tgindex
Ethio university information

Ethio university information

Статистика

በሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የተላለፉ አበይት ጉዳዮች የሚያገኙበት ቻናል ነው መረጃዎችን 💯% አረጋግጠን ነው የምናቀርብላቹ Buy ads: https://telega.io/c/ethio_uv_info

Последний пост
25 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
81
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 943
+14 за 4 дн.
Сутки
+5
+0,17%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 028
40 постов
Вовлечённость
34,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 81
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 25 апр.1 4291

    የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17-20/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል፡፡ በርካታ የሪሚዲያል ተፈታኝ ተማሪዎች የዒድ አል አደሃ በዓልን በመጥቀስ አስተያየት አድርሳችሁናል። ይሁን እንጂ ረዕቡ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም የኢድ አል አደሃ በዓል በመሆኑ በዕለቱ ፈተና እንደማይሰጥ አገልግሎቱ አያይዞ ገልጿል፡፡ @ethio_uv_info

  • 25 апр.1 2361

    በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ለ7ኛው ምርጫ የመራጭነት ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17-24/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ፖርታል 👇 https://uni.mirchaye.nebe.org.et ምዝገባውን ለማከናወን ምን ያስፈልጋል? ➫ በሚገኙበት ዩኒቨርሲቲ ኔትዎርክ ላይ መሆን፣ ➫ ስልክ፣ ኮምፒውተር ወይም ላፕቶፕ፣ ➫ ብሔራዊ…

  • በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ለ7ኛው ምርጫ የመራጭነት ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17-24/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ፖርታል 👇 https://uni.mirchaye.nebe.org.et ምዝገባውን ለማከናወን ምን ያስፈልጋል? ➫ በሚገኙበት ዩኒቨርሲቲ ኔትዎርክ ላይ መሆን፣ ➫ ስልክ፣ ኮምፒውተር ወይም ላፕቶፕ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ ሲያወጡ የወጣበት የስልክ ቁጥር፡፡ @ethio_uv_info

  • የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በሌላ በኩል ፦ - የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም - የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም - የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም - የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ይሰጣል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም @ethio_uv_info

  • 2 апр.1 016из vip channels

    የተለያዩ ➠ አስገራሚ አስተማሪ እንዲሁም አዝናኝ ታሪኮችን ➠ የፍልስፍና ፅሁፎችን ➠ Motivation Quotes ➠ መፅሀፍትን በPDF ➠ ግጥም የሚያገኙባቸው ቻናሎች

  • Channel photo removed

  • የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልፀዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት የመልቀቂያ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደነበር፣ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም መድረክ ላይ የተገኙት ሚኒስትሩ አስታወሰዋል፡፡ ዘንድሮ ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን፤ በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ይሠራል ብለዋል። ክልሎች በቂ ኮምፒዩተር፣ ኔትዎርክ እና አማራጭ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት እንዲዘጋጁ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ፤ ለተማሪዎች በቂ ስልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በዚህም የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል። በ2017 ዓ.ም ለመልቀቂያ ፈተናው ከተቀመጡ 585,882 ተማሪዎች መካከል 134,609 ወይም 23% ያህሉ ፈተናውን በኦንላይን የወሰዱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ @ethio_uv_info

  • #AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራጭ የመምህራን ትምህርት ፕሮግራም (Alternative Teacher Training Program) ለመማር አመልክተው ለተመረጡ አመልካቾችን ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህም ለስልጠናው ተመዝግባችሁ የተመረጣችሁ አመልካቾች ከዚህ በታች ባለው ውሳኔ መሰረት የሚጠበቅባችሁን እንድትፈፅሙ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡ ውሳኔ 1: የትምህርት ወጪያችሁ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ተሸፍኖ፣ ነገር ግን የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት በግላችሁ ሸፍናችሁ፤ በመደበኛው (በቀን) መርሐግብር ወይም ከሰኞ እስከ ዓርብ በማታው መርሐግብር ወይም በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር መማር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህን ዕድል መጠቀም የምትፈልጉ አመልካቾች (የስማችሁ ዝርዝር በሊንኩ አማካኝነት ይገኛል) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ የትምህርት ማስረጃችሁን በመያዝ ከየካቲት 09-13/2018 ዓ.ም በአካል በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። ውሳኔ 2: ከላይ በተሰጠው አማራጭ መጠቀም የማትችሉ አመልካቾች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሚያካሒደው የተማሪ ቅበላ በመደበኛው ፕሮግራም ሙሉ ወጪያችሁ (የትምህርት፣ የምግብ እና የመኝታ) ተሸፍኖ ቅድሚያ ተሰጥቷችሁ የምትገቡ መሆኑን ተገልጿል፡፡ ለዚህም በነሐሴ 2018 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የተመረጡ አመልካቾችን ዝርዝር ለማየት 👇 https://www.aau.edu.et/announcements/detail?title=Alternative~Teacher~Training~Program @ethio_uv_info

  • без подписи

  • без подписи

  • ላለፉት 15 ቀናት ሲካሔድ የቆየው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ለ10ኛ ጊዜ ሲካሔድ የቆየው የስፖርት ፌስቲቫሉ፤ በ15 ልዩ ልዩ የስፖርት አይነቶች በሁለቱም ጾታ በ48 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ከ7,500 በላይ አትሌቶችን አስተናግዶ ፍጻሜውን አግኝቷል። @ethio_uv_info

  • የፋይዳ መታወቂያ ያውጡ! ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡ ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡ @ethioየፋይዳ መታወቂያ ያውጡ! ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡ ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡ @ethio_uv_info

  • #ERMP #BluePrint የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) የመግቢያ ፈተና የካቲት 09 እና 10/2018 ዓ.ም በተመረጡ የፈተና ማዕከላት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ተፈታኞች የፈተናውን መመሪያ፣ ብሉ ፕሪንት፣ የተፈታኞች ዝርዝር እና ሌሎች መረጃዎችን ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ 👇 https://www.moh.gov.et/ermp-announcements @ethio_uv_info

  • #JinkaUniversity በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ የማርበርግ ቫይረስ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ በጤና ሚኒስቴር ተረጋግጦ ጥሪ እስከሚደረግላችሁ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል። በሌላ መረጃ፤ ከአሪ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ትምህርት ለመከታተል ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ውጪ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም ወደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ የ21 ቀናት Quarantine ወስዳችሁ በዩኒቨርሲቲው ነፃ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት እያገኛችሁ በመቆየት ከማርበርግ ቫይረስ ነፃ መሆናችሁ ሲረጋገጥና የምስክር ወረቀት ከተሰጣችሁ በኋላ ወደየተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንድትገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል። @ethio_uv_info

  • #Update የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል። የምዝገባ ጊዜው ከተቋማት በቀረበ ጥያቄ እና ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት እስከ አርብ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ስዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እንዲሁም የግል ተፈታኞች ምዝገባችሁን በተራዘመው ጊዜ እንድታጠናቅቁ ተብሏል። @ethio_uv_info

  • #MekelleUniversity በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም)  መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል። የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል። @ethio_uv_info

  • #ተጨማሪ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም እንደሆነ መገለፁ ይታወቃል። ➫ ወሊሶ የተመደባችሁ የምትሄዱት አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ፦ 0920189695 ➫ ቡኢ የተመደባችሁ የምትሄዱት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፦ 0943165470 ➫ ቦንጋ የተመደባችሁ የምትሄዱት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፦ 0913192165 ➫ ጅግጅጋ የተመደባችሁ የምትሄዱት ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፦ 0922648636 ➫ ጋምቤላ የተመደባችሁ የምትሄዱት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፦ 0911590938 በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወል አስፈላጊ መረጃዎችን መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። @ethio_uv_info

  • በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ @ethio_uv_info

  • #ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ! የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል። @ethio_uv_info

  • #MoE በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ወደ ትምህርት ቤታችሁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ለ9ኛ ክፍል የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ወዘተ) ➫ የመኝታ አልባሳት (አንሶላ እና ብርድ ልብስ) ➫ ስትማሩ ከነበረበት ትምህርት ቤት መሸኛ እና የትምህርት ውጤት ዩኒፎርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ከያዘበት አቅራቢ ድርጅት በራሳችሁ ወጪ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ወደ ትምህርት ቤቶቹ መሔድ እንደማይቻል ተገልጿል። @ethio_uv_info