tgindex
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስለ እመቤታችን

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስለ እመቤታችን

Статистика

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
777
+3 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,13%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
242
21 постов
Вовлечённость
31,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
146
1/48двое суток
167
1/72трое суток
180

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 👉 የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ 🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

  • 👉 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ 🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

  • 👉 የእሁድ ውዳሴ ማርያም አንድምታ 🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

  • 👉 የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ 🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

  • ✟✟✟ፆሙን ለሀገራችን የሰላም የፍቅር፤ ለእኛም የበረከት ፆም ይሁንልን። አሜን!✟✟✟ Join 👉 https://t.me/emebete01

  • видео или голосовое, без подписи

  • 👉 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ 🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! #ሼር #share https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ

  • 🍀🍀🍀ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/🌿🌿🌿 ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ተሰደደ፤ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡ ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤  እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ - እንኳን አደረሰን። - የጾሙና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤አሜን

  • 🌾🌾🌾አንቺን አገኘሁ!🌾🌾🌾 - "ከሰይፍ ስለት ከጦር ሐፎት ከፀብ ክርክርም ሁሉ  ከፀብም መሣሪያ ሁሉ መሸሻ አንቺን አገኘሁ። ከጠላቶቼም እጅ መሸሻ ሰውነቴንም ከሚጠሏት ሁሉ እጅ መሸሻ አንቺን አገኘሁ። በስምሽ ያመነውን ማን ያስፈራዋል? በልጅሽስ ያመነውን ማን ያስፈራዋል? ያንበሳ ጩኸት እንደውሻ ጩኸት ይመስለዋል። የነብሮቹም ኃይል እንደ ድመት ድካም ነው።"         [ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ!]

  • የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን። ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› መዝ. ፻፴ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት ሁነኝ›› አለችው፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ከዘመናቸው ሳይደርስ፣ ታሪካቸውን ሳይማር የሠለስቱ ደቂቅን ታሪክ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ‹‹አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል›› ቢላት ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?›› ብሎ በጸለየጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት፡፡ ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባችበት፡፡ በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ያለውን ቃል ለመፈጻም እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፡፡ በመልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ፡፡ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠሩራቸው አንድም ሳይጎዳቸው በደህና ወጡ፡፡ በመጨረሻም ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ፡፡ ይህን ያህል ገድል ተጋድዬ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው፣ ጌታ በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ዳግመኛም ሥጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው፡፡ ስለሆነም በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእናታችን ለቅድስት ኢየሉጣ እና ለሕፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ ያደረገውን ይህን ታላቅ ተአምር ድንቅ ሥራ በማሰብ ከዋዜማው ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች፡፡ --- የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር። ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን! አሜን፡፡

  • 🌿🌿🌿​​ቅዱስ ገብርኤል!🌿🌿🌿 - እንኳን ለታላቁ መልአክ 'ለቅዱስ ገብርኤል' ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!! - በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፦ በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡ ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡ መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡ መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡ እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡ ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡ አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡ እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡ ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡ ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡ አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል።

  • 🌿🌿🌿ኪዳነ ምህረት!🍀🍀🍀 - "ድንግል ሆይ፤ አንቺ የአብ ተክል የሆንሽ ሁለተኛይቱ ኤደን ነሽ። በመጀመሪያይቱ ኤደን አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት ሞትን በላ፤ በአንቺ ግን የሕይወት ፍሬ ክርስቶስ ለዓለም ተገለጠ።" [ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ!] - "የጌታ እናት ሆይ! አንቺ የይስሐቅ የበግ ጠቦት የተገኘብሽ ዕፀ ሳቤቅ ነሽ፤ ዓለምን ሁሉ ከሚበላው ከኃጢአት እሳት ልጆችሽን ያዳንሽ።........እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ሲፈጥር በነጻነት ፈጠራቸው፤ ሰው ለመሆን ግን የማርያምን ፈቃድ ፈለገ፤ እርሷም 'እንደ ቃልህ ይሁንልኝ' ባለች ጊዜ ዓለም ድኅነትን አገኘች።" [ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ!] . . . እንኳን አደረሰን።

  • 🌿🌿🌿ቅድስት ሥላሴ!🌿🌿🌿 ------------------- "ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር - ሥላሴ ድንቅ፣ ግሩም፣ ልዑል ናት ትደነቃለች።" ቅዱ ያሬድ - ቅድስት ሥላሴ በአካል ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ አንድ ናቸው። ባህርይ ማለት፡- ያልተፈጠረ፣ የማይመረመር ፣ የማይታወቅ፣ ኅቡዕ፣ ረቂቅ፣ ቅድስት ሥላሴን አንድ የሚያደርግ፣የፈጣሪ ባሕርይ፣ አምላክነት፣ ማድረጊያ፣ ኋኝ ማለት ነው። ደስ.ገጽ.፻፷፮ - በባሕርይ አንድነት፦የሥላሴ መለኮትነት፣ጌትነት፣ክቡርነት፣ንጹሕነት፣ልዑልነት፣ጽኑዕነት፣ፈቃድ፣ሥምረት፣..ይነገርበታል። - በሁሉም ሲነገር ባሕርይ የነገር ሁሉ ስር መሰረት ምንጭ ማውጫ መፍለቂያ መገኛ ጠባይዕ ክዋኔ፣ኋኝ፣ ማለት ነው፡፡ - ባሕር ለታውጽእ ተብላ ብዙ ስነ ፍጥረትን እንዳስገኘች ባሕርይም መገኛ ማስገኛ ስለሆነ የአካል የስም የህላዌ ጥንት የስራ ምንጭ የግብር መሰረት ይባላል ኪዳ ወል ገጽ.፪፻፷፫ - "ባሕርይ ማለት የአካል መገኛ ስር አካል ስራውን የሚሰራበት መሰሪያ ነው።"መድ.አሚ.ገጽ.፪፻፵፯ ባሕርይ ኋኝነትን የምንገልጽበት ምሥጢር ነው። - ቅድስት ሥላሴ በአንዲት ባሕርይ አንድ ናቸው። - ወይም በኩነት ግብር በሚነገር ተዋሕዶ ሥላሴ አንድ ናቸው። - በአንዲት የባሕርይ ግብራቸው ፈጽሞ መለያየት የለባቸውም። - [ምንጭ፦ ምሥራቀ ፀሐይ ጉባዔ ቤት!] እንኳን አደረሰን።

  • "ሩጫየን ጨርሻለሁ..." ይህ ቃል ለሁሉም ሙታን የሚጠቀስ አልነበረም። - ዕድሜውን የጨረሰ ሁሉ፥ ሩጫውን የጨረሰ አይደለምና። መንፈሳዊውን ሩጫ እንኳን ሊጨርስ ያልጀመረ ሟች መቃብር ላይ 'ዕድሜየን ጨርሻለሁ' ተብሎ ቢጻፍ ሸጋ ነበር። በዛሬው ዕለት የሚታሰቡት እነቅዱስ ጳውሎስና ጴጥሮስ ግን ሲኖሩ ሩጫቸውን፥ ሲሞቱ ዕድሜአቸውን ጨርሰዋልና ይደልዎሙ ብፅዓን። በክርስትና መም ላይ ሩጫ አለ። በሩጫ ላይ ድካም አለ። በድካም ላይ የክብር አክሊል አለ። ጌታየ ደክሞልኛል ብለህ ከዚህ ሩጫ ራስህን ካገለልክ የክብር አክሊል የለህም። [በዬኔታ ሥሙር አላምረው!] - እንኳን አደረሰን።

  • የመንፈስ ቅዱስ ዋሽንት የተባለው ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ዮሐንስ በዕለተ ዓርብ መስቀል ሥር መቆሙንና እመቤታችንን በአደራ መቀበሉን ሲያደንቅ እንዲህ ይላል፦  "ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ ድንግሏን እናቱን ለድንግሉ ደቀ መዝሙር (ለዮሐንስ) አደራ ሰጠ። ንጹሕ ለንጹሕ፣ ድንግል ለድንግል ተሰጠ።" - "ሌሎቹ ወንጌላውያን (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ) የክርስቶስን ከምድር መነሣት (የሰውነቱን ነገር) በስፋት ሲጽፉ፣ ዮሐንስ ግን እንደ ንስር ወደ ሰማይ በመጥቀስ ከመለኮት ባሕርይ ጀመረ።" [ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ!]

  • ☘☘☘ ወላዲተ አምላክ! 🍀🍀🍀 - "ማርያምን 'ወላዲተ አምላክ' (የእግዚአብሔር እናት) ብሎ የማይጠራ ሰው ከክርስቲያኖች ወገን አይደለም። እርሷ በሥጋ የወለደችው በተዋሕዶ ፍጹም አምላክ የሆነውን ቃል ነው። እርሷን ማመስገን ልጇን ማመስገን ነው፤ ለእርሷ ክብር መስጠት ለአምላክ ክብር መስጠት ነው። ምክንያቱም እርሷ የአምላክ ማደሪያ ቅድስተ ቅዱሳን ናትና።" [ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ!] - "በሴቶች መካከል እንደ ማርያም ያለች ቅድስት፣ ንጽሕትና ፍጽምት አልነበረችም፣ የለምም፣ ወደፊትም አይኖርም።" [ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ!]

  • "የሰሎሞን መቅደስ በወርቅና በዕንቁ ቢያጌጥም፣ በውስጡ ካረፈችው ከዚች ሕፃን ንጽሕና ጋር ሊወዳደር አይችልም። እርሷ መቅደሱን ቀደሰችው እንጂ መቅደሱ እርሷን አልቀደሳትም፤ ምክንያቱም የሰማይና የምድር ፈጣሪ በእርሷ ውስጥ ሊያድር ወዷልና።" [ቅዱስ ያዕቆብ ዘሶርያ!] - "ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።" አባቷ ቅዱስ ዳዊት(መዝ 44፥10) - እንኳን አደረሰን።

  • "ማርያም ሆይ! በአንቺ አማላጅነት አሕዛብ ሁሉ ወደ እውነተኛው እውቀት መጡ፤ የሰይጣን ስሕተትም ጠፋ።" ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ! እንኳን አደረሰን።

  • ++ ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 21! ++ - በመጽሐፈ ስንክሳር እንደ ተመዘገበልን ሰኔ ፳ (20) ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ ሀገር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውሃ በሦስት ድንጋዮች በተወደደ ልጇ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የታነጸበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ከሚከብሩ ከእመቤታችን 33 በዓላት አንደኛው ነው፡፡ ጌታችን በዐረገ በስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ወደዱ፡፡ በዚህ ጊዜ ርዕሰ ሐዋርያት እያለ እኛ መሥራት አይገባንም ብለው ለሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ እርሱም ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር መጥቶ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፡፡ በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶ ቅዱሳን ሐዋርያትን በፊልጵስዩስ አገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሠራዉን የአብያተ ክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቤአችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡ በዚያ ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፤ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰም እሳት ሲያገኘው እንዲለመልም፣ ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳበላቸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመዉታል፡፡ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራዉም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው፤ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲኾን፣ በ፳፩ኛው ቀን (በማግሥቱ) ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ከእመቤታችን 33 ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸችው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። - እንኳን አደረሰን።

  • "ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ፡፡" - አባ ሕርያቆስ ዘብህንሳ!