዝን ነው በቀጣይ ጨዋታዎች የተሻለ እንቅስቃሴ እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል። ©Tikva Sport
ኢትዮጵያ መድን ድል አድርጓል ! በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2ለ1 አሸንፏል። የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግብ ረመዳን የሱፍ እና ዳዊት አውላቸው አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግብ አብዱ ሞሀመድ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ መድን ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አሳክቷል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 10 ኢትዮጵያ መድን :- 40 ነጥብ 13 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 38 ነጥብ @DireSoccer
የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜን ማን ይመራል ? በአርሰናል እና ፒኤስጂ መካከል የሚደረገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል። ሀንጋሪ ቡዳፔስት ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ዳንኤል ሴበርት በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩ ተመርጠዋል። ዋና ዳኛው ባለፈው ሳምንት አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1ለ0 ያሸነፈበትን ጨዋታ መምራታቸው አይዘነጋም። አርሰናል ከዚህ በፊት በዳኛው እየተመራ 4️⃣ ጨዋታዎች አድርጎ ሁሉንም ማሸነፍ ችሏል። የፍፃሜ ጨዋታው ግንቦት 22/2018 ዓ.ም በቡዳፔስት ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ይደረጋል። @DireSoccer
ሴኔጋል የወጣቶች ዋንጫ አሸናፊ ሆነች ! ሴኔጋል የአፍሪካ ትምህርት ቤቶች ሻምፒዮና ውድድር የዋንጫ አሸናፊ መሆን ችላለች። አንበሶቹ የመጀመሪያ የአፍሪካ ትምህርት ቤት ዋንጫቸውን አሸንፈዋል። የሴኔጋል ከ 15ዓመት በታች ቡድን በፍፃሜው የዩጋንዳ አቻውን በማሸነፍ ነው ባለድል የሆነው። ሴኔጋል በግማሽ ፍፃሜው ሞሮኮን 4ለ0 በማሸነፍ ነበር ለፍፃሜ ያለፈችው። ሞሮኮ በውድድሩ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ ያሸነፈች ሲሆን ነገርግን ሽልማቱን ለመቀበል ሳትቀርብ ቀርታለች። Join // https://t.me/diresoccer
ጦሩ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው መቻል በዘንድሮ የውድድር ዓመት ለዋንጫው ከታጩ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን ከ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በፊት ከመሪው ሲዳማ ቡና በ11 ነጥቦች ርቆ ተቀምጧል። ቡድኑም ከመሪው ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ በዛሬው ዕለት ወሳኝ ጨዋታውን ሀዋሳ ላይ የሚያደርግ ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ክለቡ ሁለት ወጣት ተጫዋቾችን ማዘዋወሩ ታውቋል። ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች አንዋር ሙቀዲስ ነው። የጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ፍሬ የሆነው አጥቂው አንዋር ዓምና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን ዘንድሮም ለቡድኑ 8 ግቦችን አስቆጥሮ በፉክክሩ ደረጃ 2ኛ ላይ ተቀምጧል። ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ ኝሆኝ ጋት ነው። እንደ አንዋር የጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ውጤት የሆነው የተከላካይ አማካዩ ኝሆኝ በቡድኑ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከቡድን አጋሩ ጋር በመሆን መቻልን ለሁለት ዓመት ተቀላቅሏል። ©Soccer Ethiopia Join // https://t.me/diresoccer
без подписи
ስለ ጠፉት ተጫዋቾች ምን ተባለ? ትላንት በእግርኳሱ ዙሪያ አነጋጋሪ የነበረዉ 7 የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ደቡብ አፍሪካ በመኮብለል ጥገኝነት መጠየቃቸዉ ነበር፤ነገርየዉ የኤርትራን በስፖርት ዘርፍ ያለዉ እንቅስቃሴ ለሚከታተል ሰዉ አስደንጋጭም አዲስ ነገርም አልነበረም። ትላንት ይህ ዜና በአለም አቀፍ ሚዲያዎች መዉጣቱን ተከትሎ ከኤርትራ ዉጪ የሚገኙ በርካታ ኤርትራዉያን በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በ ትዊተር(X) ሀሳባቸዉን እየገለፁ ይገኛሉ፤ብሄራዊ ቡድኑ ከዚህ በኋላ ተጫዋቾችን በዉጪ ሀገር ሆነዉ የሚጫወቱ ኤርትራውያንን ብቻ እንዲጠራ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ። ሰሞኑን በተካሄደዉ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ በርካታ የቡድኑ አባላት በዉጪ የሚጫወቱ ሲሆን 10 የሚሆኑ ተጫዋቾች ግን ከኤርትራ የተጠሩ ነበሩ፤ ወደ ሀገራቸዉ መመለስ ከነበረባቸዉ ተጫዋቾች 7 ተጫዋቾች ጠፍተዋል። ይሄም የሀገሪቷን ገፅታ ከማበላሸት አልፎ ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን ሀገሪቱ እንዳትገነባ እንቅፋት እንደሚሆን በርካቶች እየገለፁ ይገኛሉ። ከዚህ በፊት ከ 20 አመት በታች ሴት የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች በአፍሪካ ሀገራቶች ጥገኝነት በመጠየቅ ጠፍተዋል። አፍሪካዊቷ "ሰሜን ኮሪያ" በመባል የምትታወቀዉ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ሉዐላዊ ሀገር ከሆነች በኋላ በሀገሪቱ ባለዉ የጉዞ ገደብ፣ማለቂያ የሌለዉ ወታደራዊ ግዳጅን ጨምሮ በርካታ ሰብዐዊ ወንጀሎች በመንግስት በኩል እንደሚፈፀም ይታወቃል በዚህም ምክንያት ተጫዋቾች በወጡበት ሀገር ይጠፋሉ ይህም ለሀገሪቱ ከባድ ራስ ምታት ሆኗል። በጠፉት ተጫዋቾች ዙሪያ የሀገሪቱ ፌዴሬሽን እስካሁን ያለዉ ነገር የለም፤ብሄራዊ ቡድኑ በጠንካራ አቋም እንዲቀጥል ከተፈለገ ግን ሙሉ በሙሉ በዉጪ ሀገር የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ እንዲጠሩ ሀሳብ ቀርቧል። ©Sheger Sport Arena Join // https://t.me/diresoccer