Dire Dawa Administration Education Bureau General Education Quality Assurance Directorate
Статистикаይህ ቻናል የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳሬክቶሬት የቴሌግራም ቻናል ነው።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 22
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 350
- 1/48двое суток
- 401
- 1/72трое суток
- 432
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ማስታወቂያ ለመላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች በሙሉ! “ትምህርት የብሩህ ተስፋና የተሻለ ነገ መሠረት ነው!” የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2019 የትምህርት ዘመን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን፣ ታዳጊዎችን፣ ወጣቶችን፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች እንዲሁም ጎልማሶችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት ሰፊ ዝግጅት አድርጓል። በመሆኑም ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆቻችሁን በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የትምህርት ተቋማት በመውሰድና በማስመዝገብ የወላጅነትና የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። አስፈላጊ ሰነዶች የምዝገባ ሂደቱን የተቀላጠፈ ለማድረግና የተማሪዎችን መረጃ በዘመናዊ መልኩ ለማደራጀት፣ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች በምዝገባ ወቅት የሚከተሉትን ሦስት (3) መረጃዎች መያዝ ግዴታ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፦ - የልደት የምስክር ወረቀት - የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (Fayda ID) - የኤሚስ (EMIS) የተማሪዎች መለያ ቁጥር ልብ ይበሉ፦ እነዚህ የተጠቀሱት ሰነዶች ሳይሟሉ ምዝገባ ማከናወን ፈጽሞ የማይቻል በመሆኑ ወላጆች ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ቀድማችሁ እንድታዘጋጁ እናሳስባለን። ትጋት ለትምህርት ጥራት! የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
видео или голосовое, без подписи
የ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ውስጥ አንዱ የሆነውን የማጠናከሪያ ትምህርት አገልግሎት ያገኙ ተማሪዎች በጃን ት/ቤት። 👇👇👇 Telegram https://t.me/eqadirectoret Facebook https://www.facebook.com/ddebgeqad
ማስታወቂያ ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለመንግስት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል የስራና ተግባር ትምህርት በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር የተላከውን ቼክሊስት ሞልታችሁ እስከ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም እንድታስገቡ ቀደም ሲል በደብዳቤ ተገልጾላችሁ ነበር። ይሁን እንጂ እስከ አሁን ድረስ መረጃውን ያላቀረባችሁ ትምህርት ቤቶች ዝርዝራችሁ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ሲሆን እስከ ረቡዕ ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም ድረስ ለቢሮው ገቢ እንድታደርጉ ለመጨረሻ ጊዜ እናሳስባለን። በተጨማሪ እስካሁን የምረቃ ስነ-ስርዓት ያላከናወናችሁ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮግራሙን አከናውናችሁ ቀኑን ለቢሮው እንድታሳውቁ እናሳስባለን። ሪፖርት ያላቀረቡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች፦ 1. ዋሄል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 2. ጀልዴሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 3. አዲሱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 4. መልካጀብዱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 5. ማሪያምሰፈር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 6. አፈቴሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሪፖርት ያላቀረቡ መንግስታዊ ያልሆኑ (የግል) ትምህርት ቤቶች፦ 7. ቢላል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 8. መሀድልኑር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 9. ቅድስት ተሬዛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 10. ድሬ ቤተል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማሳሰቢያ፦ ይህን መመሪያ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተግባራዊ የማያደርጉ ትምህርት ቤቶች፣ ለሚፈጠረው ማንኛውም መስተጓጎል ትምህርት ቤቱ እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በቀጥታ ተጠያቂ የሚሆኑ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
"ውድ የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል። የ5 ሚሊየን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ የሚገኙ ሲሆን ፥ የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ነው። 5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል፣ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ማሳሰቢያ በድሬዳዋ አስተዳደር ለምትገኙ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን አዴሌ ከተማ የሚገኘው ኢፋ ቦሩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያመጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ተማሪዎችን አወዳድሮ መመዝገብ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በድሬዳዋ አስተዳደር የምትገኙ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ በየ ትምህርት ቤታችሁ መማር የሚፈልጉና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን አወዳድራችሁ እስከ ሰኞ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም ድረስ ዝርዝራቸውን ለቢሯችን ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን። የመወዳደሪያ መስፈርቶች 1. የ2018 ዓ.ም 8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለወንድ 83%፣ ለሴት 80% ያላቸው 2. የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ( ለወንድ 85%፣ ለሴት 75% ያላቸው 3. የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርት አማካይ ውጤት ለወንድ 75%፣ ለሴት 70% ያላቸው ለአካል ጉዳተኞች 1. 8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለወንድ 80%፣ ለሴት 77% ያላቸው 2. የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለወንድ 85%፣ ለሴት 75% ያላቸው 3. የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርት አማካይ ውጤት ለወንድ 75%፣ ለሴት 70% ያላቸው የማለፊያ ነጥብ ❖ 80% የፅሁፍ ፈተና ❖ 15% የ8ኛ ክፍል ውጤት ❖ 5 % የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት መሆኑን እንገልፃለን። የፈተና ቀን፦ ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም ፈተናው በኢንተርኔት (online) ይሰጣል። ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከል ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ አለባቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
видео или голосовое, без подписи
ቅድስት ተሬዛ ቁ.1 ት/ቤት
ማያ ት/ቤት
видео или голосовое, без подписи
ራሄል ት/ቤት
አቡነ እንድሪያስ ት/ቤት
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ብስራተ ገብርኤል ት/ቤት
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи