tgindex
ኢስላም

የተለየዩ አስተማሪ ታሪኮች ፣ወርቃማ ምክሮች የስኬታማ ሰዎች ልምድ፣ የተለያዩ መጣጥፎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው ‼️ ☞https://t.me/eross_eross ▮Share and Join

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
23
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 793
−8 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
110
30 постов
Вовлечённость
3,9%
к подписчикам
Постов в день
3,3
всего 30
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
106
1/48двое суток
121
1/72трое суток
131

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ጉድ ለት ይሰማህ ነፍስህን ከፍ ከፍ አታድርግ!

  • ስለ ቀልባችን ክፍል 4 ¸ 2 ቀልቡን ሙኒብ ፦ ወደ አሏህ ተመላሸ የሆነች ቀልብ ናት ይህች ቀልብ ጥፋትን ታጠፋለች ወንጅልንም ትፈጽማለች ነገር ግን ወዲያውኑ ወደ ጌታዋ ትመለሳለች ። አሏህ እንዲህ ይለናል ፦ <<አር_ረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራና ÷በንጹሕ ልብ ለመጣ >>(ትቅቀረባለች)። (ቃፍ፡33) ይህች ቀልብ ጌታዋን ማመጿን ተረድታ ወዲያውኑ ወደርሱ በመመለስ ለጌታዋ ያላትን ፍራቻ ታውጃለች ። ይቀጥላል ከልቤን ፍለጋ መፃፍ የተወሰድ በኡስታዝ አለሏህ መህዲ የተፃፈ ለበለጠ መረጃ መፃፉኑ ግዝታችሁ ብታነቡት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ አሏህ ልባችን ያጥራል ያረብ መልካም ምሸት ይሁንላችሁ https://t.me/eross_eross

  • 🌹ጁምዓ 🌹 ~~~~ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ .ወሰለም )እንዲህ ብለዋል ፡- አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡ ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም 🍃1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣ 🍃2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣ 🍃3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣ 🍃4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣ 🍃5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል። በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል። በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ። የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦ የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።🌱 {አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:910) [የጁመአ ቀን ሱናወች] ~‌ ~ገላን መታጠብ ~ ጥሩ ልብስ መልበስ ~ሽቶ መቀባት ለወንዶች ~ ሲዋክ ~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ ~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ። اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥👉🏿@eross_eross Add ያድርጉ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~ 𝐠𝐫up👉🏿@tewhiddd

  • ↬የጨነቀህን የውስጥህን አውጥተህ ለኔ ምትላቸው ሰዎች ታጋራቸው ይሆን ይሆናል ↬የውስጥህ የማዘን …የህመም ስሜት ልክ ግን ያለ አላህ ማንም ሊያውቅልህም ሊያነሳልህ የሚችል የለም:: @eross_eross

  • видео или голосовое, без подписи

  • የዱንያ ከዋክብቶች የሰፈሩበት ቦታ 🫆ይህ መቅበራ ከሌሎች የኢስላም መቅበራዎች ምን ለየት ያረገዋል?🫆 👉ይህ መቅበራ ላይ ከ 10 ሺ በላይ ሶሀባዎች ይገኛሉ 👉ይህ መቅበራ አብዛኞቹ የነብያችን ባለቤቶች ይገኛሉ 👉ይህ መቅበራ ኡስማን ኢብኑ አፋን ዙኑረይን ይገኝበታል 👉ይህ መቅበራ ልጃቸው ፋጢማና ኢብራሒም ሰፍረውበታል 👉ይህ መቅበራ ሀሰን ኢብኑ አልይ እዲሁም ሙሀመድ አልባቂር ጃእፈር አሳዲቅ ይገኙበታል ይህ ሁሉ የምድር ከዋክብት ብረቅዬዎቹ ትውልዶች ተቀብረውበት ሳለ አንድም ከፍ ተደርጎ የሚሰራ ቀብር የለም አንድም ቁባ ተደርጎ የተሰራ ቀብር የለም አንድም የሚሰገድለት ቀብር የለም አንድም በተለየ ሁኔታ በጊዜ ገደብ የሚዘየር ቀብር የለም ዛሬ ላይ በየ ቦታው አብሬትን ጨምሮ በአለሙ አፅናፍ የሚደረጉ የቀብር ላይ ስሕተቶች ሺርኪያቶች ከየትኛውም የዲን አንግል መረጃ የሌላቸው ናቸው አላህ ኡማውን ከዚህ ጨለማ ነፃ ያድርግልን https://t.me/eross_eross

  • ቁርዓን 🥀

  • ይህ ኢስላም ቻናላችን ሼር ሼር ሼር አድርጉት በእናንተ ምክንያት አንድ ጓደኛችሁ ቢለወጥ ለእናንተም ለዉጥ ነው ኸይር ነው አጅር አለው ሼር ስታደርጉ በኢህላሰ ይሁን አጅር ልታገኙበት ሰዎች ሊቀይሩብት ይሁን ጀዛኩም አሏህ ኸይር አሏህ ይጠብቃችሁ 👇👇👇👇join https://t.me/eross_eross እንዲሁም በቻናላችን ላይ ይቀነሰ ይጨምር የምትሉት ነገር ካለ የተለያየ ተሰጦ ያላችሁና እንዲሁም በእዉቀታችሁ አብራችሁ መሰራት የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ አናግሩን አስተያየታችሁ ሰጡን 👇👇 @eross_63

  • ስለ ቀልባችን ክፍል ➌ 1.ቀልበን ሰሊም ፦ ንፁህ የሆነች ቀልብ ራሷን ለአሏህ ትዕዛዝ ያሣደረች ከአሏህ መንገድ ያልወጣች ፣ አሏህ ያላትን እንጂ የማትፈጽም ፣ የከለከላትን የማትዳፈርና ከሽርክ (በአሏህ ላይ ከማጋራት ) የተቆጠበች ከእሱ ሌላ የማትከጅል ፣ የማትለምን በአሏህ ላይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የሌላት ምርጥ ቀልብ ስትሆን ይህንን በማስመልከት አሏህ እንዲህ ይለናል ፦ ጌታዬ ሆይ! ሰዎች ከሞት በሚቀሰቀሱበት እለት አታዋርደኝ በዚያ ዕለት ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት ንፁህ ቀልብን ይዞ የመጣ ሰው ሲቀር ((አሽ _ሹአራእ፡87_89)) ሰለዚህ ነገ የቂያማ ዕለት ማንም ሰው ምንም ይዞ በማይሄድበት በዛ መራራ እና አስቸጋሪ እለት ለማንኛውም ሰው የሚጠቅመው ንጹህ ልብን ይዞ ከጌታው ጋር መገናኘት ብቻ መሆኑን ተገንዝበን ጉዟችንን ከንፁህ ቀልብ ጋር ልናደርግ ይገባናል ። https://t.me/eross_eross ይቀጥላል .....

  • 13 авг.13удалён 13 авг.

    አስተያየት እና ቻናል ከኔጋራ መስራት የምትፈልጉ @eross_63 በዚህ ሊንክ ተጭናችሁ አናግሩኝ

  • የእስፖንጅ ፍራሽ ላይ ሶላት መስገድን በተመለከተ አጠር ባለ መልኩ ልዩ ገለፃ በሼኽ አልባኒ (ረሂመሁሏህ) ____ ሼኽ አልባኒ እንዲህ አሉ ፦ ➩ የእስፖንጁ አይነት ጥቅጥቅ ያለ ደረቅና ጠንካራ ከሆነ ሱጁድ ስታደርግ ግምባርህን አረጋግቶ የሚያቆም ከሆነ ለምሳሌ "ልክ ሰጃዳ ላይ በምትሰግድ ጊዜ ሱጁድ ስታደርግ ግምባርህን አረጋግቶ እንደሚያቆምልህ" ልክ እንደዚያ አይነት ስፖንጅ ከሆነ እዚህ ስፖንጅ ፍራሽ ላይ ሶላት መስገድ ችግር የለውም ። ➩ ነገር ግን የስፖንጁ አይነት ስስ ከሆነ ለምሳሌ ሱጁድ በምታደርግ ጊዜ ግምባርህን አረጋግቶ የሚያቆም ካልሆነና ይዞህ የሚወርድ ከሆነ እሱ ላይ መስገድ አይቻልም ። ይህ ማለት "ልክ የፊቅህ ባለቤቶች እንደሚሉት ስንዴና ገብስ የመሳሰሉት ላይ መስገድ አይቻልም ምክኒያቱም ሰውየው ሱጁድ በሚወርድ ጊዜ ግምባሩን አረጋግተው ማቆም ስለማይችሉ" ብለዋል ። ስለዚህ ስስ የሆነ እስፖንጅም ላይ መስገድ ከዚህ አይነቱ ይመደባል። ምንጭ፦ ሙተፈሪቃት ፥ ካሴት (54) 👉@eross_eross

  • =>> ህይወትህን ተደሠትባት 〰 ክፍል አንድ〰 #አይጠቀሙም፦ በአንድ ወቅት ሞባይል ስልኬ ላይ አንድ የፅሁፍ መልእክት አገኘሁ። ውድ ሼህ ሆይ! ራስን ማጥፋት የሚያስከትለው ቅጣት ምንድን ነው?" ይላል። . . አንድ ወጣት ነው የላከው። ደወልኩለትና "ይቅርታ" ጥያቄህ አልገባኝም እባክህን ድገምልኝ?" አልኩት። እሱም "ጥያቄው" ግልፅ ነው። ራስን ማጥፋት የሚያስከትለው ቅጣት ምንድን ነው?" አለኝ በተሰበረ ድምፅ። እንግዳ የሆነ መልስ ሠጥቼ ላስደነግጠው ፈለኩና "ራስን ማጥፋት ይቻላል" አልኩት። ምን?" አለና ጮኸ። በተገቢው መንገድ ትፈፅመው ዘንድ ግን ለምን አንወያይበትም?" አልኩት ። መልስ አልሠጠኝም። "ለምን ራስህን ማጥፋት ፈለክ?" አልኩት ። ስራ ማግኘት አልቻልኩም። ሰዎች አይወዱኝም። በእርግጥ እኔ ያቀራረብ ችግር አለብኝ..." በማለት ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለትና ክህሎቱን መጠቀም እንዳልቻለ የሚጠቁም ረጅም ታሪክ ይዘረዝርልኝ ጀመር።ይህ የብዙ ሰዎች ችግር ነው። ለምንድን ነው ብዙዎቻችን የበታችነት ስሜት የሚሰማን? እነሱ ከደረሱበት መድረስ እንደማንችል በማሰብ ተራራ ጫፍ ላይ ያሉ ሰዎችን ለምን እንመለከታለን። ተራራ ለመውጣት ልቡ ያልደፈረ፣ ይቀራል ጉድጓድ ውስጥ እንደተቀበረ፣ => ከዚህ መፅሀፍ ወይም ከሌላ ተመሳሳይ መፅሐፍት ተጠቃሚ የማይሆነው ሰው ማን እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋላችሁ? ለስህተቶቹ እጅ የሰጠና በውስን ክህሎቱ የረካ እድለ ቢስ ሰው። ይህ ተፈጥሮዬ ነው። ይህን መቀየር አልችልም። እንደዚህ መሆኔን ሁሉም ሰው ያውቃል። እኔ እንዴ ኻሊድ ጥሩ ተናጋሪ መሆን አልችልም። ወይም እንደ አህመድ ተግባቢ መሆን አልችልም። እኔ እንደ ዚያድ ሰው ሁሉ ሊወደኝ አይችልም። ይህ ሊሆን አይችልም ። ያ ሊሆን አይችልም። በአንድ ወቅት ከአንድ አዛውንት ጋር ስብሰባ ላይ ተገናኘን። አብዛኞቹ ታዳሚያን ጥሩ ጥበብና ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው። ሽማግሌው ከጎናቸው ካለው ሰው ጋር በማውራት ተጠምደዋል። ስብሰባው ላይ የተጋበዙት የረጅም እድሜ ባለፀጋ በመሆናቸው ነው። ንግግር አደርግኩ። በንግግሬም የሼህይኽ አብዱል አዚዝ ቢን ባዝን ብይን ጠቅሼ ነበር። ጨርሼ ስቀመጥ ሽማግሌው በኩራት እኔና ኢብኑ ባዝ ጓደኛሞች ነበርን። ከአርባ አመት በፊት ከሼህ መሐመድ ኢብን ኢብራሂም ላይ አብረን ተምረናል" አሉ። =>ይህን መረጃ ለኔ መንገር እንደፈለጉ ስላወቅኩ ዘወር አልኩ። በህይወታቸው የአንድ ስኬታማ ሰው ጓደኛ ስለነበሩ በጣም ደስተኛ ናቸው። "ለራሴ እንድህ አልኩ፦ ምስኪን ለምን እርሰዎም እንዴ ኢብኑ ባዝ ስኬታማ መሆን አልቻሉም? ኢብን ባዝ የሞቱ እለት ሰዎች በየሚንበሩ፣ በየተቋሙ፣ በየማህበሩ ፣በየመድረኩ አልቅሰውላቸዋል። በርካታ ህዝብ ነው በሳቸው ሞት ያዘነው። እርሰዎ ሲሞቱ ግን በርህራሄና በባህል ካልሆነ በስተቀር አንድ ጠብታ እንባ የሚያፈስ ሰው የለም።" ብዙዎቻችን ስለ ስኬታማ ሰዎች ስንሰማ "እከሌ አብሮ አደጌ ነው። እከሌ ጋር አብረን ተምረናል። እከሌን በደንብ አውቀዋለሁ ወዘተ" ስንል እንደመጣለን። ይህ ግን ምንም አያኮራም። የሚያኮራው እነሱ የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ ነው። ጠንከር በልና ከዛሬ ጀምሮ ያሉህን ችሎታዎች በሙሉ ለመጠቀም ቁርጠኛ ሁን። ፊትህ ላይ ያለውን መኮሳተር በፈገግታ፣ ድብርትህን በሀሴት፣ ስስትን በቸርነት፣ ቁጣን በታጋሽነት፣ የችግር ቀናትን በደስታ ቀናት ተካ። እምነትህን ወደ መሳሪያ ቀይረው። ከዚያም ስኬታማ ትሆናለህ። ህይወትህን ተደሰትባት። ምክንያቱም ለጭንቀት ጊዜ የለህም። =>ይህን እንደት ማድረግ ይቻላል? ለዚህ ነው ይህን ፅሑፍ ያዘጋጀሁት። እስከ መጨረሻው ከእኔ ጋር ቆይ። በአላህ ፍቃድ። ☆ከእኛ ጋር ትቆያለህ....... የራስህን ጥበባት የማሳደግ ውሳኔና ፅናት ካለህ። ከብቃትህና ከችሎታህ የመጠቀም ፍላጎት ካለህ። . . . . ክፍል ሁለት ፦ https://t.me/eross_eross ይ...ቀ....ጥ...ላ...ል።

  • ግራ ያጋባኝ °በወንጀል የተጨማለቁ እጆች ይዤ እጄን እንዴት ወዳንተ ላንሣ የራሕመትህን ስፋት እያወኩስ ልመናህን እንዴት ልርሣ ! °የጀሀነምን ቅጣት እያሰብኩ በምን አቅሜ ቆሜ ልሂድ የጀነትን ድሎት እያለምኩስ እንዴት ተኝቼ ልደር ! ° የቁጣህን ከባድነት እያወቅኩ እንዴት ብዬ ልቅረብህ የእዝነትህን ሁሉን አካላይነት እያወቅኩሰ እንዴት አድርጌ ልራቅህ ። °ወዳጆቼ !ይህች አጭር እድሜያችን ከመልካምና ከታላላቅ ሥራዎች ጋር በጣም ረጅም ናት ፤ ከተራና ዝቃጭ ሥራዎቻ ጋር ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ናት ። ° መልካም ሥራና ጥሩ ተስፋ ወደ አሏህ ሱብሃነሁ ታዕአሏህ በምናደርገው ጉዞ ታላላቅ ስንቆቻችን ናቸውና በርትተን እንያዛቸው ። °እናንተዬ !ወደ መንግስተ ሰማያት ከፍ በሚሉና ቁልቁል አዝቅት በሚወርዱ ሰዎች መካከል ያለው ደረጃ ምንኛ ሰፋ ! ወዳጆቼ መልካም ቀን ኸይር የምንሸምትበት ከመጥፎ የምንርቅበት አሏህ ያድረግልን ያረብ https://t.me/eross_eross

  • ስላ ቀልባችን ክፍል ❷ ቀልብ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህን ጥያቄ ማወቃችን ሰለምንነጋገረው ርዕሰ ምንነት ግልፅ መሆን ብቻ ሣይሆን የቀልብ ምንነትና ለቀልባችን መድረቅ ሰበቡን እንድናውቅና ለደረቀው ቀልባችን መፍትሔው ምን እንደሆነ ጠቋሚ ይሆናል ። ሰለዚህ በዚህ ጽሑፍ ላይ ቀልብ ማለት ምንድነው ? የቀልብ በሽታዎች መንስኤዎቻቸውና መፍትሔዎቻቸው ፣ የቀልብ ዓይነቶች በቁርአን በሐዲስ በስለፎች አስተሳሰብ ምን እንደሚመስል ለመዳሰሰ እንሞክራለን ። በቁርአን ላይ የተጠቀሱ የቀልብ ዓይነቶች በቁርአን የተጠቀሱ የቀልብ ዓይነቶች በጣም ብዙ ናቸው ። የሚከተሉትን ለአብነት እንጠቅሳለን ፦ ይቀጥላል 👉https://t.me/eross_eross

  • #ስለ ቀልባችን በሚል ተከታታይ የሆነ ፁሑፍ ለማስነበብ ወደድን ተከታተሉን ...! ክፍል አንድ ❶ ቀልባችን ለምን ይሆን ደርቀት የሚያጠቃው❓ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ያላንዳች ረዳት ለፈጠረ የሰው ልጆችን ከፍትወት ጠብታ ላስገኘ የባሮቹን ቀልቦች በጣቶች ውስጥ ላደረገና እንደፈለገው ለሚገለባበጠው እንዲሁም  ቀልባቸው ንፁህ ስለሆነና አሏህን ፈሪ ለሆኑ ባሮች ታላቅ የሆነውን ጀነተል ፈርዶውስን ላዘጋጀ ። ቀልባቸው ለጠመመ እና አሏህን አማፂ ለሆኑት ደግሞ መራራና አሳማሚ የሆነውን ቅጣት ለደገሰሰው ታላቁ ጌታችን አሏህ (ሱብሃንሁ ታአላ )ላቅ ያለ ምስጋና ይድረሰው ። አሚን የሰዉን ልጅ ከቀልብ ድርቀትና ወንጀል አላቀዉ ፍፁም ለጌታው ታዛዥ እንዲሆን ሌት ተቀን በጣሩት ታላቁ የእዝነት ነብይ ላይ ስላትና ሰላም ይስፈንባቸው። ዛሬ አለማችን ሰላጣችውና የቀድሞ መልካም ትውልዶች ይዘውት የሄዱ እስኪመስለን ልናገኘው ስላልቻልነው ነገር እናወጋለን ። በአሁኑ ሰአት ወንጀል የማይሰራ ሰው የለም ማለት ጌታውን፣ ነፍሱን እንዲሁም ማህበረሰቡን የሚያስከፋ የለም እንደማለት ሲሆን ከስዎች መካከል ደሰተኛ ሆኖ ወንጀልን የሚፈጽም ፣እየተጠራጠረ ወንጀልን የሚፈጽም ፣እየተከፋና ደስተኛ ሣይሆን ወኝጀልን የሚፈጽም ፣ ተገዶ ወንጅልን የሚፈጽም፣ ባለማወቅ ወንጅልን የሚፈጽም ሰው ምድርን ቢሞላትም ነገር ግን ከወንጀሉ ተጸጽቶ ደስተኛ ሆኖ መኖርን የማይመኝ አንድ ሰው ይኖራል ቢባል አላምንም ። ነገር ግን ብዙ ሰው ደስተኛ ሊያደርገው የሚችልን ተግባር መፈጸም ወንጀልን ከቻለ ሙሉ ለሙሉ መራቅ ካልሆነ ለሰራው ወንጀል ወደ አአሏህ መመለስንይመኛል ። ቢሆንም ግን ለዚህ የሚታደሉት ውስን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸዉ። ብዙሃኑ ለዚህ ተግባር ለምን ይሆን ያልታደለው ❓ የግል ጥያቄ ውስጤ ላይ አጫረና <<የቀልብ በሽታ ስላለበት>>ሰል ድምዳሜዬን አስቀመጥኩ ። <<ለዚህ መፍተሔውሰ ምንድን ነው>>❓ በማለት መልሼ ውስጤን ስጠይቅው <<ቀልብን ማሳመር >> የሚል መልሰ አገኘሁ ። ነገር ግን ይህንን ሰል ከልብ ወለዴ እንዳይመስላችሁ ። ታዲያ ከየት ነው ያገኘኸው (ያመጣኸው)❓ ካላችሁኝ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሃዲሰ ላይ ነቢያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ፦ አዋጅ በሰዉነት ውስጥ አንዲት ቁራጭ ሥጋ አለች እሷ ከተስተካከለች ሰዉነት በሙሉ ይስተካከላል እሷ ከተበላሽች ሰውነት በሙሉ ይበላሻል አዋጅ ! እሷም ቀልብ ናት ብለዋል ። አያችሁ ! የአንድ ሰው ማንነቱ ባጠቃላይ በቀልብ ላይ የሚሸከረከር ነው ። ቀልባችን ከማረ ሁሉ ሰውነታችን ያምራል ቀልባችን ከተበላሸ መላ ሰውነታችን ባጠቃላይ ይበላሻል እንደማለት ነው ። ይቀጥላል 👉https://t.me/eross_eross

  • ያ ነፍሱ…

  • 🥢 "አሏህ ሆይ! የወንድማችንን ነውር አታሰማን" ይላሉ አንድ የመስጂድ ኢማም፤ ሁላችንም የወንድማችንን ነውር ላለመስማት መጣር ይኖርብናል። የወንድማችንን ነውር የሰማን ዕለት ለእርሱ ያለን ክብር፣ ቦታ እና አመለካከት ከመቀየሩም ባሻገር እርሱን እንድንጠላ ያደርገናል፤ መጠላላት፣ መመቀኛኘት እና ቂም መያያዝ ደግሞ የምዕመናን ባህሪ አይደለም። ዱንያ ላይ -ወንድሞቼ- ከነውር የፀዳ አንድም ፍጡር ሊኖር እንደማይችል ከማንም አይሰወርም። "አንድም" የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ሸይኽም፣ ዓሊምም፣ ኡስታዝም፣ ኢማምም፣ የዲን ተማሪም፣ ተራው ማህበረሰብም፣ ትልቁም፣ ትንሹም ማንም ከነውር የፀዳ የለም። من ذا الذي ترضى سجاياه كلها                 ..........................  ይላል ገጣሚው! "ማነው እርሱ ሙሉ ተፈጥሯዊ ባህሪያቶቹ ሚወደድለት?" የለም። من ذا الذي ما ساء قط                 ومن له الحسنى فقط "ማን ነው ከነውር ሁሉ ፀድቶ እና መልካምነት ብቻ ኖሮት ተሳስቶ እማያውቅ ?" ይላል፤ የለም። አብዘሃኛውን ጊዜ ደግሞ ግለሰብን በተመለከተ በሰዎች መሓከል ሚሰራጩ ወሬዎች ከእውነታው የራቁ ሆነው እናገኛቸዋል። ስለዚህ -ወንድሞች- በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፤ ተራ ስለ ሰው ወሬ ይዞብን የመጣን ሰው እንዳናስተናግድ። ከህሜት፣ የሰውን ስም ከማጥፋት፣ ሰው እና ሰውን ከማጋጨት እና ከመሳሰሉት በጣም ልንርቅ ይገባል። የሙዕሚን መገለጫም አይደለም። ጨርሻለሁ! https://t.me/eross_eross

  • 🔺ስጦታ እጅግ በጣም ማራኪ የሆነ ግጥም በዓረቢኛ ቋንቋ! 💥 قصيدة رائعة بعنوان الى الله نمضي ياهنيئا لمن سبق 🎙️ بصوت الأخ خالد الغامدي ♻️ انشر فإنه من دل على خير فله  كأجر فاعله 👉@eross_eross

  • አይ ዱኒያ

  • видео или голосовое, без подписи

ኢስላም — tgindex