EBSTV NEWS
СтатистикаWelcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends. https://t.me/ebstvworldwide Inbox - @EbswhatsnewBot
- Последний пост
- 13:44
- Последнее чтение
- 14:35
- Постов за неделю
- 99
- Всего постов
- 4 880
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 364
- 1/48двое суток
- 417
- 1/72трое суток
- 449
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎችን የማደራጀቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በትናንትናው እለት ደግሞ 120 አባላት ካሉት ቡድን የተመረጡ 34 አባላት በስምንት ንኡስ ቡድኖች ተከፋፍለው የእያንዳንዱን የአጀንዳ ሃሳቦችን በጥልቀት ሲመረምሩ መዋላቸውን ገልጿል፡፡ አባላቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ስር በተደጋጋሚ የተነሱ ሃሳቦች እንዳይኖሩ የመለየት፣ ያለ ምድባቸው የተነሱ ሃሳቦችን ወደሚመለከታቸው የአጀንዳ ምድብ የመመለስ እንዲሁም የማጥራትና የማጣጣም ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ይህ ስራ የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ምክረሃሳቦችን ወጥ በሆነና ጥራት ባለው መልኩ ለማደራጀት የሚያግዝ መሆኑን ገልፆ ሂደቱ እስከ ዛሬም የሚቀጥል ይሆናል ብሏል። ስምንቱ ባለ 500 አባላት ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥም እና እንዲያደራጅ ለተቋቋመው እና 120 አባላት ላሉት ቡድን ከአንድ ቀን በፊት ማቅረባቸውን ይታወሳል፡፡መረጃው ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተገኘ ነው። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዩብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት እና በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን አስመረቁ። ከንቲባው ይሄን ያሉት የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በቱሉ ጉዶ፣ ለገዳዲ ክፍል 2፣ በረከት የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳና ሌሎችም በርካታ ጉድጓዶችን መልማታቸውን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ነው። ከንቲባዋ በመዲናዋ ከአምስት ዓመት በፊት የነበረው 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ዛሬ ላይ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ደርሷል ብለዋል፡፡ ከንቲባዋ በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅም የዛሬውን ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡ ከንቲባዋ ፕሮጀክቶቹ የመዲናዋ ነዋሪዎች ጤናና ንጽህና የሚጠብቁ፣ የወንዞችን ብክለት የሚቀንሱ እና የአካባቢ ጥበቃን የሚያጠናክሩ ናቸው ብለዋል። ከንቲባዋ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የብድር አገልግሎት እየሰጠ ላለው የዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የውሃው መገኛ አካባቢዎችን በትብብር እንድናለማ ላገዘው የኦሮሚያ ክልል እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች ፦ ✅ሩሲያ ምሽቱን በዩክሬን ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት 5 ሰዎች ተገደሉ። ✅ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በይፋ ጦርነትን የሚቋጭ ንግግር እንዲደረግ ጠየቀች። ✅ሞሮኮ የስፔን ግዛት ወደሆነችው ሴውታ ሊሻገሩ የነበሩ በርካታ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተነገረ። ✅በኢንዶኔዥያ ትናንት በተከሰተው ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 51 መድረሱ ተነገረ። ✅ኳታር 3 የኢራን አብራሪዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች በሚል በቴህራን የቀረበባትን ውንጀላ አስተባበለች። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች ፦ ✅በኢንዶኔዥያ 7 ነጥብ 7 ማግኒቲዩድ ሆኖ በተመዘገበ ርዕደ መሬት በትንሹ 38 ሰዎች ሞቱ። ✅በደቡብ ምእራብ ፈረንሳይ የተከሰተውን የሰደድ እሳት ተከትሎ ከ500 በላይ ሰዎች ከቀያቸው እንዲለቁ ተደረገ። ✅እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በፈፀመችው ጥቃት 7 ሰዎች ተገደሉ። ✅የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥ በቅርቡ የሀገራቸው ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ። ✅ሁቲ በየመን መንግስት ቁጥጥር ስር ባለው የአልማካ ወደብ ላይ በፈፀመው የሚሳኤል ጥቃት 4 ሰዎች ተገደሉ። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
https://youtu.be/YQCAd5n85Ic
https://youtu.be/N0m98qyW4ag
https://youtu.be/OV9Epav1VMo
https://youtu.be/EfSY52lcwHw
ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ነሀሴ 8 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦ 🟢ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ በገንዘብ ሊገመቱ ለማይችሉ በርካታ ጫናዎች ተጋላጭ መሆኗን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ ገለጹ። 🟢የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ፣ ማላዊ እና ናይጄሪያ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ያወጣው ወጪ እንዲከፈለው ጠየቀ። 🟢በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እና በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ትብብር የሚተገበረው ብቁ ወጣት ፕሮግራም በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶች የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ ላይ ይገኛል ተባለ፡፡ 🟢የአማራ ክልልመጪው የትምህርት ዘመን ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ለመመዝገብ ማቀዱን አስታወቀ ፡፡ #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉ የትምህርት እርከኖች ከ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስመዝገብ መታቀዱን አስታውቋል። ቢሮው በሰጠው መግለጫ በተጠናቀቀው የ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታቸው ላይ የተገኙ ተማሪዎች ቁጥር ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ እንደነበረም ጠቅሷል። ክልሉ ለመጪው የትምህርት ዘመን ከነሐሴ 18 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአዲስና የነባር ተማሪዎች ምዝገ ማካሄድ እንደሚጀመርም አሳውቋል። ክልሉ በ2018 የትምህርት ዘመን 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመዝገብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም በክልሉ ባሉ የፀጥታና መሰል ችግሮች የተነሳ ከ2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ እንደሆኑ ከዚህ ቀደም መነገሩ አይዘነጋም። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ፣ ማላዊ እና ናይጄሪያ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ያወጣው ወጪ እንዲከፈለው ጠየቀ። ሀገሪቱ 75 ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ወደ ሀገራቸው በላከበት ወቅት ወደ 300 ሚሊዮን ራንድ ገደማ ወጪ ማድረጓን ያነሱት የደቡብ አፍሪካ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ይህን ወጪ ሀገራት እንዲጋሩ ጠይቀዋል፡፡ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ እንደገና በተቀሰቀሰው የስደተኞች ተቃውሞ ምክንያት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሀገሪቱ መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ጥያቄ ላይ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች ፦ ✅አረብ ኢምሬትስ በሆርሙዝ ሰርጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት መርከቦቿ ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀች። ✅ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ ሊያካሂዱት ያለውን የተቀናጀ ወታደራዊ ልምምድ አወገዘች። ✅94 በመቶ የኩባ ዜጐች በድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ አንድ ጥናት አመለከተ። ✅የመንግስታቱ ድርጅት በገንዘብ እጥረት ምክንያት በደቡብ ሱዳን ተጠልለው ያሉ 650 ሺ ስደተኞች የምግብ ድጋፍ ሊቋረጥባቸው እንደሚችል አስጠነቀቀ። ✅በዛምቢያ ከተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በአንድ የምርጫ ጣቢያ በተከሰተ ጥቃት ሳቢያ የድምፅ ቆጠራ ሂደቱ ቆመ። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን የባህር ኃይል እገዳ ላልተወሰነ ጊዜ እንደምትቀጥል እና በቴህራን ላይ የምታደርገውን የኢኮኖሚ ጫና የበለጠ እንደምታጠናክር አስታወቀች። የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት የአሜሪካ ጦር በክልሉ የባህር ኃይል መርከቦችን በማሰማራት በኢራን ላይ የተጣለውን እገዳ ለረጅም ጊዜ ማስፈጸም የሚያስችለው አቅም እንዳለው ተናግረዋል። የእገዳው ዋና ዓላማ በኢራን ላይ የኢኮኖሚ ጫናን ማሳደግ ሲሆን፣ ይህም በአሜሪካና በኢራን መካከል የተካሄዱ የተኩስ አቁም ድርድሮች ውጤት ሳያመጡ በመቅረታቸው እንደሆነም ተገልጿል የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት በበኩላቸው በቅርቡ በኢራን ላይ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማዕቀቦች እንደሚጣሉ ጠቁመዋል። በተመሳሳይ ጊዜ በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ የሚደረገው የመርከቦች እንቅስቃሴ በአሜሪካና በኢራን መካከል ባለው ውጥረት ምክንያት የቀነሰ ሲሆን ይህም በዓለም የነዳጅ አቅርቦት ላይ ስጋት ይፈጥራል ነዉ የተባለዉ ። በኬና ደሬሳ #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የአሜሪካ መንግሥት ከ40 በላይ አገራት የቻይና ምርቶች በሌሎች አገራት በኩል ወደ አሜሪካ እንዲገቡና ከፍተኛ ታሪፍ እንዳይከፍሉ እያገዙ ነው ሲል ከሰሰ። በዋይት ሐውስ ሪፖርት መሠረት፣ የቻይና ምርቶች ከፍተኛ ታሪፍ ከሚጣልባቸው አገራት በሌሎች ዝቅተኛ ታሪፍ ባላቸው አገራት በኩል ወደ አሜሪካ እንዲገቡ እየተደረገ ነው ብሏል ። በዚህ ሂደት ከ30 ቢሊዮን እስከ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ምርቶች በተለያዩ አገራት በኩል ተላልፈዋል ነው የተባለው። የአሜሪካ የንግድ አማካሪ ፒተር ናቫሮ ከ40 በላይ አገራት በዚህ ሂደት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸው ፤ከተጠቀሱት አገራት መካከል ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ጃፓን፣ ህንድ እና የአውሮፓ አገራት ይገኙበታል ። አሜሪካ የቻይና ምርቶች በሌሎች አገራት በኩል በማለፍ ከታሪፍ እንዳያመልጡ ለመከታተል የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎችንም መጠቀም ጀምሬያለሁ ብላለች። በበኩሉ የቻይና ኤምባሲ የንግድ ጦርነቶች አሸናፊ እንደሌላቸው ገልጾ፣ የአሜሪካን የታሪፍ እርምጃዎች እንደሚቃወም አስታውቋል። ምንጭ BBC News በቤዛዊት መኮንን #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ተከሷል ተብሎ የ20 ዓመት እስራት የተፈረደበት ያን ቬዚሊየ በፕሬዚዳንታዊ ይቅርታ ከእስር እንዲፈታ ተደርጓል። ያን ቬዚሊየ ከአንድ ዓመት በፊት ከበርካታ የሠራዊት ጄኔራሎች እና በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮች ጋር በመተባበር የፕሬዚዳንት አሲሚ ጎይታን መንግሥት “በፈረንሳይ የስለላ አገልግሎት ድጋፍ” ለማዳከም ሞክሯል ተብሎ ተከሶ ነበረ። የማሊ መንግሥት ይቅርታው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የማይሽር መሆኑን ገልጾ ግለሰቡ ወዲያውኑ ከአገሪቱ እንዲወጣ መደረጉን አስታውቋል። ፈረንሳይ በበኩሏ ቬዚሊየ የፈረንሳይ ሰላይ ነበር የሚለውን ክስ ከዚህ በፊት “መሠረተ ቢስ” በማለት አስተባብላለች።https://www.theguardian.com/world/2026/aug/13/south-korea-incheon-airport-iran-war-middle-east በአቢስ ስዩም #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
የደቡብ ኮሪያው ኢንቼዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በ2026 የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት በዓለም አቀፍ የተሳፋሪ ብዛት ቀዳሚ አየር ማረፊያ ሆኗል። በአየር ማረፊያዎች ምክር ቤት ኤሲአይ ቅድመ መረጃ መሠረት፣ ኢንቼዮን 38.4 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተሳፋሪዎችን ሲያስተናግድ፣ የለንደን ሄትሮው 37.79 ሚሊዮን እና የሲንጋፖር ቻንጊ 34.53 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን በማስተናገድ ተከትለዋል። ይህ ለኢንቼዮን የመጀመሪያው የዓለም ቀዳሚነት ሲሆን፣ በ2024 እና 2025 የዓለም ቀዳሚ የነበረው ዱባይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ነበር። የኢንቼዮን ወደ ቀዳሚነት መምጣቱ በከፊል በአሜሪካና ኢራን መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከመካከለኛው ምሥራቅ የአየር ትራንዚት ማዕከላት የተዛወሩ ተሳፋሪዎች ቁጥር መጨመሩ ነው። የትራንዚት ተሳፋሪዎች ቁጥርም ከባለፈው ዓመት በ18 በመቶ ጨምሯል። ኢንቼዮን ከ158 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር የሚያገናኝ ሲሆን፣ የአየር ማረፊያው ኮርፖሬሽን በተሳፋሪዎች ምቾት ላይ በማተኮር ተወዳዳሪነቱን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠራ ገልጿል። በሲፈን ቀልቤሣ #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
Live stream finished (14 minutes)
Live stream started
የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ነሀሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች ፦ 🟢የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ8 የአጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲመካከሩ የቆዩት የአጀንዳ ቡድኖች መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታወቀ። 🟢በተያያዘ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ መሆኑን አስታወቀ። 🟢የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ 11 የሙያ ዘርፎች በመደበኛ ሥርዓተ ትምህርት ተካተው ሊሰጡ መሆኑን አስታወቀ። 🟢የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማኅበር አንድ ኪሎ ግራም የኢትዮጵያ ቡና በ2,275 ዶላር መሸጡን ይፋ አደረገ። 🟢ግብርና ሚኒስቴር በዘንድሮ የመኸር ወቅት ከ729 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል አለ። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቱርክ የግድያ ሙከራ ተወጥኖባቸው ነበር የሚለው መረጃ ላይ እምነት እንደሌለው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት አስታወቀ። ሲአይኤን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የግድያ ሙከራው መረጃ ከእስራኤል መረጃ ድርጅት የመጣና የአሜሪካ ደህንነት ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያለመ ነው። የመረጃው እውነተኛነት ላይ ጥርጣሬ ቢኖርም የፕሬዝዳንቱ ጠባቂዎች መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ወስደዋል። ትራምፕ ከቱርኩ ስጋት በኋላ አውሮፕላን እየቀያየሩ ወደ አገራቸው መመለሳቸው የተዘገበው ባለፈው ሰኞ ነበር። #EBS #EBSTVNEWS #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv