Охват к подписчикам
12,5%
ERR
Реакции к просмотрам
0,10%
108 на 50 постов
Пересылки к просмотрам
0,05%
54
Постов в день
6,0
всего 126
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 17 авг."ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ ይገኛል" - ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ===========*************============ ዲ.ዩ: ነሐሴ 11/12/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደራጀት ላይ የሚገኙ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በዩኒቨርሲቲው በአራቱም ጊቢዎች እጅግ ዘመናዊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች የተሟላላቸው የስማርት መማሪያ ክፍሎችን በማደራጀት ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። ፕሬዝዳንቱ በሀሴዴላ ጊቢ እና በማስተማሪያ ሆስፒታሉ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማደራጀት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ አውስተዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል። ዲላ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን፣ በርካታ አዳዲስ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎቹን ለመቀበል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል። ===###=== #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland1,23%
- 16 авг.የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ ==============**********=========== ዲዩ: ነሐሴ 10/2018 አ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ከተማ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ አማካኝነት ለሚገነባው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ግንባታ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የድርጅቱ ኃላፊዎች በተገኙበት የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት በኩል የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አንስተው፣ የሜሪጆይ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ተቋሙ የበኩሉን እንደሚወጣ አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው በሆስፒታሉ አማካኝነት ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ መሠል የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግም አንስተዋል። የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)ሜሪጆይ የኩላሊት እጥበት ማዕከል በከተማው መገንባቱ በጤናው ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እንደሚሆን ገልፀው፣ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ባለድርሻ አካላትን ለማስተባበር እና ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልፀዋል። በከተማው የሜሪጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ማዕከል መገንባ፣ የማህበረሰቡን የጤና ዘርፍ ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ሚላ እንደሚኖረው የገለፁት ደግሞ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የዲላ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ግርማ ደብረ ናቸው። ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር እና ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ማዕከሉ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ በትብብር ለመስራት እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ማዕከሉን እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ በመድረኩ ተገልጿል። #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲው #UniversityOfTheGreenland 1,03%
- 11 авг."በቀናነት ከሰራን፣ ችግሮች ሲኖሩ በመቀራረብ ከፈታን፣ ተቋማችንን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንችላለን" - ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ============**************============ ዲዩ: ነሐሴ 05/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በየዘርፉ የቀረቡ የ2018ዓ.ም የእቅድ ክንውን ሪፖርትን ገምግሟል። በበጀት ዓመቱ በመማር ማስተማር ዘርፍ፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በዲጅታላይዜሽን ረገድ፣ አጠቃላይ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች፣ የጤና ዘርፍ ተግባራት፣ በግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የተከናወኑ ተግባራት ለካውንስሉ ቀርበዋል። የካውንስል አባላት በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ ሀሳብና አስተያዬት ሰጥተዋል። አገልግሎት ያቆሙ መሳሪያዎችን ወደ አገልግሎት በመመለስ ረገድ የተሰራው ስራ፣ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችና የነበሩ የጉድኝት ተግባራት የሚበረታቱ ስለመሆናቸው የካውንስሉ አባላት አንስተዋል። የመምህራን የቤት ችግርን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች እንደመኖራቸው መጠን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲሰራ፣ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግም የካውንስል አባላቱ ጠይቀዋል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከካውንስሉ የተነሱ ሀሳቦችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ቀሪ ተግባራቶቻችን ላይ በማከል የተሻለ ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲኖር ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል። የትምህርት ሴክተር ሪፎርምን መሬት የማውረድ ስራ በትኩረት መሠራት እንዳለበት የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ ከሪፎርሞቹ አንዱ የሆነው የትኩረት አቅጣጫ እና የልየታ ስራ ላይ የቀሩ ተግባራትን መከወን የአዲሱ የትምህርት ዘመን ቀዳሚ ስራ መሆኑን ገልፀዋል። ቤተሙከራዎች እና ፕሮግራሞቻችንን በሀገር አቀፍ እና በዓለምአቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ በትኩረት መስራት ይኖርብናልም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ። የራስ ገዝነት ስራ ቀጣዩ የቤት ስራችን ሊሆን ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ወደዚህ ለመግባት በሚያስችሉ አመቺ ሁኔታዎች ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል። የመማሪያ ክፍሎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አክለዋል። ከመምህራን ቤቶች ጋር ተያይዞ ከካውንስሉ ለተነሳው ጥያቄ፣ የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። በቀናነት ከሰራን፣ ችግሮች ሲኖሩ በመቀራረብ ከፈታን፣ ተቋማችንን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንችላለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ የታቀዱ ስራዎች ሁሉ ከግብ እንዲደርሱ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል ድጋፉን እንድያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል። የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ የበይነ መረብ ትምህርት ስርዓትን እውን ለማድረግ በተቋም ደረጃ ስቱዲዮ ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። የፀጥታ ስራዎችን የበለጠ የማጠናከር፣ አዲሱ ሆስፒታልን ወደ ስራ የማስገባት ስራ የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት ዘርፎች አካል ስለመሆናቸውም አንስተዋል። የአመራር ብቃትን የበለጠ ለማጎልበት እንዲሁም በሁሉም ዘርፎች ላይ የተለያዩ ተከታታይ ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። በዩኒቨርሲቲው የተጀመሩ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከወትሮ በተለየ መልኩ እንደሚሰራም አውስተዋል። በዩኒቨርሲቲው ስር ያሉ የምርምር ጣቢያዎች አስፈላጊው ሁሉ መሠረተ ልማት እንዲሟላላቸው መስራት እንደሚያስፈልግም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል። በሪፖርቱ ላይ የቀረቡ መልካም ስራዎችን ለማስቀጠል፣ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይም በየደረጃው ያለው የዩኒቨርሲቲው አመራር በመቀናጀት ለተሻለ አፈፃፀም አብሮ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል። ===###=== #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ0,61%
- 21:18ማስታወቂያ0,52%
- 13 авг."ተወዳዳሪ ዜጋ የሚፈልቅባቸው ሞዴል ትምህርት ቤቶች እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል" ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) =========*************========= ዲ.ዩ: ነሐሴ 07/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር)የተመራ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ልዑክ ቡድን በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኙ የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። የየትምህርት ቤቶቹ የስራ ኃላፊዎችም ለልዑካኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በየትምህርት ቤቶቹ ያሉ የግብዓት እና ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት የተቋሙ አመራሮች ምልከታ በማድረጋቸው አመስግነው፣ ለተሻለ አፈፃፀም ከአመራሩ ጋር ተቀናጅተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር በየትምህርት ቤቶቹ ያሉ የፋሲሊቲ እጥረቶችን ማሟላት እና ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። ነገ ላይ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መጋቢ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን መደገፍ ነገን ዛሬ ላይ መስራት በመሆኑ፣ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ። መሠረተ ልማት ላይ መስራት ካልተቻለ የሚታሰበውን ብቁ ዜጋ መፍጠር ስለማይቻል፣ ትምህርት ቤቶቹ ያሉበትን ቁመና ማዬታችን ቀጣይ የምንሰራቸውን የቤት ስራዎች እንድንለይ ይረዳናል ብለዋል። ከምልከታው መልስ የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቶቹ የቅድመ ሁኔታ ግምገማን በተመለከተ የተዋቀረው ኮሚቴ፣ የጥናት ውጤቱን ለፕሬዝዳንቱና ለከፍተኛ አመራሩ አቅርቧል። የሰው ኃይል እጥረት እንዲሁም የአይሲቲ መሠረተ ልማት ጉድለቶች እና ሌሎች እንቅፋቶች ቢኖሩም፣ የመምህራን ትምህርት ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች አንዱ መሆኑ፣ በቂ የሰው ኃይልና ቤተሙከራዎች መኖራቸው፣ ትምህርት ቤቱን ለመደገፍ ትልቅ አቅም እንደሚሆን በሪፖርቱ ተመላክቷል። ለትምህርት ቤቶቹ የፋይናንስ ድጋፍ ቢደረግ፣ ለመምህራኖቹ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ቢደረግ፣ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ቢመለሱ አሁን ካለበት የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ ትምህርት ቤቶቹ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ግብዓቶች በቅርበት በመከታተል ተወዳዳሪ ዜጋ የሚፈልቅባቸው ሞዴል ትምህርት ቤቶች እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና የመሠረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፣ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ትምህርት ቤቶቹ ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ፣ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ===###=== #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland0,38%
- 14 авг.በዲላ ዩኒቨርሲቲ 11 ፕሮግራሞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው። ከየትምህርት ክፍሎቹ የተውጣጡ መምህራን ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) በስልጠናው ቦታ በመገኘት ሂደቱን የተመለከቱ ሲሆን፣ መምህራኖቹ ጠንክረው እንዲሰሩ በማበረታታት ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠውላቸዋል። #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ!0,36%
- 21:17Programs offered at Dilla University0,21%
- 17 авг.без подписи0,20%
- 14 авг.без подписи0,12%
- 14 авг.#CALL_FOR_EXTERNAL_REVIEWERS Dilla University cordially invites qualified professionals- university professors and industry experts to participate in an outcome based Educations (OBE) curriculum reviewer validation workshop scheduled for Aug 27, 2026GC. See the poster for more information! #UniversityOfTheGreenland!0,08%
- 17 авг.без подписи0,00%
- 17 авг.без подписи0,00%